የታይም አካዳሚ የቀድሞ ተማሪዎች መገናኛ ቻናል ‼️
419 subscribers
641 photos
8 videos
849 files
140 links
Time academy student
Download Telegram
የ2015 ዓ.ም የ3ኛ ተርም ቴስት የሚሰጥበት ቀን ኘሮግራም !!

ከግንቦት 30_ ሰኔ 2/2015 ዓ.ም
በነገው ዕለት የባህልና ቱሪዝም ባህል ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች የስም ዝርዝራቸው ከታች ተለጥፏል ።
መነሻ ቦታ ፡ ኮልፌ ወረዳ 05 አስተዳደር
ፅ/ቤት ዘነበ ወርቅ
መነሻ ሰዓት ፡ 6 ሰዓት
ትራንስፖርት ወረዳው አመቻችቷል !!

ተሳታፊ ተማሪዎች እና መምህራን በሰዓቱ በተገለፀው አድራሻ እንድትገኙ የኮልፌ ወረዳ 05 ትምህርት ፅ/ቤት አሳስቧል ።

እናመሰግናለን !!
በቅድሚያ በዛሬው ዕለት የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫል ኘሮግራም ላይ ተገኝታችሁ ለተሳተፋችሁ
የት/ቤታችን ተማሪዎችና መምህራን የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ትምህርት ፅ/ቤት ምስጋናውን ያቀረበላችሁ መሆኑና እኛም እንደኮራንባችሁ እየገለፅን ከላይ በፍላጎታቸው መሰረት እንሄዳለን ብለው ዛሬ በኘሮግራሙ ያልተገኙ ተማሪዎች ስም ዝርዝር ከታች እንደተገለፀው ነው !!

ከ9ኛ ክፍል
1.ንጉሱ አጀማ
2. ናኦል ጌታቸው
3. መልካም ሙሉቀን
4. ኤልሳቤጥ አለምነህ

ከ10ኛ ክፍል

1. አቤል ባልቻ
2. ኢክራም ዳንኤል
3. ዮናስ አሸብር

->->-> እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን !!! <- -< < -
በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
========================
👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዘዴዎች፤
------------------------------------------------
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡

👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። 

☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 

ለተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ!👏👏
ከሰኔ 07_09/2015 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና ኘሮግራም !!
ለታይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ :-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከቀን 07/10/2015 _09/10/2015 ዓ.ም ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል ሆኖም ሞዴል ፈተና መፈተን የሚችለው ከሁለት ሳምንት በፊት በነገርናችሁ መሰረት ሁሉንም የሚጠበቅባችሁ ግዴታ ተወጥታችሁ በእጃችሁ ክሊራንስ አስጨርሳችሁ ስትይዙ ብቻ ስለሆነ ከወዲሁ የሚጠበቅባችሁ ሁሉ እንድትወጡ እያሳሰብን ክሊራንስ አስፈርሞ ያላስጨረሰ መፈተን የማይችል/የማትችል መሆኑ በድጋሚ እንገልፃለን ።

መልካም የፈተና ዝግጅት ተመኘንላችሁ !!
ማሳሰቢያ : -
=======
1.ለሁሉም የ12ኛ ክፍል ተኀታኝ ተማረዎች በሙሉ ዛሬ በክፍለ ከተማ ደረጃ የተዘጋጀው ሞዴል ፈተና በት/ቤታችን እየተሰጠ ይገኛል ሆኖም የተማሪ ወላጆች የሚጠበቅባቸውን የወርሃዊና የቲቶሪያል ክፍያ የመክፈል ግዴታቸውን እንዲወጡ ት/ቤቱ በተደጋጋሚ ከወላጆች ጋር ውይይት ቢያደርግም አንዳንድ ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን ወርሃዊ እና የቲቶሪያል ክፍያ እንዲፈፅሙ ከሁለት ሳምንት በፊት የተነገራቸው ሲሆን አሁንም ይህንን ግዴታው ያልተወጣ ተማሪ በነገው ዕለት (08/10/2015) ፈተና መፈተን የማይችል/የማትችል መሆኑን ተገንዝባችሁ እንዲሁም በተረጋጋ ሁኔታ እንድትፈተኑ ት/ቤቱ በቂ ጊዜና ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን !!

2. ከላይ ለ12ኛ ክፍል የተገለፀው ሀሳብ ከ9ኛ-11ኛ ክፍሎችም የ2015 ዓ.ም ማጠቃለያ ፈተና ከመሰጠቱ በፊት ሀላፊነታችው እና ግዴታችሁን እንድትወጡ በድጋሚ እናሳስባለን ።

. እናመሠግናለን !! .
መልዕክት !!
=======

ለታይም ሁለተኛ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች በሙሉ:-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ ኘሮግራም ሀምሌ 6 /2015 ዓ.ም ሁሉም ወላጆችና የት/ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት ት/ቤቱ በደማቅ ዝግጅት ያከብራል ሆኖም ከተማሪ ወላጆች ባገኘነው መረጃ መሰረት አንዳንድ ተማሪዎች ከዚህ ውጪ ኘሮግራም ለማድረግ ለወላጆች አላስፈላጊ ወጪ (ወላጆችን በማሳመን የወጪ ብር ) እየጠየቁ መሆኑን ከተማሪ ወላጆች ስለተረዳን ከሀምሌ 6 ውጪ የሚኖር የትኛውም አይነት ኘሮግራም ከትምህርት ቤቱ እውቅና ውጪ መሆኑንና ት/ቤቱ ሀላፊነት እንደማይወስድ እያሳሰብን ወላጆችም ይህንን ተረድታችሁ ለልጆቻችሁ አስፈላጊ ግንዛቤ በመፍጠር ከት/ቤቱ ጋር መረጃዎች እንድትለዋወጡ በጥብቅ እና በአክብሮት እናሳውቃለን ።
የ2015 ዓ.ም የወላጆች በዓል ቀን ሀምሌ 6/2015 ዓ.ም ይከበራል ።
ለ12ኛ ክፍል ተመራቂ ተማሪዎቻችን በሙሉ :-
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሀምሌ 6/2015 ዓ.ም በአንተነህ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የወላጆች በዓልና የተማሪዎች ምረቃ ይከናወናል በመሆኑም የ12ኛ ክፍል ተመራቂዎች ጋዋን በተመለከተ
ት/ቤቱ ሁኔታዎቹን እንዲያመቻች የተማሪዎች ፍላጎት መለየት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ እስከ ሰኞ /03/11/2015/  ባለው ጊዜ ብቻ የጋዋን ፍላጎታችሁን
ለት/ቤቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን ይህንን ማድረግ ያልቻለ ተማሪ ቢኖር ጋዋን መልበስ እንደማይፈልግ ተደርጎ ስለሚቆጠር ት/ቤቱ ፍላጎታቸው ለት/ቤቱ ላቀረቡ ተማሪዎች ብቻ የምናመቻች መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ።
የወላጆች በዓል ቀን በ6/11/2015 ዓ.ም በአንተነህ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በደማቅ ኘሮግራሞች  ታጅቦ ይካሄዳል። በመሆኑም ሁሉም ወላጆች /አሳዳጊዎች /ተማሪዎች እና መምህራን በዕለቱና በሰዓቱ ተገኝታችሁ ሀላፊነታችሁን በተግባር እንድታሳዩን  በአክብሮት እንገልፃለን ።
ታይም አካዳሚ !!
::::::::::::::::::::::::

በተማሪዎች ባህርይ እና በተማሪዎች ውጤት ላይ በማተኮር እየሰራን እንገኛለን ነገን በማየት ዛሬ ላይ ተግተን እንሰራለን !!
ተመራጭ ት/ቤትም ነን እንሆናለንም !!

በተማሪዎቻችን ፣ በመምህራኖቻችን እና በወላጆች ኮርተናል እንኮራባችኋለን !!

ዛሬ በእጅጉ የተደሰትኩበት ቀን