የታይም አካዳሚ የቀድሞ ተማሪዎች መገናኛ ቻናል ‼️
420 subscribers
641 photos
8 videos
849 files
140 links
Time academy student
Download Telegram
የ2016 ዓም የትሞህርት ዘመን ምዝገባ ለነባር ተማሪዎች ከሀምሌ 07 ቀን 2015 ዓ.ም  እስከ  ሀምሌ 30 2015 ዓ.ም ብቻ 
ለአዲስ ተመዝጋቢ  ተማሪዎች ከሀምሌ 07 ቀን 2015 ዓ ም ጀምሮ ባሉን ውስን ቦታዎች ቅድሚያ የመጡትን ብቻ የሚያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ :-  ከዚህ በፊት እንደተለመደው  ቆይተው ለመመዝገብ የሚመጡት ተማሪዎች ት/ቤቱ ሀላፊነት አይወስድም
ዘንድሮ ደጋግመን ባሳወቅነው መሰረት እስከ ሀምሌ 30 ብቻ መሆኑን ተገንዝባችሁ አሁንኑ ተመዝገቡ።
https://t.me/+7LIboVIE2hY4YjJk
ለ2016 ዓ.ም አዲስ ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉን መረጃዎች ይህንን ሊንክ ተጭነው ያግኙ
ለውድ የታይም አካዳሚ ቤተሰቦች በሙሉ :-

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መረጃዎች ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ይመች ዘንድ በት/ቤታችን ስም አዲስ የቴሌግራም ቻናል ስለከፈትን አዳዲስ መረጃዎች ለማግኘት ከታች የተያያዘው ሊንክ በመጫን ቤተሰብ መሆን (join) እንደምትችሉ እየገለፅን ከዚህ በኋላ መልዕክቶቻችን የምናስተላልፈው በዚሁ ቴሌግራም ቻናል ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ሊንኩን ተጭናችሁ ቤተሰብ ሁኑ ።
https://t.me/+7LIboVIE2hY4YjJk
ለ2016 ዓ.ም አዲስ ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉን መረጃዎች ይህንን ሊንክ ተጭነው ያግኙ
ለሁሉም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ወላጆች/አሳዳጊዎች :-
//::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::://

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ ወደ መፈተኛ ጣቢያቸው /ኮተቤ ዮኒቨርስቲ/ በሰላም ገብተዋል ።

መልካም ፈተና !!
ጥብቅ ማስታወቅያ !!
::::::::::::::::::::::::::::::

የ2016 ዓ.ም የአዳዲስ እና ነባሪ ተማሪዎች ምዝገባ ከሀምሌ 10 ጀምሮ መመዝገብ እንደጀመርን ይታወቃል ሆኖም የት/ቤታችን ማህበረሰብ እንደቀድሞው የተራዘመ የምዝገባ ጊዜ ያለ መስሏችሁ እንዳትዘናጉ በተደጋጋሚ በቴሌግራም ገፃችን ገልፀንላችኋል !!

በገለፅንላችሁ መሰረት  ምዝገባው የሚቆየው እስከ ሀምሌ 30 ብቻ መሆኑን በድጋሚ እየገለፅን ከሀምሌ 30 በኋላ የሚመጡ ተማሪዎች  በየቀኑ በሚጨምር ቅጣት የሚመዘገቡ መሆኑና  እየገለፅን ላላስፈላጊ ቅጣት  እንዳትዳረጉ ከወዲሁ ልጆቻችሁን አስመዝግቡ ።

አርፍዶ የመመዝገብ ባህል አስቀርተን
ት/ቤቱ ባወጣው የምዝገባ ወቅት ብቻ ማስመዝገብ  እንለማመድ !!
አስደሳች ዜና
***

➡️❤‼️_➡️

ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ለትምህርት ቤታችን እና በአከባቢው ለሚገኙ ለሌላ ለማንኛውም ት/ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች፤
****
እንደሚታወቀው አንጋፋው ታይም አካዳሚ ላለፉት በርካታ ዓመታት በእውቀት የበለፀጉ በመልካም ሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን ሲያፈራ ቆይቷል አሁንም እያፈራ ይገኛል። በተጨማሪም መልካም ሥነ ምግባር እና አማካይ ዉጤታቸዉ ከ 95% በላይ የሆኑ በርካታ ተማሪዎችን ሙሉ ነፃ በማስተማር ለአከባቢው ማህበረሰብ የራሱን በጎ አስተዋፅኦ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።
በመሆኑም ለ2016 ዓ.ም ከእኛ ት/ቤት ሆነ ከማንኛውም ሌላ ት/ቤት አማካይ ዉጤታቸዉ ከ 95% በላይ የሆኑ እና መልካም ሥነምግባር ያላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ እንደተለመደው በነፃ ለማስተማር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች ከእኛም ሆነ ከየትም ት/ቤት ያላችሁ ነገ ሀሙስ 27/11/2015 እና አርብ 28/11/2015 ት/ቤት በመምጣት እንድታናግሩ እናሳውቃለን።
ይህ ዕድል እንዳያመልጥ ፍጠኑ....
የእኛ ተማሪ የሆናችሁ ሌላ የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤት ጓደኛ ያላችሁ ጓደኞቻችሁ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንድታሳውቁ በደስታ እንገልፃለን።
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ወላጆች/አሳዳጊዎች :-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሰላም ፈተናውን አጠናቀው ወደ ት/ቤታቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ ወላጆች ተረጋግታችሁ ቤት እንድትጠብቋቸው እየገለፅን ለተማሪዎቻችን አቀባበል አድርገን ወደየ ቤታቸው እንሸኛለን ።
በሰላም ወደየመኖሪያቸው ተሸኝተዋል ።
መልካም ውጤት ት/ቤቱ ይመኛል !!