WCU DISCIPLESHIP
1.5K subscribers
54 photos
2 videos
1 file
13 links
ደቀ መዛሙርት ህብረት 📚

-ወንጌልን መመስከር
-በቃሉ እውቀት ማደግ
-ሕይወትን ሚቀይር ህብረት
-ጤናማ አምልኮ
ትክክለኛ ደቀ መዝሙር እውነተኛውን እየሱስን አውቆ የሚከተልና ሌሎች ክርስቶስን ተከታዮችን የሚያፈራ ነው።

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው.."
ማቴ 28:19
Download Telegram
"ፀጋ ተግሣጽም  እንዲሁም አስተምህሮ አዘል ነው። ከኃጢአት እርግማን የሚቤዠን ብቻ ሳይሆን ኃጢአትን እንድንተውም ያሠለጥነናል።"
   C.Spurgeon

@wcudisciple
🥰65🔥1👏1
ክርስቶስ ኢየሱስን ማወቅ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅ ደግሞ ለሕይወታችን መሠረታዊና ወሳኝ መሆኑ አይታበልም። “የተሠራነው ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን ለማወቅ። በሕይወት ውስጥ ምን ዓላማ ሊኖረን ይገባል? እግዚአብሔርን ማወቅ። ኢየሱስ የሚሰጠን የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? እግዚአብሔርን ማወቅ። በሕይወት ውስጥ ከሁሉ የተሻለው ምርጥ ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔርን ማወቅ። ከሰዎች እግዚአብሔርን የሚያስደስተው የትኛው ነገራቸው ነው? እርሱን ማወቃቸው በዚህ ምድር የምንኖርበት ዐቢይ ምክንያት እግዚአብሔርን ለማወቅ መሆኑን ስናስተውል አብዛኞቹ የሕይወት ችግሮች  ቦታ ቦታቸውን  ይይዛሉ።እናም እግዚአብሔርን ለማወቅ ካልፈለግን የምንጓዝበትን አቅጣጫም ሆነ የዙሪያ ገባውን ምንነት ሳናይ ዐይናችን ታስሮ በሕይወት ጐዳና ዕውር ድንብራችንን እንተራመሳለን።እግዚአብሔርን ማወቅ ግን ይቻላል፤ የሚታወቀው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው (ዮሐ 1፥14፥18)።
   
       ጳውሎስ ፍቃዱ፣"የእግዚአብሔር ልጅ"
@wcudisciple
13
የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ ቤተሰብ። በዚህ channel  ላይ አገልግሎታችንን እየተካፈላችሁ  ስላላችሁ  ደግሞም ስለምታበረታቱት እጅግ ደስተኞች ነን።

በዚህ ሳምንት አድስ ተከታታይ  ፁሁፎችን  እናቀርብላቸዋለን።  ከዚህ ቀደም  "ነገረ ክርስቶስ"  በምል ርዕስ    አቅርበን ነበር።  በዚያውኑ መልክ አሁን "መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ"  በምል ርዕስ እንማማራለን።  ይህንን  ማስታወቂያ ለሌሎች በማጋራት አገልግሎታችንን  እንድትደግፉን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።
 
@wcudisciple
17👏1
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ |Sola scriptura |
ክፍል አንድ
መግቢያ

የሚያምነውን የማያውቅ እመን ባይ በዛ፥ የእውነትና የሀሰት ድንበር ደበዘዘ፥ በየአደባባዩ ጩኸት አዋክቦናል ታዲያ በዚህ በወከባው ዘመን ምን እንመን!? ማንንስ እንመን!? የዘመኑ ንፋስ ስለነካካን ህይወታችን(አኗኗራችን) በየጊዜው ይለዋወጣል፤ እውነተኛ ጽኑ መልክ አጥቶ መለዋወጥ መገለጫው በሆነ ትውልድ መካከል እንዴት እንኑር!? ተግባራዊ ምላሽ የሚሹ የክርስትያን ሁሉ ጥያቄ!

የእግዚአብሔርን ሀሳብ የሰው ሲውጠው፤ የአምልኮ ስርዓት በሰውኛ እሳቤ ሲገዛ፤ እውነት ስፍራ ሲታጣ ሐሰት ሲነግስ፤ የእውነተኛ አምላክ አገልጋይ ቤተ ክርስቲያን ከእውነት ይልቅ ስህተት ሲሆን መገለጫዋ፤ ብርሃን ሲደበዝዝ፤ ክርስትና ሕይወት አልባ ሙት ሃይማኖት ብቻ ሲሆን፤ ሕዝቤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ደም ያገኘውን 'የኃጢአት ስርየት በኩፖን'(indulgence) ስሸጥ ያለው ለሙቱና ለሕያው ሲሸምት፤ የሌለው በኃጢአት ክስ ኩነኔ ሲዘፈቅ፤ የበላይ ገዦችና ጳጳሳት ሀብት ሲያድግ ድሃው በድህነቱ ሲማቅቅ ማን እኔ አለው ይበል? 'እኔ አልሳሳትም፥ የበላይ ገዥ ነኝ' ሚለውን የሚገዛ ስህተት አልቦ ፍጹም ገዥ ይኖር ይሆን? ለአምልኮ፥ ለአስተምህሮ ክርስትና እንዲሁም ለክልስቲያናዊ አኗኗር ማን የበላይ ገዥ ፥ መንገድ ጠቋሚ ብርሃን ነው? ቤት አስተዳዳሪው(ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ....) ከተሳሳተ ማን ይሁን ልኩ? ማንስ ይሁን የበላይ ገዥው?

ይህ የመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጥያቄ ነበር። በእርግጥም የክርስትናን እምነትና አኗኗር የሚገዛና የሚመራ የበላይ ስህተት አልባ በራሱ በቂና ብቁ የሆነ ባለሥልጣን አለ! የሚል ነበር የሓዳሲያን አቋምና መፈክር። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ፣ ባለሥልጣን፣ ግልጽ፣ አስፈላጊ፣ እንዲሁም ለእምነትና ለሕይወት በቂ ነው። ክርስቲያኖች ምን ማመን እንዳለባቸው እና እንዴት መኖር እንዳለባቸው የሚወስነው የእግዚአብሔር የመጨረሻው ባለሥልጣን ቃል ነው (2 ጢሞቴዎስ 3:16–17፤ 2 ጴጥሮስ 1:20–21)።
ከሁሉ የበላይ የሆነ ስልጣኑንም በምንነቱ(የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ)፥ ከማይሳሳት አምላክ የመነጨ ስህተት አልባ መጽሐፍ ነው።

ሓዳሲያንም ይህን እውነት በማጉላት ሰውኛ ጭማሪዎችን በአደባባይ ተቃወሙ። ከቤተ ክርስቲያን መባረር፥ እንደ መናፍቅ መወገዝ ገፋ ሲል ሌላ ኃይማኖት መመስረት ዓላማቸው አልነበረም። ለእውነት ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት እንጂ። እንደ መፈከር በአደባባይ የተገለጠው "ጽድቅ በእምነት ብቻ" የሚል ቢሆንም ውስጥ ውስጡን ተሃድሶን ሲያጋግል የነበረው " መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" የሚል ነበር።
እንግዲህ እውነት ሲበረዝ አስተምህሮአችንን ሆነ ልምምዳችንን የምንዳኝበት የእውነት መለኪያ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ በሓዳሲያን ዘንድ ይታመናል፥ ይህም እውነት በየዘመኑ የተሃድሶ ምክንያት ሆኖ አለ ይኖራል።

🀄ጥላል...

@wcudisciple
13🔥4🥰2
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura |

ክፍል ሁለት

'መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ' ስንል ምን ማለታችን ነው? ምንስ ማለታችን አይደለም?
እዚ'ጋ መሰመር ያለበት እውነት ትልቁ ጥያቄ 'ማን ይገዛናል?' ሳይሆን 'ማን የሁሉ በላይ ገዥ ነው?' የሚል ነው። በጣም ግልጥ ስናደርገው ከመጽሐፉና ከትውፊቱ/ጳጳሱ/ቤተክርስቲያን አስተዳደር/በኋላው ዘመን ከተነሱት ቅዱሳን ሀሳብያን፥ ማን የሁሉ በላይ ገዥ ነው? የሀሳብ ልዩነት ከተገኘ በሁለት እኩል ባለሥልጣናት መመራት ስለማይቻለን ። ተቃርኖ ብገኝባቸው የቱ ልታመን ይገባዋል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነውና።
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስንል የቤተክርስቲያን ትውፊት፥ ጉባኤያት፥ የቤተክርስቲያን ስልጣን አለመቀበል፥ የተሳሳቱ ግላዊ ፍታቴን እያበረታታን ሳይሆን ነገር ግን እነዚህ ልሳሳቱ የሚችሉ ሲሆን ሁሉም በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን አለባቸው እያልን ነው። እንዲሁም ለስልጣኑም መገዛት አለባቸው የሚል ይሆናል።
“መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” ተሐድሶ አድራጊዎቹ፣ ከጳጳሱ የማይሳሳት ነው ከሚለው የይገባኛል ጥያቄ እና በቤተ ክርስቲያን አባቶች ጽሑፎች እንዲሁም በቃል በሚተላለፉ ትውፊቶች ውስጥ ከሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥልጣን የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን መለየታቸውን አመላካች ነበር።

ቃሉም ከራሱ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ በመሆኑ፣ ሊፈርድበት የሚችል ከእርሱ በላይ የሆነ ምንም ዓይነት ሥልጣን ወይም ሊገዛለት የሚገባው መመዘኛ የለም! እርሱ ራሱን በራሱ የሚያረጋግጥ፣የመዳን እውነትና ዕውቀት የሞላበትና ፍጹም ስህተት አልባ ነው። ሌሎቹ መመዘኛዎች ወይም ሥልጣናት ሁሉ ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ሲታዩ አንጻራዊ ናቸው (መዝ. 138:2፤ ኢሳ. 46:9-11፤ ማቴ. 24:35፤ ዕብ. 1:1-3)።

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16
¹⁶ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ቅዱሳት መጻሕፍት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡት እንደሚችሉ ያስታውሰዋል (3:15)። እርሱም ቅዱሳት መጻሕፍት ለትምህርት፣ ለተግሣጽ (ለመውቀስ)፣ ልብን ለማቅናትና በጽድቅም ለመኮትኮት (ለመምከር) ጠቃሚ እንደሆኑ ያስተምራል (3:16)። ቅዱሳት መጻሕፍት ይህ ባሕርይ ስላላቸው፣ የእግዚአብሔር ሰው ለበጎ ሥራ ሁሉ ፍጹም ሆኖ እንዲዘጋጅ ያደርጉታል (3:17)። ለዚህ ተግባር በቂም ብቁም ነው።


መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ የሚስማማና የማይቃረን ነው። እርሱ የእግዚአብሔርን የእውነት ዕውቀት፣ ባሕርይና ማንነት ያንጸባርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ የተነፈሰበት(inspired) ቃል ስለሆነ፣ ሥልጣን ያለው በመሆኑም የማይሳሳት ነው።

🀄ጥላል...

@wcudisciple
14🔥2👍1
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura |

ክፍል ሦስት

ይህ የሓዳሲያን መፈክር ከመጽሐፍ ቅዱስ ስሙም መሆኑን (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን) እንቃኝ።

አስቀድመን ከሁሉም ይልቅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱሳት መጻሕፍት አጠቃቀም ትኩረት ሰጥተን ካጠናን ይህንኑ የመጽሐፍ ቅዱስን የበላይነት የምያስጠብቅ ትምህርት እናገኛለን። ጌታችን በስጋ ከአብርሃም ቤት ስለሆነ በዘመኑም ይህን የአይሁዶችን መጽሐፍ (ብሉይ ኪዳንን) ጠቅሶ ስያስተር ይስተዋላል። እንደ ምሳሌም ጌታችን በምድረ በዳ ከፈታኙ የቀረበለትን ፈተና "ተብሎ ተጽፏል" በማለት ስመልስ በእርግጥም ከሚሰማን ስሜትና ግላዊ አመክንዮ ይልቅ ለእግዚአብሔር ቃል ስፍራ መስጠቱ የመጽሐፍ ቅዱስ የበላይነትን አጉልቶ ያሳያል።

ይበልጥ ቀረብ ስንል ደግሞ በጌታችን በምድር ቆይታው ወራት ከቅዱሳት መጻሕፍት ይልቅ ለሽማግሌዎች ወግና ትውፊት የላቀ ስፍራ የሰጡትን የእግዚአብሔርን ቃል የናቁትን ፈሪሳዊያንን እንዲህ ሲል ይወቅሳችኋል:-
የማርቆስ ወንጌል 7:8-13
8፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።
9፤ እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።...
13፤ ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።


ኢየሱስም ሆነ ሐዋሪያት ትምህርታቸውን ለመጽሐፉ ማህበረሰብ(ለአይሁዶች) ለማስረዳትና እውነትነቱን ለማረጋገጥ ከሕግ፥ ከነቢያትና ከመዝሙራት ያጣቅሱ ነበር። ማቴ 2፡17,18 የሐዋ 2፡16 ሮሜ 3፡10 እንደ ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን።

ሌላው ሐዋሪያትም በዘመናቸው በጎውን ክርስቲያናዊ ወግ እንድንይዝ ብያስተምሩንም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ስሙም ያለሆኑትን በአደባባይ እንድንቃወማቸው መክረውናል አስጠንቅቀውናል።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡8
"፤ እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።"

ወደ ቲቶ 1:13
፤ ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።


ይልቁንም ለቃሉ እውነት እጅጉን እንድንጠነቀቅና እንድንጠብቀው ይመክሩናል።
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:19 (NASV)
¹⁹ እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።



ይቀጥላል...

@wcudisciple
13🥰1
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" |Sola scriptura |
ክፍል አራት

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ፪:፲፭
---
፲፭፤ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።


ሁሉም “ትውፊቶች” እኩል ሚዛን የላቸውም። ጳውሎስ ራሱ ልክነት የጎደላቸውን ትውፊቶችን አውግዟል (ለምሳሌ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያፈርሱ የሰዎችን ትእዛዛት፤ ቈላ 2፡8)። የአዲስ ኪዳን ትውፊት በሐዋርያዊ መመሪያ (ደንብ) መፈተን እንዳለበት ያመለክታል። ትውፊቱ እውነተኛና ጠቃሚ የሚሆነው ሐዋርያዊውን ቃል ሲያንጸባርቅና ሲያስተላልፍ ነው፤ ነገር ግን ልክነቱን መዛኝ የመጨረሻው ፈራጅና ወሳኙ ሥልጣን ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ናቸው።
ሌላው ደግሞ፣ አንድ ትውፊት ሊጠበቅ (ሊያዝ) የሚገባው መሆን አለመሆኑን ሙሉ በሙሉ የሚወሰነው በዚያ ትውፊት የየራሱ ባሕርይ ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ትውፊቶች አብረው ሊጠበቁ አይችሉም፤ ስለዚህም ከተጻፈው ትውፊት (ማለትም ከቅዱሳት መጻሕፍት) ጋር የማይስማማ “በቃል የሚተላለፍ” ማናቸውም ትውፊት የተኮነነ (የተወገዘ) ይሆናል።

የአንድነት ጉዳይ
በካቶሊኮችም ሆነ በኦርቶዶክሶች የሚታመነው እሳቤ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች መከፋፈልና አንድነት ማጣት (denominational variation) ምክንያቱ ይሄው "የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ትምህርት ነው ብለው ይከሱናል። ይህ ክስ እነርሱንም መልሶ የሚነካ ክስ ቢሆንም ቅሉ።
እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ላንሳ
አንደኛ ተሓድሶን የአንድ ሰው (ሉተር) እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በሉተር የተጀመረው ሉተራዊነት፤ በጆን ካልቪን ሲመራ የነበረው ካልቪናዊነት ፤ በዝዊንግሊ የሚመራው የዳግም መጥመቂያዊያን እንቅስቃሴ ፤ በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የተነሳው ተሓድሶ ማለትም አንግሊካን እንዲሁም በራሷ በካቶሊክ የተደረገው ተሓድሶም ይጠቀሳል። ገና ከጅምሩም በፕሮቴስታንት ሓዳሲያን ዘንድ በአንዳንድ ጉዳዮች የተለያየ አመለካከት ነበራቸው በሚበዙት ብስማሙም። አንድ የሚያደርጋቸውም የሮማ ካቶሊክ ስሁት ልምምድን በአንድነት መቃወማቸው ነበር።
ሁለተኛ የአንድነታችን/የህብረታችን መሰረት እውነት መሆን አለበት። የክርስቶስ ቤተክርስትያን እውነትን ለዓለም እንዲትገልጥ ብርሃን የሆነች እንጂ ከሀሰት ጋር የምትስማማ አይደለችም። እውነት ላይ በተመሰረተ ህብረት የጌታ በረከት አለ። እውነት ተረግጦ አንድነት ገዳይ ነው።

ይቀጥላል...

@wcudisciple
❤‍🔥72🔥1
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ |Sola scriptura|

ክፍል አምስት

ቀኖና እና አዋልድ መጻሕፍት (አፖክሪፋ)

ቀኖና
“ቀኖና” የሚለው ቃል “ሕግ” ወይም “መመዘኛ፥ መለኪያ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን፣ ይህም ለእምነትና ለሕይወት መለኪያ ወይም መስፈርት መሆኑን ያሳያል። አንድ መጽሐፍ ቀኖናዊ ለመባል ከሚያስፈለጉት መስፈርቶች መካከል ጽሑፉ በነቢይ፣ በሐዋርያ ወይም ከሁለቱ በአንዱ የቅርብ ባልደረባ የተጻፈ መሆን አለበት። ስለ ቀኖና ሊታወስ የሚገባው በጣም አስፈላጊው ነጥብ፦ መጻሕፍት ቀኖና አካል ተደርገው የታወቁት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስለተጻፉ(የእግዚአብሔር ቃል ስለሆኑ) እንጂ፣ ቀኖና አካል ስለተደረጉ የእግዚአብሔር ቃል አልሆኑም። ማለትም ቤተ ክርስቲያን ቀኖናውን እራሷ አልፈጠረችውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አስቀድሞ የጻፋቸውን መጻሕፍት ለይታ አወቀች (ተቀበለች) እንጂ። ቀኖናው ለክርስቲያናዊ ትምህርትና ለሕይወት ሙሉ እና የመጨረሻው ባለሥልጣን ሆኖ ያገለግላል። ሉቃስ 24:44፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16–17፤ ይሁዳ 3።

የብሉይ ኪዳን ቀኖና
የብሉይ ኪዳን ቀኖና በዕዝራ (5ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ዓ)፣ በዮሴፍስ (95 ዓ.ም)፣ በ2ኛ ዕዝራ 14 (100 ዓ.ም) እና ጃምንያ (ያምንያ) ጉባኤ (70-100 ዓ.ም) ጸድቋል። ኢየሱስም በሉቃስ 11:51 ላይ “ከአቤል ደም ጀምሮ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ” ስላለ የአይሁድን መጻሕፍት ወሰን አረጋግጧል። የአቤል ግድያ በዘፍጥረት የተመዘገበ ሲሆን፣ የዘካርያስ ግድያ ደግሞ በአይሁድ የመጻሕፍት አደረጃጀት መሠረት የመጨረሻው መጽሐፍ በሆነው በ2ኛ ዜና መዋዕል 24:20 ላይ ይገኛል። ስለዚህ ይህ የኢየሱስ አገላለጽ ለእኛ “ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ” እንደማለት ነው። የፕሮቴስታንት ብሉይ ኪዳን በይዘቱ የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚከተል ቢሆንም፣ የመጻሕፍቱ ቅደም ተከተል ግን ይለያያል።

የሐዲስ ኪዳን ቀኖና
የሐዲስ ኪዳን ቀኖና በሐዋርያት ወይም በቅርብ ባልደረቦቻቸው አማካኝነት ከ45 ዓ.ም እስከ 95 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የተጻፉ 27 መጻሕፍትን ይዟል። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን መጻሕፍት የተቀበለቻቸው ሐዋርያዊ መነሻ ያላቸው፣ በውስጣቸው ባለው ትምህርት የታመኑ፣ በምዕመናን ዘንድ በሰፊው ተቀባይነት ያገኙ እና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በግልጽ ያሳዩ ስለነበሩ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች ለእነዚህ መጻሕፍት ሥልጣንን አልሰጧቸውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ የነበራቸውን መለኮታዊ ሥልጣን በይፋ እውቅና ሰጡ እንጂ።

አዋልድ መጻሕፍት (አፖክሪፋ)
አፖክሪፋ (Apocrypha) ከ300 እስከ 100 ዓ.ዓ ባለው ጊዜ ውስጥ ለተጻፉ 15 “የተሰወሩ” መጻሕፍት የተሰጠ ስም ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ በ1546 ከተካሄደው የትሬንት ጉባኤ (Council of Trent) ጀምሮ ከእነዚህ ውስጥ 11ዱን እንደ ቅዱሳት መጽሓፍት አካል አድርጋ ትቀበላለች (ከ1ኛ እና 2ኛ ዕዝራ እንዲሁም ከምናሴ ጸሎት በስተቀር)። መጻሕፍቱ እራሳቸው በመለኮታዊ መንፈስ መመራታቸውን አይናገሩም፣ እንዲሁም ምንም ዓይነት ትንቢት አልያዙም፤ በዚህም ምክንያት በሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኙም (ምንም እንኳ ይሁዳ 14 እና ዕብራውያን 11:35 በተዘዋዋሪ ቢጠቅሷቸውም)። መጻሕፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሉይ ኪዳን አካል ሆነው የታዩት በሰባ ሊቃናት ትርጉም (ሴፕቱአጀንት - 3ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ዓ) ላይ ቢሆንም፣ ከ700 ዓመታት በኋላ በጄሮም ቩልጌት (Vulgate) ትርጉም ላይ እስኪካተቱ ድረስ በማንኛውም የቀኖና ዝርዝር ውስጥ አልታዩም ነበር። ጄሮም (340-420 ዓ.ም) እነዚህን መጻሕፍት ከ“ቀኖናዊ” ይልቅ እንደ “የቤተ ክርስቲያን ንባብ” (ecclesiastical) መጻሕፍት አድርጎ ፈርጇቸዋል።

@wcudisciple
5❤‍🔥4🥰2🔥1
ማቴዎስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።
²⁴ እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።
²⁵ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት።
²⁶ እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
²⁷ ሰዎቹም፦ ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ።

"ሥራህን አስቤ ሳይሆን መኖርህን አስቤ ልመንህ!
የተገለጠውን የእግዚአብሔር ስራ  እያዩ እምነትን ማጣት፤ የእግዜርን መኖር  በጭፍንነት መካድ ያለንበት የአሁን  ዘመን  ትውፊት ከሆነ መሰንበቱን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ነገር  ነው።
እግዚአብሔር ሲሰራ እያየን ማመን በከበደበት ዘመን ቆመን  ይበልጡን  በሰው ሚዛን "እግዜር የለም .... ፀጥ አለ!"  በሚባልበት ሰዓት በዝምታው ውስጥ መኖሩን በማሰብ ወዳለው እምነት ማደግ ምንኛ መታደል መሰላችሁ..... ከማዕበሉ ጩኸት ጋር መስማማት በሚቀልበት በዛ ሰዓት ከእግዚአብሔር ዝምታው ስር በእምነት መቆየት፤በሰውኛ ልክ ከሚመስሉ ጩኸቶች፣ ማያስተርፉ ከሚመስሉ ነፋሳት ይልቅ፣ ልክ ከማይመስለው ግና የልክነትን ሚዛን ከሚሰብረው፣ የነገ ምስጋና ከሚሆነው ዝምታህ ጋር መተባበር ወዳለው እምነት ማደግ፤ ዝምታው ውስጥ ካለው መሰራት በኋላ ያለውን የጌርጌሴኖን ስራ  ገብቶት መፅናት ሚችልበትን እምነት የለበሰ ሰው ምንኛ ታደለ.......
ጌታ ሆይ...ለአብሮነትህ ዋስትና ስራህ አይሁነን!.... የእጂህ ላይ  ሳይሆን የፋትህ ብርሃን ላይ ቀልባችን እንዲያርፍ... በአብሮነትህ ውስጥ ስራህን እንይ። ስራህ አብሮነትህን ሳይሆን አብሮነትህ ስራህን ይጠቁመን። .....አልያማ ያልሰራህ የመሰለኝ ቀን፣ ዝም ያልከኝ ቀን፣ ማዕበሉ ያገላበጠኝ ቀን እንገዳገዳለው። እምነቴን ስራህ ላይ ሳይሆን አብሮነትህ ጋር አርገው። ማዕበሉን ፀጥ ታስብላለህ ብዬ ሳይሆን በማዕበሉ ውስጥ አብረኸኝ ነህ ብዬ ልመንህ ........
ያኔ አልንገዳገድም .... ከጩኸቱ ጋር አብሬ አልጮህም፤ ለጩኸቱ ጩኸት አላዋጣም። ዝምታህ እኔን መያዝህን አይጋርድብኝ፤ .....ስጠፋ አይገድህምን አልለውም፤ ስደቢው ከሚሉት ጋር አልተባበርም፤ብድንም ባልድንም ማለት አይከብደኝም! አብሮነትህ ሲቀድምልኝ፤ መታመኛዬ አብሮነትህ ጋር ሲሆን አይኔን ካንተ አልነቅልም ! ያኔ... ለምን ማለቴ ይለየኛል ።
እምነቴ ዝምታህ በማይገታው አብሮነትህ ላይ እንጂ ዝም ያልክ ቀን በሚጋረድብኝ (እያለ በማላየው) ስራህ ላይ አይሁን......ዝም ስትል እንኳ የኛ አባት አንተ አዋቂ ነህ ለዝምታህ አትታረምም!!ለዝምታህ በአብሮነትህ ታምነን አሜን ካለማለት እኛን አርመን እንጂ!!
ከዝምታ በኋላ ያለውን ስራህን ሳይሆን በዝምታ ውስጥ ያለኸውን አንተን ልመንህ!!
🤲🤲🤲🤲🤲አሜን

@wcudisciple
4❤‍🔥2🔥1
ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤
መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?
መዝሙር 42፥2

እግዚአብሔር ቸር ነው ። ከእጁ እንኳን ፃድቁ፥ ሀጥኡ ዝናብን እና ፀሀይን ተችሯል። አበቦች ሳይፈትሉ በምድር ደምቀው ታይተዋል። የሰማይ ወፎችም ሳይዘሩ ሳያጭዱ ከጥጋብ አልተለዩም። የሰማዩ ጌታ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል።  ጌታ ግን ለምርጦቹ ከነዚህ ፍጥረት አብልጦ ያደርግላቸዋል ። ይሁንና ከቁስ ማትረካ ነፋሳችን  በነዚህ እረፈት የላትም። ያለንበት ከንቱ አለም በጥም  ያንገላታናል፤የጠሉን እልፈ ናቸው። ለነዚህ መጮህ ስህትት አልነበረው። ሆኖም በአምላክ  ፍቅር ለተጠመደ ሰው   የእግዚአብሔር ፍት ከሁሉም የከበረ ሀብቱ ነው።  ምንም እንኳን በዚህ አለም ተዝለፍልፈን ብንታይም  በዛለው ስጋችን ውስጥ ሆነን በድንግዝግዝ ባየነው ተስፋን አግንተናል።  በልጁ ወንጌል ክብሩን  እንዳየን ደግሞም በሙላት ፍቱን ልናይ እንናፍቃለን።

ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤ ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
2 ቆሮንቶስ 5፥6-7

አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።
1 ቆሮንቶስ 13፥12

@wcudisciple
❤‍🔥93🔥2🥰1🤔1
የሰው ምኞት ገደብም እንዲሁም መዳረሻም አልባ ነው። እልፍ እያሰበ አዕምሮውን ሲያደክም በምኞትም ብዛት ልቡን ስያዝል ይኖራል። ሰው መናገር ከሚችለው በላይ ነገሮች ሁሉ አድካም ናቸው። ዐይኑ ከማየት አይጠግብም፤ ጆሮም በመስማት አይሞላም። እጅጉን ስር የሰደው እንዲሁም ልታወቀን ያልቻለ በቃኝ ያለማለት የማግበስበስ አባዜ ተጠናውቶታል። የባለጠጋ የመደኸየት ስሜት፣ጥጋብ ያልገታው ረሀብ፣ሙላት ያልያዘው ጉድለት ....ወዘተ የዘመናችን ትውልድ መልክነው።ዘመንተኛም ብቻ አይመስልም የጥንትም ነው።ከገነት እልፍ ዛፍ እና ፍሬዎች ይልቅ የተከለከለችውን አንዲቷን ዛፍ መጎምጀት የሰው የጅማረው መሰናክል ነበር።
እኛም አማኞች የዚህ ነገር ሰለባ ሳንሆን አንቀርም።ባለን ነገር አለመርካት የዘውትር  የነፍሳችን ዝለት መነሻም ሆኖ ይሆናል ። 
ነገር ግን ጳውሎስ  ለጢሞቴዎስ እንዲህ ይለዋል፦
ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው። ምክንያቱም ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለም፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም። ነገር ግን ምግብና ልብስ ካለን፣ ያ ይበቃናል። ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ። ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።
1 ጢሞቴዎስ 6፥6-10

 ጌታ ሆይ እንደ ሰደደ እሳት ገደብ ካጣ ምኞት አድነን፤ወደ መፍረስና ወደጥፋት ከሚያዘቅጠው ከብዙ ከንቱ እና ክፍ መጎምጀት ውድቀት አድነን፤የበቃኝን ህይወት ባለን ነገር መርካትን አስተምረን፤ይህም እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለበት ትልቁ ትርፍችን ነውና!!    አሜን!!

@wcudisciple
12❤‍🔥2🔥1