Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
በፓርካችን ዙፋን ቤት (ዋና ሙዚየም)የሚገኙ የነገስታት ዘውዶችን መጥተው ይጎብኙ።
Come and visit the Royal Crowns in the Unity Park's main museum (Throne House).

@UnityPark
ከአንድነት ቤተሰብ የተላኩ ጥያቄዎች

-how can I buy the ticket 🎫?

-መግብያ ለተማሪ ስንት ነው?

Answer 1፣ You can buy tickets from the official website of the park www.unitypark.et or you can purchase tickets at the gate.

መልስ 2፣ እስካሁን ለተማሪ ተብሎ ተመን የወጣለት ዋጋ የለም፣መንኛውም ኢትዮጲያዊ እድሜው ከ3 ዓመት በላይ የሆነ 200ብር መክፈል ይጠበቅበታል

ጥያቄ ካለዎት @Unityparkbot መጠቀም ይችላሉ።

If you have any question regarding our park you can use👉 @unityparkbot

@UnityPark
ከአንድነት ቤተሰብ የተላከ ጥያቄ

Where is unity park?
-Its located inside Arat kilo palace.

ለመደበኛ ሞባይል ካሜራ ይፈቀዳል?
-ሞባይል ዪዞ መግባት ይቻላል።

@UnityPark
ሶማሊያዊያን የአንበጣውን መንጋ ለምግብነት በማዋል እየተዋጉት ነው

በሃገራችን የአንበጣውን መንጋን ከፍተኛ ድምጽ በማውጣት ነበር ህዝቡ ከአካባቢው ሲያባረው የቆየው።

የጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ዜጎች ግን መፍትሄ ያሉትን ሌላ መላ ዘይደዋል። ይህም፤ የአንበጣ መንጋውን መያዝ፣ በውሃ መዘፍዘፍ፣ አጠንፍፎ በዘይት ጠብሶ መመገብ ተያዪዘውታል። ሲል BBC Amharic ዘግቦታል።


@UnityPark
Have a beautiful Sunday fams 🌼
የተለያዩ መረጃዎች በየ ሴኮንዱ በዙሪያችን ይፈሳሉ። እናንተ መረጃዎችን እንዴት አጥርታችሁ ወደራሳችሁ ታስገባላችሁ? የመረጃን ተዓማኒነት በምን ትፈትሻላችሁ?

@UnityPark
ሳተላይት ETRSS-1 ለምን አገልግሎት መዋል እንደምትችል በዋናነት የሚወስነው የምትሰራበት የፀኃይ ጨረር ክፍል (ባንድዊድዝ) ይሆናል። ጠንካራው የጨረር ክፍል ላይ ሳተላይቷ በቀላሉ ጉልበትን መመዝገብ ትችላላች። ነገር ግን ደካማ በሆነው የጨረር ክፍል ላይ በቂ ተንፀባራቂ ጉልበት ስለማይኖር ከመሬት የሚነሳ ሞገድ በሳተላይታ መመዝገብ ይችላል። ሆኖም ይህ የሚሆነው ሳተላይቷ በነኚህ የፀኃይ ጨረር ክፍሎች ላይ ባንድዊድዝ ሲኖራት ነው። ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሰዕል በደንብ አጥኑት። እንጦጦ አካባቢ የምትሰሩ ካላችሁ መረጃ ብትነግሩን በደንብ ማብራራት እንችል ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው መረጃ የለም።

ሁለገብ የትምህርት መረብ

@UnityPark
ሩዋንዳ ሁለት ተከታታይ የኢትዮጵያ ድራማዎችን በትርጉም በቴሌቪዥን ማሳየት ልትጀምር ነው!

ታዲያስ አዲስ እንደገለጸው በሩዋንዳ የሚገኘው የሀገሪቷ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ RTV ሁለት የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ድራማዎችን በትርጉም ለማስተላለፍ ከድራማው ባለቤቶች ጋር መስማማቱ ነው የተነገረው፡፡ እነዚህ ሁለት ድራማዎች 'ሰው ለሰው' እና 'ዘመን' መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡ ይህም የዘርፉን ኢንደስትሪ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ነው ተብሎለታል፡፡

ምንጭ ቲክቫህ ልዩ ልዩ

@UnityPark
የከፊል የጸሃይ ግርዶሽ በመላው ኢትዮጵያ
————————————
ሃሙስ ታህሳስ 16 2012 ዓ/ም
ከጠዋቱ 12:37 እስከ 1:26
**********
ማስጠንቀቂያ
ወደ ጸሃይ ያለ መከላከያ ፊልተር እንዳይመለከቱ

ምንጭ: Ethiopian Space Science Society

@UnityPark
መጪውን የከፊል የጸሃይ ግርዶሽን ለመከታተል ይህን ቀላል ፒን ሆል ካሜራ በመኖሪያ ቤታችን በሚገኙ ቁሳቁሶች መስራት ይቻላል
—————————————————————-
In order to view the upcoming partial solar eclipse, we can construct a pin hole camera with materials that are easily available at home
——————————————————————
https://www.youtube.com/watch?v=PMPBWLSYKaw

@UnityPark
አስኮ አዲስ ሰፈር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መምህራን በአንድነት ፓርክ።

@UnityPark
U.S. Ambassador Mike and his family at Unity Park, Addis Ababa , Ethiopia

@UnityPark
School of Tomorrow Students and Teachers at Unity Park .

@UnityPark
የመጀመሪያውን የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት በአንድነት ፓርክ ‘ህልሜ ለሀገሬ’ በሚል ርዕስ አሰናድተናል። ቶሞካ ቡናን ፉት እያሉ ኢትዮ ጃዝን ያጣጥሙ።
በነገው ዕለት ከሰአት በኋላ በአንድነት ፓርክ "ህልሜ ለሃገሬ " በሚል ርዕስ የዝነኛው ኢትዮ ጃዝ ባንድ አባላት ጎብኚዎቻችንን በሙዚቃ ያዝናናሉ። በዝግጀቱም አበጋዝ ሺዎታ ክብረወረቅ ፣ ሄኖክ ተመስገን ፣ግሩም መዝሙር ፣አሸናፊ አሊ እና ያሬድ ተፈራ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ጎብኚዎቻችን ከትኬት ክፍያ ውጪ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ይህንን የመዝናኛ ዝግጅት መታደም ይችላሉ።
Happening tomorrow afternoon at Unity Park with the Theme "My dream for my country", members of the famous Ethio Jazz band, Abegaz Shiota Kibrework, Henok Temesgen, Girum Mezmur, Ashenafi Ali and Yared Tefera will present their works to the park visitors.
Visitors can enjoy this entertainment without any extra payment other than entrance fee.
Buy your tickets now at www.unitypark.et
''ጠጥታችሁ አታሽከርክሩ" ያሉት ፖለቲከኛ ጠጥተው ሲያሸከረክሩ ተጋጩ

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ አምደኛ በሆኑበት ጋዜጣ ላይ ሰዎች ጠጥተው እንዳያሽከረክሩ ከጻፉ በኋላ፤ ጠጥተው ሲያሽከርክሩ ተይዘዋል። ብራይንል ኮለበ የተባሉት ሪፐብሊካን በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ ተጋጭተዋል ብሏል ፖሊስ።

ይህ ከመሆኑ ከአንድ ሳምንት በፊት ፖለቲከኛው ብራይን፤ በጋዜጣ ላይ ባሳተሙት ጽሁፍ ሰዎች በምንም አይነት ጠጥተው ማሽከርከር እንደሌለባቸው ጽፈው ነበር። ከአንድ ሳምንት በኋላ እርሳቸው ጠጥተው ሲያሸከረክሩ ከግዑዝ ነገር ጋር ተጋጭተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የ67 ዓመቱ ፖለቲከኛ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በሰጡት ቃል "እጅግ በጣም ይቅርታ'' ብለዋል። "ማክሰኞ ምሽት ለተፈጸመው ነገር ምንም አይነት ማስተባበያ እና ምክንያት ላቀርብ አልችልም። የወሰደኩት እርምጃ ስህተት ነው። ለዚህም በጣም ተጸጽቻለሁ" ብለዋል ፖለቲከኛው። ፖሊስ እንዳለው ፖለቲከኛው መንግሥት የሰጣቸውን መኪና ከውሃ ማስወገጃ ቱቦ ጋር አጋጭተዋል። ፖለቲከኛው አደጋው በደረሰበት ወቅት እና ፖሊስ ጣቢያ ከደረሱ በኋላ የተደረገላቸውን የአልኮል ምርመራ ማለፍ አልቻሉም። ብራይን ኮለብ ሪፐብሊካኖችን ወክለው ከሚያደርጉትን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ራሳቸውን እንዲያገሉ በተለያዩ አካላት እየተጠየቁ ነው።


@UnityPark
በዛሬው ዕለት ከሰአት በኋላ በአንድነት ፓርክ "ህልሜ ለሃገሬ " በሚል ርዕስ የዝነኛው ኢትዮ ጃዝ ባንድ አባላት ጎብኚዎቻችንን በሙዚቃ ያዝናናሉ። በዝግጀቱም አበጋዝ ሺዎታ ክብረወረቅ ፣ ሄኖክ ተመስገን ፣ግሩም መዝሙር ፣አሸናፊ አሊ እና ያሬድ ተፈራ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ጎብኚዎቻችን ከትኬት ክፍያ ውጪ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ይህንን የመዝናኛ ዝግጅት መታደም ይችላሉ።