አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አሳውቋል፡፡
ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን ይገኙበታል።
✔ ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤተማነት፤
✔ባሰተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፤
✔ላማህበረሰብ ለበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የ ተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት ነው። በዚሁ መሰረት፡-
1, ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
2, ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ
3, ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ
4, ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በአናሊቲካል ኬሚስትሪ
5, ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
6, ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
7, ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
8, ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
9, ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
10, ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን
11, ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ
12, ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።
https://t.me/voa_amharic1

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ባለፈው ቅዳሜ አምስት ሰዎችን እንደገደሉ ዶይቸቨለ ዘግቧል።
ሰዎቹ የተገደሉት፣ የዘይሴ ብሄረሰብን የዘመን መለወጫ በዓል ለማክበር በተሰበሰቡበት ወቅት ጸጥታ ኃይሎች ድንገት ደርሰው ተኩስ በመክፈታቸው እንደኾነ የዓይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የዘይሴ ብሄረሰብ ለበርካታ ዓመታት በደብዳቤና ሰላማዊ ሰልፍ የልዩ ወረዳ መዋቅር እንዲሰጠው ሲጠይቅ የነበረ ሲኾን፣ ይህንኑ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄያ ግን አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ሳይመልሰው ቀርቷል።

በአቃቂ ክ/ከተማ የማህበር ቤት ገዝተዉ የገቡ ነዋሪዎች ከከንቲባ ጽ/ቤት መጣ በተባለ እግድ ለአመታት የመንግስት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም አሉ
በአቃቂ ክ/ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች በተለይም በወረዳ 13 አለምባንክ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ አመታት በፊት የማህበር ቤት ገዝተዉ የገቡ ሰዎች ቤታቸዉን ለመሸጥ ፤ አሲዘዉም ገንዘብ ለመበደር ፣ የሊዝ ክፍያ ለመፈጸም እና ግንባታም ጭምር ለማድረግ አለመቻላቸዉን ቅሬታቸዉን አቅርበዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከ 900 በላይ ማህበራት እንደታገዱ ገልጾልናል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢ እግዱ ከከንቲባ ጽ/ቤት የመጣ በመሆኑ ከአቅሙ በላይ የሆነ እንደሆነ ነግሮናል ብለዋል።
በቁጥር በርካታ የሆኑት የማህበር ቤቶች በተለይም የግንባታ ፈቃድ ባለማግኘታቸው በወቅቱ መኖሪያ ቤቱን ሲገዙ ከነበረበት የግንባታ ግብዓት ዋጋ አሁን ላይ በከፍተኛ መጠን በመጨመሩ ለኪሳራ ዳርጎናልም ባይ ናቸዉ። የኦዲት ስራዎች እንዲከወኑ ፈቃደኛ ብንሆንም በክ/ከተማዉም ሆነ በከንቲባ ጽ/ቤት መዘግየት ተጎድተናል ብለዋል።
ህገወጦች በመካከላችሁ አሉ ይላል ክ/ከተማዉ ያሉት ቅሬታ አቅራቢዉ እኛ ባናዉቃቸዉም ማጣራት እየቻሉ ካርታ ጭምር ያላቸዉ እና ህጋዊ መንገዱን የተከተሉ ሰዎችም እየተጎዱ ነዉ ብለዋል።
በ 1997 ቦታዉ ተሰጥቶ ግንባታ ሲከናወን የቆየ ቢሆንም በተባለዉ እግድ ምክኒያት አብዛኞቹ ግንባታ አቋርጠዉ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ችሏል።
በብዛት ከቱሉዲምቱ እስከ አለምባንክ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኙት እነዚህ የማህበር ቤቶች ባለቤቶች በተደጋጋሚ ከንቲባ ጽ/ቤትም ሄደን ቅሬታ ብናቀርብ ሰሚ አጥተናል ይላሉ። "ቤት እያለኝ ተከራይ ሆኛለዉ" ያሉን አንድ ቅሬታ አቅራቢ ሰዎች ለህክምና ቤታቸዉን ሸጠዉ ለመታከም ፣ የዉርስ ጉዳዮችንም ለማስተካከል እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
በየጊዜዉ የመንግስት ፕሮጀክቶች በተጀመሩ ቁጥር ሰበብ ይደረግባቸዋል ያሉን ቅሬታ አቅራቢ ከጸረ ሰላም ሀይሎች ጋር የሚደረግ የሰላም ማስከበር ሂደትም ሌላኛዉ የሚቀርብብን ሰበብ ነዉ ብለዋል። ጠብቁ ከሚል ምላሽ በስተቀር መፍትሄ አጥተናልም ይላሉ።
አንዳንዶች እስከ 500 ሺህ ብር ድረስ ጉቦ እየሰጡ አገልግሎት ያገኙ አሉ ያሉንም ሲሆን ይህም ሌላኛዉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደፈጠረባቸዉ ገልጸዋል።
ብስራት የአዲስአበባ ከንቲባ ጽ/ቤትንም ሆነ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማን የማህበር ቤት ባለቤቶችን ጥያቄ ይዞ ለማነጋገር ቢሞክርም ለጊዜዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

የሀገሪቷ የግንቦት ወር የዋጋ ግሽበት 23.3 በመቶ ሆኖ መመዝገብ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታዉቋል!
በግንቦት ወር የተመዘገበዉ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈዉ ወር ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል።
በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች 25∙5 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች 20 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል ብሏል።
በዚህም በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በሚያዚያ ወር ከተመዘገበው 23.3 በመቶ በመሆን ከግንቦት ወር ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ነዉ የተቋሙ መረጃ የሚያሳየዉ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ20 ሺህ ገደማ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በጦርነት ምክንያት 577 ተማሪዎች ብቻ ይፈተናሉ
በአማራ ክልል አንድ ዓመት የሆነው የትጥቅ ውጊያ በትምህርት ላይ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩ ተመላከተ።
ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ብቻ ከ996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስራ ላይ የሚገኙት 32ቱ ብቻ ናቸው።
በ2016 የትምህርት ዘመን ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ከ539 ሺህ 996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ከ13 ሺህ አይበልጡም ተብሏል።
በብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎች ላይም ግጭቱ መስተጓጎል የፈጠረ ሲሆን የ6ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 791 ትምህርት ቤቶች 42 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች መፈተን ቢኖርባቸውም ለፈተና የሚቀመጡት ከ12 ትምህርት ቤቶች የመጡ 506 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
38 ሺህ 203 ተማሪዎች የ8ተኛ ክፍል ፈተና እንደሚፈተኑ ቢጠበቅም በዞኑ ባለው ከፍተኛ ጸጥታ ችግር ሳቢያ መፈተን የሚችሉት 431 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል። ከ19 ሺህ 657 የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መካከል ለፈተና ዝግጁ የሆኑት 577 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የኢህአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ ታምመው ሆስፒታል መግባታቸውን ፓርቲያቸው ተናገረ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ ታስረው ከሚገኙበት 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታምመው ራስ ደስታ ሆስፓታል መግባታቸውን የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አብርሃም ኃይማኖት ለአሻም ነግረዋታል፡፡
ሊቀመንበሩ ከሁለት ወራት በላይ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው እንደከረሙ ያስታወሱት አብርሃም ‹‹ አዋሽአርባ እንኳን ዕድሜያቸው ለገፋ እንደ እርሳቸው ዓይነት ሰው ቀርቶ ጤናማ ሰውን ህመምተኛ የሚያደርግ ስፍራ ነው ›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡
የኢህአፓ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራን ጨምሮ ሌሎች 9 ተጠርጣዎች በትናንትናው ዕለት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው የ12 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል ።
ከዚህ የችሎት ውሎ በኋላ ነበር ሊቀመንበሩ ህመሙ በርትቶባቸው ወደራስ ደስታ ሆስፒታል ያቀኑት፡፡ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታጀብው በራስ ደስታ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ቢሆንም አዳራቸው ግን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ምክትል ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡
ዝናቡ፣ ባጋጠማቸው ህመም ለሚደርስባቸው ማንኛውም ዓይነት አሉታዊ ውጤት መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆንና ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ምክትላቸው አስጠንቅቀዋል፡፡
ሊቀመንበሩ ዝናቡ አበራ ሳይካሄድ የቀረው የህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ እንደነበሩበት ይተወቃል፡፡ ሌላኛው የሰልፉ አስተባበሪ የሺዋሰ አሰፋ ባላፈው ሳምንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ሆስፒታል መግባታቸውን፣ በኋላም ከእስር መለቀቃቸውን አሻም መዘገቧ ይታወሳል፡፡

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ!
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ለመተግበር በአዋጁ የተጠቀሱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ጠ/ሚ አብይ አህመድ( ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ 100 ቀናት የህግና ፍትህ ሥርዓቱ ያለበት አፈፃፀም ግምገማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
ቀደም ሲል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ፍኖተ-ካርታው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ ስለ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል መካተቱም ተመላክቷል።
የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) የሽግግር ፍትህ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ መውጣቱን ገልጸው በፖሊሲው የተመላከቱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል በፌደራልና በክልል ደረጃ ገቢራዊ የሚደረጉ ሀገር አቀፍ ህጎችና አሰራሮች መውጣታቸውን ጠቅሰው፣ የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅን ማስተግበር፣ የወንጀል ሥነ ስርዓት አጽድቆ ገቢራዊ ማድረግም በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በአማራ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ!
የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት እንዳስታወቀው በክልሉ ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል።የክልሉ ጤና ቢሮና የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በክልሉ የወባ በሽታ በከፋ ሁኔታ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።የክልሉ ጤና ተቋማት ኃላፊዎች እንደገለፁት በክልሉ ያለው ግጭት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን አዳክሞታል።የመድኃኒት ስርጭትን ደግሞ አስተጓጉሎታል።ይህም ችግሩ እንዲባባስ አድርጓል።ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተናኛ ግንዛቤና ቸልተኝነት ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው ሲሉ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል።
የክልሉ መዲና የባህርዳር ነዋሪዎች በበኩላቸው በከተማው የወባ ስርጭት መበራከቱን ይገልጻሉ።የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት መለአከ ብርሐን ፍሰሐ ጥላሁን «አሁን በባሕር ዳር ወባ ከቤቴ ጀምሮ አለ፣ ህፃናት እየታመሙ ነው፣ ባሕር ዳር ውስጥ ግንቦት ወር የወባ መነሻ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ፣ ለህክምና ሰዎች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ወባ እየተገኘባቸው ነው፡፡» ብለዋል፡፡የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪ ኃላፊ ወ/ሮ ዓለም አሰፋ ሰሞኑን ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ያለው የትንኝ መከላከያ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ዝቅተኛ በመሆኑና ሌሎች የመከላከል ስራዎችን ቸል በማለቱ በሽታው በብዛት በከተማዋ መታየቱን አስረድተዋል፡፡ባለፈው ሳምንት 7ሺህ ሰዎች የወባ ምርመራ አድርገው በ2ሺህ 460 ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ለፓርላማ የቀረበው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን መጥለፍ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን የምክር ቤቱ አባላት አሳሰቡ!
ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች እና አስተያያቶች ካነሱት መካከል በቅርቡ ለእስር ተዳርገው የተፈቱት የፓርላማው አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ይገኙበታል።ዶ/ር ደሳለኝ ስጋት እና አስተያየት በሚል ባቀረቡት ሀሳብ ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ ወንጀል እና ሽብር ነክ አዋጆች አስፈላጊነታቸው እንደተጠበቀ ሁኖ ተቃዋሚዎችን እና መንግስትን የሚተቹ ተቋማት የነዚህ አይነት ህጎች ሰለባ ሁነው ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው በማውሳት ጥንቃቄ እንዲደረግባቸው አሳስበዋል።
አዋጆቹን ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን ለማሳደድ እንዳያውለው ምን ዝግጅት ተደርጓል ሲሉ ማብራሪያ እንዲሰጥበት በመጠየቅ አዋጆቹ የወንጀል ፍሬ የሆኑትን ብቻ ለይቶ ለመከታተል እና ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን ተገቢ ድንጋጌዎች እንዲካተቱባቸው ሲሉ አሳስበዋል።
ሌላ የምክር ቤቱ አባል በበኩላቸው በአካል በአዋጁ አንቀጽ “በቂ ቁጥጥር ከማያደርጉ የፋይናንስ ተቋማት ጋር የንግድ ግንኙነት ከመሰረተ ወይንም የነበረውን የንግድ ግንኙነት ካስቀጠለ” የሚለው ሃሳብ አሻሚ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሃሳቡ ውስብስብ ከመሆኑ ባለፈ ባንኮቹ ትክክለኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው መሆናቸውንም ሆነ አለመሆናቸውን ማን ነው የሚያረጋግጠው ሲሉ ጠይቀዋል፤ ውጭ ሀገር ያለን ባንክ እንዴት ነው ማረጋገጥ የምንችለው፣ እነዴት በዝርዝር ማስቀመጥ ይችላል ብለዋል።

ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ከእሥር ተለቀቀ!
ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ. ም በገንዘብ ዋስ ከእሥር መለቀቁን ቤተሰቦቹ ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል።ከታሰረ አሥራ አንድ ወራት ሊሞላው ሳምንት የቀረው ገጣሚ በላይ በቀለ፤ በአማራ ክልል ተደንግጎ በቅርቡ የተፈፃሚነት ጊዜው ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋር በተያያዘ በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሰባሳሚት ማረሚያ ቤት ለረጅም ወራት ታሥሮ ቆይቷል።
ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ዛሬ ስምንት ሰዓት ግድም በገንዘብ ዋስትና ከእሥር መለቀቁን እህቱ ሰላም በቀለ ለዴቼ ቬለ አረጋግጣለች።ገጣሚ በላይ ባለፈው ዓመትም የት እንደታሠረ በማይታወቅበት ሁኔታ ለሳምንታት ታስሮ ቆይቶ መለቀቁም ይታወሳል። ገጣሚው ታስሮ የቆየው ከጠያቂ እና ዘመድ ርቆ ባህርዳር ውስጥ መሆኑ ሁኔታዎችን አስቸጋሪ እንዳደረጉበት ጠበቃው ከዚህ በፊት ተናግረው ነበር።ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ «ከባሻገር ባሻገር፣ እንቅልፍ እና ሴት፣ እየሄዱ መጠበቅ እና ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ» የተሰኙ የግጥም እና የወግ መድብሎችን እንዲሁም በሲዲ የተቀናበረ የግጥም ስብስብም አበርክቷል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ክፍፍል
የፌደራል መንግሥት ለ2017 በጀት ዓመት ከያዘው 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ያህሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከፋፈል መድቧል።
ለፓርላማ በቀረበ የበጀት ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደሚታየው 13 ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸዋል።
ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግሥት መደበኛ በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 1.8 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።
ከመንግሥት ግምጃ ቤት 1.7 ቢሊዮን ብር የሚሰጠው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክፍፍሉ ሦስተኛውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያገኝ ይሆናል። ጅማ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በአራተኛ እና በአምስተኛነት ይከተላሉ።
የፌደራል መንግሥት በጀትን የሚያዘጋጀው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ባካሄደው የበጀት ስሚ መርሐግብር ዩኒቨርሲቲዎች “በተቀመጠላቸው ጣሪያ መሰረት” የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።

ህውሃት ዛሬ ባወጣው ግለጫ እኔ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ይቅርታ አልጠየኩም።በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ስህተት ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ህውሃት ሁለት ክንፍ አለው አንዱ የተሳሳተ መረጃን የሚሰጥና የሚያሳስት ቡድን ሌላኛው የተሰጠውን የተሳሳተ መረጃ የሚያርም እንደሆነ እየተሰማ ነው።
ከዚህ የሚያተርፈው ሁሌ ስሙን ከሚዲያው ላለማጥፋት የሚያደርገው አንዱ ስልት መሆኑ ብዙዎች እየገለፁት ነው።
ለአብነትም ከሰሞኑ ከፓርቲው መከፋፈል ጋር በተገናኘ የሰጠው መግለጫ ተጠቃሽ ሆኖ ቀርቧል።

የሱማሌላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ትኾናለች በማለት መናገራቸውን ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ትናንት ከመጽሄቱ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ለምትሰጠው እውቅና በምላሹ ሶማሊላንድ የባሕር በር ትሰጣታለች ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ ባለፈው ታኅሳስ የተፈራረሙት የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም። የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት ግን የመጨረሻው ስምምነት በኹለት ወራት ውስጥ ይፈረማል ብለው እንደሚጠብቁ ከአንድ ወር በፊት መናገራቸው አይዘነጋም።

በጂቡቲ የሚገኝ የሶስት መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
ከአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን እና ይህም የመንግስት አፈጻጸም 69 በመቶ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ ተገለጸ።
በጂቡቲ የሚገኝ የሶስት መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ በጂቡቲ ከሚገኘው የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ ጋር በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በመገኘት በአፈር ማዳበሪያ ዝውውር አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ተገልጿል።
የማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት እስከአሁን 27 የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ የደረሱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ24 መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዙ መሆኑን በመግለጽ፣ ቀሪ 3 መርከቦች በኦፕሬሽን ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
በዘህ መሰረት እስከአሁን 1,334,487.1 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በተሳካ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ በመቻሉ ከዓመታዊ እቅድ 68.78% መሳካቱን ኮሚቴው መግለጹን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሚኒስትሩም እስከአሁን በተሰሩ የማጓጓዝ ስራዎች ኮሚቴውን በማመስገን፣ አሁንም የአፈር ማዳበሪያ ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ኮሚቴው በማጓጓዝ ሂደቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ተቀርፈው ቀሪ የማዳበሪያ ጭነቶች በተጠናከረ መልኩ ተቀናጅቶ በመስራት በሰዓቱ ለአገራችን ገበሬዎች ማድረስ እንዲቻል አቅጣጫ መስጠታቸው ተጠቁሟል።

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የታገደውን የሩሲያ ንብረት 50 ቢሊዮን ዶላር ወለድ ለዩክሬን ለመስጠት ተስማሙ
የቡድን 7 አባል ሀገራት የታገዱ የሩስያ ንብረቶችን በመጠቀም ዩክሬን የሞስኮብ ወራሪ ሃይል ለመዋጋት እንዲረዳት 50 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ እና ለመስጠት ተስማምተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሩሲያ ጥቃት “ወደ ኋላ የማንመለስ መሆናችንን የሚያሳይ ሌላ ማሳሰቢያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። የአፀፋ ምላሽ የሰጠችው ሞስኮ ግን “እጅግ የሚያሠቃይ” የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
ገንዘቡ እስከ አመቱ መጨረሻ ይደርሳል ተብሎ ባይጠበቅም የዩክሬንን ጦርነት እና ኢኮኖሚ ለመደገፍ የረዥም ጊዜ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል። በጣሊያን በተካሄደው የበድን 7 ስብሰባ ላይ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና ባይደን በዩክሬን እና በአሜሪካ መካከል የ10 አመት የሁለትዮሽ የደህንነት ስምምነት ተፈራርመዋል።ይህም ስምምነት በኪዬቭ “ታሪካዊ” ነው። ስምምነቱ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እና የስልጠና እርዳታን ለዩክሬን የሚያካትት ነው።ነገር ግን ዋሽንግተን ወታደሮቿን ለወዳጇ እንድትልክ አይፈቅድም። እ.ኤ.አ. በ 2022 ሩሲያ ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ መውረሯን ተከትሎ 325 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት በቡድን ሰባት አባል ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመሆን ታግዷል።
የንብረቶቹ መታገድ በየዓመት 3 ቢሊዮን ዶላር በወለድ እያስገኙ ይገኛል።በቡድን ሰባት እቅድ መሰረት የ3 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ድጋፍ ሲደረግ የ50 ቢሊዮን ዶላር ብድር ዓመታዊ ወለድ ለመክፈል ይውላል። በደቡባዊ ጣሊያን ፑግሊያ በሚገኘው የመሪዎች ጉባኤ በተካሄደው የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፕሬዚዳንት ባይደን የ50 ቢሊየን ዶላር ብድር ገንዘብ ለዩክሬን እንዲሰራ ያደርገዋል እና። ወደ ኋላ እንደማንል ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሌላ ማሳሰቢያ ይልካል ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባይደን አክለው ፑቲን "እኛን ማስቆም አይችልም፤ ሊከፋፍለን አይችልም እናም በዚህ ጦርነት ውስጥ ዩክሬን እስክታሸንፍ ድረስ አብረናት እንሆናለን ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሜሪካዊያን እና ሌሎች አጋሮቻቸው ለሚያደርጉት ያላሰለሰ ድጋፍ አመስግነዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ተባለ!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ በሚያካሂደው የኃይል ሽያጭ ታሪፍ ማሻሻያ ዙሪያ ከተቋማት እና ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ መሆኑን አስታውቋል።የታቀደው የታሪፍ ክለሳ የኢነርጂ ዘርፉን ለማሳደግ እና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ሲሉ የተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ከሚዲያ ሃላፊዎች ጋር ባካሄዱት ምክክር ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከውሃ 4 ሺህ 820 ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 404 ሜጋ ዋት እና ከእንፋሎት 32 ሜጋ ዋት ኃይል እያመነጨች ትገኛለች ብለዋል።

በጋዛ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ያለ ወላጆቻቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይጠብቃቸዋ ተባሉ
በዴር ኤል ባላ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች የማያቋርጥ ሀዘን ውስጥ ሲሆኑ በርካታ ህጻናት በእስራኤል ጥቃት ወላጅ አልባ ሆነዋል። በጦርነቱ ከ15,000 በላይ ታዳጊዎች የተገደሉ ሲሆን 17,000 የሚገመቱት ደግሞ ወላጆቻቸውን አጥተዋል ወይም በሚፈፀሙ ጥቃቶች የተነሳ ተለያይተዋል። ጉዳዮች በጣም የተለመዱ ከመሆናቸው የተነሳ ሆስፒታሎች አዲስ ምህጻረ ቃል ፈጥረዋል። ይህም "WCNSF" ሲሆን ትርጓሜውም የቆሰለ ልጅ፣ በሕይወት የሚተርፍ ቤተሰብ የለም እንደማለት ነው።
አንዳንድ ልጆች ከሰሜን ጋዛ እንዲሰደዱ ከተደረጉ በኋላ ወላጆቻቸው የት እንዳሉ እንኳን አያውቁም። የዘጠኝ ዓመቷ ሚራ እና ቤተሰቧ ወደ ደቡብ ጋዛ ስንሸሽ ህይወታችንን ለማዳን ሞከርን ትላለች። ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኃላ ከአባቷ ምንም እንዳልሰማች ትናገራሉች። በፍርሃት እየኖርን ነው፤ ወደዚህ ስንሄድ በመንገድ ላይ አስከሬን አይተናል ስትል ታዳጊዋ ለአልጀዚራ ተናግራለች። እስራኤላውያን አካባቢው ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ብለዋል፣ ነገር ግን ያ ትክክል አይደለም። በሄድንበት ቦታ ሁሉ ጥቃቶች ይከተሉናል ስትል አክላለች።
የፍልስጤም ተዋጊዎች ከእስራኤል ወታደሮች ግልር የጎዳና ላይ ውጊያ እያካሂዱ ሲሆን የእስራኤል የጦር ሄሊኮፕተር ፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የጦር አውሮፕላኖች ራፋህን መደብደባቸውን ቀጥለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቅርቡ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረሳል ብለው እንደማይጠብቁ ተናግረዋል ። በቅርቡ የእርቅ ስምምነት ይደረስ እንደሆነ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጠጡት ባይደን አይሆንም፣ ግን “ተስፋ አልቆረጥኩም” ሲሉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በመውሰድ በጀርሞች መላመድ የተነሳ ከፍተኛ የጤና ስጋት መደቀኑ ተገለፀ
መድኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ መሸጥና መጠቀም ሁኔታውን ካባባሱት ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ነው ተብሏል።
በኢትየጵያ የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ትልቁ የጤና ስጋት በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት አስፋላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የመድሃኒት መረጃና አግባባዊ አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም እሸቴ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።
የስልጠናው ዓላማ አቅምን በማሳደግ የተሻለ የጤና ግብዓት ማቅረብ እንደሆነ ገልፀው ተቋሙ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ብሄራዊ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስትራቴጂ ነድፎ በተግባር ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሀኪሞች ተገቢውን መድኃኒት ማዘዝ እና የፋርማሲ ባለሙያዎችም በሀኪም የታዘዘውን መድኃኒት በአግባቡ በማደል የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ይቀንሳል ተብሏል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ትልቁ የጤና ሰጋት እና ክስተት የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ እንደሆነ አቶ ኃይለማርያም ጠቁመው ይህንን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን መስራት እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል።በስልጠናው የተመረጡ የግል የመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች ፣ የመድኃኒት ባለሙያዎችና የእንስሳት መድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች የመድኃኒት ባለሙያዎች በስልጠናው እንዲሳተፋ ተደርጓል፡፡
አሥራ ሁለተኛው የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ቀን በዛሬው እለት የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የመንግስት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማጠናከር በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።