ወግ ብቻ
18.8K subscribers
510 photos
11 videos
21 files
51 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

Creator @leul_mekonnen1
Download Telegram
ፍቅር እና ቁጥር

ስንግባባ ሰሞን እኔ መላመድን ለማምለጥ የምባትል ባተሌ ነበርኩ። የተጣመርኩት ባይኖርም ራሴን ብቻዬን እወደዋለሁ። የማልደራደርበት ማንነት ነበረኝ። ሌሎችን የማደንቅበትና የማከብርበት የማንነት መለኪያያዎችም ነበሩኝ።

እሱ ---- አላውቅም የሱን ፍላጎት........ ብቻ አላጣደፈኝም። የተለየ ፍላጎት እንዳለውም ሊያሳየኝ አልተፍጨረጨረም። የሰው ፍላጎት እና ሀሳብ ሲጫንብኝ እንደማልወድ ገብቶታል። ማባበሉ አጥንቶ የቀመረበት ነበር። ጆሮዬ ከአንዴም ሁለቴ ከድቶኛል እና በተቆለጳጰሰ የፍቅር ዓረፍተ ነገር የሚደነግጥ ልብ እንደሌለኝ አውቋል። ቀስ በቀስ ለፍፅምና የተጠጋ እሱነቱን ነው የጋተኝ። በገንዘብ ተተምነው ውድ የሆኑ ስጦታዎች እየገዛ አይደለም ያቀበጠኝ፤ በአንድ አንጎል የምናስብ እስኪመስለኝ ድረስ የሚያስፈልገኝን እና ለልቤ የቀረቡ ስጦታዎችን ነበር የሰጠኝ። ውደጂኝ አላለኝም። እንድወደው ምንም አስተዋፅኦ እንዳላደረገ ዓይነት፣ .....የቀን ተቀን እሱነቱን እየኖረ እንደሆነ ዓይነት ፣....... እኔን ለመማረክ የጨመረው ምናምኒት ትጋት እንደሌለ ፣.......... ለሃጬ እስኪዝረበረብ በሱሱ ለመተብተቤ ያበረከተው ምንም እንደሌለ ሁላ ......ከደሙ ነፃ ነኝ...... እኔ የእለት ተእለት እኔነቴን ነው የኖርኩት ዓይነት እጁን ተለቀለቀ።

የሰው ልጅ አዘቦታዊ ማንነት እንዴት እንዲህ እንከን አልባ ይሆናል ብዬ አልጠየቅኩም። በየእለቱ እየገለጠ ያስነበበኝን የማንነቱን ምሰሶዎች ሰብስቤ እሱ ነው ያልኩትን እሱን በልቤ ገነባሁ ፣ በአዕምሮዬ ሳልኩ። ለዚህ ማንነት እጅ ሰጠሁ።

እዚህ ጊዜ ላይ
ፍቅሩን ፣ ጊዜውን ፣ ጆሮውን ፣ ልቡን ፣ ገላውን ፣ትኩረቱን ያልሰጠኝ የለም። 100% እሱነቱን ያለስስት ነበር የሰጠኝ። እስክበስል ማገዶ እንደምፈጅ ገብቶታል። አልተጣደፈም። ከሞከኩኝ ኋላ እስክበሰብስ እንደምታሽ ገብቶታል።

ሱሴ የሆነ ጊዜ ላይ ....... ያለእርሱ ትንፋሽ እንደሚያጥረኝ የገባው ሰዓት ላይ .......
የሂሳብ ቀመሩን ይጫወት ጀመረ። ቀስ በቀስ ከመቶ እሱነቱ ይገምሰው ገባ። ፍቅሩንም ጊዜውንም ጆሮውኑም ልቡንም ገላውንም ትኩረቱንም በግማሽ ቦደሰው። 50% !! ልቤ የምትደገፈው ምርኩዝ ስታስስ የነጠቀኝን ትንሽ ይጨምርበታል። 75%!! ........ ጨዋታው ይሄ ነው። 100 እንደነበር ይጠፋኛል። ካጣሁት ግማሽ ይልቅ የተጨመረልኝ እሩብ ያስቦርቀኛል። ልቤ መልሳ እሱን ማምለኳን ትቀጥላለች። መልሶ ከ75% ወደ 25% ሲወርድብኝ የአየር ቧንቧዬ የጠበበ ያህል ደረቴን ያፍነኛል። መልሶ 25% እሱን ይጨምርልኛል። ግማሽ እሱነቱን እንደነሳኝ አላላዝንም። የጨመረልኝ ያስደንሰኛል።

አንድ ቀን ገላውን ለሌላ ሴት አዋሰብኝ። እዚህ ጊዜ ላይ ከሙሉ እሱነቱ 5% ፐርሰንቱን እንኳን አልሰጠኝም። በብዙ ትዕግስት እና ጥበብ ውስጤ የገነባው እሱነቱ ግን አሁንም አልተገመሰም። ወይም በቀላሉ እንዳይፈርስ አድርጎ ከዓለት ገንብቶታል። ወይም ማመን አልፈልግም። ፍንክች አይልም።

አልካደኝም። በእንባ ታጅቦ ይቅርታ ጠየቀኝ። ይቅርታውን በአግቢኝ ጥያቄ እና ቀለበት አጀበው። የምለው ገባችሁ? ከአምስት 25% ነዳው አይደል? ያደረገውን ሳይሆን ያደረገልኝን እያሰብኩ ተፍለቀለቅኩ። ስለሚወደኝ አይደል አዳራሽ ሙሉ ህዝብ ጠርቶ ፕሮፖዝ ያደረገኝ?

ሶስት ቀን የት እንዳለ እንኳን ሳይነግረኝ ዘግቶኝ ይከርምና በአራተኛው ቀን ለእናቴ ከክርስታል የተሰራ የአበባ ማስቀመጫ ገዝቶ ከች ይላል። ሶስቱን ቀን ረስቼ ለእናቴ ላሳያት ፍቅር እሸነፋለሁ።

እሱ ከሚያሳየኝ የዘቀጠ ማንነት ይልቅ በልቤ ያነገስኩት ማነነት ላይ ሙጭጭ አልኩ። በሂሳብ ቀመሩ ተወናበድኩ።

የእሱን ስዕል ከልቤ ከማፍረሴ ብዙ ቀን ቀድሞ እኔ ፈረስኩ። የእሱን እውነተኛ ማንነት አምኜ ከመቀበሌ ከብዙ ቀናት ቀድሞ የራሴ ማንነት ጠፋኝ።

መላመድን ላመልጠው የምሸመጥጥ አትሌት አልነበርኩ? እሱ ከልቤም ከህይወቴም ሲወጣ ለመሮጥም ለማምለጥም ለማሰብም የተረፈ አቅም አልነበረኝም.
** ** *****

By meri feleke


@wegoch
@wegoch
@paappii
"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።"

ቴክስት ገባልኝ

ማሂ ናት
"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ " የሚለው ብቻ በጉልህ ታየኝ ።

በቀደም "አብረኸኝ ሁን በጣም ...በጣም ከፍቶኛል" ብላኝ ያለሁበትን ጠቆምኳት ያለሁበት መጣች ። እየጠጣን፣ ትንሽ ፈገግ ቁዝምም እያለች፣ ነፍ ነገር እየቀደድን እየተጫወትን አመሸን ።

ወደ ቤቷ መሄድ እንደማትፈልግ ገባኝ ፣ ራይድ ደወልኩ፣ መነሻ እና መድረሻ ተናገርኩ ቤቴ ወሰደን ።

ቆሎ ከኮመዲኖ፣ ከፍሪጅ ቢራ አቀርብኩላት ። ቆሎ እየቆረጠምን፣ ቢራ እየጠጣን ቢጃማ አውጥቼ ሰጠኋት እና ሱቅ እቃ ገዝቼ መጣው ብዬ ወጣሁ።

ትንሽ የማልገዛውን እቃ እየጠየኩ ቆይቼ ተመለስኩ

ቢጃማዬን ለብሳ ቆየችኝ ።

ቢጃማዬን ገላዋን አስገብታበት አሳምራዋለች ። መሞናደሏን ቢጃማዬ አሳበቀባት ። አይኗ፣ ሁኔታዋ፣ አወራሯ ሁሉ ነገሯ መሞናደሏን ከልሎታል ።

ሰው ስሜትን ሳያነብ ስሜታዊ ከሆነ ምኑ ጋር ነው ስውነቱ ?

ትንሽ እንደተጨዋወትን የአልጋዬን አንሶላ ገልጠን ገባን ። አቀፍኳት ሳቅፋት ሰውነቷን ኩምትር እንዳደረገች ነበር ።

መሳቀቋ ገብቶኛል፤ ግን እንዳልገባኝ ሆኜ ግንባሯን ሳምኩት።
አሳሳሜ 'አትሳቀቂ ይሄው ትከሻዬ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር ግንባሯን በታላቅነት በአለሁልሽ ነው የሳምኳት።

መልዕክቴ በትክክል ይድረስ አይደረሳት አላወኩም ።

ሲያጉረመርም የነበረው ዶፍ ዝናብ ዘነበ
አቀፍኳት ፣ በረዳት ወይ አመነችኝ መሰል በደንብ ጥግት ብላብኝ ታቀፈች ።

"ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ?፣ የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ። እያጡ ማዘን እኮ ደከመኝ።
እንደ እናቶች ተረግሜ ፣ተደግሞብኝ ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን? ለማለት ጫፍ ላይ እየደረስኩ ነው። "

በለሆሳስ ስታወራ በጨለማው ውስጥ ኩልል ያለ እንባ ያፈሰሰች መስሎኛል ። ይሄን የቅሬታ ድምፅ ከእንባ ውጪ መተንፈስ የሚቻል አልመሰለኝም ።

"አይዞሽ ሁሉም በግዜው ይስተካከላል። ሳንካ የሆነብሽ ሁሉ ወደ ጥሩ ይለወጣል ። ትላንት የከበደን ስንት ነገር ቀሎልን የለ?"

የበለጠ አቀፍኳት ፤ ደረቴ ላይ ተኛች ።

የሆነች ነፍስ አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ። ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ። ስጋዬን ችላ ማለት የምችል አይነት ስሜት ተሰማኝ ደረቴ ላይ እንደተኛች በደስታ ፈገግ አልኩ ።

እንዳቀፍኳት እንደታቀፈችኝ ለሊት ላይ ነቃሁ፣ አየኋት እንቅልፍ ውስጥ ጭልጥ ብላለች። አምናኝ ባዶ ክፍል ራሷን ገላዬ ላይ ጥላ ተኝታለች ። ደስስ እንዳለኝ ተኛሁ።

ጠዋት ቁርስ በላን እና ሄደች። አስራ እንድ ሰአት ከሃያ ቴክስት ላከችልኝ :

"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።
መሄጃ አጥቼ መሄጃ ስለሆንከኝ አመሰግናለሁ።"

ቴክስቱን እንዳየሁት አለቀስኩ ። ለመዋሰብ ታግያት ቢሆን ኖሮ እንዴት ነበር የሚሰማት? ብዬ አሰብኩ።

አባቴ እግሩ በተቆረጠበት ሰዓት ፣
ስራ በተባረረበት ሰዓት፣
ንብረቱን በተቀማበት ሰዓት፣

የዘመዶቹን የጓደኞቹን የብዙ ሰው ስም እየጠራ "ብቻዬን ተውኝ: ብቻዬን ተውኝ" ብቻውን መተውን እየተናዘዘ በዛው አእምሮ እንደታወከ ስላስታወሰቺኝ ይሆን

ብቻ መተው ማለት ትርጉሙ ገብቶኝ ይሆን ?
ከብዙ ግዜ በኃላ ቃሉን ስለሰማሁት ይሆን?
የአባቴ ሁኔታ አይኔ ላይ ስለመጣብኝ ይሆን?

ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ የሚለው 'message' አስለቀሰኝ ።

ጌታዬን ወደ ሰማይ አንጋጥጬ አመሰገንኩት ።

"መሸሸጊያ ያጣች ድክም ያላትን ነፍስ : በኔ ምክንያት የበለጠ እንዳታዝን ስላደረከኝ አመሰግናለሁ ጌታዬ።"

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም!

'አጅሬ' የምለው...'ጊዜዬ' የሚለኝ አንድ ጌታን የተቀበለ የከንፈር ወዳጅ ነበረኝ።አብሮነታችን ዕድሜ ላይኖረው...ማህተቤን ላልፈታ...ማህተብ ላያስር ነገር...ከማይካደው እውነታ በላይ ብዙ ነገሩ ገዝቶኝ አብሬው መጓዝ ጀመርኩ።ተገኝቼ 'ማላውቅበት ቦታ ከሱ ጋር ተገኘሁ...ስጋ እየፆምኩ ስጋ የበላ እሱን ለመሳም አልግደረደርም ነበር።አንገቱ እስኪዥጎረጎር መጥጬው 'ከጠየቁህ ጊዜ ናት በል' ስል ግዳይ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር።ያውም በሁዳዴ...ያውም በአቢዩ!
ያወቅሁትኝ ሰሞን የሴት ግሳንግሴን ገፍፌ ጥዬ...እኔው ደዋይ...እኔው መልዕክት ላኪ...እኔው አጥብቆ ጠያቂ እየሆንኩ በእናትነት እና በሚስትነት መሃል የሚቀላውጥ ማንነቴን ጋትኩት።ሰከረ...ስካሩ ዕድሜ ገዛ።
በሱ ካስተናገድኳቸው እብደቶቼ ሁሉ የማልረሳው የlipstickኬን ነገር ነው።አንድ ዕለት አክስቴን ልጎበኝ በሄድኩበት lipstickኬ ማለቁ ትዝ ብሎኝ የአክስቴን ልጅ ግዥልኝ ብዬ መላክ...ዘምናኒት ጁስ ጁስ የሚል lipstick ገዝታ መምጣት...ልቀባው ወደ አፌ ሳስጠጋው የጠረኑ ማማር...ተቀብቼ ስቀምሰው የጣዕሙ ነገር...ቴዲ "ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር..."ያለው አምለሰት ይኸን መሳይ ተቀብታ ብትጠጋው ነው ብዬ እንድደመድም አደረገኝ። 'ቴዲ አንጋጦ ባየው ከንፈር እንዲህ አጉል ከሆነ አጅሬ ቁልቁል አይቶኝማ እንደምን አይስት!'የሚል ሔዋናዊ ሀሳብ ብልጭ አለብኝና ያንን እንጆሪ እንጆሪ የሚል lipstick አልጋዬ ላይ አስቀምጬ ኩሽና ገባሁ።ከኩሽና ስመለስ እማይበጃችሁ ይድረቅና ድርርርርርቅ ብዬ ቀረሁ...አንድ ከየት እንደመጣ የማላውቀው(በኋላ ሳጣራ የአክስቴ ሰራተኛ ልጅ) በግምት 3 አመት የሚሆነው ህፃን lipstickኬን ይዞ ይመጠምጣል።በድንጋጤ ነጥቄ ስመለከተው እንኳን የሚቀባ የሚታይ የለውም።ህፃኑን አየሁት...የጠባውን ያጣጥማል...'ደሜ ፈላ' ብል ደሜ ራሱ ይታዘበኛል...ተንተከተከ...ተፈናጥሮ ሰው እስኪጠብስ! የሆነ ስላችሁ የጨረሳችሁት ሁነት...በምናባችሁ እንዳማረ ተጀምሮ እንዳማረ የሚጠናቀቅ ሁነት...ሊሆን እንደማይችል ስታውቁት ልባችሁ ይወርድ የለ?እኔ ሁለመናዬ ነው የወረደው...ከእንጥሌ ጀምሮ... ልጁን በልቤ ረገምኩት...
'ከንፈርክን ስማ 'እንደ ወንድሜ ነው 'ማይህ ' ትበልህ'...'አልጋ አስይዛ ፔሬድ ላይ ነኝ ትበልህ!'... 'ፔሬዱ ሲሄድ 'ትንሽ ነው' ትበልህ' ብዬው ሳበቃ
"ቤቢ አሜን በል" አልኩት።
"አሜን"...ኤታባቱ!

እናም እኔ ወለተ ማርያም...የአብማይቱ ማርያም ልጅ...የማርቆሷ ሎጋ...ጠላታችሁን የሎስ ያክንፈውና አስተካክሎ 'ነገ' እንኳን ማለት ከማይችል ደቡቤ ጋር ከነፍኩ።ዘረኛ ነበርኩ...እልልልም ያልኩ ዘረኛ!ወንድ ጎጃሜ ካልሆነ ወንድ የማይመስለኝ!'ሲያናድደኝ የምሰድበው ስድብ እንኳን ካልገባው ምን ላደርገው ነው?' ብዬ የምራቀቂቱ...
''መቼ ይመችሃል?'' ስለው
"ነጌ"
"እንዴት አርገህ አበጃጀኸው?" ስለው
"እንደዚህ እንደዚህ 'አርግቼ' "
"እኔ ኦርቶዶክስ...አንተ ጴንጤ...በምን ስሌት አብረን እንሁን?"ስለው
" 'እምነት...ተስፋ...ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ፤ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል' ነው መፅሐፍ ቅዱስ 'የምለው' " ከሚለኝ አንድ ተላሰስ ጋር...ወደቅሁ።
መላመዳችን ሲበረታ...ቅርርባችን ልክ ሲያጣ ጥያቄዎቻችንን ሽሽት ገባን።መሄድ ብቻ!እስከሆነ ቀይ መስመር ድረስ...በድፍረት ጥያቄዎቻችንን ስር ድረስ የማንጠያየቀው የማይቀረውን መለያየት ያራቅን መስሎን ነበር።ጠንካራ አማኝም ባልሆን ፈሪ ነኝ...ነፍስ አባቴ ዘንድ ስከንፍ ሄጄ 'መናፍቅ ወድጄ ልቤ ጠፋ' አልኳቸው።
"ወለቴ"
"ኧይ አባ"
"እምን ድረስ ቀረብሽው?"
"ሲሉኝ?"
"ተመተቃቀፍ አለፋችሁ?" ሲሉኝ መሽኮርመም
"ወለቴ...አደራሽን አረከሰኝ እንዳትይኝ"
"ይፍቱኝ አባ"
"አዪዪዪዪዪ....አይ ወለቴ...ምነው?ህጉን ስታውቂው?" አሉኝ...የምፈታበት መፅሐፍ ተነበበ...ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጠመቁኝ።
ህጉ 'ከአህዛብ አትጠጉ' ይላል...እንኳን አንሶላ መጋፈፍ...ማዕድ መካፈልን ያወግዛል...ግን ከህግ በላይ የሚገዛ፣ከውግዘት በላይ የሚያስር መሳሳብ ሲመጣስ?ምኔንም መሰሰት እስካልችል ከተሸነፍኩስ?አጅሬ አንዴ የሆነ መጣጥፍ ሲያነብልኝ "ሰው ከፍቅር የሚቆራረጠው ሰጥቶ መቀበልን ሲሻ ነው...የፍቅር ምክንያቱም ውጤቱም መስጠት ነው...ስለፍቅር የሚደረጉ ዝቅታዎች ሁሉ ከየትኛውም ከፍታ ይልቃሉ...ፍቅር ውስጥ መቀበልን የሚሻ እሱ ቀሽም ነው..." ብሎኝ ነበር።ያለስስት ስለሰጠሁት ሁሉ ደስተኛ ነኝ...አይደፈርን ደፍሬ፣አይተላለፉትን ተላልፌም...ይናፍቀኛል።
በስተ መጨረሻ...ተመርቆ ከጊቢ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው
"ተጠመቅና ከመሄድህ በፊት እንጋባ" ብዬ እስከምመረቅ ያሉትን ሶስት አመታት በዕምነት ልጠብቀው መዘጋጀቴን ነገርኩት...'ያዲያቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም' እንዲሉ
"አንቺ ወደኔ እንዳትመጪ ምንድነው 'ሚያግድሽ? ቤተሰብ ነው?''አለኝ።እርግጥ ነው ቤተሰቦቼ የሚያማልደውን እየሱስ እየመገቡ አላሳደጉኝም...ከነሱ በላይ ግን...ነጌ ምጤ ሲመጣ ማን ሊያዋልደኝ?ማን ጭንቄን ሊያረግብ?የሱ ቀበቶ በቂ አልነበረምና ልቤን ዳር እስከዳር እየከረሰሰኝ...ዘለዓለም የሚመስል ፅልመት እየወረሰኝ...ሸኘሁት...ማህተብ ፈቶ ቀለበት ማሰር የለም።

ዘማርቆስ
29/08/16

By @gize_yayeh

@wegoch
@wegoch
@paappii
የሙሉ ጊዜ ደራሲት
(ማዕዶት ዘማርቆስ)

የሰው ልጅ ያለስራ ይኖር ዘንድ ይቻለዋልን?የሰማይ አእዋፋትስ በክንፎቻቸው ዛብረው ይበሉትን ከሰበሰቡ ይልቁንም ከነሱ በላይ የሆነው ሰው እጆቹን ለስራ እንዲዘረጋ አታውቁም?
ግን የሰው ልጅ አያ መሌን የመሰለ ሰው በዙሪያው እያለ እንዴት ሰርቶ መብላት ይቻለዋል?እሳቸው ጡረተኛ ሆኑና እኛ የምንሰራው ሁሉ ውጉዝ ነው ማለት ነው?ወይስ ከሳቸው ጋር ላለመጎራበጥ የግድ ዘመቻ ሄደን ቀኝ ጆሮአችን ስር መመታት አለብን?እኔን የሚገርመኝ ከግራ ጆሯቸው አንዲት ነገር አለማምለጧ!
ለአያ መሌ የዘመኑ ሰው የሚሰራው ስራ ሁሉ ከፈጣሪ ያጣላል።ነጋዴው ሁሉ በውሸት እየማለ ያተርፋል...የመንግስት ሰራተኛው ሁሉ ድሀውን ያጉላላል...ሹፌሩ ሁሉ ሴሰኛ ነው...ሀኪሙ ሁሉ አዋቂ መስሎ አላዋቂ ነው...የጀበና ቡና የምትሸጢቱ ሁሉ ሸሌ ናት...ከደሙ የፀዳው ቀኝ ጆሮውን ተመቶ ቤት የተቀመጠ ጡረተኛ ወታደር ብቻ ነው።
እሳቸው ቤት ተከራይቼ የገባሁት ይሁዳ ጌታውን ስሞ የሸጠ ቀን ይመስለኛል።እስከ ትንሳኤ መታገስ አቅቶኝ ዘመኔ ሁሉ ረቡዕ ሆነብኝ።ብቸኛዋ ተማራሪ እኔ አለመሆኔ ነው እስከዛሬም ያቆየኝ።ዘካርያስ እና ከማል የተከራየኋትን ጠባብ አንዲት ክፍል ቤት ተጎራብተው የሚኖሩ ምርጥ ወዳጆቼ ናቸው።ዘካርያስ አንድ የብስኩት ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ላብ አደር ባለትዳር ነው።ከማል ደግሞ የኮምፒውተር ባለሙያ ወንደላጤ...እኔ መሃል ያለሁቱ ጊዜ ደግሞ ያው ጊዜ ነኝ...ደራሲ ነኝ እላለሁ።
"የሙሉ ጊዜ ስራሽ ምንድነው?"ሲሉኝ ደሜ ቱግ ብሎ "ደራሲ!"እላለሁ።"ማለ...ቴ ጎን ለጎን የምትሰሪው ሌላ ስራ የለም?"ይለኛል ሌላው።'ጎንህ ይነደልና ድርሰት ስራ አይደለም?'ልል ያምረኝና መልሼ 'መተው ነገሬን ከተተው' ብዬ ዝም እላለሁ።
ታች አምና ለገና መታወቂያዬን ላሳድስ ሄጄ አዳሽ ተብየው
"ስራ..."ሲለኝ
"ደራሲ!" አልኩት ጡት አልባ ደረቴን ነፋ አድርጌ።
"ሌላ የምትሰሪው ተጨማሪ ስራ የለም?"
"ድርሰት ስራ አይደለም እንዴ?"
"አ...ይ ጎን ለጎን የምትሰሪው ካለ ብዬ ነው"
"እእእእእ....ጎን ለጎን ማለትህ ነው?"
"እ..."
"ሸማኔ!"
"ኧ?"
"ጎን ለጎን እሸምናለሁ...'ቢዝነስ ካርድ' ልስጥህ?"
"አ...ይ አመሰግናለሁ"አለና ጤነኝነቴን እየተጠራጠረ በድብንድብ ፊቱ ገላምጦኝ መዝገቤ ላይ ማህተሙን አሳረፈ።ይሄ የሸማኔ ልጅ!I love ሸማኔ!
ከአከራዬ ከአያ መሌ ጋርም የገጠመኝ ይኸው ነው።ቤታቸውን አይቼው ወድጄው ዋጋ ሁላ ተስማምተን ስናበቃ መታወቂያዬን ተቀብለው እየተንተባተቡ አነበቡና
"ስራሽ ድርስ ነው የሚለው?ነፍሰጡር ነሽ?"አሉኝ 'ችቦ አይሞላም' ወገቤን በግርታ እየቃኙ።ደራሽ በጠረጋቸው!
"አይ...ደራሲ ነው የሚለው...ግጥሞችና ታሪኮችን እፅፋለሁ...ፀሃፊ ነኝ"
"ፅፈሽስ?"
"አሳትሜ እሸጠዋለሁ"...አልተዋጠላቸውም...
"አልፎ አልፎ ደግሞ መድረኮች ላይ እየተከፈለኝ ፅሁፎቼን አቀርባለሁ"...ክፉም ደግም ሳይናገሩ መታወቂያዬን ሰጡኝና ጎበጥ ጎበጥ እያሉ ወደቤታቸው ገቡ።
በነጋታው ጧት ለማኝ እንትን ሳይል መጡና በሬን ቆፈቆፉ።ቤቴ በወረቀት እንደተዝረከረከ እየተጨናበስኩ ተነስቼ ከፈትኩላቸው።ዙሪያዬን በ 'የማነሽ መተታም' አስተያየት ቃኙና
"የስራ ቦታሽን ብትጠቁሚኝ ብየ ነው"አሉኝ።ለምንም እንዴትም ሳልል ለሳምንት ቀጠሮ ሰጥቻቸው ከወር አንዴ ወደምሳተፍበት የጥበብ ምሽት VIP አድርጌ ወሰድኳቸው።
ጓዶቼ የዛን ቀን የነካቸውን እንጃ ፋሲካ ፋሲካ የሚል ግጥም አብዝተው ነበር።መድረኩ እንደተከፈተ ለወትሮው ሽለላና ቀረርቶ ከአፉ የማይጠፋው ያሬድ "ጡትሽን ያየሁ 'ለት" የሚል ሁለት ገፅ ግጥም አነበበ።አናውቀውምና ነው?!የናቱን ጡት እንኳ 6 ወር አልጠባም'ኮ!እንደው ደርሶ ወግ ይድረሰኝ የሚል ሰው ያበሽቀኛል!ቀጥላ ለሌላው ጊዜ "ኢትዮጵያ" የሚለውን ቃል በጥብጠው የጋቷት የምትመስለው ዙፋን "ድንግል ምናባቱ" የሚል መነባነብ አቀረበች።ቀጥሎ ቢንያም ድምፁን በሚችለው ልክ አሳምሮ "ያዝ እጇን...ዝጋ ደጇን...ሳም ጉንጯን..."ብሎ ወረደ።ይሄ እርጉም አዝማሪ!ባለፈው ወር'ኮ "አጥንቴም ይከስከስ" ሲል ነበር።ወይኔ!በየመሃሉ አያ መሌን ሳያቸው መዳፋቸው ላይ አገጫቸውን ተክለው በሌላኛው እጃቸው በከዘራቸው ወለሉን እየቀበቀቡ በሆዳቸው 'ወይ ወላድ!' ሲሉ ሰማኋቸው።የኔን "ቀበቶውን ፈታሁት" የሚለውን ወግ ቢሰሙ እመር ብለው ተነስተው በቁንጥጫ እንደሚያልመዘምዙኝ ያለ ነቢይ ፍንትው ብሎ ታየኝና ቀስ ብዬ ይዣቸው ወጣሁ።መሽቶ ስለነበር ብለው ይሁን የሚሰድቡኝ ግራ ገብቷቸው ይሁን እንጃ ማታውን ምንም አላሉኝም።
ጧት ወረቀቶቼን ሰብስቤ ልወጣ ስል በረንዳቸው ላይ ተፎልለው "ጊዜወርቅ" አሉኝ።
"አያ መሌ ደኅና አደሩ?"
"አይለቅበት ለመድሃኔዔለም!...ምነው ማታ መድረኩ ላይ ሳላይሽ?"
"ው...ውይ አያ መሌ የፃፍኩትን'ኮ ረስቸው ሄጄ..."
"ነው?"
"እ...እንደው ዝንጉ ነኝ ሲፈጥረኝ" አልኳቸው።ቅማል የበላቸው ይመስል ጉያቸው ስር ከቁፋሮ መለስ ያለ ዘመቻ አካሄዱና አንድ ሲዲ አውጥተው
"ይኸንንስ አልረሳሽውም?"አሉኝ።እማይበጃችሁ ይድረቅና ድርርርርቅ ብዬ ቀረሁ!ያ ሰላቢ እያሱ ለፅሁፍሽ ይረዳሻል ብሎ የዛሬ ሳምንት የሰጠኝ የፈረንሳይ ፊልም ነው።ሌላው ይቅር...ምናለ አይቼው ቢሆን?በቃ የምናቤ እስረኛ ሊያረጉኝ ነው።ቢበዛ french kiss ቢኖረው ነው...ባስ ካለ ቢላፉና ቢተሻሹ ነው...እንደው ይሉኝታ ካጡ እሱ ቀሚሷን ቢገልብ ነው (ያንንም ለብሳ ከሆነ)...እኔን ከቤት ማስባረር ከፈለገች እግሯን ልትከፍተው ትችላለች...አናቷ ይከፈት!
"ጊዜወርቅ" ብለው ከምናቤ መንጥቀው አላቀቁኝ።
"አይከፈትም!"አልኩ በደመነፍስ ።
"ምኑ?"
"እ...ድንበራችን ለጠላት አይከፈትም!"
"ሆሆሆይ!...በይ እንኪ ከጥራጊው ጋር አውጥተሽ ጥለሽው እመቤት ናት አግኝታ ያስገባችው የጠቀመ እንደሁ ብላ..."ሲሉኝ ቅዱስ ሚካኤል ከገነት የጠራኝ ነው የመሰለኝ።ተቀብያቸው ልሄድ አልኩና ...ያው የነገር ማግኔት አይደለሁ?ዘወር ብዬ
"አያ መሌ..."አልኳቸው።
"አቤት"
"የማታውን ወደዱት?"
"እኒያ ሁላ እንዳንች ደራሲ ናቸው?
"አ...አዎ ፀሃፊዎች ናቸው"
" 'የጡቷ ስር ሙቀት እንደሳት እንደሳት
ክኒና ግዙልኝ ገደለኝ ትኩሳት' ያለውም?" ያሬድ ውጋት ይረድህ! ሰው እንዴት በግራ ጆሮው ሰምቶ እንዲህ ይሸመድዳል በጣድቁ?
"እ...አዎ ነው"አልኩ ምንተ ሀፍረቴን።
"እህምምምም...'እሳት ነው ብላቸው ቅቤ እየቀቡኝ
እስተነ ድንግሌ ንስሃ አስገቡኝ' ያለችቱም?"አሉኝ።
አይ ዙፋን!ዙፋንሽን አፈር ይነቅንቀው!እግራቸው ስር የተቀመጠችዋን ድመት አይቼ 'ይቺ ድመት 'ሚያው' ሳትል ሶስት ጊዜ ልካዳት ይሆን?'ብዬ ባስብም በፍርድ ቀን ታስጠይቀኛለችና
"አ...አዎ..." አልኩ።
"እዚህ ግቢ አይናቸውን እንዳላይ አደራ" አሉኝ ማስጠንቀቂያም ልመናም በሚመስል ቃና።ኧረ እንኳን አይናቸው ሊታይ ስልካቸውም አይመለስም።
ዋል አደር ስንል ግን ማን ወሬውን እንደሚያቀብላቸው እንጃ
"ደሞ ትናንት እዛ እመድረኩ ላይ ወጠሽ 'መንግስትን እንገልብጥ' ብለሻል አሉ"...
"ዛሬ ደሞ ያች የበቀደሚቱ ጋለሞታ 'አባይን ተሻግሮ አባይ አለ ወይ
እንደ እህል እንደ ውሃ እ*ስ ይጦ'ማል ወይ' አለች አሉ"...
"ሰልስትና 'ለታ ደሞ ያ አዝማሪ 'ጉራ ብቻ' ብሎ ዘፍኖ ከንቲባው እኔን ነው ብሎ ይፎገላል አሉ"...
አሉ...አሉ...አሉ...አሉ...ምርርርርርርርርር ሲለኝ ጨርቄን ማቄን ሳልል ልወጣ ያምረኝና...ትዝዝዝ ሲለኝ ለካ ከዘካርያስ ፍቅር ይዞኛል።ያች አራስ ሚስቱ ደግሞ ምናባቷ ነው ሳህኔን የማትመልሰው?
.
.
.
.
.
ማዕዶት ዘማርቆስ
ታህሳስ 2016 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሲምሉ ሁሉንም ቃላት እርግጥ አድርገው 'ማርያምን' እያሉ ነው ።

እማማ እቴነሽ ነው የምንላቸው ። ወፍራም ናቸው ሽንሽን ቀሚስ ነው የሚያደርጉት፣ ወገባቸው ላይ መቀነት አይጠፋም ። ቀይ ናቸው አንገታቸው ላይ ንቅሳት አለ ።

ባለሙያ ናቸው ። ሰላምተኛ ናቸው ።
በየድግስ ቤቱ ወጥ ይሰራሉ ። አይሞላላቸውም ታላቅ ወንድሜን መዳኒት ግዛልኝ ሲሉ አስታውሳለሁ ።

አንድ ቀን ልጃቸው ታስሮ ነበረ ከወር እስር በኃላ ለመፈታት የገንዘብ ዋስ ሲባል ነጠላ አንጥፈው ሲለምኑ ጎረቤት ሲያስቸግሩ አስታውሳለሁ

እማማ እቴነሽ ሃለፎም የሚባሉ ጎረቤት ነበሩአቸው ። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ተባረሩ። ሙሉ ግቢያቸውን ለእማማ እቴነሽ በአደራ አስረክበው ኤርትራ ገቡ ።

በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሃል እርቅ ሲደረግ እማማ ሃለፎም መጡ ።

የሃያ አንድ አመት ያከራየሁት ኪራይ ብለው በየወሩ ያፃፉትን መዝገቡ ጋር አስደምረው ሰጧቸው

ለሳቸው አደራ ማለት

በልጅ ፍቅር ፣ በጤና መታወክ ፣በድህነት፣ የግዜ ብዛት የማይፈትነው ፣ ቢፈትነውም የማያሸንፈው ነበር ።

ከዛ ግዜ በኃላ የአደራ ስሙ እና ትርጉሙ እማማ እቴነሽን ይመስለኛል::

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
ልገድልላት ስነሳ ትሞታለች!?
(ዘማርቆስ)

እርሜን ከቤቴ ስወጣ የሚያበሳጨኝ አላጣም...ከታክሲ ስወርድ ጠብቀው በልመና ልቤን ከሚጠቡኝ ህፃናት አንስቶ ከተማው ሁለመናው ይደብረኛል።ዱካኩን ለማስታገስ የጀበና ቡና ልከደም ብዬ ወደ ሙሉ ጠጋ ስል ያለወትሮዋ የሴት አቀማመጧን ዘንግታ መሀል ለመሃል የተተረተረ ቀይ የውስጥ ሱሪዋን በነፃ ታስጎበኘን ጀመር።ቀይ ውስጥ ሱሪዋን አልፎ ሌላ የሆነ ቀይ ነገር...ዙሪያውን የጠቆረ...

"ሙሉ!" አለ አስመላሽ ከሰጠመችበት የሀሳብ ውቅያኖስ መንጥቆ በሚያወጣ መንጠቆ ድምፅ...ዘወር አለች...ዘወር ብቻ...ከኪሱ ድፍን ሁለት መቶ ብር አውጥቶ
"ደኅነኛ ፓንት ግዥበት" ብሎ ወደ ረከቦቱ ወረወረው።እመር ብላ ተነሳችና የተጣደውን ጀበናዋን ከመቅፅበት አቀባብላ ሙሉውን ቡና አስመላሽ ግንባር ላይ ቀዳችው። የሙሉ ጀበና ከግርማው ቅንጣት ሳይተርፈው...ከድምፁ ለትውስታ ጥቂት ሳይቀረው...እንደ አንዳንዱ ሰው ልብ በሰከንድ ንክትክት አለ። ማነው ሰው ሸክላ ነው ያለው?ሸክላ ሸክላን ይሰብራል?
አስመላሽስ ምን አፉን አስከፈተው?ብሩን ከሰጣት እሷ መግዛቱ አይጠፋት...ይሄ የሰው ግም!
የሆነው ሆኖ አስመላሽ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሙሉ ምርር እያላት እንዲህ አለችኝ...
"እንደው በሆነልኝና ፍሬውን ቆርጨ ለውሻ በሰጠሁት ይኸ ቁርባ!"
"ኧረ ስለወንድ ልጅ!" አልኩ ቅፍፍ ብሎኝ።
"ምናባቱ!እየዞረ መልከፍከፉ ነው የሚቀርበት ይኸ አንከሊስ!"
"ቆይ ምንድነው ያደረገሽ?ቅድም የተናገረው ብቻ ነው እንዲህ ያበሳጨሽ?" አልኳት
"አይደለም"
"ታዲያ?"
"ኧረ ጉዱ ብዙ ነው ግዝሽ"
"ግዴለም ልስማው"
"በሜዳ አረገዝኩ ግዝሽ"
ስትለኝ ማማተብ ቀረሽ ድንጋጤ ልቤን ሰነጠቀው...ሙሉ ናታ...ሙሉ'ኮ ሙሉ ናት!ሰርቶ መከበርን፣ለሰው መኖርን፣ተደርጎላት አይደለም አድርጋ ማመስገንን፣በዚህ ጩኸታም ከተማ ዝምምም ብሎ መኖርን የተማርንባት መጽሐፋችን!ሙሉም ሳታገባ ታረግዛለች?ማናባቱ ነው ሙሉን ያለ ወግ ለመተኛት የሚደፍረው?መጽሐፋችንን በቆሻሻ እጁ የገለጠብን ማነው?

"ወድጄ አይደለም'ኮ" ስትለኝ
"ተይ ሙሉ...መቸስ ተደፍሬ ነው አትይኝም" አልኳት
"ስማኝ እስቲ ግዝሽ..."
"ምንድነው?"
"አስመላሽ...ጉዴን ያዘብኝ"
"የምን ጉድ?"
"አንድ ቀን መጥቶ የማያውቀውን 'ሰላም ልበልሽ ብዬ ነው' ብሎ ቤት መጣ...ከጓሮ ገላየን እየታጠብኩ ስለነበር 'ግባና ጠብቀኝ እየታጠብኩ ሁኘ ነው' አልኩት"
"እእእእሺ..."
"ለካስ እሱ ገብቶ የተቀመጠ መስሎ ተደብቆ ሲቀርፀኝ ነበር"
"ገላሽን ስትታጠቢ?"
"ኋላስ!ከዛልህ በነጋታው ካሴት ሲልክልኝ ዘፈን መስሎኝ እመየ ባለችበት ካሴቱን ከፈትኩት በቲቪ"
"ከዛስ?"
"ከዛ ደውዬ ምን እንደሚፈልግ ስጠይቀው በአጭር ትዕዛዝ 'ማንንም ሳታስከትይ ቤቴ ነይ' አለኝ...ሄድኩ...'በፈለኩ ሰዓት የማላገኝሽ ከሆነ ያየሽውን ካሴት አባዝቼ ሻሞ ብየ ነው የምበትነው...በፌስቡክ ሁላ ነው የምለቅብሽ' አለና 'ተጣጥበሽ ወደ ማታ ተመለሽ' ብሎ አባረረኝ"
"ይሄ ብስባሽ!ቆይ ማዘር ምን አሉ?"
"ያለኝን ስነግራት 'ለዚህ ሙርጥ ፊት እግርሽን ከምትከፍች ሙሉ ጎጃም እርቃንሽን አይቶሽ ይግረመው...ሰው ተደብቆ የቀረጠሽ እንጅ አንች ራስሽን ቀርጠሽ አትለቂው...ወሬ አንድ ሰሞን ነው' አለችኝ"
"እእእሺ..."
"አልሰማኋትም...'ወሬ አንድ ሰሞን ነው' ብሎ ነገር የለም ግዝሽ...ገላን ያህል ነገር በየሰው ቤት በካሴት አስቀምጬ...በየስልኩ ተይዤ የሞት ሞት ከምሞት የአስመላሽ መጫወቻ ብሆን ይሻለኛል ብዬ ተጣጥቤ ሄድኩለት"አለችኝ አንገቷን ደፍታ።የምለው ጠፋኝ...አስመላሽ ያንን ሊነኩት ቀርቶ ሊያዩት የሚያሳሳውን ገላዋን በገላዋ አጥምዶ መያዙ አበገነኝ።በዚያ እርሙጥሟጥ ከንፈሩ ውብ ከንፈሮቿን ሲጎርስ(ዘንዶ በጎረሰው!)...ያንን በቆሎ ለሳምንት የተዘፈዘፈበት ውኋ የሚያስንቅ ትንፋሹን ሲያጥናት...ለወትሮው በልበ ሙሉነት የምትቀስራቸው ጡቶቿን ቀን አኮማትሯቸው... በነዚያ አስቀያሚ ጣቶቹ ወገቧን ሲዞረው...መሰበሯን እያየ ጭኗን ፈልቅቆ ሲገናኛት ...አስመላሽ አስመለሰኝ...ከወፍራም አንጀቴ አንስቶ ነው የተመለሰው...ይሄ የሰው ሩብ!
"መቼ ነው?"አልኳት ቅስሜ የሷን ያህልም ባይሆን ተሰብሮ
"አይ ግዛቸው...ጊዜው ምን ይረባሃል?"
"ግዴለም ንገሪኝ"
"ሶስት ወር አለፈው"...ኩምሽሽ አልኩ።
"መጀመሪያ ሰሞን ኮንዶም እንጠቀም ነበር"
"እእእሺ"
"ሁለት ሶስቴ ከተገናኘን በኋላ ግን ከዚህ ወዲያ ኮንዶም አልፈልግም ብሎ ድርቅ አለ"
"ያንት ያለህ!ሙሉ ተመርምራችኋል ግን?"
"እኔ ተመርምሬ ነበር ከበቀደም...ግን እንመርመር ስለው...'ያንች ድህነት ቫይረስ ሆኖ ካልጨረሰን የኔውስ አይጎዳንም' ብሎ አሾፈብኝ" አለችና ተገፍቶ የመጣ እንባዋን በመዳፏ አበሰችው።ለካ "አይዞሽ"ም ጭካኔ ይጠይቃልና!
"አስገድዶ..."አልጨረሰችውም
"ደፈረሽ?"
"አዎ...ያውም እየሰደበኝ...እየረገመኝ...እየተፋብኝ..."
"እገለዋለሁ ይሄን የውሻ ልጅ!"አልኩና አፈፍ ብዬ ስነሳ እጄን ይዛ ቁጭ አረገችኝ...ጉልበታም ናት።
"የሙት ልጅ እንድወልድ አትፍረድብኝ" አለችኝ።
"በቁሙ ሞቷል'ኮ"
"የካደውን ማመኛ እድሜ ይስጠው"
"አይገርምሽም ቢሰጠው ራሱ እነጥቀዋለሁ"ብዬ ጥያት ስፈተለክ እየሮጠች ትከተለኝ ጀመር።አስመላሽን እንዴት ከምድረ ገፅ እንደማጠፋው እያሰብኩ ስለነበር መከተሏ ግድ አልሰጠኝም።ብቻ የሆነ ቅፅበት ላይ ድብልቅልቁ የወጣ ድምፅ ታክሲ ውስጥ በተቀመጥኩበት ጆሮዬን ሰርፆ ሲገባ ታወቀኝ።አቤት አንዳንዱ ሞት ፍጥነቱ!አሁን ሳናግራት አልነበር?በስንት የተነዳ መኪና ነው ስስ ነፍሷን ከአየር ላይ የቀለበብኝ?አስመላሽ በቡና የተጠበሰ ፊቱን አሳሽጎ...ፍንክቱን አስጠግኖ ለቀብር ተሰየመ...ተያየን...ተግባባን...አፈቅራት እንደነበር ያውቃልና በኔ ላይ ድል አድራጊነት ይሰማው...ወይ ሀዘን አላውቅም...ብቻ ጠጋ ብሎ "ማናችን ነን የገደልናት?" አለኝ።

ዘማርቆስ
02/09/16

@wegoch
@wegoch
@paappii
በግ ተራ እና ትዝታዎቹ
(ዘማርቆስ)

ግቢ የመግባት ዕድሉን ያገኘ ስለ በግ ተራ ማወቅ አይከብደውም።ሄዶም ባይጎበኘው ሄደው ስለጎበኙት መስማቱ አይቀርምና!'በግ ተራ' የሚለው ሐረግ ከቦታው ጋር ያለውን ግንኙነትና ለምን ይህ ስያሜ እንደተሰጠው ባላውቅም አንዳንድ ውስጠ አዋቂዎች እንደነገሩኝ ከሆነ 'በ-ግተራ' ከሚለው በመነሳት ወደ 'በግ ተራ' በሂደት እንደተደረሰ ነግረውኛል።የሌሎቹን ስለማላውቅ ከዚህ በታች ስለ በግተራ የማወጋው ሁሉ የኔን ጊቢ ብቻ የሚመለከት መሆኑን እወቁልኝ።
ፍሬሽ እያለሁ አንድ ጎደሎ ቀን የሆነ ጎደሎ ትምህርት ላጠና ቤተመፃህፍት ገባሁ...ወግ አይቀር!አስችሎኝ እስከ እኩለ ሌሊት አምሽቼ ልወጣ ብድግ ስል አንድ ያገሬ ልጅ ከርቀት ''ጠብቂኝ" አለኝ... ከሰዎች ጋር ተቀምጬ ከማወራው እየተራመድኩ የማወራው ይስበኛል።ስለ ግቢው...ስለ ቤተሰብ...ስለ 'ዲፓርትመንት' ምርጫችን...እየተጨዋወትን...ምን አስቦ እንደያዘኝ ያልገባኝን እጁን መንጭቄ ሳላስለቅቀው...እየተጨዋወትን...በመሀል ጣቱ የመዳፌን መሀል በስሱ እየነካኝ...እየተጨዋወትን...እጄን ለቆ እጁን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጎት...የደረት አጥንቴን መነካካት ሲጀምር...መጨዋወት አቆምን።
"ምን እየሆንክ ነው?" አላልኩም...ሲነካኩ ዝም ብለው ደርሰው በሰው ማላከክማ አጉል ፅድቅን መሻት ነው።
"ምን እየሆንን ነው ጃል?"
"እንጃ"...ብሎኝ ከመንገዱ ዳር ተቀመጠ።ልክ እናቷ ሹርባ ልትሰራት ተደላድላ እንደምትቀመጥ ጉብል እግርና እግሩ መሃል መሬት ላይ ዘጭ ብዬ ተቀመጥኩ...እስከዚህ ሰዓት ድረስ በግ ተራ ስለመሆኔ አላወቅሁም...ጨለማው...ፀጥታውና ንፋሱ ይህ ነው የማይባል ሰላም አለው...እጁ የማያርፍ ወዳጅ አየሩን ካልበጠበጠው በቀር።ደረቴ ላይ ቆሞ የነበረውን ጉዞ ሊቀጥል ሲል የሆነ ቅውጥ ያለ ባህላዊ ሙዚቃ በስፒከር ከፍቶ የሚንቀሳቀስ ሰው ድምፅ ተሰማን...ወዲያው 'ፀሐይ ለምኔ' የሚያስብል ባትሪ ፊታችን ላይ ተተኮሰ። ይህ ባትሪ ከበራብኝ በኋላ በገጠመኝ Post Traumatic Stress የተነሳ ለረጅም ጊዜ ባህላዊ ዘፈን ስሰማና የእጅ ባትሪ ሳይ Heart attack ይገጥመኝ ነበር።
"ኧረግ ኧረግ ኧረግ...አተ!ምናባታችሁ እያረጋችሁ ነው?"አለን ፀሐይ በእጄው ሜትሮ።ምንም እያደረግን ነው ብንላቸው ባትሪያቸው ካሳያቸው ምስል በላይ ላያምኑን የሚጠይቁን ነገርስ?'እየሾረበኝ ነው' ልበል?ወይስ ትከሻዬን እያሸኝ?ሜትሮው በፍጥነት እየተራመደ ሲቀርበን እጅና እግሬን ታስሬ ከተራራ የተፈነቀለ አለት ሊጫነኝ ቁልቁል እየተምዘገዘገ የሚወርድ መሰለኝ... በማይሆን ሰዓት ሰንፈህ የምታውቅ ወዳጄ ካለህ በቃ ያ ጭንቀትህ ነው የጨነቀኝ።
"ምንም እያደረግን አይደለም" አልኩ አንገቴን ቀብሬ።
"እና በዚህ ምሸት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?" አለና ድምፁን በሚችለው ልክ ከፍ አድርጎ ተጣራ።
"አተ ድንበሩ...ኧረ ድንበሩ ዉዉ..."
"ኧኧኧይ" ከወዲያኛው ጫፍ
"ኧረ ናማ ናማ...ና አንድ በልልኝ"
"ኧረ ምን መጣ?"
"ናማ ወዲህ መርፌና ክር ሁነው ያዝኳቸው" ሲል ሲምዘገዘግ የቆየው ድንጋይ መሃል አናቴን የተረተረኝ ያህል ሰማይ ምድሩ ጭውውውው አለብኝ።ድንበሩ ወጣት ነው።ዕድሜውን በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ገመትኩት...
"እስቲ አይ.ዲ. ወዲህ በሉ" አለ ከመምጣቱ
"አልያዝንም" በአንድ ድምፅ
"አምጡማ ልቤን አታውልቁኝ...ዶርምም ቢሆን ተከትየ መቀበሌ ስለማይቀር አጉል አትድከሙ"...መታወቂችንን ሰጠን...እያፈራረቀ ተመለከተውና
"ሚኒሊክ" አለ
"አቤት" አለ ወዳጄ
"ስሙንስ ይዘኸዋል...ጥምብ አሽከር!"አለ በቁጣ...'አምላክ ሆይ መንችኮ አልለቅም ከሚል ስድብ ሰውረኝ' ስል
"መዓዛ" አለኝ
"አቤት"
"ድንቄም መኣዛ!ውትፍ ሸሌ!" አለኝ።አቤቱ ህዝብህን አድን!
"እስቲ አሁን ምን እናርጋችሁ?" አለ ባለ ባትሪው
"ምን አደረግን ቆይ?" አለ ሚኒሊክ
"ዝም በል!የሌባ አይነ ደረቅ!ምን ስታረግ ነው የያዝኩህ?እጅህን እጡቷ ስር ከተህ ስታፍተለትል አይደለም?በል እስቲ ካድ!"
"ኧረ እንደዛ አይደለም'ኮ..."አለ የኔ አልሞት ባይ ተጋዳይ።
"ዝም በል በቃ ሚኒሊክ...እየውላችሁ ወንድሞቼ...ጥፋት አጥፍተናል...ይቅርታ እንጠይቃለን...በዚህ ሰዓት ዶርም ወይም ላይብረሪ እንጂ እዚህ አልነበረም ቦታችን...ለዚህ ደግሞ መቀጣት አለብን...ስለዚህ ተገቢውን ቅጣት ቅጡንና ሸኙን"አልኩኝ ለስለስ ብዬ።ድርበሩ ተብዬው
"እሱማ የት ይቀርልሻል!?ከቅጣቱ በፊት ግን መመከር ስላለባችሁ መታወቂያችሁን ለተማሪ ህብረት ፕሬዝደንቱ እሰጠውና ጧት ቢሮው ሄዳችሁ ታወሩታላችሁ" ሲለን በምን ቅፅበት እግሩ ላይ እንደወደቅሁ አላስታውስም...ከልደታ ማርያም አንስቼ እስከ ቅዱስ ማርቆስ አርባ አራቱን ጠርቼ እንባ ቀረሽ ልመና ለመንኩት።
"የናንተ ይበቃል አሳልፋችሁ አትስጡን...ወይ በጉልበት ስራ ወይ በገንዘብ ቅጡን...በማርያም...በአላህ...በጌታ..."ቅብጥርጥሬ ወጣ።
"ተነሽ ያንችን ብር የሚፈልግ የለም...መጀመሪያ ስትልከሰከሽ ባልተገኘሽ"አቤት የሚጠቀማቸው ቃላት ሲዘጉ!
ባለ ባትሪው ጣልቃ ገብቶ "ተዋት በቃ...ይች ካላበደች ድጋሚ አትገኝም የሷን ስጣትና የሱን አይ.ዲ. አቆየው...ያበጠ ልቡ ሲተነፍስ እንሰጠዋለን" አለ።
"ኧረ እኔ'ኮ አላጠፋሁም አላልኩም "አለ ሚኒሊክ።በዝምታ የኔን መታወቂያ መለሰልኝና
"አይደለም በለሊት በቀን እንዳላይሽ ከዚህ ልጅ ጋር...ሂጅ አሁን ጊቢ!" አለኝ።ዞር ብዬ ሳላይ ኩምሽሽ ብዬ ገባሁ።ሚኒሊክ...ስራህ ያውጣህ!
ከሶስት አመታት በኋላ በተማሪ ህብረት ስር የስነምግባር ዘርፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ሆኜ ተመረጥኩና ከሳምንት ሶስት ቀን በግ ተራንና አካባቢውን ከሌሎች የኮሚቴው አባላት ጋር እየዞርኩ ማሰስ ስራዬ ሆነ።አንድ ቀን እዚያች እኔ የተያዝኩባት አካባቢ እየተዘዋወርን እያለ አንዳንድ ቪድዮዎች ላይ የምናውቃቸውን ድምፆች አይነት የሰማን መሰለንና ጆሮአችንን ቀስርን አዳመጥን...ድምፁ ራሱ ነው...ከጎኔ ከቆመው ጓደኛዬ ሀሰን ያንን ፀሐይ ለምኔ ባትሪ ተቀብዬ ተገግ ሳደርገው...ድንበሩ ከአንዲት ልጅ ጋር ምሳር ባንገቴ ተያይዟል።
"ኢስታክፊር አላህ!" አለ ሀሰን።በቅፅበት ባትሪውን መለስ አድርጌ
"ወንድም ስትጨርሱ ብቅ በሉ ቢሮ እንጠብቃችኋለን" ብዬ ባልደረቦቼን ሰብስቤ ዘወር አልኩ።
.
.
.
@gize_yayeh

04/09/2016

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከአልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(በእውቀቱ ስዩም)

በቀደም እኛ ሰፈር እሚገኘው መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ ብየ ጎራው አልሁ ፤

ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ፥ ሜትር፥ ችካልና በሶስት ጎድጓዳ ሳህኖች የተቀመጠ ናሙና አፈር ተደርድሮ ይታያል፤

“ምን እንርዳዎ ?” አለኝ አስተዳዳሪው፤

“ የሆነች ቀለል ያለች አምስት ሺ ካሬ መሬት ፈልጌ ነበር “

“የገበሬ መሬት ነው የፈለጉት?”

“ የወዛደርም ቢሆን አይደብረኝም፤”

“ አዝናለሁ ፤ ለጊዜው የሚሸጥ መሬት የለንም’

“ እኔም የሚሸጥ ሳይሆን የሚሰጥ መሬት ነው የምፈልገው “

“ምንስ ስለሆንክ ነው ላንተ መሬት የሚሰጥህ ?”

ሰውየው ካንቱ ወደ አንተ የተሸጋገረበት ፍጥነት አስደነቀኝ ፤

‘ እስካሁን ለናት አገሬ ካደረግሁት አስተዋጽኦ አንጻር ፤ መሬት ብቻ ሳይሆን ፥ የአየር ክልል ቢሰጠኝ አይበዛብኝም”

ሰውየው ዘበኞችን ለመጥራት ስልኩን ሲያነሳ፥ ወደ መስኮት እየጠቆምኩ፥

“ እዛ ማዳ ታጥሮ የበሰበበሰ መሬት ምን ይሰራል ?”

“የወጣቶች የስራ ፈጠራ ማእከል ልንገነባበት ነው” አለኝ ፤

“ ከገነባችሁ በሁዋላስ?”

“ አልባሌ ቦታ የሚውሉ ወጣቶች ወደ ማእከሉ እንዲገቡ ይደረጋል “


“እሺ አልባሌውን ቦታ ለኔ ስጡኝ “

2

በቀደም እኛ ሰፈር እኛ ሰፈር አስፋልት ዳር ያለ ስጋ ቤት ባለቤት ጫማ ያስጠርጋል፤ እኔ ወረፋ እየጠብቅሁ ነው፤

“ ቅድምኮ የግብረሀይሉ አባላት ሱቄን በሜትር ለከትውት ሄዱ” አለ ስጋ ሻጩ ፤

“ አይይ ! ሊያፐርሱት ነው ማለት ነው” አለ ሊስትሮው ፤

“ ሊያፈርሱት እንደሆነ በምን አወቅህ ?”

“ ታደያ በሜትር የለኩት ልብስ ሊያሰፑለት ነው?”

@wegoch
@wegoch
@paappii
አለቅየው የሚወዳት ፀሀፊውን "ቀጣይ ሳምንት እረፍት ስለሆንኩኝ ወደ ውጪ ሀገር እንሄዳለን ተዘጋጂ" ይላታል

ፀሀፊዋም ወደ ባሏ ደውላ "እኔ እና አለቃዬ ቀጣይ ሳምንት የስራ ጉዞ አለን: ልጆቹን ትንከባከባለህ" ትላለች

ባልየው የሚወዳት ውሽማው ጋር ደውሎ "ሚስቴ መንገድ ልትሄድ ነው: ቀጣይ ሳምንት በነጻነት አብረን ነን"

ውሽማዋ ደግሞ በግል የምታስጠናው ልጅ ጋር ደውላ "ቀጣይ ሳምንት ሌሎች ፕሮግራሞች አሉብኝና ጥናት አይኖረንም" ብላ አመቻቸች

ትንሹ ልጅ አያቱ ጋር ደውሎ "አያቴ! አስጠኚዬ ቀጣዩን ሳምንት አልኖርም ብላለችና ከአንተ ጋር ባሳልፍ ደስ ይለኛል"

አያትየው ፀሀፊዋ ጋር ደውሎ "የነገርኩሽን ጉዞ መሄድ የምንችል አይመስለኝም:: የልጅ ልጄ ሳምንቱን ከእኔ ጋር ማሳለፍ ይፈልጋል: ስለዚህ ሰርዢው"

ፀሀፊዋ ባሏ ጋር ደውላ "አለቃዬ የግል ጉዳይ ገጥሞት ጉዞውን ሰርዞታል: ስለዚህ እዚሁ ነኝ ስለልጆቹ አታስብ"

ባልየው ውሽማው ጋር ደውሎ "ቀጣይ ሳምንት አብረን እንሆናለን ያልኩሽን ተዪው:: ባለቤቴ ጉዞውን ሰርዛለች"

ውሽማዋ የምታስጠናው ልጅ ጋር ደውላ "ፕሮግራሜ ተስተካክሏል: ቀጣይ ሳምንት ጥናታችንን እንቀጥላለን ተዘጋጅ"

ልጁ አያቱ ጋር ደውሎ "አስተማሪዬ ደውላ ቀጣይ ሳምንት ጥናት እንዳለብን ነግራኛለችና አብረን ማሳለፍ እንደማንችል ልነግርህ ነው"

አያትየው በድጋሚ ፀሀፊዋ ጋር ደውሎ "የልጅ ልጄ ቀጣይ ሳምንት አብረን እናሳልፍ ብሎኝ ነበር ነገር ግን አስተማሪው ደውላ ትምህርት እንዳለ ነግራዋለች:: ስለዚህ ጉዟችንን መቀጠል እንችላለን: ተዘጋጂ" 🤦🏾

👇🏾

ማነው ይህንን አዙሪት እያጦዘው ያለው?


By zemelak Endrias

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ስልጤ ሴት ...

[ ልዑል ፡ ዘወልደ ]

ድሮ ድሮ ፥ ስልጤ የወደደችው ወንድ ሲኮራባት እና ሲንቀባረር ስትለማመጥ አትገኝም ። ድሮ ነው ታዲያ ፥ ቀሚስ በስኒከር ማድረግ ሳይጀምሩ ሃሃ ። ብቻ እንዳሁን የከተማ ሴቶች ሆነ ብለው አያረግዙም ፥ በቀብድ አይጋቡም ። እንደውም ምን ይላሉ ...

- ገወ ምሽት ወልደ ቶባት !

ሞኘ ሚስት ቀድማ ልጅ ትሰጣለች እንደማለት ፤ ኦ ! አስረግዞ ቃላ ሊያስቆረጥምሽ? ባል ከልጁ አስቀድሞ ሚስቱም ላልተወሰነ ግዜ የመንከባከብ ግዴታ አለበት ።

ወደ ርዕሳችን እንመለስ ፥ የተመቻቸው ወንድ ሲኮራ ምን ያደርጋሉ ?! ኦጋ የሚባል ስርዓት አለ ። ቅቤና ቄጠማና ይዛ ፥ ቀጥ ብላ አባቱ ቤት ትሄዳለች ። ከዛ ፥ አባትየውን እሺ እስኪል ድረስ ደህና አርገው ቅቤ ይቀቡታል ። አተካኖ እስኪመስሉ ድረስ ሽበታቸውን ለብጣ-ለብጣ ስታበቃ ... አሁንስ ጋሼ ?! ትላቸዋለች ....

- የኔ ልጅ (አለባበጧ የተመቻቸው አባት ፥ እያቃሰቱ)

- ወዬ ጋሼ

- አንቺ እንደው መሊካ ነሽ ። የኔን ልጄን ግን አቀዋለው ፥ የወጣለት ዱ...ር...ዬ ነው ።

- ኦ ! እና ሳልቀቦት በፊት የማትነግሩኝ ?

- አይሆንሽም የኔ ቆንጆ ፥ ይቅርብሽ።

- እና እኔ ቆሜ ልቀርሎት ነ?

- እኔ ...የት ሄጄ ! የኔ ልጅ ? የት ሄጄ ! 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii
Finally 🙏
ፈጣሪ ታላቅ ነው።
አዕጋረ ፀሓይ ዛሬ ሕትመቷን ጨርሳ ለስርጭት ጃዕፋር መፅሀፍት ተልካለች። በቅርቡም በመላው አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ትዘልቃለች።
በሂደቱ ሁሉ ከጎናችን ለነበራችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።
መልካም ንባብ

ደራሲ ሚካኤል አስጨናቂ
1892 ላይ ስታንፎርድ ዩንቨርስቲ ይማር የነበረ የ18 አመት ወጣት ለትምህረቱ የሚከፍለው ገንዘብ ይቸገራል። ገንዘብ የሚጠይቀው ሰውም አልነበረውም። በዚህ ሃሳብ እያለ ከጓደኛውጋ ይማከራል ... 'ለምን የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅተን ገንዘብ አንሰበስብም?'

ሁለቱ ወጣቶች ወደ አንድ Ignacy J.Paderewski የሚባል ታዋቂ ፒያኒስትጋ ይሄዱና ማናጀሩን ያገኛሉ። ማናጀሩም $2000 ክፈሉና እንደፈቀዳችሁ አላቸው። ወጣቶቹ ሙዚቃቸውን እያጠኑ እና እየተለማመዱ ለሙዚቃ ፕሮግራማቸው ይዘጋጁ ጀመረ

ያ የተባለው ሙዚቃቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ደረሰ። ብዙ ትኬት ስላልተሸጠ ባጠቃላይ ያገኙት ገቢ 1600 ዶላር ብቻ ሆነ። ያቺን ያገኟትን ገንዘብ ይዘው ወደ Paderewski ይሄዱና እንዳሰብነው አልሆነልንም። ስለዚህ የምንመልስልህ ያገኘነውን ሙሉ 1600 እና ወደፊት ልታወጣው የምትችለው የአራትመቶ ዶላር ደረቅ ቼክ ነው ይቅርታ አሉት።

ሰውየው ግን ጭራሽ ተቆጥቶ ቼኩን ቀደደ እና ገንዘቡን አልቀበልም አላቸው። ይህ ገንዘብ ለአንዳንድ ወጪ ያወጣችሁትን ይሸፍንላችኋል። የቀረውን ለራሳችሁ ተጠቀሙት አላቸው።

ወጣቶቹ ተደንቀው አመስግነውት ወጡ። ስለተደረገላቸው መልካምነት እጅግ ተደሰቱ።

የማያውቃቸውን ሰዎች ለምን በዚህ መጠን ሊረዳቸው ፈለገ? ከእነሱ ምንንም ሳይጠብቅ ለምን ይሄንን ቸርነት አደረገላቸው? አንዳንዶቻችን "ይህንን ሰው በዚህ በተቸገረው ነገር ብረዳው ለኔ ምን እጠቀማለሁ?" ብለን እናስባለን። አንዳንድ ብሩህ ልብ ያላቸው ደሞ "ይህንን ሰው በዚህ በተቸገረበት ሰአት የአቅሜን ባልረዳው ምን ይሆናል?" ብለው ስለ እዛ ሰው ያስባሉ

ከጊዜያት በኋላ ይህ ፒያኒስት የ ፖላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነ። የተወደደ ገዢ ሆኖ በሚመራበት ዘመኑ የአለም ጦርነት ተጀመረ እና 1.5 ሚሊየን ፖላንዳውያን ተራቡ። እሱም እርዱኝ ብሎ አለማትን መለመን ጀመረ።

ወደ አሜሪካን መልዕክት ላከ። በሰአቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበሩት Herbert Hoover ወዲያው እርዳታ አደረጉለት። በዚህም የፖላንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ተደስቶ ይህንን ሰው በአካል ያለበት ሄጄ አመሰግነዋለሁ ብሎ አሜሪካ መጥቶ እጅ ነሳ። 'ለህዝቤ እና ለእኔ ላደረግህልን በጎነት አመሰግናለሁ' አለ የፖላንዱ ጠቅላይ ሚንስትር።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ግን 'ለምን ታመሰግነኛለህ?' አለው

'ከብዙ አመታት በፊት ሁለት ተማሪዎችን ለትምህርት የሚከፍሉት ሲቸገሩ በጎ ፈቃድ ያደረግህላቸው ትዝ አለህ? አንዱ ወጣት እኔ ነበርኩ'

By Mastewal Aseffa

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
Exhibition titled, “መልክ”
By Surafel Alemneh

Artawi Gallery
opened for public.

The galley opened  until 20 July 2024 starting from 2 PM - 6 PM bole, around British international school or 250m in from Yod Abyssinia, Kkare Homes, 2nd Floor


@seiloch
መናፍስት አማረኛ አወራ ?
                          በግዕዝ ሙላት

ሰማዬ ጋር የክዋክብት መብራት የአራስ ህፃን አይን መስለው ቡዝዝ ብለው በየፈርጡ ተኮልኩለዋል ። ጨለማው ከሰማዬ ብርሃን ገዝፎ መጠነኛ ንፋስ የግቢውን ዛፎች ያስደንሳቸዋል !ቅጠሎች ደሞ ሰክረዋል መሰል እዬተንገደገዱ ይወድቃሉ (የንፋሱን ውስኪ ገልብጠው)።

እዬለፈለፍኩ ነው? ግን እያወራሁ አይደለም? የተፈጥሮ የድምፅ ፀጥታ ከራሴ ጋር ሊያመካክረኝ ዝግ ስብሰባ ይዟል። ቆይ... ቆይ... ቆይ...ሲጀምር... ለምንድነው? ከራሴ ጋር ምማከረው?... እንደዛ ሲባልስ... ደባል ስዕብና በውስጤ አለ ወይስ የለም  ? ሲጀምርስ ምክክርን ከዚህ ምን አመጣው ? ብሽቅ!(አለ ያነኛው )

አንዳንዴ በቀን ኑሮ ውስጥ ያሉ ትዕይንቶች ለስዕብናችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ(political speech ሆነ መሰል ?😏ለምን የድመቱን ድርሻ አይወስዱም ምን አገባኝ? አይጥ!) (አለ ይሄኛው)

ሲጀምርስ ፖለቲካን እዚህ ምን አመጣው? አያችሁ ይሄ ነው ስዕብና ማለት ዝም ብሎ መዘባረቅ። ስዕብና ፀንቶ የሚኖር ሀውልት አይደለም! በሁኔታው ሁሉ ይቀያየራል። ለዛም ይመስለኛል ህፃን ልጅ ልጅ ሳለ ንፁህ ይሆንና የኋለኛው ማንነቱ በአረመኔነት የሚቀዬረው ።
(በሚያዬው ትዕይንት እና ገቢር መጠን...ስል ገና)
" እና እኛ ምን አገባን?' ቅማላም' ቁጭ በል" አለኝ ያነኛው(የትኛው?)

<እኔ>
ሰአቱ ስንት እንደሆነ አላቅም.. እርግጥ ነው መብራት ስለጠፋ (መጀመሪያውንም ስለሌለ)  ብቻ ስልኬም ባትሪው ዘግቷል ።ይመስለኛል ይሄን የተፈጥሮ ፀጥታ  እንዳዳምጥ ያደረገኝ ሰው የፈጠራቸው ነገሮች በቴክኒካል ችግር መደበቃቸውን ነው(ባትሪ መዝጋቱን ማለቴ ነው)።የሚገርመው ግን ተፈጥሮ የምትባለው ሴት ግን (ሁሉንም ከሴት እናገናኜዋለን!) ቴክኒካል ችግር የለባትም! አሁን አሁን የአዬር ብክለት ሚባለው ነገር ትልልቅ ትሪሊዮነሮችን ባለሀብት በገነቡት እንዱስትሪ በሚለቀቀው ጋዝ ተበከለና መልሰው በበከሉት አዬር ያገኙትን ትርፍ መልሰው የአዬር ብክለትን ለማስተካከል ይደክሙበታል።...ቆሻሻ አለ ጋሽነት። (ጋሽነት የሰፈራችን ሰው ነው ልጁ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ልጁ ጋር ያለውን ፍቅር ለመግለፅ የሚጠቀምባት ቃል ናት!ቆሻሻ አለ ጋሽነት( አለ ተኝቶ የነበረው እኔ?)

<ያነኛው እኔ>
በቃ ሰው እንዲህ ነው ዝም ብሎ መባከን መባከን መባከን(አልጨረሰም ገና) ..."አንተ ልጅ ተመለስ ተው" አለ የሆነ ድምፅ ከጨለማው መሃል' እማዬ ድረሽልኝ' ምንድነው የሰማሁት(በአካል የሚታዬው አፌተናገረ)...መናፍስት ?... አይ አይ መናፍስት አማረኛ አይችሉም! ...እና ማነው ያወራው?...ፀጥ አልኩ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ ድጋሚ..."ለምን ዝም አልክ" አለ ያ ድምፅ...'ኧረ ደገመው' አልኩና ጆሮዬን የት ጋር ድምፁ እንደመጣ አጣራው ከውስጥህ ነኝ ያለሁት አለኝ የሆነ ድምፅ!.. ግን የሆድ ድምፅ ይመስላል (እ? እንዴት ራሴው አውርቼ ራሴው ፈራሁ አንዳንዴ ከሰውነታችን የሚወጡ ትርጉም የለሽ ድምፆች የሆነ ቅፅፈት ትርጉም ይኖራቸዋል ልክ እንደዚሁ ) በድጋሚ የሚናገረው ድምፅ ተሰማኝ የራሴው ስዕብና ነው ላምን አልቻልኩም "ኧረ ቤስሚያም"አሉ አባ ጎርብጥ

<ወዲህኛው እኔ>
ነግሬቹሃለሁ ሁላችንም በሁኔታዎች የሚቀያዬር ስዕብና ነው ያለን..."መጣሁልህ አንተ ፈሳም" አለኝ ሌላ ድምፅ ከዛፉ ስር "እማዬ ድረሽ መናፍስት አማረኛ አወራ?"....እዬሮጥኩ ወደ ቤቴ....

@geez_mulat

@wegoch
@wegoch
@wegoch
..."አባዬ" (ልጅ)

..."አቤት" (አባት)

..."በግ አስተኝተን፡ አርደን፡ ደሙን አፍሥሰን፡ በጥብስ እና በቅቅል አርገን ስንበላው ነፍሱን በማጥፋታችን ሀጥያት አይሆንብንም?"(ልጅ)

..."ምን ስትል አሰብከው ልጄ? እረ አይሆንብንም።" (አባት)

..."እንዴ አባዬ እየገደልን አደለ እንዴ፡ እንዴት ሀጥያት አይሆንብንም?" (ልጅ)

..."ምን መሰለህ ልጄ... እንዴት ላስረዳህ?... ሞት እኮ በር እንጂ መጨረሻ አይደለም፡ በጉን ስንበላው በኛ ውስጥ መኖሩ ይቀጥላል እንጂ ጨርሶ አይሞትም" (አባት)

..."እረ እረ አባዬ ደሞ እንደዚ አለ እንዴ?" (ልጅ)

...."አዎ! እውነት ስልህ ፥ ያው የበላነው ተስማምቶን ሀይል እና ጉልበት አግኝተን፡ አካላዊ እድገት እያመጣን አይደል የምንኖረው ፡ ያ ታድያ እኮ በኛ ኖረ ማለት ነው ልጄ" (አባት)

..."እሺ እና ጋሽ ጀንበሬ እንደውም ባለፈው በለሊት ወደስራ ሲሄዱ ጅብ የበላቸው ጅብ ሆነው እየኖሩ ነው ማለት ነው አባዬ?" (ልጅ)

..."ወይ ጉድ ዛሬ እንደው ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት...ማነሽ 'አልማዝ ነይ እስኪ ይሄን ልጅ ወደዛ ወስደሽ ገላግይኝ'...አልሞት አልኩህ?" (አባት)

..."ምን አልክ አባዬ?" (ልጅ)

..."ምንም ወዲህ ነው የእራት ሰዓት ደርሷል እናትህን ወስደሽ አብይው እያልኳት ነው....'አንቺ አልማዝ ነይ እኮ ነው ምልሽ'. ..አትሰማኝም እንዴ?" (አባት)

..."እና ንገረኛ አባቴ ጋሽ ጀንበሬ ጅብ ሆነዋል ማለት ነው? የባቢ አባት ጅብ ናቸው ማለት ነው?" (ልጅ)

..."ሆሆ! ደሞ ነገ ት/ት ቤት ሄደህ 'የባቢ አባት ጅብ ሆኑ እንጂ አልሞቱም ብሏል አባዬ' ልትል ነው ሆሆ! ደሞ ከጎረቤቶቼ አቆራርጠኛ! በል በል የለም ያልኩህን እርሳው በቃ እንደውም ሀጥያት ነው ከንግዲህ በግ የሚባል አናርድም።. ..ግልግል እንደውም ተወዷል...ሆ! በገዛ እጄ...ቆይ እዛ ት/ት ቤት ምን ስትማሩ ነው የምትውሉት?" (አባት)

..." እርሳው? አባዬ ደሞ አንዴ ነግረኸኝ እንዴት ነው ምረሳው?...ደሞ ት/ት ቤት ሳይሆን አንተ እኮ ነህ የነገርከኝ በግን ስንበላው እኛን እንደሚሆን...ት/ት ቤት ምን አጠፉ....ህእ!" (ልጅ)

..."ማ? እኔ አልወጣኝም! አይወጣኝምም!. ..ምን ይላል ይሄ...በል ጥፋ ከዚ. ..ድራሽ አባክ ይጥፋና...አትሄድም!".....

By Mikiyas Beshada Kebede

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (Leul M.)
#ወደ_ግጥም__ወደ_ነብይ
ፈግታን ስለቸረን መነሱ ___ ስላስጠለለን ዋርካነቱ
ስለ አፅናኝ ጨዋታዎቹ ___ ሕይወት ስለሚያሞቁ ግጥሞቹ
ቅንነቱን ለማቀንቀን ___ አባትነቱን ለማወደስ
ስለ ግጥም _ _ _ ደግሞም ስለ ነብይ
ቅዳሜ እንሰበሰባለን። ፈንድቃ ቤተ ጥበብ [ ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከል:Fendika Art & Cultural Center ]

• ውብ ግጥሞች ልዩ
• ልዩ የሙዚቃ ጨዋታዎች
• ነገረ ነብይ
• የጥበብ ቅማ ቅመም

የምትወዷቸው የምንወዳቸው ሁሉ አሉ። ስለ ግጥም _ ስለነብይ።

ከ8:00 ቀደም ብላችሁ ኑ።
ቡናውም ጨዋታውም ወዳጅ ትውውቁም እንዳይቀርባችሁ።

ቅዳሜ ሀምሌ 6 2016 ዓ.ም 😍🙏🙏🙏😍

@getem
@getem
Notcoin🪙 በአዲስ አሰራር መቷል! ገብታችሁ ስሩበት


https://t.me/notcoin_bot?start=er_36367900
አባት ልጁን ለማግኘት ወደ ክፍሉ ጎራ ይላል፤ ልጁ ግን የለም። እንደለመደው አምሽቶ ሊመጣ እንደሆነ እያሰበ ክፍሉን ለቆ ሊወጣ ሲል የሆነ ነገር አስተዋለ።

አዎ ክፍሉ እንደወትሮው አልተዝረከረከም፤ በሚገባ ተፀድቶ ተስተካክሏል። አልጋውም በስርዓት ተነጥፏል፤ ወለሉ ሸልፉ ምኑ ሁሉ በወግ በወግ ሆኗል።

ግራ በመጋባት ክፍሉን እየቃኘ በመሃል ማጥኛ ጠረጴዛው ላይ ደብዳቤ ያገኛል፤ ከላይ ለ አባዬ ይላል በትልቁ።
ከፍቶ ማንበብ ጀመረ..

“ አባዬ ከትሬሲ ጋ ተያይዘን ጠፍተናል..አውቃለሁ እድሜዋ ከእኔ በ30 እንደሚበልጥ ፤ ቢሆንም እኔ ግን በጣም እወዳታለሁ። ለመጥፋት የወሰንነው እንዳረገዘችና ልጁ የኔ እንደሆነ ስትነግረኝ ነው።
ምንም ገንዘብ ስላልነበረን ከዋሌትህ ልሰርቅ ተገድጃለሁ።

ጥሩ ገንዘብ መስራት የጀመርን ጊዜ፤ የኤች አይ ቪ በሽታዋን ሆስፒታል እየሄድን ክትትል ማድረግ እንጀምራለን። ደሞ ብዙ ልጆችንም የመውለድ እቅድ አለን ፣ ጊዜው ሲደርስ ተሰብስበን መጥተን የምናይህም ይሆናል።

ቆይ ቆይ አባዬ የውሸቴን ነው ተረጋጋ፤ እዚሁ ሰፈር ነው ያለሁት የትም አሌድኩም። የኔ ፍላጎት ከፈተና ውጤቴ በላይ አስፈሪ ነገሮች እንዳሉ ለማስታወስ ነው ፤ ልታየው ከፈለክ ሌላኛው ጠረጴዛ ላይ አለልህ።
ስትረጋጋ ደውልልኝ ”

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፀጉር ቆራጩ ደምበኛውን ያዝናናል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በማጫወት ላይ ነው።
“ያ ይታይሃል?...አስፖልቱ ዳር የተቀመጠው ልጅ..?”
“አዎ”
“ከምታስበው በላይ ጅል ነው”
“እንዴት? ”
“ቆይ ላሳይህ” አለና ፤ወጣ ብሎ ልጁን ጠርቶ ወደ ውስጥ አስገባው።
“ተመልከት እንግዲህ..”

ከኪሱ አንድ የአምስት ብርና አንድ የአስር ብር ኖት አወጥቶ ሁለቱንም መሬት ላይ ጣላቸው ከዛ ልጁን “ ከሁለቱ ትልቁን ብር አንስተህ ሂድ” አለው። ይሄኔ ያ ልጅ አምስቷን ብር ብድግ አርጎ ወደ መጣበት ይመለሳል።
“አየህ ይሄን ደደብ?...በዚ እድሜው አምስት ብርና አስር ብርን መለዬት አይችልም!!”
“በጣም ሚገርም ነው” አለ ፀጉሩን ሊቆረጥ የመጣው ሰውዬ ባዬው ነገር የእውነትም ተገርሞ።

አስተናግዶት ከጨረሰ በኋላ ተሰነባብተው ተለያዩ። ይሁን እንጂ ያ ሰውዬ ቅድም ባየው ነገር ተገርሞ ብቻ ሊቀር ስላልፈለገ ልጁ ወዳለበት ሄዶ ያሳሰበውን ነገር ጠየቀው
“እውነት አንተ..አስር ብር እና አምስት' ብርን መለየት አትችልም?”
“አዪዪ..” አለ ልጁ
“አዪዪ..10 ብሩን ያነሳሁ ቀንማ ጨዋታው ያበቃል”

by Yosef Gezahegn

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።


ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!



@seiloch
@seiloch