Unity Park-አንድነት ፓርክ
558 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወሎ ግንባር በነበረ ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

" በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦርነቱ የተሳተፉት እንነዚህ አካላት ኢትዮጵያውያን ያልሆኑና የኢትዮጵያውያን ዝርያ የሌላቸው #ነጮች እና #ጥቁሮች ናቸው ብለዋል ፤ በጦርነቱ ላይ ተሳትፈውም መስዋትነት መክፈላቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!
Unity Park-አንድነት ፓርክ
Video
Video : የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ዘምተው ሰራዊቱን እንደሚመሩ በይፋ ካሳወቁ በኃላ ዛሬ በቴሌቪዥን መስኮት ለህዝብ ታይተዋል።

እየመሩት ያለው ሰራዊት ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን አሳውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ለሚዲያ በሰጡት አጭር መግለጫ ካሳጊታ መያዙን ዛሬ ደግሞ ጭፍራ እንዲሁም ቡርቃ እንደሚያዙ ገልፀዋል። "ነገምይቀጥላል ትላልቅ ድሎች አሉ " ብለዋል።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፥ "የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆም ኢትዮጵያን ማየት ነው" ያሉ ሲሆን " የኢትዮጵያ ነጻነት አስኪረጋገጥ ወደ ኋላ ማለት የለም " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሞራል ከፍተኛ ነው ፤ ጠላት ከእኛ ጋር ለመፎካከር የሚያስችል ቁመና የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።
Happy Saturday 🌄