ፍልስፍና
623 subscribers
491 photos
11 videos
478 files
39 links
"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ
Download Telegram
https://youtu.be/ONTpBvDH2lQ

አስፈላጊ የፍልስፍና ሀሳቦች ከሀኒባል ጋር 🙏
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
የኒሂሊዝም (Nihilism) ፍልስፍና መሰረቱ ጥቅሙስ ምንድን ነው?.

(አለማየሁ ገላጋይ ኢትዮጵያዊው ኒሂሊስት)


ኒሂሊዝም የሚባለው ፍልስፍና በአውሮፓ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳ ርዕዮት ነው። ኒሂሊዝም እንደሚገለፅበት አውድ እና ዲሲፕሊን የተለያዩ መልኮች ቢኖሩትም ማጠንጠኛው ሃይማኖት፣ ዕምነት፣ ባህል፣ እውቀት፣ ሕግ፣ ሥነ ምግባር ወዘተን መካድ ነው። ኒሂሊዝም መሠረቱ ጥርጥር (skepticism) ነው። ጥርጥር ዓላማው ውሸትን ለይቶ እውነት ጋር መድረስ ነው። ጥርጥር ግን በወለደችው ኒሂሊዝም የተሰኘ ልጅ ዓላማዋንም፣ ትርጉሟንም አጥታ እየሞተች ነው። ጥርጣሬ ጫፍ ሲይዝ እና ጨለምተኛነት የሚባል ቅመም ተጨምሮበት ሲበስል ኒሂሊዝምን ይወልዳል። ኒሂሊዝም ሁሉንም ነገር ያለምህረት መካድ ነውና። በኔ በኩል ጥቅም አለው ብዬ አላስብም። የአብዘርድ አቀንቃኙ አልበርት ካሙዩ እንኩዋን፣ እውነት ነው ህይወት ትርጉም የላትም፣ ግን ትርጉም የላትም ብለን ልንተዋት አይገባም፣ ትርጉም ልንፈጥርላት ግድ ነው ይለናል። አይሁዲው ቪክተር ፍራንክል ከአልበርት ካምዩ በተቃራኒ በሕይወት ለመኖር የሚያነሳሳን ነገር ትርጉም ፍለጋችን መሆኑን ቢያስረዳም።
"""""
እሴቶች: —

* የሰው ልጅ በማህበራዊ ኑሮ ዉስጥ ህልውናውን የሚያስጠብቅባቸው፣
ባህሉን የሚያስከብርባቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፍባቸው፣

* ዕውቀቱን የሚያሰፍርባቸው፣
* ስሜቱን የሚገልጽባቸውና ሥነ ምግባሩን የሚተረጉምባቸው. ናቸው።
"""""
የሰው ልጅ እነዚህን የህልውናው ምሰሶዎች የተከለበት እሴቶች አሉት፡፡ እነዚህ እሴቶች የሰው ልጅ የፈጠራቸው እና ለእነዚህ ዕሴቶች ተገዥ ሆኖ የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አንድ ማህበረሰብ እንደ ማኅበር ራሱን የሚገልጥበትና ህላዌውን የሚያዘልቅበት ባህል አለው፡፡ ባህል ለተፈጥሮአዊ ጉዳዮች የሚሰጥ “ምላሽ” (expression) ነው፡፡ እምነት፣ ሃይማኖት፣ እውቀት፣ ሞራል፣ ልማድ፣ ህግ/መተዳደሪያ ደንብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ምርትና ማምረቻ መሳሪያ፣ አልባሳት፣ ወዘተ. . . የባህል ዘርፎች ናቸው፡፡

በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ባህል አለ። ማህበረሰብ ለባሕል ያለው አመለካከት የተለያዬ ቢሆንም ለዕሴቶቹ እውቅናን መስጠት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነታቸውንም ያምናል፡፡ ነገር ግን ኒሂሊዝም እነዚህን ሰዋዊ እሴቶች ይክዳል፤ አላስፈላጊነታቸውንም ይሰብካል፡፡ መሰረት የሌላቸውና አንዳችም ጥቅም የማይሰጡ መሆናቸውን በመግለጽ በሰው ልጅ ህላዌ ውስጥ ያላቸውን ህልውና ይክዳል። ኒሂሊዝም ሕይወት ትርጉም የለሽ እንደሆነ በማመን፣ ሁሉንም ሃይማኖታዊ እና ሥነ ምግባራዊ መርሆች አለመቀበል ነው፣ ልቅ የሆነ ነፃነት ይኑርም፣ ሁሉንም ከዜሮ እንጀምረው ይላል። «ነባሩ እሴት፣ ወግ፣ ባህል፣ እምነት በአጠቃላይ ምድራዊ ህግጋትና ማህበራዊ ትብታቦች የሠውን ልጅ ነፃነት ተጋፍተዋል፤ ስለዚህ የሠው ልጂ ከእነዚህ ትብታቦችና ሠው ሠራሽ ሠንሠለቶች እስር ነፃ መውጣት አለበት» ይላል።

የሰውን ተፈጥሯዊ ምንነት ካለማወቅ የሚመነጭ የጥፋት መንገድም ይመስላል። ሰው በcognitive evolution ያገኘውና ከሌሎች እንሰሳት የለየው ነገር ቢኖር የሌለን ነገር በ association በአዕምሮው መፍጠር መቻሉ ነው። ነገር ግን ኒሂሊስቶች በዚህ መንገድ የተፈጠረው ይጥፋና በሌላ ተጨባጭ እውነት ይተካ ይላሉ። በመጀመሪያ ይህን የማይጨበጥ እውነት እንዴት ለማጥፋት ይቻለናል? ከተቻለስ፣ ሰው እራሱ መልሱ እንደማይፈጥረው ምን እርግጠኛ አደረገን? ሃይማኖት የራሱ ችግር እንዳለበት ብስማማም፣ እንደምንለው ስላሰብን የሚጠፋ አይደለም። የጠፋ ቢመስለንም ቅርጹን ቀይሮ ይቀጥላል። የተሻለው፣ ችግርንና መንስኤዎችን መለየት፣ መፍትሔን መዘየድ ነው። ችግሩ፣ ከችግሮች ከአንዱ ላይ ፊጥ ስላልን ችግር የፈታን መስሎናል። 

ይቀጥላልል
ትንሽ እረፍት @poems_Essay ከሞገስ ዘአምድ ጋር...🧘🏾‍♂️🌬
"Why Darling, l don't live at all When l'm not with You"
Ernest Hemingway
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
የቀጠለ .. ኒሂሊዝም ...



እንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያሁ ገላገይ «የተጠላው እንዳልተጠላ» መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገድ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም።

የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።
""""
አሌክሶ የኢትዮጵያን ችግር ሃይማኖት ላይ አንጠልጥሎ፣ cause-effect relation እንዳንፈልግ መንገዱን ዘግቶብናል። ሃይማኖት የችግራችን አንዱ መንስኤ ነው፣ ብቸኛው መንስኤ ግን አይደለም። የተለመደው ሃይማኖትን በኒህሊዝም ይጥፋ አይነት አካሄድ ግን መፍትሄ አይሆንም። እንደምሳሌም፣ የአውሮፓው የ500 አመታት፣ የጃፓን ቢያንስ 170 ተሰርቶበት የመጣ ነው። የመንፈሳዊ እውቀት ለሌላው secular እውቀት ቦታ እንዲለቅ (አውሮፓ) ወይም አጋዥ መሆን የሚችለውን አጋዥ በማድረግ (ጃፓን) የተሰራ ነው። አሌክስ እንደሚለው በማጥፋት አይደለም። ቱርክን ስንወስደ ደግሞ ኢምፓየር ሆኖ ከአረቢያን ኢምፓየር መውደቅ ቀጥሎ የመጣ፣ እስከ አንደኛው አለም ጦርነት ድረስ በጣም ሰፊ ግዛት የነበረው ነው። ይህም ከኢምፓየሮች ታሪክ ጋር መመርመር ያለበት ነው። ነገር ግን ሃይማኖታቸውንና  የምዕራቡን ሳይንስ ይዘው፣ የምዕራቡን የፖለቲካ ተጽዕኖ ከምስራቁም ጋር እየሰሩ ቀንሰው፣ ከአንደኛው የአለም ጦርነት ሽንፈታቸው በኋላ ቱርኮች እድገት ላይ ናቸው። ይህም ሃይማኖትን የችግራችን ዋናው መንስኤ አድርጎ መቁጠር ውሃ የማይቋጥር መሆኑን ያሳያል።
| <<ስለ ተ ስ ፋ ማጣት እና መቁረጥ እንዲሁም ስለ ሞ ት የሚያወራ ሰው ለ'ኔ የ ሞ ተ ብቻ ነው >> ትለኛለች። አጠገቧ የተቀመጥኩት ሬ ሳ መሆኔን አላስተዋለች!. |

𝚐𝚛𝚊𝚟𝚎
|........ብቸኝነት ቤቱን እኔ ላይ ከሰራ ዘመናት ተቆጠሩ...ተዘግቶ የቆየ በድር የተተበተበ ጽልመት የቆየበት መኖሪያ ሆኖል! ወደ ላይ የሚያስወጣ ደረጃ አለው...ከላይ ድምፆች ይሰማሉ...እዛው ቆሞ በሀሳብ መንቀሳቀሱን ምርጫዬ አደረኩ......


𝑔𝑟𝑎𝑣𝑒
<<.....
ድብብቆሽ እንጫወት?!እኔ ልብ ውስጥ ከተደበቅሽ አንቺን ማግኘት አይከብድም። ከራስሽ ቅርፊት ጀርባ ከተደበቅሽ ግን ማንም አንቺን በመፈለግ አይጠቀምም።
:( .........>>

#ጂብራን_Khalil
Pessimism....ጨለምተኝነት


እንደው በፍልስፍናው የዘመን ሀሳብ ጉዞ አርተር ሾፐንሀወር የሚያክል ጽልመታዊ አመለካከት ለህይወት፣ለሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ለውበት የሰጠ አሳቢ ከእርሱ በኋላ እንጂ በፊት ማግኘት ከባድ ነው።እሱ ያሳረፈውን ተፅእኖ ደግሞ ከእርሱ በኋላ በተነሱ አሳቢያን ፍልስፍና ማዕከል ጀርባ መገኘቱ ፍልስፍናዎቹን በጥልቀት እንዲዳሰሱ ጉጉት ውስጥ ይጨምራል።ከሾፐንሀወር ኋላ ኒቼ፣ካሙ፣ ሳርቴር፣ኪርጋርድ፣ቤኬት፣ሲኦራን...የፍልስፍናቸውን መጠንጠኛ እንዲቀይሩ አስችሏቸዋል፤በእርግጥ ሬኒ ዴስካርት በደረጃ አንድ ብናስቀምጠውም የሾፐንሀወርን የቀጠለ ጉልህ ሚና መዘንጋት የሚቻል አይመስለኝም። ኒቼ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት እና የጊዜ ክሽፈት ሲነግረን.. ኪርጋረደን ደግሞ የግለሰብ ልእልናን የኃይማኖት በፁኑ አስፈላጊነት ሲሰብከን... ካሙ እና ሳርቴር የህይወት ወለፈንዲነት እና የእኛን የነፃነት እንዲሁም ፈጠራዊ መንገድ አሳዩን።

  ከሾፐንሀወር  ኋላ እንደሰው የሆነ ህይወት አስፈሪነትን እና የህይወት ስቃይና መከራ እንደግለሰብ አውርዶ ያስመለከተን-ሮማዊው ፈላስፋ ኢሜል ሲኦራን ነበር።ሲኦራን ህይወታችን ላይ ያጠላውን ጥቁር ጨለማ በብእሩ ከነደፈው 𝑜𝑛 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑖𝑔ℎ𝑡𝑠 𝑜𝑓 𝑑𝑒𝑠𝑝𝑎𝑖𝑟 በተሰኘው መፅሀፉ ያሳየናል።መፅሀፉ በብዙ ቁርጥራጭ ሀሳቦች የተሞላ ሆኖ የሚያሳየን ግን ስለአንድ ነገር ብቻ ይሆናል -ስለአስፈሪዋ ህይወታችን።የሾፐንሀወርን ውለታ ላለመዘንጋት ያህል እናንሳው እንጂ የሲኦራን ፍልስፍና መለስ ብለን እንቃኛለን።


ተፃፈ በይሁዳ
በትግስት አብራችሁን ለነበራችሁ ቤተሶቦቻችን🙏🙏 አብሮነታችሁ አይለየን🙏🙏
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (MUSSIE. S)
ክፍል ሁለት

ሄግል እና ማርክስ

ማርክስ የሰው ልጅ ታርክን እና የነገሮችን ለውጥ ለማየት ሁለት ነገሮች መረዳት እንደሚያስፈልግ ይናገራል ። የመጀመሪያው dialectical materialism ሲሆን ሁለተኛው historical materialism ነው ።
ዲያሌክቲካል ማቴሪያሊዝም የሚነግረን የሰው ልጅ ታርክ የሚለወጠው በተቃርኖ ህጎች ነው እነዚህ ተቃርኖዎች የተዋቀሩት ፈላስፋው ሄግል በለያቸው በአንብሮ (Thesis) ተቃርኖ (anti Thesis) እና በአስተፃምሮ  (synthesis) ነው

Historical materialism ደግሞ የሚለ ው በሰው ልጅ ታርክ ውስጥ ያለውን ለውጥ በምናይበት ጊዜ የሰው ልጅ ታርክ የሚለወጠው በግለሰቡ አስተሳሰብ ላይ ተሞርክዞ ሳይሆን የግለሰቦች እና የአለም ተፈጥሮ የሚለወጠው አንድ  ስርአት ውስጥ ባለው የeconomy ስርአት ላይ ተሞርኩዞ ነው
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (MUSSIE. S)
ፍልስፍና
ክፍል ሁለት ሄግል እና ማርክስ ማርክስ የሰው ልጅ ታርክን እና የነገሮችን ለውጥ ለማየት ሁለት ነገሮች መረዳት እንደሚያስፈልግ ይናገራል ። የመጀመሪያው dialectical materialism ሲሆን ሁለተኛው historical materialism ነው ። ዲያሌክቲካል ማቴሪያሊዝም የሚነግረን የሰው ልጅ ታርክ የሚለወጠው በተቃርኖ ህጎች ነው እነዚህ ተቃርኖዎች የተዋቀሩት ፈላስፋው ሄግል በለያቸው በአንብሮ…
የቀጠለ....

Dialectical materialism እና Historical materialism በደንብ ለመረዳት የማርክሲዝም መዝገበ ቃላት መፈተሽ በጣም አስፈላጊ ነው ። አንብሮ (thesis) የሚባለው አንድ ሰው ለሰዎች በማቅረብ በክርክር የሚደግፈው ሀሳብ ይባላል አንብሮ ክርክር የሚያስነሳ በመሆኑ የመነሻነት ፍች አለው ክርክር መፍጠሩ የሚሮረው ውጤት የመነሻ ሀሳብ መሻሩና በተቃርኖው መተካቱ ነው ይላል ።

ተቃርኖ (antithesis) የሚባለው አንድ  ነገር ክስተት ወይም ሀሳብ  ሁሉት የተያያዙ የማይነጣጠሉና የሚወራረሱ ነገር ግን በተቃራኒ ወይም ተቃዋሚ የሆኑ ክፍሎች የሚያመለክት ሀሳብ ነው።

መዝገበ ቃሉ እንደሚለው synthesis ተቃርኖ አንብሮን ሽሮ በተራው ሲሻርና ከሁለቱ የሚገኝ ውጤቶች በአንድነት ተጠቃለው ከፍተኛ የሆነ ሀሳብ ወይም ክስተት ሲፈጥሩ አስተፃምሮ ይባላል። ይህ ማለት ግን አስተፃምሮ የአንብሮና የተቃርኖ አይደለም የሁለቱን ጠቃሚ ጠባዮች የሚያቅፍ በመሆኑ የነሱ የበላይና ከፍተኛ የእድገት ደረጃ ነው።

Historical materialism ባለፈው እንዳየነው  የሚለው በሰው ልጅ ታርክ ውስጥ ያለውን ለውጥ በምናይበት ጊዜ የሰው ልጅ ታርክ የሚለወጠው በግለሰቡ አስተሳሰብ ላይ ተሞርክዞ ሳይሆን የግለሰቦች እና የአለም ተፈጥሮ የሚለወጠው አንድ  ስርአት ውስጥ ባለው የeconomy ስርአት ላይ ተሞርኩዞ ነው ። በሌላ አባባል የሰው ልጅን ታርክ ለማጥናት ቁስ አካል / material means ላይ መሰረት ማድረግ አለብን ማለት ነው እንደማርክስ አባባል።

ይህን በቀላል አማርኛ ለማስረዳት  የማርክስ አከፋፈል mode of production / economy ላይ መሰረት ባደረገ መልኩ የሰው ልጅ ታርክን ለማጥናት ማህበረሰቦችን ለአምስት ይከፍላለቸል። እነሱም primitive community, slave owning mode of production, feudal mode of production, socialist mode of production, capitalist mode of production የሚከተሉ ናቸው።

Dialectical materialism ለማስረዳት አንዱን ስርአት መውሰድ እንችላለን። ለምሳሌ slave- master ግንኙነት ብንወስድ thesis የሚሆነው ባርያዎች  ወይም በድሮ ዘመን የነበሩ ሰዎች እራሳ ቸውን እንደ አቅም አልባ እና  የበታች እንደሆኑ  ማሰብ  ሲጀምሩ የባርያነት ሀሳብን ፈጠረ። የሱ anti thesis ደግሞ የበላይ የሆኑ ገዢዎችን ወይም slave owners, መፍጠሩ ነው ።ይህ ደሞ synthesis ፈጠረ። ማለትም የባርያ ስርአት ወይም slave owning mode production.

ይህ thesis, anti thesis እና synthesis ከprimitive society/ community እና socialism ውጪ ባሉ ስርአቶች ላይ ይሰራል። primitive society የምለው classless ወይም የሁሉት ክፍሎች /ሀሳቦች ተቃርኖ የሌለው ስርአት ነው። የፍልስፍና ትምህርት በሚለው ብሩክ አለምነህ በተዘጋጀው ቅፅ 1 መፅሐፍ ላይ የተቀመጠውን አገላለፅ ለመጠቀም ያህል socialism የምንለው ስርአት እንደ capitalism ስርአት የመደብ ግጭት የሌለው/ የተቃርኖዎች የሌሉት  ስርአት ማለትም በሰራተኛው/ወዛደሩ ወይም ገንዘብ ባለቸው እና በሌላቸው በሀብታሞች እና በድሆች  ያለ አይነት ነገር የሌለበት ስርአት ነው። ይህ ስርአት socialism የሚመጣው የcapitalism ስርአት ሲገረሰስ ነው። የcapitalism ስርአት ደግሞ የሚጠፋው ሰራተኛው በሚያስነሳው አብዮት ነው። ይህም ምንም አይነት ተቃርኖ ወይም የመደብ ግጭት የሌለበትና የሰው ልጆች ሁሉ እንደየ ሥራቸው መካፈል የሚችሉበት ስርአት ያመጣል ተብሎ ይታሰባል። ይህ ስርአት socialism ነው።
[ ካለ መረጋጋት መማር ]
~ኦሾ
[ቡድሀ]
~ኦሾ
"ጠርጥር! ፣ ጠርጥር! አንዳንዴ ከገንፎም አይጠፋም ስንጥር" ይላል ያገሬ ሰው!

በ17ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ ገኖ የወጣ አፍቃሬ−አመክንዮ ፈላስፋ ነው፤ ዴካርት። በዓለም የፍልስፍና ታሪክ ውስጥም የዘመናዊ ፍልስፍና አባት ተደርጎ ይቆጠራል። ገና በጠዋቱ እናቱ እንደወለደችው የሞተችበት ዴካርት፣ የህይወት ውጣ-ውረዱን ዘመዶቹ ቤት በማደግ መወጣት የቻለ ሲሆን አልፎ ተርፎም እውቅ የሒሳብ ልሂቅ፤ ፈላስፋ እና ሳይንቲስት እንዲሁም የዘመናዊ ፍልስፍና አባት ሊሆንም ችሏል።

ዴካርት እድሜውን የፈጀው የእውቀት መጀመሪያ ምን እንደሆነ ሲያስስ ነው፡፡ ይህ እሱ የፈለገው ቀዳማይ-እውቀት እያንዳንዱ ሰው የግሉን ህይወት ሊመሠርት የሚችልበት የማይናወጥ እውቀት ነው፡፡
ለመጠራጠር ማሰብ ያስፈልጋል፤ ከተጠራጠርን ማሰብ እንችላለን፤ ካሰብን ደግሞ ያ ያሰብነውን እንሆናለን፡፡ ጥርጣሬ መጀመሪያ ላይ ነገሮችን በሙሉ ወደ ጥያቄ ይለውጣል ኋላ ላይ ደግሞ ይገለብጥና የእርግጠኝነት ምንጭ ይሆናል፡፡
በዚህች ዓለም ላይ የማንጠረጥረው ነገር ምን አለ? ለሚለው ጥያቄ ቁጭ ብሎ ሲቆዝም ዴካርት ያገኘው መልስ ቢኖር “I think, therefore I am” የሚለውን ዓረፍተ-ነገር ነው፡፡
ሁሉን እጠራጠራለሁ፤ እኔ ራሴ በሕይወት እየኖርኩ ስለመሆኔ ግን ልጠራጠር አልችልም፤ ምክንያቱም አስባለሁ፤ ለመጠራጠር ራሱ መጀመሪያ መኖር አለብኝ፤ አሁን እያሰብኩ ነው፤ ስለዚህም እየኖርኩ ነው፡፡ (I think, therefore I am) የሚለው የዴካርት አባባል፣ ለፈላስፎች ጥልቅ የሆነ ትርጉም አለው፡፡ የጥንቱና የመካከለኛው ዘመን ሰው፣ እውቀትንና እውነትን ለማግኘት ከራሱ ውጭ ባለው ሰፊ ዓለም ውስጥ ሲባዝን ነበር፡፡ በዴካርት ፍልስፍና ውስጥ ግን የውጭውን ዓለም መዳሰሱ ቀርቶ የምርምሩ ጅማሮ ከራስ ሕልውና ሆነ፡፡
የዚህን ዓለም እውነት ለማግኘት መጀመር ያለብን “ከራሳችን” ነው የሚለው የዴካርት ፍልስፍና፤ የዕውቀትንና የእውነትን መለኪያ መስፈርትን ለማግኘት ባደረገው ጥረት ውስጥ “ተፈጥሮን” ከእውነት ምንጭነት አስወገደው! ... ለነገሩ እሱዬ መጀመሪያ መጠራጠር የጀመረው እሱ-ራሱ ነበር፡፡

እፊታችን እያየን ከምናወራቸው ተጨባጭ ነገሮች ጀምሮ የምናምናቸው ነገሮች እርግጠኞች ልንሆን አንችልም የሚለው ዴካርት ሁሉንም ነገር፤ የሚያየውን፣ የሚዳስሰውን፣ የሚያሸተውን፣ የሚቀምሰውን በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት የሚያገኘውን መረጃ በሙሉ ከመቀበል ይልቅ በጥያቄና በጥርጣሬ ያዋክባቸዋል።
እርግጠኛ የሆነ እውቀትን ለማግኘት ዴካርት የተጠቀመበት ዘዴ ደግሞ፤ ከዚህ በፊት እርግጠኛ የሆንባቸውን ነገሮች ሁሉ በመጠራጠር እና ባለመቀበል ነው። እናውቀዋለን የምንለውን ነገር ሁሉ በጥያቄ ማብጠርጠር ማለት ነው።”
ዘላቂና የማይናወጥ እውቀትን መመስረት ካለብኝ፣ እስከዛሬ በሕይወት ዘመኔ የሰበሰብኩትን እውቀት ተብዬ ሁሉ ድምጥማጡን ማጥፋት እንዳለብኝ ተገንዝቤአለሁ” ይለናል፤ “ቀዳማዊ ተመስጦ” በተባለው ድርሳኑ በአካባቢያችን ያሉ ነገሮችን ሁሉ እየበረቃቀስን እና እያብጠረጠርን መፈተሽ እንዳለብን ያሳስባል፤ ዴካርት።
ይህንንም ተከትሎ ሦስት አፈንጋጭ ሙግቶችን
ያቀርባል፤ በዘልማድ የተቀበላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማስወገድ እንዲረዱትና እርግጠኛ የሆነ እውቀት ለመመስረት እንዲችል። እያንዳንዱን እምነቱን አንድ በአንድ በመጨፍለቅ ሳይሆን መሰረታዊ የእምነቱን መርሆዎችን ማንገራገጭ እንደስልት ይጠቀማል፤ ዴካርት።
በመሰረታዊነት የተጠቀመባቸውን ሦስቱን ሙግቶች እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

ሀ) ማንኛውንም ያልተመረመረ ሀሳብ እና በስምምነት የተቀበልነውን ሁሉ በተደራጀና መመሪያዎችን በተከተለ መልኩ በጥርጣሬ መፈተሽ። ወይም ባጭሩ አፈንጋጭነት ልንለው እንችላለን። ይህ በየዋህነት የተቀበልናቸውን አስተሳሰቦች ለማጥቃት የተጠቀመበት ሙግት ነው። “ከጊዜ ወደ ጊዜ የስሜት ህዋሶቼ እያጭበረበሩኝ እንደ ሆነ ደርሸበታለሁ።” የሚለው ዴካርት፤ “ለአንዲት ጊዜ እንኳን ያታለለችኝን የስሜት ህዋሴን አለማመኔ ሁነኛ እርምጃ ነው” ይላል።

ለ) ያልጠራ፣ እራሱን ያልቻለ እና ግጭቶች/መፋለሶች ያሉበትን ሐሳብ አለመቀበል። ይሄኛው የዴካርት ሙግት "የህልም ሙግት" (The Dream Argument) እየተባለ ይጠራል።

ሐ) እራስን በማወቅ፤ ከዓለት በጠነከረ መሰረት ላይ ሐሳባችንን መስርተን፤ በማንኛውም ጥርጣሬ የማይነዋወጥ ከራስ ከውስጥ የመነጨ “እያሰብኩ ስለሆነ እኔ ኅልው ነኝ” የሚል ግለሰባዊነት ላይ መድረስ። (“Cogito, ergo sum”) “የስሜት ህዋሳት አንዳንዴ ያጭበረብሩናል።


ይቀጥላል ✍️
Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም  (Peter)
እንቀጥል አ


ባለ ጠርዙን ማማ ከሩቅ ስናየው ድቡልቡል አድርገው ያሳየናል፤ ቀጥ ያለ እንጨት ውኃ ውስጥ ብንከትተው ስብርብር ያለ ሆኖ ይታዩናል፤ ስለዚህ የስሜት ህዋሳት የሚታመን ብያኔ አይሰጡንም ማለት ነው።
አንዳንዴ ደግሞ ህልምና እውኑን መለየት ይቸግራል፤ “አልጋው ላይ እንዳልተጋደመ ሰው ሁሉ ጥርት ያሉ ምስሎችን አያለሁ፤ በህልሜ መሆኑን እንኳን የምለይበት ምንም ምልክት አጣለሁ” .... ዴካርት ይህንን እያምሰለሰለ ይቀጥልና እንዲህ ይለናል። “በስሜት ህዋሳቶቼ የማገኘውን መልእክት ባልቀበልም ይኸው ደግሞ ሌላ እውነት የሚመስል ነገር የሚያሳውቀኝ ሌላ መንገድ አለ”
የህልሙን እና የስሜት ህዋሳቱን መልእክት ይበልጥ እያፍተለተለ ከፍ ወዳለ ሀሳብ ይወሰደዋል።
“የሚያታልለኝ ኃይል አለ ማለት ነው። ፈጣሪ ይህንን ሊያደርግብኝ ይችላልን? ይህንን ካደረገብኝማ “ፍጽምና” ባህሪው ሊሆን አይችልም። ስለዚህ እኔን ለማወናበድ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሚሰራ ሌላ አወናባጅ ዲያብሎስ አለ ማለት ነው” ይላል ዴካርት።
ስለዚህም የዚህን አወናባጅ ዲያብሎስ ምክር ለማሸነፍ ሐሳቦቸን ግልጽ፣ ልዩ (እራሱን የቻለ) እና እርስ በርሱ የማይፋለስ በማድረግ ወደ ፍጹማዊው የፈጣሪ ባህሪ ማስጠጋት አለብን ማለት ነው። ሐሳባችንን በዚህ ቀመር
ማስላት ከቻልን፣ በንጹህ ልቦናችን ፈጣሪ እውነትን ስለሚለግሰን ለምናስበው ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻለናል ማለት ነው።
በዚህ የሀሳብ ቀመራዊ አስተሳሰብ እየተመራን የማንጠራጠረው እውቀት ካገኘንና ጥያቄዎቻችንን ሁሉ መመለስ ከቻልን የእራስ ኅልውና አገኘን ማለት ነው። በአካባቢያችን ያሉትን ሁሉንም እየተጠራጠርንና እየጠየቅን በቀላሉ ስለ ህልውናቸው እርግጠኛ መሆን አንችልም፤ ነገር ግን አንድ መካድና መጠራጠር የማልችለው እውነት አለ፤ ይኸውም በአሁኑ ሰዓት እያሰብኩ መሆኑን ልቦናዬ እየነገረኝ ነው።
“እያሰብኩ ስለሆነ ኅልው ነኝ ማለት ነው” ይለናል ዴካርት።
ሁሉንም የቀደሙ እውቀቶችን እንዲፈትሻቸው የነገረው አንድ እርግጠኛ የሆነ ሳይንሳዊ እውቀት ፍለጋ ሲሆን፤ አንድ እርግጠኛ እውነት ካገኘ ሙሉ ፍልስፍና አድርጎ ሥጋና ደም እንደሚሰጠው እርግጠኛ ነበር፤ ዴካርት። ስለሆነም አሁን ልቦናው የሚነግረው እርግጠኛ እውቀት እያሰበ መሆኑን ሆኖ አገኘው።
"እኔ ግን ምንድን ነኝ?" ይላል እንደገና... የሚያስብ ቁስ ነኝ ማለት ነው አዎን፣ እያሰብኩ መሆኔን መካድ ስለማልችል፤ እኔ የማስብ "ነገር" ነኝ ማለት ነው። የማስበው በአእምሮዬ ነው፤ አእምሮ ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም ረቂቅ ነገር ነው፤ ስለሆነም አይበሰብስም፣ አይፈረከስም፣ አይሞትም ማለት ነው

ሆኖም አሁንም መልስ ያላገኘንለት ነገር አለ፤ እኔ ከየት መጣሁ? እናትና አባቶቼ ለእኔ መፈጠር ምክንያቶች እንጂ ፈጣሪዎቼ አይደሉምና።
የእራሳችን አስገኝዎች እኛው እራሳችን ልንሆን ደግሞ በፍጹም አንችልም። ስለሆነም ማሰብ እንድንችል አድርጎ የፈጠረን ፍጹም እና “ገባሬ ኩሉ” የሆነ ፈጣሪ መኖሩን በዚሁ እንረዳለን ማለት ነው፤ ይለናል ዴካርት
የፍጽምና ባህሪ ያለው ፈጣሪ ደግሞ ጎደሎና ሐሰት የሆነ ነገር/ሀሳብ እንድናስብ አይፈቅድም፤ ምክንያቱም ከባህሪው ጋር አይስማሙምና ማለት ነው።
እዚህ ዓለም ላይ ያሉ ቁስ አካላትም (በሰው ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ) እውነት ናቸው ማለት ነው የተምታታ ሀሳብ እንዲኖረኝ የሚያደርገኝ ሙሉ የክፋት አቅሙን አሟጥጦ የሚጠቀም ያ “አወናባጅ ዲያብሎስ” ነው እንጂ ፈጣሪ ሊሆን አይችልም የአወናባጁን ዲያብሎስ ምክር እየለየን ማሰብ ከቻልን፣ ወደ እርግጠኛ እውቀት የምናደርገው ጉዞ የተሳካ ይሆንልናል ማለት ነው።
ልዕለ መልካምነት ባህሪው የሆነ ፈጣሪ መኖሩን ማወቅ አለብን።
እዚህ ዓለም ላይ ያለው እውነት ስለመሆኑ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ፈጣሪ ፍጹም እና የመልካሞች ሁሉ መልካም በመሆኑ፣ ለኛም ግልጽ የሆነና የጠራ ሀሳብን ይለግሰናል፡፡
ዴካርት፤ ግልጽነት፣ ልዩነት እና አለመፋለስን እንደ ሒሳብ ቀመር፣ የአንድን ጉዳይ እውነተኝነት/እርግጠኝነት የምንመዝንባቸው አድርጎ ስለቀመራቸው በቤተሰቡ ስያሜ “የካርቴዚያን ዲበ አካል” ተብሎ ተሰይሞለታል
የአውሮፓዊያን የፍልስፍና አስተምህሮ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳቦች መልስ ለመስጠት መፍጨርጨሩ አልቀረም ... ፈላስፋው አማኝ ነኝ አሊያም ኢ-አማኒ ነኝ ቢልም፣ የቀደመው የአውሮፓ ፍልስፍና የሳይንስን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ግጭት፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ረቂቅነት ማስገንዘብ፤ ወይም ሳይንስ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያፈርሳት የሚከሰተውን ባዶነት መተንተን የሚመሳስሉ ሀሳቦች ያደሉበታል የዴካርት አካሄድም ከዚሁ የተለየ አይመስልም። የስህተቶች ሁሉ ምንጭ አወናባጁ ዲያብሎስ ነው ይለናልና!
“I will suppose therefore that ... rather some evil genius of the utmost power and cunning has employed all his energies in order to deceive me.”
በመጨረሻም የበረከትን አጭሬ ልጋብዛችሁ...☺️

በር መስኮት ዘግተህ
ቀዳዳዎችን ደፍነህ
የለኮስከው ሻማ፣
"በራ" "ጠፋ" ካለ
ጠርጥር...

ቤት ያፈራው ንፋስ ከጎጆህ እንዳለ!
በብዙዎች ተወዳጅነት ያተረፈው መቀመጫውን ራሺያ ያደረገው ቴሌግራም አዲስ ህግ አስተዋውቋል !

ከአንድ ሳምንት በኃላ ቴሌግራም ተግባራዊ አደርገዋለሁ በአለው አዲሱ ህግ መሰረት ከዋናው የTelegram መተግበሪያ ውጪ የሚገኙትን የቴሌግራም ሰርቨር የሚጠቀሙ Apps እንደሚዘጋ ገልጿል።

ከአንድ ሳምንት በኃላም እንደ Plus ፣Xgram Mobogram ፣ ninja gram ፣ Hulugram የመሳሰሉትን የቴሌግራም መተግበሪያወች አዲስ አካውንት መክፈት ሲፈልጉ እና Update ማድረግ ሲፈልጉ ወደ እነዚህ መተግበሪያዎች ኮድ አይላክም።

ስለሆነም በዋናው ቴሌግራም #Official App ብቻ ነው መጠቀም የሚቻለው በ 1 ሳምንት ጊዜ ውስጥም ኦፊሻል የቴሌግራም መተግበሪያ ከ PLAY STORE ዳውንሎድ በማድረግ Login ያድርጉ ብሏል።

ከ1 ሳምንት በኃላ ከዋናው የቴሌግራም መተግበሪያ ውጪ ሁሉም የቴሌግራም ሰርቨር የሚጠቀሙት መተግበሪያዎች ይዘጋሉ ቴሌግራም እንደ አሳወቀው የሚሆን ከሆነ ነገርግን Plusን ጨምሮ Hulugram ይህንን መረጃ እያስተባበሉ ይገኛሉ ! share share
"My life was in front of me, closed, ended, like a sack, and yet, everything in it was unfinished. I tried to judge her for a moment. I would have liked to be able to tell myself: it's a beautiful life. However, it could not be judged, it was only a sketch; I was wasting my time signing policies for eternity, I hadn't understood anything. I didn't regret anything: there were many things I could have regretted [...]; death had robbed them all of their charm."

(Jean-Paul Sartre, The Wall)