በመንገዴ
676 subscribers
1.5K photos
228 videos
8 files
139 links
My own brain is to me the most unaccountable of machinery,always buzzing,humming,soaring,roaring,diving and then buried in mud.🥀
Download Telegram
🖤🤌🏾
🖤
Forwarded from በመንገዴ (Venice)
Tell me how many goodbyes and roads travelled does it take before I make peace with the grief of leaving a place....?
Forwarded from HOME || ቤት 🏚
[ እንዳንድ ነገሮች ስለድብርት፣ ራስን ስለማጥፋት ምናምን...]

(በጣም ረዘመብኝ እና በቃ እንደ series ፊልም በኢፒሶድ ከፋፈልኩት... ካልሰነፋችሁ አንብቡት፤ ባታነቡትም I don't mind)

- 1-

ሰው ሲሞት እንደአንድ ጤነኛ ሰው አዝናለሁ። ግን ለምን እንደኹ እንጃ በተለይ ወጣት ሰው ራሱን አጥፍቶ ሲሞት ይበልጥ ያሳዝነኛል። That really bothers me! ለምን? ምን ቢያጋጥመው ነው እስከሞት ያስጨከነው? ተራ curiosity ይሁን የመርዳት ፍላጎት ለይቼ ባላውቅም!



ደግነቱ በትንሹም ቢሆን አውቀዋለሁ፤ ያው ጦርነት እያመሳት ባለች ድሃ ሀገር እንደሚኖር ፣ በግሉም ብዙ ትግሎች እንዳሉበት አንድ ወጣት እኩያዬ ምን ሊሰማው እንደሚችል በትንሹም ቢሆን አውቀዋለሁ።



የሆነ አንድ የተለመደው ዓይነት ቀን ጠዋት ወደክላስ እየሄድኩ እያለ ነው ድንገት መድከሜ የገባኝ - There was something different about me.

ማለቴ ከዚያም በፊት I've been struggling for years ምናምን እኮ...I know all those ኮንፊደንስ የማጣት፣ inferiority፣ Overthinking፣ anxiety፣ feeling down and depression ሺትስ... ግን በቃ ያ ቀን ነው የሆነ ነገሬ seriously እንደተሰበረ የገባኝ... አለ አይደል this Yonathan is totally a different one ምናምን ያልኩት።

መተንፈስ ደክሟችሁ ያውቃል? That literally happened to me... ማለት ትንፋሽ አጠረኝ ምናምን ሳይሆን literally መተንፈስ ስራ ሆነብኝ...
"እንዲያው ምን ቢያታክት ሀሞቱን ቢያፈሰው
መተንፈስ ይደክመዋል ወይ ሰው?"
... የምትል ግጥም ሁላ ፃፍኩ 😅 ማለቴ ብዙ የድካም አይነት አውቃለሁ ያኔ ይሰማኝ የነበረው ድካም ግን የተለየ ነው።

That day I realized በሕይወት ያወጣችኋት እያንዳንዷ አቅም በኋላ እንደምትቀናነስ ... አለ አይደል ቀላል ናት ብላችሁ ያሳለፋችኋት እያንዳንዷ ጠጠር የምታህል ችግር ኋላ ከቢጤዎቿ ጋር ተሰብስባ ቋጥኝ ሆና መምጣቷ አይቀርም።

ግን ከሁሉ በላይ የሚጎዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? PRETENDING!! Since I was that "perfect" kid ሰዎች ለኔ የሣሉትን አይነት ሥዕል ለመሆን መፍጨርጨር ነበረብኝ ...fake it till you make it እንዲሉ። በዛ ላይ ችግሬን ከማውራት ይልቅ ውስጤ መያዝ የምመርጥ ሰው ነኝ። እና በሳቅና ሂውመር የተሸፈኑ ብዙ ሕመሞች የሆነ ቀን ሰብሰብ ብለው ይመጡና ድጌ ቀና እንዳትል አድርገው ያደቁሀል።

I knew I can't be the old me... I felt like I lost my passions, dreams and all. Oh man! That time was though! I was literally drained off... idk if I'm explaining it well or exaggerating it. ከብዙ ነገር ሸሸሁ... Even from my fellowship! And I was a leader there... ግን በቃ ስልኬን አጥፍቼ ጠፋሁ... ክላስም ድሮም ድሮ ነኝ እንኳን እንዲህ ሆኜ 😂 እና በቃ የሚታየኝ ቤቴ ነበር...that's the only place i feel safe (still 😁) ድብብቆሽ በሉት...

በተለይ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ It was hell... ጊቢ ተጀመረ፣ GC የመሆን ጭንቀት ተጨመረበት፣ ከዚያ final project የምንሰራበት group አጣሁ፣ ያበደ ጨጓራዬ ተነሳብኝ ምናምን፣ plus some family cases...በቃ በትክክል function እያደረኩ እንዳልሆነ ገባኝ... ስልኬን ዘጋሁ። እና የሆነ ቀን በር ብቻዬን ቤት ተኝቼ እያለ በር ተንኳኳ እና ስከፍት it was my friend from ጊቢ (ከ5 ኪሎ ቃሊቲ ድረስ መጣ 😅) እና ብዙ አወራን ምናምን... ግን እውነት ከወሬው በላይ knowing that የሆነ ሰው ለኔ ተጨንቆ ቤቴ ድረስ ሊፈልገኝ እንደመጣ ማሰቡ ብቻ በጣም ብርታት ሰጠኝ! እንዲህ አይነት ሰዎች ይብዙልን!!

የሆነ ጊዜ I tried counselling ምናምን። ማለቴ ለእኔ አይነት prideful ሰው "I need help" ብሎ መሄድ ትልቅ courage ይጠይቃል... sadly በቃ አለ አይደል ከአንድ ቀን አነቃቂ ምክር የበለጠ ብዙም አላገኘሁም... What I needed was a good mentor to whom I could be accountable for ምናምን ግን ያው ነገሮች እንደፈለጋችሁት አይሄዱም አይደል?
ብቻ ምን ልላችሁ ነው - ሁላችንም በብዙ ነገር ውስጥ እናልፋለን። Painless life isn't promised! ብቻ ለመበርታት እንታገል እንጂ!



How I dealt with that time? What helped me?

ማንበብ - ያን ያህልም አንባቢ ባልሆንም ጥቂት enjoy ከማደርጋቸው ነገሮች አንዱ ማንበብ ነው። At least it helped me to escape from the pain of reality for moments.

People - oh my beloved friends! ተገናኝተን፣ roast ተደራርገን እና excessively ስቀን፣ ሲደብረን አውርተን፣ ወክ አድርገን መለያየት is therapeutic!

ሌላው ነገር perfectionist'ነቴን ከላዬ ገፍፌ ለመጣል ሞከርኩ። ማለቴ ማስመሰል የለብኝም ብዬ ወሰንኩ። የሌለ ግብዝ ነበርኩ! እና Intentionally ራሴን በጽሑፎቼ ምናምን vulnerable ማድረግ ጀመርኩ። ማለቃቀስ ጀመርኩ! ጽሑፎችን suicidal ናቸው እስክባል ድረስ ውስጤ ያለውን የቆየ ሀሳብ ማውጣት ጀመርኩ። And that really helped me. እና ግጥም መጻፍ isn't luxury for me! It's kinda a painkiller!

And ማልቀስ? You have no idea how that helps! አለ አይደል ሁዲ ለብሶ፣ በጨለማ ሙዚቃ እየሰሙ እያለቀሱ ወክ ማድረግ... ain't that dramatic? 😂😂 Yeah try it - it's beautiful!



Yet still it's freaking hard!! መኖር የሚያስጠላበት ጊዜ አለ፣ out of no where ቅልብሽ የሚልበት ጊዜ አለ፣ ማሰብ የሚያቅትበት ጊዜ አለ፣ ሰው ማየት የሚያስጠላበት ጊዜ አለ፣ ከአልጋ መውረድ የሚከብድበት ጊዜ አለ፣ እልም ያለ ገጠር ሄዶ ከሰው ርቆ መክረም የሚያሰኝበት ጊዜ አለ፣ ሞት የሚናፍቅበት ጊዜ አለ፣ ተስፋ የሚጠፋበት ጊዜ አለ

Yet all this ሺት is not above us and this shall pass too!!

እና አሁንም ቢሆን በእኔ በኩል የመሞት እቅድ የለኝም 😅 ለነገሩ የምንም ነገር እቅድ የለኝም! ምንም ባይኖር ወደፊት ስለማነባቸው መጽሐፍት፣ ስለማያቸው ቆንጆ ቲያትሮች፣ ስለማሳልፋቸው heavenly moments እና ስለማገኛቸው ፀዴ ሰዎች ስል እኖራለሁ።

እና እናንተም የመሞት እቅድ አይኑራችሁ! እየታገሉ መኖር ይሻላል አይደል? ከሞት ምንም አይገኝም አይደል?

እና ያው ኤልያስ እንዳለው ነው... "ኑር ባታምንም
ላንተ ባይመስልም
ለከንቱ አልተፈጠርክም"

Cheers for the coming years we struggle together 🍻

...
I just wanted to remind you all again that if there is anything you wanna talk about...your day...something new you wanna share or just a friend to catch up with my dms are always open. And whatever it is you have been holding onto and want to just get off your chest i am here for you. @Chezed_29
በመንገዴ pinned «I just wanted to remind you all again that if there is anything you wanna talk about...your day...something new you wanna share or just a friend to catch up with my dms are always open. And whatever it is you have been holding onto and want to just get off…»
Forwarded from Hakim
አንዳንድ ነገሮች ስለድብርት ፣ ራስን ስለማጥፋት

የሆነ ቀን ማታ ከክላስ እየተመለስኩ ሰፈር ልደርስ አካባቢ የቀለጠ ድንገተኛ ጩኸት ሰማሁ እና ጩኸቱ ወደተሰማበት ጊቢ ሮጬ ሔድኩ። አንድ በአስራዎቹ እድሜ የሚገኝ ልጅ ራሱን አጥፍቶ ተገኘ። ያሳዝናል አይደል? ከዚህ በላይ የምር ያሳዘነኝ የሰዉ response ነው!

በቤተሰቡ የድንጋጤ ጩኸት የተሰበሰቡ የመንደሩ ሰዎች አጠገቤ እንደቆሙ "ምን ሆንኩ ብሎ ነው አሁን?"፣ "የበርበሬ ወጪ የለበት የጨው፥ ቅብጠት ካልሆነ በቀር"፣ "ጨካኝ ነው ለቤተሰቦቹ እንዴት አያስብም?"... ሲሉ መስማት ይበልጥ ይሳዝናል።

አዕምሮ ነክ ችግሮች ትልቁ ጉዳታቸው እንደሌሎቹ በሽታዎች አለመሆናቸው፣ ማለቴ አካላዊ አለመሆናቸው ይመስለኛል። ብዙዎቹ ምልክቶች ከባህሪ ጋር ስለሚምታቱ፣ "እሱ/እሷ ልማዱ/ዷ ነው" እየተባለ ከመታለፍ ባለፈ የሚረዳ እና የሚረ'ዳ ሰው ማግኘት ይከብዳል። ወለም ያለህ እንደሆነ ግን "ልሽህ፣ ልደግፍህ" ባዩ ብዙ ነው።

ከልብ ስብራት ይልቅ የእግር ወለምታ more sense ይሰጠናል፤ ምክንያቱም ወለምታ physical evidence ሊቀርብለት ይችላል... ማለቴ አላምን ባይ እንኳን ካለ x-ray ተነስተህ ታሳየዋለህ። ግን የልብ ስብራትና የአዕምሮ መታወክ ታማሚው ሸፋፍኖ ሊደብቀው ከመቻሉም በላይ ቢናገሩት ራሱ አጉል የስም ተቀጥያ ያሰጣል በሚል ፍራቻ ዝምታን ያስመርጣል። "Am I being dramatic? Am I just seeking attention?" በሚሉ ጥያቄዎች ምክንያት አዕምሮን ዝም ለማሰኘት መጣር እና "normal" ለመሆን መሞከር የተለመደ ነው።

የድህነታችን ሰፊ እጅ እዚህም ጋር ሳይዳብሰን የቀረ አይመስለኝም። እንኳን በፊደል መቁጠሩ ያልገፉት ወላጆቻችን ቀርቶ ተምረናል የሚሉ እኩዮቻችን ብናስረዳቸው ብዙ የማይገቧቸው ነገሮች አሉ። ምክንያቱም እንኳን የአዕምሮ ደህንነት፣ በቀን ሦስቴ መብላት ራሱ እንደቅንጦት (luxury) የሚቆጠርባት ሀገር ውስጥ ነዋ የምንኖረው! ሌላውን ትተን "depression አይደለም ብሮ ... ርቦህ ነው ብላበት ይተውሀል" የሚሉ ፖስቶችን ስንት ጊዜ አየን?

በቀላሉ መፈወስ የሚችሉ ህመሞች ለከፋ የአእምሮ ህመም ወይም ለሞት ሲዳርጉ ከንፈር መምጠጥ ምንም አንደማይፈይድ ማህበረባችን ገና የገባው አይመስልም። እና አዎ Mental health is not a luxurious thing, it's a necessity!!

ፈረንጅ እግዜር ይስጠው እኛ የማናውቃቸውን ብዙ በሽታዎች በቅጥ ከማወቅና ከመሰነድ አልፎ መድሃኒቶቹንም ቀምሞ አዘጋጅቶልናል። ግን እኛ መታከም ለምን እንደምንፈራ አይገባኝም!

ጠበሉም ፀሎቱም ጋር መሄዱ ጥሩነቱ እንዳለ ሆኖ ሀኪም ጋር መሄድ ከኃጢአት እኩል የመቆጠሩ ነገር ያስገርማል። በጥቂት ፕሮፌሽናል እገዛ የሚስተካከሉ ችግሮች በዳተኝነት ምክንያት ሲብሱ ሲባባሱ ማየት ያሳዝናል። Anxiety disorders, personality disorders, depression and bipolar disorders, ADHD (attention deficit hyperactivity disorder)... የሚባሉትን አዕምሮ ነክ ሕመሞች ስማቸውን እንኳን በቅጥ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?

ብቻ We should normalize seeing professionals, getting treatment and taking medications!

እና ከሁሉም በላይ ስለራሳችን ስንል ራሳችንን ማበርታት ያለብን ይመስለኛል። You should be your own priority! I should be my own priority! በኛ መጎዳት ውስጥ የሚጎዱ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም፣ መጀመሪያ የጉዳቱ ሰለባዎች እኛው ነን! "የእኔን ደህንነት የሚነካ የማንም expectation ቢሆን ገደል መግባት ይችላል!" ማለት መልመድ ያለብን ይመስለኛል። በቃ ለራሳችን መቆም አለብን!

ተስፋ እንዳለ ለራሳችን ማሳየት አለብን፣ አንዲትም እርምጃ ቢሆን ወደፊት ፈቀቅ ለማለት መታገል አለብን። የእኛን ያህል ማንም እኛን ሊረዳን አይችልም! I should stand for myself! You should stand for yourself!!

ግን ደግሞ ቢመርረንም ልንውጠው የሚገባን ሀቅ ያለ ይመስለኛል። ሁሉም ሰው ለየራሱ ሕይወት ተጠያቂ ነው! ምንም ብንፍጨረጨር ልንቀይረው የማንችለው ሀቅ ፣ ልናድናቸው የማንችላቸው ሰዎች አሉ አንዳንዴ። ስለዚህ ስላለፍነው እና ስላለፉት ራሳችንን እየወቀስን መኖር የለብንም። Everyone is responsible for his own actions!

የሚበጀን ስለወደፊቱ መጨነቅ ነው። በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ግድ ይሰጠናል ወይ? ጓደኞቻችንን እንሰማቸዋለን ወይ? ሲደብራቸው "አለሁ፣ አይዞኝ" እንላቸዋለን ወይ? ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሰዎች እናደርጋለን ወይ?

እኛ እግዜር አይደለንም፣ ለሁሉም ሰው መፍትሔ የለንም። ሁሉንም ሰው አድምጠን አንችለውም፤ ግን ቢያንስ ሁላችንም በዙሪያችን ላሉ ጥቂት ሰዎች concerned እንሁን።

Idk why I'm ranting all this nonsense. ምናልባት የሆነ ሰው ከጠቀመ ብዬ ነው!

እና If you're struggling, you should know this...You ain't alone! ብቻችሁን አይደላችሁም! ብዙ ታጋይ አለ! ምንም እንኳን "ሁሌም ከጎናችሁ እሆናለሁ" ምናምን ብዬ ቃል የምገባበት አቅም ባይኖረኝም። ግን I will try at least! Genuinely እርዳታ የምትፈልጉ ከሆነ ብዙ ሊረዷችሁ የሚፈልጉ ሰዎች እዚህ አሉ - Reach them out! ከሁሉ በላይ ራሳችሁን እርዱ! Stand for yourself!

እርሶ ወይም ወዳጅ ዘመድዎ በራስ ማጥፋት ሀሳቦች እየተጨነቁ ከሆነ እባክዎን በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወይም የስነ-ልቦና ማዕከል በመሄድ የባለሙያ ድጋፍ እና ሪፈራል ያግኙ።

ለአእምሮ ህክምና ተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/3KTRnDr

በYonathan Getachew (Software Engineer)
www.facebook.com/YoniiBoss

@HakimEthio
Forwarded from Insurmountable grief
Aha Psychological Services will conduct a free screening and counseling service from October 10-15, 2022 to commemorate World Mental Health Day.
To book your session, use the link below.

https://docs.google.com/forms/d/1jQTu7unYYfg5kPA0Mry4_wKt87AGGz3U27Bt8P8lOCY/edit
Sending you love🖤
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
An oldie butttt...🖤


What we stay alive for
Forwarded from Our Side of the Story (Debbie)
https://bit.ly/3EzIbTB register here!
A little rant
I dont know what it took to be aware. It all feels like i knew somehow in the back of my mind that i was steering downhill but i just kind off brushed it off with the usual "be grateful" phrase you throw whenever you fear judgement.this is me as naked as it goes. just like the old days. i think it took a while for this to come,አይደል? your girl was serving capitalism disguised as a dream. med school is really not the best place to be for anyone(truth be told) especially for a person as anxious and depressed as me. Imagine not wanting to get up and be a human most days but you have to becasue a 4 hour class is waiting for you followed by discussion with a bunch of genius wannna-bes for 2 hours about diseases even your lectureres never heard of. you are right i might probably be the most unfit of all. God only knows how many ጨጎራ disguised depression sick leaves are to come in the coming years. that is if there are any coming years here. everyday feels like dragging a body bag. well there are some good days but those good days are relative. i feel like at this point i would be amazed by days i feel healthy rather than sick. I also saw that the world has its way of making you its own no matter how much you refuse. I saw myself silently accepting injustice everywhere because i just "Have to live with it". because i dont have to be opinionated about everything or just have to fit in and dont ask too many questions. that part in the movie where they say "i dont recognize myself in the mirror" is no joke. I didnot know how i got to these points-dark circles around my eyes-i wonder how long i could go on before i fall unconscious. I cant lie that would be a good break. just to be unconscious for 1 የብርሃን አመት. joint pains that feel like my body is trying to consume itself to the ground. Words i didn't say and couldn't say are day by day acccmulating on my chest making it hard to breathe. Can you believe i almost brought another poor soul into this mess...dont worry not a baby. just a man. a poor pure hearted man I didnt want to lose because he was not one to miss. Ata boy! to the recurrent trauma responses we freed the poor human from the shackles of a mess called "my life." i guess he really got his moms blessings. I made peace with humans that drained every part of me and took for granted ones that wanted to heal me. but one thing hasn't changed እስካሁን. I still decieve myself that i am ok and then fall to a pit of nothingness. i dont learn እሱን ነው የተረዳሁት. ቀኑ ዝምብሎ ይሮጣል I think i am ok then voila---not getting out of bed,struggling to sleep,forget or dont want to eat decent human food and cut off everyone. i amnot gonnna lie i did give myself pleasure of ጲውing myself as a relief. anything to escape አይደል?

Here goes that "you got this. dont give up" part you have all been waiting for. ባክሽ ለራስሽ ዋጪው እንዳትሉኝ. i will just say this gene "one day at atime" eshi. whatever you are going through. And a small tip---get out of bed even if its really not that kind of days for you.l believe me for someone who lived with this shit for almost 8 years this does work a bit. Get that bit of sunlight-get the perk of living in living in your 12 month of sunshine country-one thing that is still free በዚህ ኑሮ ውድነት. and i might be like your high school counselor for repeating this again and again but do talk to someone. believe me we are all the same miserable humans with a bit different twist to everyone of our lives. like how me and debbie send " we got this and its gonna be ok" texts to eachother even though we highly doubt it at this point. Atleast you will have buddies to share relatable tiktoks to. and please bore me with the details of your traumas and day to day life. Just kidding. my dms have been really dry lately....maybe i just shouldnt have let go of that man...ገልቱ me i guess.

-Yeab as real a sit gets
Forwarded from Thoughts Hub (Hubeyb☁️)
My heart is bound in you, the bond of the earth with plants.
Forwarded from The Bored Therapist
አንዳንዴ ውሃ ጠምቶም ብርጭቆ ማንሳት ይደክማል?