TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ለገንዘብ ተብሎ በግብረሰዶማውያን እና በስደተኞች ጥገኝነት ጥየቃ (asylum) ጉዳይ ሀገሪቱ ያላት ፖሊሲ አይቀየርም " - ሀንጋሪ

በመጪው ሰኔ የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ይደረጋል ተብሎ እቅድ ተይዟል።

ከምርጫው ጋር ተያይዞ ስለ ግብረሰዶማውያን እና ስለስደተኞች እንዲሁም ስለሌሎች ጉዳዮች የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ከአንድ የሀገር ውስጥ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ ብዙ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ይህንን ወቅት እንደምንም ብለው መትረፍ ይፈልጋሉ ብለዋል።

" ምርጫ በሌለበት ጊዜ ማስመሰል ትችላላችሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ምርጫ ሲደረግ ግን ከህዝቡ ጋር መነጋገር አለባችሁ። ነገር ግን ሰዎች ብራስልስ ውስጥ የሚጠቀሙትን የሌቦች ቋንቋ አይረዱም። የህዝብን ቋንቋ መናገር መጀመር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

ንግግራቸውን ቀጠል አድርገው፤ " የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ፤ የብራሰልስ አካላት በሃንጋሪውያን ላይ ያላቸውን ነገር ማለትም ስደተኞችን ወደ ሀገር ውስጥ እንደማናስገባ እና የግብረሰዶማውያን አክቲቪስቶችን ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲገቡ እንደማንፈቅድ በመጨረሻ አምነዋል " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የግብረሰዶማውያን ፕሮፓጋንዲስቶችን ወደ ትምህርት ቤቶቻችን እንድናስገባ እንዲሁም ስደተኞችን ወደ ሀገራችን እንድናስገባ የሚያደርግ በዓለም ላይ ምንም አይነር ገንዘብ የለም " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

ለገንዘብ ተብሎ በግብረሰዶማውያን እና በስደተኞች ጥገኝነት ጥየቃ (asylum) ጉዳይ ሀገሪቱ ያላት ፖሊሲ እንደማይቀየር የሀገሪቱ መንግሥት አሳውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ከግብረሰዶማውያን እና ከስደተኞች መብት እንዲሁም #ከአካዳሚክ_ነፃነት ጋር በተያያዘ ብዙ ለሀንጋሪ ሊሰጥ የሚገባውን ብዙ ቢሊዮን ዩሮ (20 Billion EUR) ይዞባታል።

እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባን ግብረሰዶማዊነትን እና የፆታ ለውጥን በትምህርት ቤቶች ውስጥ #ሊያስተዋውቁ ይችላሉ የሚባሉ ነገሮችን የሚከለክል ህግ በ2021 አጽድቀዋል።

ህጉ ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስር ቤት መወርወር ያደርሳል።

ይህ ህግ የፀደቀው ህፃናትን ከ " ከግብረሰዶማውያን ፕሮፓጋንዳ " መጠበቅ በማስፈለጉ ሲሆን በዚህ ህግ ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር አለመግባባት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። የአውሮፓ ህብረቱም ከዚህና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ 20 ቢሊዮን ዩሮ ገንዘብ ይዞባታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia