Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም /IMF/ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል የ411 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ድጋፍ አጽድቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ ኢትዮጵያ በዚህ ቫይረስ ምክንያት ተጋላጭ እና ታዳጊ የሆኑ ሀገራት የብድር ክፍያ እርፍታ እንዲያገኙ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 13 ቀን 2020 ያሳለፈው ውሳኔም ተጠቃሚ እንደምትሆንም አስታውቋል።

የተቋሙ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታኦ ዣንግ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚዋ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ሚና ለማሳደግ ከተቋሙ በወሰደቸው የገንዘብ ፈንድ መልካም ለውጥ ማሳየቷን ተናግረዋል። #FBC

@unitypark
በዓለም ለ131ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ የሚከበረውን የላብ አደሮች( የሠራተኞች ቀን) አስመልክቶ
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደረሰንን መልዕክት እንደሚከተለው አቅርበናል https://telegra.ph/ETH-05-01

@unitypark
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ!

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የእስካሁን አፈፃፀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እየገመገመ ነው፡፡

የኮሚቴውን ሪፖርት እያቀረቡ ያሉት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡

ይህም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር 133 አድርሶታል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ

@unitypark
DrLiaTadesse

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ▶️ከኬንያ የተመለሰና ▶️በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰባት (7) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ስድስት (66) ደርሷል።

@Unitypark
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የዓለም የሠራተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላለፉ

On May 1, 2020 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ እየተከበረ ያለውን የዓለም የሠራተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ምንጭ ፋና

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዶ-ር-ዐቢይ-የዓለም-የሠራተኞች-ቀንን-ም/
ኪም ጆንግ ኡን ሞተዋል ?

(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

አንድ የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጪ ኪም ጆንግ ኡን ስለመሞታቸው 99 በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናገሩ።

ከሰሜን ኮሪያ አምልጦ የወጣውና ጂ ሴኦን ሁ የተባለው ይህ የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጪ እንዳመለከቱት ኪም ጆንግ ኡን ስለመሞታቸው 99 በመቶ እርግጠኛ ነኝ በማለት መናገራቸውን የለንደኑ ሚረር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ጂ ሴኦን ሁ የተሰኙት እኚህ ሰው ለሚረር እንደተናገሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከአንድ ሳምንት በፊት እንደሞቱ የገለፁ ሲሆን የፒዮንግያንግ አምባገነኑ መሪ የመሞታቸውን ዜና በዚህ ሳምንት ታሳውቃለች ብለዋል፡፡

ግለሰቡ እንዳሉት ኪም ጆንግ ኡን የልብ ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሮኛል ብለዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የመሪዋን ሞት ለማረጋገጥ እንዲሁም ብሔራዊ የሀዘን ጊዜን ለማወጅ በዝግጅት ላይ ነች ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪን በመተካት የኪም እህት ቀጣዩን የመሪነት ስልጣን እንደሚቆጣጠሩ ግለሰቡ ተናግረዋል፡፡

@Unitypark
'ሞተዋል' እየተባለ ሲነገር የከረመው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በህዝባዊ መድረክ ላይ ታዩ!

(አሐዱ ቴሌቪዥን,KCNA,YONHAP)

የመሞታቸው ጉዳይ በርካቶችን ሲያጠራጥር የሰነበተው የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከ21 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ የሚታዩበትን ምስል የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስተላልፏል።

ኪም ጆንግ ኡን ከፒዮንግያንግ በስተሰሜን 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የተገነባው 'ሰንቾን የማዳበርያ ፋብሪካ' የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ሪቫን ሲቆርጡ ታይተዋል። በስነ ስርዓቱ ላይ እህታቸው ኪም ዮ ጆንግም ተገኝተው ነበር ተብሏል።

የ36 ዓመቱ መሪ የልብ ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ተከትሎ በጠና ታመዋል የተባለው መረጃ ሐሰት ነው ሲል የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንታዊ ጽሕፈት ቤት ማስተባበሉ ይታወሳል።

ወጣቱ መሪ ቀርተው የማያውቁበት የአያታቸው የልደት በዓልን አለመታደማቸው በጠና ታመዋል የሚለው መረጃ እንዲበረታ ማድረጉን ነው የቢቢሲ ዘገባ የጠቆመው።

በተመሳሳይ አገሪቱ ያደረገችው የሚሳኤል ሙከራ ላይ አለመገኘታቸው ሌላው የመታመማቸውን ጥርጣሬ ያበረታ ጉዳይ ነበር። ኪም ጆንግ ኡን ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ከ21 ቀናት በፊት የፖለቲካ ጉባኤን እየመሩ ነበር።

@unitypark
DrLiadTadesse

በሀገራችን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 2,016 የላቦራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች #አለመኖራቸው ተረጋግጧል፡፡

በሀገራችን ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች 69 ደርሷል።

በትላንትናው ዕለት ሶስት (3) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ዘጠኝ (69) ደርሷል።

@unitypark
Unity park youtube channel
Subscribe በማድረግ በቤትዎ ሆነው ይጎብኙን
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,758 ላቦራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ደርሷል።
#የሚያሸልሙ ትምህርታዊ 30 ጥያቄ አዘጋጅተናል!

ሰላም ለእናንተ ይሁን የ አንድነት ፓርክ ቤተሰቦች፣ በዛሬው እለት እስከ ነገ ማታ 1 ሰአት የሚቆይ የሚያሸልሙ ጥያቄዎች በኢንተርናሽናል ቋንቋ በ ኢንግሊዘኛ(Engilsh language) ተዘጋጀቶ ወደ እናንተ ይቀርባል፣ ጥያቄዎቹ እናንተን ያማከሉ (general knowledge, sport, science, logic) ያካተቱ ናቸው፣ እርሶም ተወዳድረው ሽልማቶን የውሰዱ። @unitypark
ሽልማቱ!

ተወዳዳሪዎች ካስመዘገቡት ውጤት ውስጥ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡትን 3 ተወዳዳሪዎች፣ በቤትዎ ይቆዩ ጥቅል የምንሸልም መሆኑን እናሳውቃለን።
አቅጣጫ!

Start this quiz ሚለውን ይጫኑ ና፣
ወደ quiz bot ያምሩ፣
/start ይበሉት፣
I'm ready ይንኩ ጨዋታው ይቀጥላል ።
🎲 Quiz 'Educational questions'
🖊 30 questions · 30 sec