ፅኑ ጥበብ
161 subscribers
18 photos
3 files
2 links
👉ይህ ቻናል የተለያዩ የጥበብ ስራዎች የሚቀርብበት ሲሆን ለእርሶ ግጥምን 👌፣አጫጭር አስተማሪና አዝናኝ ፅሁፎችን📝 እና ልብ ወለዶችን የያዘ፣እንዲሁም አሪፍ መፅሃፍቶች📂 የሚለቀቁበት፤ ጥሩ ስብዕናን👈 መፍጠር እና መገንባት👈 የሚፈልግ ቻናል ነው!!!

ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን!!🙏🙏🙏

ለአስተያየት @Yafet212
Download Telegram
.
.


አብዛኛውን ጊዜ ሕይወት የባለቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች።የቆራጥነትና የወሳኝነት ትርጉም የሚገባህ፥ውጤቱን ካየህ ቡሃላ ነው።



( ሰመመን)
ሲሳይ ንጉሡ
3
.
.
.

እመጣለሁ ብለሽ.....?? 

ቀናቶች ተዋልደው አመታት ፈጠሩ 
አመታት በርክተው ዘመን አስቆጠሩ
እኔም ያች እስረኛ የቃልሽ ጠባቂ 
የመምጫሽን ወራት ቁጭ ብዬ ሰናቂ
ለሰው ቢያስመስለኝ የፍቅር አዋቂ 
   
ታዲያ ምን ነክቶሽ ነው...??

ወደኔ ለመምጣት ምን አሰናከለሽ
አልቆይም መጣለሁ ነበርኮ መልስሽ
እሾህና ድንጋይ የመንገዱ እንቅፋት
እውነት እሱ ይሆን ላትደርስ የገታት 
በማለት አልሁኝ ስደረድር ምክንያት
በቅዠት የዋዠቅሁ አንችን ላለማጣት  

እናማ አለሜ....
 
በስውር አለም ውስጥ አንችን እየሰፋሁ
ካስቀመጥሽኝ ቦታ መኖሬን አሰፋሁ
ካንች ወዲያ ለኔ ሴትም እርም አልኩና
በፍቅርሽ እረመጥ እንደገባሁ ዋና
ልቤን ስሸነግል ትመጣለች እያልሁ  
በቃሎችሽ እዳ እስከ ዛሬም አልሁ 

እውነት እልሻለሁ...!!

ትግስት የተሳነኝ ወንድ ልጅ አልመስልም
ብትመጭ ይሻላል ከቀረሽ አልድንም..!!
ቃልሽን አምኜው እመጣለሁ ብለሽ..
ከቀጠሮው ቦታ ምነው ለምን ቀረሽ..?? 

እመጣለሁ ብለሽ....!!🤣🤣



ማዕረግ ፀደቀ
13/09/2018 ዓ.ም
6👏2🕊1
.
.
.
.


የምቾት ችግሩ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስን አለመፍቀዱ ፣ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች መውረድን አለመፈለጉ ነው። ምቾት ጥሩ ቢሆንም ከደረጃ ላለመውረድ የሚያስከትለው ትግል በራሱ ጭንቀት ፈጥሮ ቆይቶ ምቾትን መልሶ መንሳቱ አይቀርም ። በምቾት ውስጥ ምቾት የለም !!

.
.
.

( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ


ሠናይ ምሽት ተመኘሁላችሁ!!🙏🙏
❤‍🔥4👍2🔥1
.
.
   
ሁሌም ቢሆን ራሳችንን በሰዎች ውስጥ ከማግኘት ይልቅ በራሳችን ውስጥ ማንነታችንን ፈልጎ ማግኘት ጥንካሬና ቆራጥነትን ይጠይቃል። በሰዎች ላይ መደገፍ ዘመን የሚያሻግር ቢሆን ኖሮ ራሳችንን ፈልገን ማግኘት ባልቻልን ነበር !!

    

                         

  Magi Quotes
👏43👍1
.
.
.

ነበር..........!!!!!!

አንዳንዴ ነበር ተብሎ የሚቀር ህይወት ባይኖረን ብላችሁ አስባችሁ አታውቁም....???? በተለይ ደግሞ  በደስታ ያሳለፋችኋቸውን ጊዜያቶች ፣ በስኬት የተራመዳችሁባቸውን ቅፅበታቶች፣ በፍቅር የፈካችሁባቸውን ቀናቶች፣ ከምትወዷቸው ቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁ ጋር በሀሴት የኖራችሁባቸውን ዕለታቶች ስታስታውሷቸው ነበርርር....ማለት ነበር በራሱ  አሳልፎ ለትዝታ ይሰጠናል። 

       ትላንትም ነበር እንደተባለው ዛሬም ነገ ላይ ነበርርር ሊባል ነው።በቃ ህይወት እንዲህ ዘርፈ ብዙ ናት ።ትላንትን ሽራ፣ ዛሬን አባራ ነገን ትሰጣለች።በዛው ልክ ደግሞ  መጥፎ ቀናቶችን ነበር ማለት ባንችል ኖሮ ዛሬም መጥፎ ህይወት ውስጥ እንሆን ነበር።እናም ደጉን ላለማጣት ስንል ነበር ባይኖር ማለት በራሱ  ስቃያትን አሳልፈንና አሸንፈን ነበር  እንዳንል ያደርገናል። ክፉ ቀናትን ሳስብ እንኳንም ነበር ኖረ እላለሁ።
ምክንያቱም እሱ ባይኖር ዛሬም ያን ስቃይ ላናሳልፈው እንችል ነበር።በቃ ነበርር.....


ማዕረግ ፀደቀ

ግንቦት ~18/2018 ዓ.ም
BDU
16🥰3👏1🕊1
ጊዜ .......!!


    ሲበዛ ቴንሽናም ነኝ። ማለቴ ትንሹም ትልቁም ጉዳይ እስካልተሳካልኝ ድረስ እረፍት የማይሰማኝ ሰው ከመሆኔ የተነሳ  እስካሳካው ብቻ ሳይሆን ተሳካም አልተሳካም መጨረሻውን እስካየው ድረስ አያስችለኝም።በተለይ ደግሞ ወጣትነቴን ሳስብ ማድረግ እየፈለግሁ ሳላሳካው የማልፈው ነገር እንዳይኖር መሞከር ያለብኝን ነገር አጋጣሚዎችን ተጠቅሜ እሞክራለሁ።  

    ስጣደፍና እዛም እዛም ስል የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ  << ውይ... አንች መቼ ነው የምታርፊው..?? በቃ ሁሉ አይቅረኝ ነሽ ..!!>>ይሉኛል። በእርግጥ ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ደግሞ ይህን ንግግራቸው እንደ ጥሩ ምክር ከተቀበልኩ ቡሃላም አላርፍም።እንዲያውም ጊዜ እንዳያመልጠኝ ማስተዋል በተሞላው ጥድፊያ ይበልጥ እጠመዳለሁ። ምክንያቱም ዛሬ ያልገነባሁት ማንነት ነገ ላይ ከየትም ላመጣው ስለማይችል። በወጣትነቴ ያልሰራሁት መሻቴ በእርጅናዬ ወራት ላሳካው የማልችልበት ሰፊ አጋጣሚዎች ስለሚኖሩ፣ በመስሪያዬና በመለወጫዬ ጊዜ ተዝናንቼ በጡረታ ዕድሜ ውስጥ ማረፍ ሲገባኝ በስራና በጥድፊያ ማሳለፍ ስለማልፈልግ ዛሬዬን በተቻለኝ አቅም ለመጠቀም እጥራለሁ።ለዛም ነው የሚያውቁኝ ሰዎች ሁሉ እንደዛ የሚሉኝ። 

    ለማንኛውም ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ጊዜ ሰይፍ ነው ፣ይገድላልም ያድናልም፣ ጊዜ ፈራጅ ነው፣ጊዜ ካመለጠ ታክሲ አይደለም ፤ቆሞ አይጠብቅም እንደሚሉ ሁሉ የጊዜን ተመን አውቀን መውደቅን እና አለመሳካትን ሳንፈራ መሞከርና ማድረግ ያለብንን ነገር ቀን ሳንቀጥር ዛሬውኑ ሳይረፍድ ፍርሃትን እና ይሉኝታን አሶግደን በቁርጠኝነት ተነስተን በጊዜው መሞከር እንድንጀምር ነው።  


    ሠናይ ቀን ተመኘሁላችሁ..!!🙏🙏

                     Magi syctalk
6👍4
.
.
.

ባህር ዳር........!!!!


ስፈራ ስቸር 
ካንቺ ላለመለየት
         ፍቅርሽ ገመድ ሆነና ፤
እንቡጥ አይኖቼ 
እንባ አመነጩ
       ልሰናበትሽ ቀን ደረሰና ።

የገነት ምንጯ
ለምለም ዘንባባ
         አንቺ የጣና ፈርጥ ፤
እንቁ ፅጌ ሬዳዋ
አርማ ሰማያዊዋ
ታደልኩ ካንች ስሸጎጥ።       

በጣና ስፋት
ፍቅር የሞላሽ
       እንዲሁ መውደድ የተቸረሽ ፤
አንችን አግኝቶ 
ደግሞስ የማይናፍቅሽ
     ውቢት የለም ማይመኝሽ ።

ውቢት አትገረሚ
በእኔ መወደድሽን 
            ማርኮኝ ደጅሽ ብጠና ፤
የጣናው ውሃሽ
  ጥሜን ቆርጦልኝ እንጂ
              በጥበብ ጓዳሽ ዋና።

ጋትሽኝ ከምንጭሽ 
ጨልፈሽ በፍኝሽ
ስስት አታውቂም እና ፤
ካንቺ ባህር ዳር
የናፍቆት ዕፁ  
    ከሩቅ ይጣራል ጣና..!!!



ማዕረግ ፀደቀ
9👏4👍2🙏1🕊1
.
.
. 🥹🥹🥹🥹🥹🥹

ቀን እየቆጠርሽ
ጠፍተሽ ብቅታሽ
        ለእኔነቴ ቅኔ ቢሆንም ፤
በትዝታም ውስጥ
መረሳት አለ
       በመመላለስ ፍቅር አይሆንም


ማዕረግ ፀደቀ
👍54💯1
ብርቅርቅታ # ተርጓሚ አብይ ደምሴ (2).pdf
3.1 MB
እነሆ ለአንባቢያን የቀረበ 📗📕📒

የምትፈልጓቸውን መፅሃፎች በ @Yafet212 ይፃፉልን እንለቃለን!!
👍2🙏2💯1
እንደመደበርም እንደመሰልቸትም አድርጎኝ ነበረ።  ለመኖር ምክንያት አጣሁ ማለት ጀምሬ ነበረ።

እነዚህ ትናንሽ ሀሳቦች ቀኔን መረበሽ ጀመሩ ። ጠዋት መነሳትና ድጋሜ ሌላ ተመሳሳይ አድካሚ ቀን መዋል ትርጉሙ አልታይሽ ብሎኝ ነበረ።

ከዛ ግን ቀልቤን ገዛሁ የእናቴን እጅ አየሁት። ቆዳዋ ተሸብሽቦ ደምስሮቿ በጉልህ ይታዩ ነበረ። ደነገጥኩ ያ እንደዛ የሚያሳሱ ቀያይ እጆቿ አሁን መዳፎቿ ሳይቀሩ ጠቋቁረዋል።

ውሎዋን አየሁት እንደነገሩ ነው የምትለብሰው ያ ሁሉ መሸቀርቀር የት እንደ ሄደ ግራ ገባኝ። ፈጥና ያረጀችም መሰለኝ።

ከዛ ድግስ ተጠርተን ዘመድ ቤት ስንሄድ በእያንዳንዱ ነገር ላይ የምትሰጠውን የሰላ ሂስ ሰማሁ።

እቤት ስንገባ ጠየኳት ለምን ስራሽን ተውሽው እስካሁን በጣም ምርጥ ጭንቅላት አለሽ እኮ አልኳት በቁጭት

"ኤድያ ተይው ባክሽ ሁሉም ነገር ከቤተሰቤ አይበልጥብኝም" አለች

"እስኪ ተመልከቺ እንዴት ትናንሽ እንደነበራችሁ "በእጇ ህፃን ሆነን እኔና እህቴ የተነሳነውን ፎቶ ይዛ

"አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለኔ ከምንም ነገር በላይ ነው" አለቺኝ በፈገግታ።

እንዴት እንደሆነ ባላውቅም መሰልቸቱ መደበሩ ቀርቶ ጭራሽ አዲስ ጉልበት ይሰማኝ ጀመረ።

ስለእሷ ማሰብ ከአልጋዬ ተስፈንጥሮ ለመነሳት በቂ ነበረ። እሷ መኖር ያቆመችው ለኔ ስትል አልነበር ስለዚህ እኔም የምልፈሰፈስበት ምክንያት አልነበረኝም።
ለኔ ማማር የሷ መጎሳቆል ይበልጥ አጠነከረኝ። በደንብ በኔ እስክትኮራ ድረስ...



copy
❤‍🔥4🥰31😭1
🛑 If you can keep your mind clearly focused on what you want, and refrain from thinking about what you don’t want, you will attract everything you need to achieve your goals, exactly when you are ready. Change your thinking and you change your life.


( Brian Tracy )
4👍3
❤️❤️❤️ተገናኘን...!!❤️❤️❤️
🌟🌟🌟☀️☀️🌟


ቀናቶች ለጉድ ሲነጉዱ
እኔና አንች ተገናኝተን
ሳናወጋ የልባችንን፤
በምቅ ናፍቆት ሰቆቃ
ዛሬ ነገን እየቆጠርን
ብንቆይም ለብቻችን፤
ይኸው መጣሽ አደዬ
ይኸው መጣሁ አዳምሽ
መች አስችሎን እንቀራለን፤
በእግዜር አምሳል ቸርነት
በሱ ጥበብ ጉብኝት
ላንለያይ ተዋህደን፤
እልፍ እንቅፋት ተግዳሮት
ማያሳልፍ የእሾህ አጥር
ቢነጠፍም አሜኬላ፤
ይኸው ዛሬ ተገናኘን
መንገዳችን ተጠረገ
💞 የልባችን ዛሬ ሞላ ።



ማዕረግ ፀደቀ
12💘2🕊1
.
.
.


እድሜ ጊዜ ነው።ሰው ሞተ የሚባለው እኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም ዕድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም ? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከዕድሜህ እየቀነሰብህ ነው።የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታ ጊዜ ነው። እንዴት? የሰጥኸው ጊዜ ከዕድሜህ ላይ የቀነስከው ነውና!




( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ
5👍3
.
.
. ..........!!!

መለያየት ፈራን ፥ መራራቅ አስነባን 
  ወኔ አጣ ልባችን ፣
በኛ አላምር አለ ፥ መጨከን አቃተን
  አሰረን እንባችን ።

ብቸኝነት ለምዶ ፥ መውደዱንም ክዶ 
    መኖሩ ላይፀና ፣
ሰዉ እንዴት ይለያይ ፥ በፍቅር የኖረ 
   በህይወት ፈተና ።

ልባችን የራ'ራ ፥ አይናችን በለቅሶ
እንባ የጨቀየ ፣
መለየት ምን ትርጉም ፥ ማቀድ ስንብትን
ፍቅርንም ያየ !



ማዕረግ ፀደቀ
12👍3💯1
🛑If you think about success and confidence, you will feel strong and competent, and you will perform better at whatever you attempt.

🛑  If you think about making mistakes or being embarrassed, you will perform poorly, no matter how good you really are. Pictures and image
.


(Brian Tracy )
👍31
ማጣት የማይሰብራት፤ማግኘት የማያንጠባርራት፤ ስልጣኔ ያልቀየራት፤
ጥበብ ያልጋረዳት፣ለህልሟ የምትቃትት ለምስኪን ቤተሰቧ እና ህዝቧ የምትኖር፣እሷ ዕንቁ ሴት ናት።

አንዲት ቀንም ከአይኖቿ ላይ የእንባ ዘለላ ከሰው ፊት ጠብ አድርጋ አታውቅም። ከፊቷም ላይ ውብ ፈገግታ አይጠፋም።መከፋቷን በከንፈሮቿ ደብቃ በምትኩ እንደ ጨረቃ በነጡት ጥርሶቿ ሳቅና ደስታን ታበስራለች።

የሰው ይሉኝታና ትችት ከመንገዷ አያስቀራትም። ፍፁም ፍርሃት አታውቅም።ማንነቷንም ከራሷ ጋር እንጅ ከሌሎች ጋር አታወዳድርም።

ተስፋ መቁረጥ ለሷ የሞት ያህል ነው።በችግሮቿ አትሰበርም።በርትታ ታበረታለች፤ስቃ ታስቃለች።የፈዘዘን ታነቃለች።

እጇም ንፋግነትን አያውቅም።ችግረኛ ያሳዝናታል። ልትጎርስ የቆረሰቻትንም ቢሆን ለተራበ ታጎርሳለች። ምን አለፋችሁ ሴት አይደለች የእናትነትን ምስጢር ታድላለች።

ውድቀቷ የስኬት መጀመሪያዋ እንደሆነ ታምናለች።እሷ ስኬታማ አለመሆን አትችልም። ምክንያቱም ፍርሃትን የምታሻፍር ፣ውድቀቷን የምትቀበል ፣ችግሮቿን የምትጋፈጥ፣ ከነገሮች የምትማር፣ በፈተናዎች የምትፀና ፣ሃላፊነት የሚሰማት ሴት የስኬት ሚስጢሯ ይህ ነው።


       👉አንተን ነው..

ለዛች ስኬታማ 👩ሴት ላክላት


               ማዕረግ ፀደቀ
7👍1🕊1