Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
ወደ ምናባዊ ጉብኝት እንመለሳለን አሁን ስለ ፓርኩ ግንባታ ጥቂት መረጃ ላካፍላቹ...

•ከተለያዩ ምንጮች በአምስት ቢሊዮን ብር ወጪ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (የኖቤል ተሸላሚ) የተገነባው አንድነት ፓርክ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 1,600 ሠራተኞችና ባለሙያዎች በግንባታዉ ተሳትፈዉበታል።

•የፓርኩ ግንባታ ካስፈለጉት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የመሬት አቀማመጥን ማስተካከል አንዱ ሲሆን ለፓርኩ 6000 ጊዜ የሚሆን በጭነት መኪናዎች ልዩ አፈር ወደ ፓርኩ አመላልሰዋል፡፡

•በተጨማሪም ፓርኩ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ቀደምት መኪኖች መካከል አንዱ አሁንም ድረስ ሊነዳ የሚችል በዉስጡ ያካተተ ሲሆን፣የታክሲ ሾፌሮች ማህበር አባላት ባቀረቡት አስተያየት ይህ መኪና ወደ ስፍራው እንዲገባ ተደርጓል።

•አይ.ሲ.ጂን ኢንጂነሪንግ እና ALEC ኮንትራክተር ከዱባይ ኩባንያ የመሬት አቀማመጡን ሰርተዋል፡፡
ከዛሬ ጥቅምት 3 ጀምሮ አስቀድመው በኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ ቲኬት የቆረጡ 1500 ጎብኚዎች በፓርኩ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

አንድ ሰው ፓርኩን ለመጎብኘት ለመደበኛ ትኬት 200 ብር እና ለቪአይፒ ቲኬት 1000 ብር የሚከፍል ሲሆን የውጭ ዜጎች ለመደበኛ ጉብኝት 20 የአሜሪካ ዶላር የሚከፍሉ ሲሆን ለቪአይፒ መግቢያዎች ደግሞ 50 ዶላር ይከፍላሉ ፡፡

መልካም ቀን ይሁንልን።
ዘውድ ቤት

•ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም፣ የዚህን ህንፃ ምድር ቤት የአጼ ኃይለሥላሴን ባለስልጣናት አስሮ ለማሰቃየት ተጠቅመውበት እንደነበር ታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ።

•የፀሎት ቤቱና የሥዕል ቤቱ ባለ ሁለት ፎቅ ነው። ሁለተኛው ፎቅ ላይ ከፍ ብላ የተሠራች በመስታወት የተሸፈነች ቤት አለች፤ ይህች ቤት 'ቴሌስኮፕ' ያላት ሲሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ ማየት ታስችላለች።

•በዚች እንቁላል ቤት መገናኛው ድልድይ ጋ የመጀመሪያው ስልክ የገባበት ቤት ይገኛል። ቤቱ ከድንጋይና ከእንጨት የተገነባ ነው።

•አርክቴክት ዮሐንስ የኪነ ህንፃውን ጥበብ ሲገምቱ ከአርመኖችና ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሕንዶች ሳይሳተፉበት እንደማይቀሩ ይገምታሉ።

•ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የውይይት ክበብ በመሆን አገልግሏል

•ሌላኛው ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው። ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው።

•በምድር ቤት የዙፋን ግብር ቤት ይገኛል። የነገሥታቱ መመገቢያ አዳራሽ ሲሆን ንጉሣዊ ቤተሰቦች ምግብ የሚመገቡበት ክፍል ነበር፤ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የደርግ ምክር ቤት መሰብሰቢያ በመሆን አገልግሏል።
ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያለውን የአንድነት ፓርክ በፎቶ ይጎብኙ...
የምስል ምንጭ ከቢቢሲ
ጥያቄ አለኝ

ለሁሉም(9) ክልሎች በአንድነት ፓርክ ዉስጥ እልፍኝ አንደተሰጣቸዉ ይታወቃል ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኅላ ሲዳማ ክልል መሆኑ አይቀሬ ነው ምናልባትም ሌሎችም ይከተሉ ይሆናል።

እዚጋ ለፓርኩ አስተዳደር ጥያቄ ላነሳ የፈለኩት ነገር ቢኖር ለወደፊቱ ለሚፈጠሩ ክልሎች በፓርኩ reserve ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል ወይ? የሚል ይሆናል።

ምክኒያቱም ፓርኩን እንዳየነው ከሆነ ለክልሎች የተሰጠው እልፍኝ በአንድ አከባቢ ነው። ይሄ ማለት ደግሞ ለወደፊቶቹ ክልሎች እልፍኝ ይሰጣቸዉ እንኳን ቢባል ከ9ኞቹ ገለል ካለ ቦታ መሆኑ ነው። እንደዛ ከሆነ ከአዲሱ ክልል ለመጣ ጎብኚ ደስ ማይል ስሜት ሊፈጥርበት ይችላል።

ጥያቄው ተራ ነገር ሊሆን ይችላል ነገር ግን አሁን ባለንበት ሁኔታ እርስ በእር ለመጋጨት ትንሽ ምክኒያት የሚፈልግ ማህበረሰብ ተፈጥሮዋል ታድያ በዚዉ ከቀጠልን ይሄ ጉዳይ ለወደፊቱ ችግር አይፈጥርም ትላላቹ?

በዚ ጉዳይ ላይ አስተያየት ወይም ሃሳባቹን ማካፈል ለምትፈልጉ @UnityParkBot ይጠቀሙ
አንድነት ፓርክ በ15 ቀን ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገባ!

በብሔራዊ ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ በአምስት ቢሊዮን ብር ወጪ የተሠራው አንድነት ፓርክ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ከሆነበት ከመስከረም 29/ 2012 ጀምሮ ከ 15 ሺሕ በላይ በሚሆኑ ጎብኚዎች ተጎብኝቶ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።

የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ታምራት ኃይሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከፓርኩ የሚገኘው ገቢ ፓርኩን ለማስፋፋት እና ለመጠበቅ እንዲሁም ለማሻሻል ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልጸው አረጋዊያን፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ለሀገር በጎ ውለታ የዋሉ ዜጎች ታዳጊ ህፃናት እና የጎዳና ልጆች ፓርኩን በነፃ እንዲጎበኙ መደረጉንም ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-29-8

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
ahun Be Fana TV lay alem shemach bemibalew program Andinet parkn asmelkto eyetelalefe yigegnal. arif mereja tagegnalachu bye asbalew tegabezulgn
Benegerachn lay anbesochu be parku wust bemigegnew washa wust endegebu eyayew nw
በአንድነት ፓርክ ከ300 በላይ ልዩ ልዩ የዱር እንስሳትን የያዘ ማሳያ በቅርቡ ለጉብኝት እንደሚከፈት ፓርኩ አስታወቀ።
ከዛሬ ጀምሮም በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ጎብኚዎች ፓርኩን በክፍያ እንደሚጎበኙ የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታምራት ኃይሌ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
በታላቁ ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ የተገነባው የአንድነት ፓርክ የምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት መሪዎችና ተጋባዦች በተገኙበት ባለፈው ወር መጨረሻ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን በአንድ ስፍራ የሚያስተዋውቀው ይህ ፓርክ ከያዛቸው ዋና ዋና መስህቦች መካከል ብርቅየው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ፣ ሃገር በቀል ዕጽዋት፣ የክልሎች እልፍኝ፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ ታሪካዊ ህንጻዎችና ዐውደ ርዕዮች እንዲሁም የእንስሳት ማቆያ ይጠቀሳሉ።
ፓርኩ ስራ ከጀመረ አንስቶ 17 ሺህ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት ጎብኚዎችን ያስተናገደ ሲሆን፥ 5 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱንም ነው ስራ አስኪያጁ የተናገሩት።
በቅርቡም 46 አይነት ዝርያ ያላቸው 312 ልዩ ልዩ የዱር እንስሳት “የአንድነት የእንስሳት ማሳያ”ን ይቀላቀላሉ ብለዋል።
ከኢትዮጵያና ከሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ተሰባስበው ወደ ፓርኩ ከሚገቡት የተለየ ተፈጥሮና ባህርይ ካላቸው የዱር እንስሳት ባሻገር አዕዋፋትና አሳዎችም ይኖራሉ።
#FBC
የጥቁር አንበሳ መካነ እንስሳት

•የጥቁር አንበሳ መካነ እንስሳት በአንድነት ፓርክ ከሚገኙ ሁለት መካነ እንስሳት ውስጥ አንዱ ሆኖ ኢትዮጵያን ሊወክሉ የሚችሉ የተለያየ ዝርያ ያላቸው እንሳስት ለእይታ የሚቀርቡበት ነው፡፡ ይህ ስፍራ የጥቁር መካነ እንስሳት ተብሎ የተሰየመው በሃገራችን ብቻ ከሚገኘው ባለጥቁር ጎፈር አንበሳ በመነሳ ነው፡፡ ይህ ባለጥቁር ጎፈር አንበሳ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ዴዴሳ እና አልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ በዋነኛነት የሚገኝ ነው፡፡ ይህ መካነ እንስሳት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገኙ እና የተለያየ ዝርያ ያላቸው እንስሳት መኖሪያ ሆኖ ለጎብኚዎች እይታ የሚቀርብበት ነው፡፡ ስፍራው በዋነኝነትም የጥቁር አንበሳ ማሳያ፤ የቀበሮ ማሳያ እና የውሃ ውስጥ ፍጡራን ማሳያ (አኳሪየም) አቅፎ ይገኛል፡፡ በዚህ መካነ እንስሳት ርዝመቱ 175 ሜትር የሚሆን ዋሻ ሚገኝ ሲሆን፤ ጎብኚዎች ውስጥ ለውስጥ በዋሻው በመንቀሳቀስ ለእይታ ተብለው በተዘጃጁ ሰፋፊ የመስታወት መስኮቶች ውስጥ የእንስሳቱን እንቅስቃሴ ይጎበኛሉ፡፡ በሌላ በኩል እንስሳቱ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሆኖ በተዘጋጀላቸው ሰፊ ስፍራ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም ይህ ስፍራ ለእንስሳቱ ማደሪያ፤ ምግብ ማቀነባበሪያ፤ እና የጎብኚዎች ማረፊያ ካፍቴሪያዎችን በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡