TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ መምህራን እየቆዘሙ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ ”  - ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለሚነሱ ደመወዝን መሠረት ያደረጉ ቅሬታዎች ትልቁ መንስኤ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የማኅበሩ ፕሬዜዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ምን አሉ ?

Q. በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መምህራን የሚያነሷቸው ቅሬታዎች በዚህ ዓመት ብቻ የተስተዋሉ ሳይሆን ሰንበትበት ያሉ ቢሆኑም መፍትሄ ሳይሰጣቸው አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው። ለምን ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ?

ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

“ ልክ ነው። የመልካም አስተዳደር ችግር ነው። ይሄ የመልካም አስተዳደር ችግር አገራዊ እየሆነ ነው። መምህራንም የዚህ ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል። የግምገማ ቼክ ሊስት መደረግ አለበት ብለን ከሚመለከተው ጋር እያወራን ነው።

በተለይ መምህራን ላይ የሚከሰተው ችግር ከትውልድ ጋር የተያያዘ ነው። መምህራን እየቆዘሙ፣ እያዘኑ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ። ችግሩ በፍጥነት መታረም አለበት። ”

Q. “ የመልካም አስተዳደር ችግር ” ሲሉ ምን ለማለት ነው ? ግልጽ ቢያደርጉት ?

ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

“ አንዱ ክፍያ ነው። መቼም መምህራን የመንግስት ሠራተኞች ናቸው። የወር ደመወዝ በጊዜ ማግኘት መቻል አለባቸው።

ለልማት ሲባል መምህራንን #ሳያሳምኑ ደመወዝ የመቁረጥ አይነት ቅሬታዎች አልፈው አልፈው ይመጣሉ። ከአብዛኞዎቹ በጥቂቱ እነዚህ ናቸው።

እነዚህን ችግሮች በመሠረታዊነት መፈታት ቢቻል ሌሎቹ ደግሞ በሂደት ይፈታሉ። ”

Q. ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ተፈናቃይ መምህራንን በተመለከተ ተቋምዎ ያለው መረጃ ምንድን ነው ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው ? ስንት መምህራን እንደተፈናቀሉ ተቋምዎ ያውቃል ?

ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

“ በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ። በዚህም የተፈናቀሉ ተማሪዎችና መምህራን ይኖራሉ።

በተቻለ መጠን ሰላም ወርዶ ወደ ቦታቸው ተመልሰው ስራቸውን እንዲሰሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረግን ነው። ”

ፕሬዝዳንቱ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የሰጡትን ማብራሪያ ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-10

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በቴሌብር የአየር ሰዓት በመሙላት ተጨማሪ ያግኙ!

ከዚህ በፊት ከነበረው የ 15 ብር፣ የ100 ሜ.ባ እና 10% ስጦታ በተጨማሪ በቴሌብር የአየር ሰዓት በመሙላት እስከ 25% ተጨማሪ ያግኙ!

መተግበሪያውን ከ http://onelink.to/fpgu4m ይጫኑ፤ ኑሮዎን ያቅልሉ!


#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba

በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን / ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ #ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 " አማረ እና ቤተሰቦቹ " በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል ተይዘዋል።

አሁን ላይ የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ፦
- ሮሄ፣
- ልዩነት፣
- ጣዕም፣
- አዲስ አለም፣ 
- ዘይቤ፣
- ህይወት፣
- እይታ፣  እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ ነበር።

ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፊ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።

ከላይ ከተጠቀሱት 8 የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ #ክህሎት እና #ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫ ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራ ሂደት ተረጋግጧል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች #ገንዘብ_በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች 3 ሰዎችን ፖሊስ አግኝቷል፡፡   
 
መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ  እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
ስለብፁዕነታቸው የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳወቀች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ #ደቡብ_አፍሪካ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ መሰረዛቸውን ተከትሎ #የሐሰት_ዜና በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦
- በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣
- ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር
- በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ
-  ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ከቅዱስነታቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ መርሐ ግብር ይዘው ነበር።

ይሁን እንጂ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ካለባቸው ተደራራቢና አስቸኳይ ሥራዎች አንጻር ለ10 ቀናት ሙሉ ፦
° ከጽ/ቤታቸው ርቀው መቆየት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር በመስጋታቸው
° ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሌሉበት ሁኔታ ለበርካታ ቀናት ከጠ/ጽሕፈቱ ርቀው ከተጓዙ ሥራዎች ስለሚበደሉ ቀደም ሲል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዞ ከቅዱስነታቸው ጋር በጥሞና በመወያየት #ለመሰረዝ መገደዳቸው ተነግሯል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ " ብፁዕነታቸው ወደ ኤርፖርት እንዳይሔዱ እንደተከለከሉ እንዲሁም ፓስፖርታቸው እንደተያዘ " በማስመሰል የሚሰራጨው ዜና ፍፁም መሰረተ ቢስና የሐሰት ዜና መሆኑን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከታቀደው ሐዋርያዊ ጉዞ ለመቅረት የተገደዱት በተደራራቢ ሥራ ምክንያት  መሆኑን እና የብፁዕነታቸው ፓስፖርትም ለጉዞ ሲባል ቀደም ብሎ ከሚመለከተው አካል መጥቶ በልዩ ጽሕፈት ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ እጅ የሚገኝ መሆኑን ገልጻለች።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አባቶች ጋር ሆነው በዛሬው ዕለት ደቡብ አፍሪካ ፤ ጁሐንስበርግ ከተማ በሰላም የገቡ ሲሆን ምዕመናንም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ደቡብ አፍሪካ ፦ https://telegra.ph/EOTC-05-10

@tikvahethiopia
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የዳግማ ትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡

እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl

ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ግንቦት 4 ቀን 2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን ፤ ጥያቄውን  ለመለሱ 3 ተሳታፊዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል።

ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የብር ሽልማቶን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ     
    የስኬትዎ አጋር!   

[Telegram] (https://t.me/LionBankSC)  [Facebook] (https://www.facebook.com/LionBankSC)

#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
#Adigrat

በጦርነቱ ምክንያት ከ70 ከመቶ በላይ ውድመት የደረሰበት " የዓዲግራት አዲስ የመድሃኒት ፋብሪካ " አግግሞ እስከ 110 የሚደርሱ የተለያዩ በሽታዎች የሚፈውሱ መድሃኒቶች በማምረት ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሃይለ ገ/ሚካኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ የመድሃኒት ፋብሪካው ጦርነቱ በጀመረ ማግስት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።

በእነዚህ የኤርትራ ወታደሮችም 7 ሰራተኞቹ በሞት መነጠቁንና በርካቶችም መቁሰላቸውን አስታውሰዋል፡፡

የመድሃኒት ፋብሪካው ከህዳር እስከ የካቲት 2013 ዓ.ም ባሉት ሶስት ወራት የኤርትራ ወታደሮች እንደ #ካምፕ ሲገለገሉበት እንደነበር ገልጸዋል።

" ወታደሮቹ ማሽነሪዎች ጨምሮ የተለያዩ የፅህፈት ቤት እቃዎች ዘርፈው መውሰዳቸውንና መውሰድ ያልቻሉት ፈንጅ በማጥመድ አጋይቶውታል " ብለዋል፡፡ 

ፋብሪካው ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተነፃፃሪ የጥበቃ ከለላ ስር የተወሰኑ የጥገና ስራዎች ጀምሮ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

ነገር ግን በውቅቱ በነበረው የተወሳሰበ ውግያና የፀጥታ መድፍረስ ሳይሳካለት ቀርቶ 1500 ቀዋሚና ጊዚያዊ ሰራተኞቹ ለመበተን መገደዱን አመልክተዋል።

ፋብሪካው ከጥቅምት 2015 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጥገና ስራዎች በማካሄድ ከፌደራል የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን መልሶ ለማምረት የሚያስችለው የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቱ አቶ ሃይለ ገልፀዋል፡፡

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-11

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል።

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር።

ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#Mekelle

በመቐለ ከተማ መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ በእጣ መሬት ተሰጣቸው።

ለመኖሪያ በእጣ በተሰጠው መሬት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ የመቐለ መምህራን ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል።  

ዛሬ የተካሄደው የመምህራን የመኖሪያ መሬት በእጣ የማስተላለፍ ስነ-ሰርዓት ሂደት ከጦርነት በፊት የተጀመረውን ያሰቀጠለ ነው።

ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ክልል መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ የሚሆን በዕጣ የተሰጣቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በመቐለ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ መምህራን ዛሬ ተጠቃሚ ሆነዋል።

መምህራን ደመወዝ ጨምሮ ሌሎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች በየደረጃው መመለስ እንዳለበት ይህም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የትግራይ መምህራን ፦

° በጦርነቱ ምክንያት ያልተሰጣቸው ውዙፍ 17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፣

° የመኪና የሰርቪስ አገልግሎትም ጨምሮ ሌሎችም ጥያቄዎች ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ደጋግመው ጠይቀው አጥጋቢ መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚመለከቱ ተከታታይ ዘገባዎች ስናቀርብ መቆያታችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
                                  
@tikvahethiopia            
#AddisAbaba

“ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው ” - ኮማንደር ማርቆስ

ኢዩኤል ታዬወርቅ የተባለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጣበት ከህንፃ ላይ በወደቀ ብረት በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ለአደጋው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፣ “ እኛ አገልግሎት አልሰጠንም ” ብለዋል።

ሆኖም፣ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኮማንደር በሰጡት ምላሽ፣ “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው። 4 ሰዓት ላይ ነው የሞተው በሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ” ብለዋል።

“ ሟቹ ኢዩኤል የሚባል ልጅ ነው። እድሜው 23 ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እንደሆነ ነው የተነገረኝ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ አደጋው የደረሰው “የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ሟቹ የኪነህንፃ  (Architecture) #ተመራቂ ተማሪ እነደነበር ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ አስታውቆ፣ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

“ ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር የሄደ ሲሆን፣ በማግስቱ ከታናሽ ወንድሙ ጋር እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝ ከፍተኛ ፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ  ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል ” ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia