TIKVAH-MAGAZINE
193K subscribers
22.7K photos
477 videos
74 files
3.42K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው።

በ +251913134524 ላይ ያግኙን።

ለማስታወቂያ @tikvahmagbot ላይ መረጃ ይጠይቁ።
Download Telegram
ኢትዮጵያ በኬንያ ለሚገነባው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለድርሻ ለመሆን ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ።

አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ አካባቢ ለመገንባት ላቀዱትና በቀን 700,000 በርመል ነዳጅ የማጣራት አቅም ለሚኖረው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከቀረበው የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ላይ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቷ ተገልጿል።

ይህንን የገለጹት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ ዴቪድ ንዲ በናይሮቢ በተካሄደ የካፒታል ማርኬት መድረክ ላይ እንደሆነ ነው ብሉምበርግ የዘገበው።

አማካሪው ከዚህ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መቅረቡን ነው የገለጹት።

አክለውም፥ ኬንያ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የ10 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷንና ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳም በፕሮጀክቱ ላይ የባለቤትነት ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን በመድረኩ ተናግረዋል።

እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል ተብሎ የሚገመተው ይህ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ አጠቃላይ ወጪው 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።

የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐግብሩ መስከረም ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመላክቷል።

@tikvahethmagazine
99🤣25👍19👏7🤔2🔥1😢1
“ቤት ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል” ብለው እያሰቡ ነው?🤔

🔥 ቴምር ሪል እስቴት | መገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ ፊት ለፊት ላይ አዲስ ዕድል! 🏠
💥40% ብቻ ከፍለው 60% ቤቱን ሲረከቡ እንዲከፍሉ እኛ አመቻችተንልዎታል!

💥 ልዩ ልዩ  የክፍያ አማራጮች
40% ብቻ ይክፈሉ፤ 10% ቅናሽ ያግኙ! ቀሪውን 60% ቤትዎን ከተረከቡ በኋላ መክፈል ይችላሉ
20% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን 80% በ3 ዓመት የግንባታ ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይክፈሉ።
100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ አለን

🏠 60 ካሬ – ባለ1 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 7,500,000 ብር
20% - 1.5 ሚሊየን
40% - 3 ሚሊየን
100% ከከፈሉ - 4,875,000 ብር

🏠 90 ካሬ – ባለ2 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 11,250,000 ብር
20% - 2.2 ሚሊየን
40% - 4.5 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 7,312,500 ብር

🏠 112 ካሬ – ባለ3 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 14,000,000 ብር
20% - 2.8 ሚሊየን
40% - 5.6 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 9,100,000 ብር

📞 ለበለጠ መረጃ +251 980 782 850
ቴምር ሪል እስቴት ለደንበኞቹ ታማኝ
13👍1
🔥የከተማችን ታላቁ የንግድ ማዕከል መርካቶ ተክለሐይማኖት መገኛቸውን ያረጉ በልዩነት ቅናሽ የተደረገባቸው የንግድ ሱቆች ይዘንላቹ መጥተናል!

👉በ 11 ፣ 16 ፣ 22 እና 32 ካ.ሜ አማራጭ ሲሆኑ

💰የዋጋ መነሻቸውም:-
👉ግራወንድ ላይ
ሙሉ ክፍያ : 4,950,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,495,000 ብር

👉1ኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 4,400,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,320,000 ብር

👉2ተኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 3,795,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,138,500 ብር

👉3ተኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 3,300,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 990,000 ብር

የሚያኙት ጥቅሞች:-
👉 በተጣራ ካ.ሜ (Net Area) ብቻ የሚሸጡ መሆናቸው
👉በ 4ቱም አቅጣጫ የመንገድ አማራጮች መኖሩ
👉 መረከቢያ ጊዜ 1 ዓመት መሆኑ
👉እስከ 15% የሚደርሱ ልዩ ቅናሾች ያገኛሉ

🔥ማሳሰብያ : ይህ ዋጋ የሚያገለግለው ቀድመው ለመጡ 20 ደምበኞች ብቻ ሲሆን ለበለጠ መረጃ እና ለሳይት ጉብኝት በ 0906926956 ይደውሉልን!
ቴሌግራም:- @Realeastateaddis
13
የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ በኩል የባንክ አገልግሎቶችን / Agency Banking ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

አሰራሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የንግድ ባንኮች በጋራ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩትን "ኢቲ-ስዊች" የክፍያ መረብ መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በ700 ቅርንጫፎች በሙከራ ደረጃ ሥራ መጀመሩና በወር ጊዜ ውስጥ በሙሉ አቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል።

በዚህም ደንበኞች የትኛውም የባንክ ሂሳብ ቢኖራቸው በፖስታ ቤት መስኮቶች በኩል ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ፣ የፍጆታ ክፍያዎችን መፈጸም እና የባንክ ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ ያስችላቸዋል።

በሌላ በኩል፣ ባንኮች ወጪ ለመቀነስ ሲሉ ቅርንጫፎቻቸውን በሚዘጉበት ወቅት የኢትዮ ፖስት ወደ አገልግሎቱ መግባት የተለያዩ አስተያየቶች እንዲነሱ አድርጓል።

አንዳንዶች የባንክ አገልግሎት ወደ ተንቀሳቃሽ ሞባይል በሰፊው እየተቀየረ ባለበት ወቅት ቅርንጫፎችን መሠረት ያደረገ አሰራር ውጤታማነቱ አጠራጣሪ እንደሆነ ሲገልጹ፤ ሌሎች ደግሞ አሰራሩ ባንኮች ባነሰ ወጪ ተዳራሽነታቸውን እንዲያሰፉ ይረዳል ሲሉ ያነሳሉ።

የዚህ ዘገባ ባለቤት አዲስ ፎርቹን ነው።

@tikvahethmagazine
58👍11🤔10👏5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“አይፎን 15” ካልገዛችሁልኝ ያለው ወጣት ራሱን ጨምሮ የቤተሰቡን ነፍስ ቀጥፏል።

በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ዕድሜው 18 ዓመት የሆነ ወጣት አዲስ “አይፎን 15” (iPhone 15) ስልክ እንዲገዛለት ያነሳው ጥያቄ ቤተሰቦቹ ባለመቀበላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በመውጣት እራሱን ከገደል አፋፍ ላይ አቁሞ ቆይቷል።

ወላጆቹ ለሰዓታት ሲለምኑት እና ለማሳመን ሲሞክሩ ከቆዩ በኋላ አባቱ ሊያድኑት ወደ እሱ ሲጠጉ፣ ወጣቱ አባቱን ጨብጦ በመሳቡ ሁለቱም ከገደል ወድቀው ህይዎታቸው አልፏል።

ልጇን እና ባለቤቷን በድንገት ያጣችው እናቷም በደረሰባት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤ ከተመሳሳይ የገደል አፋፍ ላይ እራሷን በመጣሏ የሷም ህይወት ማለፉ ተዘግቧል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት በዛሬው ዕለት በርካቶች ሲመለከቱት፥ በወጣቶች የአዕምሮ ጤና ዙሪያ ያለውን ስጋት አጉልቶ ያሳየ ስለመሆኑ ተነግሯል።

#ማሳሰቢያ ፡ የምትመለከቱት ቪዲዮ ስሜት የሚረቭሽ ይዘት አለው።

@tikvahethmagazine
😢21754💔26🤯12🤣7🤔5🤬4👍2👏1
#Somalia 🇸🇴

በሶማሊያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት 2026 እስከ 1.9 ሚሊዮን የሚደርሱ ህፃናት ለከባድ የምግብ እጥረት እንደሚጋለጡና ከእነዚህም መካከል ግማሽ ሚሊዮን ያህሉ ለሞት በሚዳርግ አጣዳፊ የምግብ እጥረት ሊጠቁ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መብቶች ተሟጋች ድርጅት (UNICEF) አስታውቋል።

ለሀገሪቱ ይደረግ የነበረው የሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት እስካሁን 205 የጤና እና የምግብ እርዳታ መስጫ ማዕከላት የተዘጋሩ ሲሆን፤ በቀጣይም እስከ 618 የሚደርሱ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሊዘጋጉ ይችላሉ ተብሏል።

አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት የሚሰጡትን እርዳታ በማቋረጣቸው እና በመቀነሳቸው ምክንያት ለሶማሊያ ይደረግ የነበረው የፋይናንስ ድጋፍ ከ80 በመቶ በላይ ቀንሷል።

ሀገሪቱ በከባድ ድርቅ፣ በግጭት፣ በመፈናቀል እና ከኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ በጨመረው የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ምክንያት የከፋ የአየር ንብረት እና የኢኮኖሚ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች።

Credit : Reuters

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢4239👍1
“ቤት ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል” ብለው እያሰቡ ነው?🤔

🔥 ቴምር ሪል እስቴት | መገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ ፊት ለፊት ላይ አዲስ ዕድል! 🏠
💥40% ብቻ ከፍለው 60% ቤቱን ሲረከቡ እንዲከፍሉ እኛ አመቻችተንልዎታል!

💥 ልዩ ልዩ  የክፍያ አማራጮች
40% ብቻ ይክፈሉ፤ 10% ቅናሽ ያግኙ! ቀሪውን 60% ቤትዎን ከተረከቡ በኋላ መክፈል ይችላሉ
20% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን 80% በ3 ዓመት የግንባታ ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይክፈሉ።
100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ አለን

🏠 60 ካሬ – ባለ1 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 7,500,000 ብር
20% - 1.5 ሚሊየን
40% - 3 ሚሊየን
100% ከከፈሉ - 4,875,000 ብር

🏠 90 ካሬ – ባለ2 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 11,250,000 ብር
20% - 2.2 ሚሊየን
40% - 4.5 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 7,312,500 ብር

🏠 112 ካሬ – ባለ3 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 14,000,000 ብር
20% - 2.8 ሚሊየን
40% - 5.6 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 9,100,000 ብር

📞 ለበለጠ መረጃ +251 980 782 850
ቴምር ሪል እስቴት ለደንበኞቹ ታማኝ
9🤣1
ፎቶ አንስተው በመላክ ብቻ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ

JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family

ET Creatives
5👍2
ተጨማሪ 2ሺህ 494 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

🟢 189 የሚሆኑት እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች ናቸው!

‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2ሺህ 2494 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 312 ወንዶች፣ 163 ሴት እና 19 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል189 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

‎መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

‎መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
27
የብሬክስሩ አሻሚው የንግድ ሞዴል፤ ሌላው የፒራሚድ ስኪም?

"ብሬክስሩ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር (Breakthrough Trading S.C.)" በተመለከተ የ "ሪፖርተር" ጋዜጣ እንግሊዝኛ ዕትም ሰፊ የምርመራ ዘገባ ይዞ ወጥቷል።

በዚህ ዘገባ ኩባንያው ባለፉት 6 ዓመታት ከ100,000 በላይ ሰዎችን ማሰልጠኑን ቢገልጽም፣ የኢትዮጵያ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን (ETA) ግን ለፕሮግራሞቹ ምንም ዓይነት እውቅና ወይም ፈቃድ እንዳልሰጠ ይገልጻል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሚልኪያስ አየለ ድርጅቱ የንግድ ፈቃድ ያለውና ግብር የሚከፍል በመሆኑ የሰውነት ማበልጸግ ስልጠና መስጠት ይችላል ቢሉም፣ ፕሮግራሞቹን በባለሥልጣኑ ዘንድ ያላስመዘገቡ መሆኑን አምነዋል።

በተጨማሪም በኩባንያው ሰነዶች ላይ NLP እና ሃይፕኖቴራፒ ስልጠና እንደሚሰጥ ቢጠቀስም፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ግን በነዚህ ዘርፎች ላይ አሰልጣኝ እንደሌላቸውና ስልጠና እንደማይሰጡ ተናግረዋል።

ዘገባው ኩባንያው ከ100,000 ሰልጣኞች መካከል ስንቶቹ ዘላቂ ስኬት ላይ እንደደረሱ የሚያሳይ የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለመቻሉንም ያመላክታል።

ስለ ኩባንያው የቢዝነስ ሞዴል በሚያሳየው ክፍል፣ ሰልጣኞች ከ3,800 እስከ 52,000 ብር የሚያስከፍሉ ከአምስት በላይ የስልጠና ደረጃዎችን እንደሚገዙ ይጠቅሳል።

ስልጠናውን ያጠናቀቁ ሰዎች አዳዲስ ገዢዎችን ሲመልመሉ ከ10% እስከ 19% የሰንሰለት ኮሚሽን፣ ከ8% እስከ 15% የቡድን ማሳደጊያ ክፍያ እና በነጥብ የተሰሉ ሽልማቶችን ያገኛሉ።

በኩባንያው ሰነዶች ላይም እስከ 500,000 ነጥብ (ከ25,000 እስከ 500,000 ዶላር ግምት ያለው)፣ የመኪና እና የውጪ ጉዞ ማበረታቻዎች ተቀምጠዋል።

ይህ አሰራር አዳዲስ ሰዎችን በማስገባት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፣ በንግድ ውድድርና ደንበኞች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2005 አንቀጽ 22(6) ከተከለከለው "የፒራሚድ ስኪም" ጋር እንደሚመሳሰል የሕግ ባለሙያዎች ይሞግታሉ።

በተጨማሪም የኩባንያው የውስጥ ደንብ ከደንበኞች ለሚነሱ አቤቱታዎች ተጠያቂነቱን ወደ አባላት/መልማዮች የሚያዞር መሆኑ ተጠቅሷል።

በመጨረሻም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለስልጠና አገልግሎት የብቃት ማረጋገጫ እንደማይጠይቅ ቢገልጽም፣ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን (ETA) ክትትል አድርጎ ጥሰት ካገኘ የንግድ ፈቃዱ ሊታገድ እንደሚችል መግለጹ በዘገባው ተካቷል።

@tikvahethmagazine
137👏29🤣14👍12🤔7😢4
🔥 ታላቅ የቅድመ-ሽያጭ ቅናሽ — ቡልጋሪያ!

​በካዛንቺስ እና እንግሊዝ ኤምባሲ ያሳየነውን ስኬት ተከትሎ፣ በቡልጋሪያ የሚገኘውን አዲሱን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ለመጀመሪያዎቹ 10 ደንበኞች በ 25% ቅናሽ ይዘንላችሁ ቀርበናል!

​የቤት እና የንግድ ሱቅ አማራጮች፦

👉 ​1 መኝታ (81 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 732,066 ብር | ሙሉ ክፍያ 7,320,662 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 5,490,496 ብር)

👉​ 2 መኝታ (111 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 999,757 ብር | ሙሉ ክፍያ 9,997,573 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 7,498,179 ብር)

👉​ 3 መኝታ (169 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 1,639,541 ብር | ሙሉ ክፍያ 16,395,410 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 12,296,557 ብር)

👉​ የንግድ ሱቆች (25 - 75 ካሬ)፦ ከ 3 ሚሊዮን ብር ጀምሮ

🏢  ​የክፍያ እና የህንፃው ልዩ ባህሪያት፦

🏦 ​የባንክ ብድር፦ 50% በባንክ በ20 ዓመት ረጅም ጊዜ ክፍያ ተመቻችቷል።

📌 በPost-Tensioning ቴክኖሎጂ የተገነባ፣ ዋና ገንዳ፣ ጂም፣ ስፓ፣ የልጆች መጫወቻ እና ማራኪ የከተማ እይታ ያለው።

🚀 ዕድሉ ሳያመልጥዎት አሁኑኑ ይመዝገቡ!
📞 ስልክ፦ 0919994818
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14😢1
.
ሁሉንም እቃዎች ፖስት ስላደረግናቸው የሚፈልጉትን ያገለገለ እቃ ባሉበት ሆነው በፎቶ አይተው የወደዱትን በአካል በመምጣት አይተው እና በድንብ መርምረው መግዛት ይችላሉ።

የእቃዎቹም ዋጋ አብሮ ፖስት ስለተደረገ ዋጋ ማወዳደር ይችላሉ።

JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family

ET Creatives
5
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ተገለጸ።

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

201 ሜትር ርዝመት ያለው የግድብ ግንባታው 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የአፈር ቁፋሮ በማካሄድ አጠቃላይ ግድቡ ከሚፈልገው 7 ነጥብ 72 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ውስጥ 81 ነጥብ 2 በመቶው ማለትም 6 ነጥብ 27 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት (RCC) ሥራ መከናወኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መብራቱ ተሾመ ተናግረዋል።

የኃይል ማመንጫ ቤቱ የቁፋሮ ሥራ እንዲሁም የሲቪል ሥራው የመጀመሪያ ደረጃ የኮንክሪት ሙሌት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራውን በታቀደው ጊዜ ለማጠናቀቅ ዕቃዎች በበርካታ ፋብሪካዎች እንዲመረቱ መደረጉንም ጠቁመዋል።

የፋይናንስ አቅርቦት በተለይም የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ተያያዥ ችግሮች በግንባታው ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን ያስታወሱት ኢንጂነር መብራቱ፣ አሁን ላይ ተቋሙ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በራሱ በመሸፈኑ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል ብለዋል።

የግድብ ግንባታውን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ በጥቅምት 2021 ዓ.ም የመጀመሪያውን ተርባይን ወደ ኦፕሬሽን ለማስገባት እየተሠራ ነውም ተብሏል።

Source : EEP, EBC

@tikvahethmagazine
65👍6👏3😢3🤔1
ሲንጋፖር የውልደት መጠንን ለማሳደግ ለወላጆች የ55 ሺህ ዶላር ድጎማ ልታደርግ ነው

የሲንጋፖር መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የውልደት መጠን ለማሻሻል እና የሕዝብ ቁጥር ማነስን ለመግታት ለወላጆች እስከ 55 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ድጎማና ማበረታቻ ለመስጠት አቅዳለች።

ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በአንድ ሴት የሚመዘገበው የውልደት መጠን ወደ 0.97 ዝቅ በማለቱና ይህም ለሀገሪቱ የወደፊት የኢኮኖሚና የሰው ኃይል እድገት ስጋት በመፍጠሩ፣ አዲሱ ማበረታቻ የወላጆችን የልጅ ማሳደግ ወጪ ለመሸፈን የተዘጋጀ ነው።

ድጎማው ቀጥተኛ የገንዘብ ስጦታን፣ ለልጆች ትምህርትና ሕክምና የሚሆን የቁጠባ ሂሳብ ድጋፍን እንዲሁም የታክስ ቅናሾችን የሚያካትት ነው ተብሏል።

ይህ እርምጃ ሲንጋፖር ቀደም ሲል ታደርጋቸው የነበሩ የማበረታቻ አካሄዶችን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገ ሲሆን፣ ሀገሪቱ ያጋጠማትን የስነ-ሕዝብ ቀውስ ለመቀነስና ወጣቶች ልጅ የመውለድ ፍላጎታቸውን እንዲጨምሩ ለማድረግ ያለመ ነው።

@tikvahethmagazine
52👍6🤯3🤔1🤣1
#እንድታውቁት : "ካናዳ፤ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም!" - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" ጋር በክህሎት ልማትና በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ  በቅንጅት መሥራት የሚያስችለንን ስምምነት በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር መፈራረሙን መግለጹ ይታወሳል።

ስምምነቱ ዜጎችን በክህሎት አብቅቶ ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ለማቅረብ የሚረዳና በካናዳ መንግሥት ሙሉ ዕውቅና ያለው በመሆኑ፣ ወደ ካናዳ የሚደረገውን የዜጎች ስምሪት በሕጋዊ መንገድ ለመምራት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ተብሎለት ነበር።

ይህን ተከትሎ በርካታ አሳሳች ማስታወቂያዎች ሲሰራጩ ቆይተዋል። በተለያየ ጊዜም ከሚኒስቴሩ ጨምሮ ወደ ካናዳ የሥራ ስምሪት አለመጀመሩን ሲገለጽ ቆይቷል።

ይህን አስመልክቶም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት "ካናዳ፤ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም!" ሲል ገልጿል።

ከዚህ ቀደም የተፈጸመው ስምምነትም በዋነኛነት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልጿል።

ስምምነቱም በዋነኛነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ብቻ ያተኩራል፦

• ከካናዳ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ተማሪዎችን በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ በሚፈለጉ ክህሎቶች ማሰልጠን፤

• ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በካናዳ በሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የነፃ ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማመቻቸት።

ከዚህ ስምምነት ውጪ ሚኒስትሩ "ሚኒስቴሩ ወደ ካናዳ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ጀምሯል" በማለት የተሳሳተ መረጃ ከሚሰጡ፤ "ወደ ካናዳ እንልክዎታለን" በማለት ከፍተኛ ገንዘብ ከሚጠይቁና "ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ውክልና ተሰጥቶናል" ከሚሉ አጭበርባሪዎች ዜጎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

አያይዞም፥ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ስምምነት ወደ ተፈራረመችባቸው ሀገራት በህጋዊ መንገድ ዜጎችን በመሰማራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ሀገራቱም ፦

🇸🇦 ሳውዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ
🇯🇴 ጆርዳን
🇶🇦 ኳታር
🇱🇧 ሊባኖስ
🇰🇼 ኪዌት ናቸው።

ሚኒስቴሩ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ በ9138 በነፃ የስልክ መስመር ወይም info@mols.gov.et  እና በአቅራቢ በሚገኝ የህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
51👍7🤔1
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ማቀዳቸውን አስታወቁ።

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ካይነሩጋባ በፈረንጆቹ 2031 በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል።

ጄኔራል ሙሁዚ ቀደም ሲል በ2026 በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ አባታቸው ዮዌሪ ሙሴቬኒ በድጋሚ ለመወዳደር በመወሰናቸው ምክንያት ውሳኔያቸውን ወደ 2031 ማራዘማቸውን ገልጸዋል።

ከ1986 (እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር) ጀምሮ ሀገሪቱን በፕሬዚዳንትነት በመምራት ላይ የሚገኙት የ81 ዓመቱ ዮዌሪ ሙሴቬኒ፣ ስልጣናቸውን ለልጃቸው ለማስረከብ መንገድ እያመቻቹ ነው የሚለው ግምት በስፋት የሚነሳ ቢሆንም አባታቸው ግን ይህንን ሲያስተበድሉ ቆይተዋል።

@tikvahethmagazine
🤣6920🤯4