"እና አበባው ሳይደርስሽ ከእጄ ቀረ ። እናቴም ያኔ አበባውን ስሰጣት እንዴት ሆኜ እንዳመጣሁት አልጠየቀችም ። ማለት ፥ ስላልጠየቀች ለመቅጠፍ የከፈለኩትን መስዋዕትነት አልተረዳችም ። በልጅ ሩሄ አበባ ያህል ነገር ከሰው አጥር ላይ አርጄላት ፥ በቅጡ እንኳ አልባረከችኝም ። ከንቱ ድካም ነበር ። አበርክቶቴ መገፋት የጀመረው ከያኔ አንስቶ ነው ፤ እርኩስ እንደሚሠዋው በግ ፥ እሳት ከራማ ወርዶ እንደማይበላው ...።"
Forwarded from Hakim
ሁለት ውብ ታሪኮች ከአማኑኤል ሆስፒታል
==========================
አማኑኤል ሆስፒታል የሰው ድክመት፣ ውድቀት፣ ህመም ብቻ የሚሰማበት የሚመስላቸው ሰዎች አይጠፉም፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የመነሳት፣ የጥንካሬ፣የፅናትና የፍቅር ውብ ታሪኮች ይስተናገዳሉ፡፡ ሁለቱ በዚህ ሳምንት ከገጠመኝ እነሆ፦
1) አማኑኤል የሴቶች ዋርድ የሀኪሞች ክፍል ተቀምጬ ካርድ ላይ እየፃፍኩ ነው፡፡ በሩ ገርበብ ብሏል፡፡ አንድ ታካሚ ከአልጋዋ ከነጋ አልተነሳችም፡፡ የደበራት ትመስላለች፡፡ ገርበብ ባለው በር ትታየኛለች፡፡ አንድ ወጣት ሴት ፍራፍሬ በፌስታል ይዛ ልትጠይቃት ትገባለች። አይኗ ብርት ብሎ ከአልጋዋ ወዲያው ተነሳች። ተቃቀፉ፡፡ በቀናት ውስጥ ያላየንባት ደስታ ውስጥ ሆና መጫወት ጀመሩ፡፡ ጠያቂዎን አውቃታለሁ፡፡ ከሳምንት በፊት እዚሁ ሆስፒታል እዚሁ ክፍል ተኝታ ነበር፡፡ ጓደኛዋን ልትጠይቅ መምጣቷ ነው፡፡ ተኝታ የምትታከመው ድንገት አቀረቀረች፡፡ አይኗን ሳታነሳ ጓደኛዋን "ግን የምንድን ይመስልሻል?" ብላ ጠየቀቻት፡፡ ጓደኛዋ እቅፍ አደረገቻት "እሱ የፈጣሪ ስራ ነው፡፡ እኛ ግን መድሀኒታችንን እንወስዳለን አለቻት፡፡"...
አንድ የኩላሊት ጠጠር ቀዶጥገና ሀኪም "ሀኪሙ ጠጠሩን ያወጣል፤ የሚያድነው ግን አምላክ ነው፡፡" ያለው ትውስ አለኝ፡፡
2) ታካሚ ወንድሙን ይዞ ኦፒዲ ይገባል፡፡ መልካቸው በጣም ይለያያል፡፡ "እባካችሁ ተኝቶ ይታከም?" አለን፡፡ "ያልተለመደ ፀባይ ሲታይበት አከራዮቻችን ቤት እንድንለቅ ጠየቁን፡፡ ለትንሽ ጊዜ ቢተኛ?" አለን፡፡ "ቤተሰቦቻችሁ የት ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት፡፡ መልሱ ያልጠበቅኩት ነበር፡፡ "ከተለያየ ቤተሰብ ነው የመጣነው ግን ወንድሜ ነው፡፡ በማደጎ አብረን ነው ያደግነው፡፡ እሱ ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ እኔ ዱርዬ ነበርኩኝ፡፡ ማደጎውን ጥዬ ወጣሁ፡፡ ከዛ ጥሩ ያልሆነ ህይወት ነው ያሳለፍኩት፡፡ የተለያዩ ቦታዎች ዞሬ ስመለስ እሱ ኮሌጅ ተመርቋል ግን አእምሮውን አሞታል፡፡ ማንም አጠገቡ የለም፡፡ ስንገናኝ እኔ ያለፈው ህይወቴን ትቼ በእምንቴ ጠንክሬ ነበር፡፡ አሳከምኩትና ደህና ሆነ፡፡ አብረን መኖር ጀመርን፡፡ አሁን አመታት ሆኖናል፡፡ አንዳንዴ ያስቸግረኛል፡፡ ነገር ግን እኔ ራሴን ብዙ እንደተደረገለት ሰው ነው የምቆጥረው፡፡ ስለዚህ እሱን ማገዝ መቻሌን እንደ እድል ነው የማየው፡፡"....
በየሚዲያው በሚታየውና በሚሰማው እጅጉን ኮስምኖ የነበረው በሰብአዊነት ላይ የነበረኝ ግምት ሲለመልም ተሰማኝ።
መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው ፤ የአእምሮ ህክምና ሀኪም
@HakimEthio

Forwarded from ስናስብ *አለ አይደል....*
ህፃንነቴ በናፍቆት እጣን አዕምሮዬን ሲስበው
ያ *ውሻ በልቶኝ በልቶኝ በልቶኝ በልቶኝ...* ብዬ ለእኩያ ወዳጆቼ በኩራት የተረኩላቸው ጀብዱ ትዝ አለኝ...
በምክንያት ነው ትዝ ያለኝ.. የሰው ውሻ ለምጄ
ከህፃንነቴ አልተሻልኩም ... እያለቀስኩ ወደ ቤቴ እሮጣለው
ወዳጄን አገኘዋለው... እኩያዬ ባይሆንም ጓደኛዬ ነው .... ፈጣሪ ነኝ ብሎኛል.... ከዛም እናወራለን ....ይጠይቀኛል ....መልስለታለው
*ምን ሆነክ ነው ምታለቅሰው?*
*ውሻ በልቶኝ በልቶኝ በልቶኝ.....*
.
@snasb_hasab

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
This found me and it felt like the universe was really talking to me. I wanted it to find you too. Healing is this. This is true healing. No filters or beautiful words to inorder to beautify it. So if this does find you,just know that it's not just you.🖤
Forwarded from Debbie's Lens
Come and explore our city with me at night and let’s hear the streetlights tell stories🖤