Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
1.04K subscribers
865 photos
42 videos
99 files
49 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
ሰላም የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለቀዳም ስዑር በሰላም አደረሳችሁ እያልን የኆኅተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ነዳያንን ለማስፈሰግ ሲባል ሳምንቱን በሙሉ ውድ ኦርቶዶክሳውያንን ባላቸው ከበረከቱ እንዲክፈሉ ቅስቀሳ ሲደረግ ቆይቷል ፤ ዛሬ ላይ ደግሞ ለነገ የታሰበው በጎ ተግባር እንዲሳካልን እኛ የግቢ ጉባኤ ወንድም እህቶች መጥተን ማገዝ የምንችል ከበረከቱ እንድንካፈል በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
            — ዕብራውያን 13፥7 -


ውድ የግቢ  ጉባኤያችን አባላቶች  እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳቹ።

በግቢ ጉባኤያችን ዛሬ የክርስቶስን ትንሳኤ እያከበርን  በክርስቶስ ደም የተዋጀችዋን  የግቢ ጉባኤያችንንም ምስረታ የምናስብበት ዕለት ነው።ምንም እንኳን እንደቀድሞ  በዛሬዋ ዕለት  ሚያዚያ 27 ጉባኤ ዘርግተን እንዳስለመድነው ትልቁን ቤተሰባችንን ሰብስበን ያለፈውን ትውስታችን መነጋገር መመካከር ባንችልም ይህን መርኃግብራችን  ለግንቦት 25/2016 ዓ.ም ከወዲሁ  ቀጠሮ አስያዝናቹ።

ግቢ ጉባኤያችሁ እናታችሁ እናንተን  ልጆቿን ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅቷን ጀምራለች። እናንተም እናታችሁ በጠራቻችሁ ቀን ተሰባስባችሁ እደጇ ትገኙ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።


መልካም በዓል
Forwarded from Emun sebe Aman
"ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው። ይህን ያህል ትዕግሥት እንደ ምን ያለ ትዕግስት ነው።
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው። ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው።
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው። ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው።
በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት።
አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ በአዳም ፊት የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ።

የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው፤ ምን ከንፈር ነው፤ ምን አንደበት ነው።
የፍቅር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ኅሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል።
የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ።" ቅድስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤" ሮሜ.6:5
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን(ለሁላችንም) የትንሤኤ ቀን በሠላም አደረሳችሁ!!!
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች።

ማስታወቂያ 📢

እንኳን ለማዕዶት በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዐቢይ ጾም ወቅት ተጀምሮ በነበረው የወረብ ጥናት ላይ ተሳታፊ የነበርን እንዲሁም በጥናቱ ላይ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ጥናቱ ስለሚቀጥል በተሰጠው ቀን እና ሰዓት እየተገኘን እንድናጠና ለማሳሰብ ወደድን።

የጥናት ቀናት እና ሰዓታቸው…

• ማክሰኞ — 6:00 ሰዓት ጀምሮ
• ሐሙስ — 7:30 ሰዓት ጀምሮ እና
• ቅዳሜ — 8:30 ሰዓት ጀምሮ ጥናቱ የሚኖር ይሆናል።

የቅዱስ ያሬድ ረድኤት ከረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ