ትምህርት ሚኒስቴር
176K subscribers
456 photos
2 videos
46 files
476 links
📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው

📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት ሊጀምር ነው። ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም ለሚገቡ ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጀሉ ዑመር (ዶ/ር) ተናግረዋል። የሙያ ብቃት ማረጋገጫው ከመጪው መስከረም ጀምሮ መሰጠት የሚጀመር ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀና የገበያውን…
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት ሥልጠና ፕሮግራሞች መርሃ-ግብር ሊጀምር ነው
***
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት ሥልጠና ፕሮግራሞች መርሃ-ግብር እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ጀይሉ ዑመር (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲውን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ራስ ገዝ ለማስገባት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የፕሮፌሽናል ሴርቲፊኬት ሥልጠና ፕሮግራሞች መርሃ-ግብር  መስጠት ለመጀመር መወሰኑን ነው ያነሱት።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሲሆን፤ መርሃ-ግብሩ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ እንደሆነም አስታውቀዋል።

የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት ሥልጠና ፕሮግራሞች መርሃ-ግብር በሁሉም ዘርፎች ላይ እንደሚሰጥ ጠቁመው:- ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል፡፡

በተጨማሪም በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ከሙያቸው ጋር በተያያዘ በመርሃግብሩ መሳተፍ  እንደሚችሉ ተገልጿል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለአዲስ አበባ (6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ) ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አጭር መረጃ

📄የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ይሰጣል(ፈተናው የ8ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

📄የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል!!(ፈተናው የ6ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

📄የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በአዲስ አበባ   በበይነ መረብ (Online) ብቻ በተመረጡ ት/ቤቶች ይሰጣል::

📄የ12ኛ ክፍል(Social )ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም በተመረጡ ት/ቤቶች  ይሰጣል::
(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ ክፍል  በነባሩ ስርዓተ ት/ት(ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ) እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት እንዲሁም ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ት/ት  ይሸፍናል

📄የ12ኛ ክፍል(ተፈጥሮ ሳይንስl)ፈተና ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም በተመረጡ ት/ቤቶች   የሚሰጥ   ይሆናል(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ ስርዓተ ት/ት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

📄ተማሪዎች ይህንን መረጃ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አንድታረጉ::

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች፤ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

(መርሐግብሩ ከላይ ተያይዟል።)

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የትግራይ ክልል በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞ በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የሚፈተኑበት መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአክሰስ ሚኒ-ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት የተሰጠውን ትምህርት ተከታትለው አጠናቀዋል።

50 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሰርተፊኬት እነደተበረከተላቸው ተገልጿል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል።

በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል።

በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል" የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡

የሪሚዲያል ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቻ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል፡፡

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ማጣራት የሪሚዲያል ፈተና ከሰኔ 1-7/2016 ዓ.ም ወይም ከሰኔ 8-14/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ 

ዘንድሮ ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ከታህሳስ ወር ጀምሮ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም፡፡ ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል እንዲሁም አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ስለመሆኑ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተባለ ነገር የለም፡፡

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⭐️ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ

በሀድያ ዞን ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀን አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀን (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰነድ ማስረጃዎችን፣ጥቆማዎችን እና መመሪያዎችን በማጣቀስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ሌላም የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱንም በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባለፉት 9 ወራት ከ1ሺህ በላይ ሃሰተኛ ሰነዶች ለአገልግሎት ቀርበው እንደነበር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ


አገልግሎቱ ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በቀን በአማካይ ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለምእሸት መሸሻ፤ባለፉት 9 ወራት ከ715 ሺህ በላይ ጉዳዮች ያለቀጠሯቸው እንደተስተናገዱ ገልጸው፤  በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ከገቢም አንፃር ከአምናው የተሻለ አፈጻጸም እንደተመዘገበ ነው የተናገሩት፡፡

በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መሰረታዊ ችግር እንደነበር የተናገሩት ባለሙያው፤ በ9 ወራት አፈጻጸም ከ1ሺህ በላይ ሃሰተኛ ሰነዶች እንደተገኙ እና ከእነዚህም ውስጥ የማንነት መታወቂያ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዝ ገልጸዋል፡፡

ከሀሰተኛ ማንነት ጋር ተይይዞ የሚቀርቡ ሰነዶች ለተቋሙ ስራ ተግዳሮት እንደፈጠሩበትም ነው የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚው የተናገሩት፡፡

ተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ማሻሽያ እንዳደረገ የገለጹት አቶ አለምእሸት፤ በቀጣይ ጊዜያት ከሃሰተኛ የሰነድ ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዘመናዊ አሰራሮች ተግባራዊ መደረጋቸው ይቀጥላል ብለዋል፡፡

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር በብሔራዊ ደረጃ በወረቀትና በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና፣ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ ተማሪዎች እንዲዘጋጁ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ላፕቶፕም ሆነ ሌሎች ግብዓቶችን አዘጋጅተው በፈተና ወቅት ኢንተርኔት ከተጠለፈ ወይም ከተቋረጠ እነሱም ሆኑ ሚኒስቴሩ ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚወድቁ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ያሉት፣ የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር ተወካይ ወ/ሮ ሐረገወይን ገረሱ ናቸው፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች እንዲህ ዓይነት መሠረተ ልማት ያሟላሉ ወይ የሚለውን ራሱ ሚኒስቴሩ መፈተሽ እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ ሐረገወይን፣ በአገር ደረጃ በትምህርት ቤቶች የኢንተርኔት አቅርቦት ተደራሽ ሆኖ ሲስተሙ በምንም ዓይነት ምክንያት ሳይቋረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ተሞክሮ ስለሌለ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ ራስ ገዝ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ እና ምርምር ላይ በስፋት እየሰራ ቢሆንም አመርቂ አይደለም ተባለ‼️

ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ከሆነ በኋላ በምርምር እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም አጥጋቢ እንዳልሆነ ነው የተመላከተው፡፡

ምንም እንኳን የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከላት ቢገነቡም የእስካሁኖቹ በሚጠበቀዉ ልክ ዉጤታማ አለመሆናቸዉን ተናግረዉ፤ አሁንም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የተላበሰ የምርምር ጣቢያ ለመክፈት እና ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ እንዳለ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ካሱ ጂልቻ ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተቀራርበዉ ባለመስራታቸው ዉጤታማ እንዳልሆኑ የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ ይህን ችግር ለመቅረፍ ምሁራን የተሻለ የምርምር ዉጤት እንዲያቀርቡ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቀዋል፡፡

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲተዋወቁ መምህራኑ በፍጥነት ራሳቸዉን በማብቃት ተማሪዎችን ማገዝ እንዳለባቸው የተናገሩት ዶክተር ካሱ፤  ይህ ካልሆነ ግን አብሮ መጓዝ እንደማይቻልና ተቋሙም ብቁ ያልሆኑ መምህራንን እንደማያስቀጥል ገልጸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዉጤቶች እስከ ዓርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም መቅርባቸዉን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ ይሰጣል።

በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከላይ በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡

ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በአድራሻው ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን  የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች #ከተደለደሉበት_ክለስተር_ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም የማይችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
A plus VIP Channel .pptx
4.2 MB
📇 የ12ኛ ክፍል ኦንላይን ፈተናን ተማሪዎች እንዴት አድርገዉ መፈተን እንዳለባቸዉ የሚያስረዳ የቴክኒካል ስልጠና ማንዋል!!

📇 Online ለምትፈተኑ ተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው ተመልከቱት!!🥰

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ የተዘጋጀ መለማመጃ

በተቀመጠው መመሪያ መሠረት የኦንላይን ፈተናውን ይለማመዱ።


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
#ExitExam #ReExam

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።
2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል። ( የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር)

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

(የባለሥልጣኑ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM