ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
​​💔የባከነች_ነብስ💔

♥️
♥️

🛎የመጨረሻው ክፍል🛎

...🖊 <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

❇️//ተፈፀመ//❇️

🔮የባለታሪኳ መልዕክት

👉 የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!


💈ምስጋና
👉ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ
!



,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

t.me/write_event
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​ድሮ አስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለን ነፍሰ ቀጭኑ ኬሚስትሪ መምህራችን እንዲህ ሲሉ ጠየቁን ።
ውሀ ከምን እና ከምን ንጥረ ነገሮች ነው የተፈጠረው ?🙂
ብዙ ተማሪዎች ይህችን ቀላል ጥያቄ ለመመለስ ተቅለበለብን ። መምህሩ ግን ከሁሉም ተማሪ ይልቅ ትኩረታቸውን ስንሻው ላይ አድርገው እንዲመልስ አስገደዱት ።
ስንሻው ከእንቅልፉ የተነሳ ይመስል አይኑን አሻሽቶ ትንሽ ቆየና መምህሩ ጥያቄውን እንዲደግሙለት ጠየቃቸው። /በነገራችን ላይ የስንሻው አባት ልጃቸው ትምህርት እንዳይገባው ተደግሞበታል ብለው ስለሚያስቡ እሱን ይዘው ያልተንከራተቱበት ፀበል አልነበረም ። ኋላ ላይ ቢታክታቸው ጊዜ እርግፍ አድርገው ተውት ! እርሱም ትምህርት አይንህን ላፈር ብሎ ማንበብ እና ማጥናቱን እርግፍ አድርጎ ተወው /
"እኛ የምን ጠጣው ውሀ ከምንና ከምን ውህደት ተፈጠረ ? " ብለው ጥያቄውን ደገሙለት ።
ውሀ ልማት እና ቀበሌ ተዋህደው በገጠሙት የቧንቧ መስመር ነው የተፈጠረው ! ብሎ ሲመልስ ያልደነገጠ ተማሪ አልነበረም ። ሁላችንም እያሾፈ ነው ብለን በትኩረት አየነው ።
እሱ እቴ !
ልቡ ደጭ እንኳ አላለም !
“ስ ! ውይ ይቅርታ” አለን መልሶ .... በቃ ኦክሲጂንና ሀይድሮጂን ታውሰውት ነው ማለት ነው ብለን ማስተካከያውን በጉጉት መጠባበቅ ያዝን !
“ውሀ ልማት እና ሰሜን ሸዋ ዞን በመተባበር ነው “ ብሎ እርፍ አለው ።
ነፍሰ ቀጭኑ መምህራችን በንዴት ተነፋፍተው ነብር አከሉ ! አለ አይደል የቤት ውስጥ ድመት ስትቆጣ እንዴት ነው ኩፍ የምትለው ?
መምህራችን ኩፍ አሉ ።
በስመአብ !
አስተማሪ ሲናደድ ለካ እንደዚህ ያስፈራል ?
ከአስተማሪም ሁሉ ደግሞ ኬሚስትሪ አስተማሪ ሲናደድ በጣም ያስፈራል ። የሆነ ሰልፈሪክ አሲድ ከላብራቶሪ አንስተው ፊቱ ላይ የሚከለብሱበት ሁሉ መሰለን ።
“ተነስ !”
ስንሻው ተነሳ ።
“እነ ሚካኤል ፣ እነ እዮብ እነ አቤል ኢንጅነር ወይ ዶክተር ሲሆኑ ሻንጣ ተሸካሚያቸው እንደምትሆን አልጠራጠርም “ ብለው ሞራሉ ላይ ቀዝቃዛ ውሀቸውን ከለበሱበት ።
እንደፈራነው ከወራት በኋላ ስንሻው ማትሪክን ወደቀ ። እኛ ፈተናውን በጥሰን አለፍን ።
እኛ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለዩንቨርሲቲ ስንዘጋጅ ስንሻው የሆነ ትምህርት እንደከረሜላ አሽጎ የሚሸጥ ኮሌጅ ዲፕሎማ መማር እንደጀመረ ሰማን ።
ግቢ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስንሆን ስንሻው ቀበሌ ስራ አጊንቶ መግባቱ ተነገረን ። ያኔ በሱ ሙድ ያልያዘ አልነበረም ።
እንደውም አንድ ቀን በድሉ የሚባል ቸካይ የነበረ ተማሪ ወደኔ ጠጋ ብሎ "ስንሻው በዚህ ድድብናው ቀበሌ ስራ ማግኘቱም ተመስገን ነው ብሎ ገለፈጠ ። "ስንሻው እኮ ቀን ስራ እንኳ ይበዛበታል ። እንደ ህንዶች ሰባቴ ቢፈጠር ሰባት ጊዜም ትምህርት አይገባውም" አለኝ ቀጥሎ ።
ስንመረቅ ግን የነፍሰ ቀጭኑ ሰውዬ እርግማን ለስንሻው ምርቃት ሆኖ እርፍ አለው ።
የከተማችን አስተዳደር ተመራቂ ተማሪዎች ተደራጅታችሁ ኮብልስቶን አንጥፉ ምናምን ብሎ በስብሰባ ሰበብ ሲጀናጀነን ስንሻው ተከብሮ የከተማችን ከንቲባ ሆኖ ነበር ።
ጭራሽ እዛ አመዳችን ቡን ባለ ተመራቂ ተማሪዎች ፊት ቀርቦ ስለ ስራ ፈጠራ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠን ። ኢንጅነር ነን ዶክተር ነን ብላችሁ አትኮፈሱ የጀበና ቡና ብታፈሉ ትችላላችሁ ። ለምሳሌ ሚካኤል እዮብ አቤል በኢንጅነሪንግ እና ዶክትሬት ተመርቃችሁ ሰፈር ለሰፈር ከምታውደለድሉ የጀበና ቡና ብታፈሉ ምን ችግር አለው ? ብሎ በምሳሌነት ጠቀሰን ። እኔ እንዳስተማረን ሳይሆን እንደ ሰደበን ቆጥሬው እሳት እንደነካው ላስቲክ ተኮራመትሁኝ ።
ከስብሰባው በሁላ ስንሻውን ለማናገር ከተቀመጥሁበት ተነስቼ ተራመድኩኝ ። የልጅነት ጓደኛዬ ስለሆነ ሰላምታ ልሰጠው አስቤ ነው የቀረብሁት ። በሰዓቱ ከየት መጣ ያልተባለ ጠባቂው በመዳፉ ጭብጦ አሽቀነጠረኝ ።
ቀና ብዬ አየሁት !
“ምን አጠፋሁ አለቃ?”
ፈርጣማው ጠባቂ በቁጣ ቱግ ብሎ እንዲህ አለኝ
“አንተ ምን አይነት ደፋር ነህ ባክህ ? ክቡር ከንቲባችንን ለመቅረብ አይደለም ሻንጣቸውን ለመሸከም ብትመጣ እንኳ ማስፈቀድ ነበረብህ “ 🙂
#ሚካኤል አስጨናቂ


https://t.me/Write_Event
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
<<ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?>> ትላለች አንደኛዋ።
<<እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!>> ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።

ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
<<ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?>> ይለኛል።
<<ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?>>
<<አይ ሻማው ይሁን በቃ!>> ይላል እየተቅለሰለሰ።

አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። <<ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!>>

ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው።

የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም!

ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "beauty and the beast" ሆሆ!
ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል።
<<ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም>> ስለው
<<ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!>>

እያሳዘነ ያስቀኛል።

ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ።
<<አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?>>
<<አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!>> አለ አሁንም እያለቀሰ!
<<እሺ ምንድን ነው?>>
<<እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!>>

ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ።

ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው?

የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ።

የፈሪ ትልቁ ችግር.....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም!

<<ለማን ተናግረህ ነው?>> ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት።

የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም።

ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ።

የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን <<ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?>> አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው።

ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ።

አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ!

አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል።

ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ።

ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ <<አባቴ ማነው?>> ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው?

<<ተረት ተረት>>
<<የመሰረት>>
<<በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች>>
<<እእእሽ>>
<<ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?>>
<<ምን?>>
<<ሻማ! በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን እጠፋለሁ ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!>>
<<ምን አደረገች?>>
<<በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።>>
<<ከዛስ?>>
<<ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..>> እያለ የሚቀጥል ተረት
!

ታሪኩን ከወደዳችሁትና እንደዚ አይነት አጫጭር ታሪኮችን እንድንፅፍላችሁ ከፈለጋችሁ share አድርጉት።😊👍👍

Join
@write_event
እናት ልጇን እያጠባች ጎረቤቷ አይታ.. ''pa! እንደ አባቱ ነው ሚጠባው''😊
@write_event
ቂጥ ለመውደዳችን ማህበረሰቡ ተጠያቂ ነው..

ለዳቦም ለድስቱም ቂጥ ይጣፍጣል እየተባልን ነው ያደግነው🤷‍♂

@write_event
( "ሰላም እለኪ" )


የአምስት ሺ ዘመን
የታሪክ ባለቤት
የአፍሪካ ቀንድ ኩራት
ክብርት እመቤት
🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጺያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.

ጋራ ሸንተረሩ
ለምለሟ ሀገሬ
ንፋስ ቢያይልብሽ
ድንገት መጥቶ ዛሬ
ፈርጠም ባለው ክንድሽ
በልጆችሽ ካዝማ
ቀንሽ ብቅ ሊል ነው
አይዞሽ እናት እማማ
🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጺያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.

የፊደል ቀማሪ
የዘመን ቆጣሪ
የጥበብ መፍለቂያ
የሀይማኖት መታያ
ቅድስት




🇪🇹
ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጵያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ
.


.
.
የሰው ዘር መገኛ
የእውቀት ሊቀኛ
የአክሱም ላሊበላ
እንዴት ታደልሽ ምነኛ
ባረኮተ እግዚሔር
የሰጠን ለእኛ
.
..

ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.

ባጎረሰ እጅሽ
ምላሽሽ ንክሻ
ብትሆን ምድርሽ ዛሬ
የእንባ መፍሰሻ
የሰው ሞት ብዛቱ
አራዊቱ ሳይቀር
አንቺን ይቀብርሽ ዘንድ
ታስቦልሽ ነበር
ላያድር ነገር
ማምሸትን ፈለገ
አቅምሽን ሊፈትን
እያፈገፈገ
አደባ ከጀርባሽ
ዞሮ ሊዋጋ
አንቺን አዋርዶ
ንግስናን ፍለጋ
.
.
.

ይህ ሁሉ ቢሆንም .......
ምኞት አይከለከል
ተመኝቶ ነበር
ሀይልሽን ፈትሾ
እንዲህ በአንዴ ሊቀበር

እንኪያስ ደግሜ ልበል.......

🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹

ይብቃ መፍሰሱ
የደም ጅረቱ

የተስፋቸው መጨለም
የህጻናት ሞቱ
ስደት እንግልቱ
ከእናት ጉያ
የልጅ መነጠቅ
በርሀብ አድማ
በሞት ከመድረቅ
የወጣት መቀጨት
ከመንገድ መቅረት
ሌላውን ጨምሮ
ይሔ ሁሉ ይብቃ
የሰላም ይሁን
ቦታው ፈረቃ
.
.
.

ሰላም ለአንቺ ይሁን ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.
.

ፍክት በይ ሀገሬ
እንደ አደይ አበባ
የሰላም ባለቤት
ከአንቺ ዘንድ ይግባ
ይመርብሽ እማ
ቀሚስሽ ይንዘርፈፍ
ደምቀሽ ታይልን
ከአለም ብለሽ ከፍከፍ
ልጆችሽን ስብስብ
እቅፍ ድግፍ አርጊ
የብርሀንሽን ሚስጢር
እግዚሄርን ፈልጊ
.
.
.
.

🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ለአንቺ ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.
.

የአብስራ/YeAmenLij
.
.
.
..
"ስለ ኢትዮጲያ" 🇪🇹 "ክፉ አትይ!ክፉ አትስማ!ክፉ አትናገር"
(ሊቁ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ)










🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ::


@write_event
ፈገግ !

ደሞዙ ላይ በስህተት 100 ብር ተጨምሮ ሲከፈለው ምንም ያላለው ሙላ ነስሩዲን በቀጣዩ ወር ደሞዝ ከፋዩ 100 ብር ቀንሶ ሲከፍለው ግን አስር ገፅ አቤቱታ ፅፎ አመለከተ።

ደብዳቤውን ያነበቡት የመሥሪያ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሙላ ነስሩዲንን በትዝብት እየተመለከቱ እንዲህ አሉት፣ "አሁን 100 ብር ተቀነሰብኝ ብለህ አስር ገፅ አቤቱታ ፃፍክ...ባለፈው ወር ግን በስህተት 100 ብር ሲከፈልህ አንዲት ቃል አልተነፈስክም?"

"የመጀመሪያ ስህተት ስለሆነ ነዋ..." አለ ሙላ ነስሩዲን እጆቹን ዘርግቶ...
@Write_Event
BRO ወጣት ነህ ጉልበት፣ እውቀት፣ ድፍረት፣ አላማ እና Confidence አለህ በርታ እና እራስህን ለውጥ..
ስለ ቺኳ አታስብ ሲሳካልህ ፋዘሯን ቀበሌ ሄደህ ሁለት ጃምቦ🍺🍺 መጋበዝ ነው ጠዋት ጀሮዋን እየጎተቱ በርህ ላይ ያመጡልሀል Bottle ከገዛህ ደሞ ታናሽ እህቷን ይመርቁልሀል 😜🤣🤣
@write_event
የወደፊት ልጄ እናትህን እየመረጥኩልህ ነው አይዞህ የማይጣፍጥ ጡት አትጠባም እየቀመስኩልህ ነው😜🤣
@write_event
ጡቷን በእጇ ደግፋ ፎቶ ትልክልኛለች እንዴ...

#My_Sister መቅዶኒያ እንኳን እንደዚህ አረጋዊያንን አልደገፈም🤣😂
@write_event
ወደ ክፍለ ሀገር ለበዓል እየሔድን🚌 አንዱ #ፔስታል_ፔስታል... ብሎ መኪና ውስጥ ቀውጦ ተደናግጠን ስንሰጠው...
:
የያዘውን #ጫት🌿 ሁለት ቦታ ከፍሎ አስቀመጠበት

እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ
FIAS

* በኮሚሽን የሚሰራ የማስታወቂያ ድርጅት ነው።
* ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር ይሰራል።

እና በቀን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ለተመዘገቡ አባላቶቹ ይሰጣል። ስራዎቹ እጅግ በጣም ቀላል ናቸው። ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። በዛ ቢባል 5 ዲቂቃ ቢወስዱ ነው። አንድ አባል የሚሰጠው የስራ ብዛትና የሚያገኘው ብር እንደ ደረጃው ይለያያል። ደረጃዎቹ VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4, & VIP-5 ናቸው።


* You must start with 9 when entering a phone number.

* If you have more questions, you can ask.


👇👇👇👇👇👇👇

1. VIP 1

* ይህ ደረጃ አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 4 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 6 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 24 ብር, በወር 724.00 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

2. VIP 2

* ይህ ደረጃ አባሉ 3,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 6 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 84 ብር, በወር 2,520 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

3. VIP 3

* ይህ ደረጃ አባሉ 6,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 11 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 176 ብር, በወር 5,280 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

4. VIP 4

* ይህ ደረጃ አባሉ 10,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 17 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 18 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 306 ብር, በወር 9,180 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

5. VIP 5

* ይህ ደረጃ አባሉ 30,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 38 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 25 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 950 ብር, በወር 28,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።


Register lemadreg yihenen link yixkemu👇👇👇👇


https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=xamOWZQw&t=1651737586654
ለ Online ስራ ፈላጊዎች በሙሉ!!
=========////=========

ሠላም ለናንተ! ድጋሜ መጥቻለሁ።
በቀደመው post ላይ ስለ FIAS የተወሰነ ብያችሁ ነበር ። አብዛኞቻችሁ ስለድርጅቱ እና ስለሰራው የተወሰነ ማብራሪያ እንፈልጋለን ባላችሁት መሰረት፣ ስለድርጅቱ ባሰባሰብኩት መረጃ እና በገባኝም መጠን የተወሰነ ላብራራ ወድጃለሁ።
FIAS ማለት፣ ከዓለም አቀፍ ዋና ዋና የማስታወቂያ ድርጅቶች ጋር የሚሰራ ድርጅት ሲሆን፣ በሀገራችን ስራ ከጀመረ እጅግ በጣም ትንሸ ጊዜው ነው። የድርጅቱ ዋና አላማ፣ ሶሻል ሚዲያወችን ማለትም YouTube, Facebook, twitter, tiktok..... ተጠቅሞ ፣ የራሱ FIAS በሚባል ፕላትፎርም በመፍጠር በትስስር ( በ link) በጣም ብዙ ቁጥር ያለው audience (አባል) በመፍጠር፣ ድርጅታቸውን፣ ምርት እና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ ከሚፈልጉ እጅግ ግዙፍ ከሆኑ አለማቀፍ ድርጅቶች ማለትም እንደ Amazon, eBay, Alibaba, DHL.... እና ከመሳሰሉት ድርጅቶች ጋር በአጋርንት መስራት ነው። አባላቶቹን ተጠቅሞ ድርጅታቸው በአለም አቀፍ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተደራሸ እንዲሆኑ (እንዲተዋወቁ) ይሰራል።

ዋናው ጥያቄ?????

አባላት እንዴት ይመዘገባሉ? ተመዝግበውስ ምን ይሰራሉ? ሰርተውስ ምንያህል ክፍያ ያገኛሉ? ክፍያውንስ እንዴት ይፈፀማል? የሚሉት ስለሆኑ እና የኔም ጥያቄዎች ስለነበሩ፣ የገባኝን እና ትንሽም ብትሆን የቀን ገቢ ስለጀመርኩ ፣ ሂደቱን በተወሰነ እገልፃለሁ ።

1ኛ ..........መመዝገብ......

የሚማያስፈልጉ ነገሮች :-"invitation link" ፣ ስልክ ቁጥር እና internet የሚሰራ ስልክ ወይም pc ብቻ!!

ወደ ድርጅቱ ለመመዝገብ፣ ምዝገባው በአዲስ መል ከሆነ የግድ "invitation link" ወይም ከአሁን በፊት የተመዘገበ ሰው ሲጋብዛችሁ ነው። ምዝገባው በነፃ ከመሆኑም በላይ የማበረታቻ 50 ብር ቦነስ አለው። የ FIAS አካውንት ልክ እንደቴሌ ብር ስለሆነ የሚከፈተው በስልክ ቁጥር ብቻ ነው።

2ኛ ..........የሚሰሩ ስራዎች........

i,ዋና ስራ:-
በ24 ሰዓት ውስጥ 1ጊዜ internet ላይ ሆነን ከ2-5 ደቂቃ በደረጃችን የተቀመጠልንን ስራ "Task" ተጭኖ መውጣት ነው።
በደረጃችን ሲባል፣ ለማብራራት የሰክል የFIAS አካውንት ስንከፍት ከ VIP0 እስከ VIP5 ደረጃዎች አሉት። VIP0 ማለት ስንመዘገብ የሚሰጠን ደረጃ ሲሆን ከVIP1 ጀምሮ ግን ምዝገባው በእድገት ወይም በክፍያ ይሆናል።

የቀን ገቢ በደረጃ ሲቀመጥም እንደሚከተለው ነው።

VIp0: በ24 ሰዓት 3 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 5ብር ሲሆን 3x5 በቀን 15ብር ይሰራል።

VIp1 : በ24 ሰዓት 4 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 6ብር ሲሆን 4x6 በቀን 24ብር ይሰራል። በወር 720ብር፣ ዓመታዊ ገቢው 8640ብር ነው።

Vip2:በ24 ሰዓት 6 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 14ብር ሲሆን 6x14 በቀን 84ብር ይሰራል። በወር 2520ብር፣ ዓመታዊ ገቢው 30240ብር ነው።

Vip3: በ24 ሰዓት 11 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 16ብር ሲሆን 11x16 በቀን 176ብር ይሰራል። በወር 5280ብር፣ ዓመታዊ ገቢው 63360ብር ነው።

Vip4 :በ24 ሰዓት 17 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 18ብር ሲሆን 17x18 በቀን 306ብር ይሰራል። በወር 9180ብር፣ ዓመታዊ ገቢው 110160 ብር ነው።

Vip5 : በ24 ሰዓት 38 ተግባራትን (tasks) ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። የ1 task ዋጋ 25 ብር ሲሆን 38x25 በቀን 950 ብር ይሰራል። በወር 28500 ብር፣ ዓመታዊ ገቢው 342000 ብር ነው።

bii, ተጨማሪ ስራ:
ይሄው እኔ እያደረኩ እንዳለው ሌሌሎች ጓደኞቻችን በእኛ link እንዲመዘገቡ በማድረግ invitation comission ማግኘት ነው። ኮሚሽኑ መጠን እና አከፋፈል ስትመዘገቡ በስፋት በግልፅ ታገኙታላችሁ። እኔ ምመክረው ግን ሰው ተመዝግቦ ሳያልቅ የራሳችን team/branch ማስፋት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም በእኛ link የገቡት ሁሉ በየቀኑ ስራ በሰሩ ቁጥር፣ የገቢያቸውን 3% በየቀኑ ገቢ አለን። ስለዚህ አንድ ሰው 1 FIAS አካውንት ብቻ ስለሚኖረው አሁን ተሻምተን ጓደኞቻችንን በእኛ link ካላስመዘገብናቸው በሌላ መግባቱ ስለማይቀር እየከሰርን ነው። ጨዋታው ብዙ የሰራ ወይም invite ያደረገ አሁን ሳይሆን ወደፊት በጣም ብዙ ገቢ አለው። ብዙ አባል በስሩ ያለው አባል ምንንም ሳይሰራ የአባሉን ስራ 3% በየቀኑ ገቢ ያገኛል። ስለዚህ መፋዘዙ ይቅርና ቶሎ ዳይ ወደ ስራ........

3ኛ.......የሰራነውን ብር እንዴት እናወጣዋለን/እንጠቀማለን?............

እንደየደረጃችን የሰበሰብነውን ብር ለማውጣት ከተመዘገብን ከ 3ቀን በኋላ ወደ FIAS አካውንት በመግባት ድርጅቱ ለጊዜው ከሚሰራባቸው ባንኮች ማለትም (ንግድ ባንክ እና የአቢሲኒያ ባንክ) የግል አካውንታችን ጋር ይተሳሰር እና የሰራነውን ብር ወደ ባንክ አካውንታችን በማስተላለፍ ማውጣት ይቻላል። ለዚህ እኔም እያወጣሁበት ስለሆነ ምስክር ነኝ።

ስለዚህ ብዙዎች እየተራወጥን ስለሆነ የታችኛዋን ማስፈንጠሪያ link በመጫን ተመዝገቡ እላችኋለሁ!!

👇👇👇👇👇👇👇
https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=xamOWZQw&t=1651740262971
ቻርልስ ዳርዊን

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ሀሁ
ፀሀፊ ፦ በላይ ደስታ

ቻርልስ ዳርዊን፣ እ.ኤ.አ 1809 በእንግሊዝ ሀገር ውስጥ የተወለደና በምርምሩ እጅግ ታዋቂ የሆነ፣ የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪና ሳይንቲስት ነው፡፡ በዝግመተ ለውጥ ጥናት አያሌ ምርምሮችን ካከናወነ በኋላ፣ በ1882 ህይወቱ በማለፉ፣ በዌስት ሚኒስተር ቤተ-መጽሐፍ ቅዱስ ስፍራ ውስጥ ተቀበረ።

ዳርዊን፣ “ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ከአንድ አካል እየተሻሻለ የመጣ ነው” የሚል አመለካከት ነበረው:: በምድር ላይ የሚገኙ፣ ሕይወት ያላቸው ነገሮች አመጣጥ፣ ከአንድ ትልቅ ዛፍ ጋር እንደሚመሳስል አድርጎ ያስብ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ፣ ሌሎች ሰዎች “ይህ የሕይወት ዛፍ” መጀመሪያ ላይ አንድ ነጠላ ግንድ እንደነበረ፣ ይህ ግንድ የመጀመሪያዎቹን ውስብስብ ያልሆኑ ሌሎች እንደሚያመለክት አድርገው ማመን ጀመሩ። ከዚያ ግንድ አዳዲስ ዝርያዎችን እንደበቀሉና ቅርንጫፎች ደግሞ፣ የዕፅዋትና የእንስሳት ቤተሰቦች እንደሆኑ፤ ከዚያም፤ በአሁኑ ጊዜ ያሉት በዕዕዋትና በእንስሳት ቤተሰቦች ውስጥ የሚመደቡት የተለያዩ ዝርያዎች በሙሉ፣ እንደ ቀንበጥ እንደበቀሉ ያምኑ ነበር።

ቻርልስ ዳርዊን ግን፣ “በዓይናችን ልናያቸው የምንችላቸው ትናንሽ ለውጦች መኖራቸው፣ ትላልቅ ለውጦችም ሊከሰቱ እንደሚችሉ ያረጋግጣሉ” በማለት አስተምሯል። በእርግጥ እነዚህን ትላልቅ ለውጦችን፣ ማንም ሰው አላያቸውም:: እንደ ዳርዊን አመለካከት ከሆነ ውስብስብ እንዳልሆኑ ተደርገው የሚታሰቡት የመጀመሪያዎቹ የሴል ዓይነቶች፣ በጣም ረጅም በሆነ ዘመን ውስጥ አዝጋሚ ለውጥ በማድረግ፣ በምድር ላይ የሚገኙትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕያዋን ነገሮች አስገኝተዋል። ይህም የሆነው ሴሎቹ በጊዜ ሂደት “እጅግ አነስተኛ የሆኑ መሻሻሎችንና ለውጦችን” በማሳየታቸው እንደሆነ ዳርዊን ያስተምራል።

ብዙ ተመራማሪዎች፣ ይህ አባባል ምክንያታዊ እንደሆነ ስምምነት ላይ ደርሰው ቆይተዋል። “በአንድ ዝርያ ውስጥ ትናንሽ ለውጦች ሊከሰቱ ከቻሉ፣ በዝግመተ ለውጥ አማካኝነት፣ በጣም ረጅም በሆነ ዘመን ውስጥ፣ ትላልቅ ለውጦች ሊከሰቱ የማይችሉበት ምን ምክንያት ይኖራል?” ብለው ያስባሉ። በዘመኑ፣ የዝግመተ ለውጥ ትምህርት የተመሠረተው በሦስት መላ ምቶች ላይ እንደሆነም ተጽፏል።

1. ለአዳዲስ ዝርያዎች መገኘት መሠረቱ ሚውቴሽን ነው።

ሚውቴሽን በዕዕዋትና በእንስሳት ጂን ላይ በአጋጣሚ የሚከሰት ለውጥ ነው፡፡ የማክሮ ኢቮሉሽን ትምህርት፣ “ሚውቴሽን አዳዲስ ዝርያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆኑ የዕፅዋትና የእንስሳት ቤተሰቦችን ሊያስገኝ ይችላል” በሚል እምነት ላይ የተመሠረተ ነው።

2. ተፈጥሯዊ ምርጦሽ፣ አዳዲስ ዝርያዎች እንዲፈጠሩ አድርጓል።

ዳርዊን፣ “ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጋር መላመድ የቻሉት ሕያዋን ነገሮች በሕይወት መቀጠል ሲችሉ፣ መሉ በሙሉ መላመድ ያልቻሉት ግን በጊዜ ሂደት ሞተው ያልቃሉ” ብሎ ያምን ነበር፡፡ ይህን ሂደት፣ ተፈጥሯዊ ምርጦሽ ብሎ ጠርቶታል። በዘመናችን የሚገኙ የዝግመተ ለውጥ አማኞች ደግሞ “የሕያዋን ነገሮች ዝርያዎች፣ ከዘመዶቻቸው በመለየት የነበሩበትን አካባቢ ለቀው አዲስ በሆነ አካባቢ መኖር በሚጀምሩበት ጊዜ፣ ተፈጥሯዊ ምርጦሽ፣ በአዲሱ አካባቢ ለመኖር የሚያስችላቸው የጂን ለውጥ ያደረጉ ዝርያዎችን ብቻ ይመርጣል" ብለው ያስተምራሉ። በዚህም ምክንያት፣ እነዚህ ተነጥለው መኖር የጀመሩት ዝርያዎች፣ ቀስ በቀስ ተለውጠው፣ ፈጽሞ አዳዲስ ዝርያዎች እንደሚሆኑ የዝግመተ ለውጥ አማኞች ይናገራሉ::

3. ቅሪተ አካላት፣ ትላልቅ ዝግመተ ለውጥ መካሄዳቸውን ያረጋግጣሉ፤

በወቅቱ የነበሩ ሳይንቲስቶች ያገኟቸው ቅሪተ አካላት፣ ትላልቅ ዝግመተ ለውጦች መካሄዳቸውን እንዳረጋገጡ የሚጠቁም ሐሳቦች አስፍረዋል። “በውኃ ውስጥም ሆነ በየብስ ላይ መኖር በሚችሉና በደረታቸው በሚሳቡ እንስሳት መካከል፣ በደረታቸው በሚሳቡና በአጥቢ እንስሳት መካከል፤ እንዲሁም በዝንጀሮና መሰል ፍጥረታት መስመር ላይ በሚገኙት የተለያዩ እንስሳት መካከል፣ የተካሄደውን ሽግግር የሚያሳዩ በርካታ ቅሪተ አካላት በመገኘታቸው፣ ከአንዱ ዝርያ ወደ ሌላው የተደረገ ሽግግር መኖሩን የሚያሳይ ቢሆንም፣ ሽግግሩ መቼና እንዴት እንደተከናወነ በውል ለማወቅ አስቸጋሪ ስለመሆኑ ተጽፈዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ ሳይንቲስቶች ከዳርዊን አስተሳሰብ የተለየ ሀሳብ ማራመድ ጀምረዋል። የበርካታ ባለ አንድ ሴል ነፍሳትን፣ እንዲሁም የዕፅዋትንና የእንስሳትን ጄኔቲክ ኮዶች ማነጻጸር ችለዋል። እንዲህ ያለውን ንጽጽር ማድረጋቸው፣ ዳርዊን ስለ “ሕይወት ዛፍ” የተናገረውን መላምት ያረጋግጣል ብለው አስበው ነበር። ይሁን እንጂ እንዳሰቡት አልሆነም።

በርካታ ሳይንቲስቶች፣ “ሕይወት ያላቸው ነገሮች፣ ከአንድ አካል ተሻሽለው የመጡ ናቸው” የሚለው ጽንሰ ሐሳብ፣ በቅሪተ አካላት ማስረጃዎች የተደገፈ እንደሆነ ይናገራሉ። ለምሳሌ፣ የቅሪተ አካላት ማስረጃዎች መሰረት፣ "ዓሦች ተለውጠው አምፊቢያን፣ በደረታቸው የሚሳቡ እንስሳት ደግሞ እጥቢ እንስሳት ሆነዋል” የሚለውን ሐሳብ እንደሚደግፉ በመግለጽ ሲከራከሩ ቆይተዋል።

በቅሪተ አካል ጥናት ላይ የተሰማሩትና ዴቪድ ራውፕ የተባሉ የዝግመተ ለውጥ ምሑር እንዲህ ብለዋል፤"በዳርዊን ዘመን የነበሩ ጂኦሎጂስቶችም ሆኑ የዘመናችን ጂኦሎጂስቶች ያገኙት ነገር፣ ህይወት ያላቸው ነገሮች ቀስ በቀስ እየተለወጡ እንደመጡ የሚያሳይ ማስረጃ ሳይሆን የተዘበራረቀና ወጥነት የሌለው ሆኖ አግኝተውታል፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች በቅሪተ አካላት ስብስብ ቅደምተከተል ውስጥ ድንገት ብቅ ይሉና፣ በኖሩባቸው ዘመናት በመሉ፣ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳያሳዩ ወይም ምንም ዓይነት ለውጥ ሳይከሰትባቸው፣ ድንገት የሚጠፉ ናቸው በማለት ገልጸዋል፡፡

የፍልስፍና እሳቤዎቹ

የሰው ልጅ ከሌላው እንስሳ የሚለየው በደረጃ ብቻ ነው፡፡

የሰው አፈጣጠር መነሻ፣ እንደሌላው እንስሳ ሁሉ ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።

በሰውና በዝንጀሮ መካከል ፍጡር ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን እስካልተቻለ ድረስ፣ ሰው ከዝንጀሮ የሚለየው በአይነቱና በስሩ ብቻ ሳይሆን በደረጃውም ነው ማለት ይሆናል፡፡

ሰውም ሆነ እንስሳ፣ ስለአንድ ነገር የሚኖራቸው አስተሳሰብ ተመሳሳይ ሲሆን፣ ነገር ግን ሰው በጉዳዩ ላይ ያለው መረዳት፣ ማስተዋልና ደመነፍሳዊ ንቃቱ፣ ከእንስሳት የበለጠ በመሆኑ እራሱን በደረጃ ለየ፧ ይህ ደረጃ ደግሞ ሰውን ከእንስሳ ብቻ ሳይሆን በሰዎች መካከልም እንዲሁ ልዩነት ፈጥሯል፡፡

ፍጥረታት ከትውልድ ትውልድ በተሸጋገሩ ቁጥር ለውጥ ያመጣሉ እንጂ፣ እንደነበሩ ለዘመናት አይቀጥሉም፡፡

ተተኪው ዘር፣ በከፍተኛ ደረጃ እየበዛና እየተከማቸ ይሄዳል፣ ተተኪው ዘር በበዛ ቁጥር፣ የጥንቱን እያጠፋውና እያወደመው ይሄዳል።

የእንስሳት ማሰብና የሰው ልጅ ማሰብ፣ በየራሱ ደረጃ የሚገለጥና የሚታይ ነው።

የሰው ልጅ ሃሳብ ሶስትዮሽ መልክ ያለውና ከደመነፍሳዊ ሀሳብ የጸዳ ነው።

የሰው ልጅ ሀሳብ ውበትን የሚያፈልቅ ሲሆን፣ የእንስሳት ሀሳብ ግን ውበትን ማፍለቅ የሚችል አይደለም::

የሰው ልጅ ተፈጥሮ፣ ባለፉት ሰማኒያ ሺህ አመታት ውስጥ በዝግመተ ለውጥ እዚህ የደረሰ፣ ተለዋዋጭ ሂደትን አስተናግዳል፡፡

የሰው ልጅ ህልውና በማያቋርጥ ለውጥ ላይ እንደተመሰረተ የሚያረጋግጥ ታሪክ ያለው ፍጡር ነው።

የሰው ልጅ፣ በተፈጥሮው ማህበራዊ እንስሳ ነው፡፡

https://t.me/Write_Event
ሜዲቴሽን
Mindful meditation( ሙሉ አዕምሮ ሜዲቲሽን)

በጣም የታወቀው ሙሉ አዕምሮ ሜዲቴሽን የመጣው ከቡድሂዝም ነው። ሙሉ አዕምሮ ሜዲቴሽን ስጋትን፤ዲፕሬሽንንና ሌሎችን ስነ-ልቦናዊ በሽታዎችን ለመከላከል ከተጀመረ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል።

በምዕራቡ አለም ከአለፉት 20 አመታት ወዲህ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት 250 የሚሆኑ ማዕከላት ከላይ የጠቀስናቸውንም ሆነ ሌሎችንም ዘመናዊ መድሃኒት ማስታገስ ያልቻላቸውን በሽታዎች እንደ ደም ብዛት፣ ስኳር ግፊት የመሳሰሉትን በሽታዎች በመከላከል ትልቅ ውጤት አስገኝቶኣል።

ትንፋሻችን ላይ ትኩረት ማድረግ፤ማስተዋል፤ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ ትኩረት ማድረግ ላይ መሰረት በማድረግ

አንጎላችን ውስጥ ሃሳብ ሲገባና ሲወጣ ማስተዋልንና ምንም አይነቱ ዳኝነት ሳይሰጡ የሃሳብን መምጣትና መሄድ እንደ ሁለተኛ ሰው ዳኝነት ሳይሰጡ መታዘብ መቻልን፤ ያካትታል።

ፍርሃት ሲሰማን “ፍርሃት መጣ" ንዴት ሲሰማን አሁን ደግሞ "ንዴት መጥቷል” ሌላም ሌላም እያልን የተለያየ ስሜታችንን መምጣቱንና መሄዱን ማስተናገድ መቻል፤በስሜታችን አለመጠለፍንና ስሜቶቻችንንና ሃሳባችንን መንገድ ዳር ቆመን መኪኖች በአጠገባችን ሲመጡና ሲያልፍ እንደምናየው ስሜቶቻችን ሲፈራረቁ፤ሲመጡና ሲሄዱ ማየት መሞከር ነው።

ትንፋሽህን ስተነፍስ፤ በአለህበት ክፍል ውስጥ ያለው አየር ሁኔታ በቆዳህ ላይ ስሜቱ ሲሰማህ፤ ይቀዘቅዛል ወይስ ይሞቃል? አልፎ አልፎ ሃሳብ ይመጣል፤በጥንቃቄ ትኩረት ስጠው መምጣቱንም ተቀበለው --
ሲሄድም መሄዱም ልክ መኪና እንደሚሄድ አስተውለው፤ መኪናን ለማስተውል ማቆም አይስፈልግምና፤ ሌላው ደግሞ ይመጣልና፤ ይህ ነው የሙሉ አዕምሮ ሜዲቴሽን መግቢያ ቀዳዳው።

የዚህ አይነቱ ልዩ ትኩረት ከስጋትና ከጭንቀት ራሳችንን ለማላቀቅ ይረዳናል።

በቀን ውስጥ በማንኛውም ሰአት በየትኛውም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻላል።በቀላሉ አሁን እንኳን ይህን መጽሃፍ እያነበብክ ማድረግ ትችላለህ።በእጅህ ላይ የመጻህፉን ክብደት እንዲሰማህ ማድረግ፤የመጽሃፉን ሽፋን ከለርና የፊደሎቹን አጣጣል በመመልከት ትኩረትህን አሁን ወደ አለህበት ቦታና ሰአት ማምጣት
ትን ወደ አሁን ሰአትና ወደ አሁን ቦታ ማምጣት መቻል ትችላለህ።ትኩረትን ወደ አሁን ሰአትና ወደ አሁን ቦታ ማምጣት መቻል ነገ ወይም የዛሬ አመት ይህ ችግር ቢፈጠር ምን አደርጋለሁኝ የሚለውን ስለ ወደፊት
መጨነቅ እንዲቀንስ ያደርግልናል። ምን አልባት የፈራነው ችግር ጭራሽ ላይፈጠር ይችል ይሆናል።

ይቀጥላል .
" የፍቅር ትንታኔ

እንኳን ምድራዊ ሀብትና እውቀት ይቅርና ሰማያዊ ጸጋዎች ያለፍቅር ከባድ ናቸው፡፡
ፍቅርን ስትይዝ ሁሉንም ጸጋ ያዝክ ማለት ነው፡፡
የሃይማኖት ፍቅርና ጉልላት ፍቅር ነው፡፡
ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ባንተ ልብ አለ፡፡
አንተም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አለህ፡፡

ፍቅር ድል አለው፡፡ ስለፀጋ ስጦታዎች ብዙ ጭቅጭቅ አለ ስለሚበልጠው ጸጋ ስለፍቅር ግን ስብከት ጠፍቷል፡፡ ስለፈውስ ብዙዎች ይለምናሉ ነፍስን ስለሚፈውሰው ፍቅር ግን አይፀልዩም፡፡
ማንኛውመ መንፈሳዊ ነገር በእውቀት በእምነት በፍቅር ካልተደረገፈ ሀጢያት ነው፡፡

ትንፋሽ ድንገት የሚቋረጥ ሲመስልህ ፣ የልብህ ምቾት የቀዘቀዙ መስሎ ሲሰማህ ፣ ተስፋህ ጭልጥ ሲልብህ የምትድነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡
እንጨት በምስጥ ፣ እህል በነቀዝ ፣ ልብስ በብል ይበላል ፣ ሰውን ጥላቻ ይገዘግዘዋል፡፡
ሌሎች በኃይል እንዲሰሩ ሞተሩ ፍቅር ነው፡፡

ፍቅር ከሌለ ሰማዕትነት ሊኖር አይችልም፡፡
በየዕለቱ ሰማዕትነት ላይኖር ይችላል፡፡
በየዕለቱ መስዋዕትነት ግን አለ እርሱም ጥላቻን እንቢ ማለት ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ደረጃ ፣ በሁሉም ፀጋ ውስጥ በሁሉም ዘመን ደግሞም ለዘለዓለም የሚፈለግ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
በፍቅር የማይቃጠሉ ልቦች ወንድማቸውን ለመስቀል ይጨክናሉ፡፡

ቤተክርስቲያን የቆመችበቶ ምሶሶ ፍቅር ነው ፣ ያለፍቅር ትወድቃለች፡፡

ፍቅር ራሳችንን በሰው ውስጥ ሰዎችን በራሳችን ውስጥ የምናይበት መስታወት ነው፡፡
ፍቅር ያላቸው ሌሎችን የማስተካከል አቅም አላቸው፡፡
ፍቅር በቀላሎች ሰፈር ያላት ስያሜ ምስኪንነት ፍርሃት ነው፡፡
መንገዶችን ከመስራት ፍቅርን መገንባት ይቀድማል፡፡
የተሰሩት መንገዶች በጥላቻ ይዘጋሉ፡፡
ትልቁ ርዕዮተ አለም ፣ የማይከሽፍ መሳሪያ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ፍቅር ትልቁ ስጦታ ፣ ትልቁ መንገድ ፣ ትልቁ መሪ ነው፡፡

ዓይን ያለ ፍቅር ምን አገባኘ ይላል፡፡ ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ ምላስ ያለፍቅር ከወጣ ይሰብራል፡፡ እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል፡፡
እግር ያለ ፍቅር ከሔደ ድልድይ ያፈርሳል፡፡
ፍቅር የሌለው ሰማዕት ክርስቶስን አላወቀምና በከንቱ ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች እንደጎደለን ብንናገርም በዋናነት የጎደለንፍቅር ነው፡፡

ፍቅርበመጨረሻው ዘመን ይቀዘቅዛል እንጂ አይጠፋም፡፡
ያለፍቅር የተሰበኩ ነፍሰ ገዳይ ይሆናሉ፡፡ ለማፍቀር የልብ ፈቃድና የእግዚአብሔር ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ፍቅር በግልፅነት የምትከብር ናት ፍፁም የምትሆነውም ፍርሃትን ስታሸንፍ ነው፡፡

#ፍቅር_እራሷ_ጌጥ_ናትና_ጌጥ_አትፈልግም፡፡
#ፍቅር_ጽንፍ_የለሽ_ናትና_ዘረኘነት_አይስማማትም፡፡
#ተብራርቶ_ያላለቀ_ትንታኔ_ፍቅር_ብቻ_ነው፡፡
በፍቅር ያጌጡ በወርቅ ከተኝቆጠቆጡ ይበልጣሉ፡፡

ምኞት ዳርቻ ጥማትም እርካታ የሚያገኘው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ያለፍቅር የተዘረጉ ምፅዋቶች ከዱላ አይተናነሱም፡፡
#ኅሊናውን_አጉድለን_ሆዱን_የሞላንለት_ከሰጠነው_የሰረቅነው_ይበዛል፡፡

ፍቅር ሁሉም የሚሰጠው ምፅዋት ነው፡፡
ፍቅርን የማይሰጥ ድሃ የማይቀበል ሀብታምም የለም፡፡ ጎዶሎዎቾ መልካም የሚሆኑት በፍቅር ብቻ ነው፡፡
ሩጫህን የጀመርከው ያለ ጭብጨባ ብቻህን መሮጥ የጀመርህ ቀን ነው፡፡

#የታየህን_እይ_እንጂ_የሚያዩህን_አትይ_ትወድቃለህና፡፡"


😍🙏😍
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

"ፍቅር ማለት በምትወደው ነፍስ ውስጥ ራስን መግደል ነው"

ለብዙዎቻችን "ምስጢር" የሆነው ፍቅር ከሰው ልጅ የቀሕይወት ልምዶች ውስጥ አስደናቂውና አይረሴው ነገር ቢሆንም ሊያጤኑት የወደዱ ግን እጅግ ጥቂቶች ሆነው ተገኘተዋል፡፡ ለፍቅር አመጣጥና ዕድገት በየሰው ሕይወት ውስጥ7 በሚደንቅ ስነፅሁፋዊ አገላለፅ ሲቀርብና ሲያስደንቀን ኖሯል፡፡

ፍቅር በታላላቅ ደራስያን ብዕር ተፅፉል ፣ በታላላቅ ድራማዎች ላይ ተሰርቷል ፣ ባለቅኔዎች ተቀኘተውበታል.....ነገር ግን ፍቅር ምንድነው?
የሚለው ጥያቄ "መልስ አገኘሁለት" በማለት ለመፃፍም ሆነ ለመናገር የደፈረ "አልተገኘም"

አንድ ወንድ አንዲት ሴት ያፈቅራል ይህን የተለመደና በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ስሜት ተራ ክስተት አድርጎ ማለት የፍቅር ሀያልነት እንደማሳነስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
የፍቅር ሀያልነትን ጠቀሉን የተቋደሱ ሁቹ ሲመሰክሩ፡- "ፍቅር ከህይወት ጡት ውስጥ እንደሚፈልቅ ወተት አድርገን እንውሰደው"ይላሉ

የፍልስፍናው ጎራ ሰዎችም በዚያ ይስማማሉ፡፡ ሕፃን ልጅ የእናቱን ጡት ሲመለከት የሚሰማውን ደስታ ያህል በወጣትነት ዘመንም በሴቷ ላይ የሚያየው ቁንጅና እንዲሁ ያደርገዋል፡፡ ዳሩ ቁንጅናዋን የፍቅሩ ምክንያት አድርጎ መውሰድም የሚከብድ ነው፡፡

ምክንያቱም
#ቁንጅና_ፍቅርን_ከሚፈጥረው_በላይ
#ፍቅር_ቁንጅናን_ይፈጥራልና ፡፡

እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን፡፡ በትክክል የፍቅራችንን ክፋይ ያገኘን መስሎን በፍቅር የደከምንባቸው ጊዜያት መለስ ብለን ተመልክተን ደግሞ መሳሳታችንን ስንረዳ መለያየትን በቦታው ተክተን ወደሌላ የፍለጋ ጉዞ እንሰማራለን፡፡

ፍቅርን በባግህዋን ሽሪ ራጅናሽ(ኦሾ) እይታ ደግሞ ለማየት እንሞክር፡፡

ኦሾ "No Water, No Moon" በተሰኘው መፅሐፉ ፍቅርን እንዲህ አስቀምጦታል:-

"ብዙዋች በፍቅርና በወዳጅነት መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው በጎዳናው ላይ ሲዳክሩ ይስተዋላል፡፡ አንድ መስለው ይታዩዋቸዋል ነገር ግን አንድ አይደሉም፡፡ ይመሳሰሉባቸዋል ነገር ግን በእውነታው አይመሳሰሉም፡፡

እንዲያውም ከወዳጅነት ይለቅ ከፍቅር ጋር የሚመሳሰሉ ጥላቻ ነው፡፡
ጥላቻ ተቃራኒውን ነው - ወዳጅነት የጥላቻን እውነታ ደብቆ የፍቅርን መልክ ይይዛል፡፡
ነገር ግን ፍቅርን እየገደለ ነው፡፡
አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ ማሰብ(Possessiveness) መርዘኛ ነገር የለም፡፡ ይህን በሚገባ ከተሰጃችሁ ወደ ቀጣይ ጉዳይ እንዝለቅ....." ይላል፡፡

"ለብዙዎችእንዲህ ሆኗል ለናንተም እንዳይሆንባችሁ ልንገራችሁ ምክንያቱም7 በፍቅርና በግንኙነት መካከል ያለው ልዩነት ግራ አጋብቷቸዋል፡፡
በተለይም ከውጪ ሆነው ሲመለከቱ የኖሩ ሰዎች ሰለባው ሲሆኑ ኖረዋል ወዳጅነትና የግል ማድረግን እንደፍቅር ወስደውት አይቻለሁ፡፡
በዚህ መንገድም እውነተኛውን ነገር አጥተውታል

"ሰውን የግል ለማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ ስሜት ጥላቻ ይሻላል፡፡
#በጥላቻ_ውስጥ_ውሸት_የለም፡፡
ከዚያ በላይ ደግሞ ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል፡፡
የሰውን ልጅ የግል የማድረግ ፍላጎት ግን ፈፅሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም፡፡

"ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው፡፡"
ፍቅር ማለት ሞት ነው፡፡
የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው፡፡


ዕለት ዕለት ወደ ጥለቅ የነፍሷም ቦታ ትወስዳለህ ፍቅር ወደ ምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው፡፡
ጉዞውም ማቆሚያ የለውም፡፡
አንዲት ሴት ስታፈቅራት አንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት፡፡
ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡
አንባቢዎቼ፣ የሃገሬ ውዶች! ዛሬ የስኬትን ሃሳብ እንጀምርና ለጥቂት ቀናት እንቆይበት::
የተሸወደው ሰውዬ …
“ስኬት ማለት ለብዙዎች ሰው ጥቅም የሚውልን ነገር መፍጠርና ያንንም በማድረግ ጉዞና ሂደት ውስጥ ደስተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ በዚህ አመለካከት ላይ ካተኮርክና የእኔ ነው ብለህ ከያዝከው አንተ ስኬታማ ማንነት አለህ” – Kelly Kim
ታሪኩ ከተከናወነ ረጅም አመታት አስቆጥሯል፡፡ አንድ ቀን አንድ እጅግ ባለጸጋ የሆነ አባት ልጁን ወደ አንዲት ገጠር ይዞት ሄደ፡፡ የጉዞው ዋና አላማ ልጁ በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ተመልክቶ ምን ያህል ድሆች እንደሆኑ እንዲገነዘብና እርሱ ያለውን የተሻለ ሁኔታ እንዲያደንቅ ነው፡፡ በዚያ በሄዱበት አካባቢ በአንድ እጅግ በጣም ድኃ ቤተሰብ ነው ብለው ባሰቡት ቤተሰብ እርሻ ውስጥ ሁለት ቀናት በማደር አሳለፉ፡፡ በእነዚህ ሁለት ቀናት ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ካደረጉና ማየት የፈለጉትን ሁሉ ከተመለከቱ በኋላ ጉዞአቸውን አጠናቅቀው ወደቤታቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡
ወደቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ በአባት አነሳሽነት ውይይት ጀመሩ፡፡
አባት፡- “ጉዞው እንዴት ነበር?” በማለት ልጁ ከጉዞው እንዲማርለት የፈለገውን ነገር መማሩን ለማረጋገጥ ጠየቀው፡፡
ልጅ፡- “ጥሩ ነበር” በማለት ብዙም ስሜት በማይገልጽ መልኩ አጭርና ግልጽ መልስ መለሰለት፡፡
አባት፡- “ሰዎች በምን አይነት ድህነት እንደሚኖሩ አየህ?” የሚልን ተከታይ ጥያቄ በማቅረብ የበለጠ ማብራሪያን ለማግኘት ሙከራ አደረገ፡፡
ልጅ፡- “አዎን” በማለት አሁንም አጭር መልስ ሰጠው፡፡
አባት፡- “እስቲ ከዚህ ጉብኝት ምን እንደተማርክ ንገረኝ”
ልጅ፡- “እኛ አንድ ብቻ ውሻ እንዳለንና እነሱ ግን አራት ውሾች እንዳላቸው አየሁ፡፡ እኛ የጓሮ አትክልታችን ጋር ብቻ አንድ የመዋኛ ስፍራ አንዳለን፣ እነሱ ግን ከቤታቸው አጠገብ መጨረሻው የማይታይ ትልቅ ወንዝ እንዳላቸው አስተዋልኩ፡፡ እኛ ከውጪ ያስመጣነው የአትክልት ስፍራ መብራቶች አሉን፣ እነሱ ግን ማታ ማታ የሚያበሩላቸው ኮከቦች አሏቸው፡፡ ከእኛ በረንዳ አሻግረን የምናየው ረዥም አጥራችንንና ከዚያም ሕንጻዎችን ነው፣ እነሱ ግን ከጸሃይ መውጫ እስከ መግቢያ ይታያቸዋል፡፡ እኛ የምንኖርበት ትንሽ መሬት አለችን፣ አነሱ ግን አይተን የማንጨርሰው ሰፊ መሬት አላቸው፡፡ እኛ የሚያገለግሉን ሰራተኞች አሉን፣ እነሱ ግን ሌሎችን ያገለግላሉ፡፡ እኛ ምግባችንን ገዝተን እንመገባለን፣ እነሱ ግን ምግባቸውን ተክለውና አብቅለው ይመገባሉ፡፡ እኛን እንዲጠብቀን በዙሪያችን የግንብ አጥር አድርገናል፣ እነሱ ግን እንዲጠብቋቸው በዙሪያቸው ወዳጆቻቸውንና ጓዋደኞቻቸውን አድርገዋል፡፡”

የልጁ አባት እርሱ በብልጽግናና በድህነት ላይ ያለው እይታ ከልጁ እይታ እጅግ ስለተራራቀበት የሚለው አጥቶ ዝም አለ፡፡ በመጨረሻም ልጁ እርሱ ያለውን ግንዛቤ አባቱ በሚገባ እንዲያውቅለት በመፈለግ እንዲህ ሲል ንግግሩን አጠናቀቀ፣ “አባቴ ሆይ፣ ምን ያህል ድሆች እንደሆንን ስላሳየኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡”
ሃብትና ብልጽግና ምንድን ነው? ስኬትስ ምንድ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚለኩትስ በምንድን ነው? አንድ ሰው ለስኬት የሰጠውን ትርጉም በመመልከት ስለማንነቱ መናገር ይቻላል፡፡ ይህ ስኬት የሚባለው ነገር ትርጉም ትክክለኛነት እጅግ አስፈላጊ ነውና በሚገባ አስብበት፡፡ ምናባት ሳታስበው ስኬት ውስጥ ይሆን ያለኸው?

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
@Write_Event
አስተማሪ አጭር ታሪክ .!


አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን
በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ https://t.me/Write_Event
በአንድ ቋንቋ ውስጥ መወለድ፣ በአንድ አካባቢ ማደግ የሰው ልጆች በዝግመተ ለውጥ ያመጡትና የሚያሳምረን ልዩ ቀለም ነው፡፡

ዓለም ልሙጥ ብትሆን አትማርክም፡፡ ባሳደጉን፣ ባስተማሩን፣ ባገኘናቸው ሰዎችና በዓለም ሁነቶች ማንነት እንገነባለን፡፡

የሰው ልጅ ያለ ባሕል አይኖርም። ነገር ግን የትኛውም ማንነት ውስጣችን ካለው እምቦቀቅላ (inner child) የሚያወጣን ከሆነ መልካም ማንነት አይደለም።

የሰው ሐዘን የማይሰማን፣ የሰው ነገር የማይቆረቁረን ደረጃ ላይ ከደረስን እና የኔነት ግንቡ ተልቆ ከሰው በላይ እንደሆንን ከተሰማን፣ ያ ትክክለኛ ማንነታችን አይደለም፡፡

እዚህ ስለተወለድኩ የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም፡፡ የትኛውም ማንነት በተወለድንበት ቦታ፣ ባየናቸው ሰዎችና በተማርናቸው ትምህርቶች የሚቀየር እንጂ እውነተኛ ማንነታችን አይደለም፡፡

.
.
ታሪክን ዞር ብለን እንይ፡፡ ታሪክ መማሪያና ዛሬን ማስተካከያ ቢሆን መልካም ነው፡፡

ዝም ብሎ በታሪክ መኩራትም መልካም አይደለም። ታሪክ ሊያኮራን የሚገባው ተቀብለነው፣ ከውስጡ መልካም ነገር ይዘን፣ የኛን ሕይወት ካሻሻልነበት ነው።

የኛን ሕይወት ማጥፊያ ከሆነ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ማንነት መፈተሽ አለበት፡፡ ሰው በጣም ሲከፋው ቤተሰቦቹ ቤት ሄዶ ጭንቀቱን አራግፎ ይመለሳል አይደል?

አሁን ወደ ሰውነት ወይም ወደተነሳንበት ማንነት የምንሮጥበት ጊዜ ነው፡፡ ሰው ነን ስንል የሰው ሁሉ ሕመም ይገባናል፡፡ ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው፡፡ ታሪክ ለሌላ እኩያዬ፣ ሌላ ገጽታ እንዳለው መረዳት አለብኝ፡፡

ማናችንም ከመቶ፣ ከሺህ ዓመት በፊት አልኖርንም። የምናውቀው የተወሰኑ ዐሥርት ዓመታትን ነው፡፡ ሌላው ተጽፎ ያነበብነው ነው፡፡

ታሪክ እንደ ጸሐፊው ሊበረዝ እንደሚችል ማወቅ አለብን፡፡ ስለምንጽፈው ታሪክ እንጂ ስለተጻፈ ታሪክ መሞት የለብንም፡፡ ስለተጻፈ ታሪክ ማንም ሰው መሞት የለበትም፡፡

በአብዛኛው የገነባነው ማንነት የተሰበከ ማንነት ነው፡፡ የተነገረን ማንነት እንጂ የኖርነው ማንነት አይደለም፡፡

ከተነገረን ማንነት የኖርነው ማንነት ይበልጣል፡፡ ይሄ በግልጽ የሚታየን ራቅ ስንል ነው። የተሰጠንን ማንነት አንድ ጊዜ እንደ ልብስ አውልቀን አስቀምጠነው፣ እንደ ሰው ወይም እግዚአብሔር እንደፈጠረው ሰው ራሳችንን ካየን በኋላ ሌሎች ማንነቶችን ደግሞ ከዚያ በኋላ ብናጠይቃቸው መልካም ነው፡፡

ለኔ ቀላሉ መንገድ ራሴን አለማመን ነው፡፡ ጭንቅላቴ ውስጥ የሚመጡ ሐሳቦችን መካድ ግዴታዬ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም እውነት ይሄ ነው ወይ? ብዬ መጠየቅ አለብኝ፡፡ ታሪክ በውሸት ተጽፎ እኩዮችሽ በጋራ ካመኑበት ትክክል የመሆን አቅም ያገኛል።

ለምሳሌ በብዙ ነገሥታት ሥልጣኔ ያለፉ አፍሪካዊያን ከአፍሪካ ተወስደዋል፡፡ ታሪካችን ከቅኝ ግዛት እንዳልጀመረ ይታወቃል፡፡ አፍሪካዊያን ካሪቢያን ተወስደው የተጻፈላቸው ታሪክ ግን አፍሪካዊያን “ባሪያ እንደሆኑ” ያስተምራል። ማንም ሰው ታሪኩን ጽፎ ራሳቸውን በዚህ መንገድ እንዲቀበሉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ታሪክ ሲነገረን ከዛሬ ጋር ማገናዘብ አለብን፡፡

ሮፍናን

https://t.me/Write_Event