ቃላዊ
346 subscribers
39 photos
5 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
እኔና አንቺ!
( በረከት በላይነህ).

በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።

ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።

ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።

በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።

‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
◈◈ Join ◈◈
👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
የጠፋው በግ

ከመንጋው ሾልከ ◎ ከህብረት ተነጥዬ
በኦና ተጉዤ ◎ የቀረሁ ብቻዬ

ከዘጠና ዘጠኙ◌ እኔ ነኝ ያአንዱ
ከእረኛዬ እቅፍ◎ ጠፍቼ ከመንገዱ
ከዓለም ተዘፍቀ ◌ተጣልቼ ከውዱ
ከስቼ የጠቆርኩ ◌ባለ እድፍ ዘመዱ

ግና

ታማኙ ዘመደ ◎ የበጎቹ እረኛ
መች ሬሳኝ እኔን ◎ እንደ ወረተኛ
ለኔ ተቸንክሮ ◎ በደሙ አጠበኝ
በዘላለም ፍቅሩ◎ ልጁ አደረገኝ

ቃል የአዮ ልጅ ( @kaliye06)
◈◈ Join ◈◈
👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Evensst
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፤ለዓላማ መቆም፤ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፤ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርዓያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው??????"

ዶ/ር #ምህረት_ደበበ
◈◈ Join ◈◈
👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Evensst
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
ወርቃማ ሀሳቦች

🔱“ሀሳብ በሞራል ካልተገዛ አደገኛና አጥፊ ሊሆን ይችላል፤ህሊናችን የሞራል ማዕከላችን ስለሆነ የቱ ነው ጥሩ፣ የቱ ነው መጥፎ የሚለውን ይለያል፤ ሞራል ሲጠፋ ሀሳብ ኒውክለር ቦምብ ይሆናል፤ ሞራል ጥሩ ሲሆን ግን ኒውክለር መብራት ይሆናል”

ዶ/ር ምህረት ደበበ


🔱"መኖርና መሞት የሰው ልጅ አይቀሬ ዕጣ ፈንታ ቢሆንም ዓላማ ያላቸው ሰዎች አለመሞታቸውን የሚያረጋግጡት በእስትንፋሳቸው መኖር ሳይሆን ለህብረተሰቡ በሚያበረክቱት መልካም ሥራ ነው፡፡"

ፍቅረማርቆስ ደስታ


🔱" ፍቅር የተንኮል የምቀኝነትና የክፋትን አረም ነቅለን በምትኩ ሩህሩንትን፣ የዋህነትንና አርቆ አሳቢነትን የምናለመልምበትና የንፅህናችንን ህብር መአዛ ጠረን የምናሸትበት መስባዊ መልክ ናት፡፡"

🔱"እዚህ ሀገር አዕምሮ በማሰልጠን ፖለቲካዊ ሂደትን የመግራት ባህል፣ ቆም ብሎ የማሰብ ልምድ፣ ቸኩሎ ያለመወገን ጥንቃቄ፣ አቅምን የማመዛዘን ባህል አለመኖር እና ለደመራው “እሳትም አበባም” እያቀበለ መጓዝ መለመዱ ትልቁ ችግራችን ነው። "

🔱"የምትማረው ሰው ሁሉ እውቅና በሰጠው መንገድ ተጉዘህ ቦታና መተዳደርያ ለማግኘት ነዉ ። የምታነበው ግን በህይወት አንተ ብቻ እውቅና የሰጠኸው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው!"

አለማየሁ ገላጋይ

🔱‹‹ሁለት ዓይነት የፍትህ መመሪያዎች አሉ፡፡ አንደኛው ማንም አለመጉዳት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለማሕበረሰቡ ደህንነት ዘብ መቆም ነው፡፡››

ማርከስ ቱሊስ

🔱" አንድ የደስታ በር ሲዘጋ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል። እኛ ግን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ተዘጋው በር እንጂ ወደተከፈተልን አናይም፡፡"

ሔለን ኬለር

◈◈ Join ◈◈
👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Evensst
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
ሶሊያና

(ኤፍሬም ስዩም)
-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
የማጀትሽ ድርሻ💚💛
.
.
ይግረምሽ... እማ💚 !!
.
የደቦ ቀናትን ፡ 'ለቱን እንዳልቀጡ
ሰብል ሳይሰበስቡ ፡ ሳይወቁ ሳይወቅጡ
እንጀራውም ቀርቦ ፡ ተካፍሎ ከወጡ
ከአፍ አድርገው ፡ ቸኮሉ ለብጥብጡ
.
አይ አሳርሽ!
.
በጃንሆይ ሰንደቅ ፡ የስኒን ልኬቱ ቡና
አቦልን ሲደግሙ ፡ በበረካ ፣ ቶና
አቀዳድሽ ከራስ ፡ በ'መቤት ጀበና
ግና መች ሰከነ ፡ ጠጭው ደነፋና
.
እማይዬ...💛
.
የጠላሽ ጉልበቱ ፡ በጥንስሱ ይማርካል
ከአንጀት ሳይዘልቅ ፡ በመልኩ ይረታል
ሆድ ያሳደረው ፡ በቀል ይቅር ለብቅል
በግብዝነት ያስከፋሽ ፡ ለንስሐ ይደፋል
.
እናናዬ...
.
የማጀትሽ ድርሻ ፡ ለሀገር ነበረ
በደሙ ቃልኪዳን ፡ ካንቺ ለታሰረ
በሰውነቱ ለሰው ፡ እንደሰው ለኖረ
ንዋይ ላልወሰነው ፡ ደሙን ለገበረ

ዕሁድ ፳፰- ፪- ፪፼፲፬ ዓ.ም
ከምሽቱ ፭ ፡ ፵፭
@kaliye06
ከዘፍጥረት ቀን ከጥንቱ ጀምሮ
ጥንድ ነበረ የሰው ጆሮ
የሩቁን አድማጩ ከቤት ከማጀቱ
አሁንማ ያሰጋል አንዱም መስማቱ
𝙠𝙖𝙡
ከበደ ሚካኤል
'
ዝ ን ጀ ሮ
🦧 🦧
አንዲት ዝንጀሮ ናት
የምታስደንቀን፣
ሥራዋን ስናስብ
ዘዴኛ ናት ብለን።
አንድ ቀን ስትሄድ
ጥቅጥቅ ባለው ጫካ፣
በመላው አካሏ
ብዙ እሾህ ተሰካ።
እንዳትቀመጥም
ወይም እንዳትቆም፣
ወግቶ አስጨንቋት
ተጠምቃ በደም።
አንድ ሰው አየና
ቀርቦ ጠየቃት፣
'የቱን ልንቀልልሽ
ንገሪኝ' አላት።
'ሁሉንም ለማውጣት
አልተቻለኝም፣
ቸኩያለሁና
ጊዜ አላገኝም'።
'ከነቀልህልኝስ'
አለችው 'ጌታዬ፣
መጀመሪያ ይውጣ
የመቀመጫዬ፤
ቂጤ መሬት አርፎ
ትንፋሼን ካገኘሁ፣
የቀረውን ሁሉ
እኔ አወጣዋለሁ'።
ይህንን ተናግራ
ዝንጀሮ አረፈች፣
እሾሁን በተራ
እያወጣች ጣለች።
👇
የመቀመጫችን
የአገር ነገር፣
ከሌላው ጣጣችን
ይቅደም ይጀመር።
በጣም ቢቸግረን
በጣም ቢከፋን፣
ይኽንን ታግሰን
ለአገር ከለፋን፣
ኋላ ደስ ይለናል
አንቁረጥ ተስፋን።
--------------------------
ኢትዮጵያ ትቅደም 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
📖 📖 📖 📖 📖
@poem06
የመሻገር_ሲቃ
ደራሲ- ኢቫን ካንኪር (ዩጎዝላቪያ)
ተርጓሚ- ያዕቆብ ብርሃኑ

በእያንዳንዱ ምሽት ታዳጊዎቹ ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊት ሰብሰብ ብለው ማውጋት ይወዳሉ፡፡ በሰፊው ምድጃ አጠገብ ተቀምጠው ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ያንሾካሹካሉ። በደብዛዛው መስኮት በኩል ወደ ክፍሉ የሚያጮልቁትን የምሽት ፍዝ አንጸባራቂ ብርሃናት ህልም በተሞሉ ዓይኖቻቸው ይመለከታሉ፡፡ በእያንዳንዷ ጥጋጥግ የፀጥታ ጥላዎች ግር የሚሉ እንግዳ ተረቶችን ተሸክመው ይገዝፋሉ፡፡

ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ቢናገሩም ቅሉ ወደ አዕምሮአቸው የሚመጡት የጸሐይ ብርሃንና ግለት (የስሜት) ከፍቅርና ተስፋ ጋር የተጠላለፉባቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ ለእነሱ የሚቀጥለው ጊዜ በሙሉ አንድ ረጅም የደመቀ ክብረ በዓል ነው፡፡ በገና እና በፋሲካ በዓል መካከል እንኳን የሁዳዴ ጾም የለም፡፡ እዚያ የሆነ ቦታ በአበቦች ካሸበረቀው መጋረጃ ጀርባ የምልዓተ ሕይወት እርግብግቢት፣ ትርታ ሁሉ በጸጥታ ከብርሃን ወደ ብርሃን ይንቆረቆራል፡፡

ቃላት በለሆሳስ ይነገራሉ፤ በከፊል ብቻ ግንዛቤ መረዳት ይወሰድባቸዋል። የትኛውም ተረት መነሻም ሆነ ቅርጽ፣ የትኛውም ተረት መቋጫ የለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንድ ጊዜ አራቱም ልጆች ያወራሉ። ሆኖም ማንኛቸውም አይደናገሩም፡፡ ሁሉም ዓይኖቻቸውን ትኩር አድርገውና ተመስጠው የእያንዳንዱን ቃል ግልጽና እውነተኛ መሆን፣ የእያንዳንዱ ተረት ጉልህና ሕይወታዊ መልክ፣ የእያንዳንዱ ተረት ሞገስ ያለው አጨራረስ በብሩህና በጣም አስደሳች በሆነው ጸዳል በኩል መንፈሳቸውን ሰብስበው ይመለከታሉ፡፡

የምሽቱ የሰከረ ድንግዝግዝ ብርሃን መልካቸውን ከማመሳሰሉ የተነሳ የአራት ዓመቱን ታዳጊ ቶንቼክ ከታላቋና አስር ዓመቷ ሎይዝካ መለየት አይቻልም፡፡ ሁሉም ቀጭን ጠባብ ፊቶችና ትላልቅ የተበለጠጡ ወደ ውስጥ የሚመለከቱ ዓይኖች አሏቸው፡፡

በዚያ ምሽት ግን የሆነ ያልታወቀ ነገር ካልታወቀ ቦታ ከሀይለኛና ቁጡ እጆቹ ጋር ወደ ብሩህና አስደሳቹ ብርሃን ገብቶ በተረቶች፣ በበዓላትና በአፈ ታሪኮች መካከል ጨካኝ ሆኖ ታየ፡፡ ደብዳቤው (ፖስታው) አባትዬው በኢጣሊያ አፈር ላይ መውደቁን የሚገልጽ ዜና አስከትሎ መጣ። የሆነ የማይታወቅ፣ አዲስ፣ እንግዳ የሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት የሚያስቸግር ነገር ገጠማቸው፡፡ እዚያው ቆሟል፤ ረጅም ሰፊ ቢሆንም፣ ነገር ግን ዓይን፣ ፊትም ሆነ አፍ የለውም፡፡

ሁኔታው ከምንም የማይመሳሰል፣ ጩኸት ከበዛበት ሕይወትም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከመንገድ ላይ፣ ከምድጃው ወጋገንም ሆነ ከተረቶቹ የማይገጥም ነገር ነበር፡፡
ምንም የማያስደስት በተለየ ሁኔታ የማያሳዝን ሙት ነገር ይመስላል፡፡ ምንም ዓይኖች ስለሌሉት ከየት እና መቼ እንደመጣ ሊያብራራ የሚችል አንደበት የለም፡፡ ልክ ከግዙፍ ግንብ ፊት እንደቆሙ ሁሉ ከዚያ አንድስ የሚያህል ጣዕረ ሞት እንግዳ ሁነት ፊት ትሁትና አይናፋር መስለው ያለ ንቅናቄ ቆሙ፡፡
‹‹ግን መቼ ነው የሚመለሰው?›› አለ ቶንቸክ በመገረም፡፡

ሎይዝካ ጎንተል አድርጋውና በቁጣ ስሜት ተመልክታው፤
‹‹ከወደቀ እንዴት ተመልሶ ሊመጣ ይችላል?›› አለችው፡፡
ሁሉንም ዝምታ ዋጣቸው፡፡ እዚያ ግዙፍ ጥቁር ግንብ ፊት ቆሙ፡፡ ከግዙፉ ነገር ባሻገር ምንም ማየት አልቻሉም፡፡
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ›› ሳይጠበቅ የሰባት ዓመቱ ማቲቼ አሳወቀ፡፡ ሁኔታው ልክ ትክክለኛውን ሀሳብ እንዳገኘ ሰው ነበር።
‹‹በጣም ትንሽ እኮ ነህ!›› የአራት አመቱ ቶንቼክ ገሰጸው፡፡

ደቃቃዋና ህመምተኛዋ ሚልካ በእናቷ ግዙፍ የአንገት ልብስ ተውጣና የመንገደኛ ሻንጣ መስላ ከሆነ የጨለማው ጥግ በዚያ ስስ ቀጭን ድምፅዋ፤
‹‹ጦርነት ግን ምን ይመስላል? ማቲቼ ንገረን? ታሪኩን ንገረን?››
ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹ደህና፣ ጦርነት ማለት እንዲህ ነው። ሰዎች በጩቤ ይወጋጋሉ፤ በሰይፍ ይሞሻለቃሉ፤ በጠመንጃ ይገዳደላሉ። የበለጠ ሰው መውጋትሽ፣ መቆራረጥሽ ስኬት ነው፡፡ ይህን ስላደረግሽ ማንም ምንም አይልሽም፡፡ ምክንያቱም የሚደረገው እንዲያ ነው፡፡ ጦርነት ማለት ይሄ ነው፡፡››

‹‹ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ የሚቆራረጡት የሚሞሸላለቁት?›› ሚልካ ነበረች፡፡
‹‹ለንጉሱ ነዋ!›› አለ ማቲቼ… ሁሉም በዝምታ ተሸበቡ፡፡
በደብዛዛው ርቀት በፈዘዙ ዓይኖቻቸው ስር የሆነ ግርማ ያለው አንፀባራቂ ነገር ድንገት ብልጭ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ላይ እንዳሉ ሁሉ ትንፋሻቸው እንዳይሰማ ሆነው ደንዝዘው ተቀመጡ፡፡ የተጫናቸውን ከባድ ዝምታ ለመስበር በሚመስል ሁነት ማቲቼ በፍጥነት ሀሳቡን ሰብስቦ፤
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ፡፡ ጠላቶቼን እፋለማቸዋለሁ፡፡›› አለ፡፡
‹‹ጠላት ግን ምን ይመስላል? ቀንድ አለው እንዴ?›› ድንገት ሚልካ በቀጭን ድምፅዋ ጠየቀች፡፡

‹‹አለው! አለው እንጂ ከሌለውማ ምኑን ጠላት ሆነ፡፡›› የተበሳጨ በሚመስል ጉልህ በሆነ ድምጽ ቶንቼክ መለሰላት፡፡ ሆኖም ማቲቼ ራሱ ትክክለኛውን መልስ አላወቀውም፡፡
‹‹ቀንዶች… ያለው አይመስለኝም፡፡›› በሚርበተበትና ዝግ ባለ በሚቆራረጥ ድምጽ መለሰ፡፡
‹‹እንዴት ቀንድ ሊኖረው ይችላል፡፡ ጠላት እኮ እንደኛው ሰው ነው፡፡›› ሎይዝካ ባለመቀበል ድምጽዋን አሰማች፡፡ መልሳ አሰብ አድርጋ ሌላ ሀሳብ ጨመረች፤
‹‹ብቻ ነፍስ የለውም!››

ረዘም ካለ ዝምታ በኋላ ቶንቼክ ጥያቄ አቀረበ፤
‹‹ግን ሰዎች በጦርነት ላይ እንዴት ነው የሚወድቁት? ልክ እንደዚህ ወደ ኋላ?›› አወዳደቁን አሳየ፡፡
‹‹ይገድሉታል!›› ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹አባቴ ጠብመንጃ ሊያመጣልኝ ቃል ገብቶልኛል፡፡››
‹‹ከወደቀ እንዴት ጠብመንጃ ሊያመጣልህ ይችላል?›› ሎይዝካ ለዘብ ባለ ቁጣ መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እና እንዲሞት አድርገው- ገደሉት?››
‹‹ገደሉት!››
የማይታመን ዝምታና ሀዘን በሰፊው በተበለጠጡ የታዳጊ ዓይኖቻቸው በኩል ወደ ጨለማው፣ ወደ ሆነ የማይታወቅ ነገር፣ ወደ ልብ፣ ወደ አዕምሮ አፈጠጠ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ከጎጆው በር ውጭ አግዳሚ ወንበር ላይ ወንድና ሴት አያቶቻቸው ቁጭ ብለው ነበር፡፡

የመጨረሻዎቹ የምሽት ደማቅ ቀይ ጸዳል የተላበሱ የፀሐይ ጨረሮች ጨለምለም ባለው የግቢው መናፈሻ ቅጠላቅጠሎች ላይ አብረቅራቂ ጨረሮቻቸውን ፈንጥቀዋል፡፡ ከፈረስ ጋጣው በኩል ከሚሰማው መጎርነን የጀመረ፣ ጉርምርምታ የሚመስል፣ የተራዘመ፣ የታፈነ የመንሰቅሰቅ ልቅሶ በስተቀር ምሽቱ ፀጥ ያለ ነበር፡፡ ይሄው ልቅሶ እንስሳቱን ለመንከባከብ በሚል ወደ ጋጣው የሄደችው የልጅ እግሯ እናት የሀዘን እንጉርጉሮ መሆኑ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ሁለቱ እድሜ የተጫናቸው ሰዎች ልክ ከዚህ በፊት ለዓመታት፣ ለረጅም ዘመናት አድርገውት የማያውቁ ይመስል አንዱ የሌላውን እጅ አጥብቆ ይዞ ጭብጥ፣ ኩርምትና ጥግትግት ብለው፣ ምንም ሳይናገሩ እንባ በሌላቸው በተራቆቱ ዓይኖች ደንገዝገዝ ያለው ወገግታ ላይ አፍጥጠው ተቀመጡ፡፡
____ተፈፀመ___

@Write_Event
@Write_Event
የመሻገር_ሲቃ
ደራሲ- ኢቫን ካንኪር (ዩጎዝላቪያ)
ተርጓሚ- ያዕቆብ ብርሃኑ

በእያንዳንዱ ምሽት ታዳጊዎቹ ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊት ሰብሰብ ብለው ማውጋት ይወዳሉ፡፡ በሰፊው ምድጃ አጠገብ ተቀምጠው ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ያንሾካሹካሉ። በደብዛዛው መስኮት በኩል ወደ ክፍሉ የሚያጮልቁትን የምሽት ፍዝ አንጸባራቂ ብርሃናት ህልም በተሞሉ ዓይኖቻቸው ይመለከታሉ፡፡ በእያንዳንዷ ጥጋጥግ የፀጥታ ጥላዎች ግር የሚሉ እንግዳ ተረቶችን ተሸክመው ይገዝፋሉ፡፡

ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ቢናገሩም ቅሉ ወደ አዕምሮአቸው የሚመጡት የጸሐይ ብርሃንና ግለት (የስሜት) ከፍቅርና ተስፋ ጋር የተጠላለፉባቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ ለእነሱ የሚቀጥለው ጊዜ በሙሉ አንድ ረጅም የደመቀ ክብረ በዓል ነው፡፡ በገና እና በፋሲካ በዓል መካከል እንኳን የሁዳዴ ጾም የለም፡፡ እዚያ የሆነ ቦታ በአበቦች ካሸበረቀው መጋረጃ ጀርባ የምልዓተ ሕይወት እርግብግቢት፣ ትርታ ሁሉ በጸጥታ ከብርሃን ወደ ብርሃን ይንቆረቆራል፡፡

ቃላት በለሆሳስ ይነገራሉ፤ በከፊል ብቻ ግንዛቤ መረዳት ይወሰድባቸዋል። የትኛውም ተረት መነሻም ሆነ ቅርጽ፣ የትኛውም ተረት መቋጫ የለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንድ ጊዜ አራቱም ልጆች ያወራሉ። ሆኖም ማንኛቸውም አይደናገሩም፡፡ ሁሉም ዓይኖቻቸውን ትኩር አድርገውና ተመስጠው የእያንዳንዱን ቃል ግልጽና እውነተኛ መሆን፣ የእያንዳንዱ ተረት ጉልህና ሕይወታዊ መልክ፣ የእያንዳንዱ ተረት ሞገስ ያለው አጨራረስ በብሩህና በጣም አስደሳች በሆነው ጸዳል በኩል መንፈሳቸውን ሰብስበው ይመለከታሉ፡፡

የምሽቱ የሰከረ ድንግዝግዝ ብርሃን መልካቸውን ከማመሳሰሉ የተነሳ የአራት ዓመቱን ታዳጊ ቶንቼክ ከታላቋና አስር ዓመቷ ሎይዝካ መለየት አይቻልም፡፡ ሁሉም ቀጭን ጠባብ ፊቶችና ትላልቅ የተበለጠጡ ወደ ውስጥ የሚመለከቱ ዓይኖች አሏቸው፡፡

በዚያ ምሽት ግን የሆነ ያልታወቀ ነገር ካልታወቀ ቦታ ከሀይለኛና ቁጡ እጆቹ ጋር ወደ ብሩህና አስደሳቹ ብርሃን ገብቶ በተረቶች፣ በበዓላትና በአፈ ታሪኮች መካከል ጨካኝ ሆኖ ታየ፡፡ ደብዳቤው (ፖስታው) አባትዬው በኢጣሊያ አፈር ላይ መውደቁን የሚገልጽ ዜና አስከትሎ መጣ። የሆነ የማይታወቅ፣ አዲስ፣ እንግዳ የሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት የሚያስቸግር ነገር ገጠማቸው፡፡ እዚያው ቆሟል፤ ረጅም ሰፊ ቢሆንም፣ ነገር ግን ዓይን፣ ፊትም ሆነ አፍ የለውም፡፡

ሁኔታው ከምንም የማይመሳሰል፣ ጩኸት ከበዛበት ሕይወትም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከመንገድ ላይ፣ ከምድጃው ወጋገንም ሆነ ከተረቶቹ የማይገጥም ነገር ነበር፡፡
ምንም የማያስደስት በተለየ ሁኔታ የማያሳዝን ሙት ነገር ይመስላል፡፡ ምንም ዓይኖች ስለሌሉት ከየት እና መቼ እንደመጣ ሊያብራራ የሚችል አንደበት የለም፡፡ ልክ ከግዙፍ ግንብ ፊት እንደቆሙ ሁሉ ከዚያ አንድስ የሚያህል ጣዕረ ሞት እንግዳ ሁነት ፊት ትሁትና አይናፋር መስለው ያለ ንቅናቄ ቆሙ፡፡
‹‹ግን መቼ ነው የሚመለሰው?›› አለ ቶንቸክ በመገረም፡፡

ሎይዝካ ጎንተል አድርጋውና በቁጣ ስሜት ተመልክታው፤
‹‹ከወደቀ እንዴት ተመልሶ ሊመጣ ይችላል?›› አለችው፡፡
ሁሉንም ዝምታ ዋጣቸው፡፡ እዚያ ግዙፍ ጥቁር ግንብ ፊት ቆሙ፡፡ ከግዙፉ ነገር ባሻገር ምንም ማየት አልቻሉም፡፡
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ›› ሳይጠበቅ የሰባት ዓመቱ ማቲቼ አሳወቀ፡፡ ሁኔታው ልክ ትክክለኛውን ሀሳብ እንዳገኘ ሰው ነበር።
‹‹በጣም ትንሽ እኮ ነህ!›› የአራት አመቱ ቶንቼክ ገሰጸው፡፡

ደቃቃዋና ህመምተኛዋ ሚልካ በእናቷ ግዙፍ የአንገት ልብስ ተውጣና የመንገደኛ ሻንጣ መስላ ከሆነ የጨለማው ጥግ በዚያ ስስ ቀጭን ድምፅዋ፤
‹‹ጦርነት ግን ምን ይመስላል? ማቲቼ ንገረን? ታሪኩን ንገረን?››
ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹ደህና፣ ጦርነት ማለት እንዲህ ነው። ሰዎች በጩቤ ይወጋጋሉ፤ በሰይፍ ይሞሻለቃሉ፤ በጠመንጃ ይገዳደላሉ። የበለጠ ሰው መውጋትሽ፣ መቆራረጥሽ ስኬት ነው፡፡ ይህን ስላደረግሽ ማንም ምንም አይልሽም፡፡ ምክንያቱም የሚደረገው እንዲያ ነው፡፡ ጦርነት ማለት ይሄ ነው፡፡››

‹‹ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ የሚቆራረጡት የሚሞሸላለቁት?›› ሚልካ ነበረች፡፡
‹‹ለንጉሱ ነዋ!›› አለ ማቲቼ… ሁሉም በዝምታ ተሸበቡ፡፡
በደብዛዛው ርቀት በፈዘዙ ዓይኖቻቸው ስር የሆነ ግርማ ያለው አንፀባራቂ ነገር ድንገት ብልጭ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ላይ እንዳሉ ሁሉ ትንፋሻቸው እንዳይሰማ ሆነው ደንዝዘው ተቀመጡ፡፡ የተጫናቸውን ከባድ ዝምታ ለመስበር በሚመስል ሁነት ማቲቼ በፍጥነት ሀሳቡን ሰብስቦ፤
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ፡፡ ጠላቶቼን እፋለማቸዋለሁ፡፡›› አለ፡፡
‹‹ጠላት ግን ምን ይመስላል? ቀንድ አለው እንዴ?›› ድንገት ሚልካ በቀጭን ድምፅዋ ጠየቀች፡፡

‹‹አለው! አለው እንጂ ከሌለውማ ምኑን ጠላት ሆነ፡፡›› የተበሳጨ በሚመስል ጉልህ በሆነ ድምጽ ቶንቼክ መለሰላት፡፡ ሆኖም ማቲቼ ራሱ ትክክለኛውን መልስ አላወቀውም፡፡
‹‹ቀንዶች… ያለው አይመስለኝም፡፡›› በሚርበተበትና ዝግ ባለ በሚቆራረጥ ድምጽ መለሰ፡፡
‹‹እንዴት ቀንድ ሊኖረው ይችላል፡፡ ጠላት እኮ እንደኛው ሰው ነው፡፡›› ሎይዝካ ባለመቀበል ድምጽዋን አሰማች፡፡ መልሳ አሰብ አድርጋ ሌላ ሀሳብ ጨመረች፤
‹‹ብቻ ነፍስ የለውም!››

ረዘም ካለ ዝምታ በኋላ ቶንቼክ ጥያቄ አቀረበ፤
‹‹ግን ሰዎች በጦርነት ላይ እንዴት ነው የሚወድቁት? ልክ እንደዚህ ወደ ኋላ?›› አወዳደቁን አሳየ፡፡
‹‹ይገድሉታል!›› ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹አባቴ ጠብመንጃ ሊያመጣልኝ ቃል ገብቶልኛል፡፡››
‹‹ከወደቀ እንዴት ጠብመንጃ ሊያመጣልህ ይችላል?›› ሎይዝካ ለዘብ ባለ ቁጣ መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እና እንዲሞት አድርገው- ገደሉት?››
‹‹ገደሉት!››
የማይታመን ዝምታና ሀዘን በሰፊው በተበለጠጡ የታዳጊ ዓይኖቻቸው በኩል ወደ ጨለማው፣ ወደ ሆነ የማይታወቅ ነገር፣ ወደ ልብ፣ ወደ አዕምሮ አፈጠጠ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ከጎጆው በር ውጭ አግዳሚ ወንበር ላይ ወንድና ሴት አያቶቻቸው ቁጭ ብለው ነበር፡፡

የመጨረሻዎቹ የምሽት ደማቅ ቀይ ጸዳል የተላበሱ የፀሐይ ጨረሮች ጨለምለም ባለው የግቢው መናፈሻ ቅጠላቅጠሎች ላይ አብረቅራቂ ጨረሮቻቸውን ፈንጥቀዋል፡፡ ከፈረስ ጋጣው በኩል ከሚሰማው መጎርነን የጀመረ፣ ጉርምርምታ የሚመስል፣ የተራዘመ፣ የታፈነ የመንሰቅሰቅ ልቅሶ በስተቀር ምሽቱ ፀጥ ያለ ነበር፡፡ ይሄው ልቅሶ እንስሳቱን ለመንከባከብ በሚል ወደ ጋጣው የሄደችው የልጅ እግሯ እናት የሀዘን እንጉርጉሮ መሆኑ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ሁለቱ እድሜ የተጫናቸው ሰዎች ልክ ከዚህ በፊት ለዓመታት፣ ለረጅም ዘመናት አድርገውት የማያውቁ ይመስል አንዱ የሌላውን እጅ አጥብቆ ይዞ ጭብጥ፣ ኩርምትና ጥግትግት ብለው፣ ምንም ሳይናገሩ እንባ በሌላቸው በተራቆቱ ዓይኖች ደንገዝገዝ ያለው ወገግታ ላይ አፍጥጠው ተቀመጡ፡፡
____ተፈፀመ___
"በዚህ ምድር ላይ ሦስት ዓይነት ሰዎች አሉ፤ የመጀመሪያዎቹ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉና እሱንም ያገኙ ሲሆኑ፤ ቀጣዮቹ ደግሞ እሱን በመፈለግ የሚደክሙና ነገር ግን ያላገኙት ናቸው፤ የመጨረሻው ዓይነቶች እሱን ሳይፈልጉ የሚኖሩ ነገር ግን ያገኙት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ አዋቂና ደስተኞች ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ሞኞችና በመከራ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፤ በመጨረሻ የምናገኛቸው ደግሞ ደስተኞች ያልሆኑ ነገር ግን አዋቂዎች ናቸው።
አንድ ቀን ከደቀ መዝሙራቸው አንዱ ወደ ሱፊው መምህር በመምጣት፦ "መምህር ሆይ የሚያፈቅራትን ሴት ማግባት ከቻለ ሰው በላይ ደስተኛ አይገኝም?" በማለት ይጠይቃል። "አለ እንጂ፤ ያገባትን ሴት ያፈቀረ እሱ የበለጠ ደስተኛ ነው" በማለት መለሱለት። ፍቅር ከመቀበል ይልቅ በመስጠት ላይ የተመሰረተ ልምምድ መሆኑን የምታሳየን ነች።
አንድ ጠያቂ የሱፊውን መምህር ሙዛፊርን በዓይናቸው የማያዩትን ነገር "አምላኬ ነው" በማለት እንዴት ሊያመልኩት እንደቻሉ ጠየቃቸውና እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ "በበረሃ ስትሄድ የግመል ዱካ በረዥሙ ተዘርግቶ ብታይ በዚያ ቦታ ግመል ማለፉን ትጠራጠራለህን!" አሉ። ጠያቂውም "ዱካውን ካየሁማ እንዴት እጠራጠራለሁ!" አለ። መምህሩም "እንግዲያውስ የአምላካችን ዱካዎች ደግሞ እኛ ብሎም ይኸ ዓለም ነውና ለእምነቴ የግድ እሱን ማየት የለብኝም" አሉት።

ጥበብ ቅጽ ፪ ከጲላጦስ(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

https://t.me/Write_Event
"ቀላል፣ የተዋበ፣ ፀጥታ የሞላበት፣ ተደሳችና የተባረከ ሕይወት መኖር የምትሻ ከሆነ የአእምሮን ስግብግብ ጥያቄዎች ጣላቸውና በምትካቸው የልብህ መልሶች ተካባቸው። የአእምሮ ጠቢብነት ነገሮችን እያወሳሰበ ዕለት ተዕለት ጥያቄን መከመር ነውና የሕይወትህ ጌታ ልብህን አድርገው። "

ኦሾ💛💛💛
https://t.me/Write_Event
--------ተስፋ-----
====ሮፍናን====
💚

ኩሽያ ፑዴ ዴንዚቴ
ቤሳ ቤሳ ቤሳ ቤስቴ ቤሳ

ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬን ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም

እልፍ ሲሄድ እልፍ ይመጣል
እልፍ ወስዶ እልፍን ይሰጣል
ለአመስጋኝ ሰው ላጣም ላገኘው
ተስፋን ስንቅ አርጎ ይይዛታል

ብርርርርርርር ይላል ልቤ ገና
ሁሉን አልፎ ቀና
ይበራል ልቤ ወቶ ከላይ
ተስፋው ነው ከሰማይ
የያዝኩት ወድቆ ቢረግፍም ብንን
ብንን ትንን
የቀናው ጥምም
ቢልም እድል ካልሆነው ጋር ዝምም
ዝምም ምንም
እጁ የለም ምንም
ምሰጠው እነሳለሁ ደግሜ
ነገን ቀድሜ
ስወድቅም እነሳለሁ ደግሜ
ደግሜ ደግሜ ደግሜ
ራሴን ሸልሜ

ፍሬ ከአፈር ይወድቃል
ቀን ጠብቆ ኖሮ
ከዚያዝ ትንሽ ፍሬ ዛፍ ይነቃል
ላባ ቀለም ይነክራል
የጠቢብ ሰው ስራ
በትንሽ ብራና አገር ይመክራል
ግንበኛ የናቀው ድንጋይ
ማዘኑን ይተው ተመርጧል
ሊውል ከመዓዘኑ ላይ
መዳን አለ በስቃይ
መጥፋት አለ በደስታም
መልካም ብቻ እርሱ የባረከው ሰማይ
ውሸታም አለም በውሸት ቀለም ስዕል ስሎ
በውሸት ምሎ


ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬን ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም

ሲሆን ሲሆን ሲሆን የቀና ሲሆን
ደስታ ነው ሀሳብ ሲሳካ ሲሆን
ደስታ ነው ሀሳብ ሲሳካ ሲሆን

ያዝልኝ
ያዝልኝ
ያዝልኝ
ያዝልኝ
ገባሁ

ደሀ እናት ተስፋዋን በልጇ አየችው
አየችው አየችው በልጇ አየችው
ተስፋዋ ልጇ ቢሆን
ተስፋዋ ልጇ ቢሆን
አንድ አመት ሳይሞላው
ተስፋዬ አለችው
ተስፋዬ አለችው
ተስፋዬ አለችው ስሙን

ተስፋዬ
ተስፋዬ
ተስፋዬ ያድጋል ተስፋ ሆኖ
ተስፋዬ ይመረቃ ጉልበት ስሞ
ጉልበቷ የተሳመው የተስፋዬ እናት
ተመስገን አለች ተስፋን ለሰጣት
ሮፍናን ተስፋን አይጥልም ያዝ ነው
የስኬት ሚስጥሩ መንገድም አንድ ነው
መፅናት እራስን ለማንሳትህ ቁልፍ ነው
ያኔ ተራራው ይናዳል ዝርግ ነው
ስኬት ሲደርሱ መች አለቀና
በማግኘት ውስጥ ማጣትም አለና
ጎበዝ ይለኛል ይህ አለም ሲዋሽ


ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬን ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም

አለም ውሸታም
ውሸታም አለም

ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ



t.me/Write_Event
የታርክ ድግግሞሽ በቅብብሎሽ አልፎ
በወንበዴው ስሌት ሚስኪን ተሰልፎ

ይሄው ...

ዛሬም በኛ ዘመን በርባኖች ሲተርፉ
እንደ ቅዱሱ ክርስቶስ ሚስኪኖች አለፉ።

#አዮነት(ቃልኪዳን )

==Join us==

@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አጓጊ እና አስተማሪ ተከታታይ ታርክ ይዘን ቀርበናል 🙏
ክፍል 1⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ከእለታት በአንዱ ቀን እንደወትሮዬ ስልኬ ካርድ ስለጨረሰ በአቅራቢያዬ ወደሚገኝ ሱቅ እየተጣደፍኩ ፊትለፊቴ ያገኘሁትን ሲሊፐር እየጎተትኩ ከቤቴ ወጣው............. የባለሱቁ ደንበኛ እንደመሆኔ ካርድ ስወስድ ያለክፍያ ነው ማለትም ደሞዝ ሲደርስ የወሩን እዘጋለው............ታድያ እንደደረስኩ "ቶፊቄ ካርድ ፋቅልኝ" የሚል አጭር ትእዛዝ ሰጠሁ "የስንት ይሁን" አለ በዛለ አንደበት "አንተ ደሞ እስኪ ዱካክህን እንዳታጋባብኝ የተለመደውን " ብዬው ፍቆ የሰጠኝን ካርድ እየሞላው መንገዴን በመቀጠል ላይ እያለው ድንገት ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ጫማዋን አጎንብሳ የምታስር እንስት አይኔ ውስጥ ገባች አጠገቧ እስክደርስ ድረስ ምን እንዳስገደደኝ ባላውቅም አይኔን መንቀል አልቻልኩም ነበር.............
እየቀረብኩ ስመጣ ይበልጥ ማረከቺኝ የሽቶዋ ጠረን ገዳይ ነገር ነው.................የለበሰችው ቡናማ ቀሚስ ጥቁር ሹራብና ቡኒ ሂጃብ ከቅላቷ ጋር የሚገርም ግርማ ሞገስን አላብሷታል............ስሜ ብሩክ ይባላል የአንድ አነስተኛ ሱፐር ማርኬት ሰራተኛ ነኝ ወደታሪኬ ስመልሳችሁ........ አጠገቧ ስደርስ ቆምኩና " ምነው ገመዱን በፓስወርድ ነው እንዴ የምታስሪው" አልኳት ቀና ብላ አይታኝ ፈገግ አለችልኝ "ያው የማግዝሽ ነገር ካለ ብዬ ነው" ብዬ የማይገናኝ ነገር ዘባረቅኩ አሁንም ምንም አላለችም ዝም ብላኝ መንገዷን ቀጠለች "ማውራት አትችልም እንዴ" ብዬ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ ድንገት "እ እ እዚ ሰፈር ነህ አይደል" የሚል ለስለስ ያለ ድምፅ ተሰማኝ "ምን አልሺኝ" አልኳት ሳልሰማት ቀርቼ ሳይሆን ድጋሚ ድምፅዋን ለመስማት ነበር "ካላስቸገርኩህ ታክሲ መያዣውን ቦታ ብታሳየኝ" አለች በውስጤ "ተገኝቶ ነው" እያልኩ "እረ ችግር የለውም ግን ክፍያ አለው" አልኳት ያንን ፈገግታዋን አሳየቺኝና መንገድ ጀመርን...............
ታክሲ መያዣው ካለንበት ቅርብ ስለነበር ወዲያው ደረስን "ደርሰናል" አልኳት መለየቷን እየጠላው "እሺ በጣም አመሰግናለው" አለቺኝ............. በርራ የምትጠፋ ይመስል ደንግጬ እጇን ያዝኳትና "በሰላም መድረስሽን ለማረጋገጥ ስ. ል. ክ. " ብዬ ሳልጨርስ " ችግር የለውም ያንተን ስጠኝና በሰላም መድረሴን አሳውቅሀለው" አለች እሺ ብዬ ቁጥሬን ሰጥቼ ተሰናበትኳት............ ስመለስ መንገዱ ረዘመብኝ ደሞስ ፀሀዩ እንዴት ነው የሚያቃጥለው በፈጣሪ ሲገርም ከሷ ጋር እያለው እኮ ምንም አልታወቀኝም ነበር በራሴ እየተገረምኩ የቤቴን በር ከፍቼ ገባሁ።

ክፍል 2⃣
ይቀጥላል

◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
💞Join & share💞
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
ክፍል 2⃣

ፀሀፊማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ፀሀዩ ያዛለውን ሰውነቴን ለማሳረፍ ያክል እንደገባው አልጋዬ ላይ ተንጋለልኩ። ነገር ግን የቅድሟ እንስት አሁንም አይኔ ላይ ትንከራተትብኛልች። እሷን እያሰብኩ በድንገት አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ስሟን እኮ አልነገረቺኝም ኤጭ ምኑ ከንቱ ነኝ በራሴ ተናደድኩ "ድጋሚ አገኛት ይሆን" ስል በድንገት "ማንን ነው ብሩኬ" ብሎ ሀምዛ በሩን ከፍቶ ገባ። ሀምዛ ማለት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ነው።ለካ ሳይታወቀኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ነበር። "ምን ባክህ ያቺ ባለፈው ዱቤ የወሰደችውን ልጅ እኮ እስካሁን አልመጣችም ስለሷ እያሰብኩ ነው" ብዬ የመጣልኝን ተናገርኩ። " እንዴ ገና ትላንት እኮ ነው የወሰደችው መቼስ በእሁድ ቀን ቤትህን አንኳኩታ እንድትመልስ አልፈለክም አይደል" ብሎ ሳቀ። አይ የኔ ነገር ልጅቷማ የሆነ ነገር አስነክታኛለች እንጂ በጤናዬማ እንዲ አልዘላብድም አልኩ በውስጤ "እና አኖጣም እንዴ ምነው ዛሬ ፈዘሀል" አለ ሀምዛ " እረ ምን እፈዛለው ሻይ ቡና እንበል እስኪ ትንሽ ድብርቱ ከለቀቀኝ" አልኩትና ኤርፎኔን እና ስልኬን ይዤ ከቤት ወጣን።
በተደጋጋሚ ስልኬን ባየውም እስካሁን አልደወለችም።
ደሞም ግራ ገባኝ ለሰአታት ብቻ ላየዋት ሴት እንዲ መጨነቄ ለራሴም ገርሞኛል። ሀምዛ ሁኔታዬ ከቅድም ጀምሮ ደስ ያለው አይመስልም" ብሩኬ ችግር አለ እንዴ ዛሬ ልክ አይደለህም" አለኝ። ሰምቼዋለው ግን ምንም ማለት ስላልፈለኩ ዝም አልኩት። እሱም ሰለቸው መሰለኝ ጥያቄውን አቁሞ መሄድ ጀመረ።የእጄን ሰአት አየሁት 9:45 ይላል። ስልኬንም በዛው ሾፍ አረኩት ምንም አዲስ ነገር የለም። ውስጤ ዝም ብሎ ይረበሽብኛል ምን እየተሰማኝ እንደሆነ እንኳን በግልፅ ሳይገባኝ ካፌው ደረስን። አስተናጋጇ ልትታዘዘን መጣች " ምን ይምጣ" አለች በሚለማመጥ አይነት ድምፅ "ቡና" አልኩ " ደሞ ከመቼ ጀምሮ ነው ቡና መጠጣት የጀመርከው" አለ ሀምዛ እንደመገረም ብሎ። " ማማዬ ቡናውን ለኔ አርጊውና ለሱ ቀዝቃዛ ማልት አምጪለት" ብሎ ሸኛት።
ቀና ብሎ ሲያይኝ አንገቴን ስልኬ ላይ እንደተከልኩ ነኝ። " ይቅርታ ብሩኬ ዝም ስትል ጨነቀኝ እኮ ቆይ የተፈጠረ ነገር ካለ ንገረኝ መደባበቅ ጀመርን እንዴ" አለኝ ሲመረው። የዛሬው ሁኔታዬ ከወትሮው ተከይቶበታል ለዛም ነው በተደጋጋሚ የሚጠይቀኝ "ኡፍፍፍፍፍፍ" አልኩኝና "እሺ በቃ እንደዛ አታስብ ሁሉንም እነግርሀለው" አልኩት። አስተናጋጇ የታዘዘችውን ይዛ መጣችና አቋረጠችን።
አቅርባ ከሄደች ቡሀላ ሀምዛ ቡናውን እያማሰለ እንድቀጥል ምልክት ሰጠኝ። እኔም ለመናገር ጉሮሮዬን ጠራርጌ " ምን መሰለህ ሀምዚ ቅድም ካርድ ልገዛ ስወጣ" ብዬ ሳልጨርሰው ስልኬ ጠራ ደንግጬ አየሁት የማላውቀው ቁጥር ነበር ደስስስስ የሚል ስሜት ሁለመናዬን ሲወረኝ ይታወቀኛል ስልኩን ይዤ ፈዝዤ ቀረው "ብሩኬ" አለ ሀምዛ ቀና ስል "አንሳው እንጂ ምን ያፈዝሀል" አለኝ አንገቴን በእሺታ ነቅንቄ ስልኩን አነሳሁት........

ክፍል3⃣
ይቀጥላል
◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
💞Join & share💞
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
ክፍል 3⃣

ፀሀፊማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

"ሄሎ" አልኩኝ ከስልኩ የሚመጣውን ድምፅ ለመስማት በጉጉት ላይ እንዳለው።
"ሄለው"የሚል የሴት ድምፅ ተሰማኝ ደስታ ይሁን እብደት የማላውቀው ስሜት ከመቀመጫዬ አስነሳኝ ሀምዛ ሁኔታዬን በግርምት ከመመልከት ውጪ ምንም ሊል አልደፈረም ብቻ እንደቆምኩ አስታወሰኝና ተቀምጬ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቴን ስልኩ ላይ አደረኩ።
" እ እ ይቅርታ ማን ልበል" አልኳት ስሟን ለማወቅ እየጓጓው "እስክደውልልክ እየጠበክ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ ለማንኛውም ቅድም የሸኘኸኝ ልጅ ነኝ ላመሰግንህና በዛውም በሰላም መድረሴን ልነግርህ ነው የደወልኩት" አለቺኝ። ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ድጋሚ የማላገኛት መስሎ ተሰማኝና በሚያሳዝን አስተያየት ሀምዛን ቀና ብዬ አየሁት አይቶኝ ፈገግ አለ "ምስጋናው እንኳን በአካል ቢደርሰኝ ደስ ይለኛል" አልኳት እየፈራው "ውይ በጣም ይቅርታ እሩቅ ነው ያለሁት ያለሁበት መምጣት ከቻልክ ግን ችግር የለውም" አለች በፍጥነት " ባንድ አፍ የት እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ ነገ እመጣለው" አልኩ "እንደመገረም ብላ እሺ ያለሁበትን ቴክስት አረግልሀለው" አለችኝ "ግን እኮ ስምሽን አልነገርሽኝም" አልኩኝ "ፍርዶስ እባላለው ያንተን ማን ልበል" አለች "እ እ ብሩክ ብሩክ ነው ስሜ" አልኩ እየተንተባተብኩ "እሺ በቃ ብሩክ እንደዋወላለን ቻው" ብላ ስልኩን ዘጋችው።

ቀና ብዬ ሀምዛን ሳየው ፊቱ ተቀያየረብኝ በቅንድቤ ምልክት እየሰጠው ምነው ብዬ ጠየኩት
"ይቅርታ አድርግልኝና ሁኔታህ ምንም ደስ አላለኝም ሲቀጥል ነገ ስራ ገቢ ነህ እኮ እንዴት እመጣለው ትላታለህ?" ብሎ አፈጠጠ። እውነቱን ለመናገር ያልኳትን ነገር በቅጡ ራሱ አላስታውስም ግን ምንም ልበላት ምን ውስጤ ልክ እንደሆንኩ እየነገረኝ ነው "አንተ ደሞ ሁሉንም ታካብደዋለህ በቃ ለቦስ ማታ ደውዬ እንዳመመኝና መምጣት እንደማልችል እነግረዋለው የቀረውን አንተ ታሳምንልኛለህ በል አሁን ተነስ እንሂድ እየመሸ ነው" አልኩትና ሂሳብ ከፍለን ወጣን።

"ብሩኬ ካልደበረህ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" አለኝ ሀምዛ "ምንም ባትጠይቀኝ ደስ ይለኝ ነበር ግን ምንድነው ጥያቄህ" አልኩት።
"ቆይ እሷ ማን ናት ቅድም እኮ ያስጨነቀህን ነገር ጀምረህልኝ ነበር አልጨረስከውም" አለኝ ሀምዛ ሁኔታዬ በጣም ግራ አጋብቶታል ለዛም ነው ስለሁኔታው ለማወቅ በጣም እየጣረ ያለው። እኔም ደስ ይበለው ብዬ ከመጀመሪያ ጀምሬ የተፈጠረውን ተረኩለት። ሰምቶኝ ሲያበቃ "ግን ትንሽ አልፈጠንክም? በዛ ላይ እንደነገርከኝ ከሆነ ሀይማኖታችሁ ይለያያል እያሰብክ ያለኸው ትክክል አይደለም" አለኝ እውነት ለመናገር ሀይማኖት ሚባለውን ነገር ያሰብኩት አሁን ነው ግን ለሱ የግድ መልስ መስጠት ስለነበረብኝ " የወደድኳት እሷን ነው ደግሞስ ሀይማኖት ከሰውነት ይበልጣል እንዴ? ሰው ሲኖር ነው አይደል ሀይማኖት የሚኖረው? ደግሞስ ሀይማኖት የሚባለው ነገር ሀይልና ገደብ ቢኖረው እኔን ሊያስቆመኝ አይችልም ነበር?" ሳይታወቀኝ ሀምዛ ላይ አፈጠጥኩበት "እሺ በቃ ብሩኬ አትናደድ እኔ እንደዛ አስቤው አይደለም" አለኝ እንደመረጋጋት እያልኩ "ባታስበው ነው ሚሻለው" ብዬው ተሰነባብተን ወደ ቤቴ ገባሁ።

ስልኬን ልሰካው ስል ቴክስት ገባልኝ ቴክስቱን ከፈትኩት ከቅድሙ ስልክ ነበር አድራሻዋን ልካልኛለች ደስ እያለኝ ስልክ ቁጥሯን ስልኬ ላይ "F የኔ" ብዬ ሴቭ አረኩትና በጥዋት እንደምመጣ ቴክስት አረኩላት "እሺ ደውልልኝ" የሚል አጭር መልእክት ላከችልኝ ደስስስስስስስስ አለኝ። ለቦስ መደወል ስለነበረብኝ ደውዬ ያሰብኩትን ድራማ ተወንኩና በመስማማት ስልኩ ተዘጋ።
እኔም ሲጨናነቅ የዋለውን አይምሮዬን ለማሳረፍ ያክል ጋደም አልኩ ግን እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ከብዙ ልፋትና ልምምጥ ቡሀላ ሸለብ አደአደረገኝ።

ክፍል 4⃣
ይቀጥላል

◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆

💞Join & share💞
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
ክፍል 4⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ከእንቅልፌ ስነቃ እጄ ላይ ያለው ሰአት ከጥዋቱ 4:23 ይላል ስራ መሄድ አልፈለኩም በዛ ላይ አርፍጃለው ግን ደግሞ እቤት መዋሉን አልፈልገውም ጭንቀቱ ሊገለኝ ነው የሚደርሰው ስልኬን አየሁት የሀምዛ ሶስት ሚስኮል አለው። ተጨንቆ ነው የሚሆነው ከትላንት ጀምሮ ስልኩን አልመለስኩለትም ልብሴን ቀያይሬ ወደ ሱቅ ለመሄድ ወጣው።
ስደርስ ሀምዛ ውጪ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት ገና እንደደረስኩ በጥያቄ ማጣደፍ ጀመረ"ቆይ አንተ ለምንድነው ስልክ ማታነሳው በዛ ላይ ትላንት ቀኑን ሙሉ ስጨነቅ ነበር እንዴት ዝም ትላለህ አንዴ እንኳን አደውልም እንዴ?" አለኝ"ኡፍፍፍ በናትህ ሀምዛ ከቻልክ ዝም በለኝ" ብዬው ወንበሩን ስቤ ተቀመጥኩ "እሺ ትላንት የተፈጠረውን በዝርዝር እንድትነግረኝ እፈልጋለው" አለኝ አጠገቤ ወንበር አምጥቶ እየተቀመጠ

*ትውስታ 1
ወፎች ንጋትን ሊያበስሩ ዝማሬያቸውን ሲያሰሙ በልምምጥ የወሰደኝ እንቅልፍ ካለሁበት መለሰኝ ቀጠሮውን እያሰብኩ ያደርኩበትን ልብስ ቀያይሬ በእርግጠኝነት ለመነሳት ያክል ደወልኩላት ብዙ ጥሪዎች ካለፉ ቡሀላ አነሳችው
"ሄለው" አለች
"ከእንቅልፍሽ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?"
"አይ ተነስቼ ነበር ደና አደርክ"
"ደህንነቴን እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም ማደሩን ግን አድሪያለው"
ሳቀችና "ዋናው ማደርህ ነው" አለች
" እ. እ. ከቤት እየወጣሁ ስለሆነ እንዳታረፍጂ ልነግርሽ ነበር የደወልኩት" አልኩኝ እየፈራው
"እሺ ስትደርስ ደውልልኝ" አለችኝና ስልኩን ዘጋችው።
ፈጥና ስለዘጋችው ብገረምም ጥዋት ስለሆነ ጃኬቴን ደርቤ ከቤት ወጣው
መንገድ ላይ እያለው መልሼ ደወልኩላትና የምንገናኝበትን ካፌ ተነጋግረን ስልኩ ተዘጋ
ቦታው ላይ ስደርስ የተሳፈርኩበትን ታክሲ ሂሳብ ከፍዬ ወረድኩና ቀጥታ ወደቀጠሮው ቦታ አመራው ስደርስ አልመጣችም ቦታ ያዝኩና ደወልኩላት ስልኩ አይነሳም መንገድ ላይ ትሆናለች ብዬ አሰብኩና ቀዝቃዛ ውሀ አዝዤ የእጄን ሰአት ተመለከትኩት 5:10 ይላል እንደምትመጣ እያሰብኩ ጥበቃዬን ቀጠልኩ ትንሽ ከቆየው ቡሀላ ስልኳን በድጋሚ ሞከርኩት ዝግ ነበር ግራ ገባኝና ደጋግሜ ሞከርኩት አሁንም አይሰራም ውስጤ የተተረማመሰ ስሜት ይሰማኛል ብቻ ትንሽ መታገሱ ይሻላል ብዬ ስልኩን መሞከር አቆምኩና እንዲሁ መጠበቅ ጀመርኩ በዛ መሀል ድንገት ስልኬ ጠራ በደስታ ውስጥ ሆኜ ሳየው ሀምዛ ነበር ተናድጄ ዘጋሁበት በድጋሚ ደወለ ድምፁን አጠፋሁትና ዝም አልኩት በዚ ሰአት የሱን የማያልቅ ጥያቄ የምመልስበት ጊዜ የለኝም ብዙ ሞክሮ ሲሰለቸው መደወሉን አቆመና ቴክስት ላከልኝ "ለምንድነው ስልክ ማታነሳው" ይላል መልእክቱ አይቼው ዝም አልኩት
ሳይታወቀኝ ብዙ ቆየው መሰለኝ አስተናጋጇ ድጋሚ መጥታ "ምን ይምጣ" አለችኝ "ሰው እየጠበኩ ነው" አልኳትና ሰአቴን አየሁት 8:30 ሆኗል ስልኳን መሞከር እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ደወልኩ አሁንም እንደተዘጋ ነው።

ክፍል 5⃣
ይቀጥላል
◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆

💞Join & share💞
👇👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
<<……እኔ መምህር አይደለሁም ምክንያቱም ምንም የማስተምራችሁ ነገር የለኝም ። ማስተማር ማለት ማስለመድ ነው፤ ማስተማር ማለት አንድን የተወሰነ እምነት መስጠት ነው፤ ማስተማር ማለት ቃላት የፖለቲካ ዘይቤዎች፤ ፍልስፍናዎች መስጠት ነው። እኔ ደግሞ ምንም ነገር እየሰጠኋችሁ አይደለም። የኔ ስራ መስጠት ሳይሆን ማንኛውንም ነገር፣ ከሆነ ቦታ ሰብስባችሁ ያጠራቀማችሁትን ሁሉንም ነገር #ለማጥፋት_መሞከር ነው። መሰብሰብ ስለምትወዱ ከእኔም ሰብስባችሁ ሊሆን ይችላል። ደቃቅ የብረት ብናኞች ከየአቅጣጫው መጥተው ማግኔት ላይ እንደሚጣበቁ ሁሉ፤ ብዙ ነገሮች ከሁሉም አቅጣጫ እየመጡ ይጣበቁባችኋል። የዚህ አይነቱን ያለማቋረጥ የወዳደቁ ነገሮችን የመሰብሰብ ሁኔታ ለማጥፋት ነው የኔ ፍላጎት_ ይህንን ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ። ... >>
/ ኦሾ /

ምንጭ ፦ ብርሃነ ኅሊና



┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
ክፍል 5⃣

ፀሀፊ ማኪ

#ያልተፈታ_ቅኔ

ሰአቱ በጣም እየሄደ ነው እሷን ለማግኘት ከመጓጓቴ የተነሳ ካፌው ውስጥ ያለውን ሰው እንኳን አላስተዋልኩም ውስጤን ማረጋጋት ስላቃተኝ ስልኳ አልሰራም እያለኝ እንኳን ደጋግሜ መሞከሬን አላቋረጥኩም ደግሞም ግራ ገባኝ መቅረት ከፈለገች ቀርቻለው አትልም እንዴ? እላለው መልሼ ደግሞ ምናልባት ችግር አጋጥሟት ይሆን? እያልኩ እጨነቃለው ከበሩ ፊት ለፊት ስለሆነ የተቀመጥኩት ሰው በገባ ቁጥር እሷ የመጣች እየመሰለኝ ካሁን አሁን ገባች እያልኩ ከበሩ ላይ አይኔን መንቀል አልቻልኩም።
አሁንም ሰአቴን አየሁት በጣም ረፍዷል ከዚ ቡሀላ እንደማትመጣ ራሴን አሳምኜ የውሀውን ሂሳብ ከፍዬ ከካፌው ወጣው ስልኳን በድጋሚ ብሞክረውም ሊሰራልኝ አልቻለም ውስጤ ምን አይነት ስሜት እንዳለ እንኳን ሳይገባኝ ታክሲ ይዤ ወደቤቴ መመለስ ጀመርኩ።
በሀሳብ ብዙ ቦታ መሄድ ጀመርኩ በትንሹ ተናድጃለው ግን ደግሞ ችግር ገጥሟት ቢሆንስ ብዬም ተጨንቂያለው በመሀል የታክሲው ረዳት "ባባ ሂሳብ" ብሎ ከገባሁበት ስምጥ የሀሳብ ባህር ጎትቶ አሶጣኝ "እሺ ይቅርታ" ብዬ ሂሳብ ከፈልኩ እና ደግሞ መውረጃዬም ስለተቃረበ ሀሳቤን ሰብስቤ ለመውረድ ተዘጋጀው እንደደረስኩ "ወራጅ አለ" አልኩትና ከታክሲው ወረድኩ የሆነ ባዶነት ውስጤን ሲወረኝ ታወቀኝ ሀይለኛ ራስ ምታት ወዲያው ራሴን ወጥሮ ሲይዘኝ ይታወቀኛል ድጋሚ የማላገኛት መሰለኝ ብቻ እንደምንም የእርምጃዬን ፍጥነት ጨምሬ እቤት ደረስኩ ገና እንደገባው እንደምንም ልብሴን ቀያይሬ አልጋዬ ላይ ራሴን አሳረፍኩት ድካሙ ነው መሰለኝ ወዲያው እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

#ከትውስታ_መልስ
የተፈጠረውን አጠር አድርጌ ለሀምዛ ተረኩለት በዝምታ ካዳመጠኝ ቡሀላ
"እና ዛሬ ደወልክላት" አለኝ

"አይ አልሞከርኩትም"አልኩት

"ለምን አሁን አትሞክረውም"አለኝ
እሺ ብዬ ስልኳን ሞከርኩት መጥራት ጀመረ ነገር ግን አይነሳም በድጋሚ ሞከርኩት አሁንም ይጠራል አታነሳውም በጣም ስለተናደድኩ ስልኬን ወረወርኩት ሀምዛ ሁኔታዬ ግርምትን ፈጥሮበታል ስልኬን እንደምንም አፋፍሶ ይዞልኝ መጣና ስልኩን ገጣጥሞ ከፍቶ ቁጥሯን በራሱ ስልክ ላይ መዝግቦ ደወለላት ብዙም ሳይጠራ አነሳችው
"ሄሎ" አለ ሀምዛ ተናድጄ ስልኩን ቀማሁትና
"ይቅርታ ካስቸገርኩሽ ግን ቢያንስ ስልኩን አንስተሽ በግልፅ መናገር ትችዪ ነበር ለማንኛውም ቀጥረሺኝ ስለቀረሽ ደስ ብሎኛል"ብያት ስልኩን ዘጋሁት። ውስጤ ቅጥል ሲል ይታወቀኛል ለሀምዛ ስልኩን ልመልስለት ስል ደግማ ደወለች ዘጋሁትና ድጋሚ ከደወለች እንዳያነሳ አስጠቅቄ ስልኩን ሰጠሁት።
ትንሽ ከቆየው ቡሀላ ለመሄድ ተነሳው ሀምዛ
"ብሩኬ ወዴት ነው?" አለኝ
"እኔንጃ ብቻ ከደወለች እንዳታነሳው ነገ እንገናኛለን" ብዬው መንገዱን ጀመርኩ በመሀል ስልኬ ጠራ *F የኔ* ይላል ተናድጄ ዘጋሁትና ስልኩን "#ያልተፈታ_ቅኔ" ብዬ ሴቭ አደረኩት ስሙን ድጋሚ ሳነበው ፈገግ አስባለኝ።

በመንገዴ ያገኘሁት ሬስቶራት ገባሁና ቀዝቃዛ ቢራ አዝዤ ቁጭ አልኩኝ ሬስቶራንቱ ውስጥ የተከፈተው ስፒከር የታምራት ደስታን ዘፈን ያጫውታል በዘፈኑ ተመስጬ አንድ ሁለት ማለት ጀመርኩ።
🎤ሰው ኖሮሽ እንደሌለው
🎤ለይምሰል መታየቱ
🎤ማስረዳት መንገር ስትችይ
🎤ሁሉንም በሰአቱ
🎤ፍቅር ፍቅር ሲያሰኘኝ
🎤ትዝ ሲለኝ ስሜቱ
🎤ቆይ ለምን አስፈለገ
🎤ማስመሰል መዋሸቱ.......

ክፍል 6⃣
ይቀጥላል
◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━

┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❝Join & share
👇👇👇👇👇
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
📚 @Write_Event
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛