University of Gondar (UoG)
10.9K subscribers
2.77K photos
3 videos
2 files
115 links
University of Gondar is one of a pioneer public higher education institution with commendable achievements in teaching, research and community services.
Download Telegram
A professional development training on trauma-focused therapy: theory and techniques took place at the University of Gondar!
፨፨፨?፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Dr. Waganesh Zeleke from Virginia Commonwealth University, USA delivered a training on trauma, its impact and trauma-focused therapy at the University of Gondar on June 21, 2023.

The list of participants included staff and students from various campuses of the University of Gondar.
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Devoted to Excellence!
Public and International Relations Directorate
June 21, 2023
የአርሶ አደሮች ስልጠና፣ ግብዓት እና የስራ ርክክብ ተደረገ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ RISA (Research and innovation system in Africa) ድርጅት ጋር በመተባበር የተሻሻሉ የሩዝ ቴክኖሎጅዎችን ለአርሶ አደሮች ለማስፋትና የንብ እርባታን ከአቦካዶ አትክልት ጋር በማቀናጀት የማርና የአቦካዶ ምርትን ለመጨመር የሚያስችል ስራ ለመስራት ስልጠናዎችን መስጠትን ጨምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ሰኔ 17/2015 ዓ.ም ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችሉ የስልጠና፣ ግብዓት እና የስራ ርክክብ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ምጥርሀ እና ሰንደባ ቀበሌዎች ተካሂዷል፡፡ በርክክብ መርሀግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘን ጨምሮ የኮሌጅ ዲኖች፣ የተለያዩ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የጎንደር ዙሪያ ዋና አስተዳዳሪ፣ የግብርና ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዙሪያ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነጋ ብርሀኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰቡ የጀርባ አጥንት ነው ያሉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት ምርጥ ዘርና የማዳበሪያ ግብዓት በማቅረብና በሌሎች ዘርፎች ወረዳውን ሲደግፍ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ በበኩላቸው አካባቢው በእምቅ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ በመሆኑ ይህንን መልካም አጋጣሚ ማህበረሰቡ እንዲጠቀምበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ምርጥ ዘር በማቅረብ፣ ትራክተር በማስተዋወቅና አሁን ደግሞ በ RISA ፕሮጀክት አማካኝነት የተሻሻሉ የሩዝ ቴክኖሎጅዎችን ለአርሶ አደሮች በማስፋትና የንብ እርባታን ከአቦካዶ አትክልት ጋር በማቀናጀት የማርና የአቦካዶ ምርትን በመጨመር የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በእለቱ በሩዝ ምርት ለተመረጠው 50 የምጥርሀ ቀበሌ ለሚገኙ የድሀድሀ፣ ሴቶችና የአካል ጉዳተኛ አርሶ አደሮች ከፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ስልጠና ማዕከልና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመተባበር ምርጥ የሩዝ ዘር እና ማዳበሪያ እንዲሁም ሌሎች ግብዓት ርክክብ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም የንብ እርባታን ከአቦካዶ አትክልት ጋር በማቀናጀት የማርና የአቦካዶ ምርትን መጨመር ላይ እንዲሰራ ለተመረጠው የሰንዳባ ቀበሌ 100 አርሶ አደሮች ለንብ ማነብ ስራ የሚያስፈልጉ ሙሉ ግብዓቶችና ቁሳቁሶችን ርክክብ ተደርጓል፡፡ ወደፊትም የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚሰሩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ከፋለ እንየው ተናግረዋል፡፡

ግብዓቱንና ምርጥ ዘሩን ላገኙ የተመረጡ አርሶ አደሮች የሩዝ ቴክኖሎጅ ፕኬጅ ስልጠና እና በንብ ማነብና በአቦካዶ ምርት ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ደግሞ ንብ ለማነብና አቦካዶ ልማት አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎች ተሰጥቶ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 18/2015
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናውን በተሻለ ውጤት ለማለፍ በቂ ዝግጅት አድርገናል-የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተፈታኝ ተማሪዎች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ጎንደር ሰኔ 17/2015(ኢዜአ)፦ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናውን በተሻለ ውጤት ለማለፍ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተፈታኝ ተማሪዎች ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲው የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ መኩሪያው አያሌው "ዘንድሮ በአገር ደረጃ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በተሻለ ውጤት ለማለፍ በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ" ሲል ተናግሯል።

"ላለፉት ተከታታይ ወራት ፈተናውን በብቃት ማለፍ የሚያስችል ድጋፍ ዩኒቨርሲቲው አድርጎልናል።" ተማሪ መኩሪያው፣ ሞዴል ፈተናዎች ለዋናው ፈተና በበቂ እንዲዘጋጅ ያእንዳነሳሱትም ገልጿል።

በሲቪል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ዘርፍ ተፈታኝ የሆነው ተማሪ ዮናስ በላይ በበኩሉ፣ ለመውጫ ፈተናው በበቂ ሁኔታ ከማጥናት ባለፈ የስነ-ልቦና ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ፈተናውን በውጤት ለማለፍ ዝግጅት ማድረጉን የተናገረው ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ መሳይ ደርበው ነው።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኝ ለኢዜአ እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን መውጫ ፈተና የሚወስዱ 12 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በዩኒቨርሲቲው፣ በ87 የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱም አክለዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 3ሺህ 159 መደበኛ ተማሪዎች ሲሆኑ 8ሺህ 676 ያህሉ ደግሞ በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች ሲማሩ የቆዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሁሉም ተማሪዎች በመውጫ ፈተናው ማለፍ እንዲችሉ ባለፉት ወራት በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ግብር ሃይል ተቋቁሞ የማብቃት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በህክምና ሳይንስ ኮሌጅና በሕግ ትምህርት ቤት ውስጥ የተመራቂዎችን ብቃት መለካት የሚያስችል የመውጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሱት ዶክተር ካሳሁን፣ ይህን ተሞክሮ መሰረት ያደረገ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስረድተዋል።

ከዝግጅቶቹ መካከልም በኦን ላይ የሚሰጠውን ፈተና ተማሪዎች ያለ ችግር መውሰድ እንዲችሉ ከ2ሺህ 300 በላይ መፈተኛ ኮምፒውተሮችን ማዘጋጀት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በፈተና ወቅት የኢንተርኔት መቆራረጥና መዘግየት ችግር እንዳያጋጥም የኢንተርኔት አቅምን የማሳደግ ሥራ መሰራቱን ገልጸው፣ "የኤሌክትሪክ ሃይል ቢቋረጥም ጄኔሬተሮች ዝግጁ ተደርገዋል" ብለዋል።

የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በቂ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በባለሙያዎች የስልጠናና የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉንም ተናግረዋል።

ለሁሉም ተፈታኞች ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረጉ የማጠናከሪያ ትምህርቶች በመስጠት ከዚህ ቀደም ከተማሯቸው ኮርሶች ጋር የተዛመዱ ሞዴል ፈተናዎችን ለልምምድ እንዲወስዱ መደረጉንም ዶክተር ካሳሁን ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል 100 ያህሉ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ጠቁመው፣ የቅድመ ዝግጅት ስራው እነሱንም ተደራሽ ማድረጉን አመልክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና የተማሪዎችን እውቀት፣ አቅምና ብቃት ለመገንባት የሚያነሳሳ፣ የትምህርት ጥራትንም ደረጃ በደረጃ ለማረጋጋጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ለውጤታማነቱ አበክሮ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በመደበኛ፣ በማታና በርቅት የትምህርት መርሃ ግብሮች ከ40ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ እያስተማረ ይገኛል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኢዜአ እንደዘገበው
የተሻሻለ የዶሮ ቤትን ከጓሮ ጥምር ግብርና ጋር የማቀናጀት አስፈላጊነት በሚል ርዕስ የተሰራ የፕሮጀክት ውጤት ቀረበ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የተሻሻለ የዶሮ ቤትን ከጓሮ ጥምር ግብርና ጋር የማቀናጀት አስፈላጊነት በሚል ርዕስ የተሰራ ፕሮጀክት የማስተዋወቂያ መርሀ-ግብር ሰኔ 19/2015 ዓ.ም በጠዳ ግቢ ቀረበ።

በፕሮግራሙ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ካህሊ ጀምበሬ፣ የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው መኩሪያ፣ የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ተፈሪ አለም፣ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ መኩሪያው ዘውዴ እንዲሁም የፕሮጀክቱ አባላት ተገኝተዋል።

እንስሳትና ሰብልን በአንድ ላይ ማምረት መቻሉ፣ ዶሮን ከአውሬ በመጠበቅ የተሻለ የእንቁላል ምርት እንዲሰጡ ለማድረግና ዶሮዎችን በቤት ውስጥ በማዋል ቀለባቸው ሳይረጋገጥና ሳይባክን ለመጠቀም እንደሚረዳ የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው መኩሪያ አብራርተዋል።

የዶሮዎቹን ፅዳጅ በመጠቀም ለማዳበሪያ የምናውለውን ወጭ ለመቀነስ እንደሚረዳ እና የእርባታ ሂደትንና አሰራርን እንደሚያቀል የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ካህሊ ጀምበሬ ገልፀዋል።

በአካባቢ በሚገኝ ቁሳቁስ መሰራት መቻሉ እንዲሁም ቀላልና ተመራጭ የገቢ ማስገኛ መሆኑን የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ተፈሪ አለም አብራርተዋል።

የዶሮ እርባታን ከሌሎች የጥምር ግብርና ክፍሎች ጋር ማቀናጀት አወንታዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ የተጠቃሚዎችን ኑሮ ማሻሻል ዋና አላማው መሆኑን የደን ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ መኩሪያው ዘውዴ ተናግረዋል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 19/2015 ዓ.ም