ስንዴ #ከውጪ ገዝቶ ለማስገባት የጨረታ፤ የዝግጅት እና የትራንስፖርት ጊዜን ጨምሮ ማዕከላዊ ገበያ ላይ ለመድረስ አመት ሊፈጅበት ይችላል! ነገር ግን ጠንክረን ብንሰራ በብዙ ክልሎች ስንዴ በአመት ውስጥ 3ቴ ማምረት የምንችልባቸው ብዙ #እድሎች አሉን!
#በምግብ_እራስን_መቻል አስፈላጊነት ላይ ግን የእውነት የጋራ ስምምነት አለን?

አፍሪካ ከቅኝ ገዢዎቻ ነጻ መውጣት ከጀመረችባቸው 1956 ጀምሮ እስከ 2001 ማለትም በ45 ዓመታት ውስጥ 80 የተሳኩ የመንግስት ግልበጣ እና 247 ያልተሳኩ ወይም የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎችን አድርጋለች፡፡
አፍሪካ ላለፉት 11 ዓመታት ማለትም ከ2010 ወዲህ ብቻ 12 የተሳኩ የመንግስት ግልበጣዎች እና 30 ያልተሳኩ የመንግስት ግልበጣ ሙከራዎች በድምሩ 42 መፈንቅለ መንግስት እና የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አስተናግዳለች፡፡
#ለምሳሌ፡- ቡርኪና ፋሶ በ11 ዓመት ውስጥ የዛሬ ሳምንት የተሳካ የመንግስት ግልበጣ እና 2 ሙከራ፤ ማሊ በ11 ዓመት ውስጥ 3 የተሳካ የመንግስት ግልበጣ እና አንድ ሙከራ (2012፤ 2020፤ 2021 (በዓመት ሁለት ጊዜ)፤ ሱዳን በ11 ዓመት ውስጥ 2 የተሳካ የመንግስት ግልበጣ እና 2 ሙከራ (2021 በአንድ ወር ውስጥ ሙከራም የመንግስት ግልበጣም አከናውናለች)፤ ሌሎቹ የተሳካ መፈንቅለ መንግስት ካከናወኑት መካከል ኒጀር፤ ሊቢያ (ሂደቱ የቀጠለ ግልበጣ)፤ ዝምባብዌ፤ ግብጽ እና ጊኒ ናቸው፡፡
ለንጽጽር ላለፉት 11 ዓመታት #በእስያ 4 የተሳኩ የመንግስት ግልበጣ ተደርገዋል! ማለትም የመን 2 ጊዜ፤ ታይላንድ እና ማይናማር አንድ አንዴ እንዲሁም 2 የግልበጣ ሙከራ ቱርክ እና ባንግላዲሽ ሲሆኑ #በአውሮፓ ባለፉት 11 ዓመታት ሞንተኔግሮ አንድ ሙከራ፤ #በላቲን_አሜሪካዋ በኢኳዶር አንድ ሙከራ ብቻ ነው የተከናወነው፡፡
#ለምሳሌ፡- ከአትዮጲያ በስተቀር አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከአውሮፓ ቅኝ ገዢዎቻቸው በአንጻራዊነት ነጻ የወጡት (አብዛኛው ሀገር ቀጥተኛ ባይሆንም እስካሁን በተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት ውስጥ ነው!) 1960ዎቹ ጀምሮ በርካታ የመፈንቅለ መንግስት እና የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በትጋት አድርገዋል! ይህ ማለት #የፖለቲካም ሆነ #የኢኮኖሚ ተቋም ለመገንባት የሚሆን ጊዜ አልነበራቸውም፡፡
መንግስታትን በሃይል መለወጥ ወይም መፈንቅለ መንግስት በብዙ የዓለማችን ሀገራት ከሺ ዓመታት በፊት ነበረ ልማድ ነው! #ለምሳሌ፡- ጃፓን የመጀመሪያው የመንግስት ግልበጣ ያደረገችው የዛሬ 1566 ዓመት ሲሆን በታሪኳ 16 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት አድርጋለች ነገር ግን የመጨረሻውን ሙከራም ሆነ ግልበጣ ያከናወኑት የዛሬ 52 ዓመት ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- አሜሪካ በታሪኳ 10 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ 88 ዓመት ነበር፤ ስፔን በታሪኳ 36 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ 37 ዓመት ነበር፤ ኢራን በታሪኳ 25 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ 42 ዓመት ነበር፤ ፈረንሳይ በታሪኳ 17 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ 60 ዓመት ነበር! ይህ የሚያሳየው ተቋማትን የመገንባት ሙከራቸው ለረጅም ዓመታት ከዚህ ሁኔታ አርቋቸዋል፡፡
#ለምሳሌ፡- ኢትዮጲያ ላለፉት 121 ዓመታት 6 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻ ሙከራዋ 2019 ነበር (የአማራ ክልል አመራሮች የሞቱበትን ወቅትን የመጨረሻ ብሎ ጥናቱ ይቆጠራል)፤ ቡርኪና ፋሶ በ60 ዓመት ውስጥ 11 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ ሳምንት ነው፤ ሱዳን በ60 ዓመት ውስጥ 10 ጊዜ ሙከራም የተሳካም መፈንቅለ መንግስት ስታደርግ የመጨረሻዋ የዛሬ 2 ወር ነው፤ ወዘተ፡፡
አልጀዚራ ከዚህ ቀደም ዋቢ ባደረገው ጥናት አፍሪካ አህጉር ወስጥ ከ1960 እስከ 2000 ብቻ በየዓመቱ በአማካይ 4 መፈንቅለ መንግስት ይደረግባታልም ይሞከርባታልም ብሏል፡፡ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ብቻውን ባይሳካም በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ውድመት የሚያስከትል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
Why Nations Fail መጽሃፍ ሀገራት ድሃ የሚሆኑበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ ዋናው ምክንያት በሰዎች በሚፈጠር #የፖለቲካ እና #የኢኮኖሚ ተቋማት ሁኔታ ነው! ድህነት የሚመጣውም የሚባባሰውም ብሏል! ስለዚህ አፍሪካ በመንግስት ግልበጣ ተጠምዳ ሃብቷና ለመጠቀምም ሆነ ተቋማትን ለማጠናከር የሚሆን አቅም መፍጠር ተቸግራለች፡፡
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ሲጀመር ጊኒ፤ ማሊ፤ ሱዳን እና ቡርኪና ፋሶ መፈንቅለ መንግስት ካደረጉ የወራት እድሜ ይዘው ነው! 14 አባል ሀገራት ለህብረቱ የሚገባቸውን መዋጮ ባለመክፈል ማስጠንቀቂያ አለባቸው (60 ከመቶ የህብረቱ በጀት ድጎማው ከዓለም አቀፍ ተቋማት ነው! ዋነኞቹ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ቻይና፤ የአውሮፓ ህብረት፤ ወዘተ)፡፡
ህብረቱ በ50 ዓመት ውስጥ ማሳካት የሚፈልገው ግብ አፍሪካን በዓለም ላይ ተጽኖዋ የጎላ (Transforming Africa into the global powerhouse of the future) ማድረግ ነው! 50 ዓመት ረጅም ባለመሆኑ ከመጣንበት ሁኔታ አንጻር በግሌ የህብረቱ ወሳኝ አጀንዳ "በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማስጠበቅ የፖለቲካ መረጋጋት መፍጠር " መሆኑ ነው የሚሰማኝ፡፡
አፍሪካ በብዙ መልኩ እራሷን ጠንካራ በማድረግ በዓለም ላይ ተፎካካሪ አህጉር ለመሆን #የመሪዎችን_ቁርጠኝነት እና #የዜጎችን_ትብብር መፈለጓ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በአባል ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ያስፈልጋል (የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና መመስረቱ አንዱ መልካም እርምጃ ነው)፡፡ ይህ ጉዳይ አፍሪካ ላደጉ ሀገራት ካላት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እና መልኩን እየቀየረ ከመጣው የቀጠናዊ ፉክክር አንጻር ቀላል ነው ብዬ አላስብም!
በአንጻሩ አፍሪካ የዓለም ሁኔታ ሀገራትን እና ዜጎችን ለተጽኖ አጋላጭነቱ አሁን ከደረሰበት ደረጃ አንጻር ከመጪው 50 ዓመት ይልቅ ያለፉት 50 ዓመታት የተሻሉ እድሎች ኖረዋት እንዳባከንን ይሰማኛል (አፍሪካ በየጊዜ የነበሯትን የለውጥ ራዕይ የነበራቸው መሪዎቿን አባክናለች)፡፡
የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ የተሳካ እንዲሆን ምኞቴ ነው! መጪው ጊዜ ለአባል ሀገራት እጥፍ ስራ የሚጠይቅ ነው!
ለማስረጃ እንዲሆናችሁ ጽሁፎቹን ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.aljazeera.com/news/2021/12/28/2021-year-military-coups-return-to-the-stage-in-africa.
(https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_coups_and_coup_attempts_since_2010)
Patrick J. McGowan African Military coups d'état, 1956-2001: Frequency, Trends and Distribution

Al Jazeera
2021, the year military coups returned to the stage in Africa
This year, there were four successful military takeovers across the continent, up from one in 2021.
#ይህ_ዜና_ጥሩ_ነው!
ትናንት የወጣው የብሉንበርግ ዜና Ethiopian Bonds Swing From Near-Worst to Best as Conflict Eases በዓለም ላይ ካሉ ታዳጊ እና ቦንድ ለሽያጭ ካቀረቡ ሀገራት መካከል የኢትዮጲያ ቦንድ ብዙ መሻሻል አሳይቷል! ቢያንስ በዶላር 6 ሳንቲም የፍላጎት ጭማሪ አሳይቷል! ለዚህ እንደምክንያት የቀረበው በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመነሳት አዝማሚያ እንዲሁም ለ15 ወራት በበርካታ ስፍራዎች ተንሰራፍቶ የቆየው ጦርነት ጋብ ከማለቱ ጋር እንደሚገናኝ በግራፍ አውጥቷል፡፡
የኢትዮጲያ የውጪ ቦንድ ወይም Ethiopia Sovereign Dollar Bond ማለት ኢትዮጲያ በዓለም ላይ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ከኢትዮጲያ ቦንድ እንዲገዙ በምትኩ ኢትዮጲያ ወለድ አስባ የምትከፍላቸው ሰነድ ማለት ነው፡፡ ቦንዱ ለሽያጭ የሚቀርበው የውጪ ምንዛሬ ክፍተትን ለመሙላት፤ የቆዩ የውጪ እዳዎችን በአፋጣኝ ለመክፈል፤ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት፤ ወዘተ ሲባል ነው፡፡
ቦንድ ለውጪ ገበያ ማቅረብ የተለመደ የፋይናንስ አሰራር ነው! ነገር ግን የቦንዱ ዋጋ ወይም የሸማቾች ፍላጎት በሁኔታዎች የሚለዋወጥ መሆኑ ነው ዜና የሚሆነው፡፡
#ለምሳሌ፡- በባይደን አስተዳደር ኢትዮጲያ ከአሜሪካ የቀረጥ ነጻ ገበያ (AGOA) እንድትወጣ የተወሰነው ውሳኔ እና ጦርነት ያቀረበችው ቦንድ ፍላጎት ላይ መቀዛቀዝ ፈጥሮ ዋጋው ዝቅ ማለት ጀምሮ ነበር! የወቅቱ የሮይተርስ ዜና Ethiopia dollar bond hits record low after US move on duty free access የሚል ነበር፡፡
እኔ በግሌ የቦንድ ዋጋው ማደግ የጀመረው የህዳሴው ግድብ የሙከራ ደረጃ ላይ መድረሱም ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ምክንያት የሃይል አቅርቦት በመጪው ጊዜ ኢትዮጲያ የወሰደችውን ብድር የመክፈል አቅም ይፈጥርላታል በሚል መተማመኛ ሊሆን እንደሚችል ይሰማኛል፡፡
ስለቦንድ በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት በሀገር ውስጥ የህዳሴ ግድብ ሲጀመር መንግስት ቦንድ ለዜጎች መሸጥ ጀምሮ ነበር (ዜጎች በባንክ በኩል የገዙበትን መጠን ልክ የቦንድ ሰርተፍኬት ይቀበላሉ) በስምምነቱ መሰረት መንግስት (በየ 5 ዓመቱ) ወለድ እየጨመረ የቦንዱን ሰርተፍኬት እየተረከበ ክፍያ ይፈጽማል፡፡ ቦንድ ሽያጭ ማለት የፋይናንስ እጥረትን በጊዚያዊነት ለመሙላት የሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ማለት ነው፡፡
ኢትዮጲያ ለዓለም ገበያ #የአንድ_ቢሊየን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ አቅርባለች እና በዓመት 6.9% ወለድ ለመክፈል ፍላጎት ስላላት Ethiopia sovereign dollar bond በሚል ለሽያጭ ከቀረበ ቆየት ብሏል፡፡ ስለዚህ ያዋጣናል የሚሉ አካላት የፈለጉትን ያህል መጠን ቦንድ ከኢትዮጲያ በመግዛት ከወለዱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጲያ የመክፈያ ወቅቱን ጠብቃ ለሸጠችው ቦንድ 69 ሚሊየን ዶላር ወለድ ጨምራ ትከፍላለች ማለት ነው (ቁጥሮቹ ሮይተርስ ላይ ይኖራሉ የተለወጠ ነገር ካለ ጨምሩበት)፡፡
በተለይ የውጪ ምንዛሬ እጥረት በገጠመ ወቅት የቦንድ ገበያ ዋጋ ከፍ ማለት የብድር አቅም ከመጨመሩ በተጨማሪ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ የተወሰነ እንደመተማማኛ እና ሌሎች የአጋር ሀገራ የድጋፍ ስምምነቶች ላይ አወንታዊ ሚና ይኖረዋል፡፡

የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ መሰረቱን ያደረገው ኢ-መደበኛ ሴክተር ላይ ሆኖ ሳለ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ #እስኪያልቅ ይህን ሴክተር ጎዳና ላይ አልይ ማለት ስሜት አይሰጥም!
#ናሙና_መረጣ!
*
ጥናት በሚሰራበት ወቅት መወሰድ ያለበት ናሙና መወሰን ያለበት በሁለት መሰረታዊ ስልት ነው! እነሱም እኩል እድል የማግኘት (Probability) እና ውስን እድል የማግኘት (Non- Probability) በሚል መስፈርት የሚወሰዱ ናቸው፡፡ ማንኛውም አጥኚ ከሁለቱ ስልት አንዱን ወይም ሁለቱንም ቀላቅሎ ሊጠቀም ይችላል! ዋናው ቁም ነገር ለምን እንደተጠቀመ እና ለምን መጠቀም እንዳልፈለገ የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡
ለዚህ የሚረዳው ስለሁሉም የናሙና ስልቶች ምንነት፤ ለየትኛው እንደሚያስፈልጉ እና ባህሪያቸውን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ የናሙና መረጣ ስልት ጥልቅ እና ሰፊ ነው ለጊዜው ግን መሰረታዊ የሚባሉትን በምሳሌ እንያቸው!
Probability/Random
#Simple_Random Sampling:- ይሄ ዘዴ የሚጠቅመው ጠቅላላ ከሚኖረው የጥናት አካል Target Population በስሌት የተገኘውን Sample Size ያለ ምንም ልዩነት እኩል እድል እንዲያገኙ እንደሎተሪ በእጣ ለማውጣት ነው፡፡ ይህ ዘዴ አድሎ የሌለበት በመሆኑ በአብዛኛው ለተዓማኒነት የቀረበ ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- በአንድ ወረዳ አንድ ሺህ ሰው ኖሮ 250 ሰዎች ናሙና ቢኖር እነዚህ ሰዎች ጋር ለመድረስ ከቤት ቁጥራቸው በመነሳት ከጠቅላላ ነዋሪዎች 250 ሰው መምረጥ (ሁሉም ነዋሪ የመመረጥ 1/1000 እኩል እድል አለው ማለት ነው)፡፡ አጥኚው ከቤት ቁጥር በመነሳት ነዋሪውን ለመለየት ከፈለገ በቀላል ምሳሌ የቤት ቁጥር 1፤11፤21፤31፤41(አስር አስር የቤት ቁጥር በመዝለል ሊወስድ ይችላል)፡፡ ዋናው ቁም ነገር ቀድሞ የቤት ቁጥሮቹ ውስጥ የሚኖረውን ነዋሪ የማያውቀው ከሆነ ከናሙና ተዓማኒነት ትችት (Bias) ይድናል ማለት ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- እቁብ ውስጥ ያሉ ሰዎች የመጀመሪያ እጣ ለማውጣት ከአንድ እስከ አስር ጽፈው ቢጠቀልሉ እና ቢያነሱ ሁሉም ሰው እቁቡን የማግኘት 1/10 እድል አለው ማለት ነው (ለኔ አልወጣም አድሎ ተደረገብኝ የሚል ክስ ሊመጣ አይችልም) ይህ በራሱ Simple Random Sampling ዘዴ ነው፡፡
#Stratified_Cluster_Area Sampling:- እነዚህ ናሙናዎች ተቀራራቢ ባህሪ አላቸው! የናሙና ዘዴው የሚያገለግለው የጥናት ወካዮችን በአካባቢ ለመለየት ሲፈለግ ነው! በላይኛው ምሳሌ በወረዳው የሚኖሩ ሰዎች ውስጥ 250ዎቹን ከአንድ ቦታ ላለመውሰድ ነዋሪውን በሚኖርበት በመንደር/በጎጥ ለመለያየት ሲፈለግ ያገለግላል! ስለዚህ ከሁሉም መንደር ተመጣጣኝ ውክልና ለማግኘት ያግዛል ማለት ነው፡፡
#Multi_Stage Sampling:- የመጨረሻው የናሙና ደረጃ ላይ ለመድረስ የተኬደበትን ዙር ለማስረዳት ያገለግላል፡፡ #ለምሳሌ፡- አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ወረዳ ላይ ጥናት ለመስራት መጀመሪያ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች አንዱ ክፍለ ከተማ እንዴት እንደተመረጠ፤ ከተመረጠው ክፍለ ከተማ ስር ከሚኖሩ ወረዳዎች መካከል እንዴት አንዱ ወረዳ እንደተመረጠ፤ በወረዳው ስር ከሚገኙ መንደሮች ወካይ ናሙና እንዴት እንደተወሰደ፤ ከመንደሮቹ ውስጥ የአባወራው ቤት ቁጥር እንዴት እንደተመረጠ የተኬደበትን መንገድ ለማሳየት ያገለግላል፡፡
Non-Probability/Non-Random
#Judgment Sampling:- ይህ ዘዴ እንደጥናቱ ለናሙናነት መወሰድ ያለባቸው ናሙናዎች በውሳኔ መወሰድ ሲኖርበት የሚያገለግል ነው፡፡ በላይኛው ምሳሌ ከ250ዎቹ ናሙናዎች መካከል የራሳቸው መኖሪያ ቤት ያላቸውን ብቻ መርጦ ለመውሰድ ቢወስን እንደማለት ነው፡፡ ወይም መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉት ይምጡ ቢባል፤ እቁቡ ለተቸገረው #ለእገሌ ይሰጠው ቢባል፤ ወዘተ ማለት ነው፡፡ በቀላል ቋንቋ አጥኚው ሆን ብሎ (#Purposive) ናሙና የሚወሰዱትን አካላት ማንነት ቀድሞ ወስኗል (የዚህ አይነቱ ዘዴ የተዓማኒነት መጓደል ጥያቄ ይነሳበታል)፡፡
#Quota Sampling:- ከስሙ እንደሚያስታውቀው ናሙና የሚወሰዱ አካላትን ለማመጣጠን ቁጥር መመደብ አስፈላጊ ሲሆን የሚወሰድ የናሙና አይነት ነው! #ለምሳሌ፡- ከ250ዎቹ መካከል ወንድ የዚህን ያህል ሴት የዚህን ያህል ቢባል፤ ድግሪ ያላቸው የዚህን ያህል፤ ዲፕሎማ የዚህን ያህል፤ ወዘተ ተብሎ ምደባ ቢሰራ፤ ከሁሉም ወረዳ የዚህን የዚህን ያህል ሰው ቢባል፤ ወዘተ ማለት ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ዘዴ የተዓማኒነት መጓደል ጥያቄ ይነሳበታል! ምክንያቱም ኮታ ለመሙላት ሲባል ናሙና መወሰድ የሚገባቸው ሰዎች ከጥናቱ ውጪ የመሆን እድል ይኖራቸዋል፡፡
#Panel Sampling:- ናሙና ተወሳጆቹን ካላቸው ባህሪ በመነሳት ክፍፍል ለመስራት ያገለግላል፡፡ #ለምሳሌ፡- ከ250ዎቹ መካከል ከ20-30ዓመት ውስጥ ያሉትን ለመምረጥ፤ ከ2010-2013ዓ/ም የተመረቁትን፤ ወዘተ በሚል ከፋፍሎ ለማጥናት ሲታሰብ ሊያገለግል ይችላል፡፡
#Snowball Sampling:- ናሙና የሚወሰዱ አካላትን በቀላሉ ማግኘት በሚያስቸግርበት ወቅት #ውክልና የመስጠት አይነት ዘዴ ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- ከመንገድ በታች ያሉ፤ ከወንዝ ወዲያ ያሉ፤ ጎዳና ተዳዳሪዎች፤ በኮሮና ስለተያዙ፤ ወዘተ እየተባለ Respondents በቀላሉ ማግኘት ሲያስቸግር ለጥቂቶች የውክልና ናሙናዎችን ሊያመለክት ይችላል፡፡
የናሙና አይነቶች ምክንያታዊ ስለሆኑ ከየጥናቱ አንጻር ሲወሰዱ ለምን እንደተመረጡ ምክንያት መጥቀስ ግዴታ ነው! የናሙና አይነቶቹ ጠንካራም ደካማም ጎን ሊኖራቸው ይችላል፡፡ አንድ አጥኚ በአንድ ጥናት ውስጥ ከሁለቱንም ቀላቅሎ የመጠቀም መብት አለው፡፡
#ለምሳሌ፡- በአዲስ አበባ ወጣቶች ስራ አጥ የሚሆኑበትን ምክንያት ለማጥናት ከ11 ክፍለ ከተማ አንድ ክፍለ ከተማ (Simple Random Sampling) መምረጥ፤ በተመረጠው ክፍለ ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱን (Systematic Sampling) ቢመርጥ፤ በተመረጠው ወረዳ ስር ከሚገኙ መንደሮች ስራ አጥ ይበዛበታል በሚል ምክንያት (Judgment Sampling) ተጠቅሞ አንዱን መንደር ቢመርጥ፤ ከወጣቶቹ መካከል ከ2010-2013ዓ/ም የተመረቁ ቢል (Panel Sampling)፤ ከየዲፓርትመንቱ አስር አስር ወጣት እጠይቃለሁ ቢል (Quota Sampling)፤ ወዘተ ይችላል፡፡
ዋናው ቁም ነገር ይህን ስልት በጋራ የተጠቀመው ተዓማኒ እና ትክክለኛ ውክልና እና የጥናት ውጤት ለማምጣት መሆኑን ማሳመን ብቻ ነው፡፡

ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ጥቆማ ከተሰጠባቸው ከጠቅላላ 42 እጩዎች መካከል 55% (12 ሙሉ ፕሮፌሰር እና 11 ዶክትሬት(Ph.D)) ያላቸው መሆናቸውን እንዴት አያችሁት?
አፍሪካ እቃን በእቃ የመገበያየት ሂደት ውስጥ ልትገባ ትችላለች?
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና መመስረቱ የአፍሪካ የመጪው ጊዜ ተስፋ መሆኑ ግልፅ ነው! ምክንያቱም በአባል ሀገራት መካከል የንግድ እና የመሰረተ ልማት ትስስር መፈጠሩ አፍሪካውያን ያላቸውን ሀብት በተሻለ ተጠቅመው ለማደግ ያግዛቸዋል።
ስለዚህ በዛሬው በህብረቱ ስብሰባ ይህንን ቀጠናዊ ነፃ የንግድ ትስስር ማሳደግ ተገቢ መሆኑ ላይ የተነሳው ሃሳብ በጣም ተገቢም ትክክልም ነው።
የአፍሪካ ሀገራት ከካፒታል እጥረት እና እሴት ባልተጨመረባቸው የውጪ ንግድ ሸቀጦቻቸው የታወቁ ናቸው! ስለዚህ የቀጣይ የንግድ አጋርነቱ የሚፈተነው አንዱ በውጪ ምንዛሬ አቅርቦቻቸው እጥረት ምክንያት ነው።
የአፍሪካ ሀገራት Balance of Payment ዝቅተኛ ነው (በውጪ ሀገራት ለግዢ ላዘዙት ቁሳቁስ ተገቢውን ክፍያ መፈፀም በመቸገር የብድር ጫና ያስተናግዳሉ)። ይህ ሁኔታ አፍሪካ ውስጥ ባሉ ሁለት ሀገራት መካከል በቀላሉ የሚተላለፉት መሆን ይችላል?
#ለምሳሌ፦ ኬንያ ለታንዛኒያ ለላከችው የአንድ ሚሊየን ዶላር ቡና ክፍያ ምን ያህል ጊዜ ቢዘገይ ትታገሳለች? ያደጉ ሀገራት አፍሪካን የእዳ ጫና ውስጥ ከሚከቱበት መንገድ አንዱ ባለ እዳ ማድረግ በመሆን ይህ ዘዴ ጥቅም ላይ ውሎ ያውቃል።
ተመሳሳይ እሴት ያልተጨመረበት ምርት የሚልኩ ሁለት ሀገራት የፍላጎት መቀዛቀዝ ሊያጋጥማቸው ይችላል! ስለዚህ በንግድ ቀጠናው ከተለዩ ከ3ሺ በላይ ቁሶች መካከል የተሻለ የምርት እና የዋጋ እድል (Comparative Advantage) ያላቸውን ከመለየት በተጨማሪ ትክክለኛ አጋር እና እሴት ወደመጨመር ያደገ ስትራቴጂ ማዘጋጀት ተጠባቂ ነው።
የአፍሪካ ህብረት በጠቅላላው ወይም በጎንዮሽ የተናጠል የሀገራት ምክክር ወቅት አባል ሀገራት የውጪ ምንዛሬ ክምችቶቻቸውን ማሻሻል እስኪችሉ ድረስ የነፃ የንግድ ቀጠና አባል ሀገራት ምርትን በአቻ ምርት ዋጋ መለዋወጥ የሚችሉበትን መንገድ ቢያስቡ ወይም ቢነጋገሩ መጥፎ ነው?
የነፃ ገበያ በሚፈጠርበት ወቅት ሀገራት በተናጥል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ረጅም ድርድር እንደሚያደርጉ ይታወቃል።
#ለምሳሌ፦ የአንድ ሚሊየን ዶላር ቡና የላከ ሀገር ለቡና ግዢው የሚከፈል አንድ ሚሊየን ዶላር መክፈል ከማይችል ሀገር በምትኩ የአንድ ሚሊየን ዶላር አቻ ወርቅ፤ ጣውላ፤ ነዳጅ፤ ወዘተ በልዋጭ ቢገበያይ በውጪ ምንዛሬ እጥረት ሊከሰት የሚችልን የገበያ ልውውጥ ክፍተትን ለመሙላት #ውስን ስምምነቶች ቢፈቀድ መጥፎ ነው? (እዳን በቁስ መክፈል በአፍሪካ አዲስ ልምድ አይደለም)።
ለውይይት የቀረበ ነፃ ሃሳብ ነው!

The Ethiopian Economist View
በሀገራችን 3 ክልሎች (ትግራይ፤ አማራ እና አፋር) ጦርነት ውስጥ ቆይተው፤ 2 ክልሎች በድርቅ እየተፈተኑ (ሶማሌ እና ኦሮሚያ) እንዲሁም 2 የሰላም እጦት ያለባቸው ዞኖችን የያዙት (ቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ) እያሉ ኢኮኖሚው የወጪ እና የገቢ ፈተና ውስጥ እንደሆነ አይካድም። ጦርነት እና ግጭት ሚሊዮን አምራቾችን የሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊዎች አድርጓል፤ የማምረቻ እና የንግድ ተቋማትን አውድሟል፤ የምርት መቀነስን…
በጥናት ፅሁፋችሁን በምሰሩበት ጊዜ Reference ስትጠቅሱ ትኩረት መስጠት ያለባችሁ #ሃሳቡ ላይ ወይስ #የሃሳቡ_ባለቤት ላይ?
በጥናት ስራ ውስጥ ዋቢ (Reference) የሚጠቀሰው በሁለት መንገድ ነው። አንደኛው According to ወይም "እገሌ እንዳለው" ብሎ ሃሳቡን መፃፍ ሲሆን ሁለተኛው ሃሳቡን ፅፎ በመጨረሻ የሃሳቡን ባለቤት ስም መግለጽ ነው።
#ለምሳሌ፦ According to (Abebe, 2021) "ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ መሆን የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ዋስትና አይሆንም" በማለት ውስጥ ግነቱ ያለው ሃሳቡ ላይ ሳይሆን የሃሳቡ ባለቤት ላይ ነው። አበበ እንዳለው ብሎ ሲጀምር አበበ ይህን ለማለት ያለው ተዓማኒነት ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ቀድሞ ያመጣል።
የዚህ አይነት አገላለፅ በጣም ጥንቃቄ እና የሃሳቡን ባለቤት ተፅዕኖ ፈጣሪነት ማረጋገጥ ይገባል #ለምሳሌ፦ አዳም ስሚዝ እንዳለው፤ ካርል ማርክስ እንዳለው፤ ኔልሰን ማንዴላ እንዳለው፤ ፖል ካጋሜ እንዳለው፤ አለማየሁ ገዳ እንዳለው፤ የዓለም ባንክ እንደተረጎመው፤ ወዘተ በማለት ሰዎቹ ወይም ድርጅቶቹ በአቅማቸው ለትርጓሜ አሳማኝ እንደሆኑ መነሻ ማድረግ ይቻላል።
#ለምሳሌ፦ "ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ መሆን የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ዋስትና አይሆንም" (Abebe, 2021)" ብሎ ማስቀመጥ ውስጥ የሚገነው በቅድሚያ ሃሳብ ነው። አንባቢ ሃሳቡን በጥልቀት ከመረመሩ በኋላ ነው የሃሳቡ ባለቤት ማን ነው? ወደሚለው የሚሄዱት።
ብዙ ጊዜ የሚመከረው ወሳኝ የሆኑ በተለይ የቃላት ፍቺ (Definition) ለመጥቀስ እገሌ እንዳለው በሚል ሊጀመር ይችላል! ምክንያቱም አብዛኛውን አንባቢ የሚያስማማ የትርጉም ፍቺ የታወቁ ተቋማት ወይም የሃሳቡ አመንጪዎች የሰጡት እንዲወሰድ ይመከራል።
#ለምሳሌ፦ ዘነበ በ2021 "ውጤታማነት" ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንደተረጎመው ብትሉ። ብዙም ስሜት አይሰጥም አንደኛ #ዘመኑ ሁለተኛ ትርጓሜ ሰጪው ማነው? የሚለው ጥያቄ ያስነሳል (WFP, 2021 ስለ ውጤታማነት የሰጠው አዲስ ትርጓሜ ብትሉ ግን ተቀባይነት አያጣም)።
የጥናት አሰራር በየጊዜው ማሻሻያ እየተደረገበት ነው የሚሄደው #ለምሳሌ፦ ዋና ርዕስ አፃፃፍ (በግራ በኩል መፃፍ፤ ማሀል ላይ ማድረግ፤ Underline ማድረግ፤ ፎንት መጨመር፤ Italic ማድረግ፤ ዋቢ አገላለፅ (Harvard, APA)፤ ወዘተ በየጊዜው ሲለዋወጠ ነው ዛሬ ላይ የደረሰው።
#ለምሳሌ፦ 1983 ጥናቱን ያቀረበ ሰው፤ 2003 ጥናት ከሰራ ሰው እንዲሁም 2018 ካጠና ሰው መካከል መሰረታዊ ልዩነት መኖሩ የጥናት አሰራር በሂደት ያለውን መሻሻል ያሳያል። በቀላሉ ለድግሪ፤ ለማስተርስ፤ ለሶስተኛ ድግሪ መጠቀም የሚመከረው የቃላት ወይም የፊደል ብዛት በሂደት ተሻሽሏል።
#Tip የሁለተኛ ሰው ዋቢ አጠቃቀም (ዘነበ, 2018 Cited in Abebe, 2021) የሚል አጠቃቀም የዘነበን ዋና ፅሁፍ ማግኘት ካልተቻ የሚደረግ ቢሆንም የዘነበን ትክክለኛ ሃሳብ አይታችሁ እስካላረጋገጣችሁ ለስህተት ልትዳረጉ ስለምትችሉ ዝም ብላችሁ አበበን አምናችሁ አትውሰዱ።
በአጋጣሚ የብዙ ሰዎች ጥናት ስመለከት የተቀላቀሉ የዋቢ አገላለፅ ስለምመለከት እግረ መንገድ ጥቆማ ለመስጠት ያህል ነው።
Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ወደ ሀገር ቤት ከመጡ 119ሺ ዳያስፖራዎች ወደ ሰርኩሌሽን የገባ ገንዘብ/ዶላር፤ የኢንቨስትመንት ፍላጎት፤ የማህበራዊ ተሳትፎ፤ ሁነቶች፤ ወዘተ ዘርዝሮ #በቁጥር_ሪፖርት ማቅረቡ ይበረታታል! (በሪፖርት የቀረቡ ቁጥሮችን ከዜናዎች ተመልከቱ እና ተወያዩባቸው)።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር "ላለፉት 6 ወራት 1.1 ሚሊየን ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሪያለሁ ብሏል"።
#ጥያቄ፦ ጦርነት እና ግጭት ላለፉት 6 ወራት ስንት የስራ እድሎችን አጠፋ? #የተፈጠረው የስራ እድል እና #የጠፋው የስራ እድል ሲቀናነስ ፖዘቲቭ ከመጣ መልካም ነው። ሪፖርቱ እንዲህ ቢቀርብ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ኢኮኖሚው ስራ አጥነትን ለመቋቋም የሄደውን ርቀት ያሳያል።
#ለምሳሌ፦ በጦርነት እና ግጭት ምክንያት አንድ ሚሊየን የተፈናቀለ አርሶ አደር ቢኖር እና ላለፉት 6 ወራት ካላመረተ በጊዚያዊነትም ቢሆን #ስራ_አጥ ነው።
የኢኮኖሚ ሪፖርቶችን የሚያቀርቡ ሚኒስትር መስሪያቤቶች ዙሪያ መለስ ምልከታ ያለው እና አብዛኞቻችን የምንረዳው እና የምናምነው አይነት ሪፖርት እንዲሆን ቢደረግ መጥፎ አይደለም።

ለረጅም ጊዜ የምሰራበት አካባቢ ጥላ ዘርግቶ ጫማ የሚጠርግ ልጅ አለ እና የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ይካሄድ ስለነበር ላለፉት 10 ቀናት አትስሩ መባሉን ተከትሎ ብቅ አላለም ነበር እና ዛሬ ሳገኘው...
"ላለፉት 10 ቀናት ምን ሰራህ?" አልኩት እሱም "#ህገ_ወጥ ሰራሁ" አለኝ። (ቦታ ሳይዙ መንገድ ላይ የሚደረግ ንግድን ህገወጥ ብለን ነው የምንጠራው አለኝ)።
"ምንድን ነው ህገወጥ?" አልኩት።
"ማታ ማታ ካልሲ እና ፓንት ምናምን ሸጥኩ" አለኝ።
"ከዚህ ቀደም ሸጠህ ታውቃለህ እንዴ? እና ያዋጣል?" ስለው።
"ሸጬ አላውቅም መሯሯጥ አለው ግን #ሃሪፍ ነው" አለኝ።
የዚህን አይነት ሁኔታ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ውስጥ #Opportunity_Cost ወይም ተነፃፃሪ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ውጤት ይባላል። በከልካይ እና በተከልካይ መካከል ያለ ውጤት እንደማለት ነው።

ፕሮጀክቶች ያስወጡት ጠቅላላ ወጪ የዚህን ያህል #ቢሊየን እየተባለ የሚቀርበው የፕሮጀክቶቹ ግዙፍነት እንዳለ ሆኖ #ሙስና እና #የዋጋ_ንረትን ማጠቃለላቸው የሚካድ አይሆንም።
#ለምሳሌ፦ በወረቀት ላይ የአንድ ቢሊየን ብር ትክክለኛ የፕሮጀክት ፕላን የተሰራለት ፕሮጀክት በጨረታ ወቅት፤ በግብዓት ግዢ ወቅት፤ በሙያ ግመታ እና ክፍያ ወቅት፤ ወዘተ 10% ሙስና ቢኖር (በጨዋ ግምት!) ፕሮጀክቱ 1.1 ቢሊየን ብር ሊደርስ ይችላል።
#ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ በሙስና ስትለካ ከ163 የዓለም ሀገራት 125ኛ ደረጃ ነች (LEGATUM INSTITUTE በ2021 ባደርገው ጥናት)።
ፕሮጀክቱ ለመጠናቀቅ 3 ዓመት የፈጀ ቢሆን እና በየዓመቱ በአማካይ 30% የዋጋ ንረት ቢጨምር የፕሮጀክቱ ዋጋ #በቀላሉ 1.4 ቢሊየን ብር ደረሰ ማለት ነው።
ስለዚህ የአንድ ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ለምርቃት ወቅት 1.4 ቢሊየን ብር ፈጅቷል ተብሎ ቢቀርብ፡ የሙስና (100 ሚሊየን ብር) እና የዋጋ ንረት (300 ሚሊየን ብር) ድርሻ የመሆን እድል አለው።
በብዙ ቢሊየን ብር ፕሮጀክቶችን መስራት ማለት የፕሮጀክት ግዝፈትን ብቻ አያሳይም! ከፍተኛ የዋጋ ንረት፤ የግብዓት እጥረት፤ የመፈጸም አቅም መቀነስ፤ ሙስና፤ የጥናት ክፍተት፤ ወዘተ ማለትም ነው።
ስለዚህ ተቋማዊ አሰራር (Institutionalization) የተዳከመ መሆኑ እየታወቀ በየደረጃው ያለ #ሙስና የፕሮጀክት ወጪ መጋነን ምክንያት እንደሆነ በሪፖርት የማይቀርብ ግን እየገመትነው የምንሄደው ሃቅ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሮጀክቶች ቢሊየኖችን ማስወጣታቸው እንጂ ቢሊየን ማስወጣት የጀመሩበት ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያት በቁጭት እና በዝርዝር ሲነገር አንሰማም።

#በበጣም_አልስማማም እና #በአልስማማም መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? (Strongly Disagree እና Disagree)።
የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የሚያከናውኑ ሰዎች በተለይ በመጠይቅ የሚሰበስቧቸው መረጃዎች (Data) የተለያዩ ባህሪያት አላቸው። ከነዚህ የመረጃ አይነቶች መካከል #Likert የሚባለው አንዱ ነው።
#ለምሳሌ፦ "በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች አድሎ አለባቸው" የሚል ጥያቄ የቀረበለት አንድ ተገልጋይ (Respondent) ለቀረበለት ጥያቄ እንዲህ ብሎ እንዲመልስ መጠየቅ ማለት ነው።
1. በጣም እስማማለሁ (Strongly Agree)
2. እስማማለሁ (Agree)
3. ተአቅቦ (Neutral)
4. አልስማማም (Disagree)
5. በጣም አልስማማም (Strong Disagree)
ሰውየው በጣም እስማማለሁ (Strongly agree) ቢል "በጣም አድሎ አለ እያለ ነው" ወይም በጣም አልስማማም (Strongly disagree) ቢል "በጣም አድሎ የለም" እያለ ነው። በተመሳሳይ እስማማለሁ (Agree) ቢል "አድሎ አለ" ወይም አልስማማም (Disagree) ቢል "አድሎ የለም" እያለ ነው።
ጥያቄው በተለያዩ ምላሽ ሰጪዎች እድሜ፤ ፆታ፤ የትምህርት ደረጃ፤ ወዘተ አንፃር ሲለካ በአገልግሎት ወቅት አድሎ ስለመኖሩ #በጣም_እስማማለሁ እና #በእስማማለሁ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ይቻላል?
ምክንያቱም ለበጣም እስማማለሁ እና ለእስማማለሁ የራሱ መለኪያ (Indicators) ካልተቀመጠ በስተቀር መጠይቅ የሚሞላውን ሰው የዚህ አይነት ምርጫ በመስጠት የሚገኝን መልስ መተንተን ሚዛን ያስታል።
#ለምሳሌ፦ እርካታን ለመለካት ተጠያቂውን #በጣም_እረክቻለሁ እና #ረክቻለሁ ብሎ እንዲመልስ ብትጠይቁት አንዱን ሊመርጥ ይችላል ነገር ግን በበጣም መርካት እና መርካት መካከል ልዩነቱ በግልፅ ስላልተዘረዘረለት 150 ሰዎችን ብትጠይቁ እና 100ዎቹ በጣም ረክቻለሁ ብለው ቢመልሱ እና ለመቶዎቹ የበጣም መርካትን #መነሻ መስፈርት ብትጠይቁ የተለያየ ነው የሚሆነው።
በዓለም ላይ ከዛሬ 85 ዓመታት በፊት ጀምሮ የዚህ አይነት መጠይቅ አቀራረብ (Likert) ስልት ጥቅም ላይ ይውላል። ነገር ግን አሻሚ በመሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምርጫዎችን ወደ ሶስት (እስማማለሁ፤ ተአቅቦ እና አልስማማም) ወይም ወደ ሁለት (እስማማለሁ እና አልስማማም) የመለወጥ አካሄዶች አሉ።
ሌላው አሻሚ ነገር ደግሞ Neutral የሚለው ምርጫ ነው። "በተቋም አድሎ አለ?" የሚል መጠይቅ የቀረበለት ተገልጋይ "ተአቅቦ ወይም Neutral" የሚል መልስ ቢሰጥ በትንታኔ ወቅት ሲቀርብ በብዛት ስሜት አይሰጥም።
#ለምሳሌ፦ ሰዎች ተስማምቻለሁ እና አልተስማማውም፤ ረክቻለሁ እና አልረካሁም በሚል መልሶቻቸው መካከል አሻሚ ልዩነት ባለመኖሩ ሁለት ምርጫ (Binary) መልስ ያላቸውን መጠቀም ለጥናት ውጤት ተዓማኒነት በብዙ ይመከራል።
እድሜ ስንት ነው? (18፤ 20፤ 30 ቢል መልሱ Continuous data ይባላል)፤ ፆታ? ለሚለው ጥያቄ ወንድ ወይም ሴት የሚል ምርጫ ቢሰጠው መረጃው Binary ወይም Dummy ይባላል)፤ እድሜ? ከ18-25 ዓመት፤ 26-30 ዓመት፤ 31-35 ዓመት የሚል ምርጫ ቢሰጠው መረጃው (መልሱ Categorical data ይባላል)፤ እርካታ? ለሚል ጥያቄ በጣም እስማማለሁ፤ እስማማለሁ፤ ተአቅቦ፤ አልስማማም እና በጣም አልስማማም የሚል ምርጫ ሲሰጠው መረጃው Likert data ይባላል።