TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦
➡️ 61  ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣
➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣
➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

" የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

በአሜሪካ በተካሔደ ዓለም አቀፍ የሮቦፌስት ውድድር ታዳጊ ኢትዮጵያውያን የሮቦቲክስ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆኑልን።

በውድድሩ 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን በተለያዮ ዘርፎች የተሳተፉ ሲሆን ከ10 ዓመት በታች በሮቦፓሬድ ምድብ የተወዳደረው ታዳጊ ማሸነፉ ተሠምቷል።

ሌላኛው ታዳጊ ተወዳዳሪ ከ14-16 ዓመት ምድብ ተሳትፎ ስፔሻል አዋርድ ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

በየውድድሩ ከ1-3 ድረስ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Via @tikvahuniversity
#GondarUniversity

ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ #በተለያየ_ጊዜ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ #አንጋፋ የሚባሉ ምሁራን ፤ መምህራንን ፣ ሰራተኞችን ፣ ተመራቂ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው ታላቅ #ባለውለታ የሆኑ አባትን በሞት ተነጥቋል።

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እነማንን #በሞት ተነጠቀ ?

🕯አባሆይ አሰፋ ዘለቀ🕯

የመሬት ርስታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ካበረከቱት 59 አርሷደሮች መካከል አንዱ ነበሩ። በ1963 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ቁጥር መጨመር እና የሚሰጠውም የትምህርት ዓይነት እየሰፋ በመምጣቱ ግቢውን ወደ ማራኪ አካባቢ ማስፋፋት ሲፈልግ አባሆይ አሰፋ ዘለቀ ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን በማራኪ ከፍተኛ ቦታ አካባቢ የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ለማስፋፊያ እንዲሆን በመፍቀድ ትውልድ እንዲቀረጽበት በማድረግ ዘመን ማይሸረው አበርክቶ አድርገዋል፡፡ በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

🕯ፕሮፌሰር ሞገስ ጥሩነህ🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ መምህር ፣ ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ።

🕯ዶ/ር ሰለሞን ይርዳው🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ ባልደረባ ነበሩ። ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በህክምናው ሙያ በመተማ ሆስፒታል አገልግለዋል። ከ1992/93 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሙያቸው አገልግለዋል። በማስተማርም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በጤና እክል ህይወታቸው አልፏል።

🕯መምህር ደመቀ ደሱ 🕯

አንጋፋ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ነበሩ። በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ ለ40 ዓመታት ገደማ  በማስተማር ሙያ እንዲሁም በትምህርት ክፍል እና በዲን ኃላፊነት አገልግለዋል።

🕯አቶ ፍስሃ ሞሴ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም Nutrition & Dietetics Department ውስጥ የChief laboratory Technical Assistant ባለሙያ ነበሩ። ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄዱበት በደንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል።

🕯አቶ አታለል ምስጋናዉ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚዮሎጂ ት/ክፍል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ መምህርና በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነበሩ። በ31 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

🕯ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ🕯

የኪነህንፃ / #Architecture / ተመራቂ ተማሪ ነበር። የትንሳዔ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር ባሄደበት ከፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ነበር።

🕯አቶ ሙሉአለም ይትባረክ🕯

በህክምናና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ የተማሪዎች ምኝታ ቤት አስተባባሪ ነበሩ። በህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አጠቃላይ 8 አንጋፋ ምሁራን ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ ተማሪ እንዲሁም የተቋሙን ባለውለታ ታላቅ አባት በሞት ተነጥቋል።

የጤና እክል ፣ ድንገተኛ አደጋ ፣ የመኪና አደጋ የህልፈተ ህይወት መንስኤዎቹ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ካገኘው መረጃ ተረድቷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር " - ጠንካራው የይቅርታ ሰዉ ዳግማዊ አሰፋ (ዳጊ)

የህግ ባለሞያና ደራሲ ዳግማዊ አሰፋ ከዓመታት በፊት በሀዋሳ ከተማ በእሱ እና በጓደኛው እጅ ላይ ከነበረ የፍትህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ጉቦ አንቀበልም !! " በማለቱ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መጎዳቱ ይታወሳል።

በዚህ አደጋ ጠንካራ የወጣት እጆቹ አልታዘዝልህ ብለዉታል። በአከርካሪዉ ዙሪያ ያሉ ነርቮች መጎዳትም ቆሞ እንዳይሄድ እንቅፋት ሆነዉበታል።

በዚህ ምክኒያት በሰው እጅ መብላቱ መልበሱ እና መንቀሳቀሱ ፈተና ቢሆንበትም ዛሬም ተስፋው ከሱ አልፎ ለሰዎች ይደርሳል።

ያልተሰበረው መንፈሱ የተሰበሩትን ይጠግናል ፤ ያልወደቀው ምራሉም የወደቁትን ያነሳል።

በዚህ ትጋቱ ያልተገታዉ ዳግማዊ ከህመሙ ጋር እየታገለ ስቃዩን እየተሰቃዬም ቢሆን አርፎ መቀመጥን አልወደደም ሁለት መጽሀፍት ለተደራሲያን አብቅቶ ለብዙዎች ህይዎት መቃናት ምክኒያት ሆኗል።

በዚህ ዓመትም ሌላ መጽሀፍ ሊያስመርቅ እየሰራ ነው። የቀደሙ ሁለቱ መጽሀፍትም በአፋን ኦሮሞ ታትመዉ ለመዉጣት ጫፍ መድረሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከምንም በላይ ለሰዎች መትረፍ ሲችል የሰዎችን ድጋፍ ይፈልግ ዘንድ ብርቱ ክንዶቹ ዝለው ስራዎቹን መከወን ያቅታቸው ዘንድ ምክኒያት የሆነውን ሰው " ይቅር ብየሀለሁ " ማለቱ ለትንንሽ ጥፋት ይቅርታ ማድረግ ለከበዳቸዉ ሁሉ ታላቅ ትምህርት የሰጠ ሰው ነው።

ጠንካራው ዳግማዊ ከሁለት ዓመት በፊት ውጭ ወጥቶ መታከም ከቻለ መዳን እንደሚችል ሀኪሞች ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ተደስተዉ ጎ ፈንድሚ ቢያቋቁሙም ወቅቱ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገራችን ችግር ላይ የነበረችበት ወቅት  በመሆኑ እንዳስቆመው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

" አሁን ላይ  ' ጎፈንድሚውን እንጀምር  ዘንድ ፈቃድህን ብቻ ስጠን 'ላሉኝ ጓደኞቼ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ "  ብሏል።

ድኖ ለብዙዎች መትረፍ ሲችል ' ሀገሬ ችግር ላይ ናት " ብሎ የዘገየዉ ዳግማዊ ምንም እንኳን ብዙ ችግሮቹን " ወዳጆቼን አላስጨንቅም " ብሎ ቢደብቅም በቶሎ መታከም እንዳለበት ግን አሁን ላይ ብዙ ምልክቶችን አሳይቷል።

ይህ ተከትሎም ሁሉም ደጋግ ኢትዮጵያውያን እገዛ እንዲያደርግለት ወዳጆቹ እየተረባረቡ ይገኛሉ።

ዳግማዊ ፥ " ' 2 ሺህ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ሁለት ሁለት መቶ ሰው ይዘዉ የአንድ ማኪያቶ የሚሆን 57 ብር በማዉጣት ያሳክሙሀል ' ብሎ ወዳጄ መምህር ወሌ ሀሳቡን ጀምሮታል " ብሏል።

" ዳግማዊ ገንዘቡ ተሰብስቦልህ ታክመህ ስትድን በእጆችህ ቀድመህ ልትሰራ የምታስበዉ ምንድን ነው ? " በማለት የቲክቫህ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ጥያቄ አቅርቧል።

ከረዥም ዝምታ በኋላ ፦

" አይገርምህም አስቤዉ አላዉቅም ... ግን እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር። "

ዳግማዊ አሰፋን ማገዝ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያላችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዉያን ፦
በጎፈንድሚ 👉 https://gofund.me/d93d0840
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 👉1000310977938
በዳሽን ባንክ 👉 5016527877077
በአቢሲንያ ባንክ 👉 39796821 በኩል ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

ስልክ እንፈልጋለን ለምትሉም ፦ 0909888857 ላይ መደወል ትችላላችሁ።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን…
#Update

ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም ደግሞ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰዉ  ፥ " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መቃጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር " ET154 " ሚያዝያ 29/2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን እና አውሮፕላኑ በሰላም ቦሌ ኤርፖርት ማረፉን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
“ 20 እናቶች በደም እጦት ሕይወታቸው አልፏል ” - ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል

ከ60 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሕዝቦች የሚገለገሉበት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ባጋጠመው ከፍተኛ የደም እጥረት ሳቢያ በተለይ እናቶች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

ላጋጠመው የደም እጥረት ምክንያቱ የደም ባንክ አለመኖር መሆኑን የገለጸው ሆስፒታሉ በዚህም ደም የሚሹ ታካሚዎች ለሕልፈተ ሕይወት እየተዳረጉ መሆኑን አስረድቷል።

የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ኢያሱ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያና ለሌላ አንድ ሚዲያ በሰጡት ቃል ፣ “ በ6 ወራት ውስጥ በተከሰተው የደም እጦት ሳቢያ 20 እናቶች ሕይወታቸው አልፏል ” ብለዋል።

የደም ባንክ እንዲቋቋም ሆስፒታሉ ለጤና ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ደም ባንኩን ማቋቋም እንዳልተቻለ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከደም እጥረቱ ባሻገር በሆስፒታሉ በርካታ የወባ ታካሚዎች በመኖራቸው መጨናነቅ እንደፈጠረ፣ ሆስፒታሉ የምርመራ ግብአቶችን ጨምሮ የኦክስጂን እጥረት እንደፈተነው ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቃቸው አንድ የጤና ሚኒስቴር ፒአር ባለሙያ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ፣ “ እኔ የፒአር ባለሙያ ነኝ የሚመለከተውን ነው እንጂ የማገናኝህ መልስ አልሰጥህም ” ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የተቋሙ አካላት ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia