TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠናቋል 🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ 👉 1ኛ 🇪🇹 ዳዊት ስዩም 👉 2ኛ በመሆን ወደ ፍፃሜው አልፈዋል። #የሴቶች_5000_ሺህ_ሜትር @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የ10 ሺህ ሜትር ባለ ወርቅ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ በሁለተኛው ምድብ የ5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድሯን እያካሄደች ትገኛለች።

@tikvahethiopia
#Update #ኢትዮጵያ🇪🇹

በወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ በተደረገ ውድድር የሀገራች ልጅ ቶሎሳ ቦደና ወደ ግ/ፍፃሜ ውድድሩ ማለፍ ችሏል (ባስመዘገበው ፈጣን ሰዓት) ።

ሌላኛው የማጣሪያ ውድድር ተሳታፊው ኤርሚያስ ግርማ ወደ ግ/ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

የማጣሪያ ውድድሮቹ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፉክክር የነበረባቸው ነበሩ።

More : https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያ በ3,000 ሺህ ሜትር መሰናክል ብር 🥈 እና ነሀስ 🥉 አገኘች።

ወርቅውሀ ጌታቸው ለሀገሯ ብር ስታስገኝ ሌላኛዋ አትሌታችን መቅደስ አበበ ነሐስ አስገኝታለች።

ትውልደ ኬንያዊቷ ለካዛኪስታን የምትሮጠው ጂፕሩቶ ወርቅ አግኝታለች።

የሀገራችን ልጆች በውድድሩ ያሳዩት ፉክክር እጅግ በጣም የሚደንቅ ነበር።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአሜሪካ በመቀጠል በ3 ወርቅ በ4 ብር እና በ1 ነሀስ ከዓለም 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

እንኳን ደስ አለን🇪🇹❤️ !!

@tikvahethiopia
#ፀሀይ_ባንክ

ፀሀይ ባንክ ቅዳሜ ሀምሌ 16/2014 በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ባንኩ በ2.9 ቢሊዮን የተፈረመ ካፒታልና በ734 ሚሊዮን በስራ ላይ የዋለ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ብር 100 ሺህ በማድረግ በ373 ባለአክሲዮኖች የባንክ ኢንዱስትሪውን ተቀላቅሏል፡፡

ምን ይዞ መጥቷል ?

👉 የባንኩ ዓላማ የባንክ ኢንዱስትሪውን
መቀላቀል ብቻ ሳይሆን ፤ በፋይናንስ ዘርፉ በቂ ትኩረት ያላገኙትን የጥቃቅንና አነስቸኛ ፤ ግብርናውን ዘርፍ ፤ የአምራች ኢንዱስትሪውን እንዲሁም አዋጪ ለሆኑ #የፈጠራ_ስራዎች እና #ስራ_ፈጣሪዎች ተደራሽ መሆንና ለሁሉም የሆነ ባንክ ሆኖ አዳዲስ ስልቶችን በመንደፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ቀልጣፋና ደንበኛ ተኮር የሆነ አገልግሎት ለመሥጠት መሆኑን አሳውቋል።

👉 የባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማዘን ዘመኑን የዋጀ መደበኛውን የባንክ አገልግሎት እና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በማቅረብ በኢንዱስትሪው ውስጥ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን፤ የተሻለ የባክ አገልግሎት ይዞ በመግባት ለሁሉ የሚያገለግል ባንክ እንደሚሆን ገልጿል።

👉 ስራ ሲጀምር ከሕብረተሰቡ የሚሰበሰበውን ከፍተኛ ሆነ ሃብት መልሶ የሕብረተሰቡን ህይወት ለሚያሻሻልና ልማቱን ሊያፋጥን ለሚችሉ ስራዎች እንዲውል ትኩረት ሰጥቶ እደሚሰራ ገልጿል።

👉 በባንኩ የምረቃ ዕለት በ30 ቅርንጫፎች በመጀመርና በቅርብ ቀን የቅርጫፎቹን ቁጥር ከ50 በላይ እንደሚያሳድግ የገለፀ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ 100 ቅርንጫፎችን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለክፈት የሚያስችለውን ስራ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#SNNPRS

አንደኛ በመኸር ዝናብ መዛበት ሁለተኛ በግጭት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች መጨመር በደቡብ ክልል የተረጂዎችን ቁጥር ጨምሯል።

የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንደሚለው፤ አሁን ላይ በደቡብ ክልል 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፋ ረሃብ / የምግብ ዋስትና ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል ተንብዩዋል።

የከፋ ለሆነ የምግብ ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ የተባሉት ከዚህ ቀደም የምግብ ችግር ኖሮባቸው በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሲደገፉ የነበሩ (917 ሺህ)፣ በግጭት የተፈናቀሉ (122 ሺ) ፣ በመኸር ዝናብ መጥፋት ምርት ያላገኙ (2.3 ሚሊዮን) ነዋሪዎች ናቸው።

በደቡብ ክልል የከፋ የምግብ እጦት ካለባቸው አካባቢዎች አንዱ የኮንሶ ዞን ህፃናት እና እናቶች ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸውን ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።

በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት እየደረሰ እንዳለሆነ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

አንድ የኮልሜ ክላስተር ነዋሪ ፦

" ምንም አይነት እየመጣ አይደለም። ምንም አይነት ድጋፍ አላገኘንም። እኛ መጠበቅ ካለብን መንግሥት እንዲደርስልን ነው። ከሞት እንዲታደገን ነው። በገንዘብም ቢሆን መንግሥት እንዲረዳንና ከዚህ ዓመት ቢያሻግረን ብለን ነው የምንማፀነው። "

ሌላ ነዋሪ ፦

" አንደኛ ዝናብ ጠፋ ፣ በዛ ላይ የከብት ሳርም የለም። በመንግስት በኩል የሚደረግ እርዳታም የለም " ብለዋል።

የኮንሶ ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፈኔ ቲጫኖ በዞኑ ካላት ተረጂዎች እስካሁን ድጋፍ ያገኙ ግማሽ እንኳን እንደማይሆኑ ተናግረዋል።

በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር ጀምሮ የምግብ ድጋፍ ፈላጊው ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/SNNPRS-07-21

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኮንሶ ያለው የምግብ እጥረት ! በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው ኮንሶ ዞን በተከሰተ የምግብ እጥረት ሳቢያ 13 ሕጻናት መሞታቸውን ተሰምቷል። በኮንሶ ዞን ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚጥለው ዝናብ ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ እንዲሁም በተከታታይ በነበሩ ግጭቶች የተነሳ ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አቶ ተስፋዬ ጫሬ የኮንሶ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " ከሐምሌ…
#ማስታወሻ

ከዚህ ቀደም በኮንሶ ስለተከሰተው የምግብ እጥረት መረጃ መለዋወጣችን እና የዞኑ የመንግስት ተጠሪ ባለው የምግብ እጥረት ሳቢያ 13 ሕጻናት መሞታቸውን መግለፁ አይዘነጋም።

ስለ ኮንሶ ሁኔታ ማወቅ ያለብን ምን ምን ጉዳዮች ናቸው ?

- ነዋሪዎች ለችግር የተጋለጡት ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚጥለው ዝናብ ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ እና በተከታታይ በነበሩ ግጭቶች የተነሳ ነው።

- ከሐምሌ 1 ጀምሮ ባሉት 6 ወራት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 190 ሺህ 825 ይሆናል።

• 122 ሺ 735 በዝናብ እጥረት ለችግር የተጋለጡ
• 68,087 በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው እርዳታ የሚጠብቁ ናቸው።

- ዞኑ በበልጉ ምርት 3,137,244 ኩንታል ለማምረት አስቦ ነበር ነገር ግን አሁን ሲሰራ ሊገኝ ይችላል ተብሎ የታሰበው 476,874 ምርት ነው። ይሄ ማለት 16% የዞኑን ህዝብ ይመግባል። ቀሪው አንድ መቶ ዘጠና ሺ ስምንት መቶ ሀያ አምስት ዜጎች ከሀምሌ በኃላ ሊራቡ ይችላሉ።

ነዋሪዎችን ለማገዝ ምን እየተደረገ ነው ?

በመንግስት ተቋማት ከሚደረግ ድጋፍ ውጭ የኮንሶ ልማት ማህበር ነዋሪዎችን ለመታደግ ዘመቻ እያደረገ ነው።

እንዴት ? ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በተረጋገጠው አካውንት 1000056435364 ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድጋፋቸውን እንዳያደርጉ ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ ነው።

ማህበሩ በተረጋገጠው የፌስቡክ አካውንቱ (Konso Development Association/KDA) ላይ ድጋፍ እያደረጉ ያሉ ዜጎችን ድጋፍ ያደረጉትን የብር መጠን ከፎቷቸው ጋር በማጋራት ሌሎችን የማነሳሳት ስራ እየሰራ ነው።

ከዚህ ባለፈም በቡድን እና በግል የምግብ እህል በመግዛት ወደ ልማት ማህበሩ ቢሮች ድጋፎች እንዲሰበሰቡ እያደረገ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ፦

" ...የ20/80 ባለ ሶስት መኝታ ቤት እጣ ውስጥ ያልተካተተ መሆኑ ይታወቃል ይህም ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 9 አመታት ያህል ሳያቋርጡ በመቆጠብ ላይ ቢገኙም በ14ኛ ዙር አጣ ውስጥ ሳይካተት መቅረቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በእጣው ተሳታፊ ያልሆኑ የማህበረሰብ ከፍሎች መግለጻቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ማወቅ ተችሏል፡፡

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካለው ገቢ አንጻር በ1997 እና 2005 ዓ/ም ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ ምዝገባ በማካሄድ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር መቅረፍ ሲገባው በቀደመው አሰራር የነበረውን ኢፍትሃዊ፣ ለዘረፋና ለማጭበርበር የተመቸ የእጣ አወጣጥ አሰራር የቀጠለ መሆኑን በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡

ስለዚህ ከዚህ አሰራር ራሱን በማረም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች ግልፀኝነትንና ፍትሃዊነትን በተከተለ ሁኔታ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡ "

(የኢሰመጉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Update

ስቴም ፓወር (STEMpower) ከቪዛ (Visa) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት 4 ዙሮች ከ600 በላይ ሰልጣኞችን አሳትፏል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ ሰልጣኞች መካከል የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ መሬት በማውረድ ሥራ የጀመሩ እና ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉ ሰልጣኞች ይገኙበታል።

አሁን ደግሞ 5ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት ምዝገባው እየተካሄደ ነው።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 6 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, Coaching and Pitching)

• 9 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ ሐምሌ 22 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3PK7LY2

#StemPower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስ_አበባ አዲስ አበባ ውስጥ የቀጠለው ዝርፊያና ጥቃት ! ከሰሞኑን የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ላይ እየደረሰ ስላለው ወንጀል መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም። ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ማመልከታችንም የሚታወስ ነው። ለማስታወስ ፦ 👉 አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራበትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት : t.me/tikvaheth…
#ፍትሕ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እና ዝርፊያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ባለፉት ሳምንታት ብቻ 3 በዚሁ አገልግሎት ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ዝርፊያን ጨምሮ ጥቃት ተፈፅሟል (በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ብቻ ሪፖርት የተደረገ) ።

ትላንት ግን ከዝርፊያም ባለፈ የሰው ህይወት ተቀጥፏል።

በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ወገኖች ጉዳዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሆኑን በመግለፅ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ እየጠየቁ ናቸው።

የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ትላንትና በግፍ የተገደለውን ሳልሀዲን ሀሰን ፍትህ እንዲያገኝ ዛሬ ተሰብሰው ጠይቀዋል።

ትላንት ሳልሃዲን አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ገርጂ 24 ኤርትራ ቆንፅላ ፅ/ቤት አካባቢ ተገድሎ መገኘቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ነው ፍትህ እንዲገኝ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪዎች ድምፃቸውን ያሰሙት ፤ ቤተሰቦቹንም ሄደው አፅናንተዋል።

በስራቸው ላይ እያሉ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እና አስተማማኝ ደህንነት እጦት እየተባባሰ መምጣቱን የሚገልፁት አገልግሎት ሰጪዎቹ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

Photo Credit : Solomon Muchie (DW)

@tikvahethiopia