ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➎


...🖊ለረጅም ጊዜ እንደማዉቀዉ የልብ ጓደኛ ነፃነት ስለተሰማኝ ለቁርስ የታዘዘዉን ምግብ በነፃነት እስከምጠግብ በላሁ። የሀምሌ የጠዋት አየር ከቅዝቃዜና ካፊያ ጋር ተዳምሮ ከአልጋ አትዉጡ አትዉጡ የሚያስብል ቢሆንም እኔ ግን ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በማደርገዉ ጉዞ ድንገት ከተዋወኩት ልጅ ጋር በነፃነት ቁርስ በላሁ!...ይገርማል! በህይወት ዘመኔ እንደዚህ ከሰዉ ጋር በፍጥነት ተግባብቼ አላዉቅም ለዛዉም ከወንዶች ጋር... ለቁርስ የተመደበዉ ሰዓት በመጠናነቁ ወደ መኪናዉ ተመለስን።
እና በትምህርት ዉጤትሽ መበላሸት ምክንያት ሀዘን ስለተሰማሽ አክስትሽ ጋር የተወሰኑ ጊዜያትን ለማሳለፍ ነዋ የአዲስ አበባ ተጓዥ የሆንሽዉ?
አዎ!አልኩት ምንም ነገር ሳልደብቅ ስለራሴ ሁሉንም ነገር በመናገሬ ሀፍረት እየተሰማኝ!
እኔ የምልህ...ቁርሱ ላይ...አልኮል ነገር ቀላቅለህበት ነበር?
እንዴት?
ስለራሴ ብዙ መናዘዜ የታወቀኝ አሁን ነዉ! አንተን እኮ ከስምህና ከጨዋታህ ዉጪ ብዙም
አላወኩህም!
ስለራሴ ነግሬሽ እንድታዉቂኝ አልፈልግም ድርጊት ከቃል ይበልጣል ድርጊቶቼን አይተሽ ታዉቂኝ ይሆናል... ''ነገም ሌላ ቀን'' ነዉ እኮ!
እና ሌላ ጊዜም እንገናኛለን እያልከኝ ነዉ?
አዲስ አበባን ከሩቅ ስትመለከቻት ነዉ ሰፊ የምትመስለዉ ቀረብ ብለሽ ከዉስጧ የምትፈልጊዉ ነገር ካለ ትጠብልሻለች... ሁለታችን ከተፈላለግንባት ደግሞ ምን ያህል እንደምትጠብልን አስቢዉ ፈገግ አልኩ!... ለቁርስ የወረደዉ ተሳፋሪ ሙሉ በሙሉ ወደ መኪናዉ ስለተመለሰ ጉዞ ተጀመረ...
ጨዋታ፣ቁምነገር፣ቀልድና ሳቅን ከአቤል እያገኘሁ የማልረሳዉንና ጥሩ ትዝታ ጥሎብኝ እንደሚያልፍ እርግጠኛ የሆንኩበትን ጉዞ እያከናወንኩ ነዉ። መኪናዉ ይሄዳል...ዛፎችና ሰዎች በፍጥነት ሽዉ እያሉ ወደ ሗላ ይቀራሉ...ተሳፋሪዎች ያወራሉ...እፎይታ ተሰምቶኝ ጉዞዬን ቀጥያለሁ...

ይቀጥላል...

📒📕📘📙📗

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➏



...🖊መነሻዉ ከጅማ ከተማ ሆኖ ከንጋቱ 11:30 የተጀመረዉ ጉዞ ከቀኑ 8:00 አካባቢ መድረሻዉን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አድርጎ በሰላም ተጠናቀቀ። ከመኪናዉ እንደወረድኩ ለአክስቴ ልጅ ለእየሩስ ደወልኩላት መምጣቴ አስቀድሞ ስለተነገራት ኮንትራት ታክሲ ይዛ መስቀል አደባባይ አካባቢ እየጠበቀችኝ እንደሆነ ነገረችኝ። እኔ እንዲቸገር ባልፈልግም አቤል ግን የያዝኩትን ሻንጣ ተሸክሞ እየሩስ የቆመችበት ቦታ ድረስ አደረሰኝ። አቤልን ከእየሩስ ጋር አስተዋዉቄዉ እንዲደዉልልኝ የስልክ ቁጥሬን ከሰጠሁት በሗላ ቻዉ ብሎ መሰናበቱ ከበደኝ! በዝምታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ትኩር ብዬ ስመለከተዉ ሁኔታዬ ከእኔ አልፎ እየሩስንም ስለገረማት
እዚሁ የማደር ሀሳብ አለሽ እንዴ? አለችኝ!
ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰዉ ድንገት ከገባሁበት ዝምታ ብንን ብዬ ነቃሁ።
ስለ ሁለም ነገር አመሰግናለሁ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር! መልካም ቀን ይሁንልህ!
አሜን መልካም ቀን ይሁንልን!
አቤል ያልገባኝን ስሜት አስታቅፎኝ እኔና እየሩስን ተሰናብቶን ሄደ! ከእየሩስ ጋር በቀጥታ ሳሪስ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድን ከአቤል ጋር እንዴት እንደተዋወቅንና በአንድ ቀን የተሰማኝን ግራ የሚያጋባ ስሜት አጫወትኳት። እየሩስ የእናቴ እህት ልጅ ብቻ ሳትሆን የእድሜ እኩያ ጓደኛዬ፤የልቤን ሚስጥር ተጋሪ እህቴም ጭምር ነች።
አንዳንዴ ብዙ ግምት ሰጥተን ከጠበቅነዉ ነገር ይልቅ ድንገት የምናገኘዉ ደስታን ይሰጠናል አለችኝ!
እንዴት?
ልክ እንደ ፈተና ዉጤትሽና እንደ አቤል ማለት ነዋ!
እየሩስ የተናገረችዉ ነገር ሙሉ በሙሉ እዉነት ቢሆንም ደህና የረሳሁት ሀዘን ስለቀሰቀሰችብኝ
ከዚህ በሗላ ስለ ትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ማሰብ አልፈልግም የእሱን ሀዘን ሽሽት ነዉ እዚህ የመጣሁት !
እንጂ አንቺ ናፍቀሽኝ አይደለም እያልሽኝ ነዉ?
ከምልሽ በላይ ነዉ የናፈቅሽኝ የእኔ ዉድ እህት ብዬ እቅፍ አደረኳት።
በሰላም አዲስ አበባ መድረሴን ለማሳወቅ ወደ አባቴ ስልክ ብደዉልም ስልኩ አልሰራም አለኝ ምናልባት ኔትወርክ ይሆናል ብዬ ወደ እናቴ ደወልኩ ከተደጋጋሚ ጥሪ በሗላ ስልኳን አነሳች!
ሄሎ...እማ...አዲስ አበባ ደርሻለሁ...ከእየሩስ ጋር ወደ ቤት እየሄድን ነዉ!...ሄሎ..
...እሺ!...የእናቴ ድምፅ በለቅሶ የታጀበ ነበር!
እማ...ምንድነዉ...የተፈጠረ ነገር አለ?
ሄዷል! አለችኝ!
ማነዉ የሄደዉ?
አ.ባ.ት.ሽ ... ላይመለስ... ተሰናብቶን...ሄዷል!
ስልኬ ከእጄ ላይ ሸርተት ብሎ ወደቀ...

ይቀጥላል...


📚📚

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➐



...🖊እዉነትም ሀዘን ከእኔ ፍቅር ይዞታል! አልያም ደግሞ በእኔ ይቀናብኛል ማለት ነዉ! ትንሽ ፈገግ ስል ደስታዬን የሚያጠፋ ሳቄን የሚገድል ችግር መፍጠሩን ተያይዞታል። አባቴ ሰላም ሁኑ የሚል መልዕክት በቁራጭ ወረቀት ላይ አስፍሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን እናቴ ነገረችኝ! ያለችበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ዛሬን አድሬ ነገ እንደምመጣ ብነግራትም አሷ ግን መምጣቴን አጥብቃ ስለተቃወመች የተወሰኑ ቀናትን አዲስ አበባ ለመቆየት ወሰንኩ።
አድካሚ ህይወት...አድካሚ መንገድ...አድካሚ ቀን!... የእየሩስ ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
ምናልባት በስራ ምክንያት የሄደበት ጉዳይ ሊያቆየዉ ስለሚችል ሊያስጨንቃችሁ ስላልፈለገ ይሆናል መልዕክት የተወላችሁ!አየሩስ ነበረች!
መልስ ልሰጣት አልቻልኩም! ምን አይነት ምላሽ ልሰጣትስ እችላለሁ? በወቅቱ አልነበርኩ ሰዉ ስላልነበረበት ሁኔታ እንዴት በእርግጠኝነት መናገር ይቻለዋል?
ደ.ክ.ሞ.ኛ.ል! በህይወቴ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ችግሮች አድክመዉኛል! አልኳት! እንባዬ ያለ ከልካይ ይወርድ ስለነበር ሁኔታዬ እየሩስን አሳዘናት የተወሰነ እረፍት እንዳደርግ ከአልጋ ዉስጥ አስገብታኝ
አንድ ሁለት ቀናትን እዚህ እናሳልፍና ወደ ጅማ አብረን እንሄዳለን! አሁን ግን ተረጋግተሽ እረፍት ማድረግ ይኖርብሻል! ብላ ተሰናብታኝ ወጣች!
እኔ ቀጥ ብዬ መቆም ስፈልግ ህይወት ታንገዳግደኛለች! ይነጋል ሰዉም አብሮ ከንጋቱ ጋር ይነቃል፤ይመሻል ሰዉም አብሮ ከምሽቱ ጋር ይተኛል!... ህይወት በድግግሞሿ ዉስጥ የሰዉን ልጅ አቅፋ ትሽከረከራለች... የሰዉ ልጅም በህይወት አዙሪት ዉስጥ ይዞራል! ድካም...ለቅሶ...ሀዘን...ተደራርበዉ ለእንቅፍ አሳልፈዉ ሰጡኝ... ሽልብ አደረገኝ...

ይቀጥላል...



📚

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➑



...🖊መሸትሸት ሲል ከእንቅልፌ ነቃሁ እየሩስ ከአጠገቤ ጋደም ብላለች። ስልኬ ላይ አምስት ሚስኮል አገኘሁ ሁለቱ የእናቴ ሲሆን የተቀረዉ አዲስ ቁጥር ነበር በቀጥታ ወደ እናቴ ደዉዬ ስለ አባቴ አዲስ ዜና ካለ ጠየኳት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ በሀዘን ተዉጣ ነገረችኝ እኔም እሷን ትቼ አዲስ አበባ ብዙ መቀመጥ እንደማልችል እንደዉም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ወደ ጅማ እንደምመለስ አሳምኛት ስልኩን ዘጋሁት።
...ምሳ እንኳን አልበላሽም አሁን ተነሺና እራት እንብላ
ይቅርብኝ አራበኝም! ...ይልቅ ነገን እዚህ አሳልፌ ከነገ ወዲያ መመለስ ይኖርብኛል አብረን እንሄዳለን?
እየሩስ ሀሳቤን አልተቃወመችኝም። ስልኬ ላይ ወዳገኘሁት አዲስ ቁጥር ደወልኩ አቤል ነበር ድምፁን ስስማ ልቤ ድንግጥ አለ! ልክ እንደተማረከ ወታደር ለምን የልቤን እንደምናዘዝለት ባላዉቅም አዲስ አበባ ከደረስኩ በሗላ የገጠመኝን ሁሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኩት!
ከቻልሽ ነገ ላግኝሽ እኔ ጋር የረሳሽዉ እቃ አለ አለኝ!
ግራ ገባኝ እስከማስታዉሰዉ ድረስ እሱ ጋር የረሳሁት ምንም ነገር የለም ቢሆንም ነገ ከእየሩስ ጋር ትኬት ለመቁረጥ ወደ መስቀል አደባባይ እንደምንመጣና በዛዉ ላገኘዉ እንደምችል ነገርኩት የሚሰራበት ቦታ ቦሌ አካባቢ እንደሆነ ነግርኝ እሱ ያለበት ቦታ ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ። እየሩስ እራት እንድበላ ብታስጨንቀኝም ፍቃደኛ ልሆንላት ስላልቻልኩ እሷ ጋር ያለዉን ለእኔ እኔ ጋር ያለዉን ደግሞ ለእሷ እያጫወትኳት እንቅልፍ ወሰደን... እንደሌላዉ የሀምሌ ቀን ዝናብ ያስጨነቀዉ ሳይሆን ቀለል ያለ ብሩህ ጠዋት ነበር ከእየሩስ ጋር አርፍደን ተነሳን ጥሩ ቁርስ...የሚገርም ምሳ...ቤተሰባዊ መስተንግዶ ስለተደረገልኝ በትንሹም ቢሆን ሀዘኔን ቀለል አደረገዉ።
ወደ ጅማ የምንሄድበትን የጉዞ ትኬት አክስቴ ከምትደክሙ ብላ ሰዉ አስልካ አስቆረጠችልን። ሲኒማ ፊልም ልናይ ነዉ በሚል ሰበብ ከእየሩስ ጋር 11:30 ላይ ተያይዘን ወጣን! ለአቤል ደዉዬ እየመጣሁ እንደሆነ ስነግረዉ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ አሳወቀኝ ስደርስ እንደምደዉል ነገርኩት...
እየሩስ ምናልባት ብቻሽን ሊያገኝሽ አስቦ ይሆናል እኔ እዛዉ አካባቢ ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ልቆይና ስትጨርሺ አብረን እንመለሳለን አይሻልም? አለችኝ!
ልቤን ፍርሀት... ፍርሀት እያለዉ እሺ አልኳት...

ይቀጥላል...



📚

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔


ክፍል_➒

...🖊አቤል የሚሰራበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫና መጠገኛ የሆነዉን ሱቅ አስጎበኘኝ ሱቁ የታላቅ ወንድሙ እንደሆነ ነገር ግን ከጅማ ድረስ እየመጣ ለመቆጣጠር ስለማይመቸዉ እሱ በሀላፊነት እንደሚያስተዳድርለት ነገረኝ።
ሱቁ አነስ ያለ ነገር ግን በርካታና ጥራት ያላቸዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለዓይን በሚማርክ ሁኔታ ተደርድረዉበታል የሱቁን ጉብኝት እንደጨረስን እራት እንድንበላ ጠየቀኝ ብዙ ማምሸት እንደማልችልና ነገ ተጓዥ ስለሆንኩ በጊዜ ገብቼ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ አስረዳሁት
ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ! ተረጋግቼ ላወራሽ የምፈልገዉ ነገር ስላለ ነዉ?
ሰዉን ቶሎ ከሚያምኑት ወገን ባልመደብም ብቻ አቤል ምን አይነት አስማት እንዳለዉ አልገባኝም ልቃወመዉ አልቻልኩም። ከሱቁ ወጥተን እዛዉ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ ተለቅ ያለ ሆቴል ገባን! ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮ ስለነበር በተለያዩ አይነት ከለር ብልጭ ድርግም የሚሉት መብራቶች ለስለስ ብሎ ከሚንቆረቆረዉ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ጋር ተዳምረዉ ለሆቴሉ ልዩ ዉበት አጎናፅፈዉታል። እኔና አቤልን ለተመለከተን በፍቅር ረጅም ጊዜ ያሳለፉ ጥንዶች እንጂ በጣት የሚቆጠር የትዉዉቅ ቀናቶች ያለን አንመስልም። በእኔ ምርጫ ብሎ ከታዘዘዉ የበግ ጥብስ ላይ ደጋግሞ አጎረሰኝ ለሴት ልጅ ያለዉ አክብሮትና ጨዋታ አዋቂነት አቤልን ያለ ምንም ፍርሀት ግልፅ ሆኜ በነፃነት እንዳወራዉ እያደረጉኝ ነዉ! የመጠጥ ተጠቃሚ አለመሆኑን ነገር ግን ይህ ምሽት ያለ ወይን አይደምቅም ብሎ ወይን ታዘዘ! በሁለታችንም ብርጭቆ ልዩ ስሜትን በሚሰጥ እርጋታ ወይኑን ቀዳዉ
እንግዲህ እኔ ጋር የረሳሽዉ...ንግግሩን እንደጀመረ ስልኬ ጠራ እየሩስ ነበረች አቤልን ይቅርታ ጠይቄ ላናግራት ወደ መፀዳጃ ሄድኩ ከ30 ደቂቃ በሗላ እንደምጨርስ ነግሬያት ተመለስኩ
ለጥሩ ምሽታችንና እኔ ጋር ለረሳሽዉ ነገር ፅዋችንን እናንሳ! እሱ ጋር ምን ልረሳ እችላለሁ? ዉስጤ የበለጠ ለማወቅ ስለጓጓ ብርጭቆዉን አንስቼ ተጎነጨሁ አቤል ምን እንደሚያወራ ባይገባኝም የሆነ ነገር ያወራልኛል ምስሎች ብዥዥ...ብዥዥ... እያሉብኝና የእንቅልፍ ስሜት ሲጫጫነኝ ይታወቀኛል
...ጠዋት እራሴን ከማላዉቀዉ ክፍል አልጋ ዉስጥ አገኘሁት ፊት ለፊቴ ካለዉ ወንበር ላይ አቤል ሲጋራ እያጨሰ ነበር መንቃቴን ሲመለከት ከት ብሎ ሳቀብኝ
ወፏ ወደ ወጥመዷ ገብታለች! አለኝ የማየዉ የምሰማዉ ህልም እንጂ እዉነት አልመስልሽ አለኝ
የት ነኝ? አልኩት
ሲኦል

ይቀጥላል...



https://t.me/Write_Event
" የወንድ ልጅ ህይወት ባለ አራት ተቃራኒ ግድግዳዎች ነው ። "
" ግድግዳዎቹም እናት ፣ ሚስት ፣ ሴት ልጅና እህት ናቸው ። ያደለው ወይም ያወቀበት ወንድ እነዚህን ሳጋ ፣ ማገር ፣ ቱሻ ፣ ልጥፍ ፣ ልስን ....... የማይሉ ግድግዳዎች ላይ ጣሪያ መክደን ብቻ ባለ ጎጆ ያደርገዋል ።


" እንግዲህ ወንድ ልጅ እዚህ ጎጆ ውስጥ አራቱን ግድግዳዎች የሚያቻችል የአማካኝ ተክል ምሰሶ እንጂ ነዋሪ አይደለም ። እናት ወደ ዘላለማዊ ልጅነት ትጎትተዋለች። ወንድ ልጅ በጉተታው አማካይ ሥፍራን መሳት የለበትም ። ሚስት ደግሞ የተዋጣለት ባል እንዲሆን ወደ እራሷ መሳቧ አይቀርም ። አሁንም እዛው ላይ ሆኖ የሚስቱ አሳሳብ ከመጠን እንዳያልፍ መቋቋም ነው ። ሴት ልጅና እህትም በየፊናቸው ወደ አባትነትና ወንድምነት ይስባሉ " ሐይ " ሳይባሉ ለአሳሳባቸው በልዝብ መልስ መስጠት ተገቢ ነው ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አለማየው ገላጋይ ( ኩርቢቷ )

ገፅ 102 - 03
"እውቀት ማለት ቦንብ መስራት መቻል ሲሆን ጥበብ ማለት ደግሞ ቦንብን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው"
ሰዎች እያወሳሰብዋት እንጂ ህይወት ቀላል ናት...ሰዎች በጨለማ ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሻማ ቢለኩሱ ለጨለማ ችግራቸው በቀላሉ መፍትሄ ያገኛሉ።

ኮንፊሺየስ
የደራሲ ቤት ፤ ገነት ቅብ ሲኦል ነው።


የደራሲነት እውነት ከሆድ ና ከጭንቅላት ፣ ከጉስቁልናና ከድሎት ፈንቅ አይል ይሁን ? ለሎች አማራጮች ፈለግን። አሁንም ዞሮ ፀጋዬ ገብረመድህን አገኘን ። ፀጋዬ "ሕሊና" መፅሔት ላይ የደራሲን እውነት ከባቢያዊ አድርጎት አገኘን ። እንድህ ይላል ።

"ህዘብ መካከል ሆነህ ነው ስለ ህዝቡ የምትፅፈው ፣ የሕዝቡ ሙቀት ካልሞቀህ ፣ በሕዝቡ ህዝባዊነት ውስጥ ካልታቀፍክ የሱን ህይወት አትተረጉምም። ስለዚህ ብዙ የብዕር ሰዎች ፣ እንደ ምሳሌ የአሁኑን ትልቁ የሩሲያ ደራሲ ሶልዘንሂትሲንን እንመልከት ፣ የታል የምፅፈው ? መሞት መጀመር ማለት እኮ ነው ከሀገር ሕዝቦች አካል ውጭ ከተለየ በኋላ ፣ የሕዝብን ሳቁንና ብሶቱን ለመካፈል ከማትችልበት ርቀት ትዝታህ ሁሉ ይተንብሀል፣ እሰው በር ላይ ተቀምጠህ ምን ትፈጥራለህ? አጥንቴ የህዝቦቼን ሙቀት ተመግቦ ያደገ ስለሆነ አፍሪካዊ ሙቀቴን እንዳጣ አልፈልግም ፣ በረዶም አልወድ ፣አለም ካደነቀው ጠንካራው የኢትዮጵያ ባህል መለየትም ለእኔ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። እርሱን ደካማ አድርጎ የማቅረብ ቅጥረኝነት ነው። ያኔም ብዕሬን ካገር ለማራቅ የተወጠነብኝ ።ደስቶየቭስኪ ካገሩ ሲወጣ ነው የብዕሩ ሞት የተቃረበው ።

ለፀጋዬ ህዝብ ባህር ነው። ደራሲ ደግሞ የባህር ውስጥ ነዋሪ ፍጡር፤ ያለ ባህር የባህር ነዋሪ ምን መጠጊያ አለው? ይሄን ይዘን ወደ ፀጋዬ ገብረመድህን ህይወት ና ሥራ ጎራ ካልን በግብርም ተተርጉሞ እናገኘዋለን ። የፈራው እና የጠላው የበረዶ አገር፣ ኑሮውን አበድኖበት ይማረር ነበር። አሜሪካ ብሮንክስ ኒውዮርክ ተቀምጦ ልቡና መንፈሱ ግን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ላይ ይንሳፈፍ ነበር ። ሥራው ግን እዚህ እንደነበረበት ዘመን አልሰላለትም። ንግግሩ በተሃ ፣ ግጥሙ ዘገባ ሆኖ ነበር ።

ዛሬ የዶላሩ ብድር ባፋቸው ገብቶ ልጓሙ
ይኸው በአዲስ ግዳጅ ፍቅር፤ወንድማማቾች ተሳሳሙ
የሚል ዜና አስታራቂዎች፣ በአለም ነጋሪት ቢያሰሙ
እኔም ቴሌግራፍ ደብዳቤ ፣ ለወንድሞች ለማቀበል...

አሁን ይሄ ምኑ የፀጋዬ ግጥም ይመስላል ? በእርግጥም እንዳለው ከሀገር መውጣቱ ሥራውን ነጥቆታል ። ይሁንና ጉዳዩ የሁሉም ደራሲዎች እውነት አይደለም ። ለምሳሌ አዳም ረታ፣የፀጋዬ ተቃራኒ ደራሲነቱን እንደሚያሰላው ይናገራል ። ለአዳም ሀገር እንደ ተራራ ነች። ካልራቋት እራሷ ላይ ሆነው ምኗም የማይታይ "ተራራኮ ቁልጭ ብሎ የሚታይህ ስትርቅ ነው" ይላላ።

ይሄን ጊዜ ነው ኦ! የደራሲ እውነት ከወዴት ነሽ? ማለት

ገፅ 166-167
መፅሐፍ -መለያየት ሞት ነው
ደራሲ-አለማየሁ ገላጋይ
​​​​💔የባከነች_ነብስ



ክፍል_➓

...🖊ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር! የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል! አለኝ
የምን ቀብር?...

ይቀጥላል...

Share ማድረግ አትርሱ💛🙏 !

https://t.me/Write_Event
ሕይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት
ደስታም - ሀዘንም


ክፉ ቀን ጥሩ ነው ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል , ክፉ ቀን አንደ ለሊት ጨለማ ነው የሌሊቱ ጨለማ ለእንቅልፍ አንደሚጠቅም ሁሉ የቀን ብርሀንም ለስራ ይበጃል ።

ለህይወት እንቅልፍም ስራም የግድ አስፈላጊዎች ናቸው . . . .


ስለዚህም ይፈራረቃሉ ። ትዕግስት መከራን እርግዛ ትወልዳለች

እንደ ሳቀ የሚቀረው ስቀው የተነሱት ፎቶ ብቻ ነው፡፡

' አዳም - ረታ '


ሼር!

https://t.me/Write_Event
#"በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደውሀ ቅርፅህን አትቀያይር "


በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ከሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው ። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሃል, አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ሊያፌዙብህ ይችላሉ


ምናለፋህ በዓለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም ልትጠላም አትችልም ። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን ።
አንድ ነገር ልንገራችሁ በህይወታችሁ ውስጥ ማንንም አትውቀስ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጧችሁዋል, መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኗችሁዋል ።

ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኗችሁዋል ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኗችሁዋል !".

ስብሐት

ሼር!!!

https://t.me/Write_Event
(ኤፍሬም ስዩም)

:- እውነት ወደ ኋላ

ገንዘብ ካለው ጋራ
ፍቅር አይኖርም ወይ ብለሽ ጠይቀሻል!?
እኔ ያንቺን እንጂ
የሌላን አላልኩም እጅግ ተሳስተሻል
አይኖርም አላልኩም...አይጠፋም ይኖራል
ይኖራል
ይኖራል
ግን?...
ከባለሐብት ጋር
ተፋቅራ 'ምናያት የቷም አይነት እንስት...
'ምን ' ትሁንም ' ምንም '
የሕይወት ታሪኳን ወደኋላ ሄደን ....ጥቂት ብንገመግም
አንድ ቡና ለሁለት ....
አብራ የጠጣችው አንድ አፍቃሪ አታጣም ።

#ኤፍሬም ስዩም

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔



ክፍል_➊➊

...🖊ከሆስፒታል አልጋ ላይ እራሴን አገኘሁት። እናቴ ላይ ጨክኖ አፈር ማልበሱ ክፉኛ ሰቀቀን ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ድካም፣ሀዘን፣ብስጭትና ረሀብ ተደማምረዉ እራሴን እንድስት ስላደረጉኝ እጅግ የምሳሳላት እናቴን እንደ ወጉ አልቅሼ መቅበር ተስኖኝ በቀብሯ ማግስት እራሴን ስቼ ለህክምና ከገባሁበት ሆስፒታል ዉስጥ ነቃሁ። መጀመሪያ ላይ የአባቴ መጥፋት የሄደበት የገባበት አለመታወቁ ክፉኛ ያስጨንቃት ነበር ምናልባት ሰዎች አደጋ አድርሰዉበት እንዳይሆን ብላም ትሰጋ ነበር እዉነታዉ ግን አባቴ በእድሜ እጅግ ከምታንሰዉ እንደዉም እንደሰዎች አባባል ከእኔ እኩያ ከምትሆን ሴት ፍቅር ይዞት ቤት ንብረቱን በትኖ ከእሷ ጋር መኮበለሉን ስትሰማ ድንጋጤ ከነበረባት ግፊት ጋር ተዳምሮ ለሞት ዳረጋት።አሁን በህይወት ለመቆየት ምን ምክንያት ይኖረኛል? ህይወት እራሷ በሀዘኔ ዳንኪራ ልትመታ!፤በለቅሶዬ ጭቃ አቡክታ ቤቷን ልትሰራ!፤የእኔን ዉጣ ዉረድ እንደ ኮሜዲ ፊልም ልትኮሞኩም ስቃይና ሀዘንን ለግሳ ለዚህች ጠማማ ዓለም ካስረከበችኝ በሗላ ጭላጭ ተስፋን እንደማትሰጠኝ ልቦናዬ ከተረዳ ሰነባብቷል። እየሩስ ከአጠገቤ ነበረች መንቃቴን ስትመለከት በፍጥነት ሄዳ ዶክተሯን ጠርታ መጣች
እንዴት ነሽ? ምን አየተሰማሽ ነዉ?
ተስፋ መቁረጥና የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት መጓጓት! ነዉ የሚሰማኝ ብዬ ለዶክተሯ ብነግራት ምነኛ ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህንን ለመረዳት እኔ የቆምኩበት ላይ ልትቆም እኔ የሚሰማኝ ሊሰማት እንደማይችል ልቦናዬ ስላወቀዉ
ደህና ነኝ! አልኳት
በእጆቿ ግንባሬን ከነካካችና የሙቀት መጠኔን ከለካች በሗላ
አሁን ደህና ነሽ ነገር ግን ሰዉነትሽ ስለተጎዳ ፈሳሽ ነገሮች በብዛት መዉሰድ ይጠበቅብሻል የማዝልሽንም መድሀኒት በአግባቡ መዉሰድ ይኖርብሻል! አለችኝ! ከእየሩስ ጋር የታዘዘልኝን መድሀኒት ተቀብዬ ወደ ቤት አመራን። አክስቴ ባለቤቷና ከአዲስ አበባ አብረዉን የመጡት ሰዎች ሀዘንተኞቹን ምሳ ሲመግቡ ደረስን! አብዛኞቹ እኔን ሲመለከቱ በሀዘን ደረታቸዉን መምታት ጀመሩ እየሩስ በፍጥነት ወደ መኝታ ክፍሌ ይዛኝ ገባች... መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ባማረ ፍሬም የተሰቀለዉን የአባቴን ፎቶግራፍ ስመለከት የንዴትና የበቀል ስሜት በደም ስሬ ዉስጥ ይሯሯጥ ጀመር...

ይቀጥላል...

ሼር ማድረግ አይርሱ !

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔



ክፍል_➊2

...🖊እንግዳ ከሌለበት ሱቅ ዉስጥ አቤል ለብቻዉን ቁጭ ብሎ አገኘሁት። ገና ሲያየኝ ፊቱ ላይ የሚታየዉ ንቀትና ትዕቢት የንዴቴን መጠን በእጥፍ ቢጨምረዉም አራሴን አረጋግቼ በእናቴ ሞት ምክንያት ወደ ጅማ ሄጄ እንደነበረ አሁን ሙሉ ገንዘቡን ልከፍለዉ እንደምችልና በምትኩ እሱ ጋር ያለኝን ፎቶና ቪዲዮ እንዲያጠፋዉ ጠየኩት። እየሩስ ወደ ሱቅ ዉስጥ መግባት ስላልፈለገች ከዉጭ ቆማ እኔና አቤልን የምናደርገዉን እንቅስቃሴ ትከታተላለች።

አሁን ፋይሎቹን አልያዝኳቸዉም ነገ እደዉልልሽና የትና እንዴት ተገናኝተን ገንዘቡንና ፍይሉን እንደምንለዋወጥ አሳዉቅሻለሁ! አለኝ

ግን...አንተ...ሙሉ በሙሉ ፋይሎቹን እንደምትሰጠኝና አንተ ጋር ኮፒ እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለኝ?

ማረጋገጫ አይኖረኝም! አንቺ ግን ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እኔን ማመን ብቻ ነዉ!
ዉስጤ ያለዉ የጥላቻና የበቀል ስሜት አንጀቴ ሲያላዉሰዉ ይታወቀኛል
ስለየትኛዉ እምነትና መታመን ነዉ የምታወራዉ ከሀዲ!! ብለዉ ዉስጤ ያለዉ ህመም በትንሹም ቢሆን እርጋታ እንደሚያገኝ ባዉቅም ቸኩዬ ነገሮችን ማበላሸት ስላልፈለኩ

እሺ! አልኩት!

ምንም አይነት ብልጠት ወይም ደግሞ ተንኮል አስባለሁ ብትዪ አሁን ካለሽበት ሁኔታ የባሰ መቀመቅ ዉስጥ እንደምከትሽ አትርሺ!
በእናቴ ሞት የተሰማኝ ሀዘን ላይ ሲያንጓጥጥ መመልከቱ ከሞትም በላይ ሞት ቢሆንም ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ትዕግስት ስለነበረ የሚናገራቸዉን ንግግሮች እየመረረኝም ቢሆን መዋጥ ግዴታ ሆነብኝ። በግምት በእድሜ አቻ ልትሆነኝ የምትችል ጠቆር ብላ የደስ ደስ ያላት ወጣት ሴት ወደ ሱቁ ገብታ በፓስታ የታሸገ ነገር አቀበለችዉ አቤል ደግሞ በምትኩ የሚሞሪ ካርድ ሲሰጣት ተመለከትኩ! ፊቷ ላይ ይታይ የነበረዉ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እሷም እንደኔ የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆኗ ምስክር ነበር። እስከመች? አልኩኝ በዉስጤ! ለሴት ልጅ ህመምና ሀዘን እየሰጠ በምትኩ ገንዘብ እየተቀበለ የሚኖረዉ እስከመች ነዉ?

ነገ ከሰአት 8:00 ሰዓት ላይ የምትችል ከሆነ እዚሁ ሱቅ መጥቼ ገንዘቡን ላቀብልህና ፋይሎቹን ስጠኝ
እደዉልልሻለሁ! ብሎ አሰናበተኝ! ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን
አክስቴ ፈቃደኛ ባትሆንም በብዙ ልመናና ለቅሶ ከጅማ ሽጬ ከመጣሁት ገንዘብ ላይ የተወሰነዉ በእናቴ ስም የሚጠራና በአክስቴ ባለቤትነት የሚተዳደር ሆቴል አዲስ አበባ ዉስጥ እንድትከፍት አስማምቼያት የተቀረዉን ገንዘብ የእናቴ የዘወትር ህልም የሆነዉና ሳትፈፅመዉ ሞት የቀደማት የእርዳታ ድርጅት መክፈት በእኔ አቅም የማይቻል ስለሆነዉ ገንዘቡን ለእርዳታ ድርጅት ለመስጠት መወሰኔን ገለፅኩላት!
ስለ እራስሽም የነገ ህይወት ማሰብ ይኖርብሻል?

አስቤያለዉ አክስቴ አሁን ለእኔ ገንዘብ ሳይሆን ማረፊያ ነዉ የሚያስፈልገኝ የማይከፈልበት ማረፊያ!

አልገባኝም!

አክስቴ እንደማይገባት አዉቃለሁ ሊገባትም አይችልም እኔ ግን ነግቶ ነገ ላይ ለመቆም ልቤ ቆሟል ሁሉም ነገር ፍፃሜዉን ሊያገኝ አንድ ምሽት ብቻ ፊት ለፊቴ ተደንቅሯል እንዳረጀ ዉሻ ሂድ ብሎ ይህንን ምሽት በካልቾ መቶ የሚያባርርልኝ ማን ይሆን? ማንም!
አይገባሽም አክስቴ ተይዉ!.

🕹የመጨረሻው ክፍል በቀጣይ ይለቀቃል ።
ክቡራን ቤተሰቦች በኛ እና በታዋቂ ደራሲያን የተፃፉ አዲስ አስተማሪ እና አጓጊ ስነ ፁሁፎች አሉን ።
ያንን አንድ ላይ ለመጋራት ቤተሰብ ያስፈልጋል ስለዚህ ለጓደኞቻቹ እና ወደ ተለያዩ ግሩፕ ሼር ማድረግ እንዳትረሱ አንድ ላይ እናንብብ 🙏

ይሄንን ስለምታደርጉ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏

https://t.me/Write_Event
​​.........አደዋ ዝም ብሎ ድል አይደለም💚
አድዋ የስነ-ልቦና ከፍታ ነው ;💛
አድዋ የእልህ ጥግ ነው ;❤️
አድዋ የነፃነት ዋጋ መለኪያ ነው ;💚
አድዋ የአገር ፍቅር ጫፍ ነው ; 💛
አድዋ የባርነት የሞት ጉድጓድ ነው ;💚
አድዋ ከመለያየታችን የለየን ድንበር ነው ;💛
አድዋ የእብሪተኞች ጥሩር ሀፍረት ነው ;❤️
አድዋ የሀበሻ የሞራል ከፍታ ነው ;💚
አድዋ የጥቁሮች አንገት ትራስ ሆኖ ቀና ያደረገ ነው ;💛
አድዋ የምኒልክ የመሪነት ጥበብ💚
የራስ መኮንን ራስነት ፣ የባልቻ ወኔ ፣ ያሉላ የድል ጮራ ❤️
ያያቶቼ የመንፈስ ከፍታ.ስጦታ ነው ።💛
አድዋ ከድል ባሻገር ሚሊዮን ርቀቶችን ከፍ ብሎ የተሰቀለው ለዚህ ነው።
💚💛❤️

💚💛
💚💛❤️

💚💛
@write_event
​​💔የባከነች_ነብስ💔

♥️
♥️

🛎የመጨረሻው ክፍል🛎

...🖊 <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

❇️//ተፈፀመ//❇️

🔮የባለታሪኳ መልዕክት

👉 የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!


💈ምስጋና
👉ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ
!



,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

t.me/write_event
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​ድሮ አስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለን ነፍሰ ቀጭኑ ኬሚስትሪ መምህራችን እንዲህ ሲሉ ጠየቁን ።
ውሀ ከምን እና ከምን ንጥረ ነገሮች ነው የተፈጠረው ?🙂
ብዙ ተማሪዎች ይህችን ቀላል ጥያቄ ለመመለስ ተቅለበለብን ። መምህሩ ግን ከሁሉም ተማሪ ይልቅ ትኩረታቸውን ስንሻው ላይ አድርገው እንዲመልስ አስገደዱት ።
ስንሻው ከእንቅልፉ የተነሳ ይመስል አይኑን አሻሽቶ ትንሽ ቆየና መምህሩ ጥያቄውን እንዲደግሙለት ጠየቃቸው። /በነገራችን ላይ የስንሻው አባት ልጃቸው ትምህርት እንዳይገባው ተደግሞበታል ብለው ስለሚያስቡ እሱን ይዘው ያልተንከራተቱበት ፀበል አልነበረም ። ኋላ ላይ ቢታክታቸው ጊዜ እርግፍ አድርገው ተውት ! እርሱም ትምህርት አይንህን ላፈር ብሎ ማንበብ እና ማጥናቱን እርግፍ አድርጎ ተወው /
"እኛ የምን ጠጣው ውሀ ከምንና ከምን ውህደት ተፈጠረ ? " ብለው ጥያቄውን ደገሙለት ።
ውሀ ልማት እና ቀበሌ ተዋህደው በገጠሙት የቧንቧ መስመር ነው የተፈጠረው ! ብሎ ሲመልስ ያልደነገጠ ተማሪ አልነበረም ። ሁላችንም እያሾፈ ነው ብለን በትኩረት አየነው ።
እሱ እቴ !
ልቡ ደጭ እንኳ አላለም !
“ስ ! ውይ ይቅርታ” አለን መልሶ .... በቃ ኦክሲጂንና ሀይድሮጂን ታውሰውት ነው ማለት ነው ብለን ማስተካከያውን በጉጉት መጠባበቅ ያዝን !
“ውሀ ልማት እና ሰሜን ሸዋ ዞን በመተባበር ነው “ ብሎ እርፍ አለው ።
ነፍሰ ቀጭኑ መምህራችን በንዴት ተነፋፍተው ነብር አከሉ ! አለ አይደል የቤት ውስጥ ድመት ስትቆጣ እንዴት ነው ኩፍ የምትለው ?
መምህራችን ኩፍ አሉ ።
በስመአብ !
አስተማሪ ሲናደድ ለካ እንደዚህ ያስፈራል ?
ከአስተማሪም ሁሉ ደግሞ ኬሚስትሪ አስተማሪ ሲናደድ በጣም ያስፈራል ። የሆነ ሰልፈሪክ አሲድ ከላብራቶሪ አንስተው ፊቱ ላይ የሚከለብሱበት ሁሉ መሰለን ።
“ተነስ !”
ስንሻው ተነሳ ።
“እነ ሚካኤል ፣ እነ እዮብ እነ አቤል ኢንጅነር ወይ ዶክተር ሲሆኑ ሻንጣ ተሸካሚያቸው እንደምትሆን አልጠራጠርም “ ብለው ሞራሉ ላይ ቀዝቃዛ ውሀቸውን ከለበሱበት ።
እንደፈራነው ከወራት በኋላ ስንሻው ማትሪክን ወደቀ ። እኛ ፈተናውን በጥሰን አለፍን ።
እኛ አስራ ሁለተኛ ክፍል አልፈን ለዩንቨርሲቲ ስንዘጋጅ ስንሻው የሆነ ትምህርት እንደከረሜላ አሽጎ የሚሸጥ ኮሌጅ ዲፕሎማ መማር እንደጀመረ ሰማን ።
ግቢ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስንሆን ስንሻው ቀበሌ ስራ አጊንቶ መግባቱ ተነገረን ። ያኔ በሱ ሙድ ያልያዘ አልነበረም ።
እንደውም አንድ ቀን በድሉ የሚባል ቸካይ የነበረ ተማሪ ወደኔ ጠጋ ብሎ "ስንሻው በዚህ ድድብናው ቀበሌ ስራ ማግኘቱም ተመስገን ነው ብሎ ገለፈጠ ። "ስንሻው እኮ ቀን ስራ እንኳ ይበዛበታል ። እንደ ህንዶች ሰባቴ ቢፈጠር ሰባት ጊዜም ትምህርት አይገባውም" አለኝ ቀጥሎ ።
ስንመረቅ ግን የነፍሰ ቀጭኑ ሰውዬ እርግማን ለስንሻው ምርቃት ሆኖ እርፍ አለው ።
የከተማችን አስተዳደር ተመራቂ ተማሪዎች ተደራጅታችሁ ኮብልስቶን አንጥፉ ምናምን ብሎ በስብሰባ ሰበብ ሲጀናጀነን ስንሻው ተከብሮ የከተማችን ከንቲባ ሆኖ ነበር ።
ጭራሽ እዛ አመዳችን ቡን ባለ ተመራቂ ተማሪዎች ፊት ቀርቦ ስለ ስራ ፈጠራ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠን ። ኢንጅነር ነን ዶክተር ነን ብላችሁ አትኮፈሱ የጀበና ቡና ብታፈሉ ትችላላችሁ ። ለምሳሌ ሚካኤል እዮብ አቤል በኢንጅነሪንግ እና ዶክትሬት ተመርቃችሁ ሰፈር ለሰፈር ከምታውደለድሉ የጀበና ቡና ብታፈሉ ምን ችግር አለው ? ብሎ በምሳሌነት ጠቀሰን ። እኔ እንዳስተማረን ሳይሆን እንደ ሰደበን ቆጥሬው እሳት እንደነካው ላስቲክ ተኮራመትሁኝ ።
ከስብሰባው በሁላ ስንሻውን ለማናገር ከተቀመጥሁበት ተነስቼ ተራመድኩኝ ። የልጅነት ጓደኛዬ ስለሆነ ሰላምታ ልሰጠው አስቤ ነው የቀረብሁት ። በሰዓቱ ከየት መጣ ያልተባለ ጠባቂው በመዳፉ ጭብጦ አሽቀነጠረኝ ።
ቀና ብዬ አየሁት !
“ምን አጠፋሁ አለቃ?”
ፈርጣማው ጠባቂ በቁጣ ቱግ ብሎ እንዲህ አለኝ
“አንተ ምን አይነት ደፋር ነህ ባክህ ? ክቡር ከንቲባችንን ለመቅረብ አይደለም ሻንጣቸውን ለመሸከም ብትመጣ እንኳ ማስፈቀድ ነበረብህ “ 🙂
#ሚካኤል አስጨናቂ


https://t.me/Write_Event
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
<<ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?>> ትላለች አንደኛዋ።
<<እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!>> ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።

ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
<<ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?>> ይለኛል።
<<ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?>>
<<አይ ሻማው ይሁን በቃ!>> ይላል እየተቅለሰለሰ።

አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። <<ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!>>

ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው።

የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም!

ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "beauty and the beast" ሆሆ!
ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል።
<<ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም>> ስለው
<<ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!>>

እያሳዘነ ያስቀኛል።

ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ።
<<አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?>>
<<አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!>> አለ አሁንም እያለቀሰ!
<<እሺ ምንድን ነው?>>
<<እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!>>

ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ።

ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው?

የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ።

የፈሪ ትልቁ ችግር.....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም!

<<ለማን ተናግረህ ነው?>> ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት።

የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም።

ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ።

የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን <<ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?>> አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው።

ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ።

አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ!

አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል።

ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ።

ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ <<አባቴ ማነው?>> ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው?

<<ተረት ተረት>>
<<የመሰረት>>
<<በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች>>
<<እእእሽ>>
<<ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?>>
<<ምን?>>
<<ሻማ! በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን እጠፋለሁ ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!>>
<<ምን አደረገች?>>
<<በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።>>
<<ከዛስ?>>
<<ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..>> እያለ የሚቀጥል ተረት
!

ታሪኩን ከወደዳችሁትና እንደዚ አይነት አጫጭር ታሪኮችን እንድንፅፍላችሁ ከፈለጋችሁ share አድርጉት።😊👍👍

Join
@write_event