ቃላዊ
342 subscribers
38 photos
6 videos
1 file
122 links
በዚህ ቻናል
◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች
◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች
◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች
◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች
◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ
በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች
በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው።

ግጥም ለመላክ
@Melikitegna_bot
Download Telegram
ለግዜር የተፃፈ ደብዳቤ
(አሌክስ አብርሃም)

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ.....
ለእልፍ አእላፍ አለቃ… ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ …መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን ….እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ …..ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው ሁለት ሽ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም...
‹‹በመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው
‹‹እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል!!
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እ ን ደ ጉ ድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ?
እኛማ ይሄውልህ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ?!
እናልህ እግዜር ሆይ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ!!
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?!
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
ያስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
ያስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር!!
ኧረ እግዜር በናትህ....
ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን!
ስንቱ ባለካባ ክብርህ የተሰጠው
ለሰላሳ ፍራንክ ለተራ ጭብጨባ አደራህን ሸጠው !
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነውኑሮ ተስማምቶታል....
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!

(እናት ፍቅር ሐገር ከሚለው የግጥም መፅሃፍ ገፅ 9 የተወሰደ)

Join n share
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
Channel photo updated
"ዝግመተ ለውጥ"

" እንጋባ" ብሎ ጠየቃት፥ አሳምነው።
አልተቀበለችውም አስማሩ፡፡ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው፡፡ ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል፡፡ ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፡፡ ካላት ታቀርባለች- ይበላሉ፡፡ አውግተው ይለያያሉ፡፡ የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም፡፡
አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ጸሃይ መጣ፡፡ እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ፡፡ ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው እረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት፡፡

ዳግም ሲመጣ ደርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም፡፡
ጃኬቱን አውልቆ ሄደ፡፡
አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው፡፡
ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!"አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፥ አጥባ አኖረችው፡፡
አንድ ቀን በጠራራ ጸሃይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፡ አስማሩ " ምነው?" አለችው። " በጠራራ ጸሃይ ብርድ ሆዴ ገባ" አላት፡፡ " ምች ይሆናል" አለቺው፡፡
የምች መድሃኒት ብታሽለት ተሻለው፡፡
ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም፡፡ ጥሎት ሄደ።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።
ትንሽ ቆይቶ፥ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ፡፡
"ምነው?" አለችው፡፡ "ላሳድሰው መሄዴ ነው፡፡ አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው።" አላት። አመነችው፡፡

ጨዋታው ደራ፡ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ላይ መጣ፡ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሽዋ ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ "ተነሽ" ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀሎት ተገኘ።
ጠጋ አለችለት፡፡


(ከዓለማየሁ ገላጋይ ኩርቢት ገጽ 11)
Join n share
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
አገሬን ብቻ ሳይሆን መንግስቴንም እወዳለሁ፣ አከብራለሁ። የምወደውና የማከብረውም በአፌ ሳይሆን ከልቤ ነው። ይህም በመሆኑ ነው እንደሌላው ሳልጠፋ በህጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ምድር ለመውጣት የፈለግሁት።

ከኢትዮጵያ ምድር ወጥቼ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም። በአሳቤ ያለው የአማርኛ የህትመት ፊደል ካለበት አገር ሄጄ የማውቀውን የኢትዮጵያን ታሪክ እያሳተምሁ ለመኖር ነው። ድግሜ የምናገረው ያደግሁበትንና የኖርኩበትን አገሬን፣ የምወደውንና የሚወደኝን የኢትዮጵያን ህዝብ ከድቼ አይደለም። ስራዬን ከማልወረስበት አገር ሰርቼ ካልሞትሁ ለመቀበር ወደ አገሬ የምመለስ ሰው ነኝ።

እንኳን ከኢትዮጵያ ውጪ ከአዲስ አበባ ደብረ ዘይት የምሄድበት ገንዘብ የለኝም። ጥረቴ መፅሃፍ በመግዛትና ይህን በመሳሰለው ስለነበረ ኑሮዬም የተመሰቃቀለ ነው። ስለዚህ ጓድነትዎን የምለምነው ሶስት ነገሮችን ነው፤

፩ኛ) የሚወዱኝን ኢትዮጵያውያንን የመሳፈሪያ ገንዘብ እንድለምንና እንዳጠራቅም እንዲፈቀድልኝ ነው። ይህን ሳላሳውቅ ልመናዬን በሚሥጥር ባደርገው የመንግስቴን ስም ለማጥፋት የተነሳሁ ስለሚመስልብኝ እንደዚያ አይነቱን ነገር አልፈለግሁም። አላደርገውም። የሚቻል ቢሆን በጋዜጣም ሆነ በቃል ለመለመን እንድችል የፈቃድ ወረቀት እንዲሠጠኝ፣ በወረቀት መፍቀዱ የማይቻል ከሆነ ግን ልመና ለመጀመር መነሳሳቴን መስሪያ ቤቱ አውቆ በቃል እንዲፈቀድልኝ ነው።

፪ኛ) የምሄድበትን አገር ርቀት የሚወስነው በልመና የሚገኘው ገንዘብ ልክ በመሆኑ ልመናዬን ስጨርስ በህጋዊ መንገድ የመውጫ ፍቃድ እንዲሠጠኝ።

፫ኛ) በምወጣበት ጊዜ ያሉኝን የኢትዮጵያ ታሪክ መፅሃፎቼንና አንዳንድ ጥርቅምቅም ማስረጃዎቼን ይዤ እንድወጣ እንዲፈቀድልኝ በማክበር እለምናለሁ።

ይህን ደብዳቤ ሥጽፍ፤ “ይበላሃል” የሚባለው የማላውቀው የበላይ አካል እንደሚበላኝ እጠረጥራለሁ። አንዳንድ ወዳጆቼም ነገሩን በሚስጥር እንዳደርገው መክረውኝ ነበር። እኔ ግን በአገሬ ላይ የማውቀው ወንጀል ያልሰራሁ ሰው በመሆኔ እንደሌባ ከኢትዮጵያ ወጥቼ ያልበደለኝም ያገሬን መንግስት ስም ለማሳማት አልፈለግም። በዚህ ምክንያት፤ ያ በይ የተባለው ህቡዕ አካል ቢበላኝም ካለሁበት የብስጭት ኑሮ የማይቀረውን ሞት ብሞት ይሻላል በማለት በግል ውሳኔዬ ይህን ደብዳቤ ፅፌሎታለሁና በሚያደርጉልኝ ከፍተኛ እርዳታ ደስ እንደሚያሰኙኝ ተስፋ አለኝ።

ይህን ደብዳቤዬን ለጏድ ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማሪያም ዓልጻፍኩም። ነገሩን አስቤው ስራ ስለሚበዛባቸው በአንድ ፣መልኩም የግል ጉዳይ አላደክማቸውም በማለት ነው። ግን ለሁለት ሰዎች ያህል እንዲረዱኝ በማለት ግልባጩን መስጠቴን ይወቁልኝ።

ጨርሰው ስላነበቡልኝ እግዚአብሄር ይሥጥልኝ። በቅርብ ጊዜ ተስፋ ያለው ደስ የሚያሰኝ መልስዎን እንደማገኝም ተስፋ አለኝ።

=====

ምንጭ:

አጤ ምኒሊክ በአገር ውስጥ የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች – በጳውሎስ ኞኞ
እንዲህ አይነት ሃገር ወዳድ አባቶቻችንን ሳይ የሰጠናቸው ክብርና ቦታ አንሶ ይታየኛልና እጅጉን አዝናለሁ
ነብሶትን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን አሜን🙏🙏🙏
"እጅህ የሚያገኘውን ስራ ሁሉ በሙሉ ሀይልህ ስራው ፣ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መስራትም ሆነ ማቀድም የለምና"።

⚜️ ጠቢቡ ሰለሞን⚜️
😱አስገራሚ ክስተት!
🔺🔺🔺🔺🔺

✍🏼በአንድ ወቅት በምናኮ ውስጥ charles chapelne አስመስሎ የመቅረብ ወይም
የኢሚቴሽን ውድድር ተካሂዶ ነበር።

አስገራሚው ነገር Charles Chaplene ማንም ባላወቀበት ሁኔታ ውድድሩ ውስጥ በመግባት 3 ወጥቶ ሽልማቱን ተቀብሏል።

ሽልማቱን በእጁ አስጊያስገባ ድረስ ማንም አላወቀውም።🤔
🙈አስገራሚ እውነታዎች!


🚺አንዲት ዘመናዊት ሴት 💃

በህይወት ዘመኗ 6 ፓውንድ ሊፒ

ስቲክ ትጠቀማለች!!!!!

😜😜😜😜

,
ጥንታዊ ፍልስፍና
🔻🔻 🔺🔺🔺


🔭የሶቅራጥስ 3ቱ 📚📚የጥያቄዎች መርሆች⁉️

አንድ ሠው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው...🗣

👉‹‹ሶቅራጥስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጥስ ግን ዝም አለ፡፡

ሰውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡

👉ሶቅራጥስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ ሀሳብ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡

የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ 👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡

ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡
👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል ማለት ነው፡፡

ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡
👉ሶቅራጥስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡

👉ሶቅራጥስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡

©ከዕውቀት_አድማስ

https://t.me/write_event
'ቀለም ና ቃል'
.
.
.
ገላዬ ለቀለም
ቀለም እኮ ነበረ
ከደም የተቀዳ
በቅብ የሰፈረ
ቃልዬ ቃልማ እኮ
በቃል ቃል ነበረ
እውነትን ሰባኪው
በቅኔው የኖረ
* * *
መች አጣነው ቃልን -- ከቃላቶች ጉያ
መቼ ጠፋ ቀለም -- ከሰው አምሳያ
'ቃል ና ቀለም' አሉ -- ከስሜቶች ቋያ
ውሃ ብንከልሰውም -- የንዳዱን መዋያ
* * *
ያሻው --- ቀለሙን
ያሻው --- ቃሉን

ብቻ ምን አለፋን --- ከፋፍለው ይመርጣሉ
ያሻቸውን ነቅለው --- ነጣጥለው ይወስዳሉ

ነው እንጂ ቃልዬ --- ቃልማ እኮ አለ
ገላ ታውቅያለሽ --- ቀለምም እንዳለ
* * *
አካል እንዳልሆነ
ብቻውን ሰውነት
ቃል እንደሆነ
ለሰው ዘውድነት
እኛ ካላወቅን
የቃልን ክቡድነት
ቃል ቀለም ምንም ነው
ያለ ህልውና ውህደት
* * *
ቀለምማ ደም ነው --- ቃል ደሞ መንፈስ
አሀዱ የነበር --- ህልውናን የምያድስ
* * *

ቃልኪዳን የአዮ ልጅ
01/03/2013 ዓ.ም
አርባምንጭ, ኢትዮጵያ
ከተባሉት ነገር --- አንድት ፍሬ ሳይረዱ
በልቤ ሙሉነት --- በደፈና ስፈርዱ
ለሰምው ተረት ነው --- የተረት ተረት
የማይሉት ቀርበው --- እቴ የመሰረት
2/3/13
IHMIS CLASS
◎ ኢትዮጵያዊነት 💚💛❤️!

ኢትዮጵያዊ...
የልቡ ባለሟል ህብረ ሰሚያዊ
ኢትዮጵያዊ....
ባመነው የሚያድር ክሱተ ህላዊ
ኢትዮጵያዊ....
እንደ ኩል የጠራ ፍፁም ሰላማዊ
ኢትዮጵያዊነት 💚!
አዛኝ እንደናቷ... ቆራጥ እንደ ዳዊት
ኢትዮጵያዊነት 💚!
ያገር አሳላፊ ... እንደንብ ሰራዊት
ኢትዮጵያዊነት 💚!
የመስኖ ዳር ፍሬ ጥዕሙ እንደ ሸዊት

ኢትዮጵያ.... 💛!
የአዳም ሞሰበ ወርቅ የግብር ማቅረቢያ
ኢትዮጵያ...💛!
የስብዕና ክብር ድርሳን መዘገቢያ
ኢትዮጵያ... 💛!
የተስፍ ጎህ ፀዳል የምስራቅ በር አጥቢያ
አንኪያስ.... !
ምንድነው ኢትዮጵያዊነት!

ኢትዮጵያዊነት💚💛❤️

ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
እልህ አለበት ሴራ ባያስቋጥር ለበቀል
በውህደት በህብረት እስከሚንቀለቀል
ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ደራ አለበት የጋለ ማረሻ የማያስውጥ
እንኳን እምነት ማተብ ቃል የማያስለውጥ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ተስፍ አለበት የሩቁን አቅርቦ እሚያሳይ
ያንጀት የማጀቱን የሗላውን መሳይ
ኢትዮጵያዊነት....💚💛
◎ አንድም - በዕምነት 💚!
◎ አንድም - በዕውነት 💛!
◎ አንድም - በሰውነት !
◎ ኢትዮጵያዊነት ለኔ.......
አይኔ.. ብይኔ.. ሰባስቶፖል!

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ዕዳ አለበት ያስራት መክሊቱ እየጎደለ
እንደ ቸርነቱ እሱ ያውቃል እሱ እየታደለ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ይሉኝታ አለበት ከሰው አፍ ላለመግባት
ለርኩስ ከሳሽ መንፈስ ቢያጣለት እልባት
◎ ኢትዮጵያዊነት... !
ፈውስ አለበት የስም ስብራት የሚጠግን
ምን ምላሽ ባይኖረው ምን ባያስመሰግን

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
አርምሞ አለበት ግብ ግብ ከራስ ጋር ፋልሚያ
አደብ በከንፈሬ እድሜ ማራዘሚያ
ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ውል አለበት ለልቡ የገባው ቃል
ስፍርና ሚዛኑን ያስታጠቀው ያውቃል
ኢትዮጵያዊነት.... !
ብሂል አለበት የእልፍ ዘመናት ትውፊት
ምንግዜም ንቅደሚት ምንግዜም ወደ ፊት

ኢትዮጵያዊነት 💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ፀፀት አለበት እንደግር እሳት የሚያቃጥል
ትላንትን በነገ በዛሬ ሊቀጥል
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
እድር አለበት እንደ ሸረሪት ድር የሚስተሳስር
መርዶ የሚለፍፍ ንጋት የሚያበስር
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ዘብ አለበት ለዛው ቀጥ እንደ ሰንደቅ
ግዳጁን ተወጥቶ መብቱን ሊያጠድቅ

ኢትዮጵያዊነት💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ጉዞ አለበት ቢሄዱት የማይዘለቅ
መልኩ የማይለወጥ ቀለሙ የማያልቅ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ጌጥ አለበት እንደ ቶጳዝዬን ፈርጥ
በጥበብ ይደምቃል ክፉ ደጉን ሳይመርጥ
ኢትዮጵያዊነት....!
ፀጋ አለበት ከፈጠረው የሚገናኝ ዘለበት
በናቱ ፈገግታ እሶን ባዘለበት
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ሞገስ አለበ በሰማዕት ገድል የደመቀ
እንዳአምባ ገሞራ የታመቀ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ፍቅር አለበት መቸም መቸ ነዶ የማያልቅ
በትህትና አጅቦ በሰላም የሚያዘልቅ
◎ ኢትዮጵያዊነት....!
ትንሳዔ አለበት የብሄረ ህያዋን ናፍቆት
ከእውነተኛው አገር ተገልጦ አሳውቆት

ኢትዮጵያዊነት💚💛

◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ጫጉላ አለበት ከሰርግ ከምላሽ ጠብቆ
ወዶ ለፈወደው ሊያስተናግድ ታጥቆ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💛!
ጽናት አለበት በቀኝ በግራ የተፈተነ
እንኳንስ የቀልብ የእጅ ያልሰባተነ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... !
ዝማሬ አለበት ከፀጥታ ዜማ ቅኝት ጠልፎ
አሻግሮ እሚያሰግር ከቀዳበት አለሰፎ
◎ ኢትዮጵያዊነት.... 💚!
ገና ብዙ አለበት. ብዙ ገና ብዙ አለበት
እንደአስተዳደሩ. ቀን እንደዋለበት

ሙሉጌታ ተስፍየ (አያ ሙሌ) የልቤ ሰው

t.me/Write_Event
በአረንጓዴ ቢጫ ~ በቀይ
የተዋበች
እምዬ ኢትዮጵያ ~ ጥበብ
ትመስላለች

ከሰሜን ተወልዳ ~ ጥጥ ፈታይ
እናቴ፣
ከደቡብ ጫፍ መጥቶ ~ ሸማኔው
አባቴ፣
ከምስራቅ ሲያስውበው ~
ስፌቱን አጎቴ፣
ከምዕራብ ተገኝቶ ~ ጥለት ሰሪ
አያቴ፣
መሃል አገር ሆና ~ ቋጨችው
አክስቴ፤
.
እንዲህ በአንድ አብረው ~
የሰሩትን ጥበብ
ቀላል ይሆናል ወይ?
እህት ወንድሞቼ ልነጥልህ ቢሉት
~ በሰበባ ሰበብ።
.
አይገርማችሁም ወይ?
ላጨልምህ ሲሉት
የአገራችን አርማ~ በሰማይ
ደመቀ
በአራቱም ማዕዘን
በሦስቱ ቀለማት ~ ምድር
ተጨነቀ ።

©ሜሮን ጌትነት

የተመቻችሁ 👍
ያልtመቻችሁ comment

ከ ሁለት አንዱን ተጠቀሙ ዝም ብሎ ማለፍ ያስቀጣል 😂
Join
•═════•••🍃🌺🍃•••═════•
🙏🙏 #Please_share 🙏🙏
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
""""ፍቅር ና በቀል""



ክፍል 1

ሁለት ልጆች ላስተዋውቃቹ ...ሀና እና ኪሩቤል በሰፈር ስሙ (ሳንቾ )

ሀና ለቤተሰቦቿ ሶስተኛ ልጅ ናት የመጀመሪያ ውንድሞ አግብቶ አንድ ልጅ የውለድ ነው። ሁለተናው ብዙ አይበላለጡም አንድ እድሜ ክልል ውስጥ ነው ያሉት እድሜዋ 22 ውስጥ ነው። ቤተሰቦቿ ሀብታም ከሚባሉት ውስጥ ይመደባሉ ። እቤት ውስጥ ሀናን እንደቁላል ነው የሚመለከቶት ምን ነገር ብትል ይደረግላታል ።

በትምህርቶ አሉ ከሚባሉት ትመደብ ነበር ነገር ግን የዩኒቨርሲቲ ውጤት መቶላት እቢ አልማርም በግል የነርሲንግ ድፓርትመንት መማር ጀምራለች ።
በረፍት ጊዜዋ የሙዚቃ እና ዳንስ ታዘውትራለች ቤተሰቦቿም ፍላጎታን ላለመጋፋት በዛ ላይ እንድትከፋ ስለማይፈልጉ ያለችውን ሁላ በእሽታ ነው የሚመሱሰላት ። ከታላቅ ውንድሞ ጋር በጣም ሚስጥረኞች ናቸው። በጣም ነው የሚዋደድት ።ምን የሚደባበኩት ነገር የለም እሱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንጂነሪንግ ተማሪ ነው። በቀጣይ ይመረቃል ።.

ትግስት ፣ ሜሮን ና ኮከቤ ጎደኞቾ ናቸው። ከአንድኛ እስከ 12 ክፍል አንድ ላይ ነው የተማሩት አንድም ቀን ሳይጣሉ በመካከላቸው የሚደባበቁት ነገር የለም። እና እናሱ እንደድል ሆኖ ውጤት አልመጣላቸውም ከዛ ነርሲግ በግላቸው እንማራለን ስላሉ ሀናም አልለያቸውም ብላ ነው የግቢው ውጤት እቢ ብላ እኩል የሆነችው ለእነሱ የተለየ ፍቅር እና ልዬ ቦታ አላት። በርግጥ በጣም ከጓደኞቿየሚያስቀኑ አንዳንቸው ላንዳቸው የሚተሳሰብ እና የሚያስቀኑ ናቸው ።
ትግስት ቀይ ብዙም ማውራት የማትውድ እረጋ ያለች ቆንጆ የምትባል ነው ። ሜሮን ከሁሉም ተስማሚ ናት ካበደው ጋር የምታብድ ከዝምተኛው እንደዛው። ኮከቤ ቀልቃላ እና ችኩል ግን በአፎ ብትናገርም ሆዶውስጥ ምን የሌለ የዋህ ፀይም ናት። በርግጥ ሀናም ትንሽ የመንቀልቀል እና የመቅበጥ ባህሪ አለባት ።

ከትምህርት እንደውጡ ውደ ሙዚቃ ዳንስ....የሚለማመድበት ያመራሉ እንደጨረሱ። ውደ ቤት ለመሄድ ሰዓቱ ስለመሸ ይርበተበታሉ። ድንገት የሀና ስልክ ጠራ "እየተነጫነጨች ስልኳን ስታየው የማታቀው ስል ነው። ላንሳው አላንሳው እያለች ማመንታት
"ሀኒ ስልኩን አንሺው ምነው?የማታቂው ነው? ትግስት ነበረች።
"አዎ ቁጥር ነው ግን ላንሳው ውድሜ ይሆናል ስላመሸው ብላ ስልኩን አንስታ
""ሄሎ ሄሎ ...ማን ልበል .....እይልለች ድምፆን ቀዝቀዝ አደረገችው:"
""ሀኒዬ እንዴት ነሽልኝ ?
ሀና ግራ በመጋባይ ...
"ይመስገነው ማን ልበል ይቅርታ አላውኩህም .....
""እንዴ አንቺ ቢጠፋ ቢጠፋ የኔ ድምፅ ይጠፋሻል ትገርሚያለሽ ..ሀና ግርማ አይደለሽ ?
ስልኩን ላውድ ላይ አድርጋውም ይቅርታ እኔ ሀና ጌታሁን እባላለው ተሳስተካል ""
""ኦ sorry...ብሎ ስልኩን ዘጋው ...
የሀና ጓደኞቾ ይሄ የዞረበት እያሉ መሳሳቅ ጀመሩ። ሀና በሀሳብ ተውጣለች ....

ስልክ የደውለው ኪሩቤል ነበር።
ኪሩቤል (ሳንቾ)ለቤተሰቦቹ አረተኛ ልጅ ነው የመጨረሻ አንድ ሴት እህትና ሁለት ውንድሞች አሉት። ከካናዳ የመጣው በሶስት ቀን በፊት ነው። ሁለቱ ውንድሞቹ እዛ ነበሩ። ውደዛ የሄደው እህቱና እናቱ ከሞቱ በኃላ አባቱና እሱ ውደ ካናዳ ሄድ። የመጣው የልጅነት ጓደኛው ጋር ነው ያረፈው። በርግጥ እሱ ተሳስቶ አልደውለም ለማውናበድ እንጂ ስልኩን ከዘጋው በኃላ ጎደኛው አማን ማን ጋር እንደደውለ ሲጠይቀው አይ ዝብዬ ቁጥር ስሞክር ነው አላቃትም ብሎ መለሰለት ።

"ሀና እቤት ስገባ ሁሉም እራት እየበሉ ነበር sorስላመሸው ማም ዳድ ብላ ግንባራቸውን ስማ እጆን ልትታጠብ ገባች። ውስጦ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶታል ፉቶ ላይ ደስታ ይነበብ ነበር። ቤተሰቦቿ ግራ ቢጋብም ደስታዋን ውደውላታል ።
""ሀኒዬ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲ መፍለቅለቅ" እናቷ ነበሩ።.
"ምን እንዲሁ ነው መደሰት አይቻልም ....
"አረ ከፈለግሽ ጨፍሪ ማን ከለከለሽ
ብሎ መለሳላት ያቤት ምግብ ሰዓት ባጠቃላይ አንድ ላይ ሲሆኑ ጨዋታቸው አይጠገብም ።..ልክ እንደጨረሱ ...ሀና ክፍሎ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍታ አሻንጉሊት አቅፋ ተመስጣ ታደምጥ ጀመር። ድንገት የሙዚቃው መቆም እያበሳጫት የጨፈነችውን አይን ገለጥ ስታደርግ .....

ይቀጥላል!!

እንዲቀጥል ለወዳጆች Share ያድርጉ

share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
@kaliye06
''ፍቅር እና በቀል '' የተሰኘ ተከታታይ ታርክ መጀመራችን ይታወሳል ይሁን እንጅ ተቆርጦ ነበር ።
አሁን መጀመራችንን በይፋ እንገልፃለን ።
ታድያስ አንድ ሰው 3ሰውን በመጋበዝ እየሰፈን ታርኩን ከዛሬ ጀምሮ እንቀጥላለን ።
share and join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
""""ፍቅር ና በቀል""""
ሀዊ ጌታቸው (ሂዊ የጌቾ)
ክፍል 2
.
.
የጨፈነችውን አይኖን ገለጥ ስታደርግ እስራዬል ውንድሞ ነው ። ኡፍፍፍፍ ኢሱ ለም ዘጋከው ብላ እዛው ውደተኛችበት ተመለሰች..
"ወደ አልጋዋ እየተጠጋ ዛሬማ የሆነ ነገር ሆነሻል እእእ ምን ተገኘ እያላት ያቀፈችውን አሻንጉሊት ተቀበላት"። ።.".እንደመሳቅ እያለች ኢሱ ታውቃለክ omg ብላ ትራሱን አንስታ ፊቶ ላይ ሸፈነችው""
"እንዴ ምን ተናገሪ ከኔ የሚደበቅ የለም ፍቅር ነው አይደል እያለ ውደ እሱ አስጠግቶ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ እግሮቹ ላይ አስተኝቶት በይ እንዲ እያየሽ አዋሪኝ ።..ከሀ እስከ ፐ ...

"ወይ ከሀ እስከ ፐ ውዶ አይስኩ አሉ ጎረቤታችን ....ምን መሰለክ የሆነ ልጅ ተሳስቶ ደውለ ስልኬ ላይ ግን ኢሲዬ ያቺ ቅፅፈት ለምን የተለየ ስሜት እንደተሳማኝ ስልኩ ከተዘጋ በኃላ "ሀኒዬ እንዴት ነሽልኝ""ያላት ቃላት ውስጤ ውስጥ ይመላለስብኛል።
""እና መጨረሻው ምን ሆነ ?እንዴት ሀኒዬ አለሽ?
"ሀና ግርማ አይደለሽ ሲለኝ አይደለሁም ....ኦ sorry ብሎ ስልኩን ጥርቅም ..ይሄን ቃላት ስትናግረው በመናደድ ስሜት ነበር ።.
እስራዬል በሁኔታዋ መሳቅ ጀመረ። አያስቅም በትራስ እንደመምታት እያለች
እረ በደንብ ነው የሚያስቀው። እኔምልሽ
ቲጂ ጓደኛሽ ሰላም ናት?
"ከተኛችበት ተነስታ ምን ቲጂ ነው ያልከቅ አንተ ምነው እሷን ብቻ ጠየከኝ ለዛም አቆላምጠክ ...
"ከናንተ ውስጥ እሷ ናት ደና ሰው ብዬ ነዋ እንዳለ ወፈፌ ብቻ ነው።.. በዛ ላይ...
"ከት ብላ ስቃ በዛ ላይ ፍቅር ይዞኛል ልትል ባልሆነ !
""እንደመኮሳተር ብሎ ብልስ እኔ ውንድምሽ ለሷ አንሳለው ,?
" ከምርክ ከሆነ ደስ ይላል ቲጂዬ ምርጥ ናት ትበዛብሀለች እየሳቀች ።..
"ስልክ ተደውሎለት በይ ደና ደሪ ብሎ ከክፍሉ እንደውጣ ሀና በጀርባዋ ተኝታ በሀሳብ ባህር ትዋኛለች ድንገት የሞባይሎ ስልክ ካለችበት የሀሳብ ባህር አስበርግጎ አስወጣት ።

በንዴት ስልኩን ስታየው የቅድሙ ቁጥር ነው ።.ከእጆ ላይ ስልኩን አልጋው ላይ ውረውረችው ተነስታ በፍጥነት የመኝታ ቤቶን በር ቆለፈችው ማመን አቅቶት አንስታ ስታየው እራሱ ነው ተርበተበተች ቀልቃላዋ ቀበጦ ሀና ውድያው ፈሪ እና ዝምተኛ አደረጋት የልብስ ቁም ሳጥን ላይ ያለውን መስታውት እያየች ለምን ደውለ? ያውቀኛል?ወይስ ....ምን ፈልጎ ነው ?ለብቻዋ መለፍለፍ ስልኩ ጥሪውን አብቅቶ ከ አምስት ደቂቃውች በኃላ ድጋሚ ጠራ እየፈራች አንስታው ።..
ለስለስ ባለ ድምፅ "" ሄሎ ምነው አሁንም ተመሳሰልኩብክ እንዴ"
"እየሳቀ no ይቅርታ ልጠይቅሽ እና ከተፈቀደልኝ አንድ ነገር ልልሽ ነበር!?

""ትንፋሾን አዘግይታ ... ይቅርታ አያስፈልገውም ደሞ አንዳንዴ ያጋጥማል አታስብ ስላከበርከኝ thanks.አንድ ነገር ያልከው ምንድነው?.
. ብላ አጠገባ ያለውን አሻንጉሊት እንደመንከስ እያለች ...
"ድምፅሽ ያምራል በዛ ላይ እርጋታሽ ድምፅሽ ሙዚቃ ትሞኪራለሽ እንዴ ?
"" ከት ብላ ስቃ ቀልደኛ ነክ ..በደረቶ ተኝታ እግሮቾን እያፈራረቀች አልጋው ላይ ታሳርፈዋለች ውስጦ ደስ ብሎታን ግን ለምን እንደሆነ እንዲ ልታናግረው እንደቻለች ለሯሷ ግርም ይላታል ...
ጫውታቸው ደራ በመሀል
" እንተዋውቅ አለማየው (አሌክስ)ብትይኝ አልጠላም ።.
ይህኔ የኪሩቤል ጓደኛ አማን አፈጠጠበት ..።ግን የአማን መቆጣት ማፍጠት ምን ሳይመስለው ...ውሬውን" ቀጠለ ..
""ሀና (ሀኒ ) ብትለኝ እጠላለው ስትለው
"እየሳቀ ተጫዋች ነሽ ሀኒዬ ...እንደዋውላለን ...ተባብለው ስልኩን እንደዘጉት
እሷ አልጋው ላይ መዝለል ጀመረች ከደቂቃዎች በኃላ እንዴ ምንድን ነው እንዲ የሚያረገኝ ....ለጓደኞቾ የዋትሳፕ ግሩፕ ላይ የተባባለችውን ሁላ voice አድርጋላቸው መብራቷን አትፍታ ተኛች

""ግን ያምሀል ስምህን ቀይረክ የምትተዋውቀው ቆይ ቆይ ልጅቶ ማናት?
"ኪሩ ይሄ ነገር አላማረኝም ..በጥርጣሬ አስተያየት እያየው .አማን ነበር
.
"አማንዬ ምን አታስብ ሰሞኑን አስተዋውቅሀለው ከንፈሮቹን እየነከሰ ሀኒ ማለት ጀመረ...

ይቀጥላል


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

ለማንኛውም አስተያየት
@kaliye06
Sand and Foam
©Kahlil Gibran
≡≡≡≡≡≡≡
አንድ ፈላስፋ ለአንድ መንገድ ጠራጊ "የአንተ ስራ ከባድና ቆሻሻ ስለሆነ አዝንልሃለሁ" አለው።
መንገድ ጠራጊውም አመሰግናለሁ ጌታዬ። እስቲ ያንተን ስራ ንገረኝ " በሚል ይጠይቀዋል።
ፈላስፋውም መለሰ " እኔ የሰው ልጆችን አዕምሮ ግብሩንና ፍላጎቱን አጠናለሁ።"
መንገድ ጠራጊውም መጥረጉን በመቀጠል በፈገግታ "እኔም አዝንልሀለሁ " አለው።
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 3
.
.
"" አማንዬ አታስብ ሰሞኑን አስተውምውቅሀለው ከንፈሮቹን እየነከሰ ቲጂ ማለት ድምፆ የሚያምር .....
ለማንኛውም አሁን እንተኛ ..

"በተደጋጋሚ መደዋውል ጀምሩ። በእሷ በኩል ሳይደውል የዋለ ቁጥር እቤት ውስጥ መነጫነጭ እና በትንሽ ነገር የመበሳጨት ነገር ...ይህን ጉዳን ለጓደኞቾ ስነግራቸው ስቀው ግን ለምን አንድ ነገር አናደርግም አሉ።
"ማክዳ ሰው እንዴት ስልክ ተሳስቶ ደውሎ ከዛ ፍቅር ምነ ምን ያዘኝ ይላይ የንቀጥ እና የጥላቻ አክት እያሳየች አብሶ የዘንድሮ ውንዶች ጋር እውነት ፍቅር አለ"

""እንደዛ አታስቢ ደሞ ሁሉም አንድ አይደሉም በዛ ላይ ከሴትም አለ። ለገንዘብ ለውለታው...ብቻ ብዙ ፍቅሮች አሉ። አንቺ ዛሬአንድ ሰው ስለጎዳሽ ያው ናቸው አትበይ ...ቲጂ ማክዳን እያየች

""በይ እሱ ድሮ ቀረ እኔ ግን fb ...በስልክ ባጋጣሚ ምነምን አይመቸኝም አብሶ ኢንተርኔት ነክ። ፍቅር ማስጀመር እንጂ ማስጨረስ....


""ሀና የነሱክ ጭቅጭቅ እና ሙግታቸውን አንድም አልሰማችም በመሀል የስልኳ ጥሪ አባነናት ስታየው እሱ ነው። እሱ ነው ስትላቸው አንሺው ለምን አንገናኝም አትይውም አሏት

"No እሱ እስኪላት ትጠብቅ ...
""ፈገግታ በተሜው ድምፅ ሀይ አሌክስ እንዴት ነክ ...ጓደኞቾ ላውድ እንዳታደርገው በመልክት ነግራዋት አድርጋ ውሬአቸውን ቀጠሉ...

""በመሀል ሀኒ የት ነሽ?ለምን አንገናኝም?

" ደንግጣ መቼ ዛሬ አሁን በመደናነር ስሜት ውስጥ ሆና ...
""ምነው አይመችሽም ጓደኞችሽ አሉ እንዴ ..
"" አዎ ሌላ ቀን እንገናኛለን
ጓደኞቾ አፋቸው ላይ የመጣውን ሳቅ በእጃቸው ይዘው .
" እሺ ነገ ምሳ ልጋብዝሽ አስቢበት እቢ ማለት አይቻልም ....
"ካመነታች በኃላ የጓደኞቾን አይኖች አይታ እሺ እንደትለው ምልክት አሳዩያት
"እሺ...
"በቃ እንደዋውላለን ብሎ ስልኩን እንደዘጋው
"ለደቂቃ የያዙትን ሳቅ ሁሉም በነፃነት መሳቅ ጀመሩ ..
"እንደዘጋችው ኡፍፍፍ ብላ ተነፈሰች
"ነገ እንዴት ሆና መሄድ እንዳለባት መነጋገር ጀመሩ።..
ለምን እቤት አንሄድም ስትላቸው እኔ ና ማክዳ የምንሄድበት ቦታ አለ። እያውቃችሁት ባይሆን ቲጂ ጋር ሂድ ..ሜሮን ነበረች።

ትግስትና ሀና ወደ ሀና ቤት አመሩ ልክ ሲደርሱ የውጪውን በር ሲያንኳኩ እንደ ድንገት ውንድሞ ሲከፍት "እንዴ ዘበኛ ሆነክ ቀረክ" ስትለው ክው ብሎ ቀረ በርግጥ የደነገጠው በአለችው ነገር ሳይሆን ቲጂን ስላያት ነው።

""እብድ ከመምጣትሽ አትልከፊኝ ሰላም ነሽ ትግስት"
ሲል እየገባች ያለችው ልጅ ዞር ብላ ምን አልክ ትግስት ነው ያልከው። ይሄውልሽ ቲጂዬ ትላንት ቲጂ እያለ እያቄመጠ ስጠራሽ አምሽቶ አንቺን ሲያይ ....የመታውቂያ ስምሽን ይጠራል ።
በሁኔታዋ ፈንጠር ብለው የቆሙት አባቷ መሳቅ ጀመሩ። ቲጂ ያለችበትን እስከምትረሳ ትስቃለች ምን ውስጡ ቢናደድም ግን ደስ ብሎታል ።..
እየተሳሳቁ ውደ ውስጥ ገብ .።

""ሀኒ ክፍል ሆነው የልብስ ቁምሳጥኑን ከፍተው ልብስ እየሞከረች ቲጂ አልጋው ላይ እግሮን አውጥታ አስተያየት እየሰጠች ለክታ የጣለችውን ልብስ እያጣጠፈች ታስቀምጠለች ።..

""ቀይ አጠር ያለች ከጀርባው ክፍት የሆነ ልብስ ስታየው wowww ምርጥ ነው ፀጉርሽን ተሰርተሽ ስለቂው ይሸፈናል ይሄ ክፍተቱ ብላ በምርጫዋ ተስማምተው ሳሎን ሄደው ፊልም ማየት ጀመሩ። ድንገት ሀኒን አባቷ ጠርተዋት ሄደች። እስራዬል ና ቲጂ ቀሩ...ሰረቅ እያለ እያያት ተጫውቺ ...እንጂ..
"በእሽታ እራሶን እየነቀነቀች ....

አንድ ሁለት እያሉ ጫውታቸውን ደራ እየፈራም ቢሆን ነገ ለምን ሻይ ብና አንልም አላት።
እንደማሰብ ብላ እሺ ብላው ስልኮን ሰጠችው ።።...

ሀና እየለፈለፈች መጣች ...

ምሽት ላይ ሀና ስልክ ሲደወልላት ወደ ክፍሏ ገብታ ማናገር ጀመረች። ኪሩቤል (አሌክስ) አናግራ እንደጨረሰች አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ተዘርግታ ታስብ ጀመር። የመኝታ ቤቶ በር ተንኳኳ....ይግብ ወንድሞ ነበር

"ዛሬ እንግዴ ስፈነጥዝ እደር ..እንደመሳቅ ብላ ...
""ማለት እንደመኮሳተር እያለ ውደ አልጋው እየተቀመጠ
"ልትዋሸኝ ባልሆነ ሁሉንም ሳዳምጥ ነበር እንድታውሩ ነው አውቄ እንዲያስጠራኝ ያረኩት..ስትለው

አንቺ ተንከሲስ ብሎ በትራስ እየመታት አቅፎ ሀኒዬ በጣም ነው የምውዳት ከምሬ ነው። የዛሬ እንዳይመስልሽ ከአመት በፊት ነው ፍቅር የያዘኝ....

""የምትፈልግክ ከሆነ ጥሩ ልጅ ናት ።ፍቅረኛ የላትም ....

መድረስ አይቀር የተቀጠረችበት ሰአት ደረሰ ...የለበሰቸውን ከለር ነገረችው ልትውጣ ስትል
ውንድሞ" ውዴት ነው"
"ኢሲዬ ስመጣ እነግርሀለው ....
""እሺ ግን እንዲ ሆነሽ....እራስሽን ጠብቂ ....
እሱም ቲጂን ስለቀጠረ ለምን አልሸኝሽም መኪና ይዛለው በሀሳብ ተስማምታ ከተቀጠረሽበት ሆቴን አድርሶት ሰዓት ስለረፈደበት በፍጥነት እየነዳ ሄደ ።.

""ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎጠራት ልክ ስታየው...

ይቀጥላል...



share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
"""ፍቅር ና በቀል"""
ሀዊ ጌታቸው
ክፍል 4
.
. "ልክ እንዳያት ሀኒ ብሎ ጠራት
የተበተነውን ፀጉራን ገለጥ አድርጋ ቀና ስትል ደነገጠች ."
"ከመቀመጫው ተነስቶ ልክ በፊት በአካል እንደሚተዋውቁ አቅፎ ሰላም አላት ግን እሷ ደንግጣ ብዙም ሰላም አላለችውም ከትንሽ ደቂቃ በኃላ
""ምን ሆነሻል እንደዚ አልጠበቅሽኝም ወይስ ....
""በመንተባተብ አይ ለዛ አይደለም ከሰው ጋር ተመሳስለክብኝ ነው"
Sorry ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ ሶፍት አውጥታ ግንባሯን እንደመጠራረግ አለች።
"ዝምታውን ለማፍረስ ብሎ "ከጠበኩሽ በላይ ቆንጆ። ነሽ ..
"አመሰግናለሁ አንተም ብላ እንደማቀርቀር አለች
"ምሳ አዘው እየበሉ ግን እሷ ውስጦ ብዙ ጥያቄዎች አደረባት ።.
"በልተው እንደጨረሱ እሱ
""በብርጭቆ ውስጥ ያለውን ውይን እየተጎነጨ ሀኒ ድፍረት አይሁንብኝ እና ቅድም ከማን ጋር ነው የተመሳሰልኩብሽ
""አይ የቆየ ታሪክ ነው እርሳው ...

"እንዴ ለምን ንገሪኝ ታሪክ መስማስ እወዳለው ...ስሙን ንገሪኝ ፍቅረኛሽ ነበር።

"አይ አይደለም የሰፈሬ ልጅ ነው በጣም ነበር የምንዋደደው ልጆች ነበርን ኪሩቤል ይባላል የሚገርምክ የቤት ስሙን በጣም ነው የምውድለት ((ሳንቾ))

"እሱ ክው ብሎ ቀረ እንዳይታውቅበት እና የት ሄደ sorry ግን ስሜትሽን እረበሽኩሽ ...
"በረጅሙ እንደመተንፈስ ብላ ካናዳ ሄዶል ይብቃን አናውራው አለችው ..

"ያኔ እሱ እንባው እንደመምጣት አለ ግን ሽንትቤት ብሎ ሄደ እራሱን በመስታውት እያየ ሀኒ በጥሩነትሽ እንዳትመጭብኝ
እያለ ውሀ እንደመርጨት ብሎ አደራርቆ። ወደ ቦታው ተመለሰ
እሺ ሀኒ ተጫውቺ ብሎ ግን ዳንስ አታለማምጅኝም?
" ችግር የለም ለምን ከኛጋር አትቀላቀልም...እንደመሳቅ እያለች .

ማታ ከተለያዬ በኃላ
ሀኒ ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ይሰማት ነበር ።በርግጥ ገና በስልክ እንዳናገራት ነበር ስለሱ ማሰብ የጀመረችው ዛሬ በአካል ስታገኛው ደሞ የበለጠ
እቤት ገብታ ሰላም ብላቸው በሆነው ባልሆነው ትስቅ ጀመር። እናቶ ሀኒዬ ምን ተገኝቶ እንዲ ፈንድሻ ያደረገሽ ዛሬ ..ምን ያው ደስታ ይከለከላይ እንዴ ብላ ውደ ሞባይሎ አቀረቀርች ..

""አይከለከልም ግን ያው አለ አይደል ...የደስታ አይነት አለው ብለን ነው አባቷ ከኮምፒውተር ላይ ገታ ብለው የሀኒን ደስታ ምክንያት ለማውቅ ።..
""እእእ ምን አልተገኛም ሰላም እደሩ ብላ ውደ ክላሷ በመግባት በደረቶ አሻንጉሊቶን አቅፋ ስሜቶን በዝምታ እንዴ በግርምት በሳቅ እያዋዛች ማዳመጥ .

"በኪሩቤል ከራሱ ጋር እንደተጣላ በሀሳብ ተውጦል ድንገት ጓደኛው ዛሬ ደሞ ብሶብካል የት እንደዋልክ ከማን ጋር እንደ ነበርክ ንገረኝ ብሎ ውጥር አድርጎታል ..

"አማን ሁሉም በጊዜው ትሰማዋለክ አሁን አትጠይቀኝ ብሎ ሌላ ውሬ ቀየረ ግን ኪሩቤል ሀናን እንዴት ውደ ፍቅር ውስጥ እንደሚከታት ነው የሚያስበው ።

"እጆቹን ወደ ስልኩ ሚሴጅ ላከ እና በረጅሙ ተንፍሶ ስልኩን ደረቱ ላይ አድርጎ ውደ ጣሪያው ተመለከት ግን ሳያስበው አይኖቹ በእንባ ተሞልተዋል

"ሀና እዛ እንቅልፍ ይዞት ስለነበር የስልኳ የቨይብሬት ጥሪ አስበረገጋት እንደማማተብ ብላ ...አይኖቾን እያሸች ስታየው የሱ ነው ያሁላ ድብርት በብርሀነ ፍጥነት ለቋት ማንበብ ጀመረች

""ሰላም ገባው አይባልም እንዴ ለማንኛውም አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ደና እደሪልኝ "" አብባ ስጨርስ መልስ ከመላክ ይልቅ ስልኩን ስማ አይኖቾን ጨፍና ስልኩን ደረቶ ላይ አድርጋ ስሜቶን ማዳመጥ ጀመረች ። ሳታውቀው በዛው እንቅልፍ ውስዶት ነበር ስትነሳ
ስልኳን ስትልየው
""good morning""""

ደነገጠች ባፀፋው መለሰችለት እና መልስ ስጠብቅ
ድንገት የመኝታ ቤቶን ሀኒ እያለ..
.

ይቀጥላል.....

|Share|Share|Share|


share and Join
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event

t.me/Write_Event