TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ? የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል። ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል። ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦ - ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ…
ፎቶ፦ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚይ ሽኩሪ ዛሬ ኤርትራ አስመራ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ተቀብለዋቸዋል።

በኃላም ሚኒስትሮቹ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሀን የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የሱዳን ጉዳይ ፣ የቀይ ባህር ደህንነት እና በጋዛ ሰርጥ ስላለው ጦርነት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ከቀናት በፊት የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
🤩የአፍሪካን ምርጦችን በላቀ ጥራት ለማየት ዝግጁ ናችሁ?🏆

🔥ከጥር 4 - የካቲት 3 2016 ድረስ  የሚካሄደው  34ተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሁሉንም 52 ጨዋታዎች በላቀ ጥራት በቀጥታ በዲኤስቲቪ  ሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ በሁሉም ፓኬጆች ይመልከቱ!

👉አንድም ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ፈጥነው የዲኤስቲቪ ዲኮደር ይግዙ!

👉የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

#AFCONonDStv #AFCON2023#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#CBE

እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***********

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.me/combankethofficial
የቻይና አቋም ምንድነው ?

ቻይና ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት አለች።

ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር አላማዎችን እና መርሆዎችን ለማስከበር መቆሟን ገልጻለች።

የሀገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን እደግፋለሁ ብላለች።

" ሶማሊላንድ የሶማሊያ አካል ነች። " ያለችው ቻይና፤ የሶማሊያን ብሄራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ የሶማሊያን ፌዴራላዊ መንግስትን እንደግፋለን ስትል አሳውቃለች።

" የቀጠናው ሀገራት በዲፕሎማሲያዊ ውይይት ቀጠናዊ ጉዳዮችን በጥሩ ሁኔታ እንደሚይዙ እና ወዳጃዊ ትብብር በማድረግ የጋራ እድገትን እንደሚያሳኩ ተስፋ እናደርጋላን  " ብላለች።

ቻይና ፤ ሶማሊያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለው አይነት ሁኔታ ከታይዋን ጋር ያለባት ሲሆን " ታይዋን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopua
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

የጋራ ም/ቤቱ ጥር 01፣ ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ፤ በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን " መግባቢያ ሰነድ" በተመለከተ የስምምነቱን ማዕቀፍ ፣ዝርዝር ይዘቱን እና ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ባሉት እድሎችና ስጋቶች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ስምምነቱን ያለልዩነት መደገፉን አሳውቋል።

ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር በመምከር ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናውን ለመወጣት ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጿል።

መንግስት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህብረተሰቤ የበኩላቸውን አውንታዊ ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ታያይዟል)

@tikvahethiopia
#መቐለ
 
ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 3 ቀናት በመቐለ ከተማ የኤሌትሪክ አገልግሎት በተለያዩ የከተማዋ አከባቢዎች ይቋረጣል።

አገልግሎቱ የሚቋረጠው በስራ ምክንያት ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ቢሮ በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ ከጥር 3 እስከ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሦስት ተከታታይ ቀናት  በመቐለና አከባቢዋ በተለያዩ ከፍለ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል ይቋረጣል ብሏል።

መ/ቤቱ በደብዳቤው አክሎ እንደገለፀው ፤ የኤሌክትሪክ ሃይል አስተላላፊ አዳዲስ  ፓሎች ለመተክልና ለጥገና በማለም አገልግሎቱ ስለሚቋረጥ ህዝቡ ሁኔታውን አውቆ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ ማሳሰቡ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ዘግቧል። 

በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በትግራይ በሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት የማስፋፍያ ፕሮጀክት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ግርማይ ግደይ እንዳሉት ፤ የእንጨት ፓሎት ወደ ኮንክሪትና አዳዲስ ትራንስፎርመሮች የመተካት ስራ ጨምሮ በሁለት ቢሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ሃይል የማሻሻያ ፕሮክጀት በመከናወን ላይ ነው ብለዋል።

የማሻሻያ ፕሮጀክቱ በ14 ማህበራት ለተደራጁ 1500 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩ ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።
                                      
@tikvahethiopia            
#AddisAbaba

“ በእኛ የህግ አማካሪ በኩል ጥፋት ነበረ ” - ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው፣ 90 ዓመት ያስቆጠረ፣  በታሪካዊ ቅርስነት መመዝገብ አለበት በሚል በፍርድ ቤት በኩል ጉዳዩ ተይዞ ነበር የተባለለት ሎሞባርዲያ ሬስቶራንት ሳይፈርስ እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥም ሰሞኑን በግብረ ኃይሎች እንዲፈርስ መደረጉ ብዙዎቹን ቅር አሰኝቷቶ ተስተውሏል።

ሎሞባርዲያ እንዳይፈርስና እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ካስተላለፈ የፈረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንን ጠይቋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “በእኛ የህግ አማካሪ በኩል #ጥፋት ነበረ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፣ “ምክንያቱም የፍርድ ሂደቱ እንዴት ፕሮሰስ እንዳደረገ አላሳወቀንም። ከዚህ በፊት ሰበር እስከሚቀርብ ድረስ አሁን ያለን የህግ አማካሪ ነው ሲከራከር የነበረው። መመሪያ ስናጸድቅና ይህን ዲስከስ ስናደርግ፣ ለማኔጅመንት፣ ለውይይት ለባለሙያ ሲቀርብ ሁሉ ነበር” ብለዋል።

“መጨረሻ ላይ እኔን #‘ታስሮ ይቅረብ’ የሚል ፍርድ መጣ (አፈጻጸም ላይ ደርሶ ማለት ነው)። መጨረሻ ላይ ‘ምንድን ነው?’ ስንል ዶክሜንት ሲመጣ የህግ አማካሪው ያሉት ‘የተቋሙ ኃላፊ ናቸው እንጂ #መመሪያውም አይፈቅድም’ የሚል ነው” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አክለውም፣ “መሀል ላይ ገባንና እኛ፣ ለፍርድ ቤት ይሄ ሁሉ አልደረሰም አንድ፣ ሁለተኛ አዋጁን ተንተርሰን በወጣ መመሪያ መሠረት ነው ውሳኔ የሰጠነው። ይሄ የዋና ዳይሬክተሩም ሳይሆን የባለሙያ ውሳኔ ነው” ብለው እንዳስረዱ ገልጸዋል።

“እሱን ከኬዙ ለጊዜው አስወጥተነዋል። ምክንያቱም አንድ የተቋም አማካሪ ወይም ነገረ ፈጅ የተቋሙን ውሳኔ ነው አይደል ማስከበር ያለበት!? መከራከር ያለበት!?” ያሉት አቶ አበባው፣ “እሱ በእኛ የሚሆነው ይሆናል” ነው ያሉት።

ዋና ዳይሬክተሩ የሎሞባርዲያን መፍረስ በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት አውድ፣ “ለባለሙያ አውርደን አምና በዚህ ሰሞን ተመዘነ። ስለዚህ አላሟላም። ከመቶ ነው የሚመዘነው። ሲመዘን 38 ነጥብ ነው ያመጣው። ይሄ ማለት ቅርስ ብለን ልንይዝ አንችልም ማለት ነው” ብለዋል።

በቅርስነት እንዲቆይ (ላለመፍረስ) ሲመዘን ስንት ነጥብ ማምጣት ነበረበት? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ከ50 በላይ መሆን አለበት። ከ49 በታች ቅርስ ሊሆን አይችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተው፣ የአቶ ጌትነትን ሞት በተመለከተ ተቋሙ ከለላ የማድረግ ኃላፊነት እንደደሌለው፣ በግለሰብ ደረጃ በሟቹ ሀዘን እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

(ሬስቱራንቱ ከ100/38 አምጥቷል ያሉባቸውን እያንዳንዱን መለኪያ መስፈርቶች እንዲያስረዱና ሌሎች ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠይቋቸው የሰጡበትን የአቶ አበባውን ዝርዝር ሀሳብ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።)

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba “ በእኛ የህግ አማካሪ በኩል ጥፋት ነበረ ” - ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው፣ 90 ዓመት ያስቆጠረ፣  በታሪካዊ ቅርስነት መመዝገብ አለበት በሚል በፍርድ ቤት በኩል ጉዳዩ ተይዞ ነበር የተባለለት ሎሞባርዲያ ሬስቶራንት ሳይፈርስ እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥም ሰሞኑን በግብረ ኃይሎች እንዲፈርስ መደረጉ…
“ ቀብሩ ዛሬ ተፈጽሟል በቢሾፍቱ ቃጂማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን። የ8 ዓመት ልጅ አለችው። እናቱ ጌትነት፣ ጌትነት ትላለች። ወንድማችን እንደወጣ ቀረ ” - የሟች ወንድም አቶ ሚሊዮን ክፍሌ

ከ1962 ዓ/ም እንደተገባ የሚወሳለት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው የ90 ዓመት ዕድሜ ጠገብ ሎሞባርዲያ ሬስቶራንት እንዳይፈርስ በፍርድ ቤት ቢወሰንም “ለልማት ይፈለጋል” በሚል በግብረ ኃይሎች ሲፈርስ የአንድ የስምንት ዓመት ልጅ አባት መሞቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሟች ቤተሰቦች አረጋግጧል።

ሎሞባርዲያ ሬስትራንት በሚፈርስበት ወቅት አቶ ጌትነት ክፍሌ የተባሉ የስምንት ዓመት ልጅ አባት የሆኑት  አቶ ጌትነት ክፍሌ ከሬስቶራንቱ ውስጥ ከነበረ ስቶራቸው መፅሐፍ ሊያወጡ ሲሉ ኮሎን እንደመታቸውና ሕክምና ቢደረግላቸውም መትረፍ ባለመቻላቸው መሞታቸውን ወንድማቸው አቶ ሚሊዮን ክፍሌ ገልጸውልናል።

የሟች ወንድም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ቀብሩ ዛሬ ተፈጽሟል ቢሾፍቱ ቃጂማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን። ኮለን ነው የመታው። የ8 ዓመት ልጅ አለችው። እናቱ ጌትነት፣ ጌትነት ትላለች። ወንድማችን እንደወጣ ቀረ” ሲሉ እያለቀሱ ተናግረዋል።

“እኛ ከመድረሳችን በፊት በሥራ ባልደረቦቹ ተደግፎ ገብቶ ነበር ጥቁር አንበሳ ሆቴል”  ያሉት አቶ ሚሊዮን፣ ችግሩ የተፈጠረው ቅዳሜ ቀን 27 2016 ዓ/ም እንደነበር፣ የመጀመሪያ እርዳታ ከተደረለት በኋላ ወደ ሌሎች የሕክምና ተቋማት ሪፈር እንደተጻፈላቸው፣ ይሁን እንጂ የመታቸው ኮሎን ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሰባቸው ሕይወታቸውን በሕክምና ማትረፍ እንዳልተቻለ አስረድተዋል።

አክለውም፣ “እናቴ ‘ጌትነት፣ ጌትነት’ እያለች ታለቅሳለች ምን ላድርጋት? የሚረዳት የነበረው እርሱ ነው። ወጥቶ ነው የቀረው። ሦስት ቀን ደፋ ቀና አልኩ ግን ሊተርፍ አልቻለም። የዚች ልጁ እጣ ፋንታስ ምንድን ነው የሚሆነው?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የሟቹን ጉዳይ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሙከራ ቢያደርግም ስልክም የጽሑፍ መልዕክትም መመለስ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

ሬስቶራንቱ/ ሕንፃው የቅርስነት መስፈርትን በማሟላት ተመዝግብ እንደቆይ፣ በኋላ በየካቲት ወር 2015 ዓ/ም   ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ኪነ ጥበባት ቢሮ፣ ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽ ሕንፃው ከቅርስነት ተሰርዟል በሚል ቀርቧል የተባለውን ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ውድቅ እንዳደረገው መረጃዎች ያመለክታሉ።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚይ ሽኩሪ ዛሬ ኤርትራ አስመራ ገብተዋል። ሚኒስትሩ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ተቀብለዋቸዋል። በኃላም ሚኒስትሮቹ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሀን የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ…
የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አደረጉ።

ከቀናት በፊት ለሶማሊያው ፕሬዜዳንት ተመሳሳይ መልዕክት መላካቸው ይታወሳል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህም ወቅት ከፕሬዜዳንት አልሲሲ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል ተብሏል።

መልዕክቱ፤ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ አህጉራዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።

ሀሙስ ምሽት በአስመራ ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ጋር የተገናኙት የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ በተለያዩ መልዕክቱን ከማድረስ ባለፈ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል።

ውይይቱ በኤርትራ እና ግብፅ መካከል በወቅታዊ ቀጠናዊና እና ዓለምአቀፋዊ ተግዳሮቶች ላይ መክሯል የተባለ ሲሆን በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አጽንኦት መሰጠቱ ተነግሯል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሀገራቸው ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ የሚል ግብዣ አድርሰዋል።

ከቀናት በፊት የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ተመሳሳይ ግብፅን ይጎብኙ የሚል መልዕክት ማድረሳቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ስምምነት አደጋ ይዞ ይመጣል ? የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ያለ አንዳች ግጭት፣ ውጊያ ከባለቤቶቹ ተደርጓል ያሉት የመግባቢያ ስምምነት አደጋ እንደማያመጣ ገልጸዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ " ኢትዮጵያ የባህር በር የላትም፤ እድገቷ በጣም ጨምሯል። በዙሪያዋ የሚተናኮሳት ፤ እሷን መተናኮስ…
#Ethiopia

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል #ጫና ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ።

አምባሳደር ሬድዋን፤ " የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣  ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ዓይነት ጫና ተቋቁመን ነበር " ብለዋል።

" የባህር በሩም እንዲሁ ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia