TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ውጤትን የተመለከተ መግለጫ!

የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ምክትል ዳይሬክተሮች ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ እና አቶ መሳይ ደምሴ፣ እንዲሁም የየክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ይልቃል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተከታታይ #ውጤቱን በተመለከተ በጋራ በተላለፈው #ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁም መሰረት በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያጋጠመ ችግር መኖሩን በተለይ በደንብ ጥሰት ዙሪያ #በማረጋገጫ የተያዘባቸው ተማሪዎች ውጤት መሰረዙ እና በደንብ ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በየደረጃው ተጠያቂ የሆኑበት ሁኔታን እንዳለ ሆኖ፤ ፈተናዎቹ ከሰጡባቸው ቀናት ሀሙስና አርብ ማለትም በ6 እና 7/10/2011ዓ.ም ከተሰጡት ፈተና ውጤቶች በተለየ ከቅዳሜና እሁድ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም በ10 እና 11 10/2011ዓ.ም በተሰጡት ፈተናዎች በግልጽ የታየ የውጤት ግሽበት መኖሩ በመረጋገጡ የዩንቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በአራቱ የትምህርት ዓይነቶች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ እነዚህም እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ጂኦግራፊ ለማህበራዊ ሳይንስ ይሆናሉ፡፡

ይህም ሲሆን ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ሊገነዘቡ የሚገባቸው ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመምህርነት ሙያ ለመማር ከመረጡ ተማሪዎች ውጪ ለዩንቨርስቲ መግቢያ ብቻ የሚያገለግልና የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተብለው ዩንቨርስቲ እንደሚገቡና ከአንድ ዓመት የፍሬሽማን ኮርሶች በኋላም በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት የፈለጉትን የትምህርት ፊልድ መርጠው መማር የሚችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የተከሰተውን #ግሽበት በተመለከተም የማጣራት ሂደቱን የሚያካሂድ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ያሳወቁ ሲሆን ተጠያቂው አካል አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በመግለጫው ማጠቃለያም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ እንደገለጹት የመቁረጫ ነጥቡን በተመለከተ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚታይላቸው መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት የተያዙት የተማሪዎች ውጤቶች #እንደሚለቀቅ ጨምረው አሳውቀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia