ዋልድባ ገዳም
4.6K subscribers
406 photos
286 videos
194 files
232 links
👉 ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በነገረ መለኮት፣ በነገረ ማርያም፣ በነገረ መስቀል፣ በነገረ ቅዱሳንና በምሥጢራት ላይ፣
👉 ወቅታዊ የቤ/ክ ሁኔታና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች፣
👉 የመንፈሳዊ ጉዞዎች ዓመታዊ መርሐ ግብር...

ለጥያቄዎ
@zeWaldiba_bot
@Gedamewali
@Elmestoagia

👇 YouTube: https://www.youtube.com/@mekoreta
Download Telegram
ከጋብቻ በኋላ ግንኙነት የሚከለከለው ለስንት ቀን ነው?

በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ተክሊል እና ሰርግ የተለያዩ ናቸው። ተክሊል ጋብቻው ሲሆን ስርጉ ደግሞ የተክሊሉ በዓል ነው። በቀደመው የቤተክርስቲያን ትውፊትም ተክሊልና ሰርግ በአንድ ቀን አይፈጸሙም ነበር። ቤተክርስቲያን ተጋቢዎች ከጋብቻ /ተክሊል በኋላ ለ40 (አርባ) ቀናት በጾምና በሱባዔ ቆይተው ሰርግ ማድረግ አለባቸው የሚል ትውፊት አላቸው።

የፍትሐ ነገስት አንቀጽ 24 ትርጓሜም "በጋብቻ ጊዜ የሚደረገው ሥርዓት ከዘረዘረ በኋላ እሱ ከአባቱ ጋር እሷም ከእናቷ ጋር ሲተኙ ይሰነብታሉ፤ ቊርባኑን በሚሹበት ጊዜ እየሔዱ ይቆርባሉ፤ አርባው ቀን ሲፈጸምም ሰርጉን ያደርጉላቸዋል" ይላል። ሙሽሮቹ ተክሊል ተፈጽሞላቸው አሰቀድሞ ቆርበው ከወጡ በኋላ ወደየቤታቸው ይሔዳሉ ቢል እሱ ከአባቱ ጋር ሴቷም ከእናቷ ጋር እየተኙ ለአርባ ቀናት ይቆያሉ።

ይህስ ከጋብቻ በኋላ ተለያይቶ መኖር አይገባም ወደ ወንዱ ቤት ይሔዳሉ ብሎ እሱ ከአባቱ ጋር ፤ ሴቷም ከእናቷ ጋር ( ከእናቷ ጋር የሚለውን የሙሸራውን እናት ለሙሽራይቱ አደርጎ መናገር ነው) እየተኙ ይሰናበታሉ ማለት ነው። በአርባ ቀን ውስጥ ሙሽራው ቤተስብ የማሰተዳደርን ሥራ ከአባቱ፣ ሙሽራይቱ ልጅ ወልዶ የማሳደግን ተግባር ከእናቷ (ከሙሽራው እናት ) እየማሩ ፣በመከከሉ እየቆረቡ ይቆያሉ።

በአርባኛው ቀን ሰርግ ይደረግላቸዋል። ይኽውም ጌታ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ፣ ሕሙማን ነፍስን በትምህርቱ እየፈወስ ከቦታ ፣ ቦታ እየተዘዋወረ ከማሰተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ 40 ቀንና ፣40 ለሊት እንደጶም፤ ሐዋርያትም ይህን ዓለም ዕጣ በዕጣ ብለው ተከፋፊለው ወንጌልን ለማሰተማር ከመውጣታቸው በፊት 40 ቀናት እንደጾሙ አብነት በማድረግ ነው።

ሙሸሮች 40 (አርባ) ቀናት የሚለያዬበት ምክኒያት ጾም ጸሎት አድርጎ፤ ሥጋ ወደሙን ደጋግሞ ተቀብሎ ትዳርንና የሚወለደውን ልጅ ለማስባረክ ነው።

እንዲሁ አድርገው ተጋብተው የተወለደው ልጅ መንፈሳዊ ቢሆን እንደ እንጦስ እንደ መቃርስ ፣ ሥጋዊ ቢሆን እንደ ቆስጠንጢኖስ እንደ አኖሬዎስ ይሆናል ፣ እንዲል ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ (24 ገጽ 323 ) ።

ሰርጉ ከተክሊሉ የመለየቱ አሰፈላጊነቱ ደግሞ ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ ፎቶ ለመነሣት ከመንገላታት፣ በድካም ምክኒያት ከሙወጣው ላብ ለመጠበቅና ለቅዱስ ቊርባን ሊሰጠው የሚገባው ክብር ለመስጠት ነው። መለያየቱን ምክንያት በማድረግ ሰርጉን ፊጽሞ ዓለማዊ ማደረግ ፣ ከልብስ መራቆትና ዘፈን ግን ተገቢ አይዴልም ።

በስርጉ ዕለት ለክርስቲያን በተፈቀደው መጠን ማጌጥ ፤መደሰት ፤መብላትና መጠጣት አልተከለከለም። ለሌሎች ሕይውት ሓላፊነት ለመውሰድ የሚፈጽሙ ምሥጢራት በጾም በጸሎት ፈቃደ በእግዚአብሔር ሊጠየቅባቸው ይገባል።

ጋብቻ ደግሞ እንዲ የአንዱን ሸክም ለመሽከም፥ልጅ ወልዶ ለማሳደግ የሚገጥም ምሥጢር ሰለሆነ ተጋቢዎች ለአርባ ቀናት እግዚአብሔር ደጅ እየጠኑና እየተማጸኑ መቆየት ይገባቸዋል።

40 ቀን እስኪፈጸም በጾምና በሱባኤ የሚሰነብቱትም እንደ ፍትሐ ነገሥት ከወላጆቻቸው ጋር በመተኛት ነው ። በአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ከእናት አባት እየተኙ ማሳለፍ የሚቻልበት ዕድል ባይመቻች እንኳን ለፈተና በማያጋልጥ ሁኔታ ማሳለፍ ይገባል።

በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያን ትውፊት ጋብቻ ከተፈጸመበት ዕለት እስከ ስርጉ ዕለት (ለ40ቀናት) ግንኙነት ማድረግ አይቻልም። የቤተክርስቲያን ትውፊት ይህ ቢሆንም አሁን ያለው ሥርዓት ስሕተት ነው ማለትም አይደለም ።ይኽውም ተክሊልና ስርግ አንደ ቀን የሚፈጸም ቢሆንም ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓት (በጥምቱ ትውፊት ጫጉላ) በዕለቱ ሰለሌለ ማለት ነው ትርጓሜ ወንጌል ስርግ ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓይ የሚደረግበት ነው። ሰለሚል ስርግ ከተክሊል / ጋብቻ ዕለት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው። ምክኒያቱም ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ በዚያው ዕለት ግንኙነት ሊደረግ አይቻልምና። በቅዱስ ቁርባን የሚገባው ጋብቻ ጥንቃቄ ሊደረግለትም ይገባልና። ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ ለሁለት ቀናት ግንኙነት ማድረግ የተከለከለ ነው።

ሁለት ቀን ማለት ለአርባ ስምንት ስዓት ማለት ነው። በምሳሌ ብናየው እሑድ ቅዱስ ቊርባን የተቀበሉ ባልና ሚስት መገናኘት የሚችሉት ዕለቱ ጾም ካልሆነ ሐሙስ ነው ማለት ነው። ሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ቢሆንም ማክስኞ ለረቡዕ አጥቢያ የሚቆጠረው ወደ ረቡዕ ሰለሆነ ጾም ነው።

የሁለት ቀን ክልከላው መሠረቱ በሉቃስ ወንጌል ካህኑ ዘካርያስ ቤተ መቅደስ ሲያጥን ብሥራተ ቅ.ገብርኤልን ስምቶ አግልግሎቱን ጨርሶ ወደ ቤቱ ከሔደ ከሁለት ቀናት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ እንደጸነስች ሰለሚናገር በዚሁ መሠረት ነው።

አንድምታ ወንጌሉ ከሁለት ቀን ኖሮ ተገናኝቷታል። ዛሬም ሕጋውያን ሰለ ሥጋ ወደሙ ክብር ለሁለት ቀን ኑረው መገናኘት ይገባቸዋል፤ በማለት በግልጽ አሰቀምጦታል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ለዘለዓለሙ አሜን!

https://www.facebook.com/sost.philip
💚💛✞በፍቅር ላዚምህ✞💚💛

በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ፣
በደም የገዛኸኝ ባለውለታዬ፤
በቃየን ጎዳና እንዳልጓዝ እርዳኝ፣
በቀናው መንገድህ ወደ ጽድቅህ ምራኝ።
----------------------
----------------------
በልቤ ትከሻ በቀል ተሸክሜ፣
ወንድሜን ጠልቼ ካንተ ፊት መቆሜ፤
ጻድቅ ቢያስመስለኝ በሰዋች እይታ፣
ጉዴን ስለምታውቅ እስራቴን ፍታ። /2/
---------------------
---------------------
ዙሪያውን ተከቦ በእሾህ ጥላቻ፣
ስብከቴ መዝሙሬ ሆኗል የቃል ብቻ፤
ማረኝና ይብቃኝ ለኀጢአት መዝመቱ፣
ፍቅር የሌለው ሰው ነው የከንቱ ከንቱ። /2/
-----------------------
-----------------------
አሸንፈህልኝ እኔ ግን ተሸነፍኩ፣
በእጄ ማልነካውን ለሰው እያሸከምኩ፤
በቃሌ ጠርቼ በግብሬ ረገምኩ፣
ባስመሳይ ማንነት እየሸነገልኩ። /2/

👏💜👇የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇💙🤝
💚💛👇👇👇👇💚💛
👉👉💚 @axum7 💚👈👈
👉👉💛 @axum7 💛👈👈
👉👉 @axum7 👈👈
💚💛👆👆👆👆💚💛
______________
-------------------
💚💛❤️👇👇👇👇💚💛❤️
👉👉💚 @waldiba 💚💚👈
👉👉💛 @waldiba 💛💛👈
👉👉❤️ https://t.me/waldiba ❤️👈
💚💛❤️👆👆👆👆💚💛❤️
💜🍀 «አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» 🌿💜

አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡ እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለሁ እንዲህ ያለ ምርቃት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምን ማለታቸው ይሆን? እያልኩ በኅሊናዬ ሳብሰለስለው ቆየሁ፡፡ «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር? ደጋግሜ አሰብኩት፡፡ ይህንን ሳወጣ እና ሳወርድ እንዳጋጣሚ ሽማግሌው ምርቃታቸውን ፈጽመው እኔ የነበርኩበት ጠረጲዛ ጋ መጡና ተቀመጡ፡፡
👉 መጠየቅ አለብኝ አልኩና አንገቴን በጠረጲዛው ላይ ሰገግ አድርጌ፦
«ደኅና ዋሉ አባቴ» አልኳቸው፡፡
«ይመስገነው! ደኅና ነኝ!» አሉኝ፡፡
«ቅድም የመረቁት ምርቃት ሰምቼው ስለማላውቅ ገረመኝ» አልኩ ወሬ ለመወጠን ብዬ፡፡
«አንተ ብቻ አይደለህም ብዙዎች ይገርማቸዋል» አሉ ፈገግ ብለው፡፡
«ምን ማለትዎ ነው? ግን»
«መጀመርያ አንድ ታሪክ ልንገርህ» አሉኝ ጃኖአቸውን ወደ ቀኝ መለስ እያደረጉ፡፡ እኔም ወንበር ቀየርኩና አጠገባቸው ተደላድዬ ተቀመጥኩ፡፡
«አንድ ጊዜ አንዲት እኅት ምክር ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ እናም እንዲህ ስትል አጫወተችኝ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት ዓመታችን ነው ሁለት ልጆችንም ወልደናል፡፡ የራሳችን ቤት እና መኪና አለን፡፡ ሁለታችንም የየራሳችን በቂ ደመወዝ የሚገኝበት ሥራ አለን፡፡ ይህንን ያህል ዓመት በትዳር ስንኖር ተጋጭተን ወይንም ተጣልተን አናውቅም፡፡ እንኳን ለመጣላት ለመፋቀረም ጊዜ አልነበረንም፡፡ ጭቅጨቅ፣ ንዝንዝ፣ በዚህ ወጣ፣ በዚህ ወረደ የሚባል ነገር በቤታችን ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም፡፡ ጎረቤቶቻችን እና የሚያውቁን ሁሉ በኛ ይቀናሉ፡፡ እርሱን ምን የመሰለች ሚስት አለችህ ይሉታል፤ እኔንም ምን የመሰለ ባል አለሽ ይሉኛል፡፡ አንድ ጊዜ ጓደኛዬን ለማየት እና በዚያውም ለመዝናናት ብዬ ናይሮቢ ሄድኩ፡፡ ባለቤቴ ሥራ ስለነበረው አልሄደም፡፡ ጓደኛዬ ትዳር ከያዘች አምስት ዓመቷ ነው፡፡ ባለቤቷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ስለሚሠራ ነው ኬንያ የሄዱት፡፡ እነርሱ ቤት አንድ ሳምንት ተቀመጥኩ፡፡ ያን ጊዜ ታድያ የኔን ትዳር ትዳር መሆኑን ተጠራጠርኩት፡፡ ጓደኛዬ ባለቤቷን በስሙ አትጠራውም፤ እርሱም እንዲሁ፡፡ ደክሞት ከመጣ እግሩን ታጥባላች፤ እርሱም እንዲሁ፡፡ ምግብ ሲበሉ እንደተጎራረሱ ነው የሚጨርሱት፡፡ ልጆቻቸውን መንከባከቡን፣ ቤት ውስጥ የሚከወነውንም ሆነ ሌላውንም አብረው ነው የሚያደርጉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኃይል ይከራከራሉ፤ ሊደባደቡ ነው ብዬ ስፈራ ለጥቂት ጊዜ ይኳረፉና ግን መልሰው ይፋቀራሉ፡፡
👉 አንድ ቀን ታድያ ጓደኛዬን፦
«ለመሆኑ ተጣልታችሁ ታውቃላችሁ?» ስል ጠየቅኳት፡፡
«በጣም እንጂ እኛ መጣላትንም መፋቀርንም እናውቅበታለን፤ ተጣልተን ተጣልተን ወጥቶልናል፡፡ ከጠብ በኋላ የሚኖረን ፍቅር ሁልጊዜ ምነው በተጣላን ያሰኘኛል» አለችኝ፡፡
🍀 ከዚያም ወደራሴ ተመልሼ አሰብኩ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ተጣልተን አናውቅም፡፡ አያድርሰውና አንድ ቀን ብንጣላ እንዴት እንደ ምንታረቅ የምናውቅበት አይመስለኝም፡፡ ክፉን አርቅ አልኩ ለራሴ፡፡ ግን እኛ ተጠባብቀን ነው ወይስ ተፈቃቅረን ነው የምንኖረው ብዬም ራሴን ጠይቄዋለሁ፡፡ ሳስበው ግን በመጠባበቅ እንጂ በመነፋፈቅ የምንኖር አይመስለኝም፡፡ እናም ትዳሬን ጠላሁት» አለችኝ፡፡
👉 ችግሯ ገብቶኛል፡፡ አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፦ «ላንቺ ፍቅር ማለት የጠብ አለመኖር ነው? ወይስ ጠብን ማሸነፍ? አልኳት፡፡
ቀና ብላ አየችኝና አልመለሰችልኝም፤ ዝም ብላ አሰበች፡፡
«ለመሆኑ ለምን እንደማትጣሉ ታውቂያለሽ?» አልኳት፡፡
«ለምን ይመስልዎታል?» ብላ እኔኑ መልሳ ጠየቀችኝ፡፡
"የማትጣሉት ስለማትገናኙ ይመስለኛል፡፡ የት ተገናኝታችሁ? የት ተነጋግራችሁ? የት ተከራክራችሁ? የት ተቀራርባችሁ ትጣላላችሁ? መጋጨትኮ ከመቀራረብ የሚመጣ ነው፡፡ እናንተ ጠብን አይደለም ያሸነፋችሁት፤ ጠብን ነው የሸሻችሁት፡፡ አለመሞት እና ሞትን ማሸነፍ ይለያያል፡፡ አለመጣላትና ጠብን ማሸነፍም እንዲሁ፡፡"
«ሐኪሞች ለምን ክትባት እንደሚወጉን ታውቂያለሽ አይደል? ክትባቱ የሚሠራው ከሞተ ቫይረስ ነው፡፡ ለምን? ያ የተዳከመ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ሲገባ ሰውነታችን ጦርነት ተከፈተብኝ ብሎ ራሱን ያዘጋጃል፤ መድኃኒት ያመርታል፡፡ ራሱን በሽታ ለመከላከል ዝግጁ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ልምድ አዳበረ፤ በሽታውን እንዴት እንደሚያሸንፍ ኃይል እና ዐቅም ገንዘብ አደረገ ማለት ነው፡፡
👉 ትዳርም ይኼ ክትባት ያስፈልገዋል፡፡ ወደፊት ከባዱ የትዳር ቫይረስ መጥቶ በበሽታ እናንተን ጠራርጎ ከመውሰዱ በፊት ደካማውን ቫይረስ መከተብ ያስፈልጋችኋል፡፡ ኃይል እና ዐቅም መፍጠር ያስፈልጋችኋል፡፡ ያልተከተበ ልጅ እና የተከተበ ልጅ ልዩነታቸው የሚታወቀው በሰላሙ ጊዜ አይደለም፡፡ ወረርሽኙ ሲገባ ነው፡፡ ያን ጊዜ ማን መቋቋም እንደሚችል ይታያል፡፡
👉 ሁለታችሁም በየፊናችሁ ትውላላችሁ፡፡ ከዚያ ወደቤት ትገባላችሁ፡፡ ራት ትበላላችሁ፡፡ ይቀጥላል፡፡ ቤትም ውስጥ ብትሆኑ አንቺ ጓዳ ነሽ፤ እርሱም ቴሌቭዥን እያየ ነው፡፡ ልቅሶ ስትሄዱ እርሱ ከወንዶች ጋር ነው አንቺ ከሴቶች ጋር ነሽ፡፡ ዓመት በዓል ሲመጣ እርሱ በግ ይገዛል፣ አንቺ ዶሮ ትገዣለሽ፡፡ እርሱ በቱታ ጎምለል ጎምለል ይላል፤ አንቺ በሐበሻ ቀሚስ ጉድጉድ ትያለሽ፡፡ ይቀርባል ትበላላችሁ፡፡ በቃ!!!
👉 "ወዳጄ የማይፈስ ውኃ ከድንጋይ ጋር አይጋጭም፤ የረጋ ውኃ ይሻግታል እንጂ ግጭት የለበትም፡፡" ወንዝ ሆኖ ሲወርድ ግን አረኹ ገደሉ፣ ዐለቱ ቋጥኙ ይላተመዋል። ለመላተም አይሄድም፤ ሲሄድ ግን ይላተማል፡፡ ከመኖር ብዛት ታድያ ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚህ ብኋላ ኩልል ብሎ መፍሰስ ነው፡፡ እዚያ ደረጃ ለመድረስ ግን ስንት ትግል፣ ስንት ልትሚያ፣ ስንት ውጣ ውረድ አለ፡፡ ይኼ ሁሉ ወንዝ ማን ቦይ ቀድዶለት መሰለሽ የሚፈስሰው? በዘመናት እየታገለ በጠረገው መንገድ እኮ ነው እንዲህ አምሮ ሲፈስስ የምታይው፡፡
👉 ትዳርም እንዲሁ ነው; እድገት ካለው፤ ሕይወት ካለው ይፈስሳል፤ ሲፈስስ ታድያ መላተም፣ መጋጨት ያጋጥማል። ይህ ግን እየተፈታ ይሄድና በኋላ የትዳር ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚያ በኋላ ኩልል እያለ መውረድ ነው፤ ፏፏቴና ዳግላስ እያለ የሚወርድ ውኃ ይኖረዋል፡፡ ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ ሕመም መሆኑ ቀርቶ ውበት ይሆነዋል፡፡
👉 አንዳንዶቹኮ ከተጋቡ በኋላ ወንድም እና እኅት ብቻ ሆነዋል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ አብሮ አዳሪ roommateዎች ሌሎቹም አብሮ ሠሪ «ባለ አክሲዮን»፡፡ አንዳንዱ ባል ገንዘብ መስጠት አይቸግረውም፤ ሃሳብ መስጠት ግን አይሆንለትም፡፡ አንዳንዷ ሚስት ቤቷን ማስተዳደር አያቅታትም፤ ባሏን ማስተዳደር ግን አይሆንላትም፡፡
🎡 ብዙዎቹ «እኛኮ አንድ ነን» ብለው የሚፎክሩት ልዩነቶቻቸውን የሚያዩበት አጋጣሚ ስለሌላቸው ነው፡፡
🌾 መች ተወያይተው?
🌾 መች ተከራክረው?
🌾 መች ተገዳድረው ያውቃሉ?
👇💝👇 ሦስት ዓይነት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ 👇💝👇
፩ኛ👉 የሚገጥሙ ባል እና ሚስት፦ እየተገዳደሩ፣ እየተጋጩ፣ እየተስማሙ፣ እየተቸገሩ፣ ችግር እየፈቱ፣ በሃሳብ እየተለያዩ፣ እየተቀራረቡ፣ እየተዋወቁ ሄደው በሂደት አንድ የሚሆኑ ናቸው፡፡
፪ኛ👉 ይጠጌ አይነኬ (የሚገጥሙ የሚመስላቸው የማይገጥሙ) ባልና ሚስት፦ የሚባሉት ደግሞ ሲታዩ የተስማሙ፣ የተፋቀሩ፣ አንድ የሆኑ፣ ጠብና ልዩነት የሌለባቸው የሚመስሉ በውስጥ ግን የተከደኑ፣ በጊዜ የሚፈነዱ፣ ያልተዳሰሱ ቁስሎች ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ በአማርኛ «ይ
ጠጌ አይነኬ» ይባላሉ፡፡ የሚገጥሙ የሚመስላቸው፤ ሰውም ሲያያቸው የሚገጥሙ የሚመስሉ፤ በእውነታው ግን መቼም የማይገጥሙ ናቸው፡፡
፫ኛ👉 ሦስተኛዎቹ ጎን ለጎን የሚሄዱ እና ምናቸውም የማይገጥም ባልና ሚስት ናቸው፡፡ አለመግጠማቸውም የሚታወቅ፤ ያልተፋቱት ለልጆቻቸው፣ ለሕግ ጉዳዮች፣ ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ እንጂ በጋብቻ ውስጥ በፍቺ የሚኖሩ ናቸው፡፡
አሁን ልጄ ራሳችሁን እዩ! መጣላት ለጋብቻ አስፈላጊ ነው እያልኩሽ አይደለም፡፡ በትዳር ውስጥ መጋጨት ብቻውን የመጠላላት ምልክት እንዳልሆነ ሁሉ፣ አለመጋጨት ብቻውንም ግን የፍቅር ምልክት አይደለም ነው የምልሽ፡፡ ለመሆኑ ለመጣላት ጊዜ አላችሁ? አንድ ወንበር ላይ መቀመጥና አብሮ መቀመጥ፤ አንድ አልጋ ላይ መተኛትና አብሮ መተኛት፤ አንድ ቤት ውስጥ መኖርና አብሮ መኖርኮ ይለያያሉ፡፡»
ከዚህ ውይይታችን በኋላ ወደ ባልዋ ሄዳ ለትዳር ጊዜ ስለመስጠት፣ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ስለመነጋገር፣ የቤት ሥራን ለሥራነቱ ብቻ ሳይሆን ለደስታ መፍጠርያነቱ አብሮ ስለ መሥራት ማንሣት ስትጀምር ነገር መጣ፡፡ <<ጭቅጭቅ ጀመርሽ!>> ይላት ጀመር፡፡ የማይስማሙባቸው ነገሮች እየታወቁ መጡ፡፡
ይገርምሃል! "በልቶ የማያውቅ ሰው ሲበላ እንደሚያመው ሁሉ፣ ተጋጭቶ የማያውቅ ሰው ሲጋጭ አያድርስብህ፡፡"

✍️💙✍️ ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ክብረት ✍️💙✍️

«አጋጭቶ የሚያጣብቅ ሸጋ ፍቅር ይስጣችሁ»

ጦማሩን ከወደዱት ለወዳጆችዎ #Share እና #Tag ያድርጉት

👇💝👇 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇💝👇
👉👉👉 https://t.me/negeretewahido
👉👉👉 https://t.me/axum7
👉👉👉 https://t.me/waldiba
💚💛👆👆👆💝👆👆👆💚💛
💚💛 በተክሊል መጋባት ምን ማለት ነው? 💚💛

ተክሊል ክብር ማለት ሲሆን ቃሉም ከለለ አከበረ ጋረደ ከሚለው ግስ የወጣ ዘር ነው። በተክሊል ወንድ «የባሏ ክብር ናት» የተባለች ረዳቱን በጽኑ ኪዳን ወይም በመንፈስ ውል የሚቀበልበት ስለሆነ የተክሊል ጋብቻ የከበረ ነው። ለሴቷም እንዲሁ።
በተጨማሪም በእግዚአብሔር ስለሚቀደስና ስለሚከበር የተክሊል ጋብቻ ቅዱስ ነው። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ በዕብ ፲፫፥፬ ላይ "መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።" ብሏል።
በኦ.ዘፍ ፩፥፳፯-፴፩ ላይ "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤ ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ።..." ተብሎ በተገለፀው መሠረት የመጀመሪያው ጋብቻ በእግዚአብሔር ፈቃድ በኤደን ገነት እንደተመሠረተ ሁሉ ዛሬም ሥርዓተ ተክሊል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል። በመሆኑም ሥርዓተ ተክሊሉ የተሟላ የሚሆነው ጸሎተ ተክሊሉ ተፈፅሞ የሚጋቡት ወጣቶች ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ብቻ ነው። በኦ.ዘፍጥ ፪፥፳፬ ላይ"ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።" ተብሎ እንደተባለም ይህ ክቡር ምሥጢር ከተፈጸመላቸው በኋላ ተጋቢዎቹ በመንፈስ አንድ አካል አንድ አሳብም ይሆናሉ።
👉 ለዚህ ክብርና የተቀደሰ ጋብቻ ለመብቃትም የሚያስፈልጉ ነገሮች፦
፩) የሃይማኖት አንድነት፡- ተጋቢዎቹ ወጣቶች በሃይማኖት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መሆን አለባቸው።
፪. ድንግልና፡- የተክሊል ሥርዓት የሚፈፀምላቸው ወጣቶች ራሳቸውን ከዝሙት ጠብቀው በድንግልና የፀኑ መሆን አለባቸው።
፫) መፈቃቀድ፡- የሚጋቡት ወጣቶች አንዳቸው ሌላውን ሊፈቅዱ ሊወዱ ያስፈልጋ፤ የሁለቱ መፈቃቀድ ሳይኖር በወላጆች ተፅእኖ ብቻ ሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈፀም አይችልም። ለዚህም ነው ተጋቢዎቹ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀርበው ሥርዓተ ተክሊሉን ሲፈፅሙ በታቦቱ ፊት መጽሐፈ ጋብቻ እየተነበበላቸው አንደኛው ሌላውን "ወድጄ ፈቅጄ ተቀብያታለሁ ወይም ተቀብየዋለሁ" ብለው ቃል የሚገቡት።
፬) እድሜ
የሚጋቡት ወጣቶች እድሚያቸው ትዳር የሚጠብቀውን ኃላፊነት ለመወጣት ብቁ ሊሆኑ ያስፈልጋል ለዚህም አስቀድሞ በፍትሐ ነገስት እንደተገለፀው ሴቷ 15 ወንዱ ደግሞ 18 ዓመት የሞላቸው መሆን አለባቸው። እንደዚህም ሁኖ ሌሎች ነገሮች ካልተሟሉ ከዚህ በላይ ቢሆን መልካም ነው።
፭) የንስሐ አባት ምስክርነት፡-
ሥርዓተ ተክሊል የሚፈፀምላቸው ወጣቶች አስቀድመው ንስሐ እየገቡ ንፅህናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የግድ የንስሐ አባት ሊይዝ ያስፈልጋል። ለንስሐ አባታቸውም ስለ ጋብቻቸውም ሆነ ስለ ማንኛውም ሕይወታቸው ሊያማክሩ ይገባል።
በዘመናችን አልፎ አልፎ እንደሚታየው «ገንዘብ ከፍዬ ወይንም ደብረ ሊባኖስ ሂጄ አገባለሁ» እያሉ ተደብቆ ሥርዓተ ተክሊል መፈፀም አይቻልም። ተጋቢዎች ካላይ የተጠቀሱትን ማሟላታቸውን በንስሐ አባት ሊረጋገጥና ይህም ሊመሰከርላቸው ያስፈልጋል። በመሆኑም የተጋቢዎች መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ኑሮ በንስሐ አባታቸው ፊት የተገለጠ ሊሆን ይገባል።
፮) የኑሮ (የኢኮኖሚ) ኣቅማቸው፡-
ሁለቱም ተጋቢዎች ወይንም ከሁለቱ አንዱ ወገን ራሱን የቻለ ሊሆን ያስፈልጋል። የኢኮኖሚ አቅማቸውም ቤተሰቡን ለማስተዳደር በቂ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል።
፯) ስለ ትዳር ማወቅ (በቂ ግንዛቤ)፡-
ተጋቢዎች ከመጋባታቸው በፊት ስለ ትዳርና አጠቃላይ ስለ ተክሊል ጋብቻ በሚገባ ሊያውቁ ይገባል። ትዳር በሦስተኛው ሰው ግፊት የሚፈፅምና ለጥቅማጥቅም ተብሎ ካልሆነም ለሙከራ የሚገባበት ሳይሆን ከልብ በመነጨ ፍቅርና ለትዳር ባለው ግንዛቤ ስለትዳር በቂ እውቀት መኖር ግድ ይላል ስለተክሊልም ቢሆን ከአባቶችና ከሰንበት ት/ቤት በቂ ዕውቀት ሊኖራቸው ይገባል።
እንግዲህ ተጋቢዎች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ካሟሉ የተቀደሰውን የሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ ከኣጽዋማት ቀናት በቀር ሊፈፀምላቸው ይችላል።
በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተፈፀመ ጋብቻ ቅዱስ ነው። በውጫዊ ተክለ ሰውነት ውበት ላይ የተመሠረተ ምስጋናም ይሁን ጥላቻ እንዲሁም ፍቅር፣ ቅድስና ከጎደላት ነፍስ የሚመነጭ ጋብቻ ግን ክፋት ነው፡፡

© ዘዋልድባ

«የተቀደሰ ጋብቻ ይስጣችሁ!!!»

ጦማሩን ከወደዱት ለወዳጆችዎ #Share እና #Tag ያድርጉት
https://www.facebook.com/sost.philip

👇💝👇 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇💝👇
👉 https://t.me/negeretewahido
👉👉👉 https://t.me/axum7
👉👉👉 https://t.me/waldiba
💚💛👆👆👆💝👆👆👆💚💛
ቀስት ወደ ፊት ሊስፈነጠር የሚችለው ወደ ኋላ በተለጠጠበት መጠን ነው።


ችግር ሲያጋጥምህ ደስ ይበልህ ከበፊቱ ወደ ተሻለው ልትስፈነጠር ነውና።ሁሌም ኢላማህን በመልካሙና በተሻለው ነገር ላይ ያነጣጥር!በፍጥነትም ትደርሳለህ።

መልካም የመስፈጠር ና የስኬት ቀን ይሁንልን ቤቲ ልክነሽ ነኝ ስኬት ማማ ላይ እንገናኝ❤️
"እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤
ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።" ብሎ በማቴዎስ ወንጌል ፮ ፥ ፴፩-፴፬ ላይ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረ እናስተውል!

በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለፊልጵስዪስ ሰዎች በላከው መልእክቱ ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦
"ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።

ፊልጵ ፬፥፬-፱

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👇💜 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 💙👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/waldiba

http://t.me/negeretewahido

http://t.me/axum7
ህብረተሰቡ የፓልም ዘይትን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ!

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምግብ ዘይቶች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ጥናቱን ዛሬ ሰኔ 5/2011 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው ይፋ ያደረገው፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ እንደገለፁት በፈሳሽ እና በሚረጉ ዘይቶች ላይ ጥናት ተደርጓል፡፡ በሚረጉ ዘይቶች ላይ የሚገኘው ‹‹ ‹‹ሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ›› ከፍተኛ መሆኑን እና በሰው ልጅ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ መሆኑ የጤና ችግር እንደሚያስከትል መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንዳሳየውም የኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ለልብ እና ለሌሎች ተዛማጅ የማይተላለፉ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ተነግሯል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ባደረገው ጥናት የፓልም ዘይት ከ50 እስከ 80 በመቶ ‹‹ሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ›› እንዳለው መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የፓልም ዘይት ደግሞ በዝቅተኛ እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል በስፋት የሚጠቀመው ነው፡፡ የጥናት ውጤቱም ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደተላከ ተገልጧል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ለንግድ ሚኒስቴር ጥቆማውን እንዳቀረበ ታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም የፓልም ዘይትን መጠቀም እንደሌለበት እና አቅም በፈቀደ መጠን ጥራት ያላቸውን ዘይቶች እንዲጠቀም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠንቅቋል፡፡

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👇💙 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 💜👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉 http://t.me/waldiba

👉 http://t.me/negeretewahido

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
💛 ዜና 💛

በ2011 ዓ.ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ያሬድና : የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የየመመሪያ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ።

በዕለቱም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

👇💚👇፨፨፨፨፨👇💛👇፨፨፨፨፨👇👇
👇✝️ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ✝️👇
👇💚👇፨፨፨፨፨👇💛👇፨፨፨፨፨👇👇
👉👉👉 http://t.me/waldiba

👉👉👉 @negeretewahido
ዲ.ን ቴዎድሮስ - ኪዳነ ምህረት እናቴ.wmv
9.1 MB
ኪዳነ ምህረት እናቴ
ምስጢረኛ የጓዳዬ...

👇💚👇፨፨፨፨፨👇💛👇፨፨፨፨፨👇👇
👇✝️ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ✝️👇
👇💚👇፨፨፨፨፨👇💛👇፨፨፨፨፨👇👇
👉👉👉 http://t.me/waldiba

👉👉👉 @negeretewahido
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

“ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል በጎዳናውም እንሄዳለን፡፡” ኢሳ. ፪ ፥ ፫

ታላቅ መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ መርሓ-ግብር
በማኅበረ ቅ/ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
💚💛👇✝️✝️✝️✝️✝️👇💚💛

✝️✝️ ስዕለት ሰሚው ቁልቢ ቅ/ገብርኤል
መነሻ ሐምሌ 17 እና 18 መመለሻ ሐምሌ 20

✝️✝️ ተአምረኛው ዘብር ቅ/ገብርኤል ከሐምሌ 18 - 19

✝️✝️ ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ከሐምሌ 18 – 19

✝️✝️ ደብረ ሊባኖስ አ/ተ/ሃይማኖት ገዳም ከነሐሴ 23 – 24

✝️✝️ ቡልጋ ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ከነሐሴ 23 - 25

✝️✝️ ስዕለት ሰሚውና እጅግ ተኣምረኛው አቡነ እጨጌ ዮሓንስ ዘጠገሮ ከነሐሴ 28 - 29

“ንእምሮሙ አበዊነ ቅዱሳን ወመካኒሆሙ ይቄዲሶ ለሰብእ”
✝️✝️ ግሸን ደብረ ከርቤ በዙር እና በደርሶመልስ

✝️👉 የዙር ጉዞ ከመስከረም 14 እስከ ጥቅምት 2
ከ100 በላይ ገዳማትና አድባራትን ያካተተ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የዙር ጉዞ በዲማ ጊዮርጊስ፣ በመርጡለ ማርያም፣ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ በአባ ጽጌ ድንግል፣ በንጉሥ ሚካኤል፣ በዳውንት፣ በተከዜ፣ በላሊበላ፣ በአቡነ አሮን፣ በደቡብ ጎንደር- ዙር አባ ገዳም፣ በአቡነ ሐራ ድንግል፣ በባህርዳር - የጣና ገዳማት (ጣና ቂርቆስ፣ ጣና ክርስቶስ ሠምራ፣ ሬማ ቅ/ወለተ ጴጥሮስ፣ ምጽሌ ፋሲለደስ፣ ዘጌ አቡነ በትረ ማርያም፣ እንጦንስ ኢየሱስ)፣ በግሼ ዓባይ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም ዙር
👉👉👉 ሙሉ የትራንስፖርት ዋጋ ግሸን ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 3000 ብር

✝️👉 ከመስከረም 14 እስከ ጥቅምት 10 በኤርትራ ዙር
ከ160 በላይ ገዳማትና አድባራትን ያካተተና ሊያመልጠዎት የማይገባ ታሪካዊ የዙር ጉዞ በዲማ ጊዮርጊስ፣ በመርጡለ ማርያም፣ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ በአባ ጽጌ ድንግል፣ በተንታ - ንጉሥ ሚካኤል፣ በዳውንት፣ በተከዜ፣ በላሊበላ፣ በወልዲያ፣ በመቐለ - ተንቤን፣ በሓውዜን - ዓዲግራት፣ በደብረ ዳሞ፣ በደቀመሓረ - አስመራ፣ በደብረ ቢዘን፣ በምጽዋ፣ በደብረሲና ማርያም፣ በከረን - ጸዓዳ ኣምባ ሥላሴ፣ በዱባርዋ ቁስቋም፣ በእንዳቦና አቡነ አብራኔዎስ፣ በመንደፈራ - ደብረ ጽጌ ዮናስ፣ በኣክሱም ጽዮን፣ በዋልድባ - (ደብረ ዓባይ፣ ሰቋር፣ ዳልሻሕ)፣ በጎንደር - ጣራ ገዳም፣ በአቡነ ሐራ ድንግል፣ በባህርዳር - የጣና ገዳማት (ጣና ቂርቆስ፣ ጣና ክርስቶስ ሠምራ፣ ሬማ ቅ/ወለተ ጴጥሮስ፣ ምጽሌ ፋሲለደስ፣ ዘጌ አቡነ በትረ ማርያም፣ እንጦንስ ኢየሱስ)፣ በግሼ ዓባይ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም ዙር
👉👉👉 ሙሉ የትራንስፖርት ዋጋ ግሸን ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 4500 ብር

✝️👉 ግሸን ደርሶ መልስ ከመስከረም 14 – 24
ከ30 በላይ ገዳማትና አድባራትን ያካተተ የግሸን ማርያም ደርሶመልስ ልዩ ጉዞ ስንሄድ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎሓ ጽዮን ማርያም፣ በዲማ ጊዮርጊስ፣ በደብረ ወርቅ ማርያም፣ በመርጡለ ማርያም፣ በገዳመ አስቄጥስ ቅ/አርሴማ፣ በመካነሰላም ኪዳነምህረት፣ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ በአባ ጽጌ ድንግል፣ በተንታ - ንጉሥ ሚካኤል ስንመለስ በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በደሴ
👉👉👉 ሙሉ የትራንስፖርት ዋጋ ግሸን ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 2200 ብር

👉✝️👉 መነሻ ቦታዎች፦
ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ አራዳ ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ፣ መገናኛ፣ ሳሪስ አቦ፣ ጀሞ 1 አደባባይ

👉👉👉 ለበለጠ መረጃ፦
0901070707 / 0941960723

✝️👇✝️ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ✝️👇✝️
👉✝️👉 http://t.me/waldiba
👉✝️👉 http://t.me/negeretewahido
ናና ሚካኤል ናና.wmv
27.9 MB
ናና ሚካኤል ናና/፪/
አዝኛለሁና በአንተ ልፅናና
ናና ሚካኤል ናና
የረዳህ አፎሚያን ሚካኤል ናና
ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና
አንተ ነህ ያዳንከዉ ሚካኤል ናና
ባህራንን ከሞት ሚካኤል ናና
ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና
እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና
ሚካኤል ደግፈኝ ሚካኤል ናና
ለመንግስቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልፅናና
ናና ሚካኤል ናና
አዝ...
ናና ገብርኤል ናና/፪/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልፅናና
ናና ገብርኤል ናና
ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና
አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና
ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና
ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና
ድምፅህን አሰማኝ ገብርኤል ናና
ነፍሴ ፅድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልፅናና
ናና ገብርኤል ናና
አዝ...
ናና ዑራኤል ናና/፪/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልፅናና
ናና ዑራኤል ናና
ቆመህ ፅዋ ይዘህ ዑራኤል ናና
ለዕዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና
ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና
እውቀት ስታድል ዑራኤል ናና
ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና
መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና
ድኘ በጸበልህ ዑራኤል ናና
በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና
እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልፅናና
ናና ዑራኤል ናና
አዝ...

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
👉 @waldiba 👈
👉 @waldiba 👈
👉 @waldiba 👈
👆👆👆👆👆👆
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ" (ሐጌ ፩፥፯-፰)
✝️ በረከቱን መሳተፍ በፈለጉ በብዙ ሰዎች ጥያቄ መሰረት ማኅበራችን የሚሰራቸውን መንፈሳዊ ግብራት በማኅበራዊ ድረገጽ መግለጥ እንጀምራለን ✝️

፩ኛ💚👉 ሙሉ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሥራ 💚👈

👉✝️👉 ፈንስሃ ገዳመ ልዳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም 👈✝️👈

👉 በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታላቁ ጻዲቅ በአቡነ ሙሴ ግብፃዊ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተፈለፈለ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ያለው፣

👉 በዚያው ዘመን ጻዲቁ ከግብፅ ባመጧቸው የሊቀ ሰማእታት ቅዱስ ጊዮርጊስና የቀዳሜ ሰማእት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥንታዊ ታቦታት ቅዳሴ ቤቱ ከብሮ 1650 ዓመታትን ያስቆጠረ #በነብር_የሚጠበቅ

👉 የጻዲቁን መካነ መቃብር ዳውንት #የዲባ_መቅደሰ_ማርያም_አቡነ_ሙሴ_አንድነት_ገዳምን የተሳለመ እስከ 55 ትውልድ ጻዲቁ ያነጻቸውን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ደጃቸውን የረገጠና ለአብያተ ክርስቲያናቱ አስፈላጊ የሆነ ማንኛውንም መብዓ ማለትም ጧፍ፣ ዕጣን፣ ዘቢብ፣ ሻማ፣ ጥላ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ ጽንሓ፣ ኩስኩስት፣ መስቀል፣ መጋረጃ፣ ምንጣፍ፣ መንበር፣ ገንዘብ፣.... የሰጠ እስከ 27 ትውልድ ሊማርለት ለታላቁ ጻዲቅ ለአቡነ ሙሴ ግብፃዊ ቃል ተገብቶለታል።

👉✝️👉 በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግንባታው ላይ ዕገዛ ለማድረግ ከፈለጉ፦
ለጥሬ ገንዘብ "ፈንስሃ ገዳመ ልዳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም" ብለው በሚከተለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገዳሙ አካውንት ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
💚👉 1000247088036 💚👈

ለቁሳቁስ ዕገዛ በስልክ አድራሻችን ተጠቅመው በማኅበራችን በኩል ወይም ለገዳሙ አበምኔት በቀጥታ በመደወል መርዳት ትችላላችሁ።
👉✝️👉 አባ ዮሴፍ የገዳሙ አበምኔት
💚👉 0906442903 / 0931496824 💚👈

👉✝️👉 ማኅበረ ቅ/ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
💚👉 0901070707 / 0941960723 💚👈

💚👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 💚👇
👉✝️👉 @waldiba
👉✝️👉 http://t.me/negeretewahido

👉✝️👉 https://www.facebook.com/252762598223194/posts/1382517365247706/
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

💚💛 ምስጢረ ጥምቀት 💚💛

👉 ከወደዱት #Like #Share #Tag #Comment ቢያደርጉ ያተርፉበታል እንጅ አይከስሩበትም።

ጥምቀት ማለት “አጥመቀ” አጠመቀ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ምስጢረ ጥምቀት በምስጢራዊው / በሃይማኖታዊው / ፍቺው በተጸለየበት ውሃ ውስጥ በሥላሴ ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው።

✝️ የጥምቀት አመሠራረት
የምስጢረ ጥምቀት መሥራች ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የመሠረተውም በሦስት መንገድ ነው። እነርሱም፡-

👉 በተግባር፡- ራሱ ተጠምቆ እንድንጠመቅ አስተምሮናል /አርአያ ሆኖናል/ ማቴ 3፡13
በትምህርት፡- “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” / ማር 16፡16 / ”እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” / ዮሐ 3፡3-6 /
👉 በትዕዛዝ፡- “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” በማለት ለቅዱሳን ሐዋርያት ትዕዛዝ በመስጠት መስርቶታል። / ማቴ 28፡19-20 /

✝️ የጥምቀት አከፋፈል / ዓይነቶች /
ጥምቀት በሁለት ይከፈላል።
👉 የንስሐ ጥምቀት ማቴ 3፡11 ፡ ማር 1፡4 ፡ ሐዋ 19፡4
👉 ልጅነት የምታሰጠዋ ጥምቀት ገላ 3፡26 ፡ ቲቶ 3፡5 ፡ 1ኛጴጥ 1፡23 ልጅነት የምታሰጠዋ ጥምቀት አንዲት ናት / ኤፌ 4፡4-5 / ነገር ግን በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ልትፈጸም ትችላለች።
እነርሱም፦

💚 በውሃ ጥምቀት፡-
ማለት በአበው ካህናት አማካኝነት በተጸለየበት ውሃ ውስጥ በሥላሴ ስም ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከባህረ ዮርዳኖስ ዳግም ልደትን በመወለድ የቅ/ሥላሴ ልጆች የምንሆንበት ነው። ዮሐ 3፡3-6፣ ሉቃ 3፡16 ፡ ሐዋ 1፡5 ፡ ሐዋ 2፡1-4 ፡ 1ኛ ቆሮ 12፡13

💛 በደም ጥምቀት፡-
ይህ የሰማዕታት የጥምቀት ዓይነት ነው። የክርስትናን እምነት በመማር ላይ ሳሉ ወይም ተምረው ሳይጠመቁ ወይም ሁለቱንም ሳያውቁ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ብለው መሥዋዕት መሆናቸውን ተመልክተው “የእነዚህ የክርስቲያኖች እምነት እውነተኛ ነው” በማለት መስክረው በሰማዕትነት የሚሞቱ ሰዎች ደማቸው /ስቃያቸው/ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ጥምቀት ይቆጠርላቸዋል። ኃጢአታቸውም ይሰረይላቸዋል።

በእንባ መጠመቅ፦
አንድ ሰው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለአማናዊቷ የሕይወት መንገድ፣ አብዝቶ እያሰበና እያዘነ ቢኖርና የልጅነት ጥምቀትን ለማግኘት በመሻት ላይ ሳለ ለመጠመቅ ካህናትን በማጣቱ ምክንያት ሳይጠመቅ ቢሞት እንባው ከመንበረ ጸባዖት ደርሳ የልጅነት ጥምቀትን ታስገኝለታለች።

✝️ የጥምቀት አፈጻጸም
የተጠማቂው ግዴታ፡- ተጠማቂው ንዑሰ ክርስቲያን ከሆነ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርቶችን ተምሮ እምነቱ የተመሰከረለት መሆን አለበት። ሕጻናት የሆኑ እንደሆኑ ግን ለሕጻናቱ የክርስትና እናትና አባት ሊሆኑ የመጡት ሰዎች ስለሕጻናቱ እምነት መስክረውላቸው እንዲጠመቁ ይደረጋል።

✝️ አጥማቂው ማን ነው?
እንዲያጠምቁ ስልጣን ያላቸው ከክህነት ደረጃዎች ውስጥ ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኢጲስ ቆጶሳት፣ ቆሞሳትና ቀሳውስት ብቻ ናቸው፤ ዲያቆናት እንዲያጠምቁ አልተፈቀደላቸውም። ማቴ 28፡19 እና ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 3 ተመልከቱ።

✝️ የክርስትና ስም አወጣጥ
ስም አንድ ሰው ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት ነው። አንድ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት ስሞች ሊኖሩት ይችላል።
👉 አባትና እናት የሚያወጡለት ስም / የተጸውኦ ስም /
👉 በጥምቀት ጊዜ የሚወጣለት ስም / የክርስትና ስም /

በክርስቶስ የሚያምን ሰው ክርስቲያን ሲባል እምነቱ ደግሞ ክርስትና ይባላል። ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ወገን የሆነ ማለት ነው። በመሆኑም በክርስቶስ አምነን በሥላሴ ስም መጠመቃችንን የሚገልጸው ስም ስመ ክርስትና ይባላል። ስያሜውም ተጠማቂው ከተጠመቀበት ዕለት ጋር ተያይዞ ሊሰየም ይችላል።

✝️ የክርስትና አባትና እናት
በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በ40 እና በ80 ቀናቸው ለሚጠመቁ ሕጻናት ስለ እምነታቸው ባለው ነገር ሁሉ ኃላፊነት የሚወስዱ የክርስትና አባትና እናት እንዲኖራቸው ያደረጉት በ4ኛው መ/ክ/ዘ የነበረው የቤተ ክርስቲያናችን የመጀመሪያው ኢጲስ ቆጶስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ናቸው። ዓላማውም መንፈሳዊ ዝምድናን / አበ ልጅነትን / ማጠናከሪያ መንገድ ነው። በአበ ልጅነት የተዛመዱ ሰዎች በጋብቻ መዛመድ አይችሉም። በሥጋ የተዛመዱ ከ7ተኛ የዝምድና ሐረግ በኋላ መጋባት የሚፈቀድ ሲሆን በአበ ልጅ ግን የተዛመደ ግን የቁጥር ገደብ የለውም / ፈጽሞ መጋባት አልተፈቀደለትም / ይህ የሚያሳየው ከሥጋ ዝምድና ይልቅ ክብር የሚሰጠው ለመንፈሳዊ ዝምድና መሆኑን ነው።

✝️ ከክርስትና አባትነትና እናትነትን የሚከለክሉ ነጥቦች
👉 የሥጋ ዝምድና ያላቸው
👉 የጋብቻ ዝምድና ያላቸው
👉 ዕድሜያቸው ለማስተማር ለማሳመን ያልደረሰ
👉 እምነት ትምህርት ችሎታ የሌላቸው
👉 እምነታቸው ከተጠማቂው ጋር ተመሳሳይ ያልሆነ
👉 የጾታ ሁኔታ በተመለከተ ወንድ - ወንድን ሴት - ሴትን ያነሣል እንጂ ወንድ - ሴትን፣ ሴት - ወንድን ክርስትና ማንሣት አይፈቀድላቸውም።

✝️ የክርስትና አባትና እናት ያለባቸው ኃላፊነት
ክርስትና ያነሷቸውን ልጆች በሥጋ ከወለዷቸው ልጆች ሳይለዩ ሕጻናቱ ዕድሜያቸውም ለትምህርት ሲደርስ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት የማስተማር ግዴታ እንዳለባቸው ቃል ይገባሉ። በገቡት ቃል መሠረት በተግባር የመተርጎም ኃላፊነት አለባቸው።

✝️ ማዕተብ /ክር/ ማሰር
ማዕተብ - ዐተበ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አመለከተ ማለት ነው። ስለዚህ ማዕተብ ማለት ምልክት ማለት ነው። በሃይማኖት አምነው ለተጠመቁ ክርስቲያኖች የሚሰጥ ምልክት / መታወቂያ / ወይም ማኅተም ነውና። ማዕተብ ማሰርን ያስተማረው በ6ኛው መ/ክ/ዘመን የነበረው ታላቁ ሊቅ አባታችን ያዕቆብ ዘእልበረዲ (ዘአልቦ ረዳኢ) ነው። ስለ ማዕተብ በመጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል። በብሉይ ኪዳን የነበሩ አባቶች ለእምነታቸው መገለጫ ምልክት ነበራቸው። ለምሳሌ ለአበ ብዙኃን አብርሃም ግዝረት ተሰጥቶት ነበር። ሮሜ 4፡13 ፡ ዘፍ 17፡9-14
👉 የማዕተብ ሦስት ዓይነት ቀለም ምክንያቶች፡- ይህ የሦስትነት ምሳሌ ነው። ሦስቱ ክሮች ደግሞ በአንድ ተገምደው መሠራታቸው የአንድነቱ ምሳሌ ነው።

👉 ክርስቲያን ማዕተብ ማሰሩ ያለው ተቀሜታ፡-
ስለ ክርስቲያንነቱ ሳያፍር ይመሰክርበታል
አጋንንትን ድል ይነሣበታል - ተጸልዮበት ተባርኮ የሚታሠር ነውና ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያገኝበታል

✝️ በምስጢረ ጥምቀት የሚታይ አገልግሎት
ተጠማቂው ውሃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ሲል
ሥርዓተ ጸሎቱ
ተጠማቂው ነጭ ልብስ ሲጎናጸፍ ወዘተ. . .

✝️ በምስጢረ ጥምቀት የሚገኝ የማይታይ ጸጋ
👉 ውሃው ወደ ማየ ገቦነት ሲለወጥ
👉 የእግዚአብሔር ልጅነትን ሲያገኝ
👉 የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ፡ ንጸሕናን ቅድስናን ገንዘብ ሲያደርግ ወዘተ. . .
ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት ምሥጢር ነው።
ማር 16÷16፣ ዮሐ 3÷5፣ ቲቶ 3÷5፣ 1ኛ ጴጥ 3÷21

ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 አመቱ በዮርዳኖስ ፣ በዩሐንስ እጂ ተጠምቆ ጥምቀታችንን መሰረተልን፣
ቀደሰልን።

ማቴ 3÷15፣ ቆላ 2÷14

✝️ የጥምቀት አስፈላጊነት
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከኒቂያ ጉባኤ በኋላ ከተነሱት አባቶች አንዱ “በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው
ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም” ራእይ ፳፥፮ የሚለውን የወንጌላዊው
ዮሐንስን አባባል በተረጎመበት የእግዚአብሔር ከተማ በሚለው መጽሐፉ ላይ ፊተኛው ትንሣኤ የተባለው ሀብተ
ወልድና ስመ ክርስትና የምናገኝበት ጥምቀት እንደሆነ ገልጿል

ክርስቶስን መሠረት ያደረገ እምነት ሁሉ “ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ
አይችልም” ዮሐ. ፫፥፫ የሚለው የጌታ ትምህርት መመሪያው ሊሆን ግድ ነው፡፡ ጌታ እንዳስተማረውም ያለጥምቀት ድኅነት የለም፡፡
ጥምቀት በሚታየው አገልግሎት በውኃ ውስጥ ገብቶ መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ማለት
ሲሆን በሚታየው አገልግሎት የሚገኘው የማይታይ ጸጋ ግን ብዙ ነው፡፡ የሚከተሉት በጥምቀት የሚገኙ የማይታዩ
ጸጋዎች ናቸው፡-
👉👉 ድኅነት
“ያመነ የተጠመቀ ይድናል” ማር. ፲፮፥፲፮፡፡ የድኅነት ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ
እንደተናገረው ዘላለማዊ ድኅነትን ለማግኘት የሚሻ ሁሉ ወልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት አምኖ መጠመቅ ግድ
ይለዋል፡፡
ከጌታ ከቃሉ የተማረ ቅዱስ ጴጥሮስ የመምህሩን ትምህርት መሠረት አድርጎ “ጥቂቶች ማለት ስምንት
ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፤ የእግዚአብሔር ትዕግስት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡
ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም” ብሏል፡፡
፩ኛ ጴጥ. ፫፥፳-፳፩፡፡ ኖኅና ቤተሰቡ የዳኑበት ውኃ ምሳሌነቱ የጥምቀት መሆኑን ገልጾ አሁንም በክርስቶስ
የባሕርይ አምላክነት ያመኑ ሁሉ በጥምቀት ድኅነትን እንደሚያገኙ በግልጽ ቃል ተናግሯል፡፡
👉 መዳን ስንል
የእግዚአብሄርን መንግሥት ወርሶ የዘላለም ሕይወት ባለቤት መሆን ማለት ነው፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና
ይግባውና መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ አይሁድ ለነበረው ለኒቆዲሞስ ዘርግቶለት በነበረው የሌሊት
የትምህርት መርሐ ግብር ትምህርቱን በተመስጦ ኅሊና በሰቂለ ልቡና ይከታተል ለነበረው ለኒቆዲሞስ የድኅነት በሩ
ጥምቀት እንደሆነ ገልጾለታል “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ
እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ ይችልም” ዮሐ. ፫፥፭፡፡

👉👉 ዳግም ልደት
ዳግም ልደት ያስባለው ከሥጋ ልደት የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን ስህተት ምክንያት አጥተነው
የነበረውን የልጅነት ጸጋ የምናስመልሰው በውኃ በምናደርገው ጥምቀት ነው፡፡ ዳግም ከሥላሴ የምንወለደው በውኃ በምናደርገው ጥምቀት ነው ጌታችን “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገባም” ዮሐ. ፫፥፭ በማለት ለኒቆዲሞስ መናገሩን ልብ ይሏል፡፡ ጌታችን እንደተናገረው ጥምቀት የልጅነትን ጸጋ የምናገኝበት ምሥጢር ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጥምቀት ዳግም ከእግዚአብሄር የምንወለድበት ታላቅ ምሥጢር መሆኑን እንዲህ ሲል አስተምሯል “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፉ ዘር አይደለም” ፩ኛ ጴጥ. ፩፥፳፫፡፡ ይህ ጥምቀት የዘላለም ሕይወት እንደሚያሰጥ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ደግሞ “ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች” አለ፡፡ መዝ. ፳፩፥፳፱"፡፡ አቡቀለምሲስ ዮሐንስም “እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ” ብሏል ዮሐ ፩፥፲፫፡፡ ጌታችን በግልጽ ቃል እንደተናገረው የልጅነት ጸጋ የሚገኘው በውኃ
ውስጥ ብቅ ጥልቅ በማድረግ በሚፈጸመው ገቢር እንጂ አንዳንዶች ከልቦናቸው አንቅተው እንደሚናገሩት ቃለ ወንጌልን በመስማት ብቻ የሚገኝ እይደለም፡፡
👉👉 ሥርየተ ኃጢአት

“ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት” የቁስጥንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖት፡፡ በ381 ዓ.ም. በቁስጥንጥንያ በመቅዶንዮስ ክህደት ምክንያት ከመላው ዓለም የተሰባሰቡት 150 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መቅዶንዮስን ካወገዙ በኋላ ባወጡት አንቀጸ ሃይማኖት ላይ ካሰፈሩት አንቀጽ አንዱ በጥምቀት ሥርየተ ኃጢአት እንደሚገኝ ነው፡፡
እነዚህ አባቶች በቅዱስ መጽሐፍ የሰፈረውን በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች አማካይነት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሾልኮ የገባን የስህተት ትምህርት ለማጥራት፣ እምነትን ለማጽናትና ምእመናንን ከውዥንብር ለመታደግ አንቀጸ ሃይማኖትን ወስነዋል፡፡ የአበው ውሳኔ መጽሀፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ መሆኑን ከሚከተሉት ማስረጃዎች እምንገነዘበው እውነታ ነው፡- በድንቅ አጠራሩ ለአገልግሎት የተጠራው ቅዱስ ጳውሎስ ከኃጢአቱ ይነጻ ዘንድ“አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ”መባሉን አስተውሉ፡፡
የሐዋ. ሥራ ፳፪፥፲፮፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ሃምሣ ተሰብስበው ለነበሩት አይሁድና ወደ ይሁዲ
እምነት ለገቡት በትምህርቱ ልቡናቸው በተነካ ጊዜ “ምን እናድርግ?” ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸው “ንስሐ ግቡ
ኃጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ” የሚለውን ነበር፡፡ የሐዋ. ሥራ
፪፥፴፯-፴፰፡፡ ይህ ታዲያ ከሌላ በረት ለመጡ በጎች እንጂ በበረቱ ተወልደው በበረቱ ላደጉት በጎች አይደለም፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ማለቱ የእርሱን የባሕርይ አምላክነት ለመግለጽ እና ዓለም እንዲቀበለው
ለማስተማር እንጂ ጥምቀት መፈጸም የሚገባው በሥላሴ ስም መሆኑን ጌታችን ራሱ አስተምሯል፡፡ ማቴ ፳፰፥፲፱፡፡

👉 ክርስቶስን በሞቱ የምንመስልበትና በትንሣኤው የምንተባበርበት

“ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁ እኛ በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን” ሮሜ. ፮፥፫-፬፡፡ ማጥመቅ በፈሳሽ ውኃ ነው፤ ጥልቅ ውኃ በማይገኝበት ጊዜ ግን ውኃ በሞላበት ገንዳ ይፈጸማል ይህም ካልሆነ ውኃ ቀድቶ የተጠማቂውን መላ አካል ውኃው እንዲያገኘው በማድረግ በእጅ እየታፈኑ ያጠምቁታል፡፡ በጥምቀት ጊዜ የተጠማቂው አካል በውኃ እንዲጠልቅ መደረጉ “ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን” ሮሜ. ፮፥፬ የሚለውን በገቢር ለመግለጽ ነው፡፡ እንዲሁም ተጠማቂው ከውኃ ውስጥ ብቅ ማለቱ “በጥምቀት ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር ሥራ በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሳችሁ” ቆላ. ፪፥፲፪ ያለውን እንዲሁ በድርጊት ለማሳየት ነው፡፡
አጥማቂው ካህን “አጠምቀከ በስመ አብ አጠምቀከ በስመ ወልድ አጠምቀከ በስመ መንፈስ ቅዱስ” እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያደረገ ድርጊቱን ሦስት ጊዜ መፈጸሙ በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት አምኖ መጠመቁን ለማጠየቅ ሲሆን እንዲሁም የጌታን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር አድሮ መነሳቱንና ተጠማቂዎችም ኋላ በትንሣኤ ዘጉባኤ ንቃ መዋቲ የሚለው አዋጅ ሦስት ጊዜ በሚታወጅበት ጊዜ በቀዋሚ አካል በምትናገር አንደበት ከራስ ጠጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ከቁጥር ሳይጎድሉ ከሰውነታቸው ሳይከፈሉ ወንድ በአቅመ አዳም ሴት በአቅመ
ሔዋን መነሳታቸውን ለማዘከር ነው፡፡ ስለዚህ “ከክርሰቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር
እናምናለን” ሮሜ. ፮፥፰ በሚለው የሐዋርያው ቃለ ትምህርት መሠረት ጥምቀት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሞቱ የምንመስልበት በትንሣኤውም
ርበት ታላቅ ምሥጢር ነው፡፡

👉 የክርስቶስ አካል መሆናችን የሚረጋገጥበት

በዘመነ ብሉይ የአብርሃም ወገኖች የአብርሃም ልጆች መሆናቸው ይረጋገጥ የነበረው በግዝረት ነበር፡፡ግዝረት
በኦሪቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ መለያ ነበር፡፡ ያልተገረዘ ሁሉ ከሕዝቡ ተለይቶ እንዲጠፋ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ
ነበር፡፡ ዘፍ. ፲፯፥፲፬፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በአምሳልነት ሲፈጸም የኖረው ግዝረት በዘመነ ሐዲስ
በጥምቀት መተካቱን አበክሮ ያስገነዝባል “በክርስቶስ ገዛሪነት የኃጢአትን ሕዋስ ሰንኮፍ ቆርጦ በመጣል ሰው ሰራሽ ያይደለ ግዝረትን የተገዘራችሁበት፤በጥምቀት ከእሱ ጋር ተቀበራችሁ ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር
ረዳትነትም በሃይማኖት ከእሱ ጋር ለመኖር በእስዋ ተነሣችሁ” ቆላ. ፪፥፲፩-፲፪፡፡ ግዝረት ለሕዝበ እግዚአብሔር
የአብርሃም የቃል ኪዳን ተሳታፊዎች የመሆናቸው መለያ ምልክት እንደነበር ሁሉ ጥምቀት ደግሞ በጌታ በኢየሱስ
ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የጸጋው ግምጃ ቤት ከሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ጸጋ ተሳታፊ
ያደርጋቸዋል፡፡ በጥምቀት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን “ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ ትሆኑ
ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና” ገላ. ፫፥፳፯ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው
በጥምቀት ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንሆናለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ያደሰውን አዲሱን ሰውነት የምንለብሰውና የክርስቶስ ተከታዮች የምንሆነው በጥምቀት ነው፡፡ ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ጥምቀትም አንዲት ናት፤ አትከለስም፣ አትደገምም፡፡ ኤፌ. ፬፥፭፡፡

ማጠቃለያ፡-
👉 ምስጢረ ጥምቀትን መፈጸም የሚችሉት ካህናት ብቻ ናቸው፡፡
👉 ምስጢረ ጥምቀት የምስጢራት ሁሉ መግቢያ በር ነው፡፡
👉 ምስጢረ ጥምቀት አይደገምም፡፡

የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን::

💚👉ፔጃችንን Like & Follow ያድርጉ 💚👈

💚👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን💚👇
👉✝️👉 http://t.me/waldiba
👉✝️👉 http://t.me/axum7
👉✝️👉 http://t.me/negeretewahido