Tsegaye R Ararssa
15.8K subscribers
1.71K photos
255 videos
164 files
2.6K links
TA
Download Telegram
የዘር ማጥፋት ወንጀል በትግራይና በተጋሩ ላይ--የ NLI ዘገባና አንድምታው (Random Notes)
==========================
በትግራይ ጦርነት ወቅት: በዘር ማጥፋት ዘመቻ ተሰማርተው የነበሩ: ያስተባበሩ: ያሴሩ: የረዱ: የቀሰቀሱ: በተጨባጭም በአካል ተገኝተው የፈፀሙና ያስፈፀሙ በሙሉ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ (ስንናገር የነበረው ሃቅ) በሰሞኑ የNEW LINES INSTITUTE ዘገባ በሚገባ ተተንትኗል::

ይሄ ሙያዊ ትንተናን የያዘ ዘገባ: ተጠያቂነትን ለመተግበርና ለተጠቂዎች ፍትህን ለማስገኘት ለሚደረገው ትግል ትልቅ ግብኣት ሆኖ እንደሚያገለግል ይታመናል::

ያም ሆኖ: በተጨባጭ የደረሰው ግፍ እጅግ መጠነ-ሰፊና ከተዘገበውም ብዙ እጥፍ በላይ መሆኑን: ሁነቱን በወቅቱ የተከታተሉት: በተጠቂነት በውስጡ ያለፉት: በተራፊነት የታገሉት: በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ (በከበባ ምክንያት የተራቡትን: የታመሙትንና ያለቁትን ከጨመርን ደሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ) ወገኖቻችን "ሕይወት" ይመሰክራል::

የዘር ማጥፋት ወንጀል: የክፋት ጥግ (“the epitome of human evil”) ነው ይላል: የተመድ መግለጫ ቁ. 96/1(1946):: የሰው ልጆችን የሚያጎድል (ማለትም: ተጠቂዎችን ገድሎ/አጥፍቶ: የሰው ዘርን የሚያደኸይ) ክፋት ተደርጎ የሚታየውም ከዚህ አንፃር ነው:: በሚፈፀምበት ጊዜም: ተጠቂውን ከሚጎዳው በላይ: አድራጊውንና (የተረፍነውን) የሚያሰየጥነው: በዚሁ ምክንያት ነው:: በዚህ ወንጀል በተጠቂዎች ላይየሚፈጸመው ጭካኔ (brutality): ከአድራጊዎቹም ያለፈና የዘለቀ ማሕበረሰባዊ ጭካኔ መሆኑን አመላካች ነው የሚባለውም በዚህ ምክንያት ነው:: ...

ድርጊቱ በግለሰቦች ቢፈፀምም: ባለቤቱ መንግሥትም ነው:: ተጠያቂነቱም የግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆን: የመንግሥታዊ ሥርዓቱም ነው:: የምግባር ተጠያቂነቱ (the moral responsibility) ደግሞ የተጠቃሚዎች (beneficiaries): የግድየለሽ የሩቅ-ተመልካቾች (bystanders)ም ነው:: የማሕበረሰቡም ነው::

ለዚህ ነው: ይሄ ወንጀል: ሁለ-ገብ (pervasive) ማህበረሰባዊ ሥረ-መሠረት አለው የሚባለው:: ለዚህም ነው: ይሄ ወንጀል የሚፈጸምባቸው ማሕበረሰቦች: አንድም ቀድሞውኑም የሚያስተዛዝን ማህበራዊ ትስስር (social fabric) አልነበራቸውም: ወይም የነበረው ትስስር (fabric) ፈርሷል የሚባለው::

የሆነ ሆኖ: አሁን ወንጀሉ በተጨባጭ እንዴትና በማን እንደ ተፈጸመ--በመጠኑም ቢሆን--የሚያሳይ ዘገባ ቀርቧል:: በዚህም እውነቱ ተቀብሮና ታፍኖ እንዳይቀር ለማድረግ የሚያስችል የመጀመሪያ ሊባል የሚችል እርምጃ ተወስዷል:: (ይሄም የተጎጂዎችን እውነት በማስታወስ--re-call በማድረግ ወይም እንዲመለስና እንዲታወስ/እንዲጠራ በማድረግ--ሃቃቸው ህያው ሆኖ እንዲኖር ይረዳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን::)

በዘር ማጥፋትና በሌሎች መጠነሰፊ ወንጀሎች (mass atrocity crimes) ለተጎዱ ግለሰቦችና ቡድኖች ፍጹም ፍትሕን ማስገኘት ባይቻልም (because of the fundamental incommensurability between harm and punishment) : ቢያንስ ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡ: ይሄን ያስፈጸመ መንግሥትና ያስቻለው አገርና ማሕበረሰብም ለህሊና ፍርድ ስለሚቀርብ: ምናልባት እንደ ሕዝብ እራስን ለማረቅም ይጠቅም ይሆናል:: ማሕበረሰቡ ህሊና ካለው:: (መቼም በተደጋጋሚ እንደገለፅኩት: በበኩሌ: ኢትዮጵያም እንደ አገር: ማሕበረሰቡም እንደ ሕዝብ--ቢያንስ ፖለቲካና ፍትሕን በሚመለከት--ህሊና የላቸውም:: ከነበራቸውም ታውሯል ብዬ ከደመደምኩ ዓመታት አልፈዋልና እውነትን በመጋፈጥ እራሱን ያርቃል የሚል ተስፋ (ወይም illusion ይሉት ቅዠት) የለኝም::)

ለማንኛውም: ይህቺ ዘገባም ባወጣችው የእውነት ጨረር ተጠቅመን የእነ አብይን የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢያንስ ለፍትህ ትዕይንት (for some spectacle of justice) ለማብቃት ዕድሉ መኖሩ አንድ ነገር ነው:: ለእርሱም ቢሆን ገና ብዙ ሥራ ይጠብቃልና ወገብን ጠበቅ ማድረግ ያስፈልጋል::

(በሌሎች ሕዝቦች ላይ ለተፈጸሙትና እየተፈጸሙ ላሉትም ቀን ይወጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን:: ለዚህም ተግተን መሥራት ይጠበቅብናል::)

https://newlinesinstitute.org/rules-based-international-order/genocide-in-tigray-serious-breaches-of-international-law-in-the-tigray-conflict-ethiopia-and-paths-to-accountability-2/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR1uAKMTOFiZ9qyeftoDY4MaOuSPZ2Cc36XNFWsftDzt7jPOX-giNiKdXwI_aem_AcAOBMHiFe2kQIDuNwj3Nx-GAnFfjo8wOZxbjjl9DGrlGltX0Qp9J6kRFypI0_EQ2W_EIJUspfWkEH-9XLUySgdy


#AbiyAhmed_is_a_genocidaire! #Abiy_to_ICC!
Just finished working on a draft of the submission we want to lodge with the Parliamentary Sub-Committee on Human Rights. This submission is specific to the issue of accountability measures to be taken in regards to those involved in the crime of genocide, war crimes, and crimes against humanity in Ethiopia (especially those committed in Tigray).
#Abiy_to_ICC #AbiyAhmed_Is_a_Genocidaire
መካን: መክኖ ሊያመክን ይኳትናል--"የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት" አቀንቃኝ ልሂቅ
=====================
የኢትዮጵያብሔርተኝነት አቀንቃኝ ነን እያለ እራሱን የሚያንቆለጳጵሰው ልሂቅ: ንጉሳዊ አገዛዝ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ አንድም አገር የሚተዳደርበት ወይም የሚገነባበት የፖለቲካ ሃሳብ ማፍለቅ አቅቶታል:: ከዚህም የተነሳ: ለ50 ዓመታት ሃሳብ-የለሽና ቤት-የለሽ ሆኖ ሲንቀዋለል ቆይቷል::

የኦሮሞ ወጣት በደሙ ባመጣው ለውጥ ተጠቅሞና የቄሮን ትግል ጠልፎ ሥልጣን በያዘው በአብይ አህመድ ዘመንም: አብይ ላይ ተንጠላጥሎና የፋሽስት አንጋሽ ከመሆን አልፎ: አገርን ወደፊት የሚያራምድ አንድም ሃሳብ ለማፍለቅ ባለመቻሉ: "ወደ ቀድሞው ክብር" እንመለስ እያለ ማላዘኑን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው::

ይሄ ቡድን ነጥፏል:: የሃሳብ መካን ስለሆነ: መቃወም እንጂ መምራት: ማፍረስ እንጂ መገንባት: ማግለል እንጂ ማካተት: በአጠቃላይም: አሉታዊ እንጂ አወንታዊ ፖለቲካ አያውቅም:: ከሃሳብ ነፃ በመሆኑም ነው "መደመር" በሚባል ስብከት አይሉት መፈክር ዙሪያ ተኮልኩሎ ሲያብድ የነበረው:: ጥላቻ እንጂ የሕዝብና የአገር ፍቅር ስለሌለው: በክህደት ከጠላት ጋር አብሮ አገርንና ወገንን መውጋት: ሕዝቦችንና እሴታቸውን ማውደም: ያልከበደው:: ለዚህ ነው: ያደፋፈረውና የአስፈፀመው ወንጀል-ነውሩን (የሴት ልጆችን በዘመቻ መደፈርን በጭምር) ጌጡ አድርጎ አደባባይ ለመውጣት ያላፈረው::

በሃሳብ ልዕልና ለሥልጣን መብቃት እንደማይችል ስለሚያውቅ: በሴራ: በተንጠልጣይነትና በማስመሰል መኖርን ያውቅበታል:: ሃሳብ-የለሽና ግብረ-ብኩን ስለሆነ: ሃሳብ ያላቸውን: ይፈራል: ይጠላል: ያገላል:: ከባሰም: ያሳድዳል: ያጠለሻል: በሃሰት ይከሳል: ያፍናል: ይገድላል: ፈፅሞ ለማጥፋትም እስከሚችለው ድረስ ይጏዛል::

ይሄን ሁሉ አድርጎ ካልተሳካለት: አቋሙን ቀይሮ ከዚሁ በባላንጣነት ፈርጆ ሊያጠፋ ከሞከረው ኃይል ጋር "ወንድማማችነቱን": የተጋባ-የተዋለደ መሆኑን: ከእነርሱ ጋር የአንድ እምነትና የአንድ አገር ልጅ መሆኑን በመስበክ አሰላለፍ ለማስተካከል ብሎ ይቅለሰለሳል:: "ሌሎች መሃላችን ገብተው አጣሉን እንጂ እኛ ለ3ሺህ ዘመናት በሰላም አብረንኖረናል" እኮ እያለ ብዙ ይዘበዝባል:: "ኢትዮጵያዊ" ይቅርባይነትህን ሊያስታውስህና በሰላም አብራችሁ እንድትቀጥሉ: ይለምንሃል::

በዚያው ወቅት: በተመሳሳይ መንገድ: ከአንተ በተቃራኒ ጎራ ለተሰለፉ ሌሎች ኃይሎችም ተመሳሳይ ትርክት አይሉት ንግርት እያዘራ እነሱንም ለማራራትና በአንተ ላይ ለሚደረግ ሌላ ዙር ግፍ ወይም ሴራ ከጎኑ ለማሰለፍ ይውተፈተፋል::

"ኢትዮጵያ አንድ ነች" እያለ ያደነቁርሃል:: እሱ የሚያደራጃቸው የፖለቲካ ኃይሎች ለአንድ ወር እንኳን በአንድነት መዝለቅ ተስኗቸው: 44 ቦታ ሲሰነጣጠቁ ዕለት ዕለት ትታዘባለህ:: ይሄንንም የዴሞክራሲያዊነቱ ውጤት መሆኑን ሊያስረዳህ ይሞክር ይሆናል:: ለእነርሱ ፓርቲዎች መሰነጣጠቅና መብዛት ምክንያት የሆነውን "ዴሞክራሲያዊ ሕብራዊነት" በጥቂቱ እንኳን ጨልፎ ለአገሪቱ ሕዝቦች ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉን ወይም አለመፍቀዱን ፈፅሞ አያስተውልም:: ሃሳብ የለሽነቱ: ፍፁም የሆነ የምግባር መታወር (moral blindness) ውስጥ ሆኖ እንዲዳክር ያደርገዋል::

እንዲህ እንዲህ እያለ: የሃሳብ መካን (መሴና) ሆኖ ሲንከራተት ይቆይና: መለስ ብሎ: የእራሱን ኦናነት ለመሸሽ በሚመስል መንቀዥቀዥ: ሌሎችን (በተለይ "የብሔር" ፖለቲካ ኃይሎችን: ከእነሱም ውስጥ በተለይ ኦሮሞዎችን) ማንጏጠጥ ይጀምራል:: ዓይኑን በጨው ታጥቦም: "ኦሮሞ 50 ዓመት ታግሎ ምንም ድል አላገኘም" እያለ የተለመደ የማጠልሸት ፕሮፓጋንዳ ተግባሩን ይደጋግማል (ድግምት እራስን የማሳመኛ መንገዱ ሳይሆን ይቀራል?)::

እሱ ስለነጠፈና ስለ መከነ: ሁሉም እንዲነጥፉ ከመመኘት አልፎ: እነሱም ነጥፈዋል: መክነዋል: በማለት የነቀፋ ፉጨቱን በየአደባባዩ በየሚዲያው ያፏጫል::(መቼም በሚድያና በሌሎች ሃይማኖት-ወ-ባህል: ትምህርት-ወ-ኪነ-ጥበብ: ወዘተ ላይ እንዳላቸው hegemony መጠን ሃሳብ ኖሯቸው ቢሆን ኖሮ...!)

ለመሆኑ: በእርግጥም የኦሮሞ የፖለቲካ ትግል እስከዛሬ ድረስ ምንም ድል አላስቆጠረምን? የኦሮሞ (እና የሌሎቹ ብሔራዊ ትግል አራማጅ) ልሂቃንስ ተጨባጭ ሃሳቦችን አላበረከቱምን?

የእነሱ አዎንታዊ ሃሳብ የፖለቲካ ምህዳሩን ባይይዘው ኖሮ: "የኢትዮጵያ" ልሂቅ (ነኝ ባዩ) ምንን ይቃወም ነበር? የእነሱ ሃሳብ መድረክ ባይናኝበት ኖሮ: (ለምሳሌ ያህል):

*በብሔር መደራጀትን(የብሄር ፖለቲካ ይቁም" እያሉ) መቃወምን ከየት ሊያመጣው ነበር?

*ብሔራዊ ማንነትን ("መታወቂያ ይቀየር"? እያሉ) እንዴት ይቃወሙ ነበር?

*ፌደራሊዝምን ("ከፋፋይ ነው"!) ከየት አምጥተው ይቃወሙ ነበር?

*በቋንቋ መጠቀምን (የኦሮሞ: የትግራይ: ወዘተ ቤክህነት ማቋቋም ቤተክርስቲያኒቱን ማፍረስ ነው" እያሉ) ማንንና ምንን ይቃወሙ ነበር?

*ሕገ-መንግሥቱን (ከየት መጥቶ እና) በምን ምክንያት ይቃወሙ ነበር?(ለነገሩ: ሕገ-መንግሥት የአገር ማስተዳደሪያ ሃሳቦችና እሴቶች ማህደር መሆኑን መች ይረዱና?!? ፌደራሊዝም: የራስን እድል በራስ መወሰን: እኩልነት: የእርምት እርምጃዎች: ወዘተን የመሳሰሉ ተራማጅ ሃሳቦች ትልቅ የፖለቲካ እሳቤዎች--ሃሳቦች--መሆናቸው መች ይገባቸዋል?!?)

*ክልሎችን በመቃወም ("ይፍረሱልን" እያሉ) እንደምን ያላዝኑነበር?

*የብሔሮችን ቀን: ግንቦት 20ን:ወዘተ የመሳሰሉ (አይከበሩ እያሉ) የሚያጥላሏቸውና የሚያንቋሽሹአቸውን ክቡር ቀናት ከወዴት ያመጡአቸው ነበር?

እነዚህ ምሳሌዎች የእነሱን ሃሳብ-የለሽና አሉታዊ ክርክር ብቻ ያለው ፖለቲካ (negative politics) የሚያሳዩ ናቸው:: ከዚያም አልፎ: ይሄን ሁሉ የሚቃወሙትን ሃሳብ ያመነጩት: እነሱ ሊያናንቁ የሚሞክሩት--የኦሮሞን ጨምሮ--ብሔራዊ ትግል የሚያራምዱ ኃይሎች በአጠቃላይ መሆናቸውን በግልጽ ያስረዳል::

የብሔሮች የፖለቲካ ትግል ባጠቃላይ: የኦሮሞ ትግል በተለይ: (ለእነዚህ ለምሥጋና-ቢስ የአፍ "ኢትዮጵያውያን" ጭምር) ያስገኘውን ድል (ወይም ጥቅምና ትርፍ) በዝርዝር እመለስበታለሁ:: ለዛሬ ... አበቃሁ::

(ይቀጥላል)
የቱንም ያህል ውሸት ብትከምርና የቱንም ያህል ጥቅስ ብትደረድር: ለቀሰቀስከው: ላስፈፀምከው: ለደገፍከውና ለፈፀምከው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተጠያቂነት አትድንም:: አዲሱ የጦርነት ቅስቀሳም ሆነ "ያቆሰልነው አውሬ ናቸውና እናጥፋቸው" የሚለው ፉከራህ: ቀድሞ ያደረስከውን ጉዳት ማመንህን:አሁንም በዚያው የዘር ማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተህ እንዳለህ ከማሳየቱ በቀር ከወንጀለኝነት ነፃ ሊያደርግህ አይችልም::

#Dagnachew_is_a_dead_man_walking!
#Genociders2ICC!
Two days ago, Professor Hassen Mohammed, who hails from the Somali region, gave an interview to Kush Media, an Oromo news media. I listened to what the professor had to say on a number of issues, and here is my takeaway.

First of all, it is clear that the professor has an axe to grind when it comes to the TPLF, which he accuses of being a minority party that assembled satellite organizations from every nation and ruled Ethiopia for 27 years with an iron fist. He also claims that the federal system that was in place during the TPLF’s rule was fake and intended to divide and rule. Further, he is of the view that the TPLF was in the service of the interests of the United States and never cared about the country. (By the way, he makes the same accusations regarding the Prosperity Party). Obviously, he is entitled to his opinion, and I am not here to defend the TPLF, which, by its own admission, does not dispute that it made many strategic miscalculations. Even then, I also believe that the professor is not entitled to his own facts.

During the interview, I noticed that the professor, wittingly or unwittingly, made a couple of serious misrepresentations of facts about how Eritrea got involved in the Tigray war and whether Eritrea still occupies Irob land (and even if there are people who are called "Irob."

According to the professor, Eritrea joined the war on Tigray after the latter launched missiles to Asmara. Therefore, Eritrea presumably joined the war in self-defense. This is factually erroneous and patently a lie. Abiy and Issayas (and the Amhara Fanos and Special Forces) had been plotting to attack Tigray long before the missiles were launched. I refer readers to the extensive report in the New York Times regarding the genesis of the Tigray war. Read also the book by the then-head of security of the Amhara region (now deceased), who wrote that preparations to attack Tigray started long before the launching of the missiles. Other independent sources have also reported that troops were amassed in all directions to attack Tigray. In short, Eritrea would have joined the war on Abiy's side regardless of the missile attacks because the decision to invade Tigray was planned and agreed to well in advance.

The other lie is the professor's assertion that Eritrea has not occupied Ethiopian territory, particularly in reference to the area called "Irob" - located in east Tigray. Well, this is completely untrue. Just this past week, the United Nations issued a report on the human rights violations in Ethiopia that included human rights abuses in Irob's more than 50 villages by Eritrea that continues to occupy the land and called for its withdrawal. That is also the official position of the US and the EU, which have repeatey called for the withdrawal of Eritrean forces from Irob. Most of all, nobody denies that some of the Irob people have fled their homes and now live in shelters in Adigrat. So, it is beyond me where the hell the professor got his "facts."

Finally, I was dumbfounded when I heard what the professor said regarding the Irob people and their history. By the way, this issue is very personal for me. (During my younger years, I was a member of the EPRP based in Irob land, where I stayed for over two years). While I was there, I have learned a lot about the Irob people, their history, and culture. It is true that the Irob people belong to the Saho ethnicity and speak the same language. However, the Irob people are a distinct clan, mostly Catholic unlike their brethren in Eritrea who are Muslims. The Irob people identify themselves as Ethiopians. It is also worth noting that Irob land had never been part of Eritrea during the Italian colonial rule or after Eritrea was federated with Ethiopia - and even after Haile Selassie annexed Eritrea and made it a province. Irob land has always been under Tigray administration. These are the facts!! The professor was therefore telling fiction. He even had the audacity to disparage the proud people of Irob that the name "Irob" itself was a TPLF creation.
I personally know that the Irob people have been calling themselves Irob for hundreds of years.

Professor, your beef with the TPLF does not give you the right to create facts right out of your pockets.

_by Zemenay Bahta.
"ዶሮ ብታልም ጥሬዋን" አሉ:: ከሲንጋፖር ምን ተማርክ ቢሉት: "ጭከና/ጭካኔ/መጨከን" አለ አሉ ዲያቆን ዳንኤል!

የመጀመሪያው የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ሊ ኳን ዪው (Lee Kuan Yew) በአንድ ወቅት: ለተሳካ የአገር ዕድገት እና ዘላቂ ማህበራዊ ለውጥ (ማለትም ለSocial Transformation): 1ኛ) ብርቱ መሪ (strong leadership), 2ኛ) ውጤታማና ከሙስና የራቀ ቢሮክራሲ/ሲቪል ሰርቪስ (Effective administration/civil service), እና 3ኛ) ማህበረሰባዊ ሥነ-ሥርዓት (social discipline) ያስፈልጋል ይል ነበር::

እና ይሄ ማህበረሰባዊ ሥነ-ሥርዓት የተባለውን የዕድገትና የለውጥ አንጏ: ዲያቆን ዳንኤል ሲተረጉምና ሲረዳው: "ጭካኔ" ሆኖ ታየው:: ድሮስ በጭካኔ የዘር ማጥፋትን የቀሰቀሰና ያስፈጸመ ሰው: ከጭካኔ (brutality) የተሻለ መፍትሔ መች ይታየዋል?

#Genocidaires2ICC
#Abiy_Ahmed_is_a_genicidaire!
#Daniel_Kibret_is_a_genocidaire!
Ethiopia, not just its officials, Stands accused of Genocide
=================
When Abiy weaponised the House of Federation (HOF) to stop all legal relationships with Tigray in 2020, in effect, it moved to eject and expel Tigray from the Federation. This is why we have been saying that the primary legal tie between Tigray and Ethiopia now is the Pretoria Ceasefire Agreement which invokes the constitution secondarily, and that only in regard to the implementation of the terms of the ceasefire.

Ever since the regime’s fateful act of ejecting Tigray from the Ethiopian Federation, the constitutional tie was broken. As far as Tigray was concerned, the constitution was rendered inoperative. Whether the Pretoria Agreement’s vague invocation of the constitution has a restorative significance is unclear, and is yet to be debated among lawyers.

Nevertheless, the fact that the regime ejected one of its regions from the federation at will as a prelude to its genocidal war will be remembered as a historical first in the empire’s constitutional-legal narrative.

And this formal act of isolating Tigray is one evidence showing how the genocidal campaign was a premeditated, systematic, and coordinated project of the Ethiopian government. This is where it formally began.

This is why the Ethiopian State as such stands accused for the crime of genocide. For this makes for a comprehensive indictment of Ethiopia before ICJ.
Channel photo updated