WENDE TUTORIAL
12.1K subscribers
351 photos
10 videos
357 files
300 links
For any Promotion dm 👉👉 @wende161721 👉History for Grade 12, New curriculum grade 12 history, grade 12 Geography, Grade 12 Economics in Amharic on Youtube
Download Telegram
WENDE TUTORIAL
ከፍተኛ ውጤት ! በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 591.6 ከ600 ተመዝግቧል። ተማሪው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ ተማሪ ነው። ከሴት ደግሞ 583 ከ600 ሲሆን ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
ከፍተኛ ውጤት !

በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 576.2 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ተመዝግቧል።

በሴት 569.1 ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
1🥰1
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)

- የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል።

- ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት።

- ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን  550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው።

- ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው።

- ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል።

#በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል)

1. አዲስ አበባ 32.3%
2. ሀረሪ 22.67%
3. አፋር 15.6%
4. አማራ 15.56%
5. ድሬዳዋ 11.29%
6. ትግራይ 11.2%
7. ኦሮሚያ 10.53%
8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23%
9. ሶማሌ 9.2%
10. ሲዳማ 6.95%
11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12%
12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82%
13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92%
14. ጋምቤላ 3.74%

በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል)

1. ኦሮሚያ 20,807 ተማሪዎች
2. አዲስ አበባ 18,646 ተማሪዎች
3. አማራ 15,225 ተማሪዎች
4. ትግራይ 3,146 ተማሪዎች
5. ደቡብ ኢትዮጵያ 3,011 ተማሪዎች
6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 2,800 ተማሪዎች
7. ሲዳማ 1,827 ተማሪዎች
8. ሶማሌ 1,616 ተማሪዎች
9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 835 ተማሪዎች
10. አፋር 705 ተማሪዎች
11. ሀረሪ 599 ተማሪዎች
12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 457 ተማሪዎች
13. ድሬዳዋ 410 ተማሪዎች
14. ጋምቤላ 280 ተማሪዎች

- ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው።

- ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል።

ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ?

• ኦሮሚያ 156
• አማራ 98
• ደቡብ ኢትዮጵያ 86
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69
• ትግራይ 48
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22
• አፋር 21
• ሲዳማ 16
• ሶማሌ 9
• ድሬዳዋ  5
• ሀረሪ 3
• ጋምቤላ 2
• አዲስ አበባ 1

- ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል።

በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ?

• ኦሮሚያ 37
• አዲስ አበባ 24
• አማራ 8
• ደቡብ ኢትዮጵያ 4
• ትግራይ 4
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3
• ሲዳማ 2
• አፋር 1
• ድሬዳዋ 1
• ሀረሪ 1
• ሶማሌ 1
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1

- በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም።

- የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ?

በተፈጥሮ ሳይንስ
🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ
🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ

በማህበራዊ ሳንይንስ
🥇 ከወንድ 👉  576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት

-  ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል።

- ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ።

- ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን።

- ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ።

- ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል።

📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
5
1,501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል ነገ ማክሰኞ በመላው ሀገራችን እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

የዘንድሮው በዓል የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮን መሠረት በማድረግ " የፍትሃዊው ነብይ " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ መርሐ-ግብሮች ይከበራል።

ለመላዉ የWENDE TUTORIAL የሙስሊም ማህበረሰብ መልካም በዓል!!!🙏🙏

@WENDETUTORIAL
@WENDETUTORIAL
2
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።

የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት መለቀቁን በመግለጽ ተማሪዎችና ወላጀችን የሚያደናግር ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

እስካሁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ የፈተናው ውጤት ይፋ ስለመደረጉ በይፋ አላሳወቀም።

ትክክለኛ የተረጋገጡ መረጃዎች ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ የሚገኙ በመሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ የተለያዩ አካላትና ገጾች ትጠነቀቁ ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ያስተላልፋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የፈተናው ውጤት ሰኞ ወይም እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።

ውጤት ሰኞ ዕለት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፈተናው ውጤት ይፋ ሲደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ በይፋ የሚያሳውቅ ሲሆን እንዴት ማየት እንደሚቻልም ተቋሙ ገለጻ ያወጣል። እኛም ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
🥰21🔥1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።

ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።

@Ethionews433 @Ethionews433
4
Hey Guys How are you?🥰

How was the Result?
#JalalGirma👏

የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591. 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

#ODA_SPECIAL_BOARDING_SCHOOL

@tikvahethiopia
WENDE TUTORIAL
#JalalGirma👏 የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591. 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። #ODA_SPECIAL_BOARDING_SCHOOL @tikvahethiopia
#HedasieZemenu👏

በአማራ ክልል፣ አዊ ብሄ/አስተዳደር እንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ህዳሴ ዘመኑ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 583.03 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግባለች።

#AgewMider #HedasieZemenu #የሀገርተስፋዎች👏

@tikvahethiopia
WENDE TUTORIAL
Photo
#RobelGetachew👏

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመላው ተፈታኞች ከፍተኛውን ሁለተኛ ውጤት ያመጣው በሀዲያ የሚገኘው የሊችጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪው ሮቤል ጌታቸው ሲሆን ያስመዘገበው ውጤት 590.08 ነው።

#Lichgogo #Hadiya #ከሀገርተስፋዎች👏

@tikvahethiopia
WENDE TUTORIAL
Photo
#SademAbdulaziz 👏

በማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወንዶች ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ ሳደም አብዱልአዚዝ ሲሆን ያስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 576.25 ነው። ሳደም በኦሮሚያ ክልል፣ የዶዶላ ኢፋቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።

#DodolaIfaBoruuBoardingSchool
#የሀገርተስፋዎች👏

@tikvahethiopia
WENDE TUTORIAL
#SademAbdulaziz 👏 በማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወንዶች ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ ሳደም አብዱልአዚዝ ሲሆን ያስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 576.25 ነው። ሳደም በኦሮሚያ ክልል፣ የዶዶላ ኢፋቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። #DodolaIfaBoruuBoardingSchool #የሀገርተስፋዎች👏 @tikvahethiopia
#MekdelawitSurafel👏

በማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሴቶች ከፍተኛውን ውጤት ያመጣችው መቅደላዊት ሱራፌል ስትሆን ያስመዘገበችው 569.17 ነው። መቅደላዊት ሱራፌል በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ሱፐር ሆሊ ሴቪየር ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።

#SuperHolySaviour #AddisAbaba #የሀገርተስፋዎች👏

@tikvahethiopia
📌 በ2018 ENTRANCE እና REMEDIAL ውጤት ያመጣችው ተማሪዎች ለFreshman ትምህርታችሁ የሚያግዛችሁ የPRIVATE class አዘጋጅተናል። እንደምታውቁት ጊቢ ስትገቡ

የምትማሩአቸው ትምህርቶች
ስርአቱ
ፈተናውና ASSIGNMENT
Grade አያያዝ እና አሰራር
መምህራን

እነዚህ ነገሮች ለናንተ አዲስ ናቸው። ስለዚህ እኛም እስከዛሬ እንደነበረን ቆይታ በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ እና ስለ Freshman ጥሩ ግንዛቤ ለመስጠት እነሆ እየጠበቅናችሁ ነው🥰

🥇የቀደመ ሁሌም አሸናፊ ነው🏆

📌ለመመዝገብ ዋጋው 👉300 ብር ሲሆን
👉 CBE= 1000475112664
👉Telebirr= 0967582833 ላይ
ከከፈሉ በኋላ SCREENSHOT አድርገው @wende161721 ላይ ይላኩልን 🥰
2
Forwarded from quality botton
 ለተማሪዎች ጠቃሚ መረጃዎችን፣ የትምህርት ምክሮችን እና አነቃቂ መልዕክቶችን የምታገኙበትን ምርጥ ቻናሎች ልጋብዛቹ 👇