ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ሕይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት
ደስታም - ሀዘንም


ክፉ ቀን ጥሩ ነው ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል , ክፉ ቀን አንደ ለሊት ጨለማ ነው የሌሊቱ ጨለማ ለእንቅልፍ አንደሚጠቅም ሁሉ የቀን ብርሀንም ለስራ ይበጃል ።

ለህይወት እንቅልፍም ስራም የግድ አስፈላጊዎች ናቸው . . . .


ስለዚህም ይፈራረቃሉ ። ትዕግስት መከራን እርግዛ ትወልዳለች

እንደ ሳቀ የሚቀረው ስቀው የተነሱት ፎቶ ብቻ ነው፡፡

' አዳም - ረታ '


ሼር!

https://t.me/Write_Event
#"በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደውሀ ቅርፅህን አትቀያይር "


በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ከሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው ። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሃል, አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ሊያፌዙብህ ይችላሉ


ምናለፋህ በዓለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም ልትጠላም አትችልም ። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን ።
አንድ ነገር ልንገራችሁ በህይወታችሁ ውስጥ ማንንም አትውቀስ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጧችሁዋል, መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኗችሁዋል ።

ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኗችሁዋል ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኗችሁዋል !".

ስብሐት

ሼር!!!

https://t.me/Write_Event
(ኤፍሬም ስዩም)

:- እውነት ወደ ኋላ

ገንዘብ ካለው ጋራ
ፍቅር አይኖርም ወይ ብለሽ ጠይቀሻል!?
እኔ ያንቺን እንጂ
የሌላን አላልኩም እጅግ ተሳስተሻል
አይኖርም አላልኩም...አይጠፋም ይኖራል
ይኖራል
ይኖራል
ግን?...
ከባለሐብት ጋር
ተፋቅራ 'ምናያት የቷም አይነት እንስት...
'ምን ' ትሁንም ' ምንም '
የሕይወት ታሪኳን ወደኋላ ሄደን ....ጥቂት ብንገመግም
አንድ ቡና ለሁለት ....
አብራ የጠጣችው አንድ አፍቃሪ አታጣም ።

#ኤፍሬም ስዩም

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔



ክፍል_➊➊

...🖊ከሆስፒታል አልጋ ላይ እራሴን አገኘሁት። እናቴ ላይ ጨክኖ አፈር ማልበሱ ክፉኛ ሰቀቀን ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ድካም፣ሀዘን፣ብስጭትና ረሀብ ተደማምረዉ እራሴን እንድስት ስላደረጉኝ እጅግ የምሳሳላት እናቴን እንደ ወጉ አልቅሼ መቅበር ተስኖኝ በቀብሯ ማግስት እራሴን ስቼ ለህክምና ከገባሁበት ሆስፒታል ዉስጥ ነቃሁ። መጀመሪያ ላይ የአባቴ መጥፋት የሄደበት የገባበት አለመታወቁ ክፉኛ ያስጨንቃት ነበር ምናልባት ሰዎች አደጋ አድርሰዉበት እንዳይሆን ብላም ትሰጋ ነበር እዉነታዉ ግን አባቴ በእድሜ እጅግ ከምታንሰዉ እንደዉም እንደሰዎች አባባል ከእኔ እኩያ ከምትሆን ሴት ፍቅር ይዞት ቤት ንብረቱን በትኖ ከእሷ ጋር መኮበለሉን ስትሰማ ድንጋጤ ከነበረባት ግፊት ጋር ተዳምሮ ለሞት ዳረጋት።አሁን በህይወት ለመቆየት ምን ምክንያት ይኖረኛል? ህይወት እራሷ በሀዘኔ ዳንኪራ ልትመታ!፤በለቅሶዬ ጭቃ አቡክታ ቤቷን ልትሰራ!፤የእኔን ዉጣ ዉረድ እንደ ኮሜዲ ፊልም ልትኮሞኩም ስቃይና ሀዘንን ለግሳ ለዚህች ጠማማ ዓለም ካስረከበችኝ በሗላ ጭላጭ ተስፋን እንደማትሰጠኝ ልቦናዬ ከተረዳ ሰነባብቷል። እየሩስ ከአጠገቤ ነበረች መንቃቴን ስትመለከት በፍጥነት ሄዳ ዶክተሯን ጠርታ መጣች
እንዴት ነሽ? ምን አየተሰማሽ ነዉ?
ተስፋ መቁረጥና የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት መጓጓት! ነዉ የሚሰማኝ ብዬ ለዶክተሯ ብነግራት ምነኛ ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህንን ለመረዳት እኔ የቆምኩበት ላይ ልትቆም እኔ የሚሰማኝ ሊሰማት እንደማይችል ልቦናዬ ስላወቀዉ
ደህና ነኝ! አልኳት
በእጆቿ ግንባሬን ከነካካችና የሙቀት መጠኔን ከለካች በሗላ
አሁን ደህና ነሽ ነገር ግን ሰዉነትሽ ስለተጎዳ ፈሳሽ ነገሮች በብዛት መዉሰድ ይጠበቅብሻል የማዝልሽንም መድሀኒት በአግባቡ መዉሰድ ይኖርብሻል! አለችኝ! ከእየሩስ ጋር የታዘዘልኝን መድሀኒት ተቀብዬ ወደ ቤት አመራን። አክስቴ ባለቤቷና ከአዲስ አበባ አብረዉን የመጡት ሰዎች ሀዘንተኞቹን ምሳ ሲመግቡ ደረስን! አብዛኞቹ እኔን ሲመለከቱ በሀዘን ደረታቸዉን መምታት ጀመሩ እየሩስ በፍጥነት ወደ መኝታ ክፍሌ ይዛኝ ገባች... መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ባማረ ፍሬም የተሰቀለዉን የአባቴን ፎቶግራፍ ስመለከት የንዴትና የበቀል ስሜት በደም ስሬ ዉስጥ ይሯሯጥ ጀመር...

ይቀጥላል...

ሼር ማድረግ አይርሱ !

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔



ክፍል_➊2

...🖊እንግዳ ከሌለበት ሱቅ ዉስጥ አቤል ለብቻዉን ቁጭ ብሎ አገኘሁት። ገና ሲያየኝ ፊቱ ላይ የሚታየዉ ንቀትና ትዕቢት የንዴቴን መጠን በእጥፍ ቢጨምረዉም አራሴን አረጋግቼ በእናቴ ሞት ምክንያት ወደ ጅማ ሄጄ እንደነበረ አሁን ሙሉ ገንዘቡን ልከፍለዉ እንደምችልና በምትኩ እሱ ጋር ያለኝን ፎቶና ቪዲዮ እንዲያጠፋዉ ጠየኩት። እየሩስ ወደ ሱቅ ዉስጥ መግባት ስላልፈለገች ከዉጭ ቆማ እኔና አቤልን የምናደርገዉን እንቅስቃሴ ትከታተላለች።

አሁን ፋይሎቹን አልያዝኳቸዉም ነገ እደዉልልሽና የትና እንዴት ተገናኝተን ገንዘቡንና ፍይሉን እንደምንለዋወጥ አሳዉቅሻለሁ! አለኝ

ግን...አንተ...ሙሉ በሙሉ ፋይሎቹን እንደምትሰጠኝና አንተ ጋር ኮፒ እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለኝ?

ማረጋገጫ አይኖረኝም! አንቺ ግን ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እኔን ማመን ብቻ ነዉ!
ዉስጤ ያለዉ የጥላቻና የበቀል ስሜት አንጀቴ ሲያላዉሰዉ ይታወቀኛል
ስለየትኛዉ እምነትና መታመን ነዉ የምታወራዉ ከሀዲ!! ብለዉ ዉስጤ ያለዉ ህመም በትንሹም ቢሆን እርጋታ እንደሚያገኝ ባዉቅም ቸኩዬ ነገሮችን ማበላሸት ስላልፈለኩ

እሺ! አልኩት!

ምንም አይነት ብልጠት ወይም ደግሞ ተንኮል አስባለሁ ብትዪ አሁን ካለሽበት ሁኔታ የባሰ መቀመቅ ዉስጥ እንደምከትሽ አትርሺ!
በእናቴ ሞት የተሰማኝ ሀዘን ላይ ሲያንጓጥጥ መመልከቱ ከሞትም በላይ ሞት ቢሆንም ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ትዕግስት ስለነበረ የሚናገራቸዉን ንግግሮች እየመረረኝም ቢሆን መዋጥ ግዴታ ሆነብኝ። በግምት በእድሜ አቻ ልትሆነኝ የምትችል ጠቆር ብላ የደስ ደስ ያላት ወጣት ሴት ወደ ሱቁ ገብታ በፓስታ የታሸገ ነገር አቀበለችዉ አቤል ደግሞ በምትኩ የሚሞሪ ካርድ ሲሰጣት ተመለከትኩ! ፊቷ ላይ ይታይ የነበረዉ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እሷም እንደኔ የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆኗ ምስክር ነበር። እስከመች? አልኩኝ በዉስጤ! ለሴት ልጅ ህመምና ሀዘን እየሰጠ በምትኩ ገንዘብ እየተቀበለ የሚኖረዉ እስከመች ነዉ?

ነገ ከሰአት 8:00 ሰዓት ላይ የምትችል ከሆነ እዚሁ ሱቅ መጥቼ ገንዘቡን ላቀብልህና ፋይሎቹን ስጠኝ
እደዉልልሻለሁ! ብሎ አሰናበተኝ! ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን
አክስቴ ፈቃደኛ ባትሆንም በብዙ ልመናና ለቅሶ ከጅማ ሽጬ ከመጣሁት ገንዘብ ላይ የተወሰነዉ በእናቴ ስም የሚጠራና በአክስቴ ባለቤትነት የሚተዳደር ሆቴል አዲስ አበባ ዉስጥ እንድትከፍት አስማምቼያት የተቀረዉን ገንዘብ የእናቴ የዘወትር ህልም የሆነዉና ሳትፈፅመዉ ሞት የቀደማት የእርዳታ ድርጅት መክፈት በእኔ አቅም የማይቻል ስለሆነዉ ገንዘቡን ለእርዳታ ድርጅት ለመስጠት መወሰኔን ገለፅኩላት!
ስለ እራስሽም የነገ ህይወት ማሰብ ይኖርብሻል?

አስቤያለዉ አክስቴ አሁን ለእኔ ገንዘብ ሳይሆን ማረፊያ ነዉ የሚያስፈልገኝ የማይከፈልበት ማረፊያ!

አልገባኝም!

አክስቴ እንደማይገባት አዉቃለሁ ሊገባትም አይችልም እኔ ግን ነግቶ ነገ ላይ ለመቆም ልቤ ቆሟል ሁሉም ነገር ፍፃሜዉን ሊያገኝ አንድ ምሽት ብቻ ፊት ለፊቴ ተደንቅሯል እንዳረጀ ዉሻ ሂድ ብሎ ይህንን ምሽት በካልቾ መቶ የሚያባርርልኝ ማን ይሆን? ማንም!
አይገባሽም አክስቴ ተይዉ!.

🕹የመጨረሻው ክፍል በቀጣይ ይለቀቃል ።
ክቡራን ቤተሰቦች በኛ እና በታዋቂ ደራሲያን የተፃፉ አዲስ አስተማሪ እና አጓጊ ስነ ፁሁፎች አሉን ።
ያንን አንድ ላይ ለመጋራት ቤተሰብ ያስፈልጋል ስለዚህ ለጓደኞቻቹ እና ወደ ተለያዩ ግሩፕ ሼር ማድረግ እንዳትረሱ አንድ ላይ እናንብብ 🙏

ይሄንን ስለምታደርጉ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏

https://t.me/Write_Event
​​.........አደዋ ዝም ብሎ ድል አይደለም💚
አድዋ የስነ-ልቦና ከፍታ ነው ;💛
አድዋ የእልህ ጥግ ነው ;❤️
አድዋ የነፃነት ዋጋ መለኪያ ነው ;💚
አድዋ የአገር ፍቅር ጫፍ ነው ; 💛
አድዋ የባርነት የሞት ጉድጓድ ነው ;💚
አድዋ ከመለያየታችን የለየን ድንበር ነው ;💛
አድዋ የእብሪተኞች ጥሩር ሀፍረት ነው ;❤️
አድዋ የሀበሻ የሞራል ከፍታ ነው ;💚
አድዋ የጥቁሮች አንገት ትራስ ሆኖ ቀና ያደረገ ነው ;💛
አድዋ የምኒልክ የመሪነት ጥበብ💚
የራስ መኮንን ራስነት ፣ የባልቻ ወኔ ፣ ያሉላ የድል ጮራ ❤️
ያያቶቼ የመንፈስ ከፍታ.ስጦታ ነው ።💛
አድዋ ከድል ባሻገር ሚሊዮን ርቀቶችን ከፍ ብሎ የተሰቀለው ለዚህ ነው።
💚💛❤️

💚💛
💚💛❤️

💚💛
@write_event
​​💔የባከነች_ነብስ💔

♥️
♥️

🛎የመጨረሻው ክፍል🛎

...🖊 <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

❇️//ተፈፀመ//❇️

🔮የባለታሪኳ መልዕክት

👉 የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!


💈ምስጋና
👉ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ
!



,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

t.me/write_event
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​ድሮ አስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለን ነፍሰ ቀጭኑ ኬሚስትሪ መምህራችን እንዲህ ሲሉ ጠየቁን ።
ውሀ ከምን እና ከምን ንጥረ ነገሮች ነው የተፈጠረው ?🙂
ብዙ ተማሪዎች ይህችን ቀላል ጥያቄ ለመመለስ ተቅለበለብን ። መምህሩ ግን ከሁሉም ተማሪ ይልቅ ትኩረታቸውን ስንሻው ላይ አድርገው እንዲመልስ አስገደዱት ።
ስንሻው ከእንቅልፉ የተነሳ ይመስል አይኑን አሻሽቶ ትንሽ ቆየና መምህሩ ጥያቄውን እንዲደግሙለት ጠየቃቸው። /በነገራችን ላይ የስንሻው አባት ልጃቸው ትምህርት እንዳይገባው ተደግሞበታል ብለው ስለሚያስቡ እሱን ይዘው ያልተንከራተቱበት ፀበል አልነበረም ። ኋላ ላይ ቢታክታቸው ጊዜ እርግፍ አድርገው ተውት ! እርሱም ትምህርት አይንህን ላፈር ብሎ ማንበብ እና ማጥናቱን እርግፍ አድርጎ ተወው /
"እኛ የምን ጠጣው ውሀ ከምንና ከምን ውህደት ተፈጠረ ? " ብለው ጥያቄውን ደገሙለት ።
ውሀ ልማት እና ቀበሌ ተዋህደው በገጠሙት የቧንቧ መስመር ነው የተፈጠረው ! ብሎ ሲመልስ ያልደነገጠ ተማሪ አልነበረም ። ሁላችንም እያሾፈ ነው ብለን በትኩረት አየነው ።
እሱ እቴ !
ልቡ ደጭ እንኳ አላለም !
“ስ ! ውይ ይቅርታ” አለን መልሶ .... በቃ ኦክሲጂንና ሀይድሮጂን ታውሰውት ነው ማለት ነው ብለን ማስተካከያውን በጉጉት መጠባበቅ ያዝን !
“ውሀ ልማት እና ሰሜን ሸዋ ዞን በመተባበር ነው “ ብሎ እርፍ አለው ።
ነፍሰ ቀጭኑ መምህራችን በንዴት ተነፋፍተው ነብር አከሉ ! አለ አይደል የቤት ውስጥ ድመት ስትቆጣ እንዴት ነው ኩፍ የምትለው ?
መምህራችን ኩፍ አሉ ።
በስመአብ !
አስተማሪ ሲናደድ ለካ እንደዚህ ያስፈራል ?
ከአስተማሪም ሁሉ ደግሞ ኬሚስትሪ አስተማሪ ሲናደድ በጣም ያስፈራል ። የሆነ ሰልፈሪክ አሲድ ከላብራቶሪ አንስተው ፊቱ ላይ የሚከለብሱበት ሁሉ መሰለን ።
“ተነስ !”
ስንሻው ተነሳ ።
“እነ ሚካኤል ፣ እነ እዮብ እነ አቤል ኢንጅነር ወይ ዶክተር ሲሆኑ ሻንጣ ተሸካሚያቸው እንደምትሆን አልጠራጠርም “ ብለው ሞራሉ ላይ ቀዝቃዛ ውሀቸውን ከለበሱበት ።
እንደፈራነው ከወራት በኋላ ስንሻው ማትሪክን ወደቀ ። እኛ ፈተናውን በጥሰን አለፍን ።
እኛ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለዩንቨርሲቲ ስንዘጋጅ ስንሻው የሆነ ትምህርት እንደከረሜላ አሽጎ የሚሸጥ ኮሌጅ ዲፕሎማ መማር እንደጀመረ ሰማን ።
ግቢ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስንሆን ስንሻው ቀበሌ ስራ አጊንቶ መግባቱ ተነገረን ። ያኔ በሱ ሙድ ያልያዘ አልነበረም ።
እንደውም አንድ ቀን በድሉ የሚባል ቸካይ የነበረ ተማሪ ወደኔ ጠጋ ብሎ "ስንሻው በዚህ ድድብናው ቀበሌ ስራ ማግኘቱም ተመስገን ነው ብሎ ገለፈጠ ። "ስንሻው እኮ ቀን ስራ እንኳ ይበዛበታል ። እንደ ህንዶች ሰባቴ ቢፈጠር ሰባት ጊዜም ትምህርት አይገባውም" አለኝ ቀጥሎ ።
ስንመረቅ ግን የነፍሰ ቀጭኑ ሰውዬ እርግማን ለስንሻው ምርቃት ሆኖ እርፍ አለው ።
የከተማችን አስተዳደር ተመራቂ ተማሪዎች ተደራጅታችሁ ኮብልስቶን አንጥፉ ምናምን ብሎ በስብሰባ ሰበብ ሲጀናጀነን ስንሻው ተከብሮ የከተማችን ከንቲባ ሆኖ ነበር ።
ጭራሽ እዛ አመዳችን ቡን ባለ ተመራቂ ተማሪዎች ፊት ቀርቦ ስለ ስራ ፈጠራ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠን ። ኢንጅነር ነን ዶክተር ነን ብላችሁ አትኮፈሱ የጀበና ቡና ብታፈሉ ትችላላችሁ ። ለምሳሌ ሚካኤል እዮብ አቤል በኢንጅነሪንግ እና ዶክትሬት ተመርቃችሁ ሰፈር ለሰፈር ከምታውደለድሉ የጀበና ቡና ብታፈሉ ምን ችግር አለው ? ብሎ በምሳሌነት ጠቀሰን ። እኔ እንዳስተማረን ሳይሆን እንደ ሰደበን ቆጥሬው እሳት እንደነካው ላስቲክ ተኮራመትሁኝ ።
ከስብሰባው በሁላ ስንሻውን ለማናገር ከተቀመጥሁበት ተነስቼ ተራመድኩኝ ። የልጅነት ጓደኛዬ ስለሆነ ሰላምታ ልሰጠው አስቤ ነው የቀረብሁት ። በሰዓቱ ከየት መጣ ያልተባለ ጠባቂው በመዳፉ ጭብጦ አሽቀነጠረኝ ።
ቀና ብዬ አየሁት !
“ምን አጠፋሁ አለቃ?”
ፈርጣማው ጠባቂ በቁጣ ቱግ ብሎ እንዲህ አለኝ
“አንተ ምን አይነት ደፋር ነህ ባክህ ? ክቡር ከንቲባችንን ለመቅረብ አይደለም ሻንጣቸውን ለመሸከም ብትመጣ እንኳ ማስፈቀድ ነበረብህ “ 🙂
#ሚካኤል አስጨናቂ


https://t.me/Write_Event
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
<<ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?>> ትላለች አንደኛዋ።
<<እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!>> ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።

ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
<<ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?>> ይለኛል።
<<ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?>>
<<አይ ሻማው ይሁን በቃ!>> ይላል እየተቅለሰለሰ።

አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። <<ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!>>

ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው።

የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም!

ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "beauty and the beast" ሆሆ!
ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል።
<<ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም>> ስለው
<<ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!>>

እያሳዘነ ያስቀኛል።

ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ።
<<አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?>>
<<አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!>> አለ አሁንም እያለቀሰ!
<<እሺ ምንድን ነው?>>
<<እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!>>

ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ።

ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው?

የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ።

የፈሪ ትልቁ ችግር.....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም!

<<ለማን ተናግረህ ነው?>> ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት።

የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም።

ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ።

የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን <<ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?>> አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው።

ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ።

አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ!

አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል።

ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ።

ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ <<አባቴ ማነው?>> ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው?

<<ተረት ተረት>>
<<የመሰረት>>
<<በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች>>
<<እእእሽ>>
<<ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?>>
<<ምን?>>
<<ሻማ! በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን እጠፋለሁ ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!>>
<<ምን አደረገች?>>
<<በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።>>
<<ከዛስ?>>
<<ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..>> እያለ የሚቀጥል ተረት
!

ታሪኩን ከወደዳችሁትና እንደዚ አይነት አጫጭር ታሪኮችን እንድንፅፍላችሁ ከፈለጋችሁ share አድርጉት።😊👍👍

Join
@write_event
እናት ልጇን እያጠባች ጎረቤቷ አይታ.. ''pa! እንደ አባቱ ነው ሚጠባው''😊
@write_event
ቂጥ ለመውደዳችን ማህበረሰቡ ተጠያቂ ነው..

ለዳቦም ለድስቱም ቂጥ ይጣፍጣል እየተባልን ነው ያደግነው🤷‍♂

@write_event
( "ሰላም እለኪ" )


የአምስት ሺ ዘመን
የታሪክ ባለቤት
የአፍሪካ ቀንድ ኩራት
ክብርት እመቤት
🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጺያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.

ጋራ ሸንተረሩ
ለምለሟ ሀገሬ
ንፋስ ቢያይልብሽ
ድንገት መጥቶ ዛሬ
ፈርጠም ባለው ክንድሽ
በልጆችሽ ካዝማ
ቀንሽ ብቅ ሊል ነው
አይዞሽ እናት እማማ
🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጺያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.

የፊደል ቀማሪ
የዘመን ቆጣሪ
የጥበብ መፍለቂያ
የሀይማኖት መታያ
ቅድስት




🇪🇹
ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጵያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ
.


.
.
የሰው ዘር መገኛ
የእውቀት ሊቀኛ
የአክሱም ላሊበላ
እንዴት ታደልሽ ምነኛ
ባረኮተ እግዚሔር
የሰጠን ለእኛ
.
..

ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.

ባጎረሰ እጅሽ
ምላሽሽ ንክሻ
ብትሆን ምድርሽ ዛሬ
የእንባ መፍሰሻ
የሰው ሞት ብዛቱ
አራዊቱ ሳይቀር
አንቺን ይቀብርሽ ዘንድ
ታስቦልሽ ነበር
ላያድር ነገር
ማምሸትን ፈለገ
አቅምሽን ሊፈትን
እያፈገፈገ
አደባ ከጀርባሽ
ዞሮ ሊዋጋ
አንቺን አዋርዶ
ንግስናን ፍለጋ
.
.
.

ይህ ሁሉ ቢሆንም .......
ምኞት አይከለከል
ተመኝቶ ነበር
ሀይልሽን ፈትሾ
እንዲህ በአንዴ ሊቀበር

እንኪያስ ደግሜ ልበል.......

🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹

ይብቃ መፍሰሱ
የደም ጅረቱ

የተስፋቸው መጨለም
የህጻናት ሞቱ
ስደት እንግልቱ
ከእናት ጉያ
የልጅ መነጠቅ
በርሀብ አድማ
በሞት ከመድረቅ
የወጣት መቀጨት
ከመንገድ መቅረት
ሌላውን ጨምሮ
ይሔ ሁሉ ይብቃ
የሰላም ይሁን
ቦታው ፈረቃ
.
.
.

ሰላም ለአንቺ ይሁን ሰላም ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.
.

ፍክት በይ ሀገሬ
እንደ አደይ አበባ
የሰላም ባለቤት
ከአንቺ ዘንድ ይግባ
ይመርብሽ እማ
ቀሚስሽ ይንዘርፈፍ
ደምቀሽ ታይልን
ከአለም ብለሽ ከፍከፍ
ልጆችሽን ስብስብ
እቅፍ ድግፍ አርጊ
የብርሀንሽን ሚስጢር
እግዚሄርን ፈልጊ
.
.
.
.

🇪🇹ሰላም እለኪ ሰላም ለአንቺ ኢትዮጲያ
የነጻነት አርማ ቀደምት ጦቢያ🇪🇹
.
.
.
.
.

የአብስራ/YeAmenLij
.
.
.
..
"ስለ ኢትዮጲያ" 🇪🇹 "ክፉ አትይ!ክፉ አትስማ!ክፉ አትናገር"
(ሊቁ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ)










🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ::


@write_event
ፈገግ !

ደሞዙ ላይ በስህተት 100 ብር ተጨምሮ ሲከፈለው ምንም ያላለው ሙላ ነስሩዲን በቀጣዩ ወር ደሞዝ ከፋዩ 100 ብር ቀንሶ ሲከፍለው ግን አስር ገፅ አቤቱታ ፅፎ አመለከተ።

ደብዳቤውን ያነበቡት የመሥሪያ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሙላ ነስሩዲንን በትዝብት እየተመለከቱ እንዲህ አሉት፣ "አሁን 100 ብር ተቀነሰብኝ ብለህ አስር ገፅ አቤቱታ ፃፍክ...ባለፈው ወር ግን በስህተት 100 ብር ሲከፈልህ አንዲት ቃል አልተነፈስክም?"

"የመጀመሪያ ስህተት ስለሆነ ነዋ..." አለ ሙላ ነስሩዲን እጆቹን ዘርግቶ...
@Write_Event
BRO ወጣት ነህ ጉልበት፣ እውቀት፣ ድፍረት፣ አላማ እና Confidence አለህ በርታ እና እራስህን ለውጥ..
ስለ ቺኳ አታስብ ሲሳካልህ ፋዘሯን ቀበሌ ሄደህ ሁለት ጃምቦ🍺🍺 መጋበዝ ነው ጠዋት ጀሮዋን እየጎተቱ በርህ ላይ ያመጡልሀል Bottle ከገዛህ ደሞ ታናሽ እህቷን ይመርቁልሀል 😜🤣🤣
@write_event
የወደፊት ልጄ እናትህን እየመረጥኩልህ ነው አይዞህ የማይጣፍጥ ጡት አትጠባም እየቀመስኩልህ ነው😜🤣
@write_event
ጡቷን በእጇ ደግፋ ፎቶ ትልክልኛለች እንዴ...

#My_Sister መቅዶኒያ እንኳን እንደዚህ አረጋዊያንን አልደገፈም🤣😂
@write_event
ወደ ክፍለ ሀገር ለበዓል እየሔድን🚌 አንዱ #ፔስታል_ፔስታል... ብሎ መኪና ውስጥ ቀውጦ ተደናግጠን ስንሰጠው...
:
የያዘውን #ጫት🌿 ሁለት ቦታ ከፍሎ አስቀመጠበት

እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ
FIAS

* በኮሚሽን የሚሰራ የማስታወቂያ ድርጅት ነው።
* ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር ይሰራል።

እና በቀን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ለተመዘገቡ አባላቶቹ ይሰጣል። ስራዎቹ እጅግ በጣም ቀላል ናቸው። ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። በዛ ቢባል 5 ዲቂቃ ቢወስዱ ነው። አንድ አባል የሚሰጠው የስራ ብዛትና የሚያገኘው ብር እንደ ደረጃው ይለያያል። ደረጃዎቹ VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4, & VIP-5 ናቸው።


* You must start with 9 when entering a phone number.

* If you have more questions, you can ask.


👇👇👇👇👇👇👇

1. VIP 1

* ይህ ደረጃ አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 4 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 6 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 24 ብር, በወር 724.00 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

2. VIP 2

* ይህ ደረጃ አባሉ 3,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 6 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 84 ብር, በወር 2,520 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

3. VIP 3

* ይህ ደረጃ አባሉ 6,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 11 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 176 ብር, በወር 5,280 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

4. VIP 4

* ይህ ደረጃ አባሉ 10,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 17 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 18 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 306 ብር, በወር 9,180 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

5. VIP 5

* ይህ ደረጃ አባሉ 30,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 38 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 25 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 950 ብር, በወር 28,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።


Register lemadreg yihenen link yixkemu👇👇👇👇


https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=xamOWZQw&t=1651737586654