ቃላዊ
346 subscribers
38 photos
5 videos
1 file
121 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ አንድ (1) 🌼🌼🌼

በ5 ክፍል ብቻ የሚያልቅ

🌻እውነተኛ የፍቅር ታሪክ 🌻



ተወልጄ ያደኩት በውቧ በደሴ ከተማ ነው ደሴ ላይ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማርኩ በሇላ የኢንትራንስ ውጤቴ አሪፍ ስለነበር መቀሌ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት የትምህርት ዘርፍ ሁለት ሺህ ስምንት ላይ መቀሌ ዩኒቨርስቲን ተቀላቀልኩ መቀሌን በስምንት ቀን ውስጥ ለመድኳት ብዙ ጓድኞችን ተዋወኩ የመጀመሪያውና ለኔ ለዘላለም ከልቤ ላይ ነግሶ የሚኖረው ጓድኛየ ዘካሪያስ ይባላል የመቀሌ ልጅ ነው
እንደ ዘካሪያስ ያለ ጓድኛ ማግኘት ቢከብድም ለኔ ግን ሰቶኛል
ዛክ ጋ በቶሎ ተግባባን
አብረን መዋል አብረን ማንበብ አብረን መዝናናት የቀን ተቀን ስራችን ሆነ
አገሩን በደንብ አስጎበኘኝ ጓድኝነታችን ከጓድኝነት አልፎ ወደ ወንድማማችነት ተለወጠ እኔም የወንድሜን ያህል ወደድኩት እሱም እንደኔው
ቀኑን በውል ባላቀውም ህዳር ወር ላይ ዛክ የሴት ጓድኞቹን ሊያስተዋውቀኝ ካፌ ተቀጣጠርን
እኔም ሴቶች ጋ ስገናኝ የመጀመሪያየ ነውና አለባበሴን አሳምሬ ወደ ተቀጣጠርንበት ካፌ ከነፍኩኝ
ከካፌው በር ላይ ቁሜ ስመለከት ሚዛክን አየሁት እሱም እኔን ፍለጋ አይኑን ከወዲያ ወዲህ ሲያቅበዘብዝ ተመለከትኩት
ረጋ ባለ አረማመድ ወደ እነ ዛክ ስሄድ በድጋሜ አይኔን ከጎኑ ካሉት እንስቶች ላይ ጣልኩት

ወደኔ የዞረችዋ ጉብል አይኗ እንደ ሠማይ ከዋከብት ያበራል ፀጉራ በወገቧ ተግለስልሶ ወርዷል
ልክ ሳያት ልቤ መታ ሰውነቴ ዛለ
ሰውነቴን የሆነ የማላቀው አድስ ስሜት ወረረኝ መራመዴን ረስቼ እሷን ስመለከት መንገዴ ላይየነበረ ወንበር አደናቅፎኝ በቁሜ ተዘረርኩኝ እንደምንም አቃትቼ ለመነሳት ስመሞክር መነሳት አልቻልኩም በደቂቃ ውስጥ መውደቄን የተመለከተ የካፌው ተጠቃሚ ሰው ሁሉ ከበበኝ ይበልጥ አመመኝ በአይኔ የማውቀው ሰው አጥቼ ሰፈልግ ዛክ ዘሎ ተከመረብኝ ይርበተበታል
ደህና ነኝ ጓድኛየ ተረጋጋ አልኩትና ለመነሣት ያለ የለለ ኃይሌን ተጠቅሜ ስንጠራራ
የማላቀው ሰው ሊያግዘኝ እጄን ያዘኝ ወደ ሰውየው ቀና ስል ዳግም መውደቅን ተመኘሁ ያየሁትን ሰው ማመን አቃተኝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ☞ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,


ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ 🙏🙏
┏━━━••━━ ••━━ ••━━┓
👉 ይቀላቀሉን

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••


https://t.me/Write_Event
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ ሁለት (2) 🌼🌼🌼


🌻 እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌻



"እውነተኛ ፍቅር በመሠናክል የተከበበ ነው መሠናክሉን ለማለፍ እንጅ ከመሠናክሉ የምትሸሽ
ከሆነ ፍቅር አይደለም ምክኒያቱም ፍቅር አይፈራም ይታገሳል እንጅ"
,,,,,,,,,,,,,,,,, ዳግም መውደቅን ተመኘሁ አለንጋ የመሰሉ ጣቶቿ ከጄ መዳፍ ላይ ሲንሸረሸሩ ደስ የሚል ስቃይ ተሰማኝ እሷ ባለችበት ሁሉ መውደቅን ተመኘሁ ሰዉነቴ መርበትበት ጀመረ ህመሜን ረሳሁት እጆቿን ከእጆቼ መለየት አልፈለኩም እጆቿን ጠበቅ አድርጌ ይዠ ተነሳሁ አካሌ የኔ አልመስልህ አለኝ
የኔን መውደቅ ለመመልከት ዙሪያውን የከበበኝ ሰው አድስ አበባ ስታድየም የቡና እና የጊዮርግስ ጨዋታ ለመታደም የመጣ ያህል ነበር
ከህመሜ በላይ የሠውን አይን ፈራሁት ከቆምኩበት ሁኘ ዙሪያየን ስመለከት አይኔ ፈዘዘ
ዛክ በል ተራመድ እስኪ መልክየ አይዞህ አለኝ
እሺ ብየ ለመራመድ ስሞክር አልቻልኩምና ወደ ዛክ ዞር ብየ አልቻልኩም ጓድኛየ አልኩት
ስሟን ገና ያላወኳት ግን በደቂቃ እይታ በፍቅር የወደኩላት እንስት ልደግፍህ አለችኝና እጄን ሳብ አድርጋ ትከሻዋ ላይ አደረገችው አሁንም ሌላ ስሜት ወረረኝ የሆነ ደስ የሚል በስቃይ የተሞላ ደስታ
ከዛማ እኔስ ህመምተኛ አይደለሁ ተጠመጠምኩባት እንደምን ተገፋፍተን ከካፌው ወጣን
ዛክ ላዳ ታክሲ ፈለገ እና ወደ ሆስፒታል ሄድን ሆስፒታል ስደርስ ግን ከበፊቱ ተሻለኝ እያነከስኩም ቢሆን መራመድ እችል ነበር ነገር ግን አሁንም መታቀፍ አማረኝ ያውም በቆንጆና በምወዳት ሴት እቅፍ
ዛክ ከኛ ቀድሞ ወደ ካርድ ክፍል ሮጠ እኔም በዛክ ጓድኞች ተከብቤ ወደ ሆስፒታል ገባን
ከቆይታ በኋላ ዶክተሩ ትንሽ እረፍት ያስፈልገዋል ስላለኝ አልጋ ያስኩኝ
ዛክም ተረጋግቷል ጓድኞቼን ተዋወቃየው አለኝ
በመጀመሪያ ፀይም ዘለግ ያለች ቆንጆ ሙና እባላለሁ አለችኝ
ሁለተኛዋ እኔ ልቤ በደቂቃ ውስጥ በፍቅር የከነፈላት ባለዞማ ፀጉር መልኳ የቀይ ዳማ ዘለግ ያለች ቆንጆ አተኩራ እያየችኝ እጇን ዘረጋችና,,,,,,,,,,,,,,,☞ይቀጥላል



ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ 🙏🙏

https://t.me/Write_Event
ቃላዊ via @like
Gete Anley – Melikish Kanchee Aybeltim
#ጌቴ_አንለይ
#መልክሽ_አይበልጥሽም

🎶🎹🎹🎶
🎹🥁🥁🎹
ለኔ አዲስ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
🎶
በጄ እስክተገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነውንጂ መች ጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
🎶🎶
የብርቅዬ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
የብርቅዬ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
አንቺን ውብ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ ወድጄሽ ከሆዴ
🎶
መች አይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ከአንገት በላይ ምርጫ ከአንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ መች አየ እሱን ብቻ
🎹🥁🥁🎹
🥁🎹🎹🥁
መቼ እተውሽ ነበር ዎ አይኔስ ቢያሽ ድሮ ሆ
ባይኖር እንኳን መልክሽ ሆ ውብ ባትሆኝም ኖሮ
ቢደምቅም ባይደምቅም ሆ ቢበርደው ቢሞቀው ዎ
ላይሽ ብቻ አይደለም ሆ ልቤን የደነቀው
🎶
ከላይ ቢልም ዋለች በአደባባይ እቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጭቷ
🎶🎶
ጥቁር ነጭም ቢሆን ሆ የጥፍርሽ ቀለሙ ሆ
መች እሱ ሆነና ሆ ለኔ ብርቅ አለሙ
አይጭነቅሽ አንቺ ሆ ሀሆኖ አይሰለቸኝም ሆ
ጉዳዬ ውስጥሽ ነው ሆ ካንቺ አይበልጥብኝም
🎶🎶
መልክሽ አይበልጠሽም እንዳለሽም ባውቀው
አንቺው ነሽ መብራቷ ፍቅር ምታቀልጠው
🎶🎶
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
🥁🎹🎹🥁
ለኔ አዲስ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
🎶
በጄ እስክተገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነውንጂ መች ጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
🎶🎶
የብርቅዬ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
የብርቅዬ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
አንቺን ውብ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ ወድጄሽ ከሆዴ
መች አይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ከአንገት በላይ ምርጫ ከአንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ መች አየ እሱን ብቻ
🎹🥁🥁🎹
🥁🎹🎹🥁
ጊዜ ሲለዋወጥ ዎ ወራቱ ሲጨምር ዎ
ይነጥፍ የለም ወይ ዎ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና ሆ አርሮ ቀን ሲከብደው ዎ
መልክማ ይቀየራል ሆ ለአንድ አፍታም ቢበርደው
🎶
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቅ የሌለሽ ውበት
🎶🎶
ጊዜ ሲለዋወጥ ዎ ወራቱ ሲጨምር ዎ
ይነጥፍ የለም ወይ ዎ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና ሆ አርሮ ቀን ሲከብደው ዎ
መልክማ ይቀየራል ሆ ለአንድ አፍታም ቢበርደው
🎶
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቅ የሌለሽ ውበት
🎶🎶
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
👇👇👇👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"መልክሽ ካንቺ አይበልጥም" ሲተነተን

#ውበት እና ፍልስፍና

ፊት በውሀ ላይ እንደሚታይ ያህል ቢሆንም
የሰው ልብ እኮ ለሰውም ይታያል
የሰው ፊት ውስጡን ያሳብቃል
ሰው ውስጡ ውብ ሲሆን
ያ እውነተኛ ውብት ከድብቅነት እያለፈ
እየወጣ እየወጣ ሲመጣ
ለአይን አምሮ ያለመታየት ሚስጥር እጅግ ይገርማል....... (መልኩስ ልቡ ነው)



መልክሽ ካንቺ አይበልጥም (ጌቴ አንለይ)

መግቢያዬ በማይታይ ንግግር

ሀ :- ለምን ጥለሀት አትሄድም ስንት ውብ እና ሸጋ ሴቶች አሉልህ አይደል እንዴ?
ለ :- ሚታይህ ይህ የገረጣ ፊቷ ነው አይደለ
አስሮ የያዘኝ ግን ከውጪ የማይታየው እውነትም ካልካቸው ውብ እና ሸጋ ሴቶች በላይ ውብ የሆነ አንድ ልብ (አንድ ውሳጣዊ ቁንጅና) ይዛ ስላለች ነው። መልኳ እኮ ልቧ ነው።

አይኗ እንደ ኮከብ
መልኳ እንደ ጨረቃ
ጉንጯ የፈነዳ አበባ
ከንፈሯ ኢንጆሪ
ፀጉሯ የሀር ነዶ ...... እያለን ብዙ የግጥም ስንኞችን በሀገራችን ላይ ከተሰሩ ሙዚቃዎች ላይ መስማት ከመለመድም አልፎ የውበት መግለጫ አስተሳሰባችንን በመልክ እና በቁመና እንድንስል ሰፊ ሚናቸውን ሙዚቃዎቹ ተጫውተዋል ብዬ አስባለሁ። ያቺን ሸጋ ብንል አንዲት የምታምር ያን ጎምላላ ብንል ደግሞ አንድ መልከ መልካም ልጅ መሳላችን የማይቀር ሁኔታ ነው። ይሄ ሁሉ እይታ ሰርፀው ከተዋሀዱን የውበት መግለጫዎች እና ሙዚቃዎች ያሳደሩብንን ተፅእኖ እንደመጣ ያመለክታል። ታድያ ይህ አስተሳሰብ ያሳሰበው ይህ ተፅእኖ ልክ አይደለም ብሎ የተነሳው አንድ #የከተማ መናኝ ትናንት ተው ብሎ ዛሬ ላይ በዘመኑ እንዲህ እያለ ፍልስፍናውን ተቃርኖውን ሙግቱን ይገልፅልናል

ከላይ እዩኝ ባለች ባደባባይቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጪቷ

እንግዲህ መልክን በኢንጆሪ በፀሀይ በጨረቃ ሲመዝን የኖረውን ዘመን ተው ብሎ በብልጭልጭ አልመዝንሽም እያለ ኤልያስ - መልካ የሚባል አንድ ዘመን በጣፋጭ ዜማ ያጫውተናል።

ጥቁር ነጭም ቢሆን የፀጉርሽ ቀለሙ
መቼ እሱ ሆነና ለኔ ብርቅ አለሙ
ዘመነ እርጅናም ውብ የወጣትነት ጣፋጭ ዘመን አለው። በዚ ስንኝ ፀጉራቸው ሸብቶ ቆዳቸው ተሸብሽቦ በዘመናቸው ውብ የነበሩትን አዛውንቶች አሁንም በዘመነ ሸበቶነት ውብ እንደሆኑ ይነግረናል። ባለ ጥቁር ፀጉራማዎቹን ደግሞ ብርቄ ከላይ የደመቅሽበት ውበት አይደለም እያለ ያነጋግረናል።

መልክሽ አይበልጥሽም እንዳለሽም ባውቀው
አንቺ ነሽ መብራቷ ፍቅር የምታደምቂው

ከመልክሽ በላይ ውስጥሽ ያበራል ቤቴ ብትመጪ ክፍሌ ሚደምቀው ከላይ ባለሽ ውበት ሳይሆን እንደ መብራት አብሮቶ ጨለማው ቤቴን የሚያደምቀው ውብ ውስጣዊ አንቺ ነትሽ ነው ይለናል ይሄ መናኝ።
በዘመነ ትናንት ውበትን በላይ የመሳል ተፅእኖ እዚጋ ፈርሶ መልካቹ ልባቹ ነው በሚል ብዙ ሺ መፅሀፍ በሚወጣው አስተሳሰብ ይተካል።

ላዩም ሀላፊ ነው መልክ እና ደምግባት
ሁሌም ግን እያልፍም ብርቅ የልብሽ ውበት
ወዳጄ ዘመናችን እኮ ልባችሁ ውብ ነው እያለ በሚሰብክ ባለ ልበ መልካም መናኝ ተቃኝቷል።

መልኬ ልቤ ነው እንድል ያደረከኝ ባለ ልበ መልካሙ ኤልያስ መልካ ሆይ ክበርልኝ

ብላቴናው

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ ሶስት (3) 🌼🌼🌼


🌻እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌻


☞ሰሊና እባላለሁ ስትለኝ እጄን ዘርግቼ ቀረሁኝ አንደበቴ ዲዳ ሆነ በርጋታ መልክየ እባላለሁ አልኳት የፈጣሪ ያለህ የዚህን ያህል መርበትበት ብየ ቀልቤን ሰበሰብኩና አሁን ተሽሎኛል መውጣት እንችላለን አልኳቸው
ዛክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አይ መቆየት አለብህ እመለሳለው ብሎ ወጣ ሁለቱ ሴቶች ለኔ ባልገባኝ ወሬ ይፍነከነካሉ
ባይገባኝም አብሬ መሳቅ ጀመርኩ በመሀል የሙና ስልክ ጠራ ሙና ስልክ ለመናገር ወጣች
ሠሊና እና እኔ አንድ ክፍል ብቻችንን ደስ ይላል
ሠሊና እና እኔን ከመተያየት ያለፈ የሚያግባባን ምክኒያት ጠፋ
በመሀል አፌ እንደ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ
ማን ነበር ስምሽ አልኳት
ፈገግ አለችና መርሳት አጋጠመህ እንዴ ሰሊና አለችኝ
እኔም ስታወራ የምታወራውን ሳይሆን ከንፈሯ ሲላወስ ጉንጮቿ ትርክ ትርክ ሲሉ እየተመለከትኩ ወሬዋ ባላለቀ ሌላ ወሬ በጀመረች እያልኩ ሳስብ ሙና በሩን ከፍታ ገባች እና በፍጥነት ፓርሳዋን አንስታ ጋይስ ቻው እመለሳለው ብላ ቅብጥ ቅብጥ እያለች ወጣች

አሁን የሚያሰጋኝ ነገር የለም ከ ሰሊና ጋ ጨዋታ መጀመር እችላለሁ
በመሀል ምንም የህመም ስሜት ሳይሰማኝ
እእእእእ ወገቤ ብየ ጮህኩኝ
ሰሊና ተደናግጣ ምነው ምን ሆንክ አለችና ወደኔ ተጠጋች
ወገቤን አመመኝ ሰሊና አልኳት
በድንጋጤ ዶክተሩን ልጥራው አለችኝ እኔም በድፍረት አይ አያስፈልግም ባይሆን ወገቤን,,,,,, አላስጨረሰችኝም በፍጥነት አልችልበትም ግን ከተሻለህ ልሞክር አለችና በደረቴ እንድጋለል በአይኗ አዘዘችኝ እንዳዘዘችኝ አደረኩ
እንደ አለንጋ እጥፍ ዝርግት የሚሉ ጣቶቿን ወገቤ ላይ ስታንሸረሽራቸው እንኳንስ ያልታመመው ወገቤ የታመመው እግሬም የህመም ስሜት አይሰማውም ነበር
እጇ መድሀኒት ነው ልክ እንደ እትየ አሰፉ እትየ አሰፉ የሠፈራችን ምርጥና ተወዳጅ የባህል ሀኪም ነበሩ እትየ አሰፉ እንኳንስ የነካችው እግዜር ይማርህ ያለችው ሰው ይድናል ይባል ነበር
እኔም ወደ ሠሊና ቀና ብየ ልክ እንደ እትየ አሰፉ ነሽ ሰሊና እየተሻለኝ ነው አልኳት
ፈገግ አለችና እትየ አሰፉ ማናቸው አለችኝ
ደስ እያለኝ የሠፈራችን ሀኪም አልኳት ከት ብላ ሳቀች እኔም ተከትያት ሳኩኝ ክላሡ በሁካታ ተሞላ ይህንን የሠማ አንድ ታካሚ በር ላይ ቆመና ሲመለከተነሸ ቆየና በድንገት
"ፍቅራችሁ ያስቀናል ያርዝምላችሁ ደስ ስትሉ አለን "
ሰሊናእና እኔ በሽቅድምድሞሽ እኔ
ኧረ ፍቅረኛሞች አይደለንም
እሷ ደግሞ
እናመሠግናለን አለችና ፈገግ አለች
እኔ ግራ ገባኝ ብቻ ሰሊና ጣጣ የሌለባት መሆኗን ሳውቅ ይበልጥ ልቤ መምታት ጀመረ እሷም ከጎኔ እንደቆመች እኔም ከሷ ላይ አይኔን እንደተከልኩኝ ዛክ በሩን ከፍቶ ገባ

ዛክ በፌስታል ሙዝ እና ብርቱካን ይዟል
እንዴት ቆየህ ጓድኛየ ሰሊና ስታደርቅህ ቆየች አይደል ብሎ ከፌስታሉ ሙዝ አውጥቶ ሰጠኝ እና በል ብላ ብሎ ለነሡም አንድ አንድ አንስተው ወሪያችንን ቀጠል ከሆስፒታል መውጣት እስኪያስጠላኝጨድረስ ሆስፒታል መሆናችንን ወድጀው እያለ ዶክተሩ መውጣት እንዳለብን ነገረን ተያይዘን ወጣን

እኔም ሰሊናን እንደተለየው ቅንጭላቴ ዞረ
ዳግም የማላገኛት መሠለኝ
ነገር ግን ለሷ ያለኝ ስሜት እየጨመረ ቢሄድም በቀን በቀን እየተገናኘን መጫወት አዘወተርን አራትችንም ደስ የሚሉ ቀናቶችን እያሳለፍን አንድ ቀን ለመዝናናት ወተን የጭርቃት ኳስ ስንጫወት
ሙና እና እኔ በአንድ
ዛክ እና ሰሊና
በአንድ ሁነን ተጋጠምን የተሸነፈ ሊጋብዝ ያሸነፈ ሊጋበዝ ነበርና ጨዋታችን የደራ ነበር
በጨዋታ እንበልጣቸዋለን እኛ ግን አልተናበብንም ነበር እና አሸነፉን
ከዛ እርስ በርሳችን ስንፎጋገር ሰሊና ስማማ መልክየ አለችኝ እህ አልኳት
ከንፈሯን በእጇ እየዳሰሰች ሰሊና እና ዛክ እኮ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
አስተያየታችሁን አይተን ይቀጥላል


https://t.me/Write_Event
የመረረ ፍቅር
ክፍል አራት (4)

☞ፍቅር ህያው ነውና☜
ዛክ እና ሰሊና እኮ ስትለኝ ላስጨርሳት አልቻልኩም ደነገጥኩኝ ልቤን ፍርሀት ተሰማው ቢሆንም ግን ቁርጤን ለማወቅ እሽ! ዛክና ሰሊና አልኳት ፈገግ ብላ ቀልደኞች ናቸው ስትለኝ ልቤ ቀዝቃዛ ውሃ የተቸለሰበት ያህል ተሰማኝ ተረጋጋሁእና ወደ ዶርም ተመለስኩኝ

ዶርም ስደርስ ይበልጥ ሰላም አልሰማኝ አለ ሰሊና ናፈቀችኝ ደውየ ብቻዋን ላገኛት እንደምፈልግ ስነግራት አላመነታችም እሽ አለችና የምንገናኝበትን ቦታ እንድነግራት ጠየቀችኝ ሰው ከማይበዛበት ቦታ ቀጠርኳት

ከቦታው ቀድሜ እኔ ብደርስም እሷም ሳታስጠብቀኝ በቶሎ መጣች የማወራው ጠፋኝ እሷም ለምን እንደፈለኳት እንድነግረኝ አዋከበችኝ እኔም ከአንደበቴ ይልቅ አይነሰ እንባ እየፈሰሰው ከንፈሬ እየተንቀጠቀጠ አፌ እየተኮላተፈ ያወራ ጀመር ነገር ግን እሷም እንደኔው በፍርሀት ተዋጠችና አንገቷን ወደ መሬት ደፋች በሁለታችን መሃል ፍፁም ዝምታ ሆነ

እኔ ወንድነቴ ድፍረት ሰጠኝና ተነስቼ ወደ ሰሊና ተጠጋው
ጡቶቿ ከደረቷ ፈንገጥ ፈንገጥ ብለው ስለተቀመጡ ድፍረት ሰጡኝ ተጠጋዋት በወገቧ ስር ወርዶ ወርዶ የተነሠነሰውን ፀጉሯን ወደ ላይ ሸከፍ እየሠጠው
አ,,,,,,,, አ,,,,,,,,, አ,,,,,,,,,አፈቅርሻለው ሰሊና አልኳት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ደነገጥኩኝ ፍርሃት ተሠማኝ እንደተቃቀፍን ፍርሃታችንን አስወግደን ተመለስን በአንዴ ማሬ ሆዴ ፍቅሬ እየተባልን መጠራራት ጀመርን

ፍቅራችን ደራ ነገር ግን ለጓድኞቻችን አልነገርናቸውም ነበር ለቫላንተይን ቀን እንነግራቸዋለን ብለን ነው
እነሡም አልነቁም
የቫላንተይን ቀን ደረሠ አራታችንም አንድ ተቀጣጠርን
ይህ የሆነው
ሙና ለኔ ደውላ ስቀጥረኝ
ዛክ ደግሞ ለ ሰሊና ደውሎ ሙና ከቀጠረችኝ ቦታ ሲቀጥራት ሠሊና ከኔ ጋ ነበረች
አይነጋ የለም ነጋ ምን አስበው እንደቀጠሩን እያሰብኩ እያውሰለሰልኩ ከቦታው ደረስኩ ከቦታው ስደርስ ያየውትን ነገር ማመን አቃተኝ አይኔ ባያይስ ብየ ተመኘሁ ዛክ ቀይ አበባ ይዞ ተንበርክኮ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል

ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ

https://t.me/Write_Event
.
#የመረረ_ፍቅር


ክፍለ አምስት (5)

የመጨረሻ ክፍለ



ፍቅር ከደሴ እስከ መቀሌ ዛክ ቀይ አበባ ይዞ ከኔውቷ ንግስት ከሰሊና እግር ስር ተንበርክኳል ማመን ቢያቅተኝም ማመን ስላለብኝ አመንኩ ሳላስበው ከወደ ኋላየ ሰርፕራይዝ የኔ ፍቅር የሚል ድምፅ ተሠማኝ ፡፡
በድንጋጤ ዞር ስል ሙና ነች በቁሜ ደርቄ ቀረሁ ወደ እኔ እየተጠጋች ከተገናኘንባት ሰዓት ጀምሮ ስላንተ ያላሠብኩባት ደቂቃ ፈልጎ ማግኘት ምንኛ ይከብዳል አፈቅርሃለው አለችና ከንፈሬ ጋ ከንፈሯን አላተመችው እኔ ደንዝዣለው ሬት ሬት ከማለት ያሀፈ ምንም ጥሩ አይሰማኝም ነበር እና ከላየ ላይ መንጭቄ አሽቀነጠርኳት እና ፊቴን ወደ እነ ሰሊና ስዞር ሰሊና ፊቷ በእምባ እየታጠበ ከፊቴ ቁማለች፡፡

ጠጋ ብየ ሰሊና ወደኔ እየተጠጋች መልክየ ጠጋ እያልኳት ሰሊና ወደ እኔ እየተጠጋች መልክየ ሳናስበው ከንፈር ለከንፈር ተገጣጠምን ፍቅር አሽቀንጥሮ ከማናቀው አለም ውስጥ ወሰደን ከቆይታ በኋላ ተላቀን ዙሪያችንን ስንመለከትማንም በአካባቢያችን የለም፡፡

ደስተኞች ባንሆንም አብረን ወደ ሆቴል ሄድን አልጋ ይዘን ፍቅር ሰራን ሰሊና ለኔ የመጀመሪያየ ክህነቴን ያፈረስኩባት ለሧም የመጀመረዋ ነኝ ያቺ ቀን እንደዚሁ መሽታ እንደዚሁ ነጋች፡፡

ሲነጋ የሠሊናን አይን ለማየት ድፍረት አጣሁ ሳትሰማኝ ተነስቼ ወደ ዶርሜ ከነፍኩ ዶርም ስገባ ዛክን አገኘሁት ዛክ ሊያዋራኝ አልፈለገም ተሥፈንጥሮ ወጣ
ከመኝታየ ወረቀት ተቀምጦ አገኘሁ ወረቀቱ አንዲህ ይላል "ሠሊናን እወዳታለሁ አንተንም እንዲሁ ከሰሊና ጋር ፍቅር እንደጀመራችሁ አላውቅም ነበር ፍቅራችሁን ቀጥሉ ይህን ግን እኔ እያየሁ መቋቋም ስለማልችል ጓድኝነታችን ከዚ ላይ አቆመ ቻው ዘካረያስ"ይላል፡፡

እንባየ አሸነፈኝ ጓድኛየ ለኔ የከፈለው መስዋት ይበልጥ አሳመመኝ ሰሊናን በስልክ ቀጥሬ ዛከን አገናኘዋት ግን የማይሆን ነበር ሙናምጰከሰሊና እግር ስር ወድቃ ይቅርታ ጠየቀች ሰሊና እና እኔ ተያየን እንባችን ፈሠሠ አይናችን የደም እንባ ሊያፈስ ምንም አልቀረው፡፡

የሠሊና ሃሣብ ነበር ከአሁን በሁላ አራታችንም በእህት እና በወንድምነት እንቀጥላለን አለችኝ ሁላችንም ተስማማን፡፡በእህት እና በወንድምነት እየቀጠልን አመታት ነጎዱ ዛክ እና ሙና ሌላ ፍቅረኞች ይዘው አስተዋወቁን እኔም ለሠሊና ይምሰል የክላስ ጓድየን ፍቅረኛየ ብየ አስተዋወኳት ሰሊና እና እኔም በተገናኘን ቁጥር እየተያየን ማንባት ስራችን ሆነ ,,,,,,,,,,,, "ህይወት ትቀጥላለች ፍቅርም አታቆምም "
አለቀ !

እንግዲ እውነተኛ ታሪክ ነውና እውነታውን ብቻ ከህይወት ጋር አብሮ ይቀጥላል......

ተፈፀመ
ተፈፀመ!

ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ፡፡



ይቀላቀሉን 👉

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➊

♥️በ እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረት ♥️



...🖊ከአልጋዬ ፊት ለፊት የልብስ ማስቀመጫ ቁምሳጥን ላይ የሚገኘዉ መስታወት እኔ ስስቅም ሆነ ሳለቀስ መመልከትን ለምዶታል። አንዳንዴ ''መስታወት የልብ ጓደኛዬ ነዉ ምክንያቱም እኔ እያለቀስኩ እሱ አይስቅብኝም!'' የሚለዉ አባባል በልኬ ተሰፍቶ የተሰጠኝ ይመስለኛል... ሀዘን ደግሞ ከእኔ ፍቅር የያዘዉ ይመስል በተደጋጋሚ እየጎበኘኝና የማይድኑ የልብ ጠባሳዎችን እያስታቀፈ ወዳጄ የሆነዉ መስታወት ፊት ይገትረኛል... ከመስታወቱ ፊት ለፊት ቆሜ እራሴን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት ፀጉሬ ተንጨባሯል...በለቅሶ ብዛት የቀላዉ ዓይኔ እንኳን ለሌላ ሰዉ ይቅርና ለራሴም ፍርሀትን ስለለቀቀበኝ አይኔን ከመስታወቱ አሸሸሁ... ድካምና የእንቅልፍ እጦት ተደራርበዉ ሰላም ነስተዉ ጭንቀት ዉስጥ ከከተቱኝና ከቤት መዉጣት ካቆምኩ አንድ ሳምንት ተቆጠረ። ለቤተሰቤ የመጀመሪያም የመጨረሻም ብቸኛና ተወዳጅ ልጅ ብሆንም፤የቤተሰቦቼ ኑሮ ከራሳቸዉ አልፎ ለሌሎች ይተርፋል ከሚባል ደረጃ ላይ ቢመደብም ከልጅነቴ ጀምሮ አንድ የማዝንበት ምክንያት አለመጥፋቱ ይገርመኛል! ለነገሩ ሀዘን ጥሩ በሚባል የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይጎበኝም ያለዉ ማነዉ?። ስቃይ በገንዘብ ብዛትና በኑሮ ስኬታማነት የማይረታ መሆኑን ምስክር እንድሆንለት ያዘጋጀኝ ምስኪን ሰዉ መሆኔ ተስፋ ያስቆርጠኛል። አሁን ''የሰላም ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮከብ ተማሪ የሆነችዉ ቤዛዊት አለሙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዉጤቷ ተበላሽቶ ዩኒቨርሲቲ የመግባት ህልሟ የዉሃ ሽታ ሆነ!'' ቢባል ማን ያምናል?' ግን እዉነታዉ ይህ ነዉ! ስንት የደከምኩለትና ለስንቶች ምሳሌ የሆነዉ የትምህርት ላይ ጥንካሬዬ በአጭሩ ተቀጭቶ በሀዘን ከተለወጠ አንድ ሳምንት ተቆጠረ...

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➋



...🖊በጭንቀትና በሀዘን ከመስታወቱ ፊት ለፊት እንደቆምኩ እናቴ የመኝታ ቤቴን በር ሳታንኳኳ ከፍታ ገባች...

የዘንድሮ ልጆች ሁሉም ነገር በአንድ ጀንበር ካልተከናወነ ትላላችሁ! መታገስ እኮ ዋጋ አለዉ!''የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል!'' ሲባል አልሰማሽም? ቤዛዬ እንደ መታገስ ከባድ ስቃይ ያለዉ ነገር ባይኖርም መጨረሻዉ ግን ያማረ እንደሚሆን አትጠራጠሪ!
የእናቴ ምክርና የማፅናኛ ቃል የእናትነት ፍቅር የታከለበት ቢሆንም እኔ ግን እንኳን እሷ ቀርቶ ፈጣሪ ወደ ምድር ወርዶ አይዞሽ ቢለኝ እንኳን የምፅናና አይመስለኝም። ወላጆቼ በትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ክፉኛ ተደናግጠዉ ቢያዝኑም በሀዘኔ ላይ ሀዘን ላለመጨመር ሲሉ ብቻ ላይ ላዩን ደስተኛ መስለዉ ለመታየት ይሞክራሉ

ቤዛዬ... የአምላክ ስራዉ ድንቅ ነዉ!... ላንቺ ከዚ የተሻለና ጥሩ ነገር ቢያዘጋጅ ነዉ!....ሰዉ የሚያምርበትን ሲፈልግ.....የሚያሳምረዉን...ሰዉ የሚደምቅበትን ሲፈልግ...የሚያደምቀዉን...የሚያስከብረዉን...የሚያዛልቀዉን ማዘጋጀት የፈጣሪ ስራ ሲሆን ይህንን ድንቅ ነገር መሸለም ደግሞ የሰዉ ፀጋ ነዉና አትዘኚብኝ አለችኝ!!
ከአልጋዉ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠች። እናቴ ስለ እኔ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ መሆኑን አዉቃለሁ
ቤዛዬ አንቺን ከመዉለዴ በፊት ሶስት ጊዜ ፅንስ ተቋርጦብኛል አምላክ የእምነቴን ደረጃ ሊፈትን እንጂ ሊያሳዝነኝ እንዳልሆነ ልቦናዬ ስለሚያዉቅ አማርሬዉ አላዉቅም እርሱም የትዕግስቴን ጥግ አይቶ አመሰግንብሽ ዘንድ አንቺን ሰጥቶኛል እባክሽ ልጄ ሀዘንሽን በልክ አድርጊዉ አለችኝ።

እኔን ለማፅናናት የምታደርገዉ ሙከራ ስላሳዘነኝ ከአጠገቧ ቁጭ አልኩ
እማ...እማ...እ...እኔ.. መናገር አቃተኝ!!

ቤዛዬ ዩኒቨርሲቲ ባይሆን ምን አለበት የፈለግሽዉ ኮሌጅ ገብተሽ መማር ትችያለሽ እኮ!!

አ.ዉ.ቃ.ለ.ሁ...እማ... ግን ይሄ ለእኔ አይገባኝም...እኮ!

ለማን ምን እንደሚገባዉ መወሰን የሰዉ ስልጣን አይደለም!! በእኔ ሞት ይሁንብሽ ይሄ ሀዘን በቃሽ! አለችኝ!!

እናቴ በእኔ ሞት! እያለች ስትለምነኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ካሰብኩት ከወሰንኩበት ነገር ሳይቀር ምልስ እላለሁ እሷም ይህን ስለምታዉቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስሆን
በእኔ ሞት! ትለኛለች
አሁን ተነሺ አባትሽ ሊያናግርሽ ይፈልጋል!
በእኔ ሞት ያለችኝ እናቴን ማሳዘን ስላልፈለኩ እጄን ይዛ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ልቃወማት አልቻልኩም...

ይቀጥላል...


https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➌



ለዓይን ከሚማርከዉ ሳሎናችን ዉስጥ ካለዉ ባለግርማ ሞገስ ሶፋ ላይ አባቴ የንባብ መነፅሩን አድርጎ የስራ ወረቀቶችን ያገላብጣል። የተለያዩ አይነት የሚባሉ የጭነት መኪናዎች ዋነኛ የሚባሉ የቤተሰባችን የገቢ ምንጭ ቢሆኑም ከእነሱ በተጨማሪ ከምንኖርበት የጅማ ከተማ ዉስጥ በእናቴ ዋና ሀላፊነት የሚተዳደሩ ሁለት ሆቴሎች አሉን። አባቴ የእኔን ወደ ሳሎን መምጣት ሲመለከት ፈገግ አለ...
ዛሬም በፈተና ዉጤትሽ መበላሸት እያዘንሽ ነዉ?
እንዴት አላዝን! አባ! የለፋሁለትና የጓጓሁለት ዉጤት እኮ ነዉ!
በሀዘን የምትለዉጪዉ ምን አለና?... ነይ እስኪ ከጎኑ አስቀምጦ ፀጉሬን መዳበስ ሲጀምር...
ዛሬ ለምን እራት ዉጪ አንበላም? የእናቴ ሀሳብ ነበር እኔ ግን ከቤት መዉጣት እንደማልፈልግ ገለፅኩላት!
ዉጤትሽ የተበላሸዉ በስህተት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል እያጣራሁ ነዉ!...ግን በእንደዚህ አይነት ጭንቀት ዉስጥ መቆየቱ መፍትሔ ስለማይሆን ጠንካራ መሆን አለብሽ ደግሞ እናትሽ ጥሩ ሀሳብ ነዉ ያመጣችዉ ዛሬ እራት ዉጪ ነዉ መብላት ያለብን መንገደኛ ስለሆንሽ የመሰነባበቻ ይሆነናል
መንገደኛ...ማን ነዉ?...መንገደኛ?
አዲስ አበባ አክስትሽ ቤት የቀረችዉን የክረምት ጊዜ እንድታሳልፊ እኔና አባትሽ ወስነናል!... ላንቺም ቢሆን ከዚህ ጭንቀት እዛ ይሻልሻል!
ንግግሯ የጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ አዘል ስለነበር ዝምታን መረጥኩ።
በሉ አንድ የማገኘዉ ሰዉ አለ ለባብሳችሁ ጠብቁኝ ብሎ አባቴ ጉንጬን ስሞ ወጣ።
በይ ተነሺና ገላሽን ታጠቢ ከዚህ በሗላ ሀዘን የሚባል ነገር የለም!! እናቴ ሳምንቱን ሙሉ የሆቴሉን ሀላፊነት ለማናጀሮቹ አስረክባ ከእኔ ጋር ነበር ያሳለፈችዉ። የምለብሰዉን ልታዘጋጅልኝ ወደ መኝታ ቤቴ አመራች እናቴ በእሷ ምርጫ ልብስ መልበስን አስለምዳኛለች... የግርግዳ ሰዐቱ 10:00 መሆኑን ያመለክታል በረጅሙ ተነፈስኩ...የሀምሌ ሰማይ በደመና ተከቦ ያስገመግማል...እዝን ጭፍግግ ያለ ቀን ነበር ልክ እንደኔ ልብ...

ይቀጥላል

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➍



...🖊ይህ ሁሉ ህዝብ በሚተራመስባት ዓለም ዉስጥ እንደዚህ ብቸኛ መሆን ያዋጣል?
ከጅማ ወደ አዲስ አበባ የማደርገዉ ጉዞ በዝምታና በሀሰብ መዋጡን ያስተዋለ ከጎኔ የነበረ መንገደኛ ነበር።
ይቅርታ እኔን ነዉ?
መቼም ከአንቺ ዉጪ በሀሳብ ተዉጦ ከጎኔ የተቀመጠ ሌላ ሰዉ አይኖርም ደሞ... ይህ ቁንጅና ምን ቢበድል ነዉ በዝምታ የምትቀጪዉ?
ጠየም ያለ ተጨዋችነቱ ፊቱ ላይ የሚነበብ የደስ ደስ ያለዉ ወጣት ነበር!
ዝም ስትል ማዳመጥና ምላሽ መስጠት ትችላለህ ዝምታን ላወቀዉና ለተረዳዉ ከራስ ጋር የመማከር ዘዴ ነዉ አይመስልህም?
እኔ ፍቅርና ፍልስፍና ላይ ብዙም አይደለሁም ነገሬ ሁሉ ቀጥተኛና ግልፅ ነዉ። አቤል እባላለሁ ምድር ላይ 27 አመታትን አስቆጥሬያለሁ ከአራዶቹ መንደር ሸገር! ብሎ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ!
ቤዛዊት! እንዳንተ አገላለፅ ምድር ላይ 24 አመታትን አስቆጥሬያለሁ ከአባ ጅፋር ሀገር ጅማ!ብዬ እጁን ስጨብጥ... ለረጅም ዘመን የማዉቀዉ ነገር ግን ከጎኔ ያልነበረ...በህልሜ በሀሳቤ የሚመላስ ነገር ግን እዉነታዉ ላይ የሌለ... ብቻ የሆነ የሚያደናግር ስሜት ተሰማኝ።
ሸገር ማንን ጥየቃ እየሄድሽ ነዉ?
የቀረችዉን የክረምት ጊዜ አክስቴ ጋር ለማሳለፍ! አንተስ ከጅማ ምን ጉዳይ ገጠመህ?
ታላቅ ወንድሜ በስራ ምክንያት ከአዲስ አበባ ጅማ መጥቶ ነበር ነገር ግን እዚሁ ትዳር ይዞ እየኖረ ነዉ የተወሰኑ ሳምንቶችን እሱ ጋር አሳልፌ እየተመለስኩ ነዉ!
እና ጅማን እንዴት አገኘሃት በተደጋጋሚ ስለምመጣ ያንቺን ያህል ባይሆንም አዉቃታለሁ! ጅማ... አይናፋር ቆንጆ ሴትን ትመስለኛለች... ለመቅረብ የምታስፈራ ለመራቅ ደግሞ የምታሳሳ ልክ እንዳንቺ!
ከፍቅርና ፍልስፍና ይልቅ ቀልድ ይዋጣልሀል መሰለኝ
ተሳፋሪዎች ለቁርስ 30 ደቂቃ አላችሁ!
የረዳቱ ድምፅ ጨዋታችንን አቋረጠዉ ለነገሩ እኔም ብሆን ማታ የሽኝት ብለዉ ቤተሰቦቼ እራት ቢጋብዙኝም የምግብ ፍላጎቴ ቀንሶ ስለነበር በደንብ አለመብላቴ አሁን የርሀብ ስሜትን ፈጥሮብኝ ነበር። ተሳፋሪዎቹ ለቁርስ መዉረድ ጀመሩ
ጨዋታችን ከቁርስ ጋር ይቀጥል? አቤል ነበር!...

ይቀጥላል...

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➎


...🖊ለረጅም ጊዜ እንደማዉቀዉ የልብ ጓደኛ ነፃነት ስለተሰማኝ ለቁርስ የታዘዘዉን ምግብ በነፃነት እስከምጠግብ በላሁ። የሀምሌ የጠዋት አየር ከቅዝቃዜና ካፊያ ጋር ተዳምሮ ከአልጋ አትዉጡ አትዉጡ የሚያስብል ቢሆንም እኔ ግን ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በማደርገዉ ጉዞ ድንገት ከተዋወኩት ልጅ ጋር በነፃነት ቁርስ በላሁ!...ይገርማል! በህይወት ዘመኔ እንደዚህ ከሰዉ ጋር በፍጥነት ተግባብቼ አላዉቅም ለዛዉም ከወንዶች ጋር... ለቁርስ የተመደበዉ ሰዓት በመጠናነቁ ወደ መኪናዉ ተመለስን።
እና በትምህርት ዉጤትሽ መበላሸት ምክንያት ሀዘን ስለተሰማሽ አክስትሽ ጋር የተወሰኑ ጊዜያትን ለማሳለፍ ነዋ የአዲስ አበባ ተጓዥ የሆንሽዉ?
አዎ!አልኩት ምንም ነገር ሳልደብቅ ስለራሴ ሁሉንም ነገር በመናገሬ ሀፍረት እየተሰማኝ!
እኔ የምልህ...ቁርሱ ላይ...አልኮል ነገር ቀላቅለህበት ነበር?
እንዴት?
ስለራሴ ብዙ መናዘዜ የታወቀኝ አሁን ነዉ! አንተን እኮ ከስምህና ከጨዋታህ ዉጪ ብዙም
አላወኩህም!
ስለራሴ ነግሬሽ እንድታዉቂኝ አልፈልግም ድርጊት ከቃል ይበልጣል ድርጊቶቼን አይተሽ ታዉቂኝ ይሆናል... ''ነገም ሌላ ቀን'' ነዉ እኮ!
እና ሌላ ጊዜም እንገናኛለን እያልከኝ ነዉ?
አዲስ አበባን ከሩቅ ስትመለከቻት ነዉ ሰፊ የምትመስለዉ ቀረብ ብለሽ ከዉስጧ የምትፈልጊዉ ነገር ካለ ትጠብልሻለች... ሁለታችን ከተፈላለግንባት ደግሞ ምን ያህል እንደምትጠብልን አስቢዉ ፈገግ አልኩ!... ለቁርስ የወረደዉ ተሳፋሪ ሙሉ በሙሉ ወደ መኪናዉ ስለተመለሰ ጉዞ ተጀመረ...
ጨዋታ፣ቁምነገር፣ቀልድና ሳቅን ከአቤል እያገኘሁ የማልረሳዉንና ጥሩ ትዝታ ጥሎብኝ እንደሚያልፍ እርግጠኛ የሆንኩበትን ጉዞ እያከናወንኩ ነዉ። መኪናዉ ይሄዳል...ዛፎችና ሰዎች በፍጥነት ሽዉ እያሉ ወደ ሗላ ይቀራሉ...ተሳፋሪዎች ያወራሉ...እፎይታ ተሰምቶኝ ጉዞዬን ቀጥያለሁ...

ይቀጥላል...

📒📕📘📙📗

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➏



...🖊መነሻዉ ከጅማ ከተማ ሆኖ ከንጋቱ 11:30 የተጀመረዉ ጉዞ ከቀኑ 8:00 አካባቢ መድረሻዉን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አድርጎ በሰላም ተጠናቀቀ። ከመኪናዉ እንደወረድኩ ለአክስቴ ልጅ ለእየሩስ ደወልኩላት መምጣቴ አስቀድሞ ስለተነገራት ኮንትራት ታክሲ ይዛ መስቀል አደባባይ አካባቢ እየጠበቀችኝ እንደሆነ ነገረችኝ። እኔ እንዲቸገር ባልፈልግም አቤል ግን የያዝኩትን ሻንጣ ተሸክሞ እየሩስ የቆመችበት ቦታ ድረስ አደረሰኝ። አቤልን ከእየሩስ ጋር አስተዋዉቄዉ እንዲደዉልልኝ የስልክ ቁጥሬን ከሰጠሁት በሗላ ቻዉ ብሎ መሰናበቱ ከበደኝ! በዝምታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ትኩር ብዬ ስመለከተዉ ሁኔታዬ ከእኔ አልፎ እየሩስንም ስለገረማት
እዚሁ የማደር ሀሳብ አለሽ እንዴ? አለችኝ!
ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰዉ ድንገት ከገባሁበት ዝምታ ብንን ብዬ ነቃሁ።
ስለ ሁለም ነገር አመሰግናለሁ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር! መልካም ቀን ይሁንልህ!
አሜን መልካም ቀን ይሁንልን!
አቤል ያልገባኝን ስሜት አስታቅፎኝ እኔና እየሩስን ተሰናብቶን ሄደ! ከእየሩስ ጋር በቀጥታ ሳሪስ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድን ከአቤል ጋር እንዴት እንደተዋወቅንና በአንድ ቀን የተሰማኝን ግራ የሚያጋባ ስሜት አጫወትኳት። እየሩስ የእናቴ እህት ልጅ ብቻ ሳትሆን የእድሜ እኩያ ጓደኛዬ፤የልቤን ሚስጥር ተጋሪ እህቴም ጭምር ነች።
አንዳንዴ ብዙ ግምት ሰጥተን ከጠበቅነዉ ነገር ይልቅ ድንገት የምናገኘዉ ደስታን ይሰጠናል አለችኝ!
እንዴት?
ልክ እንደ ፈተና ዉጤትሽና እንደ አቤል ማለት ነዋ!
እየሩስ የተናገረችዉ ነገር ሙሉ በሙሉ እዉነት ቢሆንም ደህና የረሳሁት ሀዘን ስለቀሰቀሰችብኝ
ከዚህ በሗላ ስለ ትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ማሰብ አልፈልግም የእሱን ሀዘን ሽሽት ነዉ እዚህ የመጣሁት !
እንጂ አንቺ ናፍቀሽኝ አይደለም እያልሽኝ ነዉ?
ከምልሽ በላይ ነዉ የናፈቅሽኝ የእኔ ዉድ እህት ብዬ እቅፍ አደረኳት።
በሰላም አዲስ አበባ መድረሴን ለማሳወቅ ወደ አባቴ ስልክ ብደዉልም ስልኩ አልሰራም አለኝ ምናልባት ኔትወርክ ይሆናል ብዬ ወደ እናቴ ደወልኩ ከተደጋጋሚ ጥሪ በሗላ ስልኳን አነሳች!
ሄሎ...እማ...አዲስ አበባ ደርሻለሁ...ከእየሩስ ጋር ወደ ቤት እየሄድን ነዉ!...ሄሎ..
...እሺ!...የእናቴ ድምፅ በለቅሶ የታጀበ ነበር!
እማ...ምንድነዉ...የተፈጠረ ነገር አለ?
ሄዷል! አለችኝ!
ማነዉ የሄደዉ?
አ.ባ.ት.ሽ ... ላይመለስ... ተሰናብቶን...ሄዷል!
ስልኬ ከእጄ ላይ ሸርተት ብሎ ወደቀ...

ይቀጥላል...


📚📚

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➐



...🖊እዉነትም ሀዘን ከእኔ ፍቅር ይዞታል! አልያም ደግሞ በእኔ ይቀናብኛል ማለት ነዉ! ትንሽ ፈገግ ስል ደስታዬን የሚያጠፋ ሳቄን የሚገድል ችግር መፍጠሩን ተያይዞታል። አባቴ ሰላም ሁኑ የሚል መልዕክት በቁራጭ ወረቀት ላይ አስፍሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን እናቴ ነገረችኝ! ያለችበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ዛሬን አድሬ ነገ እንደምመጣ ብነግራትም አሷ ግን መምጣቴን አጥብቃ ስለተቃወመች የተወሰኑ ቀናትን አዲስ አበባ ለመቆየት ወሰንኩ።
አድካሚ ህይወት...አድካሚ መንገድ...አድካሚ ቀን!... የእየሩስ ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
ምናልባት በስራ ምክንያት የሄደበት ጉዳይ ሊያቆየዉ ስለሚችል ሊያስጨንቃችሁ ስላልፈለገ ይሆናል መልዕክት የተወላችሁ!አየሩስ ነበረች!
መልስ ልሰጣት አልቻልኩም! ምን አይነት ምላሽ ልሰጣትስ እችላለሁ? በወቅቱ አልነበርኩ ሰዉ ስላልነበረበት ሁኔታ እንዴት በእርግጠኝነት መናገር ይቻለዋል?
ደ.ክ.ሞ.ኛ.ል! በህይወቴ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ችግሮች አድክመዉኛል! አልኳት! እንባዬ ያለ ከልካይ ይወርድ ስለነበር ሁኔታዬ እየሩስን አሳዘናት የተወሰነ እረፍት እንዳደርግ ከአልጋ ዉስጥ አስገብታኝ
አንድ ሁለት ቀናትን እዚህ እናሳልፍና ወደ ጅማ አብረን እንሄዳለን! አሁን ግን ተረጋግተሽ እረፍት ማድረግ ይኖርብሻል! ብላ ተሰናብታኝ ወጣች!
እኔ ቀጥ ብዬ መቆም ስፈልግ ህይወት ታንገዳግደኛለች! ይነጋል ሰዉም አብሮ ከንጋቱ ጋር ይነቃል፤ይመሻል ሰዉም አብሮ ከምሽቱ ጋር ይተኛል!... ህይወት በድግግሞሿ ዉስጥ የሰዉን ልጅ አቅፋ ትሽከረከራለች... የሰዉ ልጅም በህይወት አዙሪት ዉስጥ ይዞራል! ድካም...ለቅሶ...ሀዘን...ተደራርበዉ ለእንቅፍ አሳልፈዉ ሰጡኝ... ሽልብ አደረገኝ...

ይቀጥላል...



📚

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➑



...🖊መሸትሸት ሲል ከእንቅልፌ ነቃሁ እየሩስ ከአጠገቤ ጋደም ብላለች። ስልኬ ላይ አምስት ሚስኮል አገኘሁ ሁለቱ የእናቴ ሲሆን የተቀረዉ አዲስ ቁጥር ነበር በቀጥታ ወደ እናቴ ደዉዬ ስለ አባቴ አዲስ ዜና ካለ ጠየኳት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ በሀዘን ተዉጣ ነገረችኝ እኔም እሷን ትቼ አዲስ አበባ ብዙ መቀመጥ እንደማልችል እንደዉም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ወደ ጅማ እንደምመለስ አሳምኛት ስልኩን ዘጋሁት።
...ምሳ እንኳን አልበላሽም አሁን ተነሺና እራት እንብላ
ይቅርብኝ አራበኝም! ...ይልቅ ነገን እዚህ አሳልፌ ከነገ ወዲያ መመለስ ይኖርብኛል አብረን እንሄዳለን?
እየሩስ ሀሳቤን አልተቃወመችኝም። ስልኬ ላይ ወዳገኘሁት አዲስ ቁጥር ደወልኩ አቤል ነበር ድምፁን ስስማ ልቤ ድንግጥ አለ! ልክ እንደተማረከ ወታደር ለምን የልቤን እንደምናዘዝለት ባላዉቅም አዲስ አበባ ከደረስኩ በሗላ የገጠመኝን ሁሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኩት!
ከቻልሽ ነገ ላግኝሽ እኔ ጋር የረሳሽዉ እቃ አለ አለኝ!
ግራ ገባኝ እስከማስታዉሰዉ ድረስ እሱ ጋር የረሳሁት ምንም ነገር የለም ቢሆንም ነገ ከእየሩስ ጋር ትኬት ለመቁረጥ ወደ መስቀል አደባባይ እንደምንመጣና በዛዉ ላገኘዉ እንደምችል ነገርኩት የሚሰራበት ቦታ ቦሌ አካባቢ እንደሆነ ነግርኝ እሱ ያለበት ቦታ ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ። እየሩስ እራት እንድበላ ብታስጨንቀኝም ፍቃደኛ ልሆንላት ስላልቻልኩ እሷ ጋር ያለዉን ለእኔ እኔ ጋር ያለዉን ደግሞ ለእሷ እያጫወትኳት እንቅልፍ ወሰደን... እንደሌላዉ የሀምሌ ቀን ዝናብ ያስጨነቀዉ ሳይሆን ቀለል ያለ ብሩህ ጠዋት ነበር ከእየሩስ ጋር አርፍደን ተነሳን ጥሩ ቁርስ...የሚገርም ምሳ...ቤተሰባዊ መስተንግዶ ስለተደረገልኝ በትንሹም ቢሆን ሀዘኔን ቀለል አደረገዉ።
ወደ ጅማ የምንሄድበትን የጉዞ ትኬት አክስቴ ከምትደክሙ ብላ ሰዉ አስልካ አስቆረጠችልን። ሲኒማ ፊልም ልናይ ነዉ በሚል ሰበብ ከእየሩስ ጋር 11:30 ላይ ተያይዘን ወጣን! ለአቤል ደዉዬ እየመጣሁ እንደሆነ ስነግረዉ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ አሳወቀኝ ስደርስ እንደምደዉል ነገርኩት...
እየሩስ ምናልባት ብቻሽን ሊያገኝሽ አስቦ ይሆናል እኔ እዛዉ አካባቢ ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ልቆይና ስትጨርሺ አብረን እንመለሳለን አይሻልም? አለችኝ!
ልቤን ፍርሀት... ፍርሀት እያለዉ እሺ አልኳት...

ይቀጥላል...



📚

https://t.me/Write_Event
​​​​💔የባከነች_ነብስ💔


ክፍል_➒

...🖊አቤል የሚሰራበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫና መጠገኛ የሆነዉን ሱቅ አስጎበኘኝ ሱቁ የታላቅ ወንድሙ እንደሆነ ነገር ግን ከጅማ ድረስ እየመጣ ለመቆጣጠር ስለማይመቸዉ እሱ በሀላፊነት እንደሚያስተዳድርለት ነገረኝ።
ሱቁ አነስ ያለ ነገር ግን በርካታና ጥራት ያላቸዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለዓይን በሚማርክ ሁኔታ ተደርድረዉበታል የሱቁን ጉብኝት እንደጨረስን እራት እንድንበላ ጠየቀኝ ብዙ ማምሸት እንደማልችልና ነገ ተጓዥ ስለሆንኩ በጊዜ ገብቼ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ አስረዳሁት
ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ! ተረጋግቼ ላወራሽ የምፈልገዉ ነገር ስላለ ነዉ?
ሰዉን ቶሎ ከሚያምኑት ወገን ባልመደብም ብቻ አቤል ምን አይነት አስማት እንዳለዉ አልገባኝም ልቃወመዉ አልቻልኩም። ከሱቁ ወጥተን እዛዉ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ ተለቅ ያለ ሆቴል ገባን! ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮ ስለነበር በተለያዩ አይነት ከለር ብልጭ ድርግም የሚሉት መብራቶች ለስለስ ብሎ ከሚንቆረቆረዉ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ጋር ተዳምረዉ ለሆቴሉ ልዩ ዉበት አጎናፅፈዉታል። እኔና አቤልን ለተመለከተን በፍቅር ረጅም ጊዜ ያሳለፉ ጥንዶች እንጂ በጣት የሚቆጠር የትዉዉቅ ቀናቶች ያለን አንመስልም። በእኔ ምርጫ ብሎ ከታዘዘዉ የበግ ጥብስ ላይ ደጋግሞ አጎረሰኝ ለሴት ልጅ ያለዉ አክብሮትና ጨዋታ አዋቂነት አቤልን ያለ ምንም ፍርሀት ግልፅ ሆኜ በነፃነት እንዳወራዉ እያደረጉኝ ነዉ! የመጠጥ ተጠቃሚ አለመሆኑን ነገር ግን ይህ ምሽት ያለ ወይን አይደምቅም ብሎ ወይን ታዘዘ! በሁለታችንም ብርጭቆ ልዩ ስሜትን በሚሰጥ እርጋታ ወይኑን ቀዳዉ
እንግዲህ እኔ ጋር የረሳሽዉ...ንግግሩን እንደጀመረ ስልኬ ጠራ እየሩስ ነበረች አቤልን ይቅርታ ጠይቄ ላናግራት ወደ መፀዳጃ ሄድኩ ከ30 ደቂቃ በሗላ እንደምጨርስ ነግሬያት ተመለስኩ
ለጥሩ ምሽታችንና እኔ ጋር ለረሳሽዉ ነገር ፅዋችንን እናንሳ! እሱ ጋር ምን ልረሳ እችላለሁ? ዉስጤ የበለጠ ለማወቅ ስለጓጓ ብርጭቆዉን አንስቼ ተጎነጨሁ አቤል ምን እንደሚያወራ ባይገባኝም የሆነ ነገር ያወራልኛል ምስሎች ብዥዥ...ብዥዥ... እያሉብኝና የእንቅልፍ ስሜት ሲጫጫነኝ ይታወቀኛል
...ጠዋት እራሴን ከማላዉቀዉ ክፍል አልጋ ዉስጥ አገኘሁት ፊት ለፊቴ ካለዉ ወንበር ላይ አቤል ሲጋራ እያጨሰ ነበር መንቃቴን ሲመለከት ከት ብሎ ሳቀብኝ
ወፏ ወደ ወጥመዷ ገብታለች! አለኝ የማየዉ የምሰማዉ ህልም እንጂ እዉነት አልመስልሽ አለኝ
የት ነኝ? አልኩት
ሲኦል

ይቀጥላል...



https://t.me/Write_Event
" የወንድ ልጅ ህይወት ባለ አራት ተቃራኒ ግድግዳዎች ነው ። "
" ግድግዳዎቹም እናት ፣ ሚስት ፣ ሴት ልጅና እህት ናቸው ። ያደለው ወይም ያወቀበት ወንድ እነዚህን ሳጋ ፣ ማገር ፣ ቱሻ ፣ ልጥፍ ፣ ልስን ....... የማይሉ ግድግዳዎች ላይ ጣሪያ መክደን ብቻ ባለ ጎጆ ያደርገዋል ።


" እንግዲህ ወንድ ልጅ እዚህ ጎጆ ውስጥ አራቱን ግድግዳዎች የሚያቻችል የአማካኝ ተክል ምሰሶ እንጂ ነዋሪ አይደለም ። እናት ወደ ዘላለማዊ ልጅነት ትጎትተዋለች። ወንድ ልጅ በጉተታው አማካይ ሥፍራን መሳት የለበትም ። ሚስት ደግሞ የተዋጣለት ባል እንዲሆን ወደ እራሷ መሳቧ አይቀርም ። አሁንም እዛው ላይ ሆኖ የሚስቱ አሳሳብ ከመጠን እንዳያልፍ መቋቋም ነው ። ሴት ልጅና እህትም በየፊናቸው ወደ አባትነትና ወንድምነት ይስባሉ " ሐይ " ሳይባሉ ለአሳሳባቸው በልዝብ መልስ መስጠት ተገቢ ነው ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አለማየው ገላጋይ ( ኩርቢቷ )

ገፅ 102 - 03
"እውቀት ማለት ቦንብ መስራት መቻል ሲሆን ጥበብ ማለት ደግሞ ቦንብን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው"
ሰዎች እያወሳሰብዋት እንጂ ህይወት ቀላል ናት...ሰዎች በጨለማ ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሻማ ቢለኩሱ ለጨለማ ችግራቸው በቀላሉ መፍትሄ ያገኛሉ።

ኮንፊሺየስ
የደራሲ ቤት ፤ ገነት ቅብ ሲኦል ነው።


የደራሲነት እውነት ከሆድ ና ከጭንቅላት ፣ ከጉስቁልናና ከድሎት ፈንቅ አይል ይሁን ? ለሎች አማራጮች ፈለግን። አሁንም ዞሮ ፀጋዬ ገብረመድህን አገኘን ። ፀጋዬ "ሕሊና" መፅሔት ላይ የደራሲን እውነት ከባቢያዊ አድርጎት አገኘን ። እንድህ ይላል ።

"ህዘብ መካከል ሆነህ ነው ስለ ህዝቡ የምትፅፈው ፣ የሕዝቡ ሙቀት ካልሞቀህ ፣ በሕዝቡ ህዝባዊነት ውስጥ ካልታቀፍክ የሱን ህይወት አትተረጉምም። ስለዚህ ብዙ የብዕር ሰዎች ፣ እንደ ምሳሌ የአሁኑን ትልቁ የሩሲያ ደራሲ ሶልዘንሂትሲንን እንመልከት ፣ የታል የምፅፈው ? መሞት መጀመር ማለት እኮ ነው ከሀገር ሕዝቦች አካል ውጭ ከተለየ በኋላ ፣ የሕዝብን ሳቁንና ብሶቱን ለመካፈል ከማትችልበት ርቀት ትዝታህ ሁሉ ይተንብሀል፣ እሰው በር ላይ ተቀምጠህ ምን ትፈጥራለህ? አጥንቴ የህዝቦቼን ሙቀት ተመግቦ ያደገ ስለሆነ አፍሪካዊ ሙቀቴን እንዳጣ አልፈልግም ፣ በረዶም አልወድ ፣አለም ካደነቀው ጠንካራው የኢትዮጵያ ባህል መለየትም ለእኔ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። እርሱን ደካማ አድርጎ የማቅረብ ቅጥረኝነት ነው። ያኔም ብዕሬን ካገር ለማራቅ የተወጠነብኝ ።ደስቶየቭስኪ ካገሩ ሲወጣ ነው የብዕሩ ሞት የተቃረበው ።

ለፀጋዬ ህዝብ ባህር ነው። ደራሲ ደግሞ የባህር ውስጥ ነዋሪ ፍጡር፤ ያለ ባህር የባህር ነዋሪ ምን መጠጊያ አለው? ይሄን ይዘን ወደ ፀጋዬ ገብረመድህን ህይወት ና ሥራ ጎራ ካልን በግብርም ተተርጉሞ እናገኘዋለን ። የፈራው እና የጠላው የበረዶ አገር፣ ኑሮውን አበድኖበት ይማረር ነበር። አሜሪካ ብሮንክስ ኒውዮርክ ተቀምጦ ልቡና መንፈሱ ግን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ላይ ይንሳፈፍ ነበር ። ሥራው ግን እዚህ እንደነበረበት ዘመን አልሰላለትም። ንግግሩ በተሃ ፣ ግጥሙ ዘገባ ሆኖ ነበር ።

ዛሬ የዶላሩ ብድር ባፋቸው ገብቶ ልጓሙ
ይኸው በአዲስ ግዳጅ ፍቅር፤ወንድማማቾች ተሳሳሙ
የሚል ዜና አስታራቂዎች፣ በአለም ነጋሪት ቢያሰሙ
እኔም ቴሌግራፍ ደብዳቤ ፣ ለወንድሞች ለማቀበል...

አሁን ይሄ ምኑ የፀጋዬ ግጥም ይመስላል ? በእርግጥም እንዳለው ከሀገር መውጣቱ ሥራውን ነጥቆታል ። ይሁንና ጉዳዩ የሁሉም ደራሲዎች እውነት አይደለም ። ለምሳሌ አዳም ረታ፣የፀጋዬ ተቃራኒ ደራሲነቱን እንደሚያሰላው ይናገራል ። ለአዳም ሀገር እንደ ተራራ ነች። ካልራቋት እራሷ ላይ ሆነው ምኗም የማይታይ "ተራራኮ ቁልጭ ብሎ የሚታይህ ስትርቅ ነው" ይላላ።

ይሄን ጊዜ ነው ኦ! የደራሲ እውነት ከወዴት ነሽ? ማለት

ገፅ 166-167
መፅሐፍ -መለያየት ሞት ነው
ደራሲ-አለማየሁ ገላጋይ
​​​​💔የባከነች_ነብስ



ክፍል_➓

...🖊ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር! የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል! አለኝ
የምን ቀብር?...

ይቀጥላል...

Share ማድረግ አትርሱ💛🙏 !

https://t.me/Write_Event