TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BeledHawo

በደቡባዊ ሶማሊያ ፤ ጌዶ ክልል ፣ በሌደሀዎ በተባለ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ሶማሊያዊ መገደላቸውን ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

በዚህ ምክንያት በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል።

ታጣቂዎቹ ሌሊት ኢትዮጵያውያን ወደ ሚኖሩበት ቤት በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 3 ሴቶች እና 3 ወንዶችን ሲገድሉ 1 ሶማሊያዊም መገደላቸው ተነግሯል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካይ በሰጡት ቃል ፤ ቅዳሜ ሌሊት 6 እሁድ 1 በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል ብለዋል።

" ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ ፣ እናት እና አባቷ ተገድለውባት ብቻዋን የቀረች ሕጻንም አለች " ሲሉ አክለዋል።

" የተገደሉት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰው በሥነ ሥርዓት ቀብራቸው እንዲፈጸም እንፈልጋለን። መንግሥት ይህን ማድረግ ይችላል። ለተገደሉትም ፍትሕ እንዲሰፍንም እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።

ጥቃቱ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።

የበለደሀዎ አስተዳዳሪ አብዲራሺድ አብዲ ፤ ግድያው ሌሊት 9 ሰዓት መፈጸሙን እንደታወቀ አመልክተዋል።

ግድያ መፈፀሙ የታወቀው የአካባቢው የፀጥታ ባልደረቦች የተኩስ ድምጽ ከሰሙ በኋላ ሲሆን 7 ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን አስረድተዋል።

" ማቾቹ በአጠቃላይ ለሥራ የመጡ ስደተኞች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው ሆስፒታል የሚሠራ አንድ ዶክተር በሰጠው ቃል በጥቃቱ የተገደሉ የ6 ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን አረጋግጧል።

በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 6 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልጿል።

ምንም እንኳን እስካሁን ከግድያው ጀርባ ማን እንዳለ ያልታወቀና ኃላፊነት የወሰደም አካል የሌለ ቢሆንም የአካባቢው አስተዳዳሪ " ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ገዳዮቹ #የአልሸባብ አሸባሪዎች ናቸው " ብለዋል።

" እስካሁን አልተያዙም። ለምን ስደተኞን ዒላማ አደረጉ ለሚለው ጥያቄ፣ ይህ ግድያ በመላው አገሪቱ ከሚፈጸመው ግድያ የሚለይ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ ሶማልኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia