ክርር ባለ እውነታዋ ..
<< አዎና የእኔ ልጅ ለምን ተቸግረህ እንደሁ ባላውቅም እስካሁንም አለማግባትህ ይከነክነኛል። እድሜ እንደሁ መላ የለውም ቁጥር ብቻ ነው።ይሊቁንስ ስምህን ማስጠሪያ ለማፍራት ብታገባ ደስታዬ ነው።እኛ እንደሆንን ለአንተ ለበኩር ልጃችን አናንስም።ምን አለኝ..!! ወንድ ነኝ ..!! ገንዘብ ላፍራ ብለህ ከሆነ የምታስበው የዕድሜ ዘለላዎችህን በከንቱ እያሳነስካቸው ነው።የገንዘብ ረድኤት በመስራት ብቻ ሳይሆን ዋናው አያያዙ ነው ።ልጄ በቂ ገንዘብ የምታገኝበት ስራ አለህ ።እስከመቼስ የማይደረስበትንና የማያልቀውን ነገን ትጠብቃለህ። >> አለችው ።
የእናቱ አነጋገር የእግሩን እሾህ አፍረጥርጣ ያወጣችለት ያህል እረፍት እና ሀሴት ተሰማውና ወደ ኋላ ተመልሶ እንጋባ እያለች ለሶስት አመት ስትጨቀጭቀው የነበረችውን ፍቅረኛውን ማስታወስ ጀመረ። እውነትም ፍቅረኛው እንጋባ እያለች መለመን የጀመረችው በፍቅር መኖር ከጀመሩ ከሁለተኛው አመት ጀምሮ ነበር። እሱም...
<< ቆይ.. የዛሬ አመት ቆይ... የዛሬ ሁለት አመት ጠብቂኝ እስከዛ ማሟላት ያለብኝን ነገር ላሟላ ካልሆነ ግን መጣደፍ አልፈልግም መታገስ ካቃተሽ የራስሽ ጉዳይ..>>
ብሏት ስለነበር ፍቅራቸው ጋዝ እንዳለቀበት ኩራዝ ደብዝዞ ነበር። እሷም መጨቃጨቋ የሴትነት ጊዜዋ አሳስቧት ብቻ ሳይሆን ከቤተሰብ ራስ ላይ ወርዳ በራሷ እግር ቆማ የምትራመድበትን እንዲሁም ቤተሰብ የምትመሰርትበትን ማዕልት ከመናፈቋም የተነሳ ነበር።
በዚህ መካከልም ፍቅራቸው እየቀዘቀዘ ልባቸውም እየሻከረ ሲመጣ እንደ ቀድሟቸው እርስ በእርሳቸው መናበባቸውም ቀነሰ።እሱም ይስራ እንጅ እንደ ውሃ ገንዘቡን ለረባውም ላረባውም መርጨት ጀመረ።አስተሳሰቡም እየላላ << ገና ልጅ ነኝ ምን አቻኮለኝ ትዳር እንደሁ እስር ቤት ነው >>ማለት ጀመረ።
ፍቅረኛውም የሚሰጣት ምላሽ እንደ ኮሶ ስለመረራት መቆጣጠሯን ችላ ብላውም ስለነበር ለዛ ነው የባህሪው መቀያየር ለአባቱ ጎልቶ የታየው። በስተ መጨረሻም እናቱ ምንም እንኳን ትዳር ይዞ ከቤቷ በቀን አስር ጊዜ አለማየቷን ስታስበው ቢያስጨንቃትም ትዳር ለወንድ ልጅ ሰብሳቢ መሆኑን ስለምታምንበት ነበር እንደ ቀልድ ሹክ ያለችው።
እሱም ፊቱ በደስታ ወዝ እየጨቀየ ፍቅረኛ እንደ ነበረችው እንጋባ ስትለው አሁን አላገባሽም በቂ ሃብት እስኪኖረኝ ታገሽ ብሏት እንደተደባበሩም ሁሉንም ነገር ለእናቱ ነግሯት እናቱም ይህን ማለቱ ስህተት እንደሆነ ከነገረችው ቡሃላ ፍቅረኛውን ይቅርታ ጠይቋት እንደሚያገባትና ለቤተሰቦቿ ሽማግሌ ሊልክ ማሰቡንም እንዲነግራት አሳሰበችው።
ከዛም እንደ ባህር ውሃ ያስፈራው የነበረው ትዳር በእናቱ ተወዶ በመገኘቱ ይህን ዜና ለፍቅረኛው ሊያበስራት ተቻኮለ። ከዛም እስከ ዛሬ ላላት ነገር ሁሉ ይቅርታ ጠይቋት ሊያገባት ማሰቡን ነገራት።እሷም የዘወትር ጥያቄዋ እልባት ስላገኘላት በሀሴት ተቀበለችው።ከዛም ሽማግሌ ተልኮ ድል ተብሎ ተደግሶላቸው ጉልቻቸውን ጀመሩ።
ከእሷ ጋር መኖር ከጀመረ ቡኋላ መጠጣቱን፣ብኩንነቱን እና ማምሸቱን ተወ።በአስተሳሰቡም እየበሰለ መጣ።ራሱን ጥንቅቅ አድርጎ ማኖር ሲጀምርም ከአባቱ ጋር መናቆሩ ቀረ።እንዲያውም ትዳር መያዙ እያስወደደው እና እያስከበረው መጣ። እናቱም በልጇ ህይወት ተደሰተች።ሃሳቡ ቀረላት።አደራዋንም ለልጇ ሚስት አስረከበች።
እሱም በሰአቱ ስራውን ሰርቶ ለቤታቸው ደግሞ የሚያስፈልገውን ነገር አሟልቶ ባለቤቱንም ማስደሰት ጀመረ።እሷም እጅግ ትሁትና ጠንቃቃ ሚስት ስለነበረች ትዳራቸውን ለማቅናት ድካም እንዳይሰማው ዘወትር ታበረታዋለች።ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት በስርአት ቁርሱን አብልታ፣ የስራ የደምብ ልብሱን ና ከረባቱን እንደ ህፃን ልጅ አስተካክላ አልብሳና አሱባ በደስታ ትልከዋለች።ከመመለሱ በፊትም ቤቷን አፀዳድታ ምግቧን ሰርታና ቡናዋን አፍልታ በገጉት ስትጠባበቅ ቆይታ ሲመጣ በፍቅር ተቀብላ ታስተናግደዋለች።በስራው ኪሳራ ሲደርስበት ሁል ጊዜም ጠንካራና ስኬታማ እንደሆነ ትነግረዋለች።ምን አለፋችሁ በአይኖቿ አይታ ስሜቱን አንብባ ሃዘን መከፋቱን ፥ማግኘት ማጣቱን የምትረዳው እናም የምታጀግነው እንቁ ሚስት ሆነችለት።
እሱም በሚስቱ መበረታታቱ ይበልጥ ጥንካሬን እንዲላበስ አደረገው።ብቻውን እየኖረ አልባረክለት እና አልበቃው ያለው ገንዘብ ተባርኮ ቤታቸውን በበረከት ሞልቶት ሲያይ <<ልስራ ጠብቂኝ.!!>> እያለ እሷን ያመናጨቀበትንና ያስከፋበትን ቀናቶች እያስታወሰ ተፀፀተ።ሊክሳትም በቁርጥ ተነስቶ በስራውም እጅግ ስኬታማ ማናጀር ሆነ። ከተጋቡ አመት እንደሞላቸውም ሴት ልጅ ወለዱ።እሱም እናቱን አያት በማድረግ አስደሰታት። በአጠቃላይ ሁለቱም በኑሯቸውም ሆነ ልጅ በማፍራታቸው ቤተሰቦቻቸውን አስደሰቷቸው። ልጃቸውን እያሳደጉ ራሳቸውንም ችለው መኖራቸው ለቤተሰቦቻቸው ትልቅ እረፍት ሆነላቸው። እነሱም በደስታ ሙሉ ሆነው ወልደው ከብደው ጥሩ ኑሮን መኖር ቀጠሉ።
ምንም እንኳን ትዳር ብስለትን ብጠይቅም የሃብት አለመትረፍረፍ ግን ሊያግደው እንደማይችል አመነበት። ትዳርም እስር ቤት አለመሆኑን ራስን ማግኛ መንገድ መሆኑን እና የስኬት መሰላል መሆኑን ተረዳበት።
" ከአንድ ስኬታማ ወንድ በስተ ጀርባ አንዲት ጠንካራ ሴት አለች..!!" የሚሉ ብዙዎች ቢሆኑም እሱ ግን
ያች ጠንካራ ሴት ከጀርባው ሳትሆን ከጎኑ ናት ሲል ይደመጣል።ለአብዛኛው የወንድ ልጅ ጥንካሬ ራሱ ብቻ ሳይሆን ከጎኑ ያለችዋ የሴት ልጅ መሆኗንም በገዛ ሚስቱ ይመሰክራል።እዚህ ለመድረሱም ጉልህ ሚና ያላት በመሆኗ እጅግ ይኮራባታል።ከዚህም የተነሳ
የሱ የስኬት ምንጭ እሷ መሆኗን ሲመሰክር
ሲል በብዙዎች ዘንድ ይደመጣል።
✍ ማዕረግ ፀደቀ
ግንቦት /08/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ

"ከአንድ ስኬታማ ወንድ ጎን አንዲት ጠንካራ ሴት አለች..!!"
ሲል በብዙዎች ዘንድ ይደመጣል።
✍ ማዕረግ ፀደቀ
ግንቦት /08/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ
❤3👏2🥰1
.
.
( ሰመመን)
ሲሳይ ንጉሡ
.
አብዛኛውን ጊዜ ሕይወት የባለቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች።የቆራጥነትና የወሳኝነት ትርጉም የሚገባህ፥ውጤቱን ካየህ ቡሃላ ነው።
( ሰመመን)
ሲሳይ ንጉሡ
❤3
.
.
.
እመጣለሁ ብለሽ.....??
ቀናቶች ተዋልደው አመታት ፈጠሩ
አመታት በርክተው ዘመን አስቆጠሩ
እኔም ያች እስረኛ የቃልሽ ጠባቂ
የመምጫሽን ወራት ቁጭ ብዬ ሰናቂ
ለሰው ቢያስመስለኝ የፍቅር አዋቂ
ታዲያ ምን ነክቶሽ ነው...??
ወደኔ ለመምጣት ምን አሰናከለሽ
አልቆይም መጣለሁ ነበርኮ መልስሽ
እሾህና ድንጋይ የመንገዱ እንቅፋት
እውነት እሱ ይሆን ላትደርስ የገታት
በማለት አልሁኝ ስደረድር ምክንያት
በቅዠት የዋዠቅሁ አንችን ላለማጣት
እናማ አለሜ....
በስውር አለም ውስጥ አንችን እየሰፋሁ
ካስቀመጥሽኝ ቦታ መኖሬን አሰፋሁ
ካንች ወዲያ ለኔ ሴትም እርም አልኩና
በፍቅርሽ እረመጥ እንደገባሁ ዋና
ልቤን ስሸነግል ትመጣለች እያልሁ
በቃሎችሽ እዳ እስከ ዛሬም አልሁ
እውነት እልሻለሁ...!!
ትግስት የተሳነኝ ወንድ ልጅ አልመስልም
ብትመጭ ይሻላል ከቀረሽ አልድንም..!!
ቃልሽን አምኜው እመጣለሁ ብለሽ..
ከቀጠሮው ቦታ ምነው ለምን ቀረሽ..??
እመጣለሁ ብለሽ....!!🤣🤣
✍ማዕረግ ፀደቀ
13/09/2018 ዓ.ም
.
.
እመጣለሁ ብለሽ.....??
ቀናቶች ተዋልደው አመታት ፈጠሩ
አመታት በርክተው ዘመን አስቆጠሩ
እኔም ያች እስረኛ የቃልሽ ጠባቂ
የመምጫሽን ወራት ቁጭ ብዬ ሰናቂ
ለሰው ቢያስመስለኝ የፍቅር አዋቂ
ታዲያ ምን ነክቶሽ ነው...??
ወደኔ ለመምጣት ምን አሰናከለሽ
አልቆይም መጣለሁ ነበርኮ መልስሽ
እሾህና ድንጋይ የመንገዱ እንቅፋት
እውነት እሱ ይሆን ላትደርስ የገታት
በማለት አልሁኝ ስደረድር ምክንያት
በቅዠት የዋዠቅሁ አንችን ላለማጣት
እናማ አለሜ....
በስውር አለም ውስጥ አንችን እየሰፋሁ
ካስቀመጥሽኝ ቦታ መኖሬን አሰፋሁ
ካንች ወዲያ ለኔ ሴትም እርም አልኩና
በፍቅርሽ እረመጥ እንደገባሁ ዋና
ልቤን ስሸነግል ትመጣለች እያልሁ
በቃሎችሽ እዳ እስከ ዛሬም አልሁ
እውነት እልሻለሁ...!!
ትግስት የተሳነኝ ወንድ ልጅ አልመስልም
ብትመጭ ይሻላል ከቀረሽ አልድንም..!!
ቃልሽን አምኜው እመጣለሁ ብለሽ..
ከቀጠሮው ቦታ ምነው ለምን ቀረሽ..??
እመጣለሁ ብለሽ....!!🤣🤣
13/09/2018 ዓ.ም
❤6👏2🕊1
.
.
.
.
.
.
.
( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ
ሠናይ ምሽት ተመኘሁላችሁ!!🙏🙏
.
.
.
የምቾት ችግሩ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስን አለመፍቀዱ ፣ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች መውረድን አለመፈለጉ ነው። ምቾት ጥሩ ቢሆንም ከደረጃ ላለመውረድ የሚያስከትለው ትግል በራሱ ጭንቀት ፈጥሮ ቆይቶ ምቾትን መልሶ መንሳቱ አይቀርም ። በምቾት ውስጥ ምቾት የለም !!
.
.
.
( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ
ሠናይ ምሽት ተመኘሁላችሁ!!🙏🙏
❤🔥4👍2🔥1
.
.
.
ነበር..........!!!!!!
አንዳንዴ ነበር ተብሎ የሚቀር ህይወት ባይኖረን ብላችሁ አስባችሁ አታውቁም....???? በተለይ ደግሞ በደስታ ያሳለፋችኋቸውን ጊዜያቶች ፣ በስኬት የተራመዳችሁባቸውን ቅፅበታቶች፣ በፍቅር የፈካችሁባቸውን ቀናቶች፣ ከምትወዷቸው ቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁ ጋር በሀሴት የኖራችሁባቸውን ዕለታቶች ስታስታውሷቸው ነበርርር....ማለት ነበር በራሱ አሳልፎ ለትዝታ ይሰጠናል።
ትላንትም ነበር እንደተባለው ዛሬም ነገ ላይ ነበርርር ሊባል ነው።በቃ ህይወት እንዲህ ዘርፈ ብዙ ናት ።ትላንትን ሽራ፣ ዛሬን አባራ ነገን ትሰጣለች።በዛው ልክ ደግሞ መጥፎ ቀናቶችን ነበር ማለት ባንችል ኖሮ ዛሬም መጥፎ ህይወት ውስጥ እንሆን ነበር።እናም ደጉን ላለማጣት ስንል ነበር ባይኖር ማለት በራሱ ስቃያትን አሳልፈንና አሸንፈን ነበር እንዳንል ያደርገናል። ክፉ ቀናትን ሳስብ እንኳንም ነበር ኖረ እላለሁ።
ምክንያቱም እሱ ባይኖር ዛሬም ያን ስቃይ ላናሳልፈው እንችል ነበር።በቃ ነበርር.....
✍ማዕረግ ፀደቀ
ግንቦት ~18/2018 ዓ.ም
BDU

❤16🥰3👏1🕊1
ጊዜ .......!!
ሲበዛ ቴንሽናም ነኝ። ማለቴ ትንሹም ትልቁም ጉዳይ እስካልተሳካልኝ ድረስ እረፍት የማይሰማኝ ሰው ከመሆኔ የተነሳ እስካሳካው ብቻ ሳይሆን ተሳካም አልተሳካም መጨረሻውን እስካየው ድረስ አያስችለኝም።በተለይ ደግሞ ወጣትነቴን ሳስብ ማድረግ እየፈለግሁ ሳላሳካው የማልፈው ነገር እንዳይኖር መሞከር ያለብኝን ነገር አጋጣሚዎችን ተጠቅሜ እሞክራለሁ።
ስጣደፍና እዛም እዛም ስል የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ << ውይ... አንች መቼ ነው የምታርፊው..?? በቃ ሁሉ አይቅረኝ ነሽ ..!!>>ይሉኛል። በእርግጥ ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ደግሞ ይህን ንግግራቸው እንደ ጥሩ ምክር ከተቀበልኩ ቡሃላም አላርፍም።እንዲያውም ጊዜ እንዳያመልጠኝ ማስተዋል በተሞላው ጥድፊያ ይበልጥ እጠመዳለሁ። ምክንያቱም ዛሬ ያልገነባሁት ማንነት ነገ ላይ ከየትም ላመጣው ስለማይችል። በወጣትነቴ ያልሰራሁት መሻቴ በእርጅናዬ ወራት ላሳካው የማልችልበት ሰፊ አጋጣሚዎች ስለሚኖሩ፣ በመስሪያዬና በመለወጫዬ ጊዜ ተዝናንቼ በጡረታ ዕድሜ ውስጥ ማረፍ ሲገባኝ በስራና በጥድፊያ ማሳለፍ ስለማልፈልግ ዛሬዬን በተቻለኝ አቅም ለመጠቀም እጥራለሁ።ለዛም ነው የሚያውቁኝ ሰዎች ሁሉ እንደዛ የሚሉኝ።
ለማንኛውም ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ጊዜ ሰይፍ ነው ፣ይገድላልም ያድናልም፣ ጊዜ ፈራጅ ነው፣ጊዜ ካመለጠ ታክሲ አይደለም ፤ቆሞ አይጠብቅም እንደሚሉ ሁሉ የጊዜን ተመን አውቀን መውደቅን እና አለመሳካትን ሳንፈራ መሞከርና ማድረግ ያለብንን ነገር ቀን ሳንቀጥር ዛሬውኑ ሳይረፍድ ፍርሃትን እና ይሉኝታን አሶግደን በቁርጠኝነት ተነስተን በጊዜው መሞከር እንድንጀምር ነው።
ሠናይ ቀን ተመኘሁላችሁ..!!🙏🙏
✍Magi syctalk
❤6👍4
.
.
.
ባህር ዳር........!!!!
ስፈራ ስቸር
ካንቺ ላለመለየት
ፍቅርሽ ገመድ ሆነና ፤
እንቡጥ አይኖቼ
እንባ አመነጩ
ልሰናበትሽ ቀን ደረሰና ።
የገነት ምንጯ
ለምለም ዘንባባ
አንቺ የጣና ፈርጥ ፤
እንቁ ፅጌ ሬዳዋ
አርማ ሰማያዊዋ
ታደልኩ ካንች ስሸጎጥ።
በጣና ስፋት
ፍቅር የሞላሽ
እንዲሁ መውደድ የተቸረሽ ፤
አንችን አግኝቶ
ደግሞስ የማይናፍቅሽ
ውቢት የለም ማይመኝሽ ።
ውቢት አትገረሚ
በእኔ መወደድሽን
ማርኮኝ ደጅሽ ብጠና ፤
የጣናው ውሃሽ
ጥሜን ቆርጦልኝ እንጂ
በጥበብ ጓዳሽ ዋና።
ጋትሽኝ ከምንጭሽ
ጨልፈሽ በፍኝሽ
ስስት አታውቂም እና ፤
ካንቺ ባህር ዳር
የናፍቆት ዕፁ
ከሩቅ ይጣራል ጣና..!!!
✍ማዕረግ ፀደቀ
.
.
ባህር ዳር........!!!!
ስፈራ ስቸር
ካንቺ ላለመለየት
ፍቅርሽ ገመድ ሆነና ፤
እንቡጥ አይኖቼ
እንባ አመነጩ
ልሰናበትሽ ቀን ደረሰና ።
የገነት ምንጯ
ለምለም ዘንባባ
አንቺ የጣና ፈርጥ ፤
እንቁ ፅጌ ሬዳዋ
አርማ ሰማያዊዋ
ታደልኩ ካንች ስሸጎጥ።
በጣና ስፋት
ፍቅር የሞላሽ
እንዲሁ መውደድ የተቸረሽ ፤
አንችን አግኝቶ
ደግሞስ የማይናፍቅሽ
ውቢት የለም ማይመኝሽ ።
ውቢት አትገረሚ
በእኔ መወደድሽን
ማርኮኝ ደጅሽ ብጠና ፤
የጣናው ውሃሽ
ጥሜን ቆርጦልኝ እንጂ
በጥበብ ጓዳሽ ዋና።
ጋትሽኝ ከምንጭሽ
ጨልፈሽ በፍኝሽ
ስስት አታውቂም እና ፤
ካንቺ ባህር ዳር
የናፍቆት ዕፁ
ከሩቅ ይጣራል ጣና..!!!
✍ማዕረግ ፀደቀ
❤9👏4👍2🙏1🕊1
እንደመደበርም እንደመሰልቸትም አድርጎኝ ነበረ። ለመኖር ምክንያት አጣሁ ማለት ጀምሬ ነበረ።
እነዚህ ትናንሽ ሀሳቦች ቀኔን መረበሽ ጀመሩ ። ጠዋት መነሳትና ድጋሜ ሌላ ተመሳሳይ አድካሚ ቀን መዋል ትርጉሙ አልታይሽ ብሎኝ ነበረ።
ከዛ ግን ቀልቤን ገዛሁ የእናቴን እጅ አየሁት። ቆዳዋ ተሸብሽቦ ደምስሮቿ በጉልህ ይታዩ ነበረ። ደነገጥኩ ያ እንደዛ የሚያሳሱ ቀያይ እጆቿ አሁን መዳፎቿ ሳይቀሩ ጠቋቁረዋል።
ውሎዋን አየሁት እንደነገሩ ነው የምትለብሰው ያ ሁሉ መሸቀርቀር የት እንደ ሄደ ግራ ገባኝ። ፈጥና ያረጀችም መሰለኝ።
ከዛ ድግስ ተጠርተን ዘመድ ቤት ስንሄድ በእያንዳንዱ ነገር ላይ የምትሰጠውን የሰላ ሂስ ሰማሁ።
እቤት ስንገባ ጠየኳት ለምን ስራሽን ተውሽው እስካሁን በጣም ምርጥ ጭንቅላት አለሽ እኮ አልኳት በቁጭት
"ኤድያ ተይው ባክሽ ሁሉም ነገር ከቤተሰቤ አይበልጥብኝም" አለች
"እስኪ ተመልከቺ እንዴት ትናንሽ እንደነበራችሁ "በእጇ ህፃን ሆነን እኔና እህቴ የተነሳነውን ፎቶ ይዛ
"አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለኔ ከምንም ነገር በላይ ነው" አለቺኝ በፈገግታ።
እንዴት እንደሆነ ባላውቅም መሰልቸቱ መደበሩ ቀርቶ ጭራሽ አዲስ ጉልበት ይሰማኝ ጀመረ።
ስለእሷ ማሰብ ከአልጋዬ ተስፈንጥሮ ለመነሳት በቂ ነበረ። እሷ መኖር ያቆመችው ለኔ ስትል አልነበር ስለዚህ እኔም የምልፈሰፈስበት ምክንያት አልነበረኝም።
ለኔ ማማር የሷ መጎሳቆል ይበልጥ አጠነከረኝ። በደንብ በኔ እስክትኮራ ድረስ...

copy❤🔥4🥰3❤1😭1
🛑 If you can keep your mind clearly focused on what you want, and refrain from thinking about what you don’t want, you will attract everything you need to achieve your goals, exactly when you are ready. Change your thinking and you change your life.
( Brian Tracy )
( Brian Tracy )
❤4👍3
❤️❤️❤️ተገናኘን...!!❤️❤️❤️
✨🌟✨🌟✨🌟✨☀️✨☀️✨🌟
ቀናቶች ለጉድ ሲነጉዱ
እኔና አንች ተገናኝተን
ሳናወጋ የልባችንን፤
በምቅ ናፍቆት ሰቆቃ
ዛሬ ነገን እየቆጠርን
ብንቆይም ለብቻችን፤
ይኸው መጣሽ አደዬ
ይኸው መጣሁ አዳምሽ
መች አስችሎን እንቀራለን፤
በእግዜር አምሳል ቸርነት
በሱ ጥበብ ጉብኝት
ላንለያይ ተዋህደን፤
እልፍ እንቅፋት ተግዳሮት
ማያሳልፍ የእሾህ አጥር
ቢነጠፍም አሜኬላ፤
ይኸው ዛሬ ተገናኘን
መንገዳችን ተጠረገ
💞 የልባችን ዛሬ ሞላ ።
✍ማዕረግ ፀደቀ
✨🌟✨🌟✨🌟✨☀️✨☀️✨🌟
ቀናቶች ለጉድ ሲነጉዱ
እኔና አንች ተገናኝተን
ሳናወጋ የልባችንን፤
በምቅ ናፍቆት ሰቆቃ
ዛሬ ነገን እየቆጠርን
ብንቆይም ለብቻችን፤
ይኸው መጣሽ አደዬ
ይኸው መጣሁ አዳምሽ
መች አስችሎን እንቀራለን፤
በእግዜር አምሳል ቸርነት
በሱ ጥበብ ጉብኝት
ላንለያይ ተዋህደን፤
እልፍ እንቅፋት ተግዳሮት
ማያሳልፍ የእሾህ አጥር
ቢነጠፍም አሜኬላ፤
ይኸው ዛሬ ተገናኘን
መንገዳችን ተጠረገ
💞 የልባችን ዛሬ ሞላ ።
✍ማዕረግ ፀደቀ
❤12💘2🕊1
.
.
.
( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ
.
.
እድሜ ጊዜ ነው።ሰው ሞተ የሚባለው እኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም ዕድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም ? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከዕድሜህ እየቀነሰብህ ነው።የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታ ጊዜ ነው። እንዴት? የሰጥኸው ጊዜ ከዕድሜህ ላይ የቀነስከው ነውና!
( ሰበዝ )
አለማየሁ ዋሴ
❤5👍3
🛑If you think about success and confidence, you will feel strong and competent, and you will perform better at whatever you attempt.
🛑 If you think about making mistakes or being embarrassed, you will perform poorly, no matter how good you really are. Pictures and image.
(Brian Tracy )

👍3❤1
ማጣት የማይሰብራት፤ማግኘት የማያንጠባርራት፤ ስልጣኔ ያልቀየራት፤
ጥበብ ያልጋረዳት፣ለህልሟ የምትቃትት ለምስኪን ቤተሰቧ እና ህዝቧ የምትኖር፣እሷ ዕንቁ ሴት ናት።
አንዲት ቀንም ከአይኖቿ ላይ የእንባ ዘለላ ከሰው ፊት ጠብ አድርጋ አታውቅም። ከፊቷም ላይ ውብ ፈገግታ አይጠፋም።መከፋቷን በከንፈሮቿ ደብቃ በምትኩ እንደ ጨረቃ በነጡት ጥርሶቿ ሳቅና ደስታን ታበስራለች።
የሰው ይሉኝታና ትችት ከመንገዷ አያስቀራትም። ፍፁም ፍርሃት አታውቅም።ማንነቷንም ከራሷ ጋር እንጅ ከሌሎች ጋር አታወዳድርም።
ተስፋ መቁረጥ ለሷ የሞት ያህል ነው።በችግሮቿ አትሰበርም።በርትታ ታበረታለች፤ስቃ ታስቃለች።የፈዘዘን ታነቃለች።
እጇም ንፋግነትን አያውቅም።ችግረኛ ያሳዝናታል። ልትጎርስ የቆረሰቻትንም ቢሆን ለተራበ ታጎርሳለች። ምን አለፋችሁ ሴት አይደለች የእናትነትን ምስጢር ታድላለች።
ውድቀቷ የስኬት መጀመሪያዋ እንደሆነ ታምናለች።እሷ ስኬታማ አለመሆን አትችልም። ምክንያቱም ፍርሃትን የምታሻፍር ፣ውድቀቷን የምትቀበል ፣ችግሮቿን የምትጋፈጥ፣ ከነገሮች የምትማር፣ በፈተናዎች የምትፀና ፣ሃላፊነት የሚሰማት ሴት የስኬት ሚስጢሯ ይህ ነው።
👉አንተን ነው..
ለዛች ስኬታማ 👩ሴት ላክላት

❤7👍1🕊1