TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት አሳወቀ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ ም/ቤት አባል የነበሩት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

አቶ ዮሐንስ ከወራት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ባለልስጣን ለረጅም ጊዜ በተለያየ የስልጣን እርከን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በኃላ ላይ ከመንግሥት ጋር መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር።

ከወራት በፊትም በአማራ ክልል ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ለእስር መዳረጋቸው መነገሩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " - አቶ ሞገስ መኮንን ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ በሰመና መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ…
#Amhara

አብዛኛው የአማራ አካባቢዎች ኃይል በመቋረጡ በጨለማ ተውጠዋል።

ኃይል የተቋረጠው በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ መበጠስ አጋጥሞ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳሳወቀው ትላንት ከባህር ዳር - በደብረ ታቦር፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸና፣ አላማጣ የተዘረጋው ባለ230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተበጥሷል። በተመሳሳይ ከደብረ ብርሃን፣ ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ የተዘረጋውም ተበጥሷል።

የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እነዚህ ሁለት መስመሮች በምን ምክንያት ነው የተበጠሱት ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፤ " መስመሩ መበጠሱን እንጂ ያረጋገጥነው በምን በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ መልሰዋል።

መቼ ነው እሺ የተበጠሱት መስመሮች ተጠግነው ህዝቡ ኃይል የሚያገኘው በሚል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበው ጥያቄ ፤ " በቀላል የሚገናኙ መስመሮች ይኖራሉ ፤ በቀላል ሊገናኙ የማይችሉ እና የተበጠሰበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን መስመር መቀየር የሚያስፈልጉም ሊኖሩ ስለሚችሉ እነዚህን እርግጠኛ ባልሆንንበት በዚህ ቀን ሊባል አይችልም " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

በሌላ በኩል ፤ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትላንት ሌሊት ባሰራጨው መግለጫ የአማራ አብዛኛው ክፍል በጨለማ የተዋጠው ንፋስ መውጫ አካባቢ የባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊ መስመር አንደኛው ፌዝ በክልሉ በሚንቀሳቀሱት " ፅንፈኛ " ሲል በጠራቸው ታጣቂዎች በመሳሪያ በመመታቱ ነው ሲል አሳውቋል።

" ይህም ህዝቡን በማሰቃየት የተወሳሰበ ችግር ውስጥ መክተት ፣ እና ክልሉን ወደ ጨለማ የመውሰድ እንቅስቃሴ ነው " ብሎ ይህ የሚደረገው ህዝብ እንዲማረር በማድረግ ለትግል ለማነሳሳት ነው ብሏል። " ይህ ዘዴ ያረጀ ያፈጀ ፣ ያለፈበትና የተነቃበት የትግል ስልት ነው " ሲል በመግለጫው ላይ ገልጿል።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የትጥቅ ግጭት መካሄድ ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል።

ክልሉ ገና ከሰሜኑ ጦርነት ባላገገመበት ወቅት የተቀሰቀሰ ሲሆን የትጥቅ ግጭቶቹ በተለያየ ቦታ እና ጊዜ እየተካሄዱ ናቸው። በዚህም የበርካቶች ህይወት እየጠፋ፣ ንብረት እየወደመ ፣ የክልሉ ኢኮኖሚም እያዳከመው መጥቷል።

በግጭቱ ምክንያት የዳታ ኢንተርኔት ከተዘጋ በርካታ ወራት ያለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መበጠስ አብዛኛው የአማራ ክፍል በጨለማ ውስጥ ገብቷል።

@tikvahethiopia