TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ይፋ አደረገ። 

ፋብሪካው በቴሌግራም ገፁ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው ፤ በ PPC አይነት ስሚንቶ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ተመን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት በአዲሱ የመሸጫ አሰራር ከፋብሪካ ሰሚንቶ ለመግዛት ፣ ለማከፋፈልና ለመቸርቸር ፍቃድ ተሰጥቶዋቸው ውል ያሰሩ አካላት ፣ በችርቻሮ የሚሸጡበት ዋጋ አውጥቷል።

ፋብሪካው ጨምሮ እንደገለፀው በትግራይ ንግድና ኤክስፓርት ኤጀንሲ የስሚንቶ ምርት ተደራሽነቱ ለማስተዳርና ለመቆጣጠር በወጣውና በፀደቀው አዲስ መመሪያ ቁጥር 02/2015 መሰረት ከፋብሪካው ገዝተው በመላ ትግራይ በችርቻሮ የሚሸጡበት  የዋጋ ተመን አውጥቷል።

አዲስ የመሸጫ ዋጋው PPC አይነት ስሚንቶ የሚመለከት ሆኖ የትራንስፓርት : የመጋዘንና አስተዳደራዊ ወጪዎች ግምት ያስገባ የችርቻሮ ዋጋ እንደተቀመጠለት የፋብሪካው የቴሌግራም ገፅ  ጠቅሶ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

(የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቢሮዉ ቁልፍ በመቀየሩና አካባቢዉ አስጊ በመሆኑ ስራ መስራት አልቻልንም " - የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ " በተቀነባበረ ድራማ ቢሯችን ከነዶክመንቱ ተቀምተናል " ሲል የሲዳማ ፌደራሊስት ፖርቲ የክልሉን መንግስት ከሰሰ። የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አት ገነነ ሀሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባሰሙት ቅሬታ እንደገለጹት ከሆነ ፤ ከወራት በፊት በዲስፕሊን ግድፈት ከፓርቲዉ የታገዱት አቶ ጴጥሮስ…
" በእኛ ክልል ደረጃ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው የሚታሰሩ ሰዎች የሉም " - አቶ ወንሰንየለህ ስምዖን (የሲዳማ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ)

የሲዳማ ክልል መንግሥት በሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ለሚቀርበው ክስ ምላሽ ሰጠ።

ክልሉ ምላሽ የሰጠው በኮሚኒኬሽን ቢሮው አማካኝነት ነው።

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ምንድነው ያለው ?

(አቶ ገነነ ሀሰና - የፓርቲው የፅ/ቤት ኃላፊ / ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ እና ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል)

- ጥቅምት 27 /2016 በክልሉ መንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች ተወሮ ተሰብሯል። ይህ ድርጊት ተፎካካሪ ፓርቲን ሆን ብሎ ለማዳከም ነው።

- ከወራት በፊት በዲስፕሊን ግድፈት ከፓርቲዉ የታገዱት አቶ ጴጥሮስ ዱቢሶ በክልሉ ፖሊስ ድጋፍ ወደቢሮዉ በመግባት የቢሮዉን ቁልፍ ቀይረውና ፋይሎቹን ይዘው ወጥተዋል።

- በወቅቱ ቢሮ ዉስጥ የነበረዉና ድርጊቱን ለመከላከል የሞከረው የፓርቲዉ አባል አቶ ሳሙኤል ላንቃሞ ተደብድበው ለእስር ተዳርገዋል።

- በአሁን ሰዓት እኔን ጨምሮ ሌሎችም ስራ አስፈፃሚ አካላት ወደ ቢሮ መግባት አልቻልንም።

- በአሁን ሰዓት ቢሮው ተወሮ ያለው በመንግሥት አካላት ነው። ሰነድ እንደፈለጉ እየበረበሩ ነው።

- ከዚህ በፊት ሲፌፓን ትደግፋላችሁ ተብለው 22 የሚደርሱ ሰዎች ታስረው ይገኛሉ። እያጣራን ነው እያሉ 2 ወር ሙሉ እስር ቤት አስቀምጠዋቸዋል። መጀመሪያ ሲያስሯቸው " ክልሉን ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል " በሚል ነው። ልጆቹ ላይ ምንም መረጃ አላገኙም ዝም ብለው እያንገላቷቸው ነው።

- 48 ሌሎች ይፈለጋሉ በሚል እየተሳደዱ ነው። የኛ አባላት ተሰደው ነው ያሉት። አብዛኛው የማዕከላዊ አባላት ስደት ላይ ናቸው።

የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ምላሽ ምንድነው ?

የሲዳማ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምዖን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል በፓርቲው አመራሮች መካከል ባለ የእርስ በእርስ ሽኩቻ እንጂ በክልሉ መንግስት ላይ የሚቀርበው ክስ እና ወቀሳ መሰረተቢስ ውንጀላ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ታስረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ወሰንየለህ ስምዖን (ለቪኦኤ ሬድዮ የተናገሩት) ፦

" መንግሥት አንዱ ግዴታው ህግ የማስከበር እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው።

በክልላችን ውስጥ በተለያየ መልኩ በአመራርነት ላይ ያላቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም እንዲሁም ከሚዲያ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በሀገር ደረጃ ባሉ ህጎች መሰረት አድርጎ ጥፋተኞች ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች አሉ። ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ሂደቱም ያለ ነው።

አያያዛቸውም ማንኛውም ዜጋ ክብሩ ተጠብቆ ተጠርጣሪ እንደሚደረገው ተደርገው ተይዘው ነው ያሉት። በህግ ስለሚታይ እሱ በሂደት ላይ ነው ያለው ሲያልቅ ለሚዲያ እናሳውቃለን።

በኛ ክልል ደረጃ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው የሚታሰር ሰው የለም። ስለዚህ ነገሮች መደባለቅ የለባቸውም። ሴኩላር መንግስት ነው ያለን ማንም ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታወቀው መልኩ የተለያየ ህጋዊ ፓርቲ አቋቁሞ የሚሰራበት ሀገር ነው ማንም በክልላችን በፖለቲካ አስተሳሰቡ ሊጠየቅ አይችልም። እንደ ሀገር እየተዳደርን ያለነው እየተመራም ያለው የፖለቲካ ስርዓት ስለማይፈቅድ በዚህ ደረጃ የሚመጣ ውንጀላ ትክክል አይደለም ብለን ነው የምናስበው። "

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ምንም እንኳን በህጋዊ መንገድ ተቋቁሞ ወደ ስራ ቢገባም በክልሉ ውስጥ በነፃነት እንዳይቀሳቀስ በርካታ ጫናዎች እየደረሱበት ፣ አባላቱም ለእስር እና ለስደት እየተዳረጉ እንደሆነ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
" የእኛን ምሩቃን ለመቅጠር ስትፈልጉ የትምህርት ማስረጃቸውን #ለማረጋገጥ ጠይቁን ፤ ትክክለኛውን ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ እንሰጣችኃለን " - ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፤ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገው የትምህርት ማስረጃ ማጣራት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም የተሠሩ #የሀሰት የትምህርት ማስረጃዎች መገኘታቸውን አሳወቀ።

ተቋሙ ፤ ህገወጥ የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት በተሰራው ስራ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ትክክለኛ ያልሆነውን ውጤት በራሳቸው ጊዜ የራሳቸው አድርገው ውጤት ማሻሸል እንደቻሉ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

" ይህ አሳፋሪ ወንጀል ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ግለሰቦቹ ይህን በመፈፀም በአቋራጭ መንገድ ስራ የመቀጠር እና የሌሎች ሰዎች የስራ እድል ጭምር በማጥፋት ድርጊት መሰማራታቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ስም ለመጥፋት እንደሞከሩ ገልጿል።

በእንደዚህ ዓይነት የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ላይ መሳተፍ ከዜጎች የማይጠበቅ ተግባር ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማትና ድርጅቶች ከዛሬ ህዳር 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የተመረቁ ምሩቃንን ለመቅጠር ሲፈልጉ የተቀጣሪዎችን መረጃ በፖስታ ቁጥር P.O.Box 667 እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ኢሜይል email address: info@wcu.edu.et በመላክ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የምሩቃንን ትክክለኛውን የትምህርት ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ሰጣለሁኝ ብሏል።

* ከላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስም የተያያዘ ሲሆን አብዛኞቹ በተለያዩ የሀገሪቱ #ባንኮች ውስጥ እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia
እርሶ ፈገግ ይበሉ ሌላውን ለፋንተም ቪ ፍሊፕ ይተዉት!

አዲሱ የቴክኖ ሞባይል ምርት የሆነው ፋንተም ቪ ፍሊፕ በ(ultra clear freecam system) በመታገዝ በእጅዎ ሳይነኩ በ 64ሜጋ ፒክስል የጀርባ እና 32ሜጋ ፒክስል የፊት ካሜራ ጥርት ባለ መልኩ የፈለጉትን ያንሱ። ከፍተኛ የባትሪ አቅም እና 45ዋት ፍስት ቻርጂንግ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ በ45 ደቂቃ 100% ቻርጅ የማድረግ አቅም የያዘ አዲስ ሞዴል ያደርገዋል። እራሶን በነፃነት ለመግለፅ ቦታ እና ጊዜ ሳይገድቦ ፍላጎቶን ያጋሩ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዳሬሰላሙ ድርድር ምን ይዞ ይመጣል ?

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በተለያዩ አከባቢ ያሉ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለምዶ (ኦነግ ሸኔ) በታንዛንያ ዳሬሰላም እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

በሰላም እጦቱ ብዙ ነገር ካፈራንበት ቀዬ ተፈናቅለናል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ዘላቂ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ወደ ነባሩ ቀዬያቸው ተመልሰው የተረጋጋ ህይወት የመምራት ተስፋቸውንም አጋርተዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ከተለያዩ  ወረዳዎች ተፈናቅለው በዚያው አከባቢ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ጃራ የተፈናቃዮች ካምፕ እንዲሁም ደቡብ ወሎ ቃሉ የተፈናቃዮች ካምፕ የተጠለሉት ተፈናቃዮቹ በድርድሩ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ወደ ተረጋጋ ህይወት በመመለስ ኑሮያቸውን ለመምራት መደላድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ድርድር ግን ለአጠቃላላው ህብረተሰብ የውይይት መድረኮች አዘጋጅቶ ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚችልና ለዚያም መደላድል የሚፈጥር መሆን ይገባል ብለዋል።

ተፈናቃዮች በዚሁ አስተያየታቸው ከታች የመንግስት መዋቅር ጀምሮ በመፈተሽ ለሰላሙ መደፈርስ መጠየቅ ያለብት አካል እንዲጠየቅ ተፈናቃዮቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ ያሉ ችግሮች በሰላም መፍታት ተፈናቃዮቹን ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንደሚመልስም ተስፋው ሰፊ ነው ሲል ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዳሬሰላሙ ድርድር ምን ይዞ ይመጣል ? በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በተለያዩ አከባቢ ያሉ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለምዶ (ኦነግ ሸኔ) በታንዛንያ ዳሬሰላም እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል። በሰላም እጦቱ ብዙ ነገር ካፈራንበት ቀዬ ተፈናቅለናል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ዘላቂ ሰላም የሚሰፍን…
ተፈናቃዮች ስለ ዳሬሰላሙ ድርድር ምን አሉ ?

#1 አስተያየት ሰጪ

" ይኸኛው ድርድር ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ያስችለዋል።

ለምሳሌ ካለንበት ቡሬ መድረስ አንችልም አይደለም ቡሬ ጊዳ እንኳን ወጥቶ መመመለስ አንችልም። ከዚህ ጉተን ደርሶ መመለስ አይቻልም ከዚህ 12 እና 13 ኪ/ሜ ርቀት ላይ እንኳን ወጥቶ መግባት አይቻልም።

ወደ እርቅ ከተገባ እና ድርድሩ ከተሰራበት ይሄ ህዝብ ከአዲስ አበባ የሚፈልገውን ገዝቶ ፣ የታመመውም ታክሞ ትምህርት የሚማረውም ትምህርቱን እንዲማር ጥሩ እንቅስቃሴ ይኖረዋል።

በተለይ ወላዶች እየሞቱ ነው። እኛ አካባቢ ሰሞኑን ብቻ 4 ወላዶች ሞተዋል በወሊድ ምክንያት ፤ እናቶች እያየናቸው እየሞቱ ነው። ወስደን የምናሳክምበት የለም። የሚያዋልድ የለም። ሆስፒታል ነቀምት፣ ጊዳ ነው ያለው መሃል ላይ ሸኔ ስላለ በየት በኩል አድርገን እንወስዳለን ? እስከዚህ ድረስ የከፋ ስቃይ አለ።

እነሱ ከታረቁ እንዲህ ያለው ነገር ይቀንሳል። "

#2 አስተያየት ሰጪ

" የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅት / ኦነግ ሸኔ እና የኢትዮጵያ መንግሥት እያደረጉ ያሉት ድርድር ማኛውም ኢትዮጵያዊ ደስ ብሎታል።

ይሄ ድርድር ዘላቂነት እንዲኖረውና ስር ሰደድ እንዲሆን ምኞታችን ነው። እንዲሁም የአማራ ህዝባዊ ፋኖ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ለህዝባዊ ፋኖ ጥሪ ቀርቦ እንዲሁ ድርድር ቢደረግ ሰላሙ ለወደፊት የተጣራና ጥሩ እንዲሆን ያደርገዋል።

ከዚህ በኃላ እነሱ ተደራድረው ሲመለሱ ተፈናቃዩም ተሳታፊ ቢሆንና አብሮ ቢሳተፍና ቢነጋገር በጣም ደስ ይለናል። ምክንያቱም ይሄ ተፈናቃይ ነው ገፈጣ ቀማሹ ፣ ኃላም ሄዶ አደጋ ላይ የሚወድቀው፣ በፊትም የወደቀው ይኸው ተፈናቃይ ነው ስለዚህ ሰላሙ ዘላቂ እንዲሆን ተፈናቃዩ በተግባር በውይይት ላይ ተሳታፊ ቢሆን መልካም ነው። "

#3 አስተያየት ሰጪ

" ድርድር መስማታችን በጣም ጥሩ ነው።

ያ ውይይት ሀገርም ያረጋጋል። እኛ ሰላም በማጣታችን ነው እዛ ካፈራነው ንብረት የወለድናቸውን ልጆችና የተለያየ ነገር አጥተን ዛሬ ቀን በፀሀይ ማታ ለብርድ ሸራ ውስጥ ያለነው።

ሰላሙ በጣም ትልቅ ነገር ነው ግን ይሄ ነገር ሲታሰብ መንግሥት እና ኦነግ ሸኔ መግባባትና ድርድር ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያ ክልል ላይ ብሄር ብሄረሰቦች ይኖራሉ በተለይ 4ቱ ወለጋ ላይ ይታወቃል እሱን ታሳቢ ያደረገና ከግምት ያስገባ ድርስር መሆን አለበት።

ሰው እንዴት እንደሚኖር ፣ ተፋቅሮ፣ አንድ ላይ መብቱ ተከብሮ ፣ የሚፈልገውን አግኝቶ ወጥቶ ገብቶ ሰርቶ እንዲኖር ነው ሰላም የሚያስፈልገው። መቼም አንደኛው ገፍቶ አንደኛው ተገፍቶ እንደማይኖር ይታወቃል ስለዚህ ይህን ከግምት ያስገባ ውይይት እና ድርድር ተደርጎ ኦሮሚያን ሰላም ለማድረግ ከሆነ በጣም ጥሩ ነው። ተስፋ ሰጪ ነው።

ሰላም ከራሳቸው ክልል ነው የሚጀምረው ፣ ከኦነግ ሸኔ ጋር ታርቆ የሚፈልጉትን መፍታት ከቻሉ ያለው ነገር ሊፈታ ይችላል። 

እዛ ኪረሙ አካባቢ ያሉ የሁሉም ወገን ነው የተፈናቀለው ይሄንን እውነት በጥልቀት የሚሰራበት ከሆነ መጀመሪያ ህዝብን መመለስ ሳይሆን አካባቢው በአግባቡ ካረጋጋና ሰላሙ ከተጠበቀለት በኃላ የተፈናቀለና የተጎዳ ህዝብ እንዴት መመለስ እንዳለበት ማቀድና ካስገባም በኃላ ምን ይደርስበታል ? ምን ያስፈልገዋል ? የሚለውን ማሰብ ያስፈልጋል። ድርግም ያለ ሀሳብ መሆን የለበትም። "

#4

" ሰላም በውይይት እንጂ በአፈሙዝ እንደማይመጣ እንረዳለን። እኛ ነገ ከነገ በስቲያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ሄዶ የመኖር ነገር ያሰጋናል። ለምን ? ቢባል ከዚህ ቀደም በየቦታው ተሰጋስገን ያለነው። አንድነት የለንም ስለዛ ገፈጣ ቀማሽ ሆነናል። አሁን ደግሞ በየቦታው ሄደን መውደቃችን ያሳስበናል፤ ከመጠን በላይ ። ያው በጠረጴዛ ዙሪያ ተወያይቶ ሰላም እንዲመጣ ሙሉ ተስፋ አለን። "

#5 አስተያየት ሰጪ

" ይሄ ተፈናቃይ ከዚህ የሄደው በእኛ ምክንያት ነው ይሄ ሰላም የሆነው በእኛ ምክንያት ነው ተብሎ ልክ ኦነግ ሸኔና የብልፅግናው ኦሮሚያ ላይ ብቻቸው የሚደራደሩት ብቻ ሳይሆን ይሄ ማህበረሰብ ይሄ ብሄር ብሄረሰብ የተፈናቀለውን ከግምት አስገብቶ ለነሱም ሰላም ያመጣል እነሱም እንደዚህ ሆነው መኖር ይችላሉ ተብሎ ያን ሰላም ለመምጣት የመነጨ ከሆነ ለእኛም ለተፈናቃዮቹ እዛም ለሚኖረው ማህበረሰብ ተስፋ አለው ጥሩ ነገር ያመጣል።

ግን የኦነግ ሰራዊት እና የመከላከያ ሰራዊት  ብቻ በመታረቅ ምንም የሚመጣ ፋይዳ አለ ብዬ አላስብም። ሲቪልም ያማከለ ከሆነ ውስጥ ላይ ወርዶ የሚከታተሉ ከሆነ እዚህ ላይ ትልቁን ሚና ይጫወቱታል ብዬ አስባለሁ። "

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
እያንዳንዱ ምርጫ እርሶን ይገልጾታል!

በተለየ መልክ ዘመኑ የደረሰበት የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ከአስገራሚ ውበት ጋር ያካተተ፣ ታጣፊ በመሆኑ በቦርሳ በኪስ ቢይዙት ልክክ የሚል በዘመኑ የመጨረሻ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ዉጤት አካቶ ወደ ላቀ ደረጃ በመድረስ ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ ለተጠቃሚዎች ቀርቧል። እራሶን በልዩነት ለመግልጽ ታስቦ እና ከፍ ያለውን ህልሞን በሚመጥን ደረጃ ተመርቶ  በአስደማሚ ውበት እና ምቾት  ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ ቀርቦሎታል ። የመጪውን ዘመን ፋሽን በአዲሱ ፋንተም ቪ ፍሊፕ ይቀላቀሉ!

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
@samcomptech

አዳዴስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች፣ ለጌመሮች, ለቪዴዮ ኢዲተሮች ፣ ለግራፌክስ ስራዎች ፣ ለዴዛይነሮች አዳዴስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እናቀርባለን።
🔵 @samcomptech

በሚገርም ፍጥነት ፣ ቅለት እና ከ 10 ሰሀት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖችም አሉን።

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።
🔵https://t.me/samcomptech 🔵 
🔼@sww2844

ስልክ፤ 0928442662 / 0940141114
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

" በከተማችን በርካታ በሴተኛ አዳሪነት ሥራ የተሠማሩ ሴቶች አሉ " - ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን

በአዲስ አበባ ከተማ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ በርካታ እንስቶች፣ አፈርማቲቭ አክሽን የሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች እንዳሉ በተደጋጋሚ ይነገራል።

እነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎች ችግር የመቅረፍ ኃላፊነት እስካለበት ድረስ  ምን እየሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ቢሮን ጠይቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን እንደገለጹት፣ " በከተማችን በርካታ በሴተኛ አዳሪነት ሥራ የተሠማሩ ሴቶች አሉ " ብለዋል።

ኃላፊዋ፣ " አሁን ካለሁበት ቢሮ አፃር በጣም በርካታ የማኅበራዊ ጉዳት የደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ወደዚህ ቢሮ ላይ እምናስተናግደው አካል ጉዳተኛ፣ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋውያን በጣም በርካታ የማኅበራዊ ጉዳይ ተጠቂ የሆኑ አካላት ቢሮየን አንኳኩተው ይገባሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

በከተማዋ ምን ያህል በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች እንዳሉ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፣ " እውነቱን ለመናገር ለጊዜው ዳታው የለኝም። ጥናት ሊመልሰው ይገባል " ሲሉ አስረድተዋል።

ኃላፊዋ ይህን ይበሉ እንጂ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በመዲናዋ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ከ25 ሺሕ በላይ ሴቶች አሉ ተብሎ እንደሚገመት፣ ቁጥራቸው ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል፣ ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ የመጠቃት ዕድላቸውም ሚዛን የደፋ እንደሆነ በአንድ ወቅት አስታውቆ ነበር።

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የዓለም የኤድስ ቀን ኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም በተከበረበት ወቅት በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች 210 ሺሕ እንደሚልቅ ገልፆ ነበር።

በወሲብ ንግድ የተሰማሩ፣ እንደ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል በተለያዩ የሥራ ዘርፎች እንዳይሳተፉ እየተገደቡ ያሉ አልካ ጉዳተኞችን በተመለከተ ቢሮው ምን እየሰራ እንደሆነ ባደረጉት ገለፃ ወ/ሮ ወይንሸት፣ በዓመት ከ10 ሺሕ በላይ የሚሆኑ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችን ካሉበት ሕይወት እንዲወጡ የሚያደርግ ፕሮጀክት " ከፍተኛ በጀት " በወጣበት እየተገነባ መሆኑን፣ የአካል ጉዳተኞችን በተመለከተም በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።

አክለውም፣ ፕሮጀክቱ ወደ 50 በመቶ ገደማ እንደደረሰ፣ ይህም በተያዘው በጀት ዓመት (2016 ዓ.ም) ወደ ሥራ ለመግባት የቅድመ ሁኔታ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ አትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
" በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና ይጀመራል " -  ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

በዘርፉ ብቃት ሳይኖራቸው፣ አቅማቸው ሳይረጋገጥና ማረጋገጫ ሳያገኙ ራሳቸውን #መሐንዲስ እያሉ የሚጠሩበትን አሠራር ያስቀራል የተባለለት እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የሚረዳ የማሠልጠኛ ማንዋልና የሚመዘኑበት መመርያ መዘጋጀቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስትር  ደኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ምን አሉ ?

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባ አንድ ባለሙያ በሚሠራበት ተቋም ውስጥ በቆየ ቁጥር የሙያ ደረጃዎች ከመስጠት ባለፈ መመዘኛ ሥርዓት ባለመኖሩ፣ ባለሙያው ለሚጠበቅበት ዕውቀትና ክህሎት ብቁ ነውወይ ሚለው አይታወቅም።

- ከኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ ያለው መመርያ በቅርቡ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ይፀድቅና ወደ ሥራ ይገባል።

- የሚወጣው መመርያ ባለሙያዎች የሚሠለጥኑበት ፣ የሚገመገሙበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ከመሆኑም በላይ የሙያ ግድፈት ሲገኝባቸውም የሚቀጡበትን አሠራር አካቷል።

- አገሪቱ አሁን ባለችበት የኮንስትራክሽን ቁመና የግንባታ ጥራት አደጋ ውስጥ ነው። ሥራ ከተጀመረ በኋላም ሆነ ከመጀመሩ በፊት የሚታየው የጥራት መጓደል አሁን ካልተፈታ በቢሊዮን ዶላሮች የሚፈስበት ዘርፍ ተመልሶ የማይወጣበት ችግር ውስጥ ይገባል።

- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የባለሙያ አቅምና የሙያ ሥነ ምግባር እየተሻሻለ ከመሄድ ይልቅ እየባሰበት ነው የሄደው ፤ ባለሙያው ከአዳዲስ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጋር የሚተዋወቅበትና ራሱን የሚያበቃበት ሳይሆን እያጠፋ የሚማርበት ሆኖ ቀጥሏል።

- በዘርፉ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች የሉም። ባለሙያዎቹ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ብቃታቸው ሊያድግ የሚችለው በራሳቸው ጥረት እንጂ፣ ከዘርፉ በሚያገኙት ትምህርትና ተቋማዊ ዕውቀት አይደለም።

- በአገር ውስጥ የበቁ የሚባሉት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው። በተለይም በምሥራቅና በደቡብ አፍሪካ አገሮች ተፈላጊ ናቸው። በአገር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችም ባሉበት ተቋም ለረዥም ጊዜ ረግተው አይቆዩም። በበገበያ ውስጥም የዋጋ ጭማሪን በየጊዜው መተንበይ በማይቻልበት ሁኔታ የግንባታ መሣሪያዎች ዋጋ አልቀመስ ብሏል።

- ግዙፍ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች ብቻ የሚይዟቸው፣ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች የውጭ ኮንትራክተሮች በሚይዟቸው ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው ዕውቀት እንዲቀስሙ የሚያደርግ አሠራር አልተዘረጋም ይህ የዘርፉ ሌላው ተግዳሮት ነው።

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የግዥ ሥርዓትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ባለሙያ አለመኖሩ ፤ ሁሉም ባወቀውና በገባው ልክ እንጂ በትክክል ሥራውን ተገንዝቦ የሚሠራ የለም።

- በኮንትራት አስተዳደር የተሰማሩ ባለሙያዎች በአንድ ጉዳይ ባለመግባባታቸው ምክንያት ክስ ሲመጣ ተመልሶ ውልን ከመቃኘት ውጪ፣ ከጅምሩ የኮንትራት ውል አስተዳደርን ዝርዝር ጉዳይ ተረድቶ የሚያስረዳ ባለሙያ የለም።

- ለኮንስትራክሽን ጥራት መጓደል ፦ በግዥ ሥርዓቱ ላይ ያለው አሠራር፣ የፕሮጀክቶች ዲዛይን የተሟላና የተደራጀ አለመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው። ወደ አፈጻጸም ሲገባ ባሉት ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች የአቅም ውስንነት የተነሳ የሚታሰበውን ጥራት ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል።

- በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከመሬት ልየታ ጀምሮ ሕንፃው ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መሟላት ያለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች፣ አጠቃላይ ይዘትና ቁመናው ምን መምሰል እንዳለበት የተቀመጡ ስታንዳርዶች የሉም። በዚህም በኢትዮጵያ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ሲገመገሙ፣ የመኖሪያ ቤት ለመባል የተሟላ ቁመና ያላቸው ከ25 በመቶ የማይበልጡ ናቸው። 75 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው።

- ለቤቶቹ ጥራት መጓደል ምክንያት ከመጀመሪያው የግንባታ ዕቅድ ጀምሮ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ መሟላት ባለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የተቃኙ አለመሆናቸው ነው።

- ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ ሚገነቡ ቤቶች ለሰው መኖሪያ ለመባል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ባሟላ መንገድ እንዲሆን፣ የሕግ ማዕቀፍና ስታንዳርድ ይዘጋጃል። በአሁኑ አሠራር ግን ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ ውል ገብቶ ግንባታ ከጀመረ በኋላ ፣ በጥራትና በጊዜው ያጠናቅ ወይም አያጠናቅ መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት የለም ብለዋል፡፡

ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መምጣቱ ላይቀር የሚያስጠብቀን የእረፍት ቀን ደርሷል! ዘና ፈታ እንበል! #መክሰስTime ደርሷል- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Looking forward to snacking on the weekend with SUNChips. #SUNChips 😋 #SunnyMoments. ☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
የሸሪዓ መርህን ለማረጋገጥ....
============
የሲቢኢ ኑር አገልግሎታችንን የሸሪዓ መርሆዎችን በጠበቀ መልኩ ለመስጠት
በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት፣ እውቅናና አመኔታን ያተረፉ፣
በዘርፉ በቂ የትምህርት ዝግጅት፣ ጥልቅ እውቀትና ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ
አምስት አባላት ያሉት የሸሪዓ መማክርት ኮሚቴ በመሰየም
ከባንካችን ጋር በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

“ዓላማችን ሲቢኢ ኑርን የሸሪዓ መርህን የተከተለ መሪ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ማድረግ ነው!”

ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ!

ትክክለኛው የቴሌግራም ገፃችን https://t.me/combankethofficial
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
" የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም #ሰላም ነው " - የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ

የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ " ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት " በሚል በየማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው አለ።

የቅዱሱ ስፍራ ህንጻም ሰላም ነው ብሏል።

" የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቀደምት ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ነው " ያለው ቢሮው " በዚህ የዓለም ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም " ብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬም መሠረት ቢስ ነው ሲል ሀልጿል።

" በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም። " ያለው ቢሮው " የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ሰላም ነው " ሲል አሳውቋል።

በላሊበላ አካባቢ በተለያየ ጊዜ ግጭት እያገረሸ የሰው፣ የንብረት ጉዳት እየደረሰ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑንም በቀጠናው የመንግሥት ኃይሎች እና የታጠቁ ኃይሎች ዳግም ግጭት ላይ ነበሩ።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአካባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት
የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን አሳውቃ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን የገለፁ ሲሆን ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ብፁዕነታቸው የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም የቅዱሱ ቅርስ የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ በጉዳዩ ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia