TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቀን ከአንድ ማኪያቶ አንድ ዶላር የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከታቀደለት በላይ 1 ሚሊዮን 569 ሺህ 412 ዶላር ተሰብስቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ በመንገድ ላይ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ #እየጨመረ መምጣቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት፤ በሀገሪቱ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡

Via~EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ተቃሎ የነበረው #የነዳጅ_እጥረት ዳግም ማገርሸቱን በከተማይቱ የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። መንግስት ችግሩ የሚቃለልበትን መንገድም እንዲፈልግ ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተመሳሳይ...

#በአዳማ ከተማ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ እየተቸገሩ እንደሆነ የከተማው ነዋሪዎች ለTIKVAH-ETH ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የት እንደደረሱ #አይታወቅም
.
.
“አቶ #ጌታቸው_አሰፋን ለመያዝ ተኩስ መግጠም አስፈላጊ አይደለም”

አቶ #ብርሃኑ_ፀጋዬ(የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ለ530 የፌዴራል ታራሚዎች #የገና_በዓልን ምክንያት በማድረግ #ምህረት መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ። የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠልና የፓለቲካ ምህዳር ለማስፋት ለታራሚዎቹ ምህረት መደረጉን ነው ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ መስከረም አራት ቀን በቡራዩ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት በተሳታፊነት በጠረጠራቸው 109 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ፡፡

ከተጠርጠሪዎቹ ውስጥ 81 የተያዙ ሲሆን፥ 28 የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጥቶባቸው እየታደኑ ነው ተብሏል፡፡

የቡራዩን ጥቃት ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በታያው የጸጥታ ችግር በማነሳሳት እና በተሳታፊነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስቀመጠው በሐዋሳ ከተማ በወላይታ በሲዳማ ብሄር መካከል ግጭት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱና ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ከ90 በላይ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባና የፖሊስ አባላትም ይገኙበታ፡፡

ጠቅላይ አቃቢህግ በምርምር ደረስኩበት ባለው መረጃ መሰረት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች እና የጸጥታ ችግሮች በተደራጀ ቡድን የሚመሩ ናቸው ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ‼️

የአማራ መስተዳድር የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ መኖሪያ ቤት ዉስጥ ትናንት የተያዘዉ የሽጉጥ «ክምር» በየሥፍራዉ #ሊከፋፈል እና #ሊሰራጭ የተቃደ እንደነበር የመስተዳድሩ የሠላም እና ደሕንነት ቢሮ አስታወቀ። ባሕርዳር በሚገኘዉ የመስተዳድሩ የልዩ ጥበቃ አዛዥ በነበሩት በኮምንደር ዉበቱ ሺፈራዉ መኖሪያ ቤት፣ በሰባት ጆንያዎች ተቋጥሮ የተገኙት ሽጉጦች ብዛት 498 ነዉ። የአማራ መስተዳድር የሠላም እና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጌድየር ጄኔራል #አሳምነዉ_ፅጌ ዛሬ ለDW እንደነገሩት ሽጉጦቹ በሙሉ አዳዲስ እና ቱርክ ሠራሽ ናቸዉ።

ሽጉጦቹ የተያዙት ጉዳዩን በቅርብ በሚያዉቁ ወገኖች ጥቆማ እና ትብብር ነዉ። ጄኔራል አሳምነዉ አክለዉ እንዳሉት ሽጉጦቹ የተያዘባቸዉ ኮማንደር ዉበቱ በቁጥርጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ «አባሪ ተባባሪ» ተብለዉ የሚጠረጠሩ ወገኖችን ለመያዝ ክትትሉ ቀጥሏል። ጄኔራል አስምነዉ «ባንድ እና በሁለት ሰዉ ይሠራል ብለን እንገምትም» ብለዋል።

አንድ የክልሉ ፀጥታ ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሕን ያክል ጦር መሣሪያ ደብቀዉ መገኘታቸዉን፣ ጄኔራል አሳምነዉ «አሳዛኝ እና አሳፋሪ» ብለዉታል። ሽጉጦቹ ሊከፋፈልላቸዉ ነበር የተባሉት ወገኞችም ሆነ የተላከበት ስፍራና የላኪዉ ማንነትም እስካሁን በይፋ አልተነገረም።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሶማሌ ላንድ ተነስተው በቶጎጫሌ ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የነበሩ ኮድ-04046፣ ኮድ-05759 ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙዎች እና ኮድ-39416 የጭነት ተሸከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸዉ 550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ ምግብ ነክ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነዉ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅግጅጋ ለመግባት ሲሞክሩ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች እንዲሁም በጉምሩክ ሰራተኞች ክትትል ታህሳስ 23/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 እስከ ምሽት 2 ሰዓት ባለዉ ጊዜ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ #ደመላሽ_ተሾመ አያይዘዉ እንደገለጹትም በድርጊቱ ተሳታፊ የነበረዉ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ዉሎ አስፈላጊዉ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዉ በቀጣይም ህብረተሰቡ ይሄን መሰል ድርጊቶች በንቃት በመከታተል ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via~EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ 117 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገባቸው ሶስት የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች በተያዘው ዓመት #እንደሚጠናቀቁ ተገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብሮድካስት ባለስልጣን ምላሽ🔝

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1፣ ድሬትዩብን የተመለከተ አንድ ዘገባ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡ ድሬትዩብ ዘገባው፣ “መልካም ሥምና #ዝናዬን በማጉደፍ ድርጅታችን በሕዝብ ላይ ያለውን ተደማጭነት እና ተዐማኒነት አላግባብ ሆን ብሎ ለመሸርሸር በማሰብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶብናል” በሚል ለብሮድካስት ባለሥልጣን ክስ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ክሱን አስመልክቶ ከሸገር የቀረበውን ምላሽ የተመለከተው የብሮድካስት ባለሥልጣን፣ “ባካሄድኩት ማጣራት ሸገር ያቀረበው ዘገባ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና ሙያዊ ሃላፊነት በተመላበት አግባብ ተዘጋጅቶ የተሰራጨ” ነው ሲል ብያኔውን ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርመራ እየተደረገ ይገኛል‼️

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከሰቱ ግጭቶች አቀነባባሪዎችን ለመለየት ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። እንዲሁም በችግር ፈጣሪ #ተማሪዎች ላይ ተቋማዊ #የዲሲፕሊን_እርምጃዎች መውሰድ ተጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"#የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል‼️"

ምዕራብ ኦሮሚያ እና ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ባለፉት ተከታታይ ወራት በርካታ ሰዉ በገደሉ እና ባፈናቀሉ ታጣቂዎች ላይ «የማያዳግም» ያለዉን እርምጃ መዉሰዱን ባካባቢዉ የሠፈረዉ ጦር አስታወቀ።

በቅርቡ «ኮማንድ ፖስት» በሚል መጠሪያ ወደ አካባቢዉ የዘመተዉ ጦር ዛሬ ባሰራጨዉ መግለጫ እንዳለዉ ቁጥራቸዉን ያልጠቀሰዉ የታጠቁ «ፀረ ሠላም» ኃይላት እጅ ሰጥተዋል፣ እጅ ባልሰጡት ላይ ደግሞ የኃይል እርምጃ ወስዶ «አበረታች» ያለዉን ዉጤት አስመዝግቧል።

ሰዉ የገደሉ፤ ሕዝብ ያንገላቱ፣ የዘረፉ፣ ያፈናቀሉና መንገድ የዘጉ ኃይላትን #መያዙንም አስታዉቋል።

በመግለጫዉ መሠረት ጦሩ፣ ከያዛቸዉ ኃይላት ላይ በርካታ የጦር መሳሪያ እና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ #ማርኳልም

ሠላምን ያዉካሉ በተባሉት ኃላት ላይ ጠንካራ እርምጃ በመወሰዱ #ተዘግተዉ የነበሩ መንገዶች፣የንግድ መደብሮች፣ የጤና እና የሌሎች አገልግሎት መስጪያ ተቋማት #መከፈታቸዉን መግለጫዉ ጠቅሶ፣ ዝርዝሩን ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።

የኦሮሚያ የጤና እና የትምሕርት ቢሮዎች በአብዛኛዉ የምዕራብ ኦሮሚያ የጤና እና የትምሕርት አገልግሎት መቋረጡን ትናንት አስታዉቀዉ ነበር።

ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ግዛቶች ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ በተባባሰዉ ግጭት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸዉ፣ በመቶሺሕ የሚቆጠሩ መፈናቀላቸዉ እና በርካታ ሐብትና ንብረት ወድሙ ወይም መዘረፉ በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ካፋ ዞን፣ ደቻ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ 9 ሰዎች በድንገተኛ ጥቃት #ተገድለዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ባንድ ሠፈራ ጣቢያ ውስጥ መሆኑን ሪፖርተር የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ አስነብቧል፡፡ በጥቃቱ ሌሎች 4 ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡ ጥቃት አድራሾቹ ከዞኑ ጠረፋማ አካባቢዎች ወይም ከአጎራባቾቹ ቤንች ማጂና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የመጡ መዔኒት የተባሉ አርብቶ አደር ጎሳ አባላት እንደሆኑ ተገምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር(wazemaradio)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ‼️

የ2011/18 የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ነን ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የዉጭ ትምህርት እድል ካልቻለም ደግሞ ሀገር ዉስጥ የማስተርስ ትምህርታችንን እንድንማር ቃል መግባታቸዉ በኢትዮጵያዊያን ህዝብ ሁሉ የታወቀ ነዉ ሁሉም ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ መዘገባቸው ይታወሳል።

ይሁን አንጂ እስካሁን ባለዉ ጊዜ ምንም አይነት የትምህርት እድልም ሆነ ስላለው ነገር ትክክለኛ መረጃም ቢሆን አላገኘንም።

በዚህም ምክኒያት፦

1, ብዙ የትምህርት እድሎች አምልጠውናል

2. የስራ እድሎችንም አልፈውናል

3. UAE scholarship አለ ሁሉንም ዶክመንት ፓስፖርትንም ጨምሮ አስገቡ ተብሎ አስገብተን ተሰረዘ ተባልን በዚህም የተነሳ ላልተገባ ወጪ ተዳርገናል፡፡

4. ወርቅ የሆነውን ጊዜያችንን በከንቱ እያሳለፍን እንገኛለን፤ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ እንረዳለን ቢሆንም እድገት የሚመጣዉ በአስቸጋሪም ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን ልማትን በጎን ማሰኬድ እንደሚቻል እናምናለን። ይህ መልዕክት ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከታላቅ አክብሮት ጋር እንዲደርስ እንጠይቃለን፡፡ እንዲሁም አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠንም እንጠይቃለን እናመሰግናለን!!

የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia