TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MadingoAfework

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MadingoAfework

የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ይፈፀማል።

ስርዓተ ቀብሩ 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ነው የተነገረው።

የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን የኮሚቴው ቃል አቀባይ ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን " የቀብር ሥነ ስርዓቱ ሐሙስ ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል። ከቀብር ሥነ ስርዓቱ አስቀድሞም የሽኝት ፕሮግራም ይካሄዳል " ብሏል።

ይህን በተመለከተ ዝርዝሩን ኮሚቴው በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ተናግሯል።

#Update : ነገ በድምፃዊ ማዲንጎ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በወዳጅነት ፓርክ ከ6 ሰዓት ጀምሮ ስንብት ይካሄዳል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸምም ተገልጿል።

@tikvahethiopia