TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን ድጋፍ አልቀበልም፡፡›› የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው

የአማራ ክልል የተፈናቃዮች የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሜቴ ‹‹ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን ድጋፍ አልቀበልም›› ብሏል።

የኮሚቴው ሰብሳቢና የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ #አገኘሁ_ተሻገር ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቀሉ ዜጎች ላደረገው ድጋፍ እናመሰግናለን፤ ነገር ግን የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ያሉበትን ችግር ያላማከለ በመሆኑ የተፈናቃዮች አሰባሳቢ ኮሜቴ ድጋፉን አልተቀበለውም›› ብለዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ውይይቱን ዛሬ በባህርዳር ከተማ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦች የ200ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የተደረገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት ስምንተኛ ዓመት ዛሬ በፓናል ውይይት ሲከበር ነው፡፡ እንደ ኢዜአ ዘገባ ድጋፉን ኢንጂነር ኤፍሬም ውብሸት የግድቡ ግንባታ የኢንጂነሪንግ ሰፖርቲንግ ኦፊስ ክፍል ኃላፊ ተረክበዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ በሱሉልታ ከተማ አስተዳድር በሚገኝ የሻማና ሳሙና ፋብሪካ ላይ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በሰው ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም፤ የእሳት አደጋው በርካታ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከለገዳዲ ግድብ ወደ አዲስ አበባ ውሃ የሚያስገባው መስመር ደርሶበት የነበረው የመሰበር ችግር #ተጠግኖ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

መስመሩ የገጠመውን ብልሽት ባፋጣኝ ለመጠገን በከተማ አስተዳደሩና በባልሙያዎች ብርቱ ርብርብ ከተደረገ በኃላ ጥገናው ተጠናቆ ዛሬ ለአገልግሎት ዝግጁ ወደመሆን ተሸጋግሯል።

ከለገዳዲ ግድብ ወደ አዲስ አበባ ውሃ ከሚያስገቡት መስመሮች መካከል አንዱ ብይዱ ለቆ የነበረ ሲሆን አሁን ጥገናው ከተጠናቀቀ በኃላ መስመሩን የማጠብና አየር የማስተንፈስ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

በችግሩ ምክንያት ውሃ የተቋረጠባቸው የመዲናዋ አካባቢዎችም ከነገ ጀምሮ አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል።

መስመሩ ለብልሽት የተዳረገውም ለረጅም ጊዜ በማገልገሉ ምክንያት እንደሆነም ተረጋግጧል።

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH🔝

በጌዳኦ ዞን ለሚገኙ #ተፈናቃዮች በእናተ በTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በኩል በተሰበሰበው #ገንዘብ_ድጋፍ ለማድረግ በዛሬው ዕለት ወጣቶች ወደስፍራው አቅንተዋል።
.
.
.
አጠቃላይ የተሰበሰብው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ እንዲሁም የተፈፀሙ ግዢዎችን በደረሰኝ ለእናተ የማሳያችሁ ይሆናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ ፓርቲ---ነእፓ🔝

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) የዛሬ የምስረታ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።

ምንጭ፦ ETHIO-NEWS FLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር-የሰላም ዋጋ ስንት ነው?🔝

በዛሬው ዕለት #በባህርዳር ከተማ "የሰላም ዋጋ ስንት ነው?" በሚል የጎዳና ላይ #የሰላም_ጉባኤ ተካሂዷል።

Via NAH(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia