ቃላዊ
346 subscribers
39 photos
5 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ክፍል 6⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

*ከሶስት ወራት ቡሀላ*
ፊርዱ ከሶስት ወር በፊት በደረሰባት ከባድ የመኪና አደጋ ሆስፒታል አልጋ ከያዘች ድፍን ሶስት ወራትን አስቆጥራለች።
ፊርዱ እህት ወንድም እንዲሁም ቤተሰብ የላትም የምትኖረው አክስቷ ቤት ነበር ብዙ ምቾት ባይኖረውም ምርጫ ስላልነበራት እና ሌላ የምትሄድበት ዘመድ ስለሌላት እዛ መኖሯን ከቅርብ ጓደኛዋ ሪሀና ሰምቻለው አክስቷ ብዙም እየመጡ አይጠይቋትም ቢሆንም ግን እኔ አንድም ቀን ከጎኗ ርቄ አላውቅም በርግጥ ሀምዛና ሪሀናም ከስራ እረፍት በሆኑ ሰአት ከኛ ጋር ናቸው። እኔ እንደሆንኩ ውሎዬም አዳሬም ሆስፒታል ከሆነ ሶስት አስቀያሚ ወራትን አስቆጥሪያለው ለምን እንደሆነ ለራሴም በማይገባኝ ሁኔታ ዛሬ ላይ ከማላውቃት ሴት ጋር ሆስፒታል ውስጥ ራሴን አጊኝቼዋለው። በሱም ደግሞ በጣም ደስተኛ ነኝ አይኗን ገልጣ የምታየኝና የማያትን ቀን በጉጉት ጥበቃ ላይ ነኝ። በጣም ነው ምታሳዝነኝ። እጇን እንደያዝኩ ይመሻል ይነጋል።
ጥዋት ላይ ሀምዛ ከእንቅልፌ ቀስቅሶኝ
"ብሩኬ ቁርስ አምጥቼልሀለው ስራ እንዳይረፍድብኝ አንተ ብላ እኔ ልሂድ" አለኝ
"እሺ ወንድሜ በጣም አመሰግናለው" ብዬው ፊቴን ለመታጠብ አብረን ወጣን። እሱን ከሸኘው ቡሀላ ፊቴን ታጥቤ ወደ ፊርዶስ አመራው እኔ ስደርስ ከነርሷ ጋር በር ላይ ተገናኘን ፊቷ ላይ የሚነበበው ነገር ደስ አይልም ብቻ ግን ምንም አላለቺኝም ዝም ብላ መንገዷን ቀጠለች። ደንግጬ ስለነበር ወደ ክፍሉ በፍጥነት በሩን ከፍቼ ገባሁ ነገር ግን ምንም አዲስ ነገር የለም። ተቀመጥኩና የፊርዱን እጅ ያዝኩት በጣም ያቃጥላል ቀና ብዬ ሳያት ፊቷን ላብ አጥምቋታል
"ነርስ! ነርስ! " እያልኩ በጩኸት ከክፍሉ ወጣው ወዲያው ነርሶቹ መጡና እኔን ውጪ እንድቆይ ነግረውኝ ተንጋግተው ውስጥ ገቡ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ ፊርዱ በሶስት ወሯ ያሳየችው አዲስ ነገር በጣም አሳሰበኝና ለሀምዛ ደወልኩለት ብዙም ሳይቆዩ ሀምዛና ሪሀና አንድ ላይ መጡ። ገና ከመምጣታቸው ጥያቄ ማብዛት ጀመሩ
"ምንድነው የተፈጠረው ብሩክ" አለች ሪሀና እጇን እያወናጨፈች
ሀምዛም በመቀጠል "ምንድነው ብሩኬ ንገረን እንጂ" ይለኛል መናገር ፈልጊያለው ግን ውስጤ ድክምክም አለብኝ እያየዋቸው ብዥዥ ይልብኛል በመሀል ድምፃቸው አልሰማ አለኝ። በስተመጨረሻም ራሴን ስቼ ከወደኩ ቡሀላ ያለውን ነገር አላስታውስም ስነቃ ራሴን አልጋ ላይ ከተሰካልኝ ግሉኮስ ጋር አገኘሁት ቀና ስል ሀምዛ በንዴት ሲመለከተኝ አስተዋልኩት ለመነሳት እየሞከርኩ"ልደበድበኝ ነው እንዴ?" አልኩት
"ቀልድህን አቁም ለምንድነው ራስህን የምትጥለው ምግብ ለምን አቶስድም ቆይ መሞት ነው እንዴ የምትፈልገው?" አለኝ በጣም እንደተናደደ ፊቱ ያሳብቅበታል
"እሱን ተወውና ስንት ሰአት ነው የተኛሁት?" አልኩት
"ትላንት ካሸለብክ ዛሬ መነሳትህ ነው ዶክተሩ ምግብም ሆነ ፈሳሽ ስለማይወስድ ነው ብሏል ባንተ ቸልተኝነት ምክንያት ይኸው እኔንም ከስራ ልታስባርረኝ ነዉ" አለ ምርር ብሎት
"ይቅርታ ሀምዚ እንዲ እንዲፈጠር ፈልጌ ያደረኩት ምንም የለም" ካልኩት ቡሀላ ፊርዱ ትዝዝዝዝ አለቺኝ የኔ ምስኪን እንዴት ሆና ይሆን? ሀምዛን ስጠይቀው ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ አክስቷም መጥታ አይታት እንደሄደችና እሷም እንዳልነቃች ነግሮኛል ግን ሳላያት አልዋጥልህ አለኝ ግን ደግሞ እኔም ለትንሽ ሰአት ማገገም ስላለብኝ ካለሁበት ክፍል ለመውጣት ተከለከልኩ። ግሉኮሱን እንደጨረስኩ ራሴን ማንቀሳቀስ ጀመርኩ ውስጤ ቢደክምብኝም በድጋሚ እሷጋ ከመሄድ እንዳያስቀሩኝ ብዬ እንደምንም ጤነኛ ለመምሰል ሞከርኩና ሀምዛ ወደሷ ወሰደኝ እና ስራ ስላለበት ማታ እንደሚመለስ ነግሮኝ ሄደ።
ገና ሳያት ደስ ይለኛል ደሞ አይኗን ስትጨፍን በጣም ውብ ናት ቅላቷ ፣የቅንድቦቿ ጥቁረት፣ የፊቷ ጥራት፣ የፀጉሯ ልስላሴ ብቻ ብዙ ልገልፃቸው በማልችላቸው ውበቶቿ ተደምሜ ፍዝዝዝዝዝዝ አልኩ።

ክፍል 7⃣
ይቀጥላል
◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━


┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 7⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ቀኑ እንዴት እንደመሸ ሳላውቀው ፀሀይ ለጨረቃ ቦታዋን ለቃለች። ፊርዱ ከተኛችበት ክፍል ወደ መፀዳጃ ሄድኩኝ በዛው ለሀምዛ ስደውልለት መምጣት እንደማይችልና ነገ በጥዋት እንደሚመጣ ሪሀናም ስራ አዳሪ እንደሆነች ነግሮኝ ጥዋት ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋሁና ወደ ውዴ ክፍል አቀናሁ።
በሩን ከፍቼ ልገባ ስል የለቅሶ ድምፅ ተሰማኝ ፊርዱ ነቃች ብዬ ተጣድፌ በሩን ከፈትኩት አንድ ከዚ በፊት ያላየሁት ሰው ነበር የፊርዱን እግር ይዞ ከድምፁ ጋር እየታገለ ያለቅሳል። መግባቴን አላስተዋለም አንገቱን ደፍቶ ማልቀሱን አላቋረጠም። መኖሬን ለመናገር ጉሮሮዬን ጠራርጌ ድምፄን አሰማሁ። ነገር ግን ቀና ሊል አልቻለም። አለቃቀሱ ደሞ በጣም ያሳዝናል ግን ማነው? እንዴት እስከዛሬ አላየሁትም? ጥያቄን በጥያቄ ማከታተሌን ትቼ ቀና እንዲል በማሰብ በሩን አንኳኳሁት ቀና አለና አየኝ እኔም አየሁት መልኩ ሊመጣልኝ አልቻለም ከተንበረከከበት ተነስቶ እምባውን እየጠረገ ወደኔ መጣና ጥብቅ አድርጎ አቅፎኝ "በጣም አመሰግናለው በጣም" አለኝ ግራ ገባኝ ምን ማለት ነው አመሰግናለው አልኩኝ ለራሴ እንደምንም አረጋጋሁትና "ምኗ ነህ?" አልኩት በጥርጣሬ አይን እየተመለከትኩት " በቅርቡ ነው ከውጪ የመጣሁት እጮኛዋ ነኝ በዚ አመት ልንጋባ ነበር ግን ምን ያደርጋል" አለኝና መንሰቅሰቅ ጀመረ። የሆነ ነገር ውስጤን ውርር ሲያደርገኝ ይታወቀኛል በንዴት ከላዬ ላይ ምንጭቅ አድርጌ አላቀኩትና
"የማን? የኔዋ ፊርዱ እጮኛ ነኝ ነው ምትለው? እ ማን ነህ አንተ? እስከዛሬ የት ነበርክ?" ብዬ አፈጠጥኩበት እሱም ግራ ገብቶት ይመለከተኛል በመሀል የፊርዱ እጆች ተንቀሳቀሱና ሁለታችንንም ወደሷ እንድንሮጥ አደረጉን በግራና በቀኝ እጆቿን ይዘን መፋጠጥ ጀመርን ከብዙ እንቅስቃሴዎች ቡሀላ የኔ ልዩ አይኗን ወደ ማላውቀው ሰው ዞራ ከፈተች ገና እንደተያዩ ሁለቱም ማልቀስ ጀመሩ እጄን ለቀቀችኝና አይኔ እያየ ሁለቱንም እጆቿን ለሱ ሰጠችው በተደጋጋሚ ከሱ የምሰማው ቃል " በጣም ይቅርታ እናቴ" የሚል ነበር ከሷ አንደበት ግን አንድም ቃል አሎጣም ዝም እንዳለች ማልቀስ ብቻ አንዴም እንኳን ሳታየኝ ነርሶቹ መጡና ሁለቱን በመከራ አላቀው እኔን ገፍተር አርገው እሱን በትግል ከክፍሉ አሶጡን።
ምን እንደሚሰማኝ ማወቅ አልቻልኩም እሷን የተነጠኩ መሰለኝ እምባዬ ዝም ብሎ ይፈሳል ዝርግፍግፍ ብዬ የኮሊደሩ በረንዳ ላይ ተሰጣው ማመን አልፈለኩም ሁሉም ነገር ህልም ቢሆን ብዬ ተመኘው እንደምንም ቀና ብዬ ሳየው ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አንገቱን አቀርቅሯል እነቀው እነቀው አለኝ በደመነፍስ ከተዘረጋሁበት ተነስቼ ወደሱ አመራሁ ባለ በሌለ ሀይሌ አንገቱን አነኩት እና
"እንዳታስበው እሺ ፊርዱ የኔ ብቻ ናት!" አልኩት ግራ ተጋብቶ ዝም ብሎ ያየኛል በመሀል ዶክተሮቹ አላቀቁንና ህመምተኛ የምንረብሽ ከሆነ እንደሚያሶጡን ነግረውን ሄዱ እልህ ቢይዘኝም ፊርዱን ለሱ ትቼ መሄድ አልፈልግምና ንዴቴን አምቄ ዝም ብዬ ተቀመጥኩኝ ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ የፊርዱ ክፍል ተከፍቶ ነርሶቹ መውጣት ጀመሩ ሁለታችንም ተሽቀዳድመን ከበብነቸውና ስለሷ ጠየቅናቸው ለጊዜው መናገር እንደማትችልና ለማዋራት እንዳንሞክር አስጠንቅቀው ነገሩንና ፊርዱ የፃፈችውን ወረቀት አሳዩን ሙባረክ ይላል ፅሁፉ በፍጥነት "እኔ ነኝ" አለ እጮኛ ነኝ ባዩ "ለጊዜው አንተ ብቻ እንድትገባ ነው የተፈቀደው አንተኛው እዚ ቆይ" አሉኝ ነርሶቹ
እሱም ዘሎ ገባ እኔም ሆድ ይፍጀው ብዬ ራሴን እያረጋጋው ቀጣይ የሚፈጠረውን ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ ከለሊቱ 9:20 ይላል የእጄ ሰአት ከክፍሉ ግን የሚወጣ ሰው የለም እዛው በተቀመጥኩበት እንቅልፍ አሸለበኝ.........


ክፍል8⃣
ይቀጥላል
◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━

┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 8⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ሀምዛ ዝም ብሎ ይጨቀጭቀኛል ለሱ ምላሽ መስጠት አልፈለኩም አንድ ነገር ለማለት በሞከርኩ ቁጥር እምባ እየቀደመኝ ተቸገርኩ አንዳንዴ ህመማችንን መግለፅ ሲያቅተን ዝምታን እንመርጣለን እንዲሁም መረዳት እየቻለ መረዳት የማይፈልግም ሰው ሲገጥመን ያለንን አቅም ለማስረዳት ከማባከን እንቆጠባለን በቃ በኔ ስሜት ውስጥም የሆነው ይህ ነው ሀምዛ ሁሉንም እያወቀ ላለመረዳት ሲል ብቻ ሁሉንም ጥለን እንድንሄድ ከጥዋት ጀምሮ ይነዘንዘኛል። የምሰማውን እንዳልሰማሁ ሆኜ እያለፍኩት ነው የማታ አዳሬን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ለነገሩ በሱም አይፈረድም ውስጤ ምን ያክል በፍቅሯ እየነደደብኝ እንዳለና ለምን ስለሷ ሳላውቅ ይሄን ያክል እንዳፈቀርኳት አለማወቄን እንዴት ሊረዳኝ ይችላል ህመሜን በውስጤ አምቄ ዝም ማለቴንስ እንዴት ይገባዋል። በኔ ጫማ እስካልተራመደ ድረስ በጫማዬ ቀዳዳ በኩል እያለፉ ስለሚወጉኝ እሾኮችና እየረገጥኩ ስለማልፋቸው ጠጠሮች ሊረዳኝ አይችልም።
በዚ መሀል አንድ ሀሳብ ብልጭ አለብኝ ቀጥታ ወደሪሀና ዞሬ አፈጠጥኩባት የደነገጠች ትመስላለች አይታኝ በሀፍረት አንገቷን ሰበረች። ዝም ልላት አልፈለኩም
"ታውቂ ነበር አይደል?" አልኳት በጥርጣሬ አስተያየት እያየዋት
"ብ ብ ሩ ኬ አንተ እንዳሰብከው አይደለም" አለች እየተርበተበተች
"ምኑ ነው እኔ እንዳሰብኩት ማይሆነው! እ ንገሪኛ ሁሉንም እያወቅሽ የጓደኛሽን ጊዜያዊ ክፍተት እንድሞላ ለምን አደረግሽ!!? ለምንድነው ይሄን ድራማ መጫወት የፈለግሽው? እ ንገሪኛ" ብዬ ራሴን መቆጣጠር እስኪሳነኝ ድረስ ጮህኩባት ሀምዛም እስካሁን አላሰበውም መሰለኝ ይህን ሀሳብ ካነሳሁ ቡሀላ መሀል ከመግባት ይልቅ በግርምት የሚፈጠረውን መከታተል መርጧል።
" እየውልህ ብሩክ ተረጋጋና ሁሉንም ላስረዳህ" አለች ሪሀና እጄን ይዛ ልታስቀምጠኝ እየሞከረች ይበልጥ ተናደድኩባት ብሰማት ጥፋቷን ላለማመን ስትል ሌላ የውሸት ታሪክ የምትፈጥር መሰለኝ ብቻ አፌ ላይ የመጣልኝን ቃል " አስመሳይ" ብቻ ብያት ከሆስፒታሉ መውጣት ጀመርኩ ሀምዛ እየተከተለ ይጠራኛል ሪሀና ግን እዛው በቆመችበት አፏን እንደያዘች ያን የሶስት ወር ምሽጌን፣ ያን የፍቅሬን ገነት፣ ያን መኖሬን የረሳሁበትንና፣ ብዙ የሆንኩበትን ሆስፒታል ለቅቄ ወጣው።
ገና እግሬ ውጪውን ሲረግጥ ዳግም እንደማልመለስ ውስጤ ሹክ አለኝ እምባዬ ሲመጣ ደግሞ ሶስት ወር ሙሉ የረሳሁት ወንድነቴ ትዝ አለኝ በራሴ ተገርሜ ፈገግ አልኩኝና እምባዬን ዋጥ አድርጌ መንገዴን ቀጠልኩ።
ሁሌም ቢሆን ለነገሮች ጥያቄን የማያጣው ሀምዛም ዝምታዬን ተጋርቶኛል። በዝምታ ውስጥ እንደሆንን የሀምዛ ቤት ደረስን። ቁልፉን መክፈት ሲጀምር ብቻዬን መሆን እንደምፈልግ ነግሬው ልሄድ ስል እሱ ሚሄድበት እንዳለ ነግሮኝ ከፍቶ አስገባኝና ከፈለኩት እንድደውልለት አዞኝ ሄደ።
አልጋው ላይ ጋደም ብዬ አይኖቼን ጨፈንኳቸው እያንዳንዱ ነገር አንድ በአንድ ይታወሰኝ ጀመር የበፊቱ ማንነቴ ፣ፊርዱን ሳላውቃት በፊት የነበረኝ ሰላምና መረጋጋት፣ ያወኳት ቀን የተሰማኝ እንግዳ ስሜት፣ የቀጠሮው ቀን፣ ከአደጋው ቡሀላ ፊርዱን እያየው ያሳለፍኳን እያንዳንዷ ለሊት፣ ቀስ በቀስ መልኩን የቀየረው ፍቅሯ ብቻ ሁሉም ነገር ትንሽ ፈገግ አልኩኝ መልሼ ደግሞ ሁሉም ነገር ገደል ሲገባ ተሰማኝ ሁሉንም ነገር መተው እንዳለብኝ ልቤን ማሳመን ጀመርኩ ፊርዱን ልተዋት፣ ውዴን ልረሳት፣ ከሂወቴ ላሶጣት አቀድኩ መወሰን ልቻል አለመቻሌን ሳላረጋግጥ ብዙ እቅዶችን አቀድኩ........

ክፍል 9⃣
ይቀጥላል

┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 9⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሳምንታትን ማስቆጠር ጀምረዋል ባዲስ መንፈስ ወደስራዬ ከተመለስኩ አራተኛ ቀኔን አስቆጥሪያለው። ጥዋት ወጥቼ ራሴን በስራ ጠምጄ ውዬ ማታ እገባለው። ስለፊርዶስ ከሰማው በጣም ቆየው ቢሆንም ግን ሁሌ አስባታለው ለሀምዛ እንደምረሳት ቃል ስለገባሁለት እሱ ፊት የረሳዃትና ደስተኛ የሆንኩ አስመስላለው ይሁን እንጂ ፊርዱ ለሰከንድ ከአይምሮዬ ጠፍታ አታውቅም ሁሌ አስባታለው በርግጥ ከነበረችበት ሆስፒታል አገግማ መውጣቷንና የአክስቷን ቤት ትታ ሙባረክ ጋር እንዳረፈች ከሪሀና ሰምቻለው ነገር ግን ሀምዛ ከሪሀና ጋር እንደምደዋወል አያውቅም ስልኳንም በድብቅ ነው ከስልኩ ላይ የወሰድኩት አላስችል ሲለኝ ስለደህንነቷ ደውዬ እጠይቃታለው ዛሬም ከስራ መልስ ልደውልላት አስቢያለው።
ምሳ ሰአት ደርሶ ስለነበር ከሀምዛ ጋር ምሳ ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ሄድን ምግቡን ካዘዝን ቡሀላ እስከሚመጣ ድረስ ሀምዛ የባጥ የቆጡን ይለፈልፋል በሱ ቤት እኔ እንዳይደብረኝና አሪፍ ሙድ ላይ እንድሆን በማሰብ ነበር ይህንን ማድረግ ከጀመረም ቆይቷል ነገር ግን እኔ ጋ ምንም አዲስ ነገር የለም ሊኖር የሚችለው ፊርዱ ስትኖር ብቻ ነው ያው ቃሌን ያከበርኩ ለመምሰል ያወራውን ሳልሰማ ሲስቅ ብቻ አብሬው እስቃለው ሀሳቤ ሌላ ጋር ቢሆንም ትኩረቴ እሱ ጋር ያለ አስመስላለው እሱም ብዙም አይጫነኝም ይሁን እንጂ ያ አሰልቺ የማያልቅ ጥያቄው ዛሬም ድረስ አለ ሁሌም ቢሆን ለሚወራው ነገር ጥያቄ አያጣም ምንም ባልመልስለትም ሲጠይቀኝ ገና ይደክመኛል።
በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ምሳችንን ከበላን ቡሀላ ወደስራ ገባን።
ከሰአት ቡሀላ አብዛኛውን ጊዜ ገበያ አይኖረንም ያው ተዘጋ ላለመባል ብቻ ሱቅ ውስጥ እንገኛለን። ሰአቱም ወደማምሻው እየተቃረበ ነው ፀሀይ ወደመግቢያዋ ተቃርባለች በጊዜ መግባት ስለፈለኩ ሱቁን ዘግቶ እንዲመጣ ለሀምዛ ነግሬው ጃኬቴን ደርቤ ከስራ ወጣሁ።
ስልኬ ካርድ ስላልነበረው አካባቢው ላይ ካገኘሁት ሱቅ ካርድ ገዝቼ ሞላሁና በቀጥታ ለሪሀና ደወልኩላት ነገር ግን ስልኳን አታነሳም ደግሜ ደወልኩ አሁንም አይነሳም እቤት ገብቼ እደውላለው ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ። ብዙም ሳትቆይ ሪቾ ደወለች አነሳሁት እና "ቅድም እኮ ስደውልልሽ አታነሺም በሰላም ነው?" አልኳት
"አዎ በሰላም ነው የት ነህ?"
"ከስራ ወደቤት እየገባሁ ነው ምነው"
" ምንም ሀምዛ አብሮክ አለ እንዴ?"
"እረ የለም እሱ ቆይቶ ነው ሚገባው ደግሞም በሱ ፊት እንዴት እደውላለው?"
"እሺ በቃ እቤት ስትገባ ደውልልኝ" ብላኝ ስልኩን ዘጋችው። ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ መልሼ ደወልኩላት ሳይነሳ ዘጋችው። ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እየጓጓው የእርምጃ ፍጥነቴን ጨምሬ እቤት ደረስኩ። እንደገባው ቀጥታ ደወልኩላት መስመሩ ተይዟል ይላል ስልኳ ጭንቅንቅ አልኩኝ መልሼ ስደውል አነሳችው
"ሄሎ ሪች"
" እ ብሩኬ ገባህ?"
"አዎ ምንድነው ቆይ?"
" መጀመሪያ ተረጋጋ ከዛ ዝም ብለህ አዳምጠኝ"
"ምንድነው እሱ ፊርዱ ደና አይደለችም እንዴ?"
" አዎ ህመሙ ትንሽ ስለባሰባት በድጋሚ ሆስፒታል ገብታለች"
" ምን! ቆይ የት ሆስፒታል ነው ንገሪኝ አሁኑኑ እመጣለው"
"አሁን መምጣት የለብህም ባይሆን ሌላ ቀን ሀምዛ ካወቀ ያዝንብሀል ተረጋግተህ እደር እኔ ያለችበትን ሁኔታ በየሰአቱ ቴክስት አረግልሀለው አትጨነቅ አሁን ስልኩን መዝጋት አለብኝ ደና እደር"
" ቆይ አንዴ ሄሎ.........ሄ ሄሎ" ዘጋችው።
ስልኩን እንደያዝኩኝ ፈዝዤ ቀረሁ ይሄ ነገር መቼ ነው ሚያበቃው? ብዬ ራሴን ጠየኩ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ፈጣሪ ግን ምን አድርጌው ነው ይሄን ያክል የሚቀጣኝ አልኩኝ
የማታውቀኝ ፍቅሬ በድጋሚ ታማ ሆስፒታል ነው ያለችው እኔ ደግሞ እቤት አልጋዬ ላይ ኡፍፍፍፍ እንዴት ይጨንቃል። በዚ ሁኔታ ውስጥ እንዳለው ሀምዛ መጣ ተነስቼ በሩን ከፈትኩለትና ገባ
"እራት በላህ? ወይስ ወጥተን እንብላ?" አለኝ ጫማውን እያወለቀ
"በልቻለው አንተ በልተህ ና" አልኩትና ፊቴን እንዳያየው ከፊቱ ዞር አልኩኝ
" እኔማ ቅድም የበላነው ራሱ አልተወራረደልኝም ግን አንተ ምን ሁነህ ነው ዛሬ ችግር አለ እንዴ?"አለኝ
ኤጭ ጀመረው ደሞ እያልኩኝ በውስጤ
" ትንሽ ራሴን አሞኝ ነው ስተኛበት ይተወኛል" አልኩት
ዝም አለኝና መሳቢያው ውስጥ የሆነ ነገር ማንኮሻኮሽ ጀመረ ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ " እንካ ይሄን ውሰድበት ይተውሀል" ብሎ ፓራሴታሞልና ውሀ ሰጠኝ ትቀበልኩትና ለማረሳሳት ያክል ስልኬን አቀብለኝ ብዬው ሲዞር ክኒኑን ኪሴ ውስጥ ከተትኩትና ውሀውን ጠጥቼ ብርጭቆውን ሰጠሁት " በል ተሸፋፍነህ ተኛ ነገ ካልተሻለህ ሀኪም ቤት እንሄዳለን" ብሎኝ ብርጭቆውን ሊመልስ ሄደ "ውይይይይይ ሀምዛ" እያልኩ ስልኬን አንስቼ ለሪቾ " አሁን እንዴት ናት" ብዬ ቴክስት አረኩላትና ቴክስት ስትልክ እንዳይሰማ ስልኬን ሳይለንት አደረኩት። ከደቂቃዎች ቡሀላ መለሰችልኝ " እስካሁን አልነቃችም ዶክተሮቹ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም መፍሰሱን ነግረውናል እና ቀዶ ጥገና ሊደረግላት ነው ከ 2 ሰአታት ቡሀላ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ያስገቧታል" አለቺኝ የምይዘው ጠፋኝ ፊርዱ አሳዘነቺኝ ይሄኔ ባንተዋወቅ ኖሮ ይሄ ሁሉ ነገር አይፈጠርም ነበር ራሴን አምርሬ ጠላሁት በሷ ቦታ እኔን ባረገኝ ብዬ ተመኘው ሁሉንም ነገር ጥዬ መጥፋት አማረኝ ግን ወዴት?
ለሪቾ "እባክሽ የሆስፒታሉን አድራሻ ንገሪኝ ነገ ልምጣ?"
ብዬ ፃፍኩላት እና ምላሿን መጠበቅ ጀመርኩ ነገር ግን ምንም ምላሽ የለም ለሊቱን ሙሉ ምላሿን ስጠብቅ አደርኩ።
ጥዋት ሀምዛን ስራ እንዳይረፍድበት ቀሰቀስኩትና ትንሽ ማረፍ እንደምፈልግ ነግሬው ለቦስ ትንሽ እንዳመመኝና የኔን ቦታ እንዲሸፍን አሳምኜው ወደስራ ላኩት። ገና እንደወጣ በቀጥታ ለሪቾ ደውልኩላት ብዙም ሳይጠራ አነሳችው
"ሄሎ ብሩክ አለች ሪቾ በደከመ ድምፅ"
" ሄሎ ሪች ፊርዱ እንዴት ሆነች?"
"አሁን ነቅታለች ግን ዶክተሮቹ የመዳን ተስፋዋ የመነመነ እንደሆነ ነግረውናል ሙባረክም ነገ ወደመጣበት ሀገር ሊመለስ ነው ብሩኬ ግራ ገብቶኛል" አለችኝ እምባ በተቀላቀለው የሲቃ ድምፅ
" እንዴት ማለት? ባክሽ ሲቀልዱ ነው ቆይ ድና አልነበር እንዴ? አትመኛቸው እነሱን ቶሎ ይሻላታል እመኚኝ". አልኳት ምን እንደማወራ እንኳን በቅጡ አላውቅም ብቻ በድጋሚ የሆስፒታሉን አድራሻ ስጠይቃት ልትሰጠኝ ፍቃደኛ አልሆነችም ግራ እየገባኝ ስልኩን ዘጋሁና እንደእብድ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ፊርዱ የኔ ምን ሆንሽብኝ? የኔ ንግስት ምን አገኘብኝ? ሳታውቂኝ ብዙ አወኩሽ ሳትነኪኝ ብዙ ዳበስኩሽ ሳታይኝ አፈቀርኩሽ ታድያ ምን አጥፍቼ ነው ጥለሺኝ ለመሄድ መንገድ የጀመርሽው? ማፍቀሬ ጥፋት ነበር እንዴ? አታደርጊውም! በጭራሽ አታደርጊውም እያልኩ በሚያቃጥል እምባ ብቻዬን ታጠብኩ ከአካሌ ላይ አንድ አካል የጎደለ መስሎ ተሰማኝ ሞት አሰኘኝ ከፊርዱ መቅደም አማረኝ ሌላ ምንም አልፈለኩም ይሄን የስቃይ አለም በራሴ ፍቃድ ልገላገለው ወሰንኩ ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ለልቤ ነግሬ ከውደኩበት ተነሳሁ......

ክፍል🔟
ይቀጥላል....

┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 🔟

ፀሀፊማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

አንድም ቀን እቅዴ ተሳክቶልኝ አያውቅም ደና ልገላገላት የነበረችውን አለም ሀምዛ በግድ እንድኖራት ፈረደብኝ ከሞት አፋፍ ላይ አስጥሎ ዳግም ወደ ህይወት አመጣኝ ደሞኮ የሚገርመኝ ሁሉንም ነገር እያየ የሚጠይቀኝ ነገር ነው። በጣም እንደተናደደብኝ ያስታውቃል እኔ ግን በስራዬ ቅንጣት ታክል ሀፍረትም ሆነ ስህተት የሰራሁ መስሎ አልታየኝም እንደውም ከሰአታት በፊት ለምን እንዳዳነኝ ተናድጄ ስጮህበት ነበር። ብቻ ሁሉም አለፈና የሚሰለቸው የሀምዛ ጥያቄ ጀምሯል
" ለምን እንዲ ማድረግን መረጥክ እኔንስ ለማን ትተህ ነው ይሄን የማይረባ ውሳኔ ልትወስን የቻልከው ቆይ እስኪ ንገረኝ ላንተ መሞት ቀላል ነው እንዴ?" አለኝ ሀምዛ በርግጥ ለአንዱም ጥያቄው መልስ አልነበረኝም "ቆይ አንተ ስራ አልነበርክ እንዴ እንዴት ልትመጣ ቻልክ?" አልኩት አጋጣሚው እየገረመኝ
" ከኔ ልትደብቅ ሞከርክ እንጂ ሁሉንም አውቅ ነበር ያላወኩ የመሰልኩት አንተን ላለማሳቀቅና ቢያንስ እኔ ጎን ስትሆን የረሳሀት መምሰልህ ትንሽ ሊጠቅምህ ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ነው እንጂ ሁሉንም ነገር አውቃለው ማታ ተኝተህ ስልክህን አይቼው ነበር ይሄን ልታስብ እንደምትችል ስለገባኝ ነው የተፈጠረውን ለቦስ ነግሬው የተመለስኩት" አለኝ ፊቱን ጭፍግግ አድርጎ
ምን እንደምለው ግራ ገባኝ " በጣም ይቅርታ ሀምዚ አንተ ትለያለክ" ብዬ አቀፍኩት
" ድጋሚ እንደዚ አይነት ነገር ብታስብ ቀድሜ ነው እሺ ምገልህ" ብሎ አሳቀኝ
በል አሁን ተነስ ፊርዱ ያለችበትን ሆስፒታል እኔ ስለማውቀው በቀጥታ መሄድ እንችላለን ብሎኝ ስልኬን ኪሴ ውስጥ ከተትኩና ወደሆስፒታሉ አመራን በመሀል ለሪቾ ደውለንላት ነበር ነገር ግን አታነሳም።
ሆስፒታል እንደደረስን ሂሳብ ከፍለን ከታክሲው ወረድንና ወደ ውስጥ አቀናን። የተኛችበትን ክፍል አጠያይቀን መግባት ጀምረናል ልክ ስንደርስ የፊርዱን አክስትና ሪቾን እያለቀሱ አገኘናቸው በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ "ምንድነው" አልኳት ለሪቾ ምንም ሳትመልስልኝ ከፊርዱ ክፍል ሁለት ዶክተሮች ወጡ በቀጥታ አጠገባቸው በመሄድ "ድናለች አይደል? እንውሰዳት?" እያልኩ ጥያቄን በጥያቄ ማከታተል ጀመርኩ
"" በጣም እናዝናለን ብዙ ሞከርን ግን ህይወቷን ማትረፍ አልቻልንም ፈጣሪ ብርታቱን ይስጣቹ"" አሉን ቀለል አርገውት የሰማሁትን ማመን ከበደኝ እግሮቼ መቆም አቃታቸው ተብረክርኬ ወደኩ ምንም የማለት አቅምን አጣው ብቻ ዝም ብዬ የሚፈጠረውን ማየት ብቻ ሆነ ስራዬ እምባዬም የት እንደገባ አላውቅም ድምፄም መውጣት አቃተው ዝምታን ለብሼ ዝምታን ጎርሼ እንደምንም ከወደኩበት ተነስቼ እግሬ ወደመራኝ አቅጣጫ መጓዝ ጀመርኩ ሀምዛ እጄን ይዞ ወደፊት መምራት ጀመረ እቤት አስገብቶኝ አጠገቤ በዝምታ ተቀመጠ እሱም ምን ማለት እንዳለበት ራሱ ግራ ሳይገባው አልቀረም ቀና ብዬ ሳየው ፊቱ በእንባ ታጥቦ ይመለከተኛል ከተቀመጥኩበት ወደ መሬት ዝርግፍ አልኩኝ ያኔ ነው እንባዬ የመጣልኝ እየጮህኩ እዬዬዬ ማለት ጀመርኩ አንዳንዴ አልቅሰን የሚድኑልን ህመሞች በማባበል ሊሽሩ አይችሉም ሀምዛም ለዛ ነው እንዳለቅስ የፈቀደልኝ አቅሜ እስኪዳከም ድረስ አለቀስኩ ማመን አለብኝ ግን ደሞ ይሄን ሊያምንና ሊቀበል የሚችል ጥንካሬ የለኝም ሁሉም አካላቶቼ አልታዘዝ አሉኝ ብቻ እዛው እንደተዘረገፍኩ መሸ ሀምዛ ደግፎ አልጋ ላይ አስተኛኝና የሚበላ ነገር ሊያመጣልኝ ሄደ።
ብዙም ሳይቆይ ምግቡን ይዞ መጣና መብላት እንዳለብኝ ደጋግሞ ማሳመን ጀመረ።
"በቃ ከዚ በላይ ማዘን የለብህም ፈጣሪ ያለው ነው የሆነው እንዲ ነበር የተፃፈው" አለኝ ሀምዛ
ምግቡን በሳህን እያቀረበ
አንድ ጉርሻ አንስቶ ወደኔ እጁን ዘረጋ ገና ምግቡን ሳየው አስጠልቶኛል እንኳን ልበላ ይቅርና ፊቴን በማዞር የመብላት ፍላጎት እንደሌለኝ ነገርኩት ሊጫነኝ ስላልፈለገ ውሀ ብቻ ጠጥቼ እንድተኛ አደረገ።
ቀናት ቀናትን እየወለዱ ፊርዱ ከዚ አለም ከተለየችና እኔም ካልጋ መነሳት ካቆምኩ ሳምንትን አስቆጠሩ ከቀናት ቡሀላ ሪቾ ልትጠይቀኝ መጣች ገና ሳያት እምባዋን ማፍሰስ ጀመረች ከራሴ እምባ ጋር እየታገልኩ "አታልቅሺ"ብቻ አልኳት ትንሽ ከቆየች ቡሀላ የምትሄድበት ቦታ እንዳለ ነገረችኝና ፊርዱ ከመሞቷ በፊት ለኔ የፃፈችውን ወረቀት ሰጥታኝ ተሰናብታን ሄደች።
ግራ ገባኝ ፊርዱ እኮ እኔን አታውቀኝም እንዴት ፃፈችልኝ ብቻ ጥያቄዬን አቁሜ ደብዳቤውን በፍጥነት ከፈትኩት ደብዳቤው እንዲህ ይላል

#ሰላም ላንተ ይሁን ብሩኬ......

ክፍል1⃣1⃣ እና የመጨረሻው ክፍል
ይቀጥላል.......

┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 1⃣1⃣
#የመጨረሻው_ክፍል

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ሰላም ላንተ ይሁን ብሩኬ እንዴት ነህ? እኔ እንኳን ስላንተ ከሰማሁ ቡሀላ ከበፊቱ ይልቅ ደህንነት እርቆኛል ምናልባት ሳላውቅ እንዳስቀየምኩህ አውቀህ ናፍቄህ ትመጣለህ ብዬ በር በሩን ሳይ ውዬ አድራለው። ያንተን ያህል ባይሆንም በስቃይ ውስጥ ሆኜም በብዙ አስቤሀለው። ይህንን ደብዳቤ እስከፃፍኩባት እለት ድረስ በይመጣል ተስፋ ስጠብቅህ ነበር ነገር ግን አንተ አልመጣህም የኔም ደህንነት ከቀን ወደ ቀን እየጠፋ ሄዷል።

ብሩክ ምናልባት ይሄ ደብዳቤ ቆይቶ ሊሆን ይችላል የሚደርስህ ቢሆንም ግን እንድታውቀው የምፈልገው ነገር አለ።
በርግጠኝነት አንተ ምታስበው የቀጠሮው ለት ወዳንተ ስመጣ ይሄ ሁሉ ነገር እንደተፈጠረ ነው አይደል?? ግን እንደዛ አይደለም ያንተን ቀጠሮ ሰርዤ የ ሙባረክን ቤተሰቦች ለማየት እና እኔ ጋር መልእክት ስለነበራቸው እሱን ላደርስ እየሄድኩ ነው አደጋው የደረሰው። ስለዚህ አንተ ራስህን እንድትወቅስ የሚያደርግህ ምንም ነገር የለም። ደሞ ሳልነግርህ ሙባረክ ማለት በቤተሰብ የተመረጠልኝ እጮኛዬ ነበር ነገር ግን አሁን የመጣው ባለበት ሀገር ሌላ ቤተሰብ እንዳለው ሊነግረኝ ነው። ለሱም ቢሆን እንዲ ስለሆነለት ፈጣሪዬን አብዝቼ አመስግኜዋለው ቢያንስ ቢያንስ በኔ ምክንያት ህይወቱ አይበላሽም ልክ ነኝ አይደል??

ደሞ ሪቾ ቀድማ ሁለንም ነገር ስላልነገረችህ እንደተናደድክባት ነግራኛለች። ሁሉንም ያልነገረችህ ላንተ አስባ ነው አትቀየማት እሺ
ሌላው ደግሞ አይኔን ሳልገልጥ ላደረክልኝ እና ለሆንክልኝ ነገር በጣም ነው ማመሰግነው ፈጣሪ ብሎ ድኜ ውለታህን መመለስ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ግን ያ የሚሆን አይመስለኝም እኔም ብሆን የመዳን ተስፋዬ ተሟጦ መሞቻዬን ቀን እየጠበኩ ነው።

ብሩኬ አንዳንዴ ይሆናል ብለን የጠበቅነው ፍፁም ተቃራኒው ሆኖ ስናገኘው የምንይዘው የምንጨብጠውን እናጣለን ሁሉም ውሸት ይመስለናል ግን እውነታው ይሄ ነው።

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው።

ከፊርዶስ

አንብቤው እንደጨረስኩ እምባዬን ዘረገፍኩት ለካ ፊርዱ እንደምትሞት ታውቅ ነበር፣ ለካ እሷ ጠብቃኝ ነበር ለምን አልሄድኩም? በፈለገቺኝ ሰአት ለምን ከጎኗ አልነበርኩም? እሱም ለበጎ ነው?? ከእለታት አንዱ ቀን ያገናኘን አምላክስ እንዲ ነው የሚለያየን? አልኩት ሀምዛን ቀና ብዬ......አይቶኝ አንገቱን ደፋ እኔም ወረቀቱን እንዳቀፍኩኝ ከተኛሁበት አልጋ ላይ ለመነሳት እግሬን ማነቃነቅ ጀመርኩ ሀምዛ በደስታና በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ በፍጥነት እንድነሳ ይረዳኝ ጀመር.....ከብዙ ጥረት ቡሀላ በእግሬ ቆምኩ ሀምዛ ዘሎ አቀፈኝ ሁለታችንም ተቃቅፈን አለቀስን ህመሜ በእንባ ታጥቦ ይወጣ ይመስል ለጉድ አነባሁ። በዚ ሁኔታ ቀኑ መሽቶ ነጋ ለሊቱን ሙሉ ሳልተኛ አደርኩ ጠዋት ሀምዛን ቅሰቀስኩትና ስራ እንዲሄድ ካደረኩ ቡሀላ ልብሴን ቀያይሬ በቀጥታ ፊርዱ ቀጥራኝ ወደቀረችበት ሆቴል አመራሁ እንደደረስኩ ያኔ የተቀመጥኩበትን ቦታ በአይኔ ስቃኘው ሰው አልተቀመጠም በቀጥታ ሄጄ ወንበሩን ስቤ ተቀመጥኩኝ።
አስተናጋጇ መጥታ "ምን ልታዘዝ" አለችኝ ቀና ብዬ አየዃት ያኔ የታዘዘቺኝ ልጅ ነበረች
"ውሀ" አልኳትና አንገቴን ደፋሁ። ብዙም ሳትቆይ ውሀውን አመጣችልኝ። ከፍቼው አንድ ተጎነጨውና ከኪሴ እስኪርብቶ እና ማስታወሻ ደብተሬን አውጥቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ


ለምን እንዲ ሆነ ማነው ሚጠየቀው፣
ያፈቀረሽ ልቤ? ወይስ እኔን ሳያውቅ የሞተው ልብሽ ነው።
ማነው ጥፋተኛው ተከሶ ሚቀጣው፣
የቀረበሽ ገላ? ወይስ እንቅልፍሽ ነው።
ንገሪኝ ማንስ ነው ሀይማኖቱን ገፍቶ ፍቅርን ያከበረ፣
ያዩሽ አይኖች ናቸው? ወይስ ልብ የሚሰርቅ ውበትሽ ነበረ።
እስኪ በይ ንገሪኝ ፅድቅ የሰራው ማነው ማንስ ሀጢያተኛ፣
ያጠፋውን ቀጥቶ ማነው የሚፈርደው ተከራክሮ ለኛ።
በእምባ መራቅ የለም ብቻ አላውቅልሽም፣
ከእለታት ባንዱ ቀን ላፈቀረሽ ልቤ ምላሽ አልሰጠሽም፣
ሲያስብሽ ውሎ ላደረልሽ ገላ ትንሽ አላዘንሽም፣
ትተሺኝ ስትሄጂ ላልኖር እንደምችል እንዴት አላሰብሽም
ብቻ አላውቅልሽም።

የፃፍኩትን ደግሜ ለራሴ አነበብኩት ትንሽ ፈገግ አስባለኝ ያኔ የፊርዱን ስልክ #ያልተፈታ_ቅኔ ብዬ ሴቭ ያረኩት ትዝ አለኝ። እውነትም ያልተፈታሽ ቅኔ ነሽ አልኩ በልቤ። ድንገት የእጅ ሰአቴን ሳየው ነው ብዙ እንደቆየው የገባኝ ማስታወሻዬን ከደንኩትና ሂሳቤን ከፍዬ ከሆቴሉ በቀጥታ ወጣሁ።


ተፈፀመ

─━━━━❤️⊱✿⊰❤️━━━━━─

https://t.me/Write_Event
📜 በፍቅር ስም *ገፅ 192 - 193

አለማየው ገላጋይ

🔔"አንድን ነገር የምትጠቀምበት አላማ ጥሩ እና መጥፎ የሚል ተቀጥላ ያሰጠዋል።በቃ!ሌላው ቀርቶ ውሃ ለልምላሜና ለጥማት ስንጠቀምበት ስለኖርን ጥሩነቱ ብቻ ይታየን ነበር።ውስጡ ሌላ ሀይል እንዳለ ተረድተን ሐይድሮጂን ቦንብ ስንሰራበት ውሀ መጥፎ ሆነ ማለት ነው? ውሀ ጥሩም መጥፎም አይደለም።ሰው ነው ጥሩ እና መጥፎ የሚለው።ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውም ሰዎች እንደ ውሀ ጥሩ የሚባልና በመጥፎነት የሚፈረጅ ሐይል ሊወጣቸው ይችላል።አንድ ሰው ከበሽታ መፈወስን እስኪ እንየው።ፈውስ ጥሩ የሚባለው ከማን አንፃር ሲታይ ነው?ምን አልባት በርስት የሚከራከር ሰው ያንን በሽተኛ ማዳን መጥፎ ሊሆን ይችላል።መግደል ደግሞ ጥሩ!የጋኔን "አብስትራክት "የሰው ልክ ከምርጫውና ፍላጎቱ አንፃር ሲታይ የሚገኝ ተጨባጭ ያልሆነ ድምዳሜ ነው።"


https://t.me/Write_Event
" One day you will ask me which is more important? my life or yours? I will say mine and you will walk away not knowing that you are my life."

- kahlil Gibran -


ኮከቦች ለመቁጠር፣
የኔና የሷ ጀርባ ከሳር ላይ ተጋድመው
ጠየቀችኝ ፍቅሬ...
"ካንተና ከኔ ህይወት የቱ ነው ሚጠቅመው?"

አይኖቼን ጨፍኜ...
"አስቤ ልንገርሽ" ቆይ አንዴ ሳልላት
የኔ ነው ሚጠቅመው ብዬ መለስኩላት::

አዘነች ከልቧ፤
አይኗ ዕንባ አቀረረ ተከፋ መንፈሷ
ህይወቴ እንደሆነች አልገባትም እሷ::

[ እዮብ ዘ ማርያም ]
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ አንድ (1) 🌼🌼🌼

በ5 ክፍል ብቻ የሚያልቅ

🌻እውነተኛ የፍቅር ታሪክ 🌻



ተወልጄ ያደኩት በውቧ በደሴ ከተማ ነው ደሴ ላይ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማርኩ በሇላ የኢንትራንስ ውጤቴ አሪፍ ስለነበር መቀሌ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት የትምህርት ዘርፍ ሁለት ሺህ ስምንት ላይ መቀሌ ዩኒቨርስቲን ተቀላቀልኩ መቀሌን በስምንት ቀን ውስጥ ለመድኳት ብዙ ጓድኞችን ተዋወኩ የመጀመሪያውና ለኔ ለዘላለም ከልቤ ላይ ነግሶ የሚኖረው ጓድኛየ ዘካሪያስ ይባላል የመቀሌ ልጅ ነው
እንደ ዘካሪያስ ያለ ጓድኛ ማግኘት ቢከብድም ለኔ ግን ሰቶኛል
ዛክ ጋ በቶሎ ተግባባን
አብረን መዋል አብረን ማንበብ አብረን መዝናናት የቀን ተቀን ስራችን ሆነ
አገሩን በደንብ አስጎበኘኝ ጓድኝነታችን ከጓድኝነት አልፎ ወደ ወንድማማችነት ተለወጠ እኔም የወንድሜን ያህል ወደድኩት እሱም እንደኔው
ቀኑን በውል ባላቀውም ህዳር ወር ላይ ዛክ የሴት ጓድኞቹን ሊያስተዋውቀኝ ካፌ ተቀጣጠርን
እኔም ሴቶች ጋ ስገናኝ የመጀመሪያየ ነውና አለባበሴን አሳምሬ ወደ ተቀጣጠርንበት ካፌ ከነፍኩኝ
ከካፌው በር ላይ ቁሜ ስመለከት ሚዛክን አየሁት እሱም እኔን ፍለጋ አይኑን ከወዲያ ወዲህ ሲያቅበዘብዝ ተመለከትኩት
ረጋ ባለ አረማመድ ወደ እነ ዛክ ስሄድ በድጋሜ አይኔን ከጎኑ ካሉት እንስቶች ላይ ጣልኩት

ወደኔ የዞረችዋ ጉብል አይኗ እንደ ሠማይ ከዋከብት ያበራል ፀጉራ በወገቧ ተግለስልሶ ወርዷል
ልክ ሳያት ልቤ መታ ሰውነቴ ዛለ
ሰውነቴን የሆነ የማላቀው አድስ ስሜት ወረረኝ መራመዴን ረስቼ እሷን ስመለከት መንገዴ ላይየነበረ ወንበር አደናቅፎኝ በቁሜ ተዘረርኩኝ እንደምንም አቃትቼ ለመነሳት ስመሞክር መነሳት አልቻልኩም በደቂቃ ውስጥ መውደቄን የተመለከተ የካፌው ተጠቃሚ ሰው ሁሉ ከበበኝ ይበልጥ አመመኝ በአይኔ የማውቀው ሰው አጥቼ ሰፈልግ ዛክ ዘሎ ተከመረብኝ ይርበተበታል
ደህና ነኝ ጓድኛየ ተረጋጋ አልኩትና ለመነሣት ያለ የለለ ኃይሌን ተጠቅሜ ስንጠራራ
የማላቀው ሰው ሊያግዘኝ እጄን ያዘኝ ወደ ሰውየው ቀና ስል ዳግም መውደቅን ተመኘሁ ያየሁትን ሰው ማመን አቃተኝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ☞ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,


ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ 🙏🙏
┏━━━••━━ ••━━ ••━━┓
👉 ይቀላቀሉን

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••


https://t.me/Write_Event
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ ሁለት (2) 🌼🌼🌼


🌻 እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌻



"እውነተኛ ፍቅር በመሠናክል የተከበበ ነው መሠናክሉን ለማለፍ እንጅ ከመሠናክሉ የምትሸሽ
ከሆነ ፍቅር አይደለም ምክኒያቱም ፍቅር አይፈራም ይታገሳል እንጅ"
,,,,,,,,,,,,,,,,, ዳግም መውደቅን ተመኘሁ አለንጋ የመሰሉ ጣቶቿ ከጄ መዳፍ ላይ ሲንሸረሸሩ ደስ የሚል ስቃይ ተሰማኝ እሷ ባለችበት ሁሉ መውደቅን ተመኘሁ ሰዉነቴ መርበትበት ጀመረ ህመሜን ረሳሁት እጆቿን ከእጆቼ መለየት አልፈለኩም እጆቿን ጠበቅ አድርጌ ይዠ ተነሳሁ አካሌ የኔ አልመስልህ አለኝ
የኔን መውደቅ ለመመልከት ዙሪያውን የከበበኝ ሰው አድስ አበባ ስታድየም የቡና እና የጊዮርግስ ጨዋታ ለመታደም የመጣ ያህል ነበር
ከህመሜ በላይ የሠውን አይን ፈራሁት ከቆምኩበት ሁኘ ዙሪያየን ስመለከት አይኔ ፈዘዘ
ዛክ በል ተራመድ እስኪ መልክየ አይዞህ አለኝ
እሺ ብየ ለመራመድ ስሞክር አልቻልኩምና ወደ ዛክ ዞር ብየ አልቻልኩም ጓድኛየ አልኩት
ስሟን ገና ያላወኳት ግን በደቂቃ እይታ በፍቅር የወደኩላት እንስት ልደግፍህ አለችኝና እጄን ሳብ አድርጋ ትከሻዋ ላይ አደረገችው አሁንም ሌላ ስሜት ወረረኝ የሆነ ደስ የሚል በስቃይ የተሞላ ደስታ
ከዛማ እኔስ ህመምተኛ አይደለሁ ተጠመጠምኩባት እንደምን ተገፋፍተን ከካፌው ወጣን
ዛክ ላዳ ታክሲ ፈለገ እና ወደ ሆስፒታል ሄድን ሆስፒታል ስደርስ ግን ከበፊቱ ተሻለኝ እያነከስኩም ቢሆን መራመድ እችል ነበር ነገር ግን አሁንም መታቀፍ አማረኝ ያውም በቆንጆና በምወዳት ሴት እቅፍ
ዛክ ከኛ ቀድሞ ወደ ካርድ ክፍል ሮጠ እኔም በዛክ ጓድኞች ተከብቤ ወደ ሆስፒታል ገባን
ከቆይታ በኋላ ዶክተሩ ትንሽ እረፍት ያስፈልገዋል ስላለኝ አልጋ ያስኩኝ
ዛክም ተረጋግቷል ጓድኞቼን ተዋወቃየው አለኝ
በመጀመሪያ ፀይም ዘለግ ያለች ቆንጆ ሙና እባላለሁ አለችኝ
ሁለተኛዋ እኔ ልቤ በደቂቃ ውስጥ በፍቅር የከነፈላት ባለዞማ ፀጉር መልኳ የቀይ ዳማ ዘለግ ያለች ቆንጆ አተኩራ እያየችኝ እጇን ዘረጋችና,,,,,,,,,,,,,,,☞ይቀጥላል



ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ 🙏🙏

https://t.me/Write_Event
ቃላዊ via @like
Gete Anley – Melikish Kanchee Aybeltim
#ጌቴ_አንለይ
#መልክሽ_አይበልጥሽም

🎶🎹🎹🎶
🎹🥁🥁🎹
ለኔ አዲስ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
🎶
በጄ እስክተገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነውንጂ መች ጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
🎶🎶
የብርቅዬ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
የብርቅዬ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
አንቺን ውብ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ ወድጄሽ ከሆዴ
🎶
መች አይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ከአንገት በላይ ምርጫ ከአንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ መች አየ እሱን ብቻ
🎹🥁🥁🎹
🥁🎹🎹🥁
መቼ እተውሽ ነበር ዎ አይኔስ ቢያሽ ድሮ ሆ
ባይኖር እንኳን መልክሽ ሆ ውብ ባትሆኝም ኖሮ
ቢደምቅም ባይደምቅም ሆ ቢበርደው ቢሞቀው ዎ
ላይሽ ብቻ አይደለም ሆ ልቤን የደነቀው
🎶
ከላይ ቢልም ዋለች በአደባባይ እቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጭቷ
🎶🎶
ጥቁር ነጭም ቢሆን ሆ የጥፍርሽ ቀለሙ ሆ
መች እሱ ሆነና ሆ ለኔ ብርቅ አለሙ
አይጭነቅሽ አንቺ ሆ ሀሆኖ አይሰለቸኝም ሆ
ጉዳዬ ውስጥሽ ነው ሆ ካንቺ አይበልጥብኝም
🎶🎶
መልክሽ አይበልጠሽም እንዳለሽም ባውቀው
አንቺው ነሽ መብራቷ ፍቅር ምታቀልጠው
🎶🎶
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
🥁🎹🎹🥁
ለኔ አዲስ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
🎶
በጄ እስክተገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነውንጂ መች ጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
🎶🎶
የብርቅዬ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
የብርቅዬ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ (እናና ዘመዴ)
አንቺን ውብ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ ወድጄሽ ከሆዴ
መች አይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ከአንገት በላይ ምርጫ ከአንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ መች አየ እሱን ብቻ
🎹🥁🥁🎹
🥁🎹🎹🥁
ጊዜ ሲለዋወጥ ዎ ወራቱ ሲጨምር ዎ
ይነጥፍ የለም ወይ ዎ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና ሆ አርሮ ቀን ሲከብደው ዎ
መልክማ ይቀየራል ሆ ለአንድ አፍታም ቢበርደው
🎶
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቅ የሌለሽ ውበት
🎶🎶
ጊዜ ሲለዋወጥ ዎ ወራቱ ሲጨምር ዎ
ይነጥፍ የለም ወይ ዎ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና ሆ አርሮ ቀን ሲከብደው ዎ
መልክማ ይቀየራል ሆ ለአንድ አፍታም ቢበርደው
🎶
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቅ የሌለሽ ውበት
🎶🎶
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
👇👇👇👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"መልክሽ ካንቺ አይበልጥም" ሲተነተን

#ውበት እና ፍልስፍና

ፊት በውሀ ላይ እንደሚታይ ያህል ቢሆንም
የሰው ልብ እኮ ለሰውም ይታያል
የሰው ፊት ውስጡን ያሳብቃል
ሰው ውስጡ ውብ ሲሆን
ያ እውነተኛ ውብት ከድብቅነት እያለፈ
እየወጣ እየወጣ ሲመጣ
ለአይን አምሮ ያለመታየት ሚስጥር እጅግ ይገርማል....... (መልኩስ ልቡ ነው)



መልክሽ ካንቺ አይበልጥም (ጌቴ አንለይ)

መግቢያዬ በማይታይ ንግግር

ሀ :- ለምን ጥለሀት አትሄድም ስንት ውብ እና ሸጋ ሴቶች አሉልህ አይደል እንዴ?
ለ :- ሚታይህ ይህ የገረጣ ፊቷ ነው አይደለ
አስሮ የያዘኝ ግን ከውጪ የማይታየው እውነትም ካልካቸው ውብ እና ሸጋ ሴቶች በላይ ውብ የሆነ አንድ ልብ (አንድ ውሳጣዊ ቁንጅና) ይዛ ስላለች ነው። መልኳ እኮ ልቧ ነው።

አይኗ እንደ ኮከብ
መልኳ እንደ ጨረቃ
ጉንጯ የፈነዳ አበባ
ከንፈሯ ኢንጆሪ
ፀጉሯ የሀር ነዶ ...... እያለን ብዙ የግጥም ስንኞችን በሀገራችን ላይ ከተሰሩ ሙዚቃዎች ላይ መስማት ከመለመድም አልፎ የውበት መግለጫ አስተሳሰባችንን በመልክ እና በቁመና እንድንስል ሰፊ ሚናቸውን ሙዚቃዎቹ ተጫውተዋል ብዬ አስባለሁ። ያቺን ሸጋ ብንል አንዲት የምታምር ያን ጎምላላ ብንል ደግሞ አንድ መልከ መልካም ልጅ መሳላችን የማይቀር ሁኔታ ነው። ይሄ ሁሉ እይታ ሰርፀው ከተዋሀዱን የውበት መግለጫዎች እና ሙዚቃዎች ያሳደሩብንን ተፅእኖ እንደመጣ ያመለክታል። ታድያ ይህ አስተሳሰብ ያሳሰበው ይህ ተፅእኖ ልክ አይደለም ብሎ የተነሳው አንድ #የከተማ መናኝ ትናንት ተው ብሎ ዛሬ ላይ በዘመኑ እንዲህ እያለ ፍልስፍናውን ተቃርኖውን ሙግቱን ይገልፅልናል

ከላይ እዩኝ ባለች ባደባባይቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጪቷ

እንግዲህ መልክን በኢንጆሪ በፀሀይ በጨረቃ ሲመዝን የኖረውን ዘመን ተው ብሎ በብልጭልጭ አልመዝንሽም እያለ ኤልያስ - መልካ የሚባል አንድ ዘመን በጣፋጭ ዜማ ያጫውተናል።

ጥቁር ነጭም ቢሆን የፀጉርሽ ቀለሙ
መቼ እሱ ሆነና ለኔ ብርቅ አለሙ
ዘመነ እርጅናም ውብ የወጣትነት ጣፋጭ ዘመን አለው። በዚ ስንኝ ፀጉራቸው ሸብቶ ቆዳቸው ተሸብሽቦ በዘመናቸው ውብ የነበሩትን አዛውንቶች አሁንም በዘመነ ሸበቶነት ውብ እንደሆኑ ይነግረናል። ባለ ጥቁር ፀጉራማዎቹን ደግሞ ብርቄ ከላይ የደመቅሽበት ውበት አይደለም እያለ ያነጋግረናል።

መልክሽ አይበልጥሽም እንዳለሽም ባውቀው
አንቺ ነሽ መብራቷ ፍቅር የምታደምቂው

ከመልክሽ በላይ ውስጥሽ ያበራል ቤቴ ብትመጪ ክፍሌ ሚደምቀው ከላይ ባለሽ ውበት ሳይሆን እንደ መብራት አብሮቶ ጨለማው ቤቴን የሚያደምቀው ውብ ውስጣዊ አንቺ ነትሽ ነው ይለናል ይሄ መናኝ።
በዘመነ ትናንት ውበትን በላይ የመሳል ተፅእኖ እዚጋ ፈርሶ መልካቹ ልባቹ ነው በሚል ብዙ ሺ መፅሀፍ በሚወጣው አስተሳሰብ ይተካል።

ላዩም ሀላፊ ነው መልክ እና ደምግባት
ሁሌም ግን እያልፍም ብርቅ የልብሽ ውበት
ወዳጄ ዘመናችን እኮ ልባችሁ ውብ ነው እያለ በሚሰብክ ባለ ልበ መልካም መናኝ ተቃኝቷል።

መልኬ ልቤ ነው እንድል ያደረከኝ ባለ ልበ መልካሙ ኤልያስ መልካ ሆይ ክበርልኝ

ብላቴናው

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🌺🌸🌺 የመረረ ፍቅር 🌺🌸🌺


🌼🌼🌼 ክፍለ ሶስት (3) 🌼🌼🌼


🌻እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌻


☞ሰሊና እባላለሁ ስትለኝ እጄን ዘርግቼ ቀረሁኝ አንደበቴ ዲዳ ሆነ በርጋታ መልክየ እባላለሁ አልኳት የፈጣሪ ያለህ የዚህን ያህል መርበትበት ብየ ቀልቤን ሰበሰብኩና አሁን ተሽሎኛል መውጣት እንችላለን አልኳቸው
ዛክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አይ መቆየት አለብህ እመለሳለው ብሎ ወጣ ሁለቱ ሴቶች ለኔ ባልገባኝ ወሬ ይፍነከነካሉ
ባይገባኝም አብሬ መሳቅ ጀመርኩ በመሀል የሙና ስልክ ጠራ ሙና ስልክ ለመናገር ወጣች
ሠሊና እና እኔ አንድ ክፍል ብቻችንን ደስ ይላል
ሠሊና እና እኔን ከመተያየት ያለፈ የሚያግባባን ምክኒያት ጠፋ
በመሀል አፌ እንደ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ
ማን ነበር ስምሽ አልኳት
ፈገግ አለችና መርሳት አጋጠመህ እንዴ ሰሊና አለችኝ
እኔም ስታወራ የምታወራውን ሳይሆን ከንፈሯ ሲላወስ ጉንጮቿ ትርክ ትርክ ሲሉ እየተመለከትኩ ወሬዋ ባላለቀ ሌላ ወሬ በጀመረች እያልኩ ሳስብ ሙና በሩን ከፍታ ገባች እና በፍጥነት ፓርሳዋን አንስታ ጋይስ ቻው እመለሳለው ብላ ቅብጥ ቅብጥ እያለች ወጣች

አሁን የሚያሰጋኝ ነገር የለም ከ ሰሊና ጋ ጨዋታ መጀመር እችላለሁ
በመሀል ምንም የህመም ስሜት ሳይሰማኝ
እእእእእ ወገቤ ብየ ጮህኩኝ
ሰሊና ተደናግጣ ምነው ምን ሆንክ አለችና ወደኔ ተጠጋች
ወገቤን አመመኝ ሰሊና አልኳት
በድንጋጤ ዶክተሩን ልጥራው አለችኝ እኔም በድፍረት አይ አያስፈልግም ባይሆን ወገቤን,,,,,, አላስጨረሰችኝም በፍጥነት አልችልበትም ግን ከተሻለህ ልሞክር አለችና በደረቴ እንድጋለል በአይኗ አዘዘችኝ እንዳዘዘችኝ አደረኩ
እንደ አለንጋ እጥፍ ዝርግት የሚሉ ጣቶቿን ወገቤ ላይ ስታንሸረሽራቸው እንኳንስ ያልታመመው ወገቤ የታመመው እግሬም የህመም ስሜት አይሰማውም ነበር
እጇ መድሀኒት ነው ልክ እንደ እትየ አሰፉ እትየ አሰፉ የሠፈራችን ምርጥና ተወዳጅ የባህል ሀኪም ነበሩ እትየ አሰፉ እንኳንስ የነካችው እግዜር ይማርህ ያለችው ሰው ይድናል ይባል ነበር
እኔም ወደ ሠሊና ቀና ብየ ልክ እንደ እትየ አሰፉ ነሽ ሰሊና እየተሻለኝ ነው አልኳት
ፈገግ አለችና እትየ አሰፉ ማናቸው አለችኝ
ደስ እያለኝ የሠፈራችን ሀኪም አልኳት ከት ብላ ሳቀች እኔም ተከትያት ሳኩኝ ክላሡ በሁካታ ተሞላ ይህንን የሠማ አንድ ታካሚ በር ላይ ቆመና ሲመለከተነሸ ቆየና በድንገት
"ፍቅራችሁ ያስቀናል ያርዝምላችሁ ደስ ስትሉ አለን "
ሰሊናእና እኔ በሽቅድምድሞሽ እኔ
ኧረ ፍቅረኛሞች አይደለንም
እሷ ደግሞ
እናመሠግናለን አለችና ፈገግ አለች
እኔ ግራ ገባኝ ብቻ ሰሊና ጣጣ የሌለባት መሆኗን ሳውቅ ይበልጥ ልቤ መምታት ጀመረ እሷም ከጎኔ እንደቆመች እኔም ከሷ ላይ አይኔን እንደተከልኩኝ ዛክ በሩን ከፍቶ ገባ

ዛክ በፌስታል ሙዝ እና ብርቱካን ይዟል
እንዴት ቆየህ ጓድኛየ ሰሊና ስታደርቅህ ቆየች አይደል ብሎ ከፌስታሉ ሙዝ አውጥቶ ሰጠኝ እና በል ብላ ብሎ ለነሡም አንድ አንድ አንስተው ወሪያችንን ቀጠል ከሆስፒታል መውጣት እስኪያስጠላኝጨድረስ ሆስፒታል መሆናችንን ወድጀው እያለ ዶክተሩ መውጣት እንዳለብን ነገረን ተያይዘን ወጣን

እኔም ሰሊናን እንደተለየው ቅንጭላቴ ዞረ
ዳግም የማላገኛት መሠለኝ
ነገር ግን ለሷ ያለኝ ስሜት እየጨመረ ቢሄድም በቀን በቀን እየተገናኘን መጫወት አዘወተርን አራትችንም ደስ የሚሉ ቀናቶችን እያሳለፍን አንድ ቀን ለመዝናናት ወተን የጭርቃት ኳስ ስንጫወት
ሙና እና እኔ በአንድ
ዛክ እና ሰሊና
በአንድ ሁነን ተጋጠምን የተሸነፈ ሊጋብዝ ያሸነፈ ሊጋበዝ ነበርና ጨዋታችን የደራ ነበር
በጨዋታ እንበልጣቸዋለን እኛ ግን አልተናበብንም ነበር እና አሸነፉን
ከዛ እርስ በርሳችን ስንፎጋገር ሰሊና ስማማ መልክየ አለችኝ እህ አልኳት
ከንፈሯን በእጇ እየዳሰሰች ሰሊና እና ዛክ እኮ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
አስተያየታችሁን አይተን ይቀጥላል


https://t.me/Write_Event
የመረረ ፍቅር
ክፍል አራት (4)

☞ፍቅር ህያው ነውና☜
ዛክ እና ሰሊና እኮ ስትለኝ ላስጨርሳት አልቻልኩም ደነገጥኩኝ ልቤን ፍርሀት ተሰማው ቢሆንም ግን ቁርጤን ለማወቅ እሽ! ዛክና ሰሊና አልኳት ፈገግ ብላ ቀልደኞች ናቸው ስትለኝ ልቤ ቀዝቃዛ ውሃ የተቸለሰበት ያህል ተሰማኝ ተረጋጋሁእና ወደ ዶርም ተመለስኩኝ

ዶርም ስደርስ ይበልጥ ሰላም አልሰማኝ አለ ሰሊና ናፈቀችኝ ደውየ ብቻዋን ላገኛት እንደምፈልግ ስነግራት አላመነታችም እሽ አለችና የምንገናኝበትን ቦታ እንድነግራት ጠየቀችኝ ሰው ከማይበዛበት ቦታ ቀጠርኳት

ከቦታው ቀድሜ እኔ ብደርስም እሷም ሳታስጠብቀኝ በቶሎ መጣች የማወራው ጠፋኝ እሷም ለምን እንደፈለኳት እንድነግረኝ አዋከበችኝ እኔም ከአንደበቴ ይልቅ አይነሰ እንባ እየፈሰሰው ከንፈሬ እየተንቀጠቀጠ አፌ እየተኮላተፈ ያወራ ጀመር ነገር ግን እሷም እንደኔው በፍርሀት ተዋጠችና አንገቷን ወደ መሬት ደፋች በሁለታችን መሃል ፍፁም ዝምታ ሆነ

እኔ ወንድነቴ ድፍረት ሰጠኝና ተነስቼ ወደ ሰሊና ተጠጋው
ጡቶቿ ከደረቷ ፈንገጥ ፈንገጥ ብለው ስለተቀመጡ ድፍረት ሰጡኝ ተጠጋዋት በወገቧ ስር ወርዶ ወርዶ የተነሠነሰውን ፀጉሯን ወደ ላይ ሸከፍ እየሠጠው
አ,,,,,,,, አ,,,,,,,,, አ,,,,,,,,,አፈቅርሻለው ሰሊና አልኳት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ደነገጥኩኝ ፍርሃት ተሠማኝ እንደተቃቀፍን ፍርሃታችንን አስወግደን ተመለስን በአንዴ ማሬ ሆዴ ፍቅሬ እየተባልን መጠራራት ጀመርን

ፍቅራችን ደራ ነገር ግን ለጓድኞቻችን አልነገርናቸውም ነበር ለቫላንተይን ቀን እንነግራቸዋለን ብለን ነው
እነሡም አልነቁም
የቫላንተይን ቀን ደረሠ አራታችንም አንድ ተቀጣጠርን
ይህ የሆነው
ሙና ለኔ ደውላ ስቀጥረኝ
ዛክ ደግሞ ለ ሰሊና ደውሎ ሙና ከቀጠረችኝ ቦታ ሲቀጥራት ሠሊና ከኔ ጋ ነበረች
አይነጋ የለም ነጋ ምን አስበው እንደቀጠሩን እያሰብኩ እያውሰለሰልኩ ከቦታው ደረስኩ ከቦታው ስደርስ ያየውትን ነገር ማመን አቃተኝ አይኔ ባያይስ ብየ ተመኘሁ ዛክ ቀይ አበባ ይዞ ተንበርክኮ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል

ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ

https://t.me/Write_Event
.
#የመረረ_ፍቅር


ክፍለ አምስት (5)

የመጨረሻ ክፍለ



ፍቅር ከደሴ እስከ መቀሌ ዛክ ቀይ አበባ ይዞ ከኔውቷ ንግስት ከሰሊና እግር ስር ተንበርክኳል ማመን ቢያቅተኝም ማመን ስላለብኝ አመንኩ ሳላስበው ከወደ ኋላየ ሰርፕራይዝ የኔ ፍቅር የሚል ድምፅ ተሠማኝ ፡፡
በድንጋጤ ዞር ስል ሙና ነች በቁሜ ደርቄ ቀረሁ ወደ እኔ እየተጠጋች ከተገናኘንባት ሰዓት ጀምሮ ስላንተ ያላሠብኩባት ደቂቃ ፈልጎ ማግኘት ምንኛ ይከብዳል አፈቅርሃለው አለችና ከንፈሬ ጋ ከንፈሯን አላተመችው እኔ ደንዝዣለው ሬት ሬት ከማለት ያሀፈ ምንም ጥሩ አይሰማኝም ነበር እና ከላየ ላይ መንጭቄ አሽቀነጠርኳት እና ፊቴን ወደ እነ ሰሊና ስዞር ሰሊና ፊቷ በእምባ እየታጠበ ከፊቴ ቁማለች፡፡

ጠጋ ብየ ሰሊና ወደኔ እየተጠጋች መልክየ ጠጋ እያልኳት ሰሊና ወደ እኔ እየተጠጋች መልክየ ሳናስበው ከንፈር ለከንፈር ተገጣጠምን ፍቅር አሽቀንጥሮ ከማናቀው አለም ውስጥ ወሰደን ከቆይታ በኋላ ተላቀን ዙሪያችንን ስንመለከትማንም በአካባቢያችን የለም፡፡

ደስተኞች ባንሆንም አብረን ወደ ሆቴል ሄድን አልጋ ይዘን ፍቅር ሰራን ሰሊና ለኔ የመጀመሪያየ ክህነቴን ያፈረስኩባት ለሧም የመጀመረዋ ነኝ ያቺ ቀን እንደዚሁ መሽታ እንደዚሁ ነጋች፡፡

ሲነጋ የሠሊናን አይን ለማየት ድፍረት አጣሁ ሳትሰማኝ ተነስቼ ወደ ዶርሜ ከነፍኩ ዶርም ስገባ ዛክን አገኘሁት ዛክ ሊያዋራኝ አልፈለገም ተሥፈንጥሮ ወጣ
ከመኝታየ ወረቀት ተቀምጦ አገኘሁ ወረቀቱ አንዲህ ይላል "ሠሊናን እወዳታለሁ አንተንም እንዲሁ ከሰሊና ጋር ፍቅር እንደጀመራችሁ አላውቅም ነበር ፍቅራችሁን ቀጥሉ ይህን ግን እኔ እያየሁ መቋቋም ስለማልችል ጓድኝነታችን ከዚ ላይ አቆመ ቻው ዘካረያስ"ይላል፡፡

እንባየ አሸነፈኝ ጓድኛየ ለኔ የከፈለው መስዋት ይበልጥ አሳመመኝ ሰሊናን በስልክ ቀጥሬ ዛከን አገናኘዋት ግን የማይሆን ነበር ሙናምጰከሰሊና እግር ስር ወድቃ ይቅርታ ጠየቀች ሰሊና እና እኔ ተያየን እንባችን ፈሠሠ አይናችን የደም እንባ ሊያፈስ ምንም አልቀረው፡፡

የሠሊና ሃሣብ ነበር ከአሁን በሁላ አራታችንም በእህት እና በወንድምነት እንቀጥላለን አለችኝ ሁላችንም ተስማማን፡፡በእህት እና በወንድምነት እየቀጠልን አመታት ነጎዱ ዛክ እና ሙና ሌላ ፍቅረኞች ይዘው አስተዋወቁን እኔም ለሠሊና ይምሰል የክላስ ጓድየን ፍቅረኛየ ብየ አስተዋወኳት ሰሊና እና እኔም በተገናኘን ቁጥር እየተያየን ማንባት ስራችን ሆነ ,,,,,,,,,,,, "ህይወት ትቀጥላለች ፍቅርም አታቆምም "
አለቀ !

እንግዲ እውነተኛ ታሪክ ነውና እውነታውን ብቻ ከህይወት ጋር አብሮ ይቀጥላል......

ተፈፀመ
ተፈፀመ!

ሼር በማረግም ለሌሎች ያካፍሉ፡፡



ይቀላቀሉን 👉

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➊

♥️በ እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረት ♥️



...🖊ከአልጋዬ ፊት ለፊት የልብስ ማስቀመጫ ቁምሳጥን ላይ የሚገኘዉ መስታወት እኔ ስስቅም ሆነ ሳለቀስ መመልከትን ለምዶታል። አንዳንዴ ''መስታወት የልብ ጓደኛዬ ነዉ ምክንያቱም እኔ እያለቀስኩ እሱ አይስቅብኝም!'' የሚለዉ አባባል በልኬ ተሰፍቶ የተሰጠኝ ይመስለኛል... ሀዘን ደግሞ ከእኔ ፍቅር የያዘዉ ይመስል በተደጋጋሚ እየጎበኘኝና የማይድኑ የልብ ጠባሳዎችን እያስታቀፈ ወዳጄ የሆነዉ መስታወት ፊት ይገትረኛል... ከመስታወቱ ፊት ለፊት ቆሜ እራሴን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት ፀጉሬ ተንጨባሯል...በለቅሶ ብዛት የቀላዉ ዓይኔ እንኳን ለሌላ ሰዉ ይቅርና ለራሴም ፍርሀትን ስለለቀቀበኝ አይኔን ከመስታወቱ አሸሸሁ... ድካምና የእንቅልፍ እጦት ተደራርበዉ ሰላም ነስተዉ ጭንቀት ዉስጥ ከከተቱኝና ከቤት መዉጣት ካቆምኩ አንድ ሳምንት ተቆጠረ። ለቤተሰቤ የመጀመሪያም የመጨረሻም ብቸኛና ተወዳጅ ልጅ ብሆንም፤የቤተሰቦቼ ኑሮ ከራሳቸዉ አልፎ ለሌሎች ይተርፋል ከሚባል ደረጃ ላይ ቢመደብም ከልጅነቴ ጀምሮ አንድ የማዝንበት ምክንያት አለመጥፋቱ ይገርመኛል! ለነገሩ ሀዘን ጥሩ በሚባል የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይጎበኝም ያለዉ ማነዉ?። ስቃይ በገንዘብ ብዛትና በኑሮ ስኬታማነት የማይረታ መሆኑን ምስክር እንድሆንለት ያዘጋጀኝ ምስኪን ሰዉ መሆኔ ተስፋ ያስቆርጠኛል። አሁን ''የሰላም ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮከብ ተማሪ የሆነችዉ ቤዛዊት አለሙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዉጤቷ ተበላሽቶ ዩኒቨርሲቲ የመግባት ህልሟ የዉሃ ሽታ ሆነ!'' ቢባል ማን ያምናል?' ግን እዉነታዉ ይህ ነዉ! ስንት የደከምኩለትና ለስንቶች ምሳሌ የሆነዉ የትምህርት ላይ ጥንካሬዬ በአጭሩ ተቀጭቶ በሀዘን ከተለወጠ አንድ ሳምንት ተቆጠረ...

https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➋



...🖊በጭንቀትና በሀዘን ከመስታወቱ ፊት ለፊት እንደቆምኩ እናቴ የመኝታ ቤቴን በር ሳታንኳኳ ከፍታ ገባች...

የዘንድሮ ልጆች ሁሉም ነገር በአንድ ጀንበር ካልተከናወነ ትላላችሁ! መታገስ እኮ ዋጋ አለዉ!''የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል!'' ሲባል አልሰማሽም? ቤዛዬ እንደ መታገስ ከባድ ስቃይ ያለዉ ነገር ባይኖርም መጨረሻዉ ግን ያማረ እንደሚሆን አትጠራጠሪ!
የእናቴ ምክርና የማፅናኛ ቃል የእናትነት ፍቅር የታከለበት ቢሆንም እኔ ግን እንኳን እሷ ቀርቶ ፈጣሪ ወደ ምድር ወርዶ አይዞሽ ቢለኝ እንኳን የምፅናና አይመስለኝም። ወላጆቼ በትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ክፉኛ ተደናግጠዉ ቢያዝኑም በሀዘኔ ላይ ሀዘን ላለመጨመር ሲሉ ብቻ ላይ ላዩን ደስተኛ መስለዉ ለመታየት ይሞክራሉ

ቤዛዬ... የአምላክ ስራዉ ድንቅ ነዉ!... ላንቺ ከዚ የተሻለና ጥሩ ነገር ቢያዘጋጅ ነዉ!....ሰዉ የሚያምርበትን ሲፈልግ.....የሚያሳምረዉን...ሰዉ የሚደምቅበትን ሲፈልግ...የሚያደምቀዉን...የሚያስከብረዉን...የሚያዛልቀዉን ማዘጋጀት የፈጣሪ ስራ ሲሆን ይህንን ድንቅ ነገር መሸለም ደግሞ የሰዉ ፀጋ ነዉና አትዘኚብኝ አለችኝ!!
ከአልጋዉ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠች። እናቴ ስለ እኔ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ መሆኑን አዉቃለሁ
ቤዛዬ አንቺን ከመዉለዴ በፊት ሶስት ጊዜ ፅንስ ተቋርጦብኛል አምላክ የእምነቴን ደረጃ ሊፈትን እንጂ ሊያሳዝነኝ እንዳልሆነ ልቦናዬ ስለሚያዉቅ አማርሬዉ አላዉቅም እርሱም የትዕግስቴን ጥግ አይቶ አመሰግንብሽ ዘንድ አንቺን ሰጥቶኛል እባክሽ ልጄ ሀዘንሽን በልክ አድርጊዉ አለችኝ።

እኔን ለማፅናናት የምታደርገዉ ሙከራ ስላሳዘነኝ ከአጠገቧ ቁጭ አልኩ
እማ...እማ...እ...እኔ.. መናገር አቃተኝ!!

ቤዛዬ ዩኒቨርሲቲ ባይሆን ምን አለበት የፈለግሽዉ ኮሌጅ ገብተሽ መማር ትችያለሽ እኮ!!

አ.ዉ.ቃ.ለ.ሁ...እማ... ግን ይሄ ለእኔ አይገባኝም...እኮ!

ለማን ምን እንደሚገባዉ መወሰን የሰዉ ስልጣን አይደለም!! በእኔ ሞት ይሁንብሽ ይሄ ሀዘን በቃሽ! አለችኝ!!

እናቴ በእኔ ሞት! እያለች ስትለምነኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ካሰብኩት ከወሰንኩበት ነገር ሳይቀር ምልስ እላለሁ እሷም ይህን ስለምታዉቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስሆን
በእኔ ሞት! ትለኛለች
አሁን ተነሺ አባትሽ ሊያናግርሽ ይፈልጋል!
በእኔ ሞት ያለችኝ እናቴን ማሳዘን ስላልፈለኩ እጄን ይዛ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ልቃወማት አልቻልኩም...

ይቀጥላል...


https://t.me/Write_Event
​​​💔የባከነች_ነብስ💔

ክፍል_➌



ለዓይን ከሚማርከዉ ሳሎናችን ዉስጥ ካለዉ ባለግርማ ሞገስ ሶፋ ላይ አባቴ የንባብ መነፅሩን አድርጎ የስራ ወረቀቶችን ያገላብጣል። የተለያዩ አይነት የሚባሉ የጭነት መኪናዎች ዋነኛ የሚባሉ የቤተሰባችን የገቢ ምንጭ ቢሆኑም ከእነሱ በተጨማሪ ከምንኖርበት የጅማ ከተማ ዉስጥ በእናቴ ዋና ሀላፊነት የሚተዳደሩ ሁለት ሆቴሎች አሉን። አባቴ የእኔን ወደ ሳሎን መምጣት ሲመለከት ፈገግ አለ...
ዛሬም በፈተና ዉጤትሽ መበላሸት እያዘንሽ ነዉ?
እንዴት አላዝን! አባ! የለፋሁለትና የጓጓሁለት ዉጤት እኮ ነዉ!
በሀዘን የምትለዉጪዉ ምን አለና?... ነይ እስኪ ከጎኑ አስቀምጦ ፀጉሬን መዳበስ ሲጀምር...
ዛሬ ለምን እራት ዉጪ አንበላም? የእናቴ ሀሳብ ነበር እኔ ግን ከቤት መዉጣት እንደማልፈልግ ገለፅኩላት!
ዉጤትሽ የተበላሸዉ በስህተት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል እያጣራሁ ነዉ!...ግን በእንደዚህ አይነት ጭንቀት ዉስጥ መቆየቱ መፍትሔ ስለማይሆን ጠንካራ መሆን አለብሽ ደግሞ እናትሽ ጥሩ ሀሳብ ነዉ ያመጣችዉ ዛሬ እራት ዉጪ ነዉ መብላት ያለብን መንገደኛ ስለሆንሽ የመሰነባበቻ ይሆነናል
መንገደኛ...ማን ነዉ?...መንገደኛ?
አዲስ አበባ አክስትሽ ቤት የቀረችዉን የክረምት ጊዜ እንድታሳልፊ እኔና አባትሽ ወስነናል!... ላንቺም ቢሆን ከዚህ ጭንቀት እዛ ይሻልሻል!
ንግግሯ የጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ አዘል ስለነበር ዝምታን መረጥኩ።
በሉ አንድ የማገኘዉ ሰዉ አለ ለባብሳችሁ ጠብቁኝ ብሎ አባቴ ጉንጬን ስሞ ወጣ።
በይ ተነሺና ገላሽን ታጠቢ ከዚህ በሗላ ሀዘን የሚባል ነገር የለም!! እናቴ ሳምንቱን ሙሉ የሆቴሉን ሀላፊነት ለማናጀሮቹ አስረክባ ከእኔ ጋር ነበር ያሳለፈችዉ። የምለብሰዉን ልታዘጋጅልኝ ወደ መኝታ ቤቴ አመራች እናቴ በእሷ ምርጫ ልብስ መልበስን አስለምዳኛለች... የግርግዳ ሰዐቱ 10:00 መሆኑን ያመለክታል በረጅሙ ተነፈስኩ...የሀምሌ ሰማይ በደመና ተከቦ ያስገመግማል...እዝን ጭፍግግ ያለ ቀን ነበር ልክ እንደኔ ልብ...

ይቀጥላል

https://t.me/Write_Event