ኢትዮጵያ ውስጥ የሸቀጦች ዋጋ ዕለት በዕለት እየጨመረ መሄዱ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። የኑሮ ውድነቱን የብዙዎችን ኑሮ እየተፈታተነ መሆኑም ይነገራል። የጤፍ ዋጋ ኩንታሉ ወደ አምስት ሺህ ብር እየተጠጋ ነው። የምግብ ዘይት ጉዳይም ሌላው የሸማች ራስ ምታት ከሆነ ውሎ አድሯል። በሀገር ውስጥ የሚታየውን የኑሮ ውድነትን መንስኤ ያመላከተው የኤኮኖሚ ባለሙያው አቶ ሁሴን አሊ ለውይይት መነሻ ያቀረቡት ጽሑፍ ከልክ ያለፈ ገንዘብ በኤኮኖሚው ውስጥ መሰራጨቱን፣ የምጣኔ ሀብቱ ከአምራች ዘርፉ ይልቅ በአገልግሎት ዘርፍ ላይ መንጠልጠሉን፣ እንዲሁም የምርትና ምርታማነት አለመጨመርና በወጪና ገቢ ንግድ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን በዋና ምክንያትነት መጥቀሱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በየምትኖሩበት አካባቢ የሸቀጦች ዋጋ መናርና የኑሮ ውድነቱ እንዴት ነው? በመፍትሄነት የሚከናወኑ ተግባራትስ አሉ?
ሶማሊያ ውስጥ በሰላም አስከባሪዎች ላይ በተነጣጠረ ጥቃት ቢያንስ አራት ሲቪሎች ሲገደሉ ዘጠኝ መጎዳታቸው ተሰማ። እማኞች ለሮይተር የዜና ምንጭ እንደገለጹት የተተኮሰው አዳፍኔ በመቃዲሹ አውሮፕላን ማረፊያ የሰፈሩ የአፍሪቃ ሕብረትና የተመድ (አሚሶም) የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃልሎችን ለመምታት ያለመ ነው። ከእማኞች አንዱ የ65 ዓመቱ መሐመድ ሼኽ መሐመድ እንዳሉት የተተኮሰው አዳፍኔ ያረፈው በጎረቤታቸው መኖሪያ ነው። በጥቃቱ ከተገደሉት አባትና ልጅ ይገኙበታል። ሌሎች ሁለት ልጆች እና እናታቸው ተጎድተዋል። ፖሊስ ለጥቃቱ አሸባብን ተጠያቂ አድርጓል። ከአልቃይዳ ጋር ትስስር እንዳለው የሚነገረው የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን በዛሬው ዕለት ቀደም ብሎ መንገድ ዳር በተቀበረ ቦምብ ፍንዳታ አንድ ወታደራዊ ባለሥልጣንን ሲገድል ሁለት ጠባቂዎቻቸውን ማቁሰሉንም የጀርመን የዜና ወኪል ዲፒኤ ዘግቧል። ጋራዌ ኦንላይን እንደዘገበው በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በጥቃቱ የተገደሉት የሶማሊያ የፀጥታ ጉዳይ ባለሥልጣን አሊ ባሪሲ አሸባብ ሁለቱንም ጥቃቶች ማድረሱ አንዳሉስ በተባለው ራዲዮ ይፋ ማድረጉንም ዘገባው ጠቅሷል። የተጠቀሰው የራዲዮ ጣቢያ የአሸባብ ደጋፊ መሆኑንም ዜናው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተመ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ ተፈጽሟል የሚባለውን የመብት ጥሰትና እንግልት በጋራ ለመመርመር መስማማታቸውን አመለከቱ። ሁለቱ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ተመልካች ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ በጥምረት የሚያካሂዱት ምርመራ በሁሉም ወገኖች ተፈጥሟል ለሚባለው ጥቃት ይበልጥ የሚፈለገውን ተጠያቂነት ተጠያቂነት ይፋ ለማውጣት ያለመ መሆኑ በጋራ መግለጫው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ቀናት ትግራይ ውስጥ የተጀመረውን መንግሥት ሕግ ማስከበር ያለውን ውጊያ በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር ተገልጿል። ሁለቱም ተቋማት በዘገባዎች ስለሚወጡ በሲቪሎች ላይ ይፈጸማሉ ስለሚባሉ የመብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች ስጋት እንዳላቸውም ተመልክቷል። ከዚህ በመነሳትም በርካታ ተዋናዮች በተሳተፉበት ግጭት ተፈጽመዋል ስለተባሉት አሳሳቢ የመብት ጥሰቶች ተጨባጭ፣ ገለልተኛ ምርመራ ባስቸኳይ መካሄድ እንደሚኖርበት መግለጫው አስታውቋል። በጋራ ምርመራውን ለማካሄድ ከስምምነት ያደረሳቸውም ሁለቱም ተቋማት ሰብዓዊ መብቶች እንዲጠበቁና እንዲከበሩ፤ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ ተጠያቂነት እንዲኖር ባላቸው የጋራ እምነት እና አቋም መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል። ለምርመራው የሚደረገው እንቅስቃሴም በተቻለ በቅርቡ እንዲሆን በማመልከትም ለመነሻ ለሦስት ወራት እንደሚካሄድ መግለጫው አመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ ከቀትር በኋላ አስመራ ገቡ። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ባሰራጩት መልእክት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርዊ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና አብሯቸው ለተጓዘው የልዑካን ቡድን አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል። የኤርትራው ባለሥልጣን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአስመራ ጉብኝት በምን ላይ እንደሚያተኩር አልገለጹም።
ፎቶ፤ ከኤርትራ ማስተወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል ትዊተር ገጽ የተገኘ

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን የተባለው የግብረ ሰናይ ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ (ኤም.ኤስ.ኤፍ) የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በትግራይ ክልል 4 ሰዎችን ሲገድሉ ሰራተኞቹ መመልከታቸውን አስታወቀ። ቡድኑ ባለፈው ማክሰኞ ለበጎ አድራጎት ስራ ከመቀሌ ወደ አዲግራት በመጓዝ ላይ ሳለ ጥቃት እንደተሰነዘረበትም ገልጿል። ወታደሮች በግልጽ የሚታወቀውን የበጎ አድራጎት ተሽከርካሪ እና ከኋላ ይከተሉ የነበሩ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ካስቆሙ በኋላ ከህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሰዎችን አስወርደው ጥቃት መፈጸማቸውን የግብረሰናይ ድርጅቱ አስተባባሪ ካርሊን ክሌኸር ተናግረዋል። «ከተሽከርካሪ አስገድደው ያስወረዷቸውን ሰዎች ወንዶቹን ከሴቶች በመለየት በወንዶቹ ላይ ግድያ ፈጽመዋል» ብለዋል። የሀኪሞቹ ቡድንም ወደ መቀሌ እንዲመለስ መገደዱንም አስተባባሪዋ ጠቅሰዋል። ወታደሮቹ ፈጸሙት በተባለው ጥቃት ላይ ከወታደራዊ ባለስልጣናት ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን የፈረንሳይ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከትናንት በስትያ ማክሰኞ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን አምነዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርቱ የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ከ100 በላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን አስታውቋል።
የዩናይትድስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆይ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ ሴናተር ክሪስ ኩንስ በኢትዬጵያ ያደረጉኝት ጉብኝት ገንቢ ውጤት የተገኘበት መሆኑንን ለህግ መወሰኛው ምክር ቤት ገልጹ። ሴናተሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በትግራይ ክልል በደረሰው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት ማሳየቱ አሜሬሪካ የውሳኔ ሃሳብ ለውጥ እንድታደርግ በር ከፋች ነው ብለዋል። ቆይታቸውንም አዎንታዊ ውጤት የታየበት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በድንበር ይገባኛል የገባችውን ውዝግብ እና በህዳሴ ግድብ ላይ የተፈ,ጠረውን አለመግባባት በድርድር ለመፍታት ፍላጎት ማሳደሯን ሴናተሩ በንግግራቸው አበረታች ብለውታል። ነገር ግን በትግራይ ክልል የተሟላ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲኖር መስራት ግጭትና ጥላቻን ማስወገድ እንዲሁም ነፃና ፍትሐዊ ምርጫን ማመቻቸት በሀገሪቱ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮች መሆናቸውን አመልክተዋል፤ መጽሄት ዝርዝሩን ይዟል።
ለአፍሪካ የሚላኩ የኮቪድ 19 ክትባቶች መዘግየት በህዝቦች መካከል «የክትባት ጦርነት » እንዳያስነሳ ያሰጋኛል ሲል የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠርያ ማዕከል አስጠነቀቀ። ማዕከሉ ማስጠንቀቂያውን የሰነዘረው አስትራዜኔካ የተባለውን የክትባት አይነት የሚያመርተው የህንዱ ሴሩም የክትባት አምራች ኩባንያ ወደ ውጭ ይልክ በነበረው የክትባት መጠን ላይ ገደብ በማኖሩ ነው ተብሏል። ይህ ደግሞ አፍሪካ ተህዋሲውን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ ጆን ንኬንጋሶንግ አሳስበዋል። አፍሪካ ማግኘት የሚገባት የክትባት መጠን እየዘገየ በሄደ ቁጥር የታማሚዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በተገኘው ጥቂት ክትባት ላይ በህዝቦች መካከል ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አንድምታ እንዳይፈጥር ያሰጋልም ብለዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ እንዳስታወቀው ታንዛንያ፣ ቡሩንዲ፣ኤርትራ፣ካሜሩን፣እና ቻድን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ድረስ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት አልደረሳቸውም። ደሃ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት በክትባት ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው ኮቫክስ አማካንነት 28 የአፍሪካ ሀገራት ከ16 ሚሊዮን በላይ የአስትራዜኔካ ክትባት ተረክበዋል። በአፍሪካ 4 ሚሊዮን ሰዎች በተሕዋሲው ሲያዙባት 110 ሺ ሰዎች ደግሞ ከኮሮና በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጽንፈኛው የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ባደረሳቸው ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች 4 ሰዎች ሲገደሉ 6 ሰዎች ቆስለዋል ። በሞርታር በተፈጸመ ጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንዲት እናት ከጨቅላ ሕጻን ልጇ ጋር ይገኙበታል። ታጣቂ ቡድኑ ሞቃዲሾ ከተማ በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት መስሪያ ቤቶች ላይ በሰነዘረው በዚሁ ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ 5 ሰዎች መቁሰላቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። የሞርታር ጥቃት የተፈጸመበት መንደር ብርቱ ጥበቃ የሚደረግበት እና ዓለማቀፍ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ የሚኖሩበት እና የሰላም አስከባሪ ሀይሎች የጦር ሰፈር ሆኖ የሚያገለግለው ሀላኔ በተሰኘ የከተማው አካባቢ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በተያያዘ ዛሬ በደረሰ ሌላ የቦምብ ጥቃት አንድ የመንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ተገድለዋል። በዚሁ የመንገድ ዳር ጥቃት የባለስልጣኑ ጠባቂዎች የነበሩ ሁለት ሰዎች በጽኑ መጎዳታቸውን አሊ ሀሰን የተባሉ የፖሊስ መኮንን ለዜና ምንጩ ነግረዋል። አሸባብ ለሁለቱም ጥቃቶች ኃላፊነት እንደሚወስድ አንዳሉስ በተባለ የሬዲዮ ጣቢያ አስታውቋል። የታጣቂ ቡድኑ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባት የምትገኘው ሶማሊያ በቅርቡ lleታካሂድ አቅዳው የነበረው ሀገራዊ ምርቻ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ሌላ ተጨማሪ ውጥረት ውስጥ ከቷታል።
በኬንያ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 4 ሰዎች ተገደሉ ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃቱ ኬንያ ከሶማልያ በምትዋሰንበት ሰሜናዊ ምስራቅ ማንዱራ መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም ። ነገር ግን በኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርስ የነበረው እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ሳይፈጽም እንዳልቀረ አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። አሸባብ የኬንያ ወታደሮች ሶማልያ መግባታቸውን ተከትሎ ኬንያን እንደሚበቀል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልጽ ቆይቷል። አለማቀፍ ዕውቅና የተሰጠውን የሶማልያ መንግስት አሸባብን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ወደ ሶማልያ beተሰማራው ከ20,000 በላይ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ኬንያ ተሳታፊ ናት። እጎአ ከ2011 ጀምሮ አሸባብ ከሶማልያ በሚዋሰኑ ግዛቶች ዋጂር ፣ ማንዴራ፣ ጋሪሳ ፣ በታና ወንዝ እና በላሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች አድርሷል። ቡድኑ የማንዱራ ግዛት 50 ከመቶ የሚሆነውን አውራጎዳና እና ከ60 በመቶ በላይ የግዛቲቱን የቆዳ ስፋት መቆጣጠሩን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አሊ ሮባ ተናግረዋል። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ ትምህርት ቤቶች አደጋ ላይ መውደቃቸው ተነግሯል።
ኬንያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን የምታስተናግድባቸውን ሁለት ግዙፍ የመጠለያ ጣቢያዎች ልትዘጋ ነው። ኬንያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጣቢያዎቹ ሲዘጉ ስደተኞቹን ወዴት እንደሚያዘዋውር እንዲያሳውቃት የ14 ቀናት ጊዜ ሰጥታለች ። ውሳኔው ጦርነት ሸሽተው በዚያ ለተጠለሉ አብዛኞቹ ሶማሊያውያን ለሆኑ ስደተኞች አሳሳቢ መሆኑን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። በዚህ ረገድ ኬንያ በጉዳዩ ላይ በተጨማሪ የመደራደር ፍላጎት እንደሌላት የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፍሬድ ማቲያንጊ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። በሶማሊያ እና በኬንያ ድንበር አካባቢ የሚገኘው ግዙፉ የዳዳብ የመጠለያ ጣቢያ የደህንነት ስጋት እንዳሳደረባት ኬንያ ገልጻለች። ምንም እንኳ በባለስልጣናቱ ማረጋገጫ ባይሰጥበትም የዳዳብ የመጠለያ ጣቢያው ለጽንፈኛው የአሸባብ የታጣቂ የምልመላ

ቦታ ሆኖ እንደሚያገለግል እና በኬንያ ውስጥ የሚደርሱ ጥቃቶች መነሻ ቦታ እንደሆነ ይታመናል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኬንያ የመጠለያ ጣቢያዎቹን ለመዝጋት የያዘችው ዕቅድ እንደደ,ረሰ,ው ትናንት ረቡዕ አስታውቋል። የዳዳብ የመጠለያ አብዛኞቹ ሶማልያውያን የሆኑ ከ200,000 በላይ ስደተኞች ሲኖሩበት የካኩባ የመጠለያ ጣቢያ ደግሞ የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሸሽተው የተጠለሉ በተመሳሳይ ከ200,000 የሚልቁ ስደተኞች ይኖሩበታል።
ለአፍሪካ የሚላኩ የኮቪድ 19 ክትባቶች መዘግየት በህዝቦች መካከል «የክትባት ጦርነት » እንዳያስነሳ ያሰጋኛል ሲል የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠርያ ማዕከል አስጠነቀቀ። ማዕከሉ ማስጠንቀቂያውን የሰነዘረው አስትራዜኔካ የተባለውን የክትባት አይነት የሚያመርተው የህንዱ ሴሩም የክትባት አምራች ኩባንያ ወደ ውጭ ይልክ በነበረው የክትባት መጠን ላይ ገደብ በማኖሩ ነው ተብሏል። ይህ ደግሞ አፍሪካ ተህዋሲውን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ ጆን ንኬንጋሶንግ አሳስበዋል። አፍሪካ ማግኘት የሚገባት የክትባት መጠን እየዘገየ በሄደ ቁጥር የታማሚዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በተገኘው ጥቂት ክትባት ላይ በህዝቦች መካከል ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አንድምታ እንዳይፈጥር ያሰጋልም ብለዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ እንዳስታወቀው ታንዛንያ፣ ቡሩንዲ፣ኤርትራ፣ካሜሩን፣እና ቻድን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ድረስ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት አልደረሳቸውም። ደሃ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት በክትባት ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው ኮቫክስ አማካንነት 28 የአፍሪካ ሀገራት ከ16 ሚሊዮን በላይ የአስትራዜኔካ ክትባት ተረክበዋል። በአፍሪካ 4 ሚሊዮን ሰዎች በተሕዋሲው ሲያዙባት 110 ሺ ሰዎች ደግሞ ከኮሮና በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ለአፍሪካ የሚላኩ የኮቪድ 19 ክትባቶች መዘግየት በህዝቦች መካከል «የክትባት ጦርነት » እንዳያስነሳ ያሰጋኛል ሲል የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠርያ ማዕከል አስጠነቀቀ። ማዕከሉ ማስጠንቀቂያውን የሰነዘረው አስትራዜኔካ የተባለውን የክትባት አይነት የሚያመርተው የህንዱ ሴሩም የክትባት አምራች ኩባንያ ወደ ውጭ ይልክ በነበረው የክትባት መጠን ላይ ገደብ በማኖሩ ነው ተብሏል። ይህ ደግሞ አፍሪካ ተህዋሲውን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ ጆን ንኬንጋሶንግ አሳስበዋል። አፍሪካ ማግኘት የሚገባት የክትባት መጠን እየዘገየ በሄደ ቁጥር የታማሚዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በተገኘው ጥቂት ክትባት ላይ በህዝቦች መካከል ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አንድምታ እንዳይፈጥር ያሰጋልም ብለዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ እንዳስታወቀው ታንዛንያ፣ ቡሩንዲ፣ኤርትራ፣ካሜሩን፣እና ቻድን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ድረስ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት አልደረሳቸውም። ደሃ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት በክትባት ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው ኮቫክስ አማካንነት 28 የአፍሪካ ሀገራት ከ16 ሚሊዮን በላይ የአስትራዜኔካ ክትባት ተረክበዋል። በአፍሪካ 4 ሚሊዮን ሰዎች በተሕዋሲው ሲያዙባት 110 ሺ ሰዎች ደግሞ ከኮሮና በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
አርዕስተ ዜና
ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት መስማማቷ ተገለጠ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኤርትራ ጦሯን ለማስወጣት የተስማማችው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አስመራ ውስጥ ባደረጉት ውይይት መኾኑንን ይፋ አድርገዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሰሜን ትግራይ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ሁለት የኤርትራ ስደተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን በቦታው ተገኝቶ ማረጋገጡን ዐስታወቀ። ሁለቱ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ 20 ሺህ ግድም ከኤርትራ እንደመጡ የሚነገርላቸው ስደተኞች ተጠልለው ይገኙ ነበር ተብሏል።
ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባውን ጀምሯል። ከ10 ሚሊዮን በላይ መራጮች ይመዘገብባቸዋል ተብለው በሚጠበቁት የደቡብና የሲዳማ የምርጫ ክልሎች ዛሬ በከፊል ተከፍተው መራጮችን ሲመዘግቡ ውለዋል።
ከግብፅ መዲና ካይሮ በስተደቡብ ሁለት የመጓጓዥ ባቡሮች ተላትመው ዛሬ በደረሰው አደጋ ቢያንስ 32 ሰዎች ሞቱ። 108 ቆስለዋል። የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ አደጋው እንዲደርስ ያደረጉ ጥፋተኞች ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዝተዋል።
ዜናው በዝርዝር
*ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት መስማማቷን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አስመራ ኤርትራ ትናንት ከሰአት በኋላ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዐስታወቁ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ ይኽንኑ ዛሬ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ይፋ አድርገዋል። ኤርትራ ጦሯን ለማስወጣት የተስማማችው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አስመራ ውስጥ ባደረጉት ውይይት መኾኑንን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት የኤርትራን ጦር በመተካት የድንበር አካባቢዎችን እንደሚጠብቅም ዐስታውቀዋል። በመልዕክታቸው በሰሜን እዝ ላይ ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ በሕወሓት ውስጥ የተሰበሰበው «ወንጀለኛ» ያሉት ቡድን በባህርዳርና በጎንደር ከተሞች ሮኬቶችን መተኮሱን አስታውሰዋል። ቡድኑ በኤርትራ ላይ ተደጋጋሚ ሮኬቶችን መተኮሱንም ገልጸው «ይህም የኤርትራ መንግሥት ድንበር አቋርጦ በመግባት ራሱን ከተጨማሪ ጥቃቶች እንዲከላከልና ብሔራዊ ደህንነቱን እንዲጠብቅ አነሣሥቶታል» ብለዋል። በዚሁ መልዕክታቸው «በትግራይ ክልል እና በኤርትራ መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መመለስ በእጅጉ እንደሚያስፈልግም» ገልጸዋል። ኤርትራ እና ኢትዮጵያ በመተማመን እና በመልካም ጉርብትና መንፈስ ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት የጀመሩትን ግንኙነት እንደሚቀጥሉበትም ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ገልጠዋል።
*የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሰሜን ትግራይ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ሁለት የኤርትራ ስደተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን በቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። የድርጅቱ የስደተኞች ጉዳይ ቃል አቀባይ ቦሪስ ቼሺርኮቭ ከጄኔቫ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፦ የሺምቤላ እና ህጻጽ የስደተኞች ጣቢያዎችን የተመለከተው የተመድ ቡድን «ሁለቱም ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን» መመልከቱን ገልጠዋል። በሥፍራው የነበሩ የሰብአዊ ርዳታ ቁሳቁሶች መዘረፋቸው እና መመዝበራቸውንም አክለው ጠቅሰዋል።
«ከተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ልዑክ ጋር ቦታውን በተመለከትንበት ወቅት ሁለቱም የስደተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ ወድመው አግንተናቸዋል። የሰብአዊ መርጃ ቊሳቊሶች በመላ ተዘርፈዋል፣ ተመዝብረዋል።»
ትግራይ ውስጥ ጦርነቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሁለቱ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ 20 ሺህ ግድም ከኤርትራ እንደመጡ የሚነገርላቸው ስደተኞች ተጠልለው ይገኙ እንደነበረም ተገልጧል። ሁለቱን ጣቢያዎች የመዘበረ እና ያወደማቸው የትኛው ኃይል እንደሆነ ግን ተመድ አልገለጠም። በጣቢያዎቹ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች ጣቢያውን ጥለው መኼዳቸው እና በአሁኑ ወቅት ያሉበት ኹኔታም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መርጃን (UNHCR)«እጅግ እንደሚያሳስበው» ቦሪስ ቼሺርኮቭ ተናግረዋል።
*ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባውን ጀምሯል። ከ10 ሚሊዮን በላይ መራጮች ይመዘገብባቸዋል ተብለው በሚጠበቁት የደቡብና የሲዳማ የምርጫ ክልሎች ዛሬ በከፊል ተከፍተው መራጮችን ሲመዘግቡ ውለዋል። በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብና የሲዳማ ክልሎች ምርጫ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ፍሬው በቀለ በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በሁለቱ ክልሎች ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ የምርጫ ጣቢያዎች መከፈታቸን ገልጸዋል። በእነኝሁ የምርጫ ጣቢያዎች ከሃያ አራት ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰልጥነው እንዲደለደሉ መደረጉንም አስተባባሪው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመራጮች ምዝገባው የሀዋሳ ከተማና የጉራጌ ዞንን ጨምሮ በተወሰኑ የክልል ከተሞችና ዞኖች ብቻ ነው በከፊል የተጀመረው። በተቀሩት አካባቢዎች ግን በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከትናንት ጀምሮ መከናወን የነበረበት የመራጮች ምዝገባ እስከአሁን አለመጀመሩን በስፍራው የሚገኘው የዶቼ ቬለ (DW) ዘጋቢ አረጋግጧል። በቦርዱ የደቡብና የሲዳማ ክልሎች ምርጫ አስተባባሪ አቶ ፍሬው በቀለ ቀጣዩን ብለዋል።
«ቁሳቁሶችን ከማሰራጨት አንጻር በተወሰነ ደረጃ መንጠባጠብ ይታያል። እሱም ቢሆን በአንድ እና ግማሽ ቀን የሚኢልቅ ይመስለኛል። አሁን መንገድ ላይ ያሉ አሉ፤ ቀድመው የመጡ አሉ። እነኚህ በተወሰነ ደረጃ ክፍተት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ለምሳሌ እንደ ደቡንብ ክልል ጉራጌ ዞን ቀድሞ ገብቷል። እየተሠራጨ ነው። ሲዳማ እና የመሳሰሉት ደግሞ መንገድ ላይ ናቸው። እነኚህ እየተሠራጩ ነው። በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዛሬ እና ነገ ተጠናቀው ይገባሉ ብለን እንጠብቃለን።»
*በእነ አቶ ስብሓት ነጋ መዝገብ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመናድ በመነሳት እና የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ የተከሰሱ 42 ተጠርጣሪዎች በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት እንዲዳኙ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። የተከሳሾች ጠበቃ ታደለ ገብረ መድኅን የተከሳሾችን ጉዳይ የመመልከት ሥልጣን ያለው ተከሳሾች ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባለበት ቦታ የሚገኝ ፍርድ ቤት ቢሆንም ዳኛው ጥያቄውን አለመቀበላቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የተከሳሾች ጠበቃ እንዳሉት፦ ዐቃቤ ሕግ ክሱን ማቅረብ ያለበት ድርጊቱ እንደተፈጸመ በተነገረበት ቦታ እና ተያዙ በተባለበት ትግራይ ክልል ነው ሲሉም አክለዋል።
«የሰሜን እዝ ጥቃት በመፈጸም ነው። ሕገ መንግሥቱን በኃይል የመናድ የሚል ነው ያቀረቡት። ስለዚህ ሕገ መንግሥቱን በኃይል የመናድ እና ተያዙበት የተባለው ቦታ ትግራይ ክልል መኾን ነው የሚያስችለው። ስለዚህ ይኼ ከሆነ የዳኛውን ሥልጣን በተመለከተ ይኼን ሊያይ አይገባም የሚል ነው። ዳኛው ማየት አለብን የሚል ነው ያስተላለፉት ውሳኔ።»
ተካሳሾቹ ዳኛ እንዲቀየር ያቀረቡት ጥያቄን በተመለከተ ውሳኔው አግባብነት አለው የለውም የሚለውን ሬጂስትራር ጽ/ቤት ትእዛዝ እስኪሰጥ መዝገቡ ለጊዜው ያለቀጠሮ መዘጋቱንም የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ይጠቊማል።
*ከግብፅ መዲና ካይሮ በስተደቡብ ሁለት የመጓጓዥ ባቡሮች ተላትመው ዛሬ በደረሰው አደጋ ቢያንስ 32 ሰዎች ሞቱ። የባቡሩ አደጋ የደረሰው ሶሀግ በምትሰኘው ደቡባዊ አውራጃ ውስጥ ነው። የአደጋው ምክንያት የተወሰኑ የባቡር ፉርጎዎች ሐዲዳቸውን በመሳታቸው እንደሆነ የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የግብፅ የጤና ሚንስትር ይፋ እንዳደረገው በባቡሮቹ ልትሚያ 32 ሰዎች ሕይወታቸውን ከማ

ጣታቸው በተጨማሪ 108 ሰዎች የመቊሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ጉዳታቸውም ከመበለዝ አንስቶ፣ ስብራት እና ቁስለት መሆኑም ተጠቅሷል። የግብጽ መንግሥት የባቡር ባለሥልጣን አደጋው የተከሰተው ከሁለቱ አንደኛው ባቡር ፊርጎዎች ውስጥ የነበሩ ሰዎች የአደጋ ጊዜ መሣሪያዎችን በመጠቀም ባቡሩን በማስቆማቸውን ነው ብሏል። ከዚያም ከኋላ ሲምዘገዘግ የመጣው ባቡር ከቆመው ባቡር ጋር ተላትሞ አደጋ መከሰቱ ተገልጧል። የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተው ጥፋተኞች፦ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዝተዋል።
*ጀርመን ውስጥ የኮሮና ተሐዋሲ ሥርጭት ከፍተኛ የሚባለው ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጠ። ምናልባትም በሥርጭቱ ሦስተኛ ዙር ከሚቀጥለው ወር አንስቶ በቀን 100,000 ሰዎች በኮሮና ተሐዋሲ ሊያዙ እንደሚችሉ የሀገሪቱ ጤና ሚንሥትር ዬንስ ሽፓን አስጠንቅቀዋል። የጀርመን የጤና ባለሞያዎች B117 በተሰኘው ልውጡ የኮሮና ተሐዋሲ ምክንያት ቀጣዩ ዙር የኮሮና ወረርሺኝን «ለመቀልበስ እጅግ አዳጋች ነው» ብለዋል። ሮበርት ኮኅ (RKI) የበሽታ ጥናትና ምርምር ተቋም በበኩሉ ዛሬ እንዳስታወቀው በ24 ሰአታት ውስጥ 21.573 ሰዎች በኮሮና ተሐዋሲ ተጠቅተዋል። ይህም ካለፈው ሳምንት ዐርብ በ4000 የሚበልጥ ነው ተብሏል። 183 ሰዎች ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ታምመው ሕይወታቸውን ማጣታቸውንም ሮበርት ኮኅ ዘግቧል። ፍራንክፉርተር አልገማይነ የተባለው ዕለታዊ ጋዜጣ እንዳተተው ከኾነ ደግሞ የጀርመን መንግሥት ልውጥ የኮሮና ተሐዋሲ በፍጥነት የተዛመተባት ፈረንሳይን የተሐዋሲው ከፍተኛ ሥርጭት አካባቢ በማለት ሊሰይም መሆኑን ዘግቧል።
*በመጨረሻም የስፖርት ዜና
የማዳጋስካር ቡድንን በአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የዙር ውድድር ባሳለፍነው ረቡዕ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ 4 ለ0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬ ወደ አይቮሪኮስት አቀና። ብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ መርሃ ግብሩ የመጨረሻ ግጥሚያውን የፊታችን ማክሰኞ ኦሎምፒክ አላሳን ዋታራ ስታዲከም ውስጥ ለማከናወን ዛሬ ወደ ርእሰ መዲና አቢጃን አቅንቷል።ተጋጣሚው አይቮሪኮስት በ7 ነጥብ የሁለተኛ ደረጃ ላይ ይጘናል። እንደ ማዳጋስካር አምስት ጨዋታዎችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ በ9 ነጥብ ምድቡን ትመራለች። 3 ነጥብ ይዛ የምድቡ መጨረሻ ላይ የምትገኘው ኒጀር እና አይቮሪኮስት አራት ጨዋታዎችን አከናውነዋል።

ዩናይትድስቴትስ ለሱዳን የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች። የገንዘብ ድጋፉ ሱዳን ከዓለም ባንክ ያለባትን ዕዳ ጨምሮ ለተፈጠረባት የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ብሎም ለኢኮኖሚያዊ መነቃቃት እንደሚያግዛት ተገልጿል። የዩናይትድስቴትስን ድጋፍ ተከትሎ መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው የልማት አበዳሪ እና ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በጋራ ባወጡት መግለጫ የዩናይትድስቴትስ ድጋፍ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ዕዳ ላለባት ሀገር እፎይታ ይሰጣታል ብለዋል። የጆ ባይደን አስተዳደር የገንዘብ ድጋፉን ለመስጠት የተስማማው ባለፈው የጥር ወር የቀድሞው የዩናይትድስቴትስ የግምጃ ቤት ሹም ሚንስትር ስቴቨን ሙችን ወደ ሱዳን ተጉዘው በነበረት ወቅት ነበር። በዚህም የግምጃ ቤቱ ለሱዳን በአጭር ጊዜ ውስጥ የምትጠቀምበትን የ1,15 ቢሊዮን ዶላር ይለቅላታል ተብሏል።የሱዳን የሽግግር መንግቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ከ10 ዓመታት በላይ በግጭት ስትናጥ የቆየችውን ሱዳንን አረጋግተው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ብርቱ ፍላጎት እንዳላቸው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። የቀድሞ የዩናይትድስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጨረሻ የስልጣን ጊዜያቸው ሱዳንን ሽብርተንነትን ከሚደግፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ መሰረዛቸው ይታወሳል።
በግብጽ መዲና ካይሮ አንድ የመኖርያ ህንጻ ተደርምሶ በትንሹ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። በምስራቃዊ የካይሮ ክፍል በምትገኘው ጂስር አል ሱዌዝ ዛሬ በደረሰው በዚሁ የህንጻ መደርመስ አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ 29 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። የአደጋ ጊዜ ደራሽ ሰራተኞች 10 ፎቆች እንደነበሩት በተገለጸው የህንጻው ፍርስራሽ ውስጥ ተጨማሪ ተጎጂዎችን እያፈላለጉ መሆኑን መንግስታዊው የአልሃራም ጋዜጣን ዋቢ አድርጎ የጀርመን ዜና ምንጭ ዘግቧል። ህንጻው ላይ የደረሰውን የአደጋ ምክንያት የሚያጣራ የቴክኒክ ቡድን ማዋቀሩን አደጋው የደረሰበት ግዛት ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። በግብጽ የመኖሪያ ህንጻዎች መደርመስ እና ጉዳት ማድረስ የተለመደ መሆኑ ነው የሚነገረው። ህንጻዎቹ በወቅቱ አለማታደሳቸው እና የግንባታ ደንቦች አለመተግበራቸው ለአደጋዎች በተደጋጋሚነት መከሰት ዋነኛ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘገባው አመልክቷል። በሌላ በኩል ትናንት በግብጽ በተፈጠረ የባቡር አደጋ የሟቾች ቁጥር 19 መድረሱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ትናንት በትንሹ 32 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል እንዲሁም 165 አደጋ ደርሶባቸዋል ብሎ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በአደጋው የሟቾች ቁጥር 19 ሲሆን በአደጋው የተጎዱት ደግሞ 185 መሆናቸውን አስታውቋል።
በሚያንማር የወታደራዊ ኃይሎች ቀን በሚከበርበት በዛሬው ቀን ወታደሮች እና ፖሊሶች በተቃውሞ ላይ የነበሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ተገደሉ። በከተማዋ የተፈጸመውን ጥቃት በገለልተኝነት እንደተመለከቱ የገለጹ አንድ አጥኚ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ላይ 91 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል። ግድያው በሃያዎች በሚቆጠሩ ከተሞች ውስጥ ተስፋፍቶ መቀጠሉን ያመለከተው ዘገባው በሀገሪቱ የሲቪል አስተዳደር ላይ መፈንቅለ መንግስት ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በአንድ ቀን በርካታ ከተገደሉት ሰዎች ቁጥር ጋር የሚተካከል ግድያ ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተነግሯል። በተመሳሳይ ጥቃት በያንጎን ከተማ ብቻ የአንድ ቀን ግድያ ከፍተኛ ቁጥር ግድያ የተመዘገበበት እጎአ መጋቢት 14 ቀን ነበር ። በዕለቱ 74 ሰዎች ተገድለውበታል።የጁንታው ቡድን ባለስልጣናት የህዝቡን ተቃውሞ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው ለግድያው መባባስ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ዘገባው አመልክቷል። የሚያንማር የፖለቲካ እስረኞች ማሕበር እንዳለው ከድህረ የሲቪል አስተዳደር መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ 328 ሰዎች ተገድለዋል።የወታደራዊ ጁንታው ዋና አዛዥ ጄነራል ሚን አሁንግ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈው ንግግራቸው የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ መሠረት ሊንድ የሚችለውን ሽብርተንነት መዋጋት እንዳለባቸው ከመግለጽ ያለፈ በሀገሪቱ ስለተቀጣጠለው ህዝባዊ ተቃውሞው ያሉት ነገር የለም።
በመላው ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭት ፍትሃዊነት እንደሚያሳስበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ትናንት ዓርብ ባወጣው መግለጫው ክትባቱን የተረከቡ ሃገራት ለዜጎቻቸው በፍትሃዊነት ለማድረስ ቁርጠኝነት ሊያሳዩ ይገባል ብሏል። ከ193 አባል ሀገራት ውስጥ 180ዎቹ ክትባቱ ደርሷቸዋል ያለው ድርጅቱ ነገርግን የደረሳቸውን ክትባት ለዜጎቻቸው በፍትሃዊነት ለማድረስ ቁርጠንነት ሊያሳዩ ይገባል ብሏል። በሊባኖስ አነሳሽነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸደቀው ፖለቲካዊ መግለጫ ዓለም አቀፍ ሥምምነቶች እና ድንጋጌዎች ቢኖሩም "የኮቪድ-19 ክትባት በአገራት መካከልም ሆነ በአገራት ውስጥ ያለው ሥርጭት ፍትሐዊ አለመሆኑ እጅግ ያሳስበናል" ብሏል። አሁንም ክትባቱን ማግኘት ያልቻሉ መኖራቸውን ልብ ያሉት የመግለጫው ፈራሚ አገራት "የምርት ሒደቱን እና ሥርጭቱን ለማሳደግ ዓለም አቀፍ አንድነት እና ዘርፈ-ብዙ ትብብር ያስፈልጋል" ብለዋል። ይኸው ሰነድ እንደሚለው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈው ኮቫክስ የኮቪድ-19 ክትባትን ለሁሉም በፍትሐዊነት መዳረሱን ለማረጋገጥ ኹነኛው መንገድ ነው። ፈራሚዎቹ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገራት አቅም ያላቸው ክትባቱን እንዲያካፍሉም አበረታተዋል። ነገር ግን ሰሜን ኮርያ ፣ ሚያንማር፣ ቤኒን፣ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶርያ እና ሲሸልስ ለሰነዱ ድጋፋቸውን መንፈጋቸው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ዘግቧል። የታዛቢነት መቀመጫ ብቻ ያላቸው ቫቲካን እና ፍልስጤምም ሰነዱን ከመፈረም ተቆጥበዋል።
የአል-ሸባብ መሪ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ በምታካሒደው ጅቡቲ በሚገኙ የአሜሪካ እና ፈረንሳይ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ጥሪ አቀረቡ።
አሕመድ ዲርዬ ወይም አሕመድ ኡማር አቡ ኡባይዳህ የተባሉት የአል-ሸባብ መሪ ትናንት ቅዳሜ በለቀቁት የቪዲዮ መልዕክት ጅቡቲን ላለፉት 22 አመታት በመሩት እና ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን አገሪቱን ለማስተዳደር ምርጫ ያሸንፋሉ ተብለው በሚጠበቁት ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ ላይ ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል።
የአል-ሸባብ መሪ "ጅቡቲን በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የታወጀው ጦርነት ሁሉ ወደሚታቀድበት እና የሚፈጸምበት የጦር ሰፈር ቀይረዋታል" ሲሉ ፕሬዝዳንቱን ወንጅለዋል።
በዚሁ የቪዲዮ መልዕክት ሰውየው "በጅቡቲ የሚገኙ የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ጥቅሞችን ዋንኛ ዒላማዎቻችሁ አድርጉ" የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል። በጅቡቲ 1,500 የፈረንሳይ እንዲሁም 4,000 የአሜሪካ ወታደሮች ያሉባቸው የጦር ሰፈሮች እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ጃፓን፣ ጣሊያን እና ቻይናም በጅቡቲ የተለያዩ ይዞታዎች አሏቸው። 👉🏾 @dwamharicbot
የሱዳን መንግሥት እና አብደል አዚዝ አደም አል-ሒሉ የሚመሩት የሱዳን ሕዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ-ሰሜን የተባለ አማፂ ቡድን በጁባ የሰላም ሥምምነት ተፈራረሙ። የዛሬው ሥምምነት ታጣቂዎችን ከአገሪቱ ጦር ማዋሐድን፣ ዴሞክራሲያዊ እና የእምነት ነጻነት የሚከበርበት ነገር ግን ዓለማዊ መንግሥት መመስረትን ቅድሚያ የሰጠ ነው።
ሥምምነቱን የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን እና የአማፂው ቡድን መሪ አብደል አዚዝ አደም አል-ሒሉ ፈርመዋል። ይኸ አማፂ ቡድን መቀመጫውን በ

ደቡብ ኮርዶፋን እና ብሉ ናይል ግዛቶች አድርጎ የሚንቀሳቀስ ነው። በደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት አሸማጋይነት የተፈረመው ሥምምነት ከሶስት ሳምንታት በኋላ ለሚቀጥለው የሁለቱ ወገኖች ድርድር መሠረት የሚጥል ነው።
👉🏾 @dwamharicbot
የተገን ማመልከቻቸው ውድቅ የሆነባቸውን ስደተኞች ለመቀበል ተባባሪ ሳይሆኑ ቀርተዋል በተባሉ አስራ ሶስት የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮችን ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ገደብ ሊጣልባቸው ይችላል ተባለ። የጀርመኑ ቬልት አም ዞንታግ ጋዜጣ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ያዘጋጀውን ሰነድ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የሸንገን ቪዛ ገደብ ሊጣልባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይገኙበታል። ዘገባው እንዳለው አገራቱ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ዜጎቻቸውን መልሶ ለመቀበል ያላቸው ፈቃደኝነት "በቂ አይደለም።" ይኸ ከሁሉም በላይ ማመልከቻቸው ውድቅ የሆነባቸውን ተገን ጠያቂዎች ይበልጥ ያሰጋል። የአውሮፓ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸውን አገሮች ማንነት በተናጠል ማረጋገጥ በዚህ ወቅት እንደማይቻል ለጀርመን ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
የጀርመኑ ቬልት አም ዞንታግ እንደሚለው ግን የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሴኔጋልን ጨምሮ ከአስራ ሶስት አገሮች ጋር ድርድር መጀመር ይፈልጋል። ትብብሩ ካልተሻሻለ ከመጪው በጋ በኋላ በአገራቱ ላይ የቪዛ ገደብ እንዲጣል የሚጠይቅ ምክረ ሐሳብ ለአውሮፓ አገራት ይቀርባል።👉🏾 @dwamharicbot
ማሕሙድ አሕመድ እና አሊ ቢራን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ድምፃውያን ሙዚቃዎችን ያሳተሙት የካይፋ ሪከርድስ መሥራች አቶ አሊ አብደላ ካይፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አሊ ታንጎ በሚል መጠሪያቸው ይበልጥ የሚታወቁት አቶ አሊ አብደላ ካይፋ በስደት በሚኖሩበት አሜሪካ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ቅዳሜ መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
ጅማ ተወልደው አዲስ አበባ ያደጉት አሊ ታንጎ የተሰማሩበትን የሙዚቃ ማሳተም ሥራ አቋርጠው ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ኑሯቸውን መጀመሪያ በየመን ከዚያም በኋላ በአሜሪካ አድርገው ቆይተዋል።
ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ አሊ ቢራ እና ሙሉቀን መለሰን ለመሳሰሉ ድምፃውያን አሊ ታንጎ ያቋቋሙት ካይፋ ሪከርድስ ሙዚቃዎቻቸውን በሸክላ ለገበያ አቅርቧል። የሙዚቃ ሕትመት ከሸክላ ወደ ካሴት ፊቱን ካዞረ በኋላም ሐመልማል አባተን ጨምሮ የበርካታ ድምፃውያንን ሥራዎች ድርጅታቸው ለገበያ አቅርቧል።👉🏾 @dwamharicbot
የዕለቱ ዜና በድምጽ
• በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ያካሔደውን ጠቅላላ ጉባኤም ሆነ የሊቃነ-መናብርት ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውድቅ አደረገ። በዚሁ ምክንያት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ያቀረበውን ጥያቄ ሳይመለከተው ቀርቷል።
• ማሕሙድ አሕመድ እና አሊ ቢራን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ድምፃውያን ሙዚቃዎችን ያሳተሙት የካይፋ ሪከርድስ መሥራች አቶ አሊ አብደላ ካይፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
• የሱዳን መንግሥት እና አብደል አዚዝ አደም አል-ሒሉ የሚመሩት የሱዳን ሕዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ-ሰሜን የተባለ አማፂ ቡድን በጁባ የሰላም ሥምምነት ተፈራረሙ።
• የአል-ሸባብ መሪ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ በምታካሒደው ጅቡቲ በሚገኙ የአሜሪካ እና ፈረንሳይ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ጥሪ አቀረቡ።
• የተገን ማመልከቻቸው ውድቅ የሆነባቸውን ስደተኞች ለመቀበል ተባባሪ ሳይሆኑ ቀርተዋል በተባሉ አስራ ሶስት የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮችን ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ገደብ ሊጣልባቸው ይችላል ተባለ። የጀርመኑ ቬልት አም ዞንታግ ጋዜጣ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ያዘጋጀውን ሰነድ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የሸንገን ቪዛ ገደብ ሊጣልባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይገኙበታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባንኮች በሚያሳርፉት ገደብ ምክንያት ለሰላማዊ የኃይል ማመንጫ አገልግሎት ይውሉ የነበሩ የኒኩልየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዋን ልትዘጋ እንደምትገደድ ኢራን አስታወቀች። ዩናይትድ ስቴትስ የጣለቻቸው ማዕቀቦች በባንክ የገንዘብ ዝውውር ላይ የፈጠረው ችግር መፍትሔ ካላገኘ «የቡሼር » የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራን ለማቆም እንደሚገደዱ የኢራን የአቶሚክ ኃይል ምክትል ኃላፊ መሐሙድ ጃፋሪ ተናግረዋል። ቡሼር የኒኩሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኢራን ከሩስያ ጋር በጋራ የምታከናውነው የኒኩልየር መርሃግብር አካል ሆኖ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ቡሼር እና ፋርስ ግዛቶች ሰላማዊ የኃይል አቅርቦት አገልግሎት ይውል እንደነበር የጀርመን ዜን ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። ሞስኮ ኢራን የኒኩልየር ኃይልን ለሰላማዊ የኃይል አቅርቦት የመጠቀም መብት እንዳላት በተደጋጋሚ ስትከራከር ቆይታለች። ዩናይትድ ስቴትስ በነዳጅ ዘይት ሃብት በበለጸገችው ኢራን ላይ በጣለችው ማዕቀብ እና ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ በሳደረባት ተጽዕኖ ምክንያት ኢራን ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ መጋለጧን ዘገባው አመልክቷል። በ2018 በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጎአ በ2018 በኢራን ላይ ጥለውት የነበረው ማዕቀብ በተለይም በሀገሪቱ ገቢ እና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ብርቱ ጉዳት አድርሷል። ኢራን አሁን አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር ማዕቀቡን እንዲያነሳላት እና ወደ ቀደመው የኑኩልየር ስምምነት እንዲመለሱ ተስፋ ሰንቃለች።
የዓለማችን ግዙፍ መርከቦች የሚተላለፉበት የግብጹ የስዊስ ቦይ ከአንድ ሳምንት መዘጋት በኋላ በብርቱ ጥረት ዛሬ ተከፍቷል። የመተላለፊያ ቦይውን ለአንድ ሳምንት ዘግቶ የነበረው ግዙፉ ኤቨር ጊቨን የተሰኘውን የንግድ መርከብ ከተሸነቆረበት በማላቀቅ ዳር ማስያዝ መቻላቸውን የመተላለፊያ ቦይው አገልግሎት ሰራተኞች አስታውቀዋል። በዚህም ለአንድ ሳምንት ያህል ጊዜ ከቀይ ባሕር ወደ ሜድትራንያን እና ከሜድትራንያን ወደ ቀይ ባሕር በመጓጓዝ ላይ የነበሩ እና መተላለፊያ አጥተው የነበሩ የተለያዩ ሃገራት መርከቦች አሁን መንቀሳቀስ መጀመራቸውን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። 4 የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ያህል ስፋት እንዳለው የተነገረለት ግዙፉ መርከብ ባለፈው ማክሰኞ ነበር በኃይለና ነፋስ ተመቶ በቦዩ ዳርቻ የተሸነቆረው። በቦዩ ዳር እንዲይዝ የተደረገው መርከቡ መች እንደሚንቀሳቀስ በዝርዝር የተባለ ነገር የለም። ግብጽ የመተላለፊያ ቦዩ በተዘጋበት በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ 95 ሚሊዮን ዶላር አጥታለች። መርከቡን በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ማንቀሳቀስ ከተቻለ የስዊስ ቦይን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ 10 ቀናት ያህል ሊወስድ እንደሚችል ተነግሯል።
በዓለም በባለጸጋዎቹ እና በደሃ ሃገራት መካከል የተፈጠረው የኮቪድ 19 ክትባት አቅርቦት ልዩነት እንደሚያሳስበው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ለኃብታም እና ደሃ ሃገራት የሚቀርበው የክትባቱ መጠን ልዩነት በየዕለቱ እየሰፋ መሄዱ እንደሚያሳስባቸው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ገልጸዋል። ዶ/ር ቴድሮስ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ባስተናገደችው «የክትባቱን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት» በተመለከተው የቪዲዮ ጉባኤ ላይ እንዳሉት «ተሕዋሲው በመላው ዓለም መሰራጨቱን እስከቀጠለ ድረስ የሰዎችን ሕይወት መቅጠፉም ይቀጥላል፤ ዓለም አቀፍ ንግድ እና ጉዞ መቋረጡ አይቀርም፤ የተንኮታኮተው የዓለም ኢኮኖሚ ለማንሰራራትም ጊዜ መጠየቁ አይቀርም።» ብለዋል። በጎርጎርሳዊው 2021 ሁሉም ሃገራት የመጀመርያዎቹ 100 ክትባትን ለሕዝባቸው መስጠት እንዲጀምሩ ድርጅቱ ጥሪ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም 36 ሃገራት አሁንም ድረስ ክትባቱን መስጠት እንዳልጀመሩ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። 16ቱ ሃገራት በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ክትባቱን ያገኛሉ ተብሎ ሲጠበቅ 20 ሃገራት ይህንኑ ዕድል አላገኙም ነው የተባለው። በዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ ክትባቱን ለደሃ ሀገራት ለማዳረስ የሚሠራው ኮቫክስ በመላው ዓለም እስከ ፊታችን የግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 238 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን እንደሚያከፋፍል ይጠበቃል። ኮቫክስ እስካሁን 32 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦች ለደሃ እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሃገራት ማከፋፈሉን ዘገባው አመልክቷል።
ደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ቢያንስ 10 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ጥቃቱ ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ በወረዳው ጌልማ ፣ ጌሊቲ እና ሙልሙል በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የጌልማ ቀበሌ ነዋሪ ነኝ ያሉ አንድ የዓይን እማኝ እንዳሉት ባለፈው ዓርብና ቅዳሜ በቁጥር በርከት ያሉ እና ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ወደ መንደሮች ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈጽመዋል።
«ከአስር በላይ ሰው ሞቷል፤ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በቃ ሦስቱም ቀበሌ ተፈናቅሏል፤ ወጥቷል። የሦስት ቀበሌ ህዝብ ወጥቶ ከቀደሙት ይልቅ ወጥቶ አሁን ጉጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው ተጠልለው የሚገኙት»
የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ በነዋሪዎቹ የተጠቀሰው የጉዳት መጠን እሳቸው ካላቸው መረጃ ጋር ልዩነት ቢኖረውም በተጠቀሰው ስፋራ ጥቃት መፈጸሙን ግን አረጋግጠዋል ።
«በተደራጀ መንገድ እርምጃ ሊወሰድብን ነው በሚል ታሳቢ ነው ወደ መንደር መጥተው 4 አርሶአደሮችን ፣ 2 የቀበሌ ሚሊሺያዎችንና 1 የወረዳ መደበኛ ፖሊስ ላይ ጥቃት አድርሰው ተሰውተዋል እነዚህ ሰዎች ። በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት አድርሰዋል። »
የሐዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ እንደዘገበው በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ታጣቂዎች በሲቪል ዜጎች ላይ የግድያ ጥቃት ሲፈጽሙ የአሁኑ የመጀመሪያቸው አይደለም ። ባለፈው የኅዳር ወር በወረዳው በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት 31 ሰዎች ሲገደሉ ፣ ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። መጽሔት ዝርዝር ዘገባ ይዟል

በአማራ ክልል ቻግኒ መጠለያ ጣቢያ አካባቢ በነበረ አንድ መጋዘን ላይ ዛሬ ረፋዱ ላይ በደረሰ ቃጠሎ ንብረት መውደሙን በአካባቢው የነበሩ ተፈናቃዮችና ባለሥልጣናት ገልጸዋል። በአካባቢው የነበሩ አንድ የዓይን እማኝ እንዳሉት ዛሬ ረፋዱ ላይ «ፎረንቅ» ከተባለው ቦታ ላይ የሚገኘው የተፈናቃዮች የእህልና

የሌሎች ቁሳቁሶች ማከማቻ መጋዝን ከነንብረቶቹ በእሳት ጋይቷል፡፡የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽነር አቶ ልጃለም ዘለዓለም በበኩላቸው በአካባቢው ካሉት 4 መጋዘኖች መካከል አንዱ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ዛሬ ከቀኑ 5፡20 መቃጠሉን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን እንደዘገበው በቃጠሎው የወደመ የንብረት መጠንን በተመለከተ ከፖሊስ የምርመራ ውጤት በኋላ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ዘላለም ገልፀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ባንኮች በሚያሳርፉት ገደብ ምክንያት ለሰላማዊ የኃይል ማመንጫ አገልግሎት ይውሉ የነበሩ የኒኩልየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዋን ልትዘጋ እንደምትገደድ ኢራን አስታወቀች። ዩናይትድ ስቴትስ የጣለቻቸው ማዕቀቦች በባንክ የገንዘብ ዝውውር ላይ የፈጠረው ችግር መፍትሔ ካላገኘ «የቡሼር » የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራን ለማቆም እንደሚገደዱ የኢራን የአቶሚክ ኃይል ምክትል ኃላፊ መሐሙድ ጃፋሪ ተናግረዋል። ቡሼር የኒኩሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኢራን ከሩስያ ጋር በጋራ የምታከናውነው የኒኩልየር መርሃግብር አካል ሆኖ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ቡሼር እና ፋርስ ግዛቶች ሰላማዊ የኃይል አቅርቦት አገልግሎት ይውል እንደነበር የጀርመን ዜን ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። ሞስኮ ኢራን የኒኩልየር ኃይልን ለሰላማዊ የኃይል አቅርቦት የመጠቀም መብት እንዳላት በተደጋጋሚ ስትከራከር ቆይታለች። ዩናይትድ ስቴትስ በነዳጅ ዘይት ሃብት በበለጸገችው ኢራን ላይ በጣለችው ማዕቀብ እና ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ በሳደረባት ተጽዕኖ ምክንያት ኢራን ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ መጋለጧን ዘገባው አመልክቷል። በ2018 በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጎአ በ2018 በኢራን ላይ ጥለውት የነበረው ማዕቀብ በተለይም በሀገሪቱ ገቢ እና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ብርቱ ጉዳት አድርሷል። ኢራን አሁን አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር ማዕቀቡን እንዲያነሳላት እና ወደ ቀደመው የኑኩልየር ስምምነት እንዲመለሱ ተስፋ ሰንቃለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ባንኮች በሚያሳርፉት ገደብ ምክንያት ለሰላማዊ የኃይል ማመንጫ አገልግሎት ይውሉ የነበሩ የኒኩልየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዋን ልትዘጋ እንደምትገደድ ኢራን አስታወቀች። ዩናይትድ ስቴትስ የጣለቻቸው ማዕቀቦች በባንክ የገንዘብ ዝውውር ላይ የፈጠረው ችግር መፍትሔ ካላገኘ «የቡሼር » የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራን ለማቆም እንደሚገደዱ የኢራን የአቶሚክ ኃይል ምክትል ኃላፊ መሐሙድ ጃፋሪ ተናግረዋል። ቡሼር የኒኩሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኢራን ከሩስያ ጋር በጋራ የምታከናውነው የኒኩልየር መርሃግብር አካል ሆኖ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ቡሼር እና ፋርስ ግዛቶች ሰላማዊ የኃይል አቅርቦት አገልግሎት ይውል እንደነበር የጀርመን ዜን ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። ሞስኮ ኢራን የኒኩልየር ኃይልን ለሰላማዊ የኃይል አቅርቦት የመጠቀም መብት እንዳላት በተደጋጋሚ ስትከራከር ቆይታለች። ዩናይትድ ስቴትስ በነዳጅ ዘይት ሃብት በበለጸገችው ኢራን ላይ በጣለችው ማዕቀብ እና ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ በሳደረባት ተጽዕኖ ምክንያት ኢራን ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ መጋለጧን ዘገባው አመልክቷል። በ2018 በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጎአ በ2018 በኢራን ላይ ጥለውት የነበረው ማዕቀብ በተለይም በሀገሪቱ ገቢ እና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ብርቱ ጉዳት አድርሷል። ኢራን አሁን አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር ማዕቀቡን እንዲያነሳላት እና ወደ ቀደመው የኑኩልየር ስምምነት እንዲመለሱ ተስፋ ሰንቃለች።
የስዌዝ-ግብፅ የዉኃ መተላለፊያ ቦይን ላለፉት 6 ቀናት የዘጋችዉ ኤቨር ጊቭን የተባለችዉ ግዙፍ የዕቃ መጫኚያ መርከብ ትናንት ተንቀሳቅሳለች።18 ሺሕ 300 ኮንቴይነር (የብረት ሰንዱቅ) ጭና ቦዩን ለማቋረጥ ትቀዝፍ የነበረችዉ ተንሳፋፊ «ኮረብታ» የዉኃዉን መስመር በመዝጋትዋ ከ420 በላይ መርከቦች መተላለፊያ አጥተዉ ሲጠብቁ ነበር። መርከቢቱ ከመተላለፊያዉ ቦይ አንደኛዉ ጠርዝ ተጠግታ የተቀረቀረችዉ መጀመሪያ ባካባቢዉ በነበረዉ ከፍተኛ ነፋስ ምክንያት ነዉ ተብሎ ነበር።ይሁንና ጉዳዩን ያጠኑ ባለሙያዎች ኋላ ላይ እንዳስታወቁት ለመርከብቱ መሸንቀር ምክንያቱ ነፋስ ብቻ ሳይሆን የመርከብቱ ግዝፈት፣የጫነችዉ ሸቀጥ ክብደትና ፍጥነትዋ ጭምር ነዉ።400 ሜትር (4 ኳስ ሜዳ) የምትረዝመዉ መርከብ 200 ሺሕ ቶን ትከብዳለች።ቀይ ባሕርን ከሜድትራኒያን ባሕር ጋር የሚያገናኘዉ የዉኃ መስመር በአብዛኛዉ ከምሥራቅ፣ ከደቡብ ምሥራቅ አፍሪቃ፣ ከእስያና ከአዉሮጳ ሸቀጦች ይመላለሱበታል።152 ዓመት ዕድሜ ያለዉ የዉኃ መስመር ላለፉት ስድት ቀናት በመዘጋቱ በዓለም የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።የጀርመኑ የኢንሹራንስ ኩባንያ አልያንስ እንደገመተዉ በመስመሩ መዘጋት የዓለም ንግድን ከ6 እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ሳያጣ አልቀረም።የዓለም የንግድ ዕድገት ደግሞ እስከ 0.4 ከመቶ አሽቆልቁሏል።
የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ባካባቢዉ «የማይገመት አለመረጋጋት» ያስክትላል በማለት አስጠነቀቁ።ኢትዮጵያ በምታስገነባዉ የሕዳሴ ግድብ ሰበብ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ ሶስቱ ሐገራት ለ10 ዓመት ግድም ተደራድረዋል።እስካሁን ግን ሁነኛ ስምምነት ላይ አልደረሱም።የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ አል ሲሲ ዛሬ ስለ ግድቡ ግንባታ ለጠየቋቸዉ ጋዜጠኞች በሰጡት መልስ «የግብፅ» ካሉት ዉኃ «ጠብታ» እንዲወሰድባት ግብፅ አትፈቅድም።«ከግብፅ ዉኃ ማንም ሰዉ አንዲት ጠብታ እንኳን መዉሰድ አይፈቀድለትም።አለበለዚያ አካባቢዉ ከማይገመት አለመረጋጋት ዉስጥ ይገባል።» ብለዋል-የቀድሞዉ የግብፅ የጦር ጄኔራል።ከዓለም ረጅም ርቀት የሚጓዘዉ የዓባይ ወንዝ አቋርጧቸዉ ለሚያልፍባቸዉ 10 ሐገራት የኑሮ መሠረትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ነዉ።ኢትዮጵያ፣ የምታስገነባዉ ግድብ ከ110 ሚሊዮን የሚበልጠዉ ሕዝቧን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በተደጋጋሚ አስታዉቃለች።አል ሲሲ በዛሬ መግለጫቸዉ ግብፅ ከዓባይ ዉኃ ያላት ድርሻ ለግብፅ «ቀይ መስመር ነዉ።» ብለዋልም።«ከዚሕ ቀደም ማንንም አላስፈራራንም፣ አሁንም ለማንም ማስጠንቀቂያ መስጠቴ አይደለም» አከሉ ፕሬዝደንቱ።
የመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና
*ዩናይትድ ስቴትስ፦ የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት መስማማቱን ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ በማሳወቃቸው መበረታቷን ገለጠች።«የኤርትራ ወታደሮች ባስቸኳይና ሙሉ በሙሉ ከትግራይ መዉጣት ግጭቱን ለማርገብ ብሎም አካባቢያዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን አስፈላጊ ርምጃ ነው» ብላለች።
*ትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ድንበር ይወጣሉ የተባሉት የኤርትራ ሠራዊት አባላት መቼ እንደሚወጡ እና ምን ያህል እንደሚወጡ ለጊዜው መረጃ እንደሌላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገለጡ።
*የግብጽ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ኢትዮጵያ አባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባው ግዙፍ ግድብ «ሊገመት የማይችል አለመረጋጋት» ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።
*ዛሬ በአይቮሪኮስት አቢጃን ውስጥ 3 ለ1 የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ አለፈ። ኒጀር በተመሳሳይ ሰአት በተደረገው ውድድር ማዳጋስካርን ያለምንም ግብ ነጥብ በመጋራት ለኢትዮጵያ ውለታ ውላለች።
ዜናው በዝርዝር
*ዩናይትድ ስቴትስ፦ የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት መስማማቱን ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ በማሳወቃቸው መበረታቷን ገለጠች። የኋይት ሐዉስ ቃል አቀባይ ጄን ፕሳኪ ትናንት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት አጠር ያለ ማብራሪያ፦ «የኤርትራ ወታደሮች ባስቸኳይና ሙሉ በሙሉ ከትግራይ መዉጣት ግጭቱን ለማርገብ ብሎም አካባቢያዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን አስፈላጊ ርምጃ ነው» ብለዋል። ቃል አቀባይዋ፦ «ይኽንን ገቢር ለማድረግ ሁለቱም መንግሥታት ባስቸኳይ ተገቢዉን ጥረት ያደርጋሉ የሚል ተስፋ አለን» ሲሉም አክለዋል። ይኽም በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከተላኩት ሴናተር ኩንስ ጋር የተደረገው ውይይት አካል መሆኑንም ገልጸዋል። የኤርትራ ጦር ውጊያ ከሚደረግበት ከትግራይ ክልል ለቅቆ እንዲወጣ ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ግፊት ስታደርግ ነበር። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አልገባም በማለት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈዉ ሳምንት ለሀገሪቱ ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ግን የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ መኖሩን አመላክተዋል። በዚያው ሳምንት አስመራ ውስጥ ከኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ከተወያዩ በኋላ ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ እንደምታስወጣ በይፋዊ የማኅበራዊ ገጾቻቸው አውጀዋል።
*ትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ድንበር ይወጣሉ የተባሉት የኤርትራ ሠራዊት አባላት መቼ እንደሚወጡ እና ምን ያህል እንደሚወጡ ለጊዜው መረጃ እንደሌላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገለጡ። ቃል አቀባዩ እስከዛሬ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ ሠራዊት አልገባም የሚል መግለጫ ሲሰጡ መክረምዎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማረጋገጫ ለምን ተጣረሰ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀጣዩን መልሰዋል። «ድንበር አካባቢ የሕግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ በነበረበት ሰአት ወደ ድንበር ገብቶ የነበረው የኤርትራ ኃይል ይወጣል የሚል መረጃ ክቡር ጠቅላይ ሚንሥትር ዶ/ር ዐቢይ በቀደም በአስመራ ካደረጉ በኋላ ስለሰማን እሱ መረጃ በቂ ነው። የውጪ ፖሊሲ አስፈጻሚው መንግሥት ነው። የአስፈጻሚው መሪ ጠቅላይ ሚንሥትሩ ናቸው። ስለዚህ በውጭ ግንኙነት እሳቸው የሚሉት ነገር [የምር]ነው የሚሆነው ማለት ነው።» ቃል አቀባዩ ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታም በዛሬው ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል። «የትግራይ ኹኔታን በተመለከተ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር በዚህ አካባቢ የተፈጸመውን የሰብአዊ ጥቃት በተቻለን ኹኔታ ለማጣራት ተስማምተዋል። የሰብአዊ መብት ድጋፉም፣ የሰብአዊ ረድዔትም እንደዚሁ በተጠናከረ ኹኔታ ቀጥሏል ማለት ነው።»
*የኢትዮጵያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ-ሽብርና ሕገመንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ችሎት፣ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው ከተከሰሱት መካከል ሦስተኛው ተከሳሽ በዋስ እንዲለቀቅ ወሰነ። ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለው ፍርድ ቤት ባሳላፈው ውሳኔ መሰረት ሦስተኛው ተከሳሽ አብዲ ዓለማየሁ የዋስትና መብቱን የሚያስከለክል ምክንያት ባለመቅረቡ 10 ሺህ ብር ዋስትና አስይዞ ከእስር መለቀቅ ይችላል ብሏል። ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በአቃቤ ሕግ የሽብር

ወንጀል ተመስርቶበት የቆየዉ አብዲ ዓለማየሁ በዚሁ ፍርድ ቤት የካቲት 18 ቀን፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ተሻሽሎ ግድያውን ለፍትኅ አካላት ባለማሳወቁ 1996 በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 443/1 መሰረት እንዲጠየቅ ተወስኖ ነበር። ተከሳሹ የተመሰረተበት ክስ ከተረጋገጠ የሚያስቀጣው ከስድስት ወራት ላልበለጠ ቀላል እስራት ብቻ መሆኑ ተገልጧል። ተከሳሽ እስካሁን ለዘጠኝ ወራት በእስራት በመቆየቱ የዋስትና መብት የሚያስከለክል ሆኖ አለማግኘቱን ፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ከሳሽ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዛሬው ችሎት ላይ ሳይታደም ቀርቷል። በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ ጥላዬ ያሚ እና ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹን ጨምሮ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ያሉ ተከሳሾች፤ ዛሬም ተከላካይ ምስክሮቻቸውን አላቀረቡም። ተከሳሾቹ ትናንት በዋለው ችሎት ከምስክሮቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ገልጸው ተለዋጭ ቀጠሮ ለዛሬ ተሰጥቷቸው ነበር። ይሁንና ዛሬም ከተከላካይ ምስክሮቻቸው ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በቂ ጊዜ አለማግኘታቸውን በጠበቃቸው በኩል ገልፀው፤ ፍርድ ቤቱ «የመጨረሻ» ያለውን ቀጠሮ ለሚያዚያ 6፣ 2013 መስጠቱን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሥዩም ጌቱ የላከልን ዘገባ ይጠቊማል።
*የግብጽ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ኢትዮጵያ አባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባው ግዙፍ ግድብ «ሊገመት የማይችል አለመረጋጋት» ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። ፕሬዚዳንቱ «የታላቁ ሕዳሴ ግድብ»ን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡም፦ «የግብጽን ጠብታ ውኃ ማንም እንዲወስድ አይፈቀድለትም» ብለዋል። አለበለዚያ ቀጣናው «ሊገመት የማይችል አለመረጋጋት ውስጥ ሊገባ ይችላል» ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ኢትዮጵያ የውኃ ሐብቷን መጠቀም መብቷ እንደሆነ እና «የታላቁ ሕዳሴ ግድብ»ም በሌሎች ላይ ይህ ነው የሚባል ችግር እንደማያመጣ በተደጋጋሚ ስትገልጥ ቆይታለች። በቅርቡም የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ለማከናወን መዘጋጀቷን ዐስታውቃለች። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ «የታላቊ ሕዳሴ ግድብ» ድርድር የውኃ ሙሌቱንም እንደሚያካትት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ይኽንን አቋሟን የአሜሪካ ልዑክ ቡድንን በቅርቡ መርተው ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት ዶናልድ ቡዝ ማሳወቋንም ገልጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ልዑካኑን ተቀብለው ባስተናገዱበት ወቅት ኢትዮጵያ ሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራትን ጎድቶ የመጠቀም ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።
*«ኤቨር ጊቭን» በተባለችዉ ግዙፍ የዕቃ መጫኚያ መርከብ ለቀናት ተስተጓጉሎ የቆየው የስዊዝ-ግብፅ የዉኃ መተላለፊያ ቦይ ዳግም እንቅስቃሴ ጀመረ። ግዙፏ እቃ ጫኝ መርከብ ጠባቡን የስዊዝ ቦይ መተላለፊያ ላለፉት 6 ቀናት በአግድሞሽ ዘግታ እንቅስቃሴ አስተጓጉላ ቆይታ ነበር። 18 ሺሕ 300 ኮንቴይነር (የብረት ሰንዱቅ) ጭና ቦዩን ለማቋረጥ ትቀዝፍ የነበረችዉ መርከብ የዉኃዉን መስመር በመዝጋትዋ ከ420 በላይ መርከቦች መተላለፊያ አጥተዉ ሲጠብቁ ነበር። መርከቢቱ ከመተላለፊያዉ ቦይ አንደኛዉ ጠርዝ ተጠግታ የተቀረቀረችዉ መጀመሪያ ባካባቢዉ በነበረዉ ከፍተኛ ነፋስ ምክንያት ነዉ ተብሎ ነበር። ይሁንና ጉዳዩን ያጠኑ ባለሞያዎች በኋላ ላይ እንዳስታወቁት ለመርከቢቱ መሸንቀር ምክንያቱ ነፋስ ብቻ ሳይሆን የመርከቢቱ ግዝፈት፣ የጫነችዉ ሸቀጥ ክብደትና ፍጥነትዋ ጭምር ነዉ። 400 ሜትር (4 ኳስ ሜዳ) ያህል የምትረዝመዉ መርከብ 200 ሺሕ ቶን ትከብዳለች። ቀይ ባሕርን ከሜድትራኒያን ባሕር ጋር የሚያገናኘዉ የዉኃ መስመር በአብዛኛዉ ከምሥራቅ፣ ከደቡብ ምሥራቅ አፍሪቃ፣ ከእስያና ከአዉሮጳ ሸቀጦች ይመላለሱበታል። 152 ዓመት ዕድሜ ያለዉ የዉኃ መስመር ላለፉት ስድት ቀናት በመዘጋቱ በዓለም የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የጀርመኑ የኢንሹራንስ ኩባንያ አልያንስ እንደገመተዉ በመስመሩ መዘጋት የዓለም ንግድን ከ6 እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ሳያጣ አልቀረም።የዓለም የንግድ ዕድገት ደግሞ እስከ 0.4 ከመቶ አሽቆልቁሏል።
*ሚያንማር ውስጥ በቀጠለው ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር ከ500 መብለጡ ተገለጠ። የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ለማድረግ አደባባይ የወጡ 510 ሰዎችን እስካሁን መግደሉን የፖለቲካ እስረኞች ረዳት ማኅበር (AAPP) ዛሬ አረጋግጧልል። ማኅበሩ በሚያንማር ትልቁ ከተማ ያንጎን ትናንት ስምንት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አክሏል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፣ ብሪታንያ እና የአውሮፓ ኅብረት የሚያንማር ወታደራዊ ጄነራሎች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወታደራዊ አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፉን በኃይል ለመቀልበስ የሚያደርገውን ሙከራ አውግዟል።
*በመጨረሻም የስፖርት ዜና፦
ኒጀር በአይቮሪ ኮስት 3 ለ1 ዛሬ የተረታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪቃ ዋንጫ ውድድር እንዲያልፍ አስቻለች። 9 ነጥብ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአይቮሪኮስት 3 ለ1 ዛሬ ቢሸነፍም 13 ነጥብ ያላት አይቮሪኮስትን ተከትሎ በሁለተኛነት ወደ አፍሪቃ ዋንቻ ማለፍ ግን ችሏል። በተመሳሳይ ሰአት በተከናወነው ግጥሚያ ኒጀር ከማዳጋስካር ጋር ያለምንም ግብ ተለያይታለች። ማዳጋስካር በ8 ነጥብ እንዲሁም ኒጀር በ4 ነጥብ አጠናቀዋል። በኢትዮጵያ እና አይቮሪ ኮስት የዛሬ ግጥሚያ ጨዋታው ሊገባደድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት የመሀል ዳኛው ባልታወቀ ሁኔታ ሜዳው ላይ ወድቀው ተደግፈው ከሜዳ ወጥተዋል። ውድድሩም ሳይጠናቀቅ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ኒጀር ማዳጋስካር አሸንፋ ከኢትዮጵያ የበለጠ ነጥብ እንዳትይዝ በማጨናገፍም ታሪክ ሠርታለች፤ ለኢትዮጵያ ደግሞ ውለታ። ቀጣዩን የአፍሪቃ ዋንጫን የምታዘጋጀው ካሜሩን ናት።
የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ እዚህ 👉🏾 https://p.dw.com/p/3rOiR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
በኮሮና ተዋህሲ መስፋፋትና የሰው ቸልተኝነት
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እና በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር መረጃ ያሳያል።ይህንን ተክትሎ የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ አስገዳጅ እርምጃዎች እና ግዴተዎችን እንዲተገበሩ፤ የማይተገብሩ አካላት ደግሞ በወንጀል እንዲጠየቁ መንግስት ያለፈው ሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ/ም ማስታወቁ ይታወሳል።
መንግስት እርምጃውን ለመውሰድ ምክንያት ሆኖኛል ያለው ደግሞ በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ አስገዳጅ የጥንቃቄ ዘዴዎችን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆን፣ በተለይም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ያለማድረግ፣ ተቀራርቦ ወይም ተጠጋግቶ መቆም ወይም መቀመጥ፣ የእጅ ንጽህናን አለመጠበቅ እና በተቋማትም ደረጃ ማስክ ላላደረገ ሰው አገልግሎት መስጠት፣ ተገልጋዮች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ያለማድረግ እና መሰል በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራትን እና የተጣሉ ግዴታዎችን የሚጥሱ ሰዎች እና ድርጅቶች በመበራከታቸው እና ለስርጭቱ መንስዔ እየሆኑ በመምጣታቸው መሆኑን ገልጿል።
ያም ሆኖ የጥንቃቄ ርምጃዎች በአግባቡ ሲተገበሩ አይታይም። እናንተስ የኮሮና ተዋህሲ መስፋፋትና የጥንቃቄ እርምጃዎች አተገባበር ላይ ያለውን መዘናጋት እንዴት አያችሁት ? አስተያየታችሁን

Deutsche Welle
የመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አካፍሉን።
በምዕራበ ወለጋ ንፁሃን ዜጎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራበ ወለጋ ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኒ ቀበሌ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰላማዊ ሰዎቸ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታዉቋል።
የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ አንዳስታወቀው ክልሉም ይሁን ሀገሪቱ የሽግግር ሂደቱን ለማሳካት እየሰሩ ቢሆንም «ከለውጥ ሂደቱ በተቃራኒ ቆመዋል»ያላቸው ሀይሎች ግን ሙሉ ሀይላቸውን ለጥፋት እያዋሉ ነው ሲል ገልጿል።
ፀረ-ለውጥ ካላቸው ሀይሎች ውስጥም ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ይህ ታጣቂ ቡድን በገጠርና በከተማ በመንግስት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም መቆየቱን አብራርቷል። በዚህ ጥቃትም በርካታ ንፁሃን ዜጎች ሲገደሉ፤አያሌ የግልና የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል ብሏል የክልሉ መግለጫ።
መግለጫው አያይዞም በትናንትናው ዕለትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃን ዜጎች ምዕራበ ወለጋ ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኒ ቀበሌ በዚሁ ታጣቂ ቡድን መገደላቸውንና በዚህ የንፁሃኑ ግድያ የክልሉ መንግስት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው አመልክቷል ።
በጥቃቱ አድራሾች ላይ የክልሉ መንግሰት የአጸፋ እርምጃ መውሰዱንም አስታውቋል።
አርስተ ዜና
-ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ባቦ ጋንበል በተባለ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በትንሽ ግምት ከ20 በላይ ሰዎች ገደሉ።ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ አቆሰሉ።የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን ቢያምኑም የገዳዮቹን ማንነትና የሟቾችን ቁጥር ግን አልገለፁም።በኒሻንጉል ክልል መተከል ዞንም ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ተስምቷል።
-ሱዳን የአልቃኢዳ አባላት የተባሉ አሸባሪዎች ከሃያ ዓመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ተቋማትና ዜጎች ላይ ላደረሱት ጥቃት 335 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለአሜሪካ ከፈለች።ካሳዉ ከ23ና ከ21 ዓመት በፊት በደረሰዉ የቦምብ ጥቃቶች ለተገደሉ ሰዎች ቤተሰቦችና ለቁስለኞች ይሰጣል ተብሏል።
-የጀርመን መንግስት አስትራ ዜኒካ የሚያመርተዉ ክትባት ዕድሜያቸዉ ከ60 ዓመት በታች ለሚገኙ ዜጎቹ እንዳይሰጥ አገደ።ዉሳኔዉ የኮሮና ተሕዋሲ ክትባትን ለሐገሬዉ ዜጋ ለማዳረስ የሚደረገዉን ጥረት ያዘገየዋል የሚል ስጋት አሳድሯል።ድጋፍም አላጣም።ዜናዉን ለማድመጥ እዚሕ ይጫኑhttps://p.dw.com/p/3rRuy

ዜና፣ መጋቢት 22፣ 2013
በአዲስ አበባና የተለያዩ አካባቢዎች የተበራከተው የወንጀል ድርጊት
የተለያዩ ጥቃቶች፣ ግድያዎች እና ዘረፋዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መስማት እየተለመደ መጥቷል። በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዋና ከተማዪቱ አዲስ አበባ ውስጥ የግድያ፣ ስርቆት እና ዘረፋ ወንጀሎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የሚወጡ ዘገባዎች ይጠቊማሉ። በአሰቃቂ ኹኔታ ግድያዎች፣ የታዋቂ ሰዎች ላይ ብርቱ ድብደባዎች እንዲሁም በጠራራ ፀሐይ ዘረፋዎች መፈጸማቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየወጡ ነው። የወንጀሎቹ አስከፊነትን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ከሰሞኑ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ያወጣው ዘገባ ያሳያል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ለአንድ ሳምንት «የተቀናጀ የጋራ የፀጥታ ኦፕሬሽን» ማድረጉን ገልጧል። ኮሚሽኑ «አዲስ አበባ ከተማን ከማንኛውም የፀጥታ ስጋት የፀዳች ለማድረግ አካኼድኩ ባለው ዘመቻ «ውጤት ማስመዝገቡን» ዐሳውቋል። ዘመቻው ተጠናቅሮ እንደሚቀጥም ጠቅሷል። አክሎም፦ «መላው የከተማው ህዝብ ለሁከትና ብጥብጥ የሚያነሳሱ መረጃዎችን ባለመቀበልና ሀሰተኛ መረጃዎችንም ባለመጋራት እንዲሁም ለፖሊስ ዓይንና ጆሮ ሆኖ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት በፍጥነት እንደተለመደው መረጃ በመስጠት እንዲተባበር» ብሏል።
በግለሰቦች ጸብ እከሌ ተገደለ፤ የእከሌ ንብረት ተዘረፈ፣ እነ እከሌ በአስከፊ ኹኔታ «ባልታወቁ ሰዎች» ተደበደቡ፣ ተገድለው ተገኙ የመሳሰሉ ዜናዎችን መስማት ግን አሁንም የተለመደ ይመስላል። ለመኾኑ በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስከፊ ወንጀሎች የመበራከታቸው ሰበቡ ምን ይሆን? አሳሳቢውን ችግር ለመቅረፍስ መፍትኼው ምንድን ነው ትላላችሁ? ተወያዩበት።
ፎቶ፦ (ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)
በሶማሌ ክልል ከ50 በላይ ሕጻናት እስር ቤት እንደሚገኙ ተገለጠ
በሶማሌ ክልል የእስረኞችን አያያዝ በተመለከተ ከሰሞኑ ጉብኝት እንዳደረገ የገለጠው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ሕጻናት በእስር ላይ እንደሚገኙ ዐስታወቀ። «በወንጀል ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው በፍርድ ቤት እስራት የተፈረደባቸውና ብዛታቸው ከ50 በላይ የሆኑ ሕፃናት በጎዴ ማረሚያ ቤት ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ጋር ተቀላቅለው» እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ዐስታውቋል። ይኽም፦ «በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 36(3) ላይ ወጣት አጥፊዎች (ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት) አካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ተለይተው መያዝ እንዳለባቸው የተደነገገውን» ይጥሳል ብሏል።
«የጎዴ ማረሚያ ቤት በራሱ ከፍተኛ መጨናነቅ ያለበት» እንደሆነ እና እስረኞችም ቅሬታ ማቅረባቸውን ኮሚሽኑ ጠቅሷል። ኹኔታው «አፋጣኝ ትኩረትና መፍትሄ የሚሻ» መኾኑንም ገልጧል። በጎዴ ማረሚያ ቤት 14 ክፍሎች እንደሚገኙ የገለጠው ኮሚሽኑ «ጉብኝቱ በሚደረግበት ጊዜ 470 እስረኞች ይገኙ ነበረ» ብሏል። «አቅም በፈቀደ መጠን ተጨማሪ የማቆያ ቦታዎችን በማዘጋጀትና በእስረኞች ሰብአዊ አያያዝ በተለይ በጅግጅጋ ከተማ በሚገኙት የዞን እና የክልል ፖሊስ ጣቢያዎች አበረታች ርምጃዎች» መታየታቸውንም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዐስታውቋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ «የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በማስከበር ረገድ በወሰዳቸው ርምጃዎች የታዩ መሻሻሎች» የሚያበረታታ መሆኑን ገልጠዋል። «በተለይ ወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት እስር ጉዳይ»ን በተመለከተ ግን «ልዩ ትኩረት እና ፈጣን ርምጃ ያስፈልገዋል» በማለት አሳስበዋል።
ፎቶ፦ (ከኢሰመኮ/ኮሚሽኑ)
ዛምቢያ፥ የኢትዮጵያ አውሮፕላኖችን ወዳልተጠናቀቀው አየር ማረፊያ ማን መራቸው?
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የኾነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን እሁድ ዕለት ዛምቢያ ንዶላ ከተማ ውስጥ ግንባታው ባልተጠናቀቀ አየር ማረፊያ ውስጥ ማረፉን ተከትሎ የዛምቢያ መንግሥት ምርመራ መጀመሩን ዛሬ ዐስታወቀ። ኮፐርቤልት በሰተሰኘው የአየር ማረፊያ ውስጥ የነበሩ የግንባታ ሠራተኞችን ያስደነቀው ክስተት ከአፍታ በኋላም ሊደገም እንደነበረ ተጠቅሷል።
ሌላ የኢትዮጵያ ቦይንግ 737 የመንገደኞች መጓጓዣ አውሮፕላን በተመሳሳዩ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተቃርቦ እንደነበር ተጠቅሷል። የዛምቢያ የመጓጓዣ ሚንስትር ሚሼክ ሉንጉ፦ «ሌላ የኢትዮጵያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጥቂት ሰአታት በኋላ ግንባታው ወዳልተጠናቀቀው አየር ማረፊያ በመጠጋት ለማረፍ ጥቂት ሲቀረው አውሮፕላን አብራሪው እንዴ ይኼ የተሳሳተ አየር ማረፊያ ነው ብሎ ተመልሷል» ብለዋል። ዛምቢያ ባደረገችው የምርመራ ቀዳሚ ውጤት የአብራሪ ችግር እንዳልኾነ ይፋ አድርጋለች።
አውሮፕላኖቹን ያሳሳተው አዲስ አየር ማረፊያ ሌላ አገልግሎት ከሚሰጥ አየር ማረፊያ አጠገብ መኾኑም ተጠቁሟል። አየር ማረፊያው ግንባታው እንዳላለቀ የሚጠቁም በነጭ ቀለም በትልቁ የእንግሊዝኛ «X» ፊደል እንደተጻፈበት፤ ኾኖም ይህ እስከ ምን ያህል ርቀት እይታ ውስጥ እንደሚገባ ግን ግልጽ አለመኾኑን የጀርመን ዜና አገልግሎት (dpa)ዘግቧል።
ወደ ዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ሲጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን በወቅቱ ግንባታው ወዳልተጠናቀቀው አየር ማረፊያ ለማረፍ ሲቃረብ አብራሪው ከተቆጣጣሪዎች ጋር ለመገናኘት መሞከሩን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። በወቅቱም ከተቆጣጣሪዎች እይታ ውጭ መሆኑ የተነገረው አብራሪው በራሱ የእይታ ጥረት አውሮፕላኑን ማሳረፉን የሀገሪቱ የመጓጓዣ ሚኒስቴር ተናግረዋ
...ሚኒስቴር ተናግረዋል። ከቆይታ በኋላ አውሮፕላኑ ቀደም ሲል ይጓዝ ወደ ነበረበት መዳረሻው መብረሩ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሌለ ነው ዘገባው ያመለከተው። አየር መንገዱ ትናንት በድረ ገጹ ባወጣው ዘገባው ስለ ክስተቱ ዝርዝር ጥናት በዛምቢያ የበረራ አገልግሎት ባለሥልጣን አገልግሎት እየተካኼደ መኾኑን ገልጧል። አየር መንገዱ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በተለይ በጭነት ማጓጓዣ የገንዘብ አቅም በመፍጠር በአፍሪቃ ብርቱው አየር መንገድ ሆኖ መቀጠል የሚያስችለውን አቅም ማዳበሩን ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጵያ አውሮፕላኖችን ወዳልተጠናቀቀው አየር ማረፊያ ማን እንደመራቸው ግን የተገለጠ ነገር የለም።
ፎቶ፦(ከኢትዮጵያ አየር መንገድ)
ቤንሻንጉል ክልል፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ እና ከጃዊ ጋር በሚያዋስነው ስፍራ ትናንት ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳሰቁ ነበር በተባሉ 15 ሽፍቶች ላይ ርምጃ መውሰዱን የመተከል ዞን አስቸኳይ ጊዜ አስዳደር/ኮማንድ ፖስትም ዐስታወቀ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በየቦታው ሽፍቶች የሚያርሱት ጥቃት በመበረታሩና እና የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ በወቅቱ ርምጃ አልወሰደም በማለት ለአምስት ቀናት በግልገል በለስ ከተማ ተዘግተው የቆዩ የንግድ ተቋማትም ሥራ መጀመራቸው ተገልጧል። ትናንት ከሰዓት ከአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ ጋር በነበረው ውይይት ላይ መሳተፋቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) በስልክ የገለጡ አንድ የግልገል በለስ ነዋሪ እና ሌሎች ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
የመተከል ዞን አስቸኳይ ጊዜ አስዳደር/ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ በስልክ ለዶይቸ ቬለ(DW) እንደተናገሩት፦ በማንዱራ ወረዳ ከዚህ ቀደምም ሚኒባስ በማስቆም በተሳፋሪዎች ላይ ጥቃት ካደረሱት መካከል ባለፈው ሳምንት 10 በሚደርሱት ላይ ርምጃ እንደተወደ አስረድተዋል። በትናት

ናው ዕለትም በተመሳሳይ በማንዱራ ወረዳ አንድ ቀበሌ ውስጥ የሰው ንብረት ሲዘርፉ የነበሩ ሽፍቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን አክለዋል።
ባለፈው ሳምንት በሚኒባስ ላይ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ የንግድ ተቋማትን የዘጉ የአካባቢው ነዋሪዎች መኖራቸውን ተናግረዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በትናንትናው ዕለት ከከተማው ወጣቶች እና የሀይማኖት አባቶች ጋር ምክክር መካሄዱንም ገልጠዋል። በመተከል ዞን በተለያዩ ጊዜያት በነበረው የጸጥታ ቸግሮች የተፈናቀሉ 190ሺ የሚደርሱ ነዋሪዎች 11 በሚደርሱ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ እንደሚገኙ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ያመልክታል።
ዘገባ፦ ነጋሣ ደሳለኝ ከአሶሳ፤ ዶይቸ ቬለ
የኪንሻሳው ንግግር ያለውጤት መጠናቀቁ ተገለጠ
በአባይ ወንዝ «የታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ምክንያት የሚወዛገቡት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ኪንሻሳ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ውስጥ ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት መቋጨቱ ተዘገበ። የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ቃል አቀባይ አህመድ ሐፌዝ ኢትዮጵያ በድርድሩ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮጳ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ኅብረት ሚናን ውድቅ አድራጋለች ማለታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት አለመስጠታቸውንም የዜና ምንጩ ጠቅሷል። ሮይተርስ በበኩሉ ለኢትዮጵያ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንሥትር ስለሺ በቀለ የላከው የአጭር ጽሑፍ መልእክት እና የስልክ ጥሪ ወዲያው ምላሽ እንዳላገኘ አትቷል።
የወቅቱን የአፍሪቃ ኅብረት የሊቀመንበርነት ሥልጣን በያዘችዉ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሸምጋይነት የተደረገዉ የሦስቱ ሃገራት ንግግር ከወራት በኋላ የተደረገ ነበር። ኢትዮጵያ ንግግሩ በአፍሪቃ ኅብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲደረግ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ዐስታውቃለች። የግድቡን ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትም ከፊታችን ባለው የክረምት ወራት ለማከናወን ማቀዷን ገልጣለች።
አማሮ፦ ነዋሪዎች «ኅልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል» አሉ
በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች «የታጠቁ» ቡድኖች በተለያዩ ቀናት በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለው ከ11 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታወቁ። በታጣቂዎቹ ጥቃት፣ ግድያና ዘረፋ ኅልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ (DW)ተናግረዋል። ታጣቃዊዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት በመዘዋወር ባደረሷቸው ጥቃቶች ነዋሪዎች ከመገደላቸው በተጨማሪ የንብረት ውደሙ ተጠቅሷል። ነዋሪዎች የመኖርያ ቄዬአቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ጨምረው ገልጠዋል።

የረቡዕ መጋቢት 29 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና
*ኢትዮጵያ የ«ታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ እንደሚከናወን ዐስታወቀች። የግብፅ ፕሬዚደንት ግን የአባይ ውኃን የሚቀንስ ማንኛውም የኢትዮጵያ እንቅስቃሴን እንደማይታገስ ዛሬ አስጠንቅቀዋል።
*በኢትዮጵያ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች የድንበር ይገባናል ግጭት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘገቡ። የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚኾን ተገልጧል።
*ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከነገ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙኃን ማድረግ እንደሚጀምሩ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ተገለጠ።
*ኢራን ቀይ ባሕር ላይ መልኅቋን ጥላ በነበረች መርከቧ ላይ ጥቃት መድረሱን ዛሬ ዐሳወቀች። የየመን የባሕር በር አካባቢ ስትቀዝፍ ፍንዳታ የደረሰባት እቃ ጫኝ መርከብ ምናልባትም የወታደራዊ ቁሶችን በመጫን ለኢራን አብዮታዊ ዘብ አገልግሎት ሳትሰጥ እንዳልቀረች ተዘግቧል።
ዜናው በዝርዝር
*ኢትዮጵያ የ«ታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ እንደሚከናወን ዐስታወቀች። ኢትዮጵያ በቀጣዩ የክረምት ወራት ግድቡን መሙላት እንደምትቀጥል የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ስለሺ በቀለ ዛሬ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ግን የአባይ ወንዝ ውኃን የሚቀንስ ማንኛውም የኢትዮጵያ እንቅስቃሴን መንግሥታቸው እንደማይታገስ ዛሬ አስጠንቅቀዋል። የግብጽ ማስጠንቀቂያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለኹለተኛ ጊዜ መኾኑ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የአፍሪቃ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማእከል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሣሙኤል ተፈራ የግብጽ እና ተባባሪዎቿ ፍላጎት ከውኃም ባሻገር ነው ብለዋል።
«የውኃ ጉዳይ ብቻ አይደለም። አረቦቹም ቢኾኑ ከዚህ በኋላ በሚፈጠረው የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የተሻለ ተጠቃሚ ሊኾኑ የሚችሉት ወደ ኢትዮጵያ ሲኾኑ ነው። እና የመጨረሻ ሊያደርጉ የሚችሉት ኢትዮጵያን እንዳትረጋጋ የሚያደርጉ ኃይላትን በመደገፍ ይኽን ሥራቸውን በደምብ አጠናክረው፤ የኢትዮጵያን ልማት እና ይኼ ግድብ ተጠናቆ የሚመጣውን የኃይል አሰላለፍ ለመቀልበስ የሚያደርጉት ጥረት ነው የሚኾነው።»
በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንሻሳ ውስጥ የተካኼደው ንግግር ትናንት ያለስምምነት መቋጨቱ ተዘግቧል። ከአፍሪቃ ኅብረት በተጨማሪ ደቡብ አፍሪቃ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮጳ ኅብረት በታዛቢነት እንዲሳተፉ ሦስቱም ሃገራት መስማማታቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ዐሳውቋል። ግብጽ እና ሱዳን የሦስቱ ታዛቢዎች ሚና ከአፍሪቃ ኅብረት እኩል እንዲሆን መፈለጋቸው ተገልጧል። ኢትዮጵያ የተጠቀሱት ሦስቱ ታዛቢዎች በሦስቱ ተደራዳሪ «ሃገራት በጋራ ስምምነት ሲጠይቁ ብቻ ሐሳብ ማቅረብ ለመፍቀድ» መስማማቷን ውጭ ጉዳይ ዐሳውቋል። ኢትዮጵያ ፍትኃዊ እና ምክንያታዊ የኾነ የአሁን እና የወደፊት በዓባይ ውኃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማንኛውንም ዓይነት ስምምነት እንደማትፈራረምም ዐስታወቃለች።
*በኢትዮጵያ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች የድንበር ይገባናል ውዝግብ ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘገቡ። ካለፈው ዐርብ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ በነበረው ግጭት ብቻ የሞቱት ሰዎች በዜና አውታሮች ከተጠቀሰው እጅግ የበለጠ መኾኑን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች የሚዘዋወሩ ምስሎች እና መረጃዎች ይጠቁማሉ። የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች ለጥቃቱ አንዱ ሌላኛውን ተጠያቂ በማድረግ ተወነጃጅለዋል። የአፋር ክልላዊ መስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነር አኅመድ ሑመድ ለሮይተርስ የዜና ምንጭ «የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሐሩክ እና ገዋኔ የተባሉ በታዎች ላይ በከባድ የጦር መሣሪያ በመታገዝ ጥቃት ፈጽሞብናል» ብለዋል። የሶማሌ ክልል ቃል አቀባይ ዓሊ በደል በበኩላቸው፦ ዐርብ እለት 25 ሰዎች እንዲሁም «ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ» ያሏቸው ሰላማዊ ሰዎች» መገደላቸውን ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ደግሞ ባለፈው አርብ ደአዋዲ እና ቀረፋ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ከ25 በላይ አርብቶ አደሮች ሲገደሉ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑት የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ የአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ካሎይታ የግጭቱ ሰበብ፦ «በሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር በኩል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን ቀበሌዎች አስመልክቶ የተላለፈው ውሳኔና የታወጀው ጦርነት ነው» ብለዋል። በመጪው ምርጫ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአካባቢዎቹ ሊከፈቱ የነበሩ 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ መወሰኑን ተከትሎ በተለይ በሶማሌ ክልል በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ መቅረቡ ይታወሳል።
*ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከነገ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙኃን ማድረግ እንደሚጀምሩ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ተገለጠ። ለስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚጠቀሙባቸው የአየር ሰአት ድልድል በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ብሮድካስት ባለሥልጣን በጋራ በተዘጋጀ መድረክ እየተከናወነ መኾኑንም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ድልድሉ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች ቴሌቪዝን፣ ራዲዮን እና የጋዜጣ አምዶችን ጨምሮ በ52 የመገናኛ አውታሮች የሚከናወን ነው ተብሏል። በእጣ ድልድሉ መሠረት፦ ፓርቲዎች ከመጋቢት 30 እስከ ግንቦት 23 ቀን ድረስ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ቅስቀሳ ማድረግ የሚችሉ መኾኑ ተገልጧል። ድልድሉ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለፌዴራል እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮች፣ የእጩ ብዛት፣ ጾታ እና የአካል ጉዳተኛ እጩ ብዛትንም መሠረት በማድረግ የተከናወነ መኾኑ ተገልጧል።
*ጅቡቲን ላለፉት ኹለት ዐሥርተ ዓመታት በፕሬዚደንትነት የመሩት ኢስማኤል ዖማር ጉሌህ ለአምስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን ሊወዳደሩ ነው። የ73 ዓመቱ የጅቡቲ ፕሬዚደንት ዐርብ በሚካኼደው ምርጫ ዛካሪያ ኢስማኤል ፋራህ ብርቱ ተፎካካሪያቸው ይኾናሉ ተብሎ ይጠበቃል።የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን በማግለላቸው ወደ ፖለቲካው በቅርቡ የገቡት የቀድሞው የንግድ ሰው ኢስማኤል ፋራህ የፕሬዚደንቱ ብቸኛ ተፎካካሪ ይኾናሉ። የ56 ዓመቱ ኢስማኤል ፋራህ ጅቡቲን ላለፉት 22 ዓመታት በመሩት ፕሬዚደንት ኢስማኤል ዖማር ጉሌህ ላይ ይህ ነው የሚባል ተግዳሮት የሚፈጥሩ አለመኾናቸውም ተዘግቧል። አብዛኛው ክፍሏ በበረሐ የተሸፈነው ንዑሷ ጅቡቲ በአፍሪቃ እና የአረብ ባሕረ ሰላጤ መካከል የንግድ መርከቦች በሚመላለሱባት ወሳኝ ሥፍራ ትገኛለች። በጦርነት ከተዳቀቀችው የመንም የምትገኘው በቅርብ ርቀት ላይ ነው።
*የጀርመን መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በጀርመን የልውጡን የኮሮና ተሐዋሲ መስፋፋት ለመቀልበስ አጠር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲበጅ መፈለጋቸው ተገለጠ። የመራኂተ መንግሥቷ ቃል አቀባዪት ዑርሊከ ዴመር ብሪታኒያ ውስጥ መጀመሪያ የተከሰተው ልውጡ የኮሮና ተሐዋሲ ጀርመን ውስጥ በፍጥነት እየተሰራጨ መኾኑ እንዳሳሰባቸው ዛሬ ከቤርሊን ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።
«አዲሱን የልውጡን የተሐዋሲ ሥርጭት በተመለከተ በአኹኑ ወቅት የተለይ ይኼ ነው የሚባል መረጃ የለንም። ኾኖም የጽኑእ ኅሙማን ክፍሎች መያዛቸው የሚነግረን ግልጽ ነገር አለ።የጽኑእ ኅሙማን ሐኪሞች ተጨንቀዋል እያስጠነቀቁም ነው።»
የኮሮና ተሐ

ዋሲ ሥርጭትን ለመግታት ገደቦችን የመጣል እና የማላላት ኃላፊነት ያለባቸው የጀርመን የፌዴራል ግዛቶች ባለሥልጣናት የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። የአንጌላ ሜርክል ፓርቲ መሪ አርሚን ላሼት ክትባት በስፋት እየተሰጠ ለኹለት ሳምንታት የሚዘልቅ «የመሸጋገሪያ የእንቅስቃሴ ገደብ» እንዲኖር ጥሪ አስተላልፈዋል። ይኽ እቅዳቸውም የጀርመን መንግሥት በሚቀጥለው ሲሰበሰብ እንዲወሰን ይፈልጋሉ።
*ኢራን ቀይ ባሕር ላይ መልኅቋን ጥላ በነበረች መርከቧ ላይ ጥቃት መድረሱን ዛሬ ዐሳወቀች። የየመን የባሕር በር አካባቢ ስትቀዝፍ ፍንዳታ የደረሰባት እቃ ጫኝ መርከብ ምናልባትም የወታደራዊ ቁሶችን በመጫን ለኢራን አብዮታዊ ዘብ አገልግሎት ሳትሰጥ እንዳልቀረች ተዘግቧል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቀይ ባሕር ላይ መልኅቋን ጥላ የነበረች የኢራን መርከብ ላይ ጥቃት መድረሱን ዛሬ አረጋግጠዋል። እቃ ጫኝ መርከቢቱ ላለፉት አምስት ዓመታት በየመን አቅራቢያ በሚገኝ ባሕር ላይ ኼድ መለስ ማለቷ ለኢራን አብዮታዊ ዘብ እያገለገለች ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳጫረ ተገልጧል። መርከቢቱ ጥቃት የደረሰባት ትናንት ነበር። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሳይድ ካኅቲብዛዴህ፦ «መርከቢቱ በከፊል ጉዳት ደርሶባታል፤ እንደ እድል ኾኖ አንድም የተጎዳ ሰው የለም» ብለዋል። ኒውዮርክ ታይምስ ላይ የወጣ ጽሑፍ ከጥቃቱ በስተጀርባ የእስራኤል እጅ እንዳለበት ጠቁሟል። የኢራን ዲፕሎማቶች የኒውክሌር ስምምነት ንግግርን ዳግም ለማስጀመር ቪዬና ኦስትሪያ ውስጥ ትናንት ስብሰባ ተቀምጠው ነበር።
የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ በድምፅ፦
እዚህ https://p.dw.com/p/3rh7X?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ማድመጥ ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት👉🏾 @dwamharicbot ይጠቀሙ።
የሆሮ ጉድሩ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ተፈናቃዮች አቤቱታ!
ከኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ከወገኖቻቸው ሞት ባለፈ ለዓመታት የአፈሩትን ሀብት ንብረት ጥለው በየቦታው መበተናቸው እንዳሳዘናቸው ከቀናት እንግልት በኋላ በህር ዳር ከተማ የደረሱ ተፈናቃዮች አመለከቱ፣
ሰሞኑን ባሕር ዳር በአማራ ክልል አደጋ መከላከልና መስተባበሪያና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን አጥር ግቢ ተጠልለው ካገኘናቸው ህፃናት፣ አሮጊቶችና እናቶች መካከል የተወሰኑትን አነጋግረናል፡፡ መንግስት በክልሉ ቋሚነት እንዲያቋቁማቸውም ጠይቀዋል፡፡
ቪዲዮ ዘገባ፦ ዓለምነው መኮንን ከባሕርዳር፤ ዶይቸ ቬለ (DW)
ካምፓላ-የግብፅና የዩጋንዳ ስምምነት
ዩጋንዳ እና ግብፅ የስለላ መረጃ ለመለዋወጥ ተስማሙ።የዩጋንዳ መከላከያ ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ ስምምነቱን የፈረሙት የዩጋንዳ የወታደራዊ መረጃ ክፍል አዛዥና የግብፅ የስለላ ድርጅት ኃላፊ ናቸዉ።የግብፁ የስለላ ድርጅት የበላይ ሜጄር ጄኔራል ሳሜሕ ሰብር ኢል-ደግዊ ካምፓላ ዉስጥ ስምምነቱን ከፈረሙ በኋላ እንዳሉት ሁለቱ ሐገራት «የዐባይን ዉኃ ስለሚጋሩ» መተባበራቸዉ የማይቀር ነዉ።ጄኔራሉ «ዩጋንዳን የሚነካ ጉዳይ ባንድ ወይም በሌላ መንገድ ግብፅንም ይነካል» ባይ ናቸዉም።ነጭ ዐባይ የሚፈልቅባት ዩጋንዳና አብዛኛዉን የዐባይ ዉኃ የምትጠቀመዉ ግብፅ ለወትሮዉ ብዙም አይጣጣሙም ነበር።የዐባይ የላይኛዉ ተፋሰስ የሚባሉት ኢትዮጵያና ዩጋንዳን የመሳሰሉት ሐገራት የዐባይ ዉኃን እንዳይጠቀሙ ግብፅ ማከላከሏን ዩጋንዳ አጥብቃ ስትቃወም ነበር። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በመገንባትዋ ምክንያት ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብ በናረበት ባሁኑ ወቅት የካምፓላና የካይሮ መንግስታት ወዳጅነት እስከ መረጃ ልዉዉጥ መድረሱ ለአንዳዳ ታዛቢዎች አስገራሚ፣ ለሌች አነጋጋሪ ሆኗል።ትናንት ማምሻ ካምላ ላይ በወጣዉ የጋራ መግለጫ መሠረት ግብፅና ዩጋንዳ «በጣም ጠቃሚ» ያሉትን መረጃ በየጊዜዉ ይለዋወጣሉ።
የደቡብ ክልል ፖለቲከኞች ቅሬታና ምርጫ ቦርድ
በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በክልሉ በበርካታ አካባቢዎች አስከአሁን የመራጮች ምዝገባ አለመጀመሩ በምርጫው ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት እሳድሮብናል አሉ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለስልጣናትም መዝገባዉ መዘግየቱን አምነዋል።ይሁንና የዘገየዉ የምርጫ ቁሳቁስ በጊዜ በየምርጫ ክልሎቹ ባለመድረሱ ነዉ ብለዋል።ምዝገባዉ በቅርቡ በሁሉም ክልል እንደሚደረግ አስታዉቃል።በደቡብ ክልል ከሚንቀሳቀሱ 20 የፖለቲካ ፓርቲዎች 13ቱ ዛሬ ሐዋሳ ዉስጥ ባደረጉት ስብሰባ በምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ላይ ተወያይተዋል።የቪዲዮ፣ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ።

ዋሽንግተን-የአሜሪካና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ዉይይት
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ፀጥታን ያናጋዉ ግጭትና ጥቃት እንዳሳሰባቸዉ አስታወቁ።ዋይት ሐዉስ እንዳስታወቀዉ የፀጥታ አማካሪዉ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ባደረጉት ዉይይት በተለይ ትግራይ ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭት እንዳሳሰባቸዉ አስታዉቀዋል።ሮይተር ዜና አገልግሎት የጠቀሰዉ የዋይት ሐዉስ ዘገባ እንዳመለከተዉ ሁለቱ ባለስልጣናት ትግራይ ዉስጥ ለተቸገረዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ስለሚቀርብበት፣ ግጭቱ ስለሚረግብበት፣ የዉጪ ወታደሮች ስለሚወጡበትና የደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደል በገለልተኛ ወገን ስለሚጣራበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።ከአፍሪቃ በሕዝብ ብዛት የሁለተኝነቱን ደረጃ በያዘችዉ ኢትዮጵያ ከትግራይ በተጨማሪ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ የጎሳ ግጭቶችና ጥቃቶችም በዉይይቱ መነሳቱ ተጠቅሷል።ዋይት ሐዉስ አክሎ እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያ በምታስገነባዉ የሕዳሴ ግድብ ሰበብ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚደረገዉ አካባቢያዊ ዉይይት መቀጠል እንዳለበት ተወያይተዋልም።
ዋና ዋና ዜናዎቹ
ዩጋንዳ ከግብጽ ጋር የስለላ መረጃዎችን ለመለዋወጥ መስማማቷን አስታወቀች። ስምምነቱ የተፈራረሙት የግብጽ የስለላ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሥልጣን አባይን ይጋራሉ ያሏቸው ዩጋንዳና ግብጽ በዚህ ረገድ ትብብራቸው የማይቀር ነው ብለዋል።
የአፍሪቃ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ለኮቪድ 19 ክትባት በአሁኑ ጊዜ ፓስፖርት እንዲኖር መታሰቡ ተገቢነት እንደሌለው አመለከተ።
የተለያዩ ሃገራት የደም መርጋት ችግር እያስከተለ ነው ለሚሉት አስትራ ዛኒካ የኮቪድ 19 ክትባት የየራሳቸውን ደንብ እያወጡ ነው። ክትባቱ ያስከትላል የተባለውን ተጓዳኝ የጤና እክል ጨምሮ ተፈላጊነቱ ማወዛገቡ ለአምራቹ ኩባንያ ችግር አስከትሏል።
ነገ በሚካሄደው የጅቡቲ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝደንት ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ አምስተኛ የሥልጣን ዘመናቸውን ሊያራዝሙ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
https://p.dw.com/p/3rjxG?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

የመጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ,ም የዓለም ዜና
አሊባባ ግሩፕ የተባለው ግዙፍ የቻይና የኤሌክትሮኒክ ግብይት ኩባንያ በአገሪቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት 18.3 ቢሊዮን ዩዋን ወይም (2.8 ቢሊዮን ዶላር) ተቀጣ። የቻይና የገበያ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኩባንያው ለአመታት ያለውን የበላይነት የመገበያያ ሥርዓቱን የሚጠቀሙ ቸርቻሪዎችን ለመገደብ እና ነፃ የሸቀጦች ዝውውርን ለመግታት ተጠቅሞበታል ብሏል። አሊባባ የተቀጣው የገንዘብ መጠን በጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም. ከነበረው 70 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ሽያጭ አራት በመቶ የሚደርስ ነው።
"ቅጣቱን በቅንነት እቀበላለሁ" ያለው አሊባባ ከዚህ በኋላ በሕጉ መሠረት ሥራውን እንደሚያከናውን አስታውቋል። የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ ባለሥልጣናት ሥራዎቹን ወደ ፋይናንስ፣ የጤና አገልግሎት እና ሌሎች ስሱ ዘርፎች እያሰፋ የሔደው አሊባባ ኩባንያ በገበያው ያለው የበላይነት እያሳሰባቸው እንደመጣ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ዛሬ ይፋ የሆነው ቅጣት ለኩባንያው መሥራች እና ቢሊየነር ጃክ ማ ተጨማሪ እንቅፋት ሆኗል። ባለፈው ሕዳር የኩባንያው የአክሲዮን ገበያ ሽያጭ በአገሪቱ ባለሥልጣናት ታግዶበት ነበር። ከእገዳው በፊት የኩባንያው መስራች ጃክ ማ ባለሥልጣናቱን የሚተች አስተያየት ሰጥተው ከአደባባይ ርቀው "የት ገቡ?" እስከ መባል ተደርሷል።👉🏾 @dwamharicbot
ሩሲያ በግብርናው ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር አታሼዎችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር አገሮች ማሰማራቷን አስታወቀች። የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳለው ከትናንት ጀምሮ በአስሩ አገሮች ሥራ የጀመሩ ባለሙያዎች "ለትብብር እና ልማት ምክረ-ሐሳቦች ማዘጋጀት፣ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥምምነቶች እና ውሎችን የተመለከቱ ሥራዎች ማከናወን" ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። "ከመንግሥታት እና የንግድ ተወካዮች ጋር ግንኙነት መፍጠር፣ በሩሲያ ኩባንያዎች እና አጋር ሊሆኑ ከሚችሉ ጋር ድርድሮችን ማመቻቸት" ከአታሼዎቹ ሚናዎች መካከል ይገኙበታል።
ከአስሩ አገሮች መካከል ከአፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አንጎላ ይገኙበታል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለበት ሁኔታ የሚፈቅድ ከሆነ ሩሲያ በሌሎች 30 አገሮች ተመሳሳይ አታሼዎች የማሰማራት ፍላጎት እንዳላት የአገሪቱ የግብርና ምኒስትር ዲሚትሪ ፓትሩሼቭ ተናግረዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
የጅቡቲ መንግሥት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ ትናንት አርብ የተካሔደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ልዩነት ማሸነፋቸውን አስታወቀ። የጅቡቲ አገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር ሙሚን አሕመድ ሼይክ ትናንት ማምሻውን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጉሌሕ በምርጫው ከተሰጡ 177,391 ድምጾች 98 በመቶውን በማግኘት አሸንፈዋል።
የጅቡቲ የምርጫ ኮሚሽን የመጨረሻውን ውጤት ዛሬ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን ምርጫውን አሸነፉ የተባሉት ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ ግን "በእኔ ላይ ላሳደራችሁት መተማመን አመሰግናለሁ" ሲሉ በትዊተር ጽፈዋል።
በአገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በተላለፈው የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትሩ መግለጫ የጉሌሕ ተፎካካሪ የነበሩት ዘካሪያ እስማኤል ፋራሕ ያገኙት ድምጽ 1.59 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
በጅቡቲ የሚገኝ የፖለቲካ ጥናት ተቋም ሊቀ-መንበር አዳን ኦማር አብዱላሒ "ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላለመሳተፍ በመወሰናቸው እና የግል ተወዳዳሪ የነበሩት ዘካሪያ ኢስማኤል ፋራሕ በሕዝቡ ዘንድ እምብዛም የሚታወቁ ፖለቲከኛ ባለመሆናቸው ምርጫው የሚጠበቀውን ያክል ብርቱ አልነበረም" ብለዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
የአል-ሸባብ አባል ነው የተባለ አጥፍቶ ጠፊ በሶማሊያ ዛሬ ቅዳሜ በፈጸመው ጥቃት ስድስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ እና የአይን እማኞች ተናገሩ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ከሞቃዲሾ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባይዶዋ ከተማ ሲሆን ግለሰቡ የታጠቀውን ቦምብ በማንጎድ በካፌው ውስጥ የነበሩ የግዛቲቱን አስተዳዳሪ ለመግደል መሞከሩን ፖሊስ አስታውቋል። አሊ ዋርድሔር የተባሉት አስተዳዳሪ ግን ከጥቃቱ ተርፈዋል።
ፖሊስ የአስተዳዳሪው "ሁለት ጥበቃዎች ከቆሰሉት መካከል ይገኙበታል። አንዱ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል። ሌሎቹ አምስት ሰዎች ሰላማዊ ሰዎች ናቸው" ብሏል።
"አጠራጣሪ" ነበር የተባለው አጥፍቶ ጠፊ ከካፌው በር ላይ እንዲቆም ቢደረግም እንዳለመታደል ሆኖ የታጠቀውን ቦምብ ማንጎዱን የአካባቢው የፖሊስ መኮንን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። አታፍ ሞአሊም የተባሉ የአይን እማኝ በፍንዳታው የተበታተነ የሰዎች አካል በየቦታው ወዳድቆ ማየታቸውን ተናግረዋል። አል-ሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።
👉🏾 @dwamharicbot
የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሥርጭት ኢ-ፍትሐዊነት አሁንም መፍትሔ እንዳላገኘ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ። የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በመላው ዓለም ለሰዎች ከተሰጡ 690 ሚሊዮን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች መካከል ለአፍሪካውን የደረሰው ከ2 በመቶ በታች ብቻ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ 45 የአፍሪካ አገሮች ክትባት የደረሳቸው ሲሆን 43ቱ ዜጎቻቸውን መከተብ እንደጀመሩ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በዚህም ወደ አፍሪካ ከተላኩ 31.6 ሚሊዮን ክትባቶች 13 ሚሊዮን የሚሆኑት ለአኅጉሪቱ ዜጎች ተሰጥተዋል። ዶክተር ቴድሮስ ትናንት አርብ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት በተለይ በደሐ እና ሐብታሞቹ አገራት መካከል የክትባቱ ሥርጭት ኢ-ፍትሐዊነት አሁንም እየተባባሰ ነው።
ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም "ከፍተኛ ገቢ ባላቸው አገራት በአማካኝ ከአራት ሰዎች አንዱ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወስዷል። ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት የተከተበው ከ500 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች አንዱ ብቻ ነው" ሲሉ አለመመጣጠኑን ገልጸዋል።
"በዓለም አቀፍ የክትባት ሥርጭት አስደንጋጭ የሆነ አለመመጣጠን አሁንም አለ። ኮቫክስ ክትባቶችን በፍጥነት እና በቅጡ ለማሰራጨት ከሌሎች አማራጮች ሁሉ የተሻለ ነው። ችግሩ ክትባቶቹ ከኮቫክስ ወጥተው ማሰራጨቱ ላይ አይደለም። ችግሩ መጀመሪያውኑ ክትባቶቹ ለኮቫክስ እንዲደርሱ ማድረጉ ላይ ነው። አንዳንድ አገሮች እና ኩባንያዎች ኮቫክስን ገሸሽ በማድረግ በራሳቸው ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያት ክትባቶችን በግላቸው ለመስጠት መወሰናቸውን ተረድተናል። እነዚህ የተናጠል አካሔዶች የክትባት ሥርጭትን ኢ- ፍትሐዊነት ያባብሱታል። የአቅርቦት እጥረት የክትባት ክምችትን እና የክትባት ዲፕሎማሲን እያባባሰ ነው" ሲሉ ዶክተር ቴድሮስ ተናግረዋል።
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4.3 ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ወረርሽኙ በሚያስከትለው ሕመም ሳቢያ 114 ሺሕ በላይ ሰዎች በአፍሪካ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ የተከሰተባትን ኬንያን ጨምሮ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ማሊ፣ ርዋንዳ እና ቱኒዝያ በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
እስከ ትናንት አርብ ድረስ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 225 ሺሕ 516 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ያወጡት ዕለታዊ መግለጫ ይጠቁማል። በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 3 ሺሕ 111 ደርሷል። 👉🏾 @dwamharicbot
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ዛሬ ቅዳሜ ከቱኒዝያ አቻቸው ካይስ ሳኢድ ተገናኝተው በሊቢያ ቀውስ እና ካይሮ ከኢትዮጵያ በምትወዛገብበት ታላቁ የኅ

ዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።
የቱኒዝያው ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ ወደ ካይሮ ለሶስት ቀናት የሥራ ጉብኝ ያቀኑት ትናንት አርብ ነበር። ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በግብጽ የውኃ ደሕንነት ላይ የሚደርስ ማናቸውም ጉዳት ተቀባይነት የለውም ያሉት የቱኒዝያው ፕሬዝዳንት አገራቸው የግብጽን አቋም እንደምትደግፍ ተናግረዋል።
በካይሮ ሁለቱ መሪዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ "ፍትሐዊ መፍትሔ እየፈለግን ነው። ነገር ግን የግብጽ ብሔራዊ ደሕንነት የእኛም ነው። የግብጽ አቋም የእኛ ይሆናል" ሲሉ ተደምጠዋል። የግብጹ ፕሬዝዳንት "ሊቢያ በትክክለኛው መንገድ ትጓዛለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ሊቢያ መከፋፈል የለባትም" ሲሉ ተናግረዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
በመጪው ክረምት የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ከመከናወኑ በፊት መረጃ ለመለዋወጥ ግብጽ እና ሱዳን የግድብ አስተዳደር ባለሙያዎችን በእጩነት እንዲያቀርቡ ኢትዮጵያ መጋበዟን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግድቡ ሁለተኛ ዙር ውኃ ሙሌት በመጪው ሐምሌ እና ነሐሴ ከመቀጠሉ በፊት ሶስቱ አገሮች መረጃ ለመለዋወጥ ግብጽ እና ሱዳን ባለሙያዎቹን እንዲጠቁሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ምኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ለአገራቱ የውኃ ምኒስትሮች መጻፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ከዚህ ቀደም ሶስቱ አገሮች ያዋቀሩት ብሔራዊ ገለልተኛ ሳይንሳዊ የጥናት ቡድን ባዘጋጀው እና በውኃ አሞላሉ ላይ በተደረሰ መግባባት መሰረት ኢትዮጵያ ግብዣውን ማቅረቧ ተገልጿል።
👉🏾 @dwamharicbot
የሚያዝያ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. የዓለም ዜና
• በመጪው ክረምት የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ከመከናወኑ በፊት መረጃ ለመለዋወጥ ግብጽ እና ሱዳን የግድብ አስተዳደር ባለሙያዎችን በእጩነት እንዲያቀርቡ ኢትዮጵያ መጋበዟን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
• የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ዛሬ ቅዳሜ ከቱኒዝያ አቻቸው ካይስ ሳኢድ ተገናኝተው በሊቢያ ቀውስ እና ካይሮ ከኢትዮጵያ በምትወዛገብበት ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።
• የአል-ሸባብ አባል አጥፍቶ ጠፊ በሶማሊያ ዛሬ ቅዳሜ በፈጸመው ጥቃት ስድስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ እና የአይን እማኞች ተናገሩ።
• የጅቡቲ መንግሥት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ ትናንት አርብ የተካሔደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ልዩነት ማሸነፋቸውን አስታወቀ።
• የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሥርጭት ኢ-ፍትሐዊነት አሁንም መፍትሔ እንዳላገኘ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ። የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በመላው ዓለም ለሰዎች ከተሰጡ 690 ሚሊዮን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች መካከል ለአፍሪካውን የደረሰው ከ2 በመቶ በታች ብቻ ነው።
• ሩሲያ በግብርናው ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር አታሼዎችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር አገሮች ማሰማራቷን አስታወቀች።
• አሊባባ ግሩፕ የተባለው ግዙፍ የቻይና የኤሌክትሮኒክ ግብይት ኩባንያ በአገሪቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት 18.3 ቢሊዮን ዩዋን ወይም (2.8 ቢሊዮን ዶላር) ተቀጣ። የቻይና የገበያ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኩባንያው ለአመታት ያለውን የበላይነት የመገበያያ ሥርዓቱን የሚጠቀሙ ቸርቻሪዎችን ለመገደብ እና ነፃ የሸቀጦች ዝውውርን ለመግታት ተጠቅሞበታል ብሏል።
የዕለቱን ዜና ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦ https://p.dw.com/p/3rpHr?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ግብጽ እና ሱዳን የግድብ አስተዳደር መረጃ ባለሞያ እንዲያቀርቡ ኢትዮጵያ ያቀረበችላቸውን ግብዣ ውድቅ ማድረጋቸውን አስታወቁ። ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በኪንሻሳ አደራዳሪነት የዛሬ ሳምንት እሁድ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያደረጉት ድርድር በድጋሚ ሳይሳካ ቀርቷል። ይኽንኑ ተከትሎም ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት የፊታችን የክረምት ወራት ከመጀመሯ በፊት የግድብ አስተዳደር መረጃ መለዋወጥ እንዲቻል ሃገራቱ ባለሞያዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ትናንት ቅዳሜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ጥሪ አቅርባለች ።
ነገር ግን ግብጽ እና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በግድቡ ሥራዎች ላይ ሕጋዊ እና አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚፈልጉ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከካይሮ ዘግቧል። ከኪንሻሳው ውጤት አልባ ድርድር በኋላ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ቀጠሮ እንደምታከናውን አስታውቃለች።
ሱዳን በበኩሏ ሁለተኛው ዙር የታላቁ የህዳሴ ግድብ የዉሃ ሙሌትን ለመቋቋም የጀበል አውሊያ ግድቧን 600 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ዉሃ ለመያዝ ማቀዷን አስታውቃለች። ዕቅዱ ለእርሻ ስራ እና ለንጹህ የመጠጥ ውሃ ፍላጎቷን ለማሟላት እንደሚያግዛት ሱዳን ገልጻለች። ግብጽ በታላቁ የአስዋን ግድብ የተከማቸው ዉሃ የሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት ለመቋቋም የሚያግዝ ከሆነ ዋናው ጉዳይ የሚሆነው የድርቅ ጊዜ አስተዳደር የተመለከተ እንደሆነ የመስኖ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል።
በኪንሻሳው ድርድር ግብጽ እና ሱዳን በአንድ ጎራ ሆነው ከአፍሪቃ ህብረት በተጨማሪ ዩናይትድስቴትስ ፣ የአውሮጳ ህብረት እና የተመድ የአደራዳሪነት ሚና እንዲኖራቸው ሲጠይቁ ኢትዮጵያ የሃገራቱን ጥያቄ ውድቅ አድርጋ ድርድሩ በአፍሪቃ ሕብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲካሄድ እንደምትፈልግ ገልጻለች።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አዲስ የጦር አዛዥ ሾሙ። በደቡብ ሱዳን መጠነ ሰፊ የመንግስታዊ መዋቅር ክለሳ መደረጉን ተከትሎ ጄነራል ሳንቲኖ ዴንግ ዎል አዲሱ የሃገሪቱ ጦር አዛዥ ሆነው ተሾመዋል።
በአዲሱ የመዋቅር ክለሳ የሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር እና የመከላከይ ሚኒስቴር ምክትል ሚንስትርም በሌሎች አዲስ ሰዎች መተካታቸውን የፕሬዚዳንቱን ቃል አቃባይ ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። በደቡብ ሱዳን እጎአ በ2013 የተቀሰቀሰው ግጭት መቋጫ ያገኝ ዘንድ በመንግስት እና በአማጽያን መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ አመት ሞልቶታል። ነገር ግን አሁንም ድረስ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ግጭቶች መቀጠላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።
ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ከቶታል እና ኖክ የነዳጅ ኩባንያዎች ጋር የ3,5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ መስመር ግንባታ ስምምነት ተፈራረሙ። በስምምነቱ መሰረት የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ የድፍድፍ ነዳጅ ከተገኘበት ምዕራባዊ የዑጋንዳ ክፍል በመነሳት ታንዛንያን አቋርጦ ለዓለማቀፉ ገበያ ድፍድፍ ነዳጅ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
የብሪታንያው ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ቱሎ ባለፈው ዓመት ሀገሪቱን ለቆ ከወጣ በኋላ የፈረንሳዩ ቶታል እና የቻይናው ኖክ በባለቤትነት ይዘውታል። ሃገራቱ ከኩባንያዎቹ ጋር አሁን የደረሱት ስምምነት የድፍድፍ ነዳጁን ማውጣት ፣ የመጓጓዣ መሰረተ ልማት መገንባት እና ድፍድፍ ነዳጁን ማጓጓዝን ያካትታል።
ግንባታው የሚጀመረው የነዳጅ ማጓጓዣ መስመሩ ከጉድጓዱ እስከ የታንዛንያዋ ታንጋ የወደብ ከተማ 1,445 ኪ,ሜ ርዝመት ይኖረዋል ተብሏል። በፊርማ ስነስረአቱ ላይ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የታንዛንያዋ አዲሷ መሪ ሳሚያ ሱሉ ተሳታፊ ሆነዋል።
ዑጋንዳ የድፍድፍ ነዳጅ ጉድጓዶቹን ያገኘችው ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚዋሰነው የአልበርቲኔ ሸለቆ