Wachemo University Students' Union
21K subscribers
5.12K photos
26 videos
314 files
674 links
"Inform. Engage. Empower."
Official Telegram Channel of Wachemo University Students' Union
Download Telegram
3
3
በህፃናት መብትቶች ዙሪያ በመሠረታዊ መብቶች(Fundamental Rights) ክለብ ለቦቢቾ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የግንዛቤ መስጫና የተማሪዎች ፓርላማ ማጠናከርያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመሠረታዊ መብቶች ክለብ ከህግ ትምህርት ቤት እና ከዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት በሌሎች ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ ሲሰጥ የነበረውን ለቦቢቾ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመብቶቻቸዉ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የተማሪዎች ፓርላማ ማጠናከሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

መምህራን ህፃናት ከሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በተለየ መልኩ ለጥቃት ተጋላጭ እንደመሆናቸው ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን የተለያዩ የግንዛቤ መስጫ ንቅናቄ መድረኮችን ማዘጋጀት ህፃናት ስለመብቶቻቸዉ እንዲያውቁ፣ የጥቃት ዓይነቶችን እንዲለዩና ጥቃት በሚደርስባቸው ግዜ ማን ጋርና ዬት መሄድ እንዳለባቸው ማሳወቅ  ህይወታቸውን ከአላስፈላጊ ስቃይ በመታደግ ነገ ለሀገራቸው አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ገልጸዋል።

እንዲሁም የተማሪዎች ፓርላማ መጠናከሩ ተማሪዎች በጽንሰ ሀሳብ ደርጃ የሚማሩትን እንደ ማስተዳደርን፣ የውክልና ስርዓትን፣ ድሞክራሲንና ሀላፊነትን ወደተግባር ለመቀየር የሚሞክሩበት መድረክ ስለሆነ  ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ከግንዛቤ መስጫ በኋላ መርሃግብሩ ላደረጉት ትብብር መምህራኖችን በማመስገን ተጠናቋል።


#FUNDAMENTAL RIGHTS CLUB
https://t.me/wcuclub
tiktok.com/@fundamentalrightsclub
14🔥2😁1🤔1
#Eid_AlFitr
#Mubarak


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች እንኳን ለ 1447ኛው የኢድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን ።



🇪🇹 ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ
🗓 መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
‎===================
🔗 Telegram | https://t.me/WCUSU
📩 Email 1 | wachemosu@gmail.com
📩 Email 2 | wcusu@wcu.edu.et
📽️ YouTube | https://youtube.com/@wachemosu2026
‎---------------------------------------------------
‎ያጋጠመዎትን ችግር ሪፖርት ለማድረግ፣ ማሻሻያ ለመጠቆም ወይም አስተያየት ለመስጠት ይሄንን Google Form ይጠቀሙ
https://forms.gle/naYWGLaQwjf6K7VKA
39😁3🤔3👍2🔥1
#Notice
#Graduation

ውድ ተመራቂዎች እንኳን ለ16ኛ ዙር የምረቃ ስነ-ስርዓት አደረሳችሁ እያልን መመረቂያ አዳራሽ መግባት የሚቻለው ከጧቱ 12:00- 1:30 ብቻ መሆኑን እንገልፃለን። ከተገለጸው ሰዓት ውጭ መግባት የማይቻል መሆኑን አውቃችሁ በጊዜ እንድትገኙ እናሳስባለን።

Registrar & Alumni Directorate


🇪🇹 ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ
🗓 መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
‎===================
🔗 Telegram | https://t.me/WCUSU
📩 Email 1 | wachemosu@gmail.com
📩 Email 2 | wcusu@wcu.edu.et
📽️ YouTube | https://youtube.com/@wachemosu2026
‎---------------------------------------------------
‎ያጋጠመዎትን ችግር ሪፖርት ለማድረግ፣ ማሻሻያ ለመጠቆም ወይም አስተያየት ለመስጠት ይሄንን Google Form ይጠቀሙ
https://forms.gle/naYWGLaQwjf6K7VKA
😁2422🥰2👍1
#Notice
#GC
#Clearance


Students Social Service Directorate


🇪🇹 ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ
🗓 መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
‎===================
🔗 Telegram | https://t.me/WCUSU
📩 Email 1 | wachemosu@gmail.com
📩 Email 2 | wcusu@wcu.edu.et
📽️ YouTube | https://youtube.com/@wachemosu2026
‎---------------------------------------------------
‎ያጋጠመዎትን ችግር ሪፖርት ለማድረግ፣ ማሻሻያ ለመጠቆም ወይም አስተያየት ለመስጠት ይሄንን Google Form ይጠቀሙ
https://forms.gle/naYWGLaQwjf6K7VKA
😁2217🤔3👏1
ዩኒቨርሲቲው በዕውቀት የበቁ፣ ተወዳዳሪና ሀገር ተረካቢ ዜጎችን በማፍራት ረገድ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል- የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ16ኛው ዙር በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራሞች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 904 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በደማቅ ስርዓት አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ ዳዊት እንደገለፁት፥

ዩኒቨርሲቲው በዕውቀት የበቁ፣ ተወዳዳሪና ሀገር ተረካቢ ዜጎችን በማፍራት ረገድ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለዚህም በንድፈ-ሐሳብና በተግባር የታገዘ የመማር ማስተማር ሥርዓትን በመከተል በዕውቀት የተሻሉ ዜጎችን እያፈራ መሆኑን ነው የገለጹት።

ዩኒቨርሲቲው በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፎች ተጨባጭ የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚጠቁሙ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የግብርና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል እመቤት ሞረዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤
ተመራቂዎች በሀገሪቱ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ ለማፋጠን ዕውቀታቸውን እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው የቀሰሙትን የንድፈ ሀሰብ ዕውቀትና ክህሎት በጥናትና ምርምር በማሳደግ ለራሳቸው፣ለማህበረሰባቸውና ለሀገሪቱ ለውጥ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ እንዳለባቸው እና ሥራ ከመጠበቅ ይልቅ የተለያዩ ሥራዎችን መፈጠር እንደሚገባቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ተማሪ መላኩ ጀማል ከሀዲይሳ ቋንቋና ስነፅሁፍ ትምህርት ክፍል 3.94 ውጤት በመምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን፣ ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ምኩራብ ተስፋዬ 3.93 በመምጣት ከአጠቃላይ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች መካከል አንደኛ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

መጋቢት 12/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.me/Wcuniversity
YouTube-Wachemo
10😁2
4
4