Voa Amharic
3.75K subscribers
348 photos
40 videos
2 files
624 links
ይህ voa amharic ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሲሰራጭ የነበረውን አሰቃቂ ግድያ የፈፀሙት የህግ አስከባሪዎች እና ተባባሪዎቻቸው እንደነበሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ኮሚሽኑ ምስክሮችን በማነጋገር እንዳጣራው ከሆነ ክስተቱ የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ውስጥ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው። የዚህም ዕለት ከዳኝነት ውጪ በተፈፀመ ግድያ አስክሬኖች እና አንድ በህይወት የነበረ ሰው በእሳት ተቃጥለዋል ። ለዚህ አሰቃቂ ግድያ መነሻው አንድ ቀን ቀድሞ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ በዚያ ዕለት «በመከላከያ ሠራዊት ታጅበው ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ፤ ወደ ማንኩሽና ወደ አሶሳ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ ጥቃት» ፈፅመው 3 ሲቪሎችን እና 20 የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ገድለዋል ብሏል። እንዲሁም 14 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል። ኢሰመኮ በመግለጫው ይፋ እንዳደረገውም ቪዲዮ ላይ የተቃጠሉት ሰዎች አስክሬን በፀጥታ ኃይሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ እና የተገደሉ 10 ሰዎች ናቸው። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ከነነብሱ ተቃጥሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ድርጊቱን «ፈጽሞ ከሕግ አስከባሪ አባሎች የማይጠበቅ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት» ነው በማለት ጥቃት ፈፃሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና የሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲያገኙ ጠይቋል። ጉዳዩን በተመለከተ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ትናንት ባወጣው መግለጫ መንግሥት « ፍፁም ከሰብአዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል» ብሏል።
የአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፀመ። በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል የተፈፀመው የቀብር ስነ ሥርዓታቸው ከፍ ባለ ክብርና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነበር። አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ባለፈው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ነበር በ84 ዐመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት። ፓትርያርኩ ትናንት በመስቀል አደባባይ የሽኝት ሥነ ሥርዓት የተደረገላቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተው ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
በዛሬው ሥርዓተ ቀብራቸው ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተው የአበባ ጉንጉን እንዳኖሩ በስፍራው የነበረው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ በላከልን ዘገባ ገልጿል።
ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ በትንሹ 19 ስደተኞች ሰምጠው ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለስልጣናት አስታወቁ። የሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እንዳሉት 23 የሚሆኑ የግብፅ እና የሶርያ ስደተኞች ቅዳሜ ጠዋት ቶብሩክ ከተባለችው ከተማ ተነስተው ነበር። ሶስት ስደተኞችን ከሞት መታደግ የተቻለ እንደሆነ እና ሰዎቹም ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። የአንድ ሰው አስክሬን የተገኘ ሲሆን ፍለጋው መቀጠሉንም የጠረፍ ጠባቂዎቹ አስታውቀዋል። የጎርጎሮሲያኑ 2022 በገባ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ብቻ ቢያንስ 192 ሰዎች የሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው ሞተዋል። ከዚህም ሌላ እንደ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መረጃ ከ2,930 በላይ ስደተኞች ተይዘው ሊቢያ ወደሚገኝ የስደተኞች ማቆያ ወይም እስር ቤት ተወስደዋል። ባለፈው የጎርጎሮሲያኑ ዓመት ብቻ ከ32ሺ በላይ ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ የተመለሱ ሲሆን 1553 የሚሆኑ ደግሞ ሰምጠው እንደሞቱ ይታመናል።
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ሰሜን አፍሪቃ ላይ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ። የፈረንሳይ ዜና ምንጭ እንደዘገበው ቱኒዚያ፣ ሞሮኮ እና ሊቢያ የመሳሰሉ ሀገራት በተለይ የስንዴ ምርቶችን ካሁኑ ማጠራቀም ጀምረዋል። ሩሲያ እና ዩክሬን ለእነዚህ ሀገራት ዋና የስንዴ አቅራቢዎች ነበሩ። እንደ አንድ የቱኒዚያ ሱፐር ማርኬት ባለቤት ገለፃ ባለፉት ቀናት ውስጥ የአንድ «ኩስኩስ» ምግብ ዋጋ በ 700 በመቶ ጨምሯል። የዱቄት ዋጋ በሶስት እጥፍ ጨምሯል። እንደ አውሮፓ ህብረት ገለፃ ባለፈው አመት ሩሲያ በዓለም ትልቋ ስንዴ ሻጭ ሀገር ነበረች። ዩክሬን ደግሞ ከዓለም አምስተኛን ስፍራ ይዛ ነበር።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ጦርነቱ በዚሁ ከቀጠለ ሀገራቱ የሚያቀርቡት የጥራ ጥሬ መጠን ስለሚቀንስ በተለይ ደሀ ሀገራት ይበልጥ ተጎጂ እንደሚሆኑ የጀርመን የልማት ሚኒስትር አሳስበዋል። ሚኒስትር ስቬንያ ሹልሰ ለአንድ የጀርመን ጋዜጣ እንደገለፁት የስንዴ እጥረቱ በደሀ ሀገሮች ላይ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትም ሊፈጥር ይችላል። ስለሆነም የዓለም አቀፍ የድጋፍ መርሃ ግብሮች ሌሎች አማራጮችን ማጤን እንዳለባቸው ሚንስትሯ ተናግረዋል።
የሩሲያ ወታደሮች የተከለከሉ የፎስፈረስ ኬሚካል ቦምቦችን በዩክሬን ምስራቃዊ ክፍል ባደረሱት ጥቃት ተጠቅመዋል ሲሉ የአካባቢው የፖሊስ ተወካይ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈፀመው ፖፓስና በተባለ አካባቢ ለእሁድ አጥቢያ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በምትገኘው ዶንባስ አንድ ስደተኞች የተሳፈሩበት ባቡር ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የዮክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል። በተመሳሳይ በዶንባስ ስደተኞች በተጠለሉባቸው ሁለት የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናት ላይ ተኩስ መከፈቱን ዩክሬን አስታውቃለች። የዩክሬን ሰብአዊ መብት ተሟጋች ሊውድሚላ ዴኒሶቫ ሩሲያ ለእሁድ አጥቢያ የተከለከለ ፎስፈረስ ተጠቅማ ጥቃት ፈፅማለች « ይህ ደግሞ የጦር ወንጀል ነው» ሲሉ ሩሲያን ከሰዋል። ሮይተርስ ዜና ምንጭ ሩሲያ ተጠቀመች ስለተባለው የፎስፈረስ ቦንብ በገለልተኛ አካል አለመጣራቱን ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ በምእራብ ዩክሬን የምታደርሰውን ጥቃት ማጠናከሯ ተዘግቧል። እንደ ዩክሬን ገለፃ ከ30 በላይ ሚሳኤሎች ተተኩሰው ቢያንስ 35 ሰዎች ሲሞቱ 134 ሰዎች ቆስለዋል። ጥቃቱ የደረሰው የአሜሪካ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ኃይሎች ለዩክሬን የሰላም አስከባሪ ኃይል ስልጠና ይሰጡ በነበረበት የጦር ሰፍር ላይ ነው። የጦር ሰፈሩ ከጎረቤት ሀገር ፖላንድ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን አንደኛ ጉባኤ አጠናቋል። ጉባኤው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህን ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መርጧል። በተጨማሪም ፓርቲው 45 የስራ አስፈጻሚ እና 225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል። ጉባኤው በሀገሪቱ ለተከሰተው የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረት አስቸኳይ መፍትሄ በመሻት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ «አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ» መጠናቀቁን ፓርቲ የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተናግረዋል። ከጉባኤው መጀመር አንድ ቀን አስቀድሞ እስከ የጉባኤው መጠናቀቅ የመንግስት የመገናኛ ብዙኃንን ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ሽፋን ሰጥተውታል። የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ «ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን በማከናወን እንዲሁም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስፈላጊ የሠነድ ማሻሻያዎችን በማድረግ እንዲያስገቡ » ባለፈው የየካቲት ወር አሳስቦ ነበር። የብልጽግና ፓርቲ ያካሄደው ጉባኤ ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ምን የተለየ ነገር ይዞ ይመጣ ይሆን ? ምንስ ተጨባጭ ለውጥ ይዞ ይመጣል ትላላችሁ ፤ ሃሳባችሁን አካፍሉን።
ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሲሰራጭ የነበረውን አሰቃቂ ግድያ የፈፀሙት «የመንግሥት የፀጥታ አባላት»ና ተባባሪዎቻቸው እንደነበሩ ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትናንት እሁድ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ የአይን ምስክሮችን በማነጋገር እንዳጣራ በገለጸበት መግለጫው እንደጠቀሰው ክስተቱ የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ውስጥ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው። በዕለቱ ከዳኝነት ውጪ በተፈፀመ ግድያ (extra-judicial killing) አስክሬኖች መቃጠላቸውንና እና አንድ በህይወት የነበረ ሰው በእሳት ተቃጥሎ መገደሉን ኮሚሽኑ አመልክቷል ።
ለዚህ አሰቃቂ ግድያ መነሻው አንድ ቀን ቀድሞ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ በዚያ ዕለት «በመከላከያ ሠራዊት ታጅበው ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ፤ ወደ ማንኩሽና ወደ አሶሳ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ ጥቃት» ፈፅመው 3 ሲቪሎችን እና 20 የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ገድለዋል ብሏል። እንዲሁም 14 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።
ኢሰመኮ በመግለጫው ይፋ እንዳደረገውም የተቃጠሉት ሰዎች አስክሬን በፀጥታ ኃይሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ እና የተገደሉ 10 ሰዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ድርጊቱን «ፈጽሞ ከሕግ አስከባሪ አባሎች የማይጠበቅ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት» ነው በማለት ጥቃት ፈፃሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና የሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲያገኙ ጠይቋል። ...
...ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የመንግሥት ሕግ አስከባሪ አባሎች እራሳቸው በግልጽ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጻሚዎች ሆነው መታየታቸው፤ ሰዎች በሕጋዊ ሥርዓት ላይ የሚኖራቸውን እምነት የሚሸረሽርና ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚያጋልጥ በመሆኑ፤ መንግሥት የምርመራውን ሂደትና ውጤት በተመለከተ የተሟላ መረጃ ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግና ፍትሕን ለማረጋገጥም የሟች ቤተሰቦችን ሊክስ ይገባል” ብለዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከትናንት በስትያ ዕለት ባወጣው መግለጫ መንግሥት « ፍፁም ከሰብአዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል» ብሏል። ነገር ግን መንግስት የጭካኔ ተግባሩን የፈጸሙ አካላት እና ተባባሪዎቻቸውን በይፋ አላስታወቀም ።
ሩስያ በዩክሬን ለምታካሂደው ጦርነት የቻይናን የኤኮኖሚ ድጋፍ መጠየቋን የአሜሪካ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሩስያ የቻይናን ድጋፍ መጠየቋ የተሰማው ዩናይትድ ስቴትስ ፤ ቻይና ሩስያን ከተጣለባት ማዕቀብ ለማስመለጥ ጥረት ብታደርግ ከባድ «መዘዝ» እንደሚጠብቃት ከገለጸች በኋላ ነው። ነገር ግን ቻይና ለዘገባው በቀጥታ መልስ ከመስጠት ይልቅ ዩናይትድ ስቴትስ ፤ ቻይና በዩክሬን ጦርነት ውስጥ የነበራትን ሚና በተመለከተ “ሐሰተኛ መረጃዎች ” እያሰራጨች ነው ስትል ወቅሳለች። የአሜሪካ ባለስልጣናት ፤ ሩሲያ የወታደራዊ ትጥቅ እና ሌሎች ድጋፎችን ከዋና አጋሯ ጠይቃለች ሲሉ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ነገር ግን ሩስያ ስለጠየቀችው የድጋፍ አይነት ለይተው ለመጥቀስ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ እና ቻይናም በዚሁ ጉዳይ መልስ አለመስጠቷን ነው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለከተው። በዋሽንግተን የቻይና ኤምባሲ ቃል አቃባይ በዚሁ ጉዳይ ከበርካታ የመገናኛ ብዙኃን ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ « ስለዚያ ጉዳይ በጭራሽ ሰምቼው አላውቅም » በማለት መልሰዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን በቀጥታ ከማውገዝ የተቆጠበችው ቻይና የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ወደ ምስራቅ አውሮጳ የሚያደርገው መስፋፋት በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለውን ውጥረት ለማባባሱ ምንያት መሆኑን ትገልጻለች። የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ዲፕሎማት ያንግ ጂቺ በጣልያን መዲና ሮም በሚገን አንድ ሆቴል በዝግ ተገናኝተው የነበረ ቢሆንም ስላደረጉት ንግግር ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሳይሰጡ ቀርተዋል። ...
... ነገር ግን የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኤሚሊ ሆርን ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ባለስልጣናቱ «በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ውድድር ለመቆጣጠር እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገው ጦርነት በቀጣናው እና በአለም አቀፍ ደህንነት ላይ ስላለው ተጽእኖ » መወያየታቸውን ገልጸዋል። ቤይጂንግ ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀችው በሞስኮ ላይ እየደረሰ ያለው ዓለማቀፍ ውግዘት እየበረታ ቢመጣም የእርሷ ወዳጅነት ግን «ጠንካራ» እንደሆነ ገልጻለች። ጦርነቱ እንዲቆምም ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን በማከል።
በሰሜናዊ ቡርኪና ፋሶ ታጣቂ ሚሊሻዎች ባደረሱት ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገደሉ ። የዛሬውን ጥቃት ጨምሮ ታጣቂዎቹ ባለፉት ሶስት ቀናት ባደረሷቸው ጥቃቶች የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ ደርሷል። የዛሬው ጥቃት ሶውም ግዛት ውስጥ በምትገኘው አርቢንዳ ከተማ ውሃ በመቅዳት ላይ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መፈጸሙን የከተማዋ ከንቲባ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ጥቃቱን ቡርኪና ፋሶን ጨምሮ በማሊ እና ኒጀር አጎራባች ቆላማ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀሰው እና ከአይ ኤስ እና አልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ሳይኖረው እንደማይቀር የሚነገርለት ታጣቂ ቡድን ሳይፈጽመው እንዳልቀረ ተነግሯል። ታጣቂዎቹ አዲስ ይዘውት በመጡት ስልታዊ እንቅስቃሴያቸው በደረቃማ አካባቢዎች በሚገኙት የውሃ ማጠራቀሚያ እና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ማነጣጠራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ትናንት እሁድ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት 13 የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ 15 ሰዎች ሲገደሉ ፤ ባለፈው ቅዳሜም እንዲሁ በአንድ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በደረሰ ጥቃት ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አመልክቷል። በደቡባዊ የሰሃራ በረሃ በሚገኙ የሳህል ቀጣና ሀገራት በተደጋጋሚ በታጣቂ የሚሊሻ ቡድኖች በሚፈጸሙ ጥቃቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በሃገራቱ ጥቃቶቹን ለመግታት ብሎም መንግስታቱን ለማገዝ በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሃገራት ወታደሮች ቢሰፍሩም ያን ያህል ውጤት ሊያመጡ አለመቻሉ ተመልክቷል። በቡርኪና ፋሶ የመንግስት የቁጥጥር አቅም መዳከሙን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ሮክ ማርክ ክርስቲያን ካቦሬን ከስልጣናቸው አሰናብቷል። የፕሬዚዳንቱን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ በጎርጎርሳውያኑ 20202 ወታደራዊ ዩንታ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥሯል።
የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአንድ,ና እና ሁለተኛ ዙሮች ለተፈተኑ ለተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የተለያየ የማለፊያ ነጥቦችን ዛሬ ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት በመጀመርያው ዙር የተፈተኑ እና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለሚያመለክቱ የተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 እና ለሴት 351 ሆኗል። በተመሳሳይ የትምህርት መስክ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል። መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ደግሞ የማለፊያ ነጥብ 300 ሲሆን በድጋሚ ለተፈተኑት ደግሞ የማለፊያ ነጥቡ 380 ሆኗል።
በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ፤ ሲሆን በተመሳሳይ የትምህርት መስክ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥቡ ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ሆኗል። እንዲሁም መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች የማለፊያ ነጥብ 250 ሆኖ በድጋሜ ለተፈተኑ ሁለቱም ፆታዎች የማለፊያ ነጥቡ 280 ሆኖ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ ደግሞ የመግቢያ ነጥቡ ዝቅ ብሎ ቀርቧል። በዚህ መሰረት ለተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ነጥብ 300 ሲሆን ለማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ደግሞ 250 ሆኗል። ...
...በሁለተኛው ዙር ለተፈተኑት እና በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር ለሚያመለክቱ መደበኛ ተማሪዎች ለወንድ 423 ለሴት 409 ፤ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 እንዲሁም መስማት ለተሳናቸው ደግሞ 350 መሆኑ ተገልጿል። በዚሁ ጊዜ በድጋሚ ለተፈተኑ ደግሞ ነጥቡ 443 ሆኗል። በሁለተኛው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተፈተኑ ተማሪዎች ለወንድ 317፣ ለሴት 305 ሲሆን ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚገኙ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል። በግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው መማር ለሚፈልጉት ለሁለቱም ጾታዎች 300 ሆኖ መመዝገቡን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። 2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለአገር አቀፍ ፈተና ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች መካከል 599,003 (96.9%) ፈተናውን መውሰዳቸውን አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ መናገራቸውን የትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት ብሔርን መሠረት አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ገለጹ። ግጭቱን በቅርበት የተመለከቱ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ያስቆጠረ ቢሆንም ትናንት ሌሊት ግን ወደ አካላዊ ግጭት ተሸጋግሯል። በተማሪዎቹ መካከል ወደ ብሄር ግጭት ያሸጋገረውን አጋጣሚ በተመለከተ አስተያየቱን ለዶይቼ ቬለ የሰጠው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ተማሪ« ጥላቻን የሚሰብክ ወረቀት በጊቢው መበተኑን » ይገልጻል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር ዉባቸው ማሞ በበኩላቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ቅጥር ጊቢው በመግባት ተማሪዎችን ለፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት ተጠቅመዋል በማለት ይከሳሉ። ኢንጅነር ውባቸው አሁን ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ያሏቸው ተማሪዎች እና ሌሎች አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አስታውቀው ነበር ።
ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ታጣቂ ሚሊሻዎች ባደረሱት ጥቃት ዛሬ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ተገደሉ ። የዛሬውን ጥቃት ጨምሮ ባለፉት ሶስት ቀናት ከ30 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።የዛሬው ጥቃት የተፈፀመው በሰሜናዊ ቡርኪና ፋሶ በአርቢንዳ ከተማ ውሃ በመቅዳት ላይ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ጥቃቱን ቡርኪና ፋሶን ጨምሮ በማሊ እና ኒጀር አጎራባች ቆላማ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀሰው እና ከአይ ኤስ እና አልቃኢዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው ታጣቂ ቡድን ሳይፈጽመው እንዳልቀረ ተነግሯል። ታጣቂዎቹ አዲስ ይዘውት በመጡት ስልታዊ እንቅስቃሴያቸው በደረቃማ አካባቢዎች በሚገኙ የውሃ ማጠራቀሚያ እና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ማነጣጠራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ትናንት እሁድ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት 13 የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ 15 ሰዎች ሲገደሉ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ በአንድ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በደረሰ ጥቃት ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አመልክቷል።
ከአንድ አመት በፊት ማሊ ውስጥ በጂሃዲስት ቡድን ታግቶ የነበረውን ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ የሚያሳይ አዲስ ቪዲዮ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እየተሰራጨ መሆኑን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገበ። ጋዜጠኛ ኦሊቨር ዱቦይን ከአንድ ደቂቃ በላይ የሚያሳየው ቪዲዮ ጋዜጠኛው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ያመላክታል። እሱም ለወላጆቹ እና ቤተሰቡ መልእክት ያስተላልፋል ተብሏል። ትናንት እሁድ ይፋ የሆነው ቪዲዮ የተቀረፀበት ቀን እና ቦታ ግን አልታወቀም።
የ47 አመቱ ጋዜጠኛ የፈረንሳይ መንግሥት እሱን ከእገታ ለማስለቀቅ “የሚቻለውን ማድረጉን እንዲቀጥልም” ያሳስባል። ዱቦይ እጎአ ከ 2015 አንስቶ ማሊ ውስጥ የሚሰራ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ነው። ጋዜጠኛው በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በተለጠፈ ቪዲዮ መታገቱን ያሳወቀው እጎአ ባለፈው ዓመት ግንቦት 5 ቀን ነበር። አጋቾቹም በማሊ ሰሜናዊ ክፍል ጋዎ ከተማ በምህፃሩ GSIM የተባለ እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ባለው ቡድን እንደሆነ ገልጿል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ባለፈው ጥር ወር ጋዜጠኛ ዱቦይን እንዳልረሱት ተናግረው ነበር።
ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ጊዜ አንስቶ ከ 2,400 በላይ ሰላማዊ ሰዎች በደቡብ ዩክሬን ማሪፖል ከተማ መገደላቸውን የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲዎች ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ገለፁ። ቦሬል ይህን ያሉት ዛሬ በሰሜን ሜክዶንያ መዲና ስኮፕዬ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። ዛሬ በሰሜን መቄዶንያን ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት ቦሬል ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ስቴቮ ፔንዳሮቭስኪና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚታር ኮቫቼቭስኪ ጋር ተነጋግረዋል። በስኮፕዮው ጋዜጣዊ መግለጫ ከ 2.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከዩክሬን እስካሁን መሰደዳቸውን የገለፁት ቦሬል
የስደተኞች ቁጥር ወደ 4-5 ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችልም አስታውቀዋል። ጀርመን እስካሁን 147 000 ገደማ የዩክሬን ስደተኞችን መመዝገቧን ዛሬ አስታውቃለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከባድ ጦርነት በማካሄድ ላይ ያሉት የዩክሬን እና ሩስያ ተወካዮች ዛሬ አራተኛውን ዙር ድርድር ጀምረዋል። የዩክሬን ተወካይ የፕሬዝዳንት አማካሪ ማይቻሎ ፖዶሊያክ ድርድሩ "ጠንካራ" ነው ሲሉ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸው ሁለቱ ወገኖች "የተለያየ አቋማቸውን" ለማቅረብ በሂደት ላይ ናቸው» ብለዋል። ድርድሩም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተቋርጦ ለነገ ተገፍቷል።ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ሶስት ድርድሮች ያለ አርኪ ውጤት መጠናቀቃቸው ይታወሳል።
በርካታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች በዩክሬን በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም ጠየቁ። በህሙማንና በጤና ተቋማት ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት “የጭካኔ ድርጊት ነው” ብለዋል የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNCEF)፣ የተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ፈንድ እና የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ሃላፊዎች። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረችበት ጊዜ አንስቶ ከ30 በላይ ጥቃቶች በጤና ተቋማት ላይ መመዝገባቸውን ድርጅቶቹ አስታውቀዋል። ከተዘገቡት ጥቃቶች ውስጥ 24 ቱ በጤና ተቋማት ላይ የነበረ ሲሆን አምስቱ ደግሞ በአምቡላንሶች ላይ እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል። በእነዚህ ጥቃቶች በአጠቃላይ 12 ሰዎች ሲገደሉ 34 ሰዎች መቁጠላቸውንም ድርጅቶቹ ጠቅሰው ባስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል። እንደ ዩክሬይን የጤና ሚኒስቴር ገለፃ ከሆነ ደግሞ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ ከ 100 በሚበልጡ የጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በዚህም ጥቃት ስድስት የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉ 12 ቆስለዋል። ከዚህም ሌላ ሩሲያ ዩክሬይንን ከወረረች ጊዜ አንስቶ 90 ልጆች መገደላቸውን እና ከመቶ በላይ ህጻናት መቁሰላቸውን የዩክሬን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ አስታውቋል። ቁጥሩ በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም።
ኬር የተሰኘው የእርዳታ ድርጅት ለሶሪያ ተጨማሪ ሰብአዊ ርዳታ እንዲደረግ ጠየቀ። ድርጅቱ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ ድጋፉን እንዲያሳድግ የተማፀነው ነገ አስራ አንደኛ ዓመት የሚሞላውን ጦርነቱ የተጀመረበትን ዕለት በማስታወስ ነው። ኬር እንዳለው 70 በመቶው የሶሪያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በቂ ምግብ አያገኝም። “ትምህርት እና የህክምና አገልግሎት ለማግኘት መሻት ‘ቅንጦት’ ሆነዋል ሲሉ የኬር ባልደረባ ፍራንዚስካ ዮርንስ ያስረዳሉ። ከሁለት ልጆች አንዱ ብቻ ትምህርት ቤት እንደሚሄድ የገለፁት ዮርንስ ብዙ ልጃገረዶች እድሚያቸው 18 ሳይሞላ እንደሚዳሩ ተናግረዋል። የኬር ጀርመን ዋና ጸሃፊ ካርል-ኦቶ ሴንትል "በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ የሚከሰቱ ብዙ ነገሮች ቢኖርም የሶሪያውያን ስቃይ አሁንም እንዳላበቃ አስታውሰው «የሶሪያ ቀውስ አሁንም ትልቅና አስቸኳይ የሰብአዊ ርዳታ ያሻል» ብለዋል።
የዓለም ዜና ፤ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ማክሰኞ
ማርያ ኦስያንስኮቫ የተባለች ሩስያዊት ጋዜጠኛ በሞስኮ በሚገኝ በአንድ የሩሲያ መንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ ስርጭት ዜና ሰዓት ላይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችዉን ወረራ በመቃወም በቀጥታ ስርጭት ላይ በድንገት ከቀረበች በኋላ ስርጭቱ ተቋረጠ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሩስያዉያን መልዕክቷ አግኝተዋል። ጋዜጠኛ ማርያ ኦስያንስኮቫ ጋዜጠኛ አባትዋ ዩክሬናዊ እናትዋ ደግሞ ሩስያዊት ናቸዉ። ጋዜጠኛዋ «ፑቲን በወንድም ህዝብ ላይ የጀመሩትን ጦርነት ያቁሙ ፤ ሩስያዉያን የሚሰራጨዉን ፕሮፖጋንዳ አትመኑ፤ እየዋሽዋችሁ ነዉ። በዩክሬን ላይ የሚካሄደዉ ጦርነት ይቁም፤ » ስትል ነዉ በድምፅም በፅሑፍም በቀጥታ ስርጭት ተቃዉሞዋን ያሰማችዉ ። ጋዜጠኛዋ እስከ 15 ዓመታት እስር ይጠብቃታል።
በኦሮሚያ ክልል ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የኢትዮ-ሴመንት ፋብሪ ሰራተኞች ከሲሚኒቶ ማውጫ ስፍራ ከታገቱ ሦስት ሳምንታት ቢሆናቸዉም እስካሁን የአጋቾቹ ማንነት እንዳልታወቀ ተነገረ። የታገቱትንም ሰዎች እስካሆኑን ማስለቀቅ እንዳልተቻለ ነዉ የተመለከተዉ። አጋቾች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር እየጠየቁ ነዉም ተብሎአል።
የሦስት የአውሮጳ ሀገራት መሪዎች ለዩክሬን ድጋፋቸዉን ለመስጠት በባቡር ወደ ዩክሬን እየተጓዙ እንደሆነ ተገለፀ። የፖላንድ፣ የቼክ ሪፐብሊክ እና የስሎቬንያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የአውሮጳ ህብረት አጋርነትን ለማሳየት ዛሬ ማክሰኞ መዲና ኪየቭ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ።
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬይን የጀመሩትን ጦርነት ለማስቆም፤ ትክክለኛ ውይይት እንዲጀምሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጥሪ አቀረቡ። ጉተረስ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደዉ ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ "የረሃብ መስፋፋት" እና የምግብ ዋስትና እጦት ሊያስከትል እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።
ሙሉ ዜናዉን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! https://p.dw.com/p/48WYQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot