TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ሲሄድ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
 
የአምቡላንስ ሼፌሩ በተተኮሰበት ጥይት #ተገደለ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይዎት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ሰዓት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል።

አቶ ወልዱ በቀን 01/05/2016 ዓ/ም ከምሽቱ/ከሌሊቱ 5፡20 አካባቢ ከተመደበበት የስራ ቦታው ‘ከነበለት’ ለመውለድ በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ወደ ‘ዓዲ ጉደም’ የተባለ ቀበሌ የሕክምና ባለሙያ ይዞ በመጓዝ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጥይት ተተኩሶበት ክፉኛ ሊቆስል ችሏል።

በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ደርሰዉለት ወደ ‘ነበለት ጤና ጣቢያ’ የተወሰደ ቢሆንም፣ ጉዳቱ ከጤና ጣብያው አቅም በላይ ስለነበር ወደ መቐለ ዓይደር ሆስፒታል ሪፈር ተብሎ እየሄደ ሳለ ሆስፒታል ሳይደርስ ህይወቱ አልፏል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ በኢቀመማ ትግራይ ክልል ማዕከላይ ዞን ቅርንጫፍ በእምባስነይቲ ወረዳ ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ የአምቡላንስ ሹፌር በመሆን በማገልገል ላይ ነበር።

የቀይ መስቀል መርህ እና ህግን ተከትሎ በታማኝነት በማገልገል ላይ የነበረው አቶ ወልዱ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት ነበር።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በማህበሩ ሰራተኞችና አምቡላንሶች እንዲሁም ንብረቶች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ገልጾ ይህ ተቀባይነት የሌለዉ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት የፈረመዉን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ስምምነት የሚጥስ ነው ብሏል።

ማንኛዉም አካል የማኅበሩን ሰራተኞችና ንብረቶች የጥቃት ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
         
@tikvahethiopia            
Forwarded from Ethio telecom
በቴሌብር ሱፐርአፕ እና በድረ ገፃችን ላይ የተካተተውን ቴሌሀብ በመጠቀም የዲጂታል አማራጮቻችንን ሁሉንም በአንድ ቦታ ያግኙ!

https://telehub.ethiotelecom.et/

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ለጥያቄና መልስ ውድድራችን ዝግጁ ነዎት?
7ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ጥር 9 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

የቴሌግራም ሊንክ https://t.me/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba “ በእኛ የህግ አማካሪ በኩል ጥፋት ነበረ ” - ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው፣ 90 ዓመት ያስቆጠረ፣  በታሪካዊ ቅርስነት መመዝገብ አለበት በሚል በፍርድ ቤት በኩል ጉዳዩ ተይዞ ነበር የተባለለት ሎሞባርዲያ ሬስቶራንት ሳይፈርስ እንዲቆይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥም ሰሞኑን በግብረ ኃይሎች እንዲፈርስ መደረጉ…
#ዝርዝር

" ሕንጻው የፈረሰው በቅርስነት መመዘኛ መስፈርቶች መሠረት ከ100 ቢያንስ 50ና ከዚያ በላይ ውጤት ባለማምጣቱ  ነው " - ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፤ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌውን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሎምባርዲያ ይገኝበት የነበረው ሕንጻ የፈረሰው በቅርስነት መመዘኛ መስፈርቶች መሠረት ከ100 ቢያንስ 50ና ከዚያ በላይ ውጤት ባለማምጣቱ ነው ብለዋል።

ሕንፃው ከ100/38 ነጥብ ያገኘ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

- የዚህ ነጥብ መመዘኛ መስፈርቶች ምን ምን ናቸው ?

- በእያንዳንዱ መመዘኛ የተሰጡት ውጤቶችስ ስንት ናቸው ? ሲል ጠይቋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ፦

* ሦስት ደረጃዎች ናቸው የሚኖሩት። ደረጃ ሀ፣ ደረጃ ለ እና ደረጃ ሐ። 

1ኛ) ደረጃ ሀ ማለት ከ100 እስከ 65 ያመጣ ነው። ከ100 እስከ 65 ውጤት ከመጣ ምንም አይነት አልትሬሽን አይደረግበትም። ለሙዚየም፣ ለባህል ማዕከል ሊደረግ ይችላል። ነገር ግን ውጫዊውንም ፣ ውስጣዊውንም ገጽታ መቀየር አይቻልም።

2ኛ) ደረጃ ለ ማለት ከ64 እስከ 50 ነው። ይሄ ደግሞ የሚይዘው ውስጥ ላይ Reinnovataion ሊሰራ ይችላል። ግን ቅርስ አይፈርስም የሚል ነው።

3ኛ) 49ና ከ49 በታች ደረጃ ሐ ነው። ይሄን ምዘና ያገኘ ደግሞ ቅርስ አይሆንም፣ መስፈርት አያሟላም የሚል ነው የሚይዘው ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በእነዚህ ደረጃዎች መሠረት ሎሞባርዲያ ይገኝበት የነበረው ህንፃ የተሰጠው ነጥብ ከስንት ስንት እንደሆነ በዝርዝር ይግለጹ ? ብሎ ጠይቋል።

* “ስታይል 7 ነጥብ ነው የሚይዘው። 3 ነጥብ ነው ያገኘው። ኮንስትራክሽን ማተሪያልን ጨምሮ 6 ነጥብ ነው የሚይዘው። 2 ነጥብ ነው ያገኘው። ዕድሜ 5 ነጥብ ነው የሚይዘው። 3 ተሰጥቶታል።

* አርክቴክት 3 ነጥብ ነው የሚይዘው። ከ3 ዜሮ ነው ያገኘው። ኢንተርየር ከ3/1 (ከሦስት አንድ) ነው ያገኘው። ታሪኩ ሲወሰድ ኢርሌር ትሬደር ነው በሚል 10 ነጥብ ነው የሚይዘው። 7 አግኝቷል።

* ኢቨንት 10 ነጥብ ነው የሚይዘው። 3 ነው ያገኘው። ኮንቴክስት ከ10/3 (ከአሥር ሦስት) አግኝቷል። አካባቢውን ጨምሮ ኮንቲኒዩቲ የሚለው 0/3 (ዜሮ ከሦስት ነው) ያገኘው። Land mark ነው የሚለው፣ ከ4/1 (ከአራት አንድ) ነው ያገኘው። 

* Usabilityን በተመለከተ Comparability አለ፣ 5 ነጥብ ነው ያለው። ዜሮ ነው ያገኘው። አዳፕታቢሊቲ ከአምስት አንድ ነው ያገኘው። ቦታው ፐብሊክ ነው ወይ? በሚለው አይደለም። ከአራት አንድ ነው ያገኘው። 

* Service (አገልግሎት) የሚሰጥበት መኝታ ቤቶችና ሌሎች ናቸው። ታችም ሱቆች ናቸው። ከሦስት ዜሮ ነው ያገኘው። ቢቆይ፣ አዲስ ቢሰራ በሚል ሦስት ሦስት (3/3) ነጥብ ነው ያገኘው። ኢንተግሪቲ (ያለበት ሁኔታ) አልትሬሽን ብዙ አልተደረገም። ከአምስት ሦስት ነው። ያገኘው።

* “Condition, in good condition ነው አምስት ነው ያገኘው ከሰባት፤ እንደዚህ ሆኖ 38 ነጥብ ይመጣል በአጠቃላይ። በዚያ መሠረት ኢቫሉየት ከተደረገ በኋላ ነው የሰረዝነው።

ያንብቡ👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-12

@tikvahethiopia
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.me/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#EOTC

ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ፈተናዋን እንዴት ማለፍ እንዳለባት በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቀዋለን ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው የተለያዩ አባቶች በተለያየ መንገድ ተናገሯቸው ስለተባሉት ጉዳዮች ተነስቶ መንግስት ቀየሜታውን ገልጾ ቤተክርስቲያን መልስ እንድትሠጥበት አሳስቧል " ያሉት ብፁዕነታቸው " ቤተክርስቲያንም በስፋት፣ በትኩረት ተወያይታበታለች (ቅዱስ ቋሚ ሲኖዶስ) ይሁን እንጂ የብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው የሚሆነው ፣ ምክንያቱም አንድ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ፤ ቀርቦ ተጠይቆ አውንታዊ መልስ ሰጥቶ ስህተት ነው ? እውነት ነው ? ብሎ የሚወሰን እንጂ ብግድ ተብሎ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በሌላ የተለያየ መልኩ እንዲህ ነው እንዲያነው ብሎ መናገር ህገ ቤተክርስቲያናችን አፈቅድም " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ሰላምን መፈለግ ፣ መሻት ፣ መልካም ነገር ማድረግ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ አቋም የላትም " ያሉት ብፁዕነታቸው ፤ " እንደ ህግ እና ስርዓታችን በአባቶች ደረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ይወስናል። ይህ ቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚለውን እንዲል አልፎታል " ሲሉ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " አሁን ግራ የሚያጋባው ትላንት ለበዓለ ጥምቀቱ የተሰየመው አብይ ኮሚቴ ከከተማ አስተዳደሩ፣  ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ፣ከታላላቅ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ ይህ ከባድ ፈተና እየተነሳ እንዳለና አሁንም በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነቱን ለይታ እንድታወግዝ ፣ የራሷን መልዕክት እንድታስተላልፍ በመንግሥት አቋም ተይዞ ለአብይ ኮሚቴው ተነግሯል " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ያራሷ ነፃነት አላት ፣ የራሷ ክብር አላት ፣ የራሷ ነፃ መድረክ ፈላጊ ናት ሁሉም እየተነሳ ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ክፉውን ክፉ፣ በጎውን በጎ፣ መልካሙን መልካም ፤ መልካም ያልሆነውን መልካም አይደለም ብላ ለማስተላለፍ የራሷ ህግ ስርዓት አላት " ብለዋል።

" የፈለገ የሚያዛት ፣ የፈለገ የሚያሽከረክራት ፣ ያልወደደ እንደ ወደደ ፍላጎቱን ምኞቱን እንድትፈፅምለት የሚጎትታት ቤተክርስቲያንን ኖራም አታውቅም ወደፊትም ልትኖር አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ቤተክርስቲያን በራሷ ነፃ መድረክ ቆማ ችግሩን ችግር ነው ብላ መናገር አለባት እያደረገችም ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይሄ በፍፅሙ አይመጥነኝም። እንዲህ አይነቱ የኔ ቃል አይደለም ብላ #ታውጃለች ግን በግልፅ መጠየቅ ያለባትን ጠይቃ መናገር ያለበትን እንዲናገር ፈቅዳ ሁሉን ነገር በአግባቡ ታደርጋለች እንጂ በኩርፊያ በአላስፈላጊ ብሂል ይሄን ካላደረግሽ በዓል ለማክበር አልችልም ፣ ከናተ ጋር ግንኙነት የለንም እስከሚባል ድረስ የሚኖረው ነገር ከማንም ከምንም በፍፁም አይጠበቅም " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዛሬ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
* የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማኅማትን፤
* የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን
* የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድኖች አባላትን በ "ወንጪ ዳንዲ ኤኮ ቱሪዝም መንደር" መቀበላቸውን የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የAU እና ኢጋድ መሪዎችን እና ዲፕሎማቶችን ከመቀበል ባለፈ ውይይቶችን አድርገው እንደሆነ የተባለ ነገር የለም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ከተጋሩ በኃላ በቀጠናው ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል።

#Ethiopia #Africa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል። ቤተክርስቲያን…
#EOTC

" ኮብልለው አልሄዱም፣ ኮብላይም አይደሉም ! "

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶክተር) ኮብልለው አልሄዱም፣ ኮብላይም አይደሉም። ለእውነት እና ለፅድቅ ለቤተክርስቲያናቸው አንገታቸውን ከሚሰጡ አባቶች አንዱ እንጂ የሚሸሹ የሚኮበልሉ ፣ የሚደበቁ የወንጀል ሰው ሊሆኑ አይችሉም። አይደሉምም።

- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቅዱስ ፓትርያርኩ ፍቃድ፣ እንደ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አውቆት ለአገልግሎት ቤተክርስቲያን ሊባርኩ ታቦታት ይዘው አስፈቅደው ሰሜን አሜሪካ ሄደዋል። ይሄ ደግሞ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ነው የሚሄዱት።

- ቆም ብላችሁ አድምጡ ! እናተ ለፖለቲካችሁ ብዙ እንደምትሉ ብዙ እንደምታስቡ ሁሉ እኛም ለሰማያዊ መንግሥታችን እንቆማለን ፤ ለምድራዊ መንግሥታችን እንገዛለን በሃይማኖት እስካልመጣብን ድረስ በሃይማኖት ከመጣ ግን መገዛት አይደለም አትገዙ ብለን እናውጃለን። ግን ግድሉ አንልም፣ ተገዳደሉ አንልም፤ ቤተክርስቲያን ቃሏ ስላልሆነ። አትገዙ ግን ትላለች አሁን ግን እዚህ አልደረስንም። ቤተክርስቲያን እያስተማረች ያለችው ሰላምን፣ ፍቅርን ብቻና ብቻ ነው።

- ያለ ስም ስም መስጠት ይሄ ማህበራዊ ሚዲያ በሚባለው ንፋስ ፣ ምንም ጭብጥ በሌለው ሃይማኖታዊውን ሰው ሃይማኖታዊ አይደለም፤ ለቤተክርስቲያን የሚሰራውን ፣ለሀገር የቆመውን ኮበለለ ፣ ከዳ የሚባል ደካማ አስተሳሰብ የቤተክርስቲያን ህልውና አያናግም።

- " ደግሞ ሰምተናል አባ ጴጥሮስ ፣ አባ አብርሃም ... ተለውጠዋል ዝም ብለዋል አድር ባይ ሆነዋል የሚለውን ፤ ከሃይማኖት ውጭ ሌላ ማደሪያ የለንም። ለኛ ማደሪያችን መዋያችን ሃይማኖታችን ናት "

- ለመንግስትን እንደ መንግስት እንድንገዛው መፅሀፍ ቅዱስ ያስገድደናልም በሃይማኖታችን እስካለመጣ ድረስ ሃይማኖታችንም ለመንግስት እንድንገዛ ያስገድደናል።

- ከዚህ ውጭ ከውስጥ የምንሰራውን በይፋ እንዲህ ነው ብለን አናወራም በሚል ዝም ብለናል።

- የወሬ ገበያ ያለው ሰው ሁሉ የወሬ ገበያው እንዲደራ ዛሬ አባ አብርሃም ፣ አባ ጵጥሮስ አልተናገሩም በሚል ሌላ ስም ልስጥ ቢል የሱ ወሬ እንጂ የኛ አይደለም።

- አባ ጴጥሮስ ሆኑ አባ አብርሃም ስራቸውን የሚሰሩት በሃይማኖታቸው መሰረት ብቻ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል።

- ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች።

- አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ ውጭ ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተክርስቲያን አትሸከምም አትቀበለም።

- ሰላሟን እያወጀች፣ ሰላሟን እየሰበከች በሰላም መንገድ ትጓዛለች።

- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን መሞትን ስራዬ ብላው ይዛ ኖራለች ወደፊትም ሞት ከሆነ በሰላም ለመቀበል ዝግጁ ናት።

- " ይሄን ካደረግሽልኝ ይሄን አደርግልሻለሁ " የሚል መደራደሪያ የላትም ፣ ሊኖራትም አይችልም። ድርድሯ ሰላምና ሰላም ብቻ ነው።

- እኔ ያልኩሽን አድርጊ የሚል በቀኝም ይሁን በግራ ፤ ከገዢውም ክፍል ይሁን እገዛለሁ የሚል ሃሳብ ቢመጣ ያን ተቀብላ የማስተናገድ አቅምም ብቃትም የላትም።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ በዓሉ ዓለም አቀፍ ስለሆነ የተለያየ እምነት ያላችሁ ልጆች ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ሆናችሁ በዓሉ በዓላችን ነው የምትሉ፣ የምትደግፉ በዓሉን እራሳችሁ አክባሪዎች ፣እራሳችሁ የፀጥታው አስተናጋጆች የሰላም መሪዎች ሆናችሁ በዓሉ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ቤተክርስቲያን መልዕክት ታስተላልፋለች።

- የፀጥታ አካላት ትላንት እንዲህ ተብያለሁ ይሄ እንደገና በተቃውሞ ካልታወጀልኝ በስተቀር ይሄን አላደርግም የሚለውን አስተሳሰብ ትቶ ህግን በህግ ስርዓትን በስርዓት ለመፈፀም አእምሮውን አስፍቶ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

- ሌላው ሌላው ችግር በመድረክ ዙሪያ፣ ማነው ጥፋተኛ ? ምን አስቦ ነው ? ምን ብሎ ነው ? የሚለውን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመክርበት የሚዘክርበት፣  የሚገሰፀውን የሚገስፅበት ፣ ከቀኖና የወጣውን ከቀኖና ወጥተሃል የሚልበት የራሱ ስርዓት ስላለው ለህጉ እንተወዋለን።

- " ይሄን በሉ ይሄን አድርገ፣ ይሄን ካላደረጋችሁ ይሄን አናደርግም " የሚባል መያዣ ነገር ቤተክርስቲያን አስተናግዳ አታውቅም ፤ ወደፊትም አታስተናግድም።

- እገሌ እገሌ ባልልም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ናት በዓሉም የህዝብ ነው ይሄን መያዣ አናድረግም ችግሩ ችግር ሳይሆን እንዲፈታ ይደረግ በመልካም ነገር በዓሉን በሰላም እናክብር ብለው የተናገሩ መሪዎች አሉ በዚህ አጋጣሚ ሊደነቁ ይገባል። ከመሪዎች የሚጠበቀው ይሄ ነው። ችግርን እንዴት እንፍታው ችግርን እንዴት እናስወግደው ፣ ሰላም እንዴት እናስፍን ነው መባል ያለበት።

- በየሄድንበት " ደግሞ ለኦርቶዶክስ፣ ለተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ቃሉም ይከብዳል በየቢሮው ስንሄድ ቢያንስ አይሆንም አይባልም " ያንን ያንን ያርሙ " ይላሉ።

- " ኦርቶዶክስ ሃገር ናት ፣ ለሀገር ዋልታ ናት፣ ምሰሶ ናት አምድ ናት ይሄን ታሪክ አይክደውም። ዘመን ቢያስረጃትም ዘመን ቢጥላትም ዘመን ያነሳታል።

- ዛሬም ሲደረግላት እያመሰገነች ነው። ለሀገር ሰላም ማድረግ ያለባትን እያደረገች ነው ፤ በየመስሪያ ቤቱ ስንሄድ " ደግሞ ለኦርቶዶክስ " የሚለው ቃል ሊታረም ይገባል።

- ቤተክርስቲያን ትከበር ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥም #በሃይማኖት_ስም እንደፈለገ የሚዋኙ ሰዎች ቆም ብለው ያዳምጡ፣ የሚናገሩትንም ይመርምሩ ፣ ሃይማኖታዊ ቃል ነው አይደለም ይበሉ ከሃይማኖታዊ ቃል ውጭ የሆነው ሁሉ የእኛ #አይደለም

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia