🇪🇹🇪🇹እኛ ኢትዮጵያውያን🇪🇹🇪🇹
432 subscribers
23 photos
2 links
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያን ታሪኳን እንወቅ እናድን እናሳውቅ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🦁🦁ስለ ኢትዮጵያ እናት ሀገራችን እንማማር! 🦁🦁
🇪🇹🇪🇹 ፓለቲካ ቦታ የለውም!🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Download Telegram
በጎንደር አካባቢ ፀረ ፋሽስት ትግል ሲመራ የነበረው ጀግና አርበኛ ጠላት ሳይቀር "ውብነት The Eagle" እያለ ይጠሩታሉ። ይሄ የተባለበት ምክንያት ባልታሰበ ቦታ እና ጊዜ እየሄደ መግብያ እና መውጫ ስላሳጣቸው ነው።አየር ዝቅ ካለ በመትረየስ ይጥላታል። በእውነት የዚ ሰው ጀግንነት ብዙ ያልተወራለት ነው ይሄ ደግሞ ያሳዝናል።
ውድ የቻናላችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ እንሆ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ እንዳለ ከልጅ ልጁ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በምድር ላይ ዳግማዊ አዳምን ሆኖ ሲያስተምረን መንገድ ሲያሳየን ቆይቶ ጌታ ለሰው ልጆች በደል ሲል ልጆቹን ለማዳን ሲል የማይሞተው ሞቶ የማይገረፈው ተገርፎ ግርማውን አንዳችም የምድርም ሆነ የሰማይ ፍጥረታት አይተውት ከፊቱ መቆም እማይችሉት ጌታ ከሰው ፊት ቆሞ ተፈረደበት በጎሉጎታም ስለኛ በደል ተሰቀለ በመሰቀሉም ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ እኛ ነፃ ወጣን እንኳን አደረሳችሁ

🇪🇹🇪🇹#ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር!!🇪🇹🇪🇹
🦁🦁🦁🦁🦁🦁🦁🦁
@weEthiopian @Abyssinian47 @Ethiopian
ክርስቶስ ተንሰአ እም ሙታን
በአብይ ሀይል ወ ስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም እምይዜሰ
ኮነ
ፍሰሀ ወሰላም
በክርስቶስ ክርስቲያን የተባላቹ እነኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በላም አደረሳችሁመልካም በዓል!
ታሪክ በዛሬው ዕለት!

በጣሊያን የወረራ ዘመን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዋ ከታጠፈ ፣ ሉዓላዊነቷ ከተደፈረ 5 ዓመታት በኋላ ነፃነቷን ያስመለሰችው የዛሬ 80 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር ነበር:: ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት ንጉሰ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአርበኞች ብርታትና መስዋዕትነት የጣሊያን ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በታላቁ ቤተ-መንግሥት ሰቀሉ፡፡

የሚያዝያ 27 የንጉሰ ነገስቱ አዲስ አበባ ገብቶ ሰንደቅ ዓለማ መስቀል ታሪካዊ ምፀትም ነበረው፡፡ ከዚያን ጊዜ 5 ዓመታት አስቀድሞ ሚያዝያ 27/1928 በዚያው ቀን ወደ ኢትዮጵያ የዘመተው የጣልያኑ ጦር አዛዥ ጄኔራል ባዶሊዩ አዲስ አበባ ገብቶ በታላቁ ቤተ-መንግሥት የጣሊያንን ባንዲራ የሰቀለበት ነበር፡፡ ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈቷ 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ደርጅታ ኢትዮጵያን ከሦስት አቅጣጫዎች ወረረች፡፡ ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር ለ8 ወራት በፅናት ተዋጋች፡፡

የጊዜዎቹ ኃያላን እንግሊዝና ፈረንሳይ የጦር መሣሪያ በግዢ እንዳታገኝ ለጣሊያን ተደርበው ስላሴሩባት ኢትዮጵያ ብቻዋን ጦርነቱን በመጋፈጧ ድል ማግኘት አልቻለችም፡፡የየግንባሮቹ የኢትዮጵያ የጦር አዛዦች ብዙዎቹ ሞተው ሠራዊቱም በመርዝ ጋዝና በአውሮኘላን ቦምብ ተደብድቦ ያለቀው አልቆ የቀረው ቀርቶ ጣልያን ጊዜያዊ ድል አግኝታ አብይ አብይ ከተሞችን ብትቆጣጠርም ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በገጠሩ ክፍል እምቢ ለነፃነቴ ፣ እቢ ለአገሬ ብለው የሽምቅ ውጊያ ጀመሩ፡፡ ንጉሰ ነገስቱም ስደት ሄደው በጊዜው ለነበረው የመንግሥታቱ ማኅበር /ሊግ ኦፍ ኔሽንስ/ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ የሚሰማቸው ግን አላገኙም፡፡

አርበኞች ግን ከቀን ወደ ቀን ድል እየተቀናጁ የጣሊያን ወታደሮችን መፈናፈኛ ፤ መግቢያ መውጫ አሳጧቸው፡፡ከጣሊያን ወታደሮች ይማርኳቸው በነበሩ መሣሪያዎች ራሳቸውን እያደራጁ አብዛኛውን የገጠር ክፍል ተቆጣጠሩት፡፡የ2ኛው የዓለም ጦርነት ሲቀሰቀስ ጣሊያን የናዚ ጀርመን አጋር ሆነች፡፡ ያን ጊዜ እንግሊዞች የጣሊያን ጠላት ሆነው ኢትዮጵያን መደገፍ ጀመሩ፡፡

ስለዚህም ወታደራዊ ድገፍ ሰጥተው ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ረዷቸው፡፡በጄኔራል ካኒንግሂም የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ከኬንያ ተነስቶ ከደቡብ አቅጣጫ ወደ መሀል ኢትዮጵያ ሲገሰግስ ፤ በጄሪራል ኘላት የሚመራው ጦር ከሱዳን ተነስቶ ወደ አሥመራ ፤ ከዚያም ከሰሜን አቅጣጫ ወደ መሐል ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሚመራውና የአርበኞችና የእንግሊዝ አማካሪዎች የሚገኙበት ጌዲዮን ተብሎ የተሰየመው ጦር ከሱዳን ተነስቶ በኦሜድላ አልፎ በጐጃም በኩል ወደ መሐል አገር ገሠገሠ፡፡በመካከለኛ ኢትዮጵያ አርበኞች በጣሊያን ወታደሮች ላይ ጥቃትቸውን አፋፋሙ፡፡ ጣሊያኖች ክፉኛ ተሸነፉ፡፡ በየቦታው ድል የመሆናቸው ዜና ናኘ፡፡

ዘመቻው ከተጀመረ 2 ወራት ሳይሞላው ፤ ጣሊያኖች አዲስ አበባን ለቀው ፈረጠጡ፡፡ መጋቢት 28/1933 ዓ.ም የጄኔራል ካኒንግሃም ጦር አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡እንግሊዞች ኢትዮጵያውን አርበኞች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ስላልፈለጉ ቀዳማዊ ኃይል ሥላሴን በደብረ ማርቆስ ለ 1 ወር ያህል እንዲቆዩ አደረጓቸው፡፡ይሁንና በአዲስ አበባ በአርበኞች ተፅዕኖና ቅሬታ የተነሳ አርበኞች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቀዱ፡፡

አፄ ኃይለ ሥላሴም ወደ አዲስ አበባ እንዲጓዙ ፈቀዱ፡፡
20 የክብር ዶክተሬት ድግሪ ያላቸው ንጉሳችን!
በጥበቡ በለጠ

ዛሬ የተወለዱበት ቀን ነው።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በአለማችን ካሉ 20 ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ ተቀብለዋል! በየዩኒቨርሲቲዎቹም ተገኝተው ታላላቅ መሪዎችና ምሁራን በታደሙበት ውብ ንግግሮች አድርገዋል፡፡ ንግግሮቻቸውን አልፎ አልፎ እጽፋቸዋለሁ፡፡ እኚህን ታላቅ ንጉስ የሚከተሉት የምድሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ አበርክተውላቸዋል፡፡
1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ
3- ግንቦት 28 ቀን 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት
4- ግንቦት 30 ቀን 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
5- ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
6- ሐምሌ 16 ቀን 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
7- ሐምሌ 29 ቀን 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሐራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ድግሪ
8- 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
9- ጥቅምት 10 ቀን 1947 ዓ.ም ከኢክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
10- ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
11- ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ድግሪ
12- ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
13- ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ድግሪ
14- ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
15- መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
16- መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
17- መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት ክብር ዶክተሬት
18- ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ የህግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
19- ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
20- ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ድግሪ ተቀብሏል፡፡

( የምንጭ ስብስብ ከአጼ ኃይለስላሴ የታሪክ መጻሕፍት)
ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከተናገሯቸው ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ !

- ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ።

- ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር ።

- ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ ። በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ።

- የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡- ‹‹ የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም ። ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ። ከአባቶቻቸው እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው ።... መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም ። ማንም ሰው መሬቱን ሊሸጥ አይችልም ። መሬትን መሸጥ፣ መስጠትም የሚችለው የመሬቱ ጌታ ነው ››

- ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡- ‹‹… እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ ››

- በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን ። ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው ።

- አባት ያለህ የአባትህን እሰጥሀለሁ፤ አባትህን መርቅ ። አባት የሌለህ አባትህ እኔ ነኝና ደጅ ጥናኝ ።

- እኔ ቤት እንጀራ የለም ። እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ ፤ እሠራሁት ትምህርት ቤት ልጆቻችሁም እያስገባችሁ አስተምሩ ።

- የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?

- ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት እንቀበላቸዋለን ። በሌላ ለሚመጡብን ግን ፤ ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም ።

- የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት ፤ የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ ፤ የሸፈቱባቸውን ፣ የወጉአቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን አይሹም ።

- አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ ፡- ‹‹ ያገሬ መሬት የሁሉም
ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፤ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው ። ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ ምን ቀርቶ እገዛለሁ ? ›› አሉ ።

ምንጭ ፡- የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ መጽሔት ቁጥር 1. ነሐሴ 1992 ዓ.ም
ከገጽ 16 እስከ 17
ጥር 5 ቀን ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ነፃ ባወጣት ሀገር የተሰቀለበት 77ኛ አመት
ከካሳ እስከ ቴዎድሮስ
-------
(አፈንዲ ሙተቂ)
-----
በ1850ዎቹ ውስጥ ነው። በጎንደር ቤተ መንግስት እልፍኝ ውስጥ ከባድ ውይይት እየተካሄደ ነበር። በውይይቱ ላይ የተገኙት እቴጌ መነን (ትልቋ)፣ ራስ አሊ፣ አንድ መነኩሴ እና ሌሎች ሹማምንት ነበሩ (ደጃች ወንድይራድ ደግሞ ወደ ኋላ ላይ ውይይቱን ይቀላቀላል)።

1ኛ ተናጋሪ (እቴጌ መነን)

አረ ለመሆኑ ምን ይሆን አሳቡ
ሸፍቶ የሄደው ከነቤተሰቡ?
---
2ኛ ተናጋሪ (ራስ ዓሊ)

ሰውዬው ኩሩ ነው የተነፋ ልቡ
ይዞ ማዋረድ ነው ይበርዳል ጥጋቡ::
---
3ኛ ተናጋሪ (አንድ መነኩሴ)

ሰውዬው ብርቱ ነው ስሙ የተጠራ
ጎበዝ እኔ ነኝ ባይ ሀይልን የማይፈራ
በዘዴ በትዕግስት ማባበል ይሻላል
በሀይል ብንለው በጣም ያውከናል፡፡
----
4ኛ (እቴጌ መነን)

እንዲህ ስትሉ ነው ስሙ የገነነው
የፈራነው መስሎት አገር የሚያብጠው
ዘዴ መላ አታብዙ ጦር ይታዘዝና
ቢቻል ከነነፍሱ ይምጣ ይያዝና
እምቢ ካለም ይሙት በገዛ ጥፋቱ
ላንድ ወንበዴ ሽፍታ አይስጋ መንግሥቱ፡፡
------
ይህ ጭውውት የተቀነጨበው “ቴዎድሮስ” ከተሰኘው የደጃች ግርማቸው ተክለሃሪያት መጽሐፍ ሲሆን በጭውውቱ ውስጥ “ለምን ሸፈተ” ተብሎ እንደ አጀንዳ የቀረበው ደግሞ የያኔው ደጃች ካሳ ሀይሉ የኋለኛው፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ መሆኑ ነው፡፡ በዚያን ወቅት ካሳ ሀይሉ ከገበሬ ቤተሰብ ተወልዶ በአስገራሚ ሁኔታ የቤተ መንግሥቱ አባል ሆኖ ነበር፡፡ ታሪክ አለው፡፡

ደጃች ካሳ በወጣትነቱ ሽፍታ ሆኖ በቋራና በደምቢያ ይዘዋወር ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ሱዳንን ከሚቆጣጠሩት የቱርክ/ግብጽ ገዥዎች ጋር የድንበር ላይ ውጊያ ያካሄዱ ነበር፡፡ ታዲያ በአንዱ ውጊያ ላይ የዘመኑ ዋና መስፍን የነበሩት የራስ ዓሊ ልጅ የሆነችው ወይዘሪት ተዋበች ተማረከች፡፡ ይህም ወሬ ለካሳ ጆሮ ደረሰ፡፡ ካሳ በወቅቱ ሽፍታ ቢሆንም የኢትዮጵያዊያን መሸነፍና በምርኮ መጋዝ በጣም አበሳጨው፡፡ በመሆኑም በቱርኮች ላይ ድንገተኛ አደጋ ጥሎ አተረማመሳቸው፡፡

ካሳ ይህንን ሲያደርግ ተዋበች ምርኮኛ መሆኗ በቁጭት ውስጥ ጥሎአት በመርዝ ጩቤ ሰውነቷን ወግታ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ በማድረግ ላይ ነበረች፡፡ ይሁንና ካሳ በቦታው ደርሶ መርዙ ወደ ሰውነቷ ጠልቆ ሳይገባ ከደሟ ውስጥ መጥጦ ተፋው፡፡ በዚህም የተዋበች ህይወት ተረፈች፡፡ ካሳም ተዋበችን በጀርባው አዝሎ ከውጊያው እየሮጠ ወጣ፡፡ ወታደሮቹም በቶሎ እንዲያፈገፍጉ ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡

ካሳ ነፍሲያዋን ያተረፈላትን ተዋበችን ለአባቷ ለራስ ዓሊ አስረከባት፡፡ ራስ ዓሊም በጀግንነቱ ተደስተው እሷኑ ዳሩለት፡፡ ሽፍትነቱን ትቶ በቤተመንግሥት እንዲኖርም አደረጉት፡፡ ይሁንና የቤተመንግሥቱ ህይወት በነጻነት መኖርን ለለመደው ካሳ የግዞት ያህል ሆነበት፡፡ በዚያ ላይ መኳንንቱ “የኮሶ ሻጭ ልጅ” እያሉ የሚያሳዩት ንቀት በጣም አቃጠለው፡፡ ተዋበችም በባሏ ላይ በሚደርሰው ንቀትና ማሽሟጠጥ በገነች፡፡ እናም በአንድ ውድቅት ላይ “አንተ ካሳ! ጎራዴህን ታጠቅና ተነሳ፤ ምንጊዜም ከጎንህ ነኝ” አለችው፡፡ ካሳም ሸፈተ፡፡
----
እንግዲህ ከላይ የቀረበው ጭውውት ካሳ በሸፈተ በማግስቱ የተደረገ ነው፡፡ በዚያ ቀን በተደረገው ምክክር ደጃች ወንድይራድ የካሳን እጅ ይዞ እንዲመጣ ታዘዘ፡፡ ወንድይራድም ከቤተመንግሥቱ ቀርቦ እየጎረነነ ትዕዛዝ መቀበሉን አረጋገጠላቸው፡፡ ይሁንና የወንድይራድ ከልክ ያለፈ ጉራ ያልጣማቸው ራስ ዓሊ “አንተ ወንድይራድ! ካሳ እንደ ሌላው ሽፍታ አይምሰልህ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው አደገኛ ተዋጊ ነው” በማለት ምክር ቢጤ ቢወርውሩለት ዳጃች ወንድይራድ እንዲህ የሚል የንቀት መልስ ሰጣቸው፡፡

አይስሙ ጌታው ሰው የሚለውን
አያስፈራም ካሳ ይንዛ ጉራውን
ገና መጣ ሲሉት አገር ጥሎ ይሸሻል
ወይንም ካንዱ ደብር ገብቶ ይደውላል፡፡
እንኳን አንድ ሽፍታ ቀማኛ ወንበዴ
ብዙ እመልሳለሁ በጦር በጎራዴ
እኔ ነኝ ወንድይራድ ታማኝ አሽከርሽ
ያን የኮሶ ሻጭ ልጅ የምቀጣልሽ፡፡

የወንድይራድ ፉከራና ድንፋታ ከካሳ ጆሮ ገባ፡፡ ካሳም “እናቴን እንዲህ የሰደበውን ባለጌ ባላሳየው እኔ ካሳ አይደለሁም” በማለት መሃላውን ሰጠ፡፡ ሁለቱ ሀይሎች ተገናኙ፡፡ ውጊያው ገና ከመጀመሩ የወንድይራድ ፉከራ የአሸዋ ላይ ቤት ሆኖ ፈረሰ፡፡ እቴጌ መነን (የራስ ዓሊ እናት) የተመኩበት ዳጃች ወንድይራድም ተማረከ፡፡ ካሳም መሃላውን ተግባራዊ አደረገ፡፡ ወንድይራድን ቀንና ማታ ኮሶ እያጠጣ ገደለው፡፡

ከዚያ በኋላ ካሳ በሀገሩ ላይ ገነነ፡፡ ማን ይቻለው? ደጃች ውቤም ሆኑ ራስ ዓሊ፣ ደጃች ተድላ ጓሉም ሆኑ ደጃች ጎሹ ሁሉም ተራ በተራ ተሸነፉ፡፡ ካሳን ያሸንፋሉ ተብለው የተጠበቁት እቴጌ መነንም በናቁት አማቻቸው እጅ ምርኮኛ ሆነው ወደቁ፡፡ የጥንቱ የቋራ ሽፍታም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ ነገሠ፡፡ ንጉሥ ለስሙ ብቻ ቤተመንግሥት የሚቀመጥበት ዘመነ መሳፍንትም አበቃ፡፡
-----
("የኤርትራ ህልም" በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ ከቀረበው "ጎንደር እንዴት ነሽ" የተሰኘ የኢትኖግራፊ ወግ የተቀነጨበ ነው)።

Wrote by Getu temesgen
#ዝክረ_በዝብዝ_ካሣ (አጤ ዮሐንስ 4ኛ)

ዛሬ ጎጃም ላይ ነኝ ፣ ጎጃም ሆኜ ንጉሱን መዘከር ወደድኩኝና የታሪክ ክስተቶችን ከጎጃሞች ቅኔ አዋቂነት ተወሼ እንዲህ ተነፈስኩኝ።

#ይገለኛል_ይሰቅለኛል_ብሎ_አንድ_ሰው_በሸሸ፣
#መላው_የጎጃም_ህዝብ_እንደ_ጭቃ_ታሸ፤
==============//================
ወቅቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1870ቹ ላይ ነው ፤ በዝብዝ ካሣ ከላስታው ዋግሹም ጎበዜ/ ዳግማዊ ተክለ ጊዮርጊስ/ ንጉሰ ነገስትንትን በጦርነት ተቀብለዋል ፤ በዝብዝ ካሳ ( አጼ ዮሐንስ አራተኛ / ንጉሰ ነገስትነቱን አውጆ ጎንደር ቤተ መንግስት በገባበት ማግስት በየአካባቢው ራሳችን ንጉሰ ነገስት መሆን እንጂ ለአንተ አንገብርልህም የሚሉ የሥልጣን ተጋሪዎች እዚህም እዚያም እያቆጠቆጡ ነበር ፤

ወዲህ #የጎጃሙ ራስ አዳል ( ንጉስ ተክለ ኃይማኖት/ ፣
ከ ወደ ሸዋ ደግሞ #የሸዋው ንጉስ ምኒልክ ቁልፍ ቦታ የተሰጣቸው ነበሩ፤

ይህንንም ተቀናቃኝነት ለማስታገስ ራስ አዳልን ንጉሰ ጎጃም አድርጎ እውቅና ሲሰጥ ፤ ምኒልክንም ንጉሰ ሸዋ በሚለው እውቅና ሰጥቶ ለማርገብ ቢያቅድም ፤ ከጎረቤት ደርቦሾች ጀሃድ አውጀው ኢትዮጵያን ለመውረር ቅድመ ዝግጅታቸውን ጨርሰው በመተማ በኩል እየገሰገሱ ነው ፤ ምክንያቱም ዛሬ ላይ ክንዱ የሚያነደው #የቋራው_ካሣ አለመኖሩን ተረድተዋልና ፤

የሱዳኖችን ጦር እንዲመክት የጎጃሙን ንጉስ ተክለ ኃይማኖትን ንጉሰ ነገስቱ ትዕዛዝ አስተላለፉ ፤ ንጉስ ተክለ ኃይማኖትም ስንቅና ትጥቅ ሸክፎ ወደ ሰሜን ገሰገሰ ፤

የንጉስ ተክለ ኃይማኖት ጦርም በደርቡሾች ላይ ድል ተቀዳጄ ፤ በዚህም የንጉሱ ጦርን ፈርጣማነት በተግባር አሳይቶ ሲመለስ ፤ ደርቡሾች ወደ ኋላ ፈረጠጡ ፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ደርቡሾች አቅማቸውን አጠናክረው ተመልሰው ኢትዮጵያን በመተማ በኩል ወረሯት ፤ ዳግመኛ አጼ ተመልሰው ንጉስ ተክለ ኃይማኖት በደርቡሾቹ ላይ እንዲዘምት ታዘዘ፤

ንጉሱም ሄደ ፣ግጥሚያውም ተደረገ ፣የደርቡሾቹ የበላይነት ተረጋገጠ ፤ የንጉሱ ልጅ ምንትዋብ አዳል ተማርካለች ፣ 12 መኳንንቶች አንገታቸው ተቀልቷል ፤ አሁን በደርቡሾቹ የበላይነት የንጉሱ ሽንፈት ታውቆ ንጉሱ ወደ ጎጃም ተመልሰዋል ፤ ይህ በእንዲህ እያለ ከ3 ዓመታት በኋላ ደርቡሹ እንደገና ሲመጡ ተክለኃማኖት እንዲዘምት ንጉሠ ነገስቱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤

ሆኖም ግን ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ‹ #እኝኛው › ብለዋል ፤ ይልቁንም ከሸዋ ምኒልክ ጋ ምክር ሰንቀዋል ፤ አጼ ዮሐንስ ንጉስ ተክለ ኃይማኖትን ሊወጋ ከመጣ ፤ ምኒልክ በበጌምድር በኩል የንጉሰ ነገስቱን ጦር መፈናፈኛ ሊያሳጣው፤ ትልቁን ባላንጣ ትንንሽ ባላንጣዎች የአሴሩት ሴራ መሆኑ ነው ፤
ሆኖም ግን የአጼ ዮሐንስም ጦር በንጉሱ አዝማችነት ጎጃምን ወረረ፣ ዘረፈ፣ አሰቃዬ ፣ ጎጃምም አምርራ አዘነች ፣ ብሶቷንም በስነ ቃል ገለጸች ፤ ይህ ሲሆን ግን ጠላቴ ነው የተባለው ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ህዝባቸውን ለወራሪ ጦር አንጋለው ጥለው መኳንቶቻቸውን አስከትለው ፣ ስንቃቸውን ሰንቀው
ጅብላና ሞተራ ከተባሉ አምባዎች ወጥተው መሸጉ ፤ ህዝቡ ግን ሜዳ ላይ ለጨካኝ ወታደር ስቃይ ተቀባይ ሆነ ፤

ይህንንም የተመለከተች ሴት ነች ከላይ ያለውን ብሶት በሥነ ግጥም የገለጸችው ፤

ዮሐንስ አራተኛም የጎጃምን ህዝብ በተቻላቸው ሁሉ በዘበዙ ፤ የጎጃምን ጥጋብ ለማብረድ የሚያርስበት በሬ ፣ የሚጠጣው ወተት፣ የሚበላው ቅቤ ና ሥጋ ማሳጣት ያስፈልጋል በሚል ውሳኔ የቀንድና የዳልጋ ከብት ሁሉ ወደ ጎንደር እንዲነዳ ትዕዛዝ አስተላለፉ ፤ አሁን ሁሉም ከብት እየተነዳ ነው ፤

ይህንን ያየች እንዲህም ብላ ተቀኝታለች፡-

// “ #እስቲ_ትንሽ_ቅቤ_የቁስል_የቁስል ፣
#ከብቱ_ከብቱ_ጎንደር_ገባ_የሚካን_ይመስል “//

ወቅቱ የጎጃም ዲያቆን ክህነት ለመቀበል ለወደ ጎንደር ይሄድ እንደነበር ለማጠየቅም ነበር //

ይህ ከሆነ በኋላ አጼ ዮሐንስ ወደ መተማ ከደርቡሽ ጋር
ግጥሚያ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እያሉ ወዳጆቻቸው
ጎጃምን እንደዚህ ማጥፋታቸው ደግም እንዳልሆነ ሲወቅሷቸው እንደ መጸጸት ብለው ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄደው ንስሃ ገብተው የወርቅ ጫማና የራስ ቁር ለቤተክርስቲያኑ ከሰጡ በኋላ ወደ መተማ አቅንቼ ከጦርነቱ ስመለስ ጎጃምን አለማዋለሁ አሉ የሚለውን የሳች ሴትዮ

// #መተማ_ተዋግተው_አጤ_ቢመለሱ ፣
#ምንኛ_ጎልድፏል_ጎጃሜ_ምላሱ //

ብላ በሰላም ከተመለሱ የጎጃሜው ሀዘንና እርግማን ከንቱ ቀረ እንደማለት ተቀኝታለች ፤ የአጤውን ሞት የተመኙበት የጎጃሜዎች ቅኔ መካከልም እንዲህ ይል ነበር ፡-

// #አይ_አጤ_ዮሐንስ_ማማሩ_ባታቸው ፣
#ከኋላ_ቀርቼ_ሲሄዱ_ባያቸው ፤ //

አሁን ደግሞ ህዝቡን ሜዳ ላይ ጥለው ራሳቸውን አምባ ላይ ሸሸገው ከቆዩ በኋላ ንጉስ ተክለ ኃይማኖት የ44 አብያተ ቤተክርስቲያን ታቦታትንና ካህናትን ይዘው አጤ ዮሐንስ 4ኛ ን ይቅርታ ጠይቀው ፣ይቅርታ ከተሰጣቸው በኋላ አጤ ዮሐንስ ወደ መተማ ለደርቡዶች ጋር ግጥሚያ ሊያደርጉ ገሰገሱ ፤

በመጨረሻም አጤ ዮሐንስ መተማ ወርደው አንገታቸው
ተቀንጥሳ በጠላት እንጂ ወድቃ ህልፈተ ህይወታቸው
በመጋቢት መጀመሪያ በ1881 ዓ.ም ጎጃም ላይ ሲሰማ
ንጉስ ተክለ ኃይማኖትም ለአጤው የቀጠሮ ለቅሶ እንዲውል በማወጃቸው በጎጃም ባህል ሰፊ ቦታ እና አስለቃሽ ተመርጦ ቀደም ብለው ገድለውትና ቅሱሙን ሰብረውት የሄዱት ህዝብ ለአጤው ነቅሶ ቆሟል ፤ ከአስለቃሶች መካከል አንዷ ድምጧን ሞረድ ሞረድ አድርጋ እንዲም አለች ፤

//#ቤቴንም_ሳያየው_ሙክቴን_ሳይበላ ፣
#ደሜን_መለሰልኝ_መሐመድ_አብደላ፣
#ልጁን_ይባርክለት_የሚያምንበት_አላ(ህ) ፤ //

ብላ እንደረደረች ፤ አሽቃብጩ ንጉስ ተክለ ኃይማኖትም እርሷ እንድትታሰርና ሌላ አስለቃሽ ቦታውን እንድትረከብ ትዕዛዝ በሰጡበት ቅጽበት ፤ ተተኪዋ አስለቃሽ የዋዛ አልነበረችምና ከፊቷ የቆሙትን ንጉስ ሳይቀር ከምንም ሳትቆጠር ፤

// #እንዴት_ተዘጋጅቷል_ተጠርጓል_መንገዱ፣
#አጤ_በሄዱበት_ንጉሱም_ይሂዱ ፤ //

ብላ የንጉሱን መኖር አለመፈለጓን በአደባባይ ገልጻለች ይባላል ፤ ይህንን ሁሉ ያስቀባጠረኝ አጤ ዮሀንስ አሊያም ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ናፍቀውኝ አይደልም ፤ ይልቁንም ሥነ ቃላችን የነበረውን ሀሳብን የመግለጽና በወቅቱ የነበሩትን የታሪክ ክስተቶችን ለመመልከት ያክል እንጂ ፡፡

ጉዱ ካሳ