TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል። የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በዛሬው የምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ፤ " የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ…
#TPLF

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የዛሬው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር።

ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን #ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።

5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

በዚህም #በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ይነሳ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ፀድቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔውን ተከትሎ ባሰራጨው መረጃ ፤ " በህወሓትና በፌደራል መንግስት በኘሪቶሪያ የተደረገውን ሥምምነት ለማጽናት ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት #አማራጭ_የሌለው ጉዳይ መሆኑን የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተነስቷል " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) መግለፃቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ትላንት ከዚህ ዓለም በሞተ ስጋ መለየታቸው መገለፁ ይታወቃል።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ/ም ምሽት ነበር ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ ከ፲፯ ዓመታት በፊት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእረ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ የተሾሙ ነበሩ።

ብፁዕነታቸው አስኬማ መላእክት ከሚለበስበት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲያገለግሉ እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል።

ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በመንበረ ጵጵስና ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከአገልጋይነት እስከ የበላይ ጠባቂነት በአባትነት አገልግለዋል።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የሚከበሩት እና የሚታወቁት የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ነው የተፈፀመው።

ዶ/ር ተወልደብርሃን ገ/እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ/ም ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የዛሬው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር። ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን #ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል። 5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። በዚህም #በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ…
#TPLF

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እንዲሁም የፌዴራል መንግስትን ወክለው ከህወሓት ጋር የተደራደሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስለ ህወሓት / TPLF ከሽብርተኛ ድርጅትነት ዝርዝር መሰረዝ በተመለከተ ምን አሉ ?

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

" #ሠላም ሰጥተን የምንቀበለው በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ያሉ ቅሬታዎችን በይቅርታ በማለፍ የትግራይም ማህበረሰብ የሀገራችን አካል በመሆኑ፣ ዜጎች ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የትግራይ ሕዝብ በም/ ቤቱ መቀመጫ አግኝተው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል እንዲወስኑ እና እንዲሳተፉ ዕድል መስጠት የሚያስችል የሠላም ስምምነቱ አካል በመሆኑ የህወሓትን የአሸባሪነት ስያሜ ማንሳት ያስፈልጋል።

ሌሎች ቀሪ ስራዎች አካታች ሀገራዊ የምክክር መድረኮችን በማመቻቸት በሀገራችን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ይሰራል። "

ህወሓት በህ/ተ/ም/ቤ ከአሸባሪ ድርጅትነት በ61 ተቃውሞ ፣ በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
" ከአሸባሪነት መሰረዙን በፅኑ እቃወማለሁ " - ኢዜማ

ኢዜማ የህወሓትን ከአሸባሪነት መሰረዝ " በፅኑ እቃወማለሁ " አለ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝን በተመለከተ ውሳኔውን በመቃወም መግለጫው አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው ፤ " ህወሓትን ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም " ብሏል።

ፓርቲው የ " ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መሰረዝ የተቃወመባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ያሳወቀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፦

- ህወሓት በፕሪቶሪያው ስምምነት አንቀጽ 6 መሠረት ትጥቅ ሙሉ በሙሉ አልፈታም።

- በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይን የሽግግር መንግሥትን የፌደራሉ መንግሥት በበላይነት እንዲያቋቁም ስምምነት ላይ ቢደረስም አሁንም ህወሓት በብቸኝነት የሽግግር መንግሥቱ አውራ ሆኗል ፤ ይኽም ህወሓት ዳግም የሀገር ስጋት የሚኾንበትን ዕድል እንደመስጠት የሚቆጠር ነው።

- በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙ፣ ሰብዓዊ ቀውስ ያደረሱ፣ ዜጎችን በጦርነት እንዲማቅቁ ያደረጉ፣ የሀገር ኢኮኖሚና፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ የከተቱ የሕወሓት አመራሮች በሕግ አልተጠየቁም።

- በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ትግራይን እንዲቆጣጠር አልተደረገም።

- የተጨፈጨፉ የሰሜን ዕዝ አባላት የመስዋዕትነት ምልክት የሚኾን ሐውልት ወይም ማስታወሻ በሰሜን ዕዝ ዋና ማዘዣ አልተደረገም።

- በህወሓት ቆስቋሽነት ሀገራችን ላይ ለደረሰው ውድመትና ሰቆቃ ፍትሕ እና ካሣ አልተሰጠም የሚሉት ይገኙበታል።

ኢዜማ ህወሓት የሚለው የፖለቲካ ድርጅት ስም በሕግ እንዲታገድ አለመደረጉ ከላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ቡድኑ ከሽብርተኝነት ሰርዞ ከተጠያቂነት ነፃ ማድረግ ሊቀለበስ የማይችል ጥፋት ነው ብሏል።

ከዚህ በኋላ በ " ህወሓት " አማካኝነት ለሚደርስ ሀገራዊ ጉዳትም ዋነኛ ተጠያቂዎች ገዢው " የብልጽግና ፓርቲ እና መንግሥት " እንደሚኾኑ ከወዲሁ እንገልጸለን ሲል አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ሌላው ቢቀር በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ግዴታዎች አየተፈፀሙ መሆኑን በቅጡ ሳያረጋግጥ፣ ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ ለፈጸመው የሀገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆን እና በህወሓት የእብሪት ጦርነት የግፍ ገፈት ቀማሽ ለሆኑ በተለይ በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ለሚገኙ ወገኖቻችን ፍትሕ ሳይሰጥ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲሰረዝ መወሰኑ ታሪክ ይቅር የማይለው ፍርደ ገምድልነት ሲል ውሳኔውን አውግዟል።

ሕወሓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላትን በመጨፍጨፍ የሀገር ክህደት ፈጽሟል ያለው ኢዜማ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ ለደረሰው ሀገራዊ ቀውስ ቁጥር አንድ ተጠያቂ ህወሓት ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Tigray

" በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ ነው " - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዛሬ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ የፌዴራል መንግስት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዜዳንትነት የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ትግበራ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ስለመግለፃቸው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ህወሓት ከሽብርተኝነት መዝገብ ስለመሰረዙ ምን አሉ ?

" በዛሬው ዕለት ህወሓት ከሽብር መዝገብ ተሰርዟል። ስለሆነም ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራው የሚጀምርበት ሁኔታ ተሟልቷል።

#በጀት የማዘጋጀትም ይሁን ሌሎች #ከእስረኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የወንጀል ክሶችን በማንሳት እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሁለቱም ወገን በኩል ግኝኑነት ተጀምሯል።

በመሆኑም በበኩላችን በጓድ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራዎቹ እንዲሳኩ ለማድረግ ሁሉንም አቅማችንን በማቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን።

የትግራይ ህዝብም በሁሉም አቅሙ የጊዜያዊ አስተዳደራችን ደግፎ እንዲሰማራ ጥሪ እናቀርባለን። "

ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን አሉ ?

" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፋጠን አሸባሪነት የሚለው ሳይነሳ ቀድመን ነው እየሰራን የመጣነው። ጊዜያዊ መንግስቱን ለማቋቋም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸውን ሁሉም ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ ነው።

ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ሁሉም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተመለከተ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ በውስጥም በውጭም መድረኮችን በማዘጋጀት ተሰርቷል።

ኮንፈረንስ በማዘጋጀት እና ከኮንፈረስን በኃላ ምርጫዎችን በማካሄድ ሊያካትታቸው የሚገባ ፈፃሚ አካላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ #ህወሓት እና #ባይቶና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሰራዊት ፣ የትግራይ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሳተፉ አካላት ተሟልተን ለማዕከላዊ መንግስቱ አሳውቀናል። "

ዶ/ር ደብረፅዮን #ህወሓትን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ድርጅታችን ህወሓት የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ሰላም የሰፈነባትና ብሔራዊ ክብሯ የተጠበቀች ትግራይን ለመገንባት ሁሉንም አቅሙን በማቀናጀት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚታገልበት ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ ምን ይዟል ? - ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። - በጸደቀው…
#ኡጋንዳ

ምዕራባውያኑ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ #እየተቃወሙ ናቸው።

የኡጋንዳ ፓርላማ ትላንት ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጋር በተገናኘ አዲስ ህግ አውጥቷል።

ይኸው ህግ በኡጋንዳ ምንድር ማንም ሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ በሚል ማንነቱን ቢገልፅ ህይወቱን ሙሉ / ለበርካታ አመታ እስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ #ሞትም ያስፈርዳል።

ይህ ህግ ትላንት ማክሰኞ በፓርላማ በከፍተኛ ድምፅ ነው የፀደቀው።

ይህንን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምዕራባውያኑ ውሳኔውን መቃወም ጀምረዋል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ህጉን " #አፋኝ " ሲል ነው የተቃወመው። ተቋሙ ህጉን " አደንጋጭ ህግ " ሲልም ገልጾ " መድሎ እና ጥላቻን ያበረታታል ስለሆነም ሀገሪቱ እንደገና ህጉን ትፈትሽ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #አንቶኒ_ብሊንከን እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ሚኒስትር #አንድሪው_ሚቼል አዲሱን ህግ ስለማውገዛቸው ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

አዲሱ ህግ የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በፈረሙ ቅፅበት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው "  ሲሉም ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ አሳስበው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ: የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ታላቁ_የረመዷን_ወር

Photo Credit : Haramain

@tikvahethiopia