TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ። ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም። " ከፍተኛ የሆነና…
#Update #GambellaUniversity

“ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ' ይነሳልን ' ያሉት ሰው #ተነስቷል ” - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ዩኒቨርሲቲው ሪፎርም ቢያደርግም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው የፋይናንስ ጉዳይ እንዳልተደረገ፣ በዚህም ችግሩ በተለይ ከክፍያና ከስልጠና ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ፒቲሽን አሰባስበው ዩኒቨርሲቲውን ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸው፤ “ በቢብስብን ነው ወደ ህዝብና ፊትና ሚዲያ የመጣነው ” ብለው የነበረ ሲሆን፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለቅሬታው ምላሽ ተሰጥቶ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ደሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ምን ማላሽ ሰጡ ?

“ ከዚህ በፊትም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ቅሬታውን አቅርበው ቅሬታውን አክኖሌጅ አድርገን በአሰራር ለውጥ ለማምጣት ከተወሰኑ መምህራን ጋር ውይይት አድርገናል፡፡

እንደተባለው በዩኒቨርደሲቲ ደረጃ ሪፎርም ተደርጓል፡፡ ያ ማለት ከዚህ በፊት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካለው አፈጻጸም አንጻር መዘጋት አለበት ተብሎ፤ ከሚዘጋ ደግሞ ሪሮርም መደረግ አለበት ተብሎ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል አለበት የሚል እምነት አለን እኛም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ያለተማሪዎችና ያለመምህራን የሚሰራው ሥራ የለም፡፡

ስለዚህ መምህራን የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ላለመመለስ ሳይሆን ወደ ሚዲያም የወጡበት 'በ72 ሰዓታት ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እርምጃ ካልተወሰደ ከዩኒቨርሲቲ በላይ ላሉት አካላት ሪፖርት እናደርጋለን ' ብለው ነው፡፡ ያንን ደግሞ እኛ መከልክል አንችልም፡፡

ፋይናንስ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጣቸውን በዬጊዜው እንዲያሻሽሉ አድርገናል፡፡

ሪፎርም አልተደረገም ማለት አልችልም ምክንያቱም እኛ ሥራ ስንጀምር የነበረውን ዳይሬክተር (ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ክፍተት አለበት የተባለውን ሰው) አንስተናል ከዛም በፊት፡፡

አሁን እዛው ክፍል የነበረ በቡድን ደረጃ ያለውን በጊዜያዊነት ነው ያስቀመጥነው፡፡ እሱንም ደግሞ ለማንሳት መጀመሪያም ፒቲሽን አቅርበው ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ፒቲሽን በሚያቀርቡበት ጊዜ ያለውን አብረን ተነጋግረናል እንደምናስተካክል፡፡

ትልቁ ችግር በቂ ፋይናንስ ባለመኖሩ ሁሉንም ጥያቄ በአንዴ መመለስ አይቻልም፡፡ ብዙ ሪፎርም ያደረግንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ 'በ72 ሰዓታት ውስጥ' የሚባለው ግን ፋይናንስ ላይ የሚሰራ ሰው ሰነድ ማስረከብ አለበት፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ክፍተት ነበረ ይህንን ሲያስተባብሩ ከነበሩ መምህራንና በከፍተኛ ማኔጅመንት።

የ10 ዓመት እድሜ ታሪክ ያለው ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ እንዳሉትም ላብራቶሪ በትክክል ሰርቪስ አልተደረገም፡፡ ግን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ ነው ያለው አሁን፡፡ ለመምህራን እውነት ለመናገር ትልቅ አክብተሮት አለን፡፡

የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ስለሚፈልጉ፣ ስለጓጉ ነው እንጂ፡፡ ይህም መብታቸው ነው፡፡ ለምን ይህንን አደረጉ አንልም፡፡ ግን መሻሻል እንዳለበት ከእነርሱ ጋርም ተነጋገረናል፡፡ ግልጽ ነው፡፡ እነርሱ ፒቲሽን አመጡም አላመጡም ያው ሪፎርሙ ይቀጥላል፡፡

ችግሩ ወዲያው የማይቀረፈው በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ የሠራተኛ ምደባ ተደርጓል፡፡ አዲስ ቅጥር ደግሞ በሲቪል ሰርቪስ አይፈቀድም፡፡ ቅጥር ተፈቅዶ ገና በፕሮሲጀር የሚከድበት ነው፡፡ የሰለጠነ ባለሙያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግኘት ይከብዳል፡፡ ጠይቀናል፤ ሊሳካ አልቻለም፡፡

' በ72 ሰዓት ምላሽ ስጡን ' የሚለውም ቢያልፍ እኛ ወስነን ስለነበረ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ይነሳልን ያሉት ሰው ከዛ ተነስቷል፡፡ ባይሉም እኛ እንደ ከፍተኛ አመራር ይህንን ወስነናል፡፡ መወሰናችንን ደግሞ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁን ያለው እውነታ ይሄ ነው፡፡

በቂ በጀት የለም፡፡ ፍላጎትና በጀት ስለማይመጣጠን ቅድሚያ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የ2015 ዓ/ም ያልተከፈሉ እዳዎች እንደተባለው የ12ኛ፤ የዊኬንድ፤ የኦቨርሎድ ክፍዎች እየተከባለሉ መጥተው 2016 ዓ/ም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡

ለመምህራን ስልጠና አለመስጠት፣ ወርክሾፕ ላይ ላብራቶሪ አለማሟላት የተፈጠረው የበጀት እጥረት በመኖሩ ነው፡፡ እጥረቱ ደግሞ እንዲፈታ ከፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተበነጋርን ነው፡፡

በጀትና የምናቅፀደው እቅድ አለመጣጣም ነው፡፡ አንዱ ያነሱት ቅሬታ 'እዛ ያለው ኃላፊ ይነሳልን' የሚል ነው ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ኮሚዩኒኬት አድርገናል፡፡ መምህራንም አሁን ሥራዎችን እየሰሩ ነው፡፡ እንደተባለው ግን በ72 ሰዓት የተባለውን አንደርስታንድ መደራረግ ያስፈልግ ነበር፡፡

ይህንን ፒቲሽን ከተፈራረሙ በኋላ መምህራንን ለማነጋር እየሄድንብት ያለውን ፕሮሲጀር ለማስረዳት ቀጠሮ ይዘንላቸው እኔ ሌላ ስብሰባ ነበረኝ፤ የአስተዳደርና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲያገኟቸው ወደ አዳራሽ ሲሄዱ አንድም ሰው እዛ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን አሁን አዲሱ ሪፎርም ላይ ባለው አመራር 24 ሰዓት በራችን ክፍት ነው፡፡

ከእነርሱ የምንደብቀው ነገር የለም አንድ ላይ ነው የምንሰራው፡፡ ቀጠሮም ይዘንላቸው እዛ ላይ አልተገኙም ” ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ክፍተት እንደነበረበት መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል፤ ለመሆኑ እርምጃ ተወስዷል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፤ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

“ ኮመንት የተደረጉት የፌደራሉ ኦዲት መስሪያ ቤት የአመቱን የኦዲት ሪፖርት ይጠይቃል፡፡ ግኝቶቹ ላይ በቂ ማብራሪያ ወይንም ግብረ መልስ ተሰጥቷል ” ነው ያሉት፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።

ጉባኤው " በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ  ' ይቃወሙናል ' የሚሉዋቸው የተወሰኑ #አመራሮች_ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው " ብለውታል።

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " ሲሉ ገልጸዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ  ፤ " የተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ህወሓት እንደ አዲስ እንደሚዘገብ የሚያደርግ ፣ ወርቃዊው የትግራይ ህዝብ ትግል የሚያጎድፍ በቀጣይ ቅርቃር ውስጥ የሚከት መሆኑን በመገንዘብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መግባባት ተደርሶ ነበር " ብለዋል።

" ይሁን እንጂ የተደረሰው መግባባትና መተማመን ወደ ጎን በመተው ' ከፌደራል መንግስት ተማምነናል ' በሚል ማደናገሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመነጋገር  ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ካድሬ በመደበቅ የተሄዴበት ሂደት ወዳልተፈለገ ወጥመድ እንድንገባ ተደርገናል " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎቱ ብቻ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝቡ ሰላም እንዳይደፈርስና እንዳይረበሽ ከህዝባችንና ከመላ አባላችን በመሆን እንታገላለን " ብለዋል።

" ሁሉም የትግራይ አቅሞች በማቀናጀት በተደራጀ ትግል ከፍተኛ ፓለቲካዊ ድርድር በማካሄድ የህወሓት ህጋዊነት በመመለስ ካጠላብን ዙርያ መለስ ፈተና በመውጣት የትግራይ የተሟላ ደህንነትና እድገት እንደሚረጋገጥ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ድርጅቱ ጉባኤውን እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ ከፍተኛ አመራር አለ " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ለሁለት የከፈለውና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ መክፈቻ ዛሬ ተደርጓል።

የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመክፈቻው ባሰሙት ንግግር ምን አሉ ?

ሊቀመንበሩ " ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና እንዳያገኝና ጉባኤው እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ #ከፍተኛ_አመራር አለ " ብለዋል።

" በፓርቲያችን ውስጥ ተፈልፎሎ ያደገ፣ ፓርቲያችን ለመበተን እየሰራ ያለው የጥፋት ቡድን ያደረገውና አሁንም እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ፥ በየሰዓቱ እየፈጠረው ባለው ማደናገርያ ሁኔታችን ከመጥፎ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህንም ለማስቆም በዘላቂነት ለመቀየር ብቸኛ መፍትሔው 14ተኛ ጉባኤ ማካሄድ እና ማካሄድ ብቻ ነው " ብለዋል።

" ህወሓት አድኖ ህዝብ ከጥፋት መታደግ የጉባኤው ዋነኛ አላማ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የድርጅቱና የህዝቡ የተሟላ ድህንነት ማረጋገጥ በሚችል መልኩ በዴሞክራሲያዊ ውይይትና ክርክር ብቃት ያላቸው አመራሮች መምረጥ ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የአሁኑ ጉባኤ ለድርጅቱ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው " በማለት አክለዋል።

" ህወሓት ፈረሰ ማለት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ፈረሰ ማለት ነው " ብለው " በዚህ ግዜ ህወሓት ከፈረሰ የፕሪቶርያው ስምምነት አይኖርም ብቻ ሳይሆን ከነአካቴው ታሪክ ሆኖ ይረሳል ማለት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ከፈረሰ የትግራይ ህዝብ ለበይ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" ስለዚህ እነዚህ ችግሮችና አደጋዎች ለመፍታት ነው ጉባኤአችን በዚህ ፈታኝ ወቅት ለማድረግ የፈለግነው ብቻ ሳይሆን የግድም ልናደርገው የተገደድነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ' ህወሓት ' ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድነው ? ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትግራዩ ጦርነት በፊት እንደ ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ስር ተመዝግቦ ይንቀሳቀስ ነበር። ነገር ግን  ቦርዱ ፓርቲው " ኃይልን መሰረተ ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል ሰርዞታል። የተወካዮች ምክር ቤትም ፓርቲውን " ሽብርተኛ ድርጅት " ሲልም ፈርጆት ነበር። ደም አፋሳሹና አስከፊው…
#Update

ሰባት የትግራይ የሲቪክ እና የንግድ ማህበራት በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረት ማድረጋቸውን ነገር ግን ጥረታቸው አለመሳካቱን አሳውቀዋል።

በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው መለያየት በድርጅቱ ዙሪያ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር አሳስበዋል።

" ፓለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት አልሞ ህዝብ ለመከፋፈል የሚደረገው ጥረት ብፅኑ እናወግዛለን " ብለዋል።

ማህበራቱ ህዝቡ የፓለቲከኞች መሳሪያ ሆኖ ደህንነቱና አንድነቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

" የትግራይ የፀጥታ ሃይሎችም የልዩነት ፈጣሪ ከሆኑ ፓለቲከኞች ሳይወግኑ የህዝብ ደህንነት መጠበቅ ይገባቸዋል " በማለት አሳስበዋል። 

ማህበራቱ ፤ በፓለቲከኞቹ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በመፍታት በኩል በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የሲቪክና ንግድ ማህበራቱ ፦
1. የትግራይ ስቪል ማሀረበረሰብ ጥምረት :
2. የትግራይ ህዝባዊ ግንኙነት ምክር ቤት
3. ጥላ የምዕራብ ትግራይ ስቪክ ማህበረሰብ ማህበር
4. የትግራይ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት
5. የትግራይ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት
6. ግርዓልታ የፓለሲ ጥናትና ስልጠና ስቪክ ማህበር
7. ማሕበር ምውሓስ ሰላምን ልምዓትን ዶብን ወሰንን ትግራይ ናቸው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አድርጉልኝ ፤ ፕሬዜዳንታችንንም እዛው ሊወጡ ሲሉ ይቅርታ ጠይቂያለሁ አሁንም ይቅርታ ደግሜ ደጋግሜ ጠይቃለሁ !! " - አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ምን አሉ ? " የብር ጉዳይ አይደለም። ለእኛ (ለአሰልጣኞች) እየተሰጠን ያለው Value የተለያየ ነው። እኔ አስተማሪ ነበርኩ ፤ በአስተማሪነት ለ9 ዓመት አገልግያለሁ የጠላሁት ማንም…
#Update

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከኢትዮጵያ መንግሥት የተበረከተላቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " አልቀበልም " ብለው መልሰው ከመድረክ መውረዳቸው ይታወሳል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ ይሆናል። ምክንያቱም ስጦታ በግድ ውሰዱ ስለማይባል " ሲል ለኤፍ ኤም 97.1 ተናግሯል።

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፤ ለሙያውና ለአሰልጣኞች የሚሰጠው ክብር ዝቅ ያለ በመሆኑ በስሜታዊነት ያንን ነገር እንዳደረጉ በዚህም ፕሬዜዳንቷን እና መላው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ ገንዘቡን ካላስተካከሉት እንደማይቀበሉም ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update

" ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው።

በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

ጉምሩክ ፤ " የሠነድ ምዝገባ እና ማጣራት ሂደቱን በአግባቡ እየሠራ ይገኛል " ብለዋል።

" የብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " ሲሉ አረጋግጠው " የቀረቡ ሠነዶች ያልተሟሉ እና ቀሪ ጉዳዮች ኖረው ተቀባይነት ያላገኙ ሠነዶች የሚስተናገዱት በዕለቱ የምንዛሪ ተመን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ " ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ " ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛ #የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#EthiopianCustomsCommission #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update

“ ሞጆ ቅርንጫፍ እየተጉላላን ነው። ትላንት የተላከውን ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ ‘አልመራበትም’ ተብሎ ” - አስመጪዎች

“ ደብዳቤው ትላንትና ከመሸ ነው እኛ ጋ የደረሰው ከዋና መስሪያ ቤት፡፡ ተመርቶ ለሚመለከተው ክፍል ሰጥጠናል ” - ሥራ አስኪያጅ ክፍሉ

አስመጪዎች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በጉምሩክ እያጋጠማቸው ስላለው ሁኔታ ፤ ክፈሉ ስለተባሉትም ከፍተኛ ቀረጥ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ምላሽ የጠየቅነው የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል፣ ኮሚሽኑ አስመጪዎቹ የሚያነሱትን ጉዳይ እንደተረዳና በሰርኩላሩ ዙሪያም ውይይት እንደሚያደርግ አስረድቶ ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ አስመጪዎቹ፣ ኮሚሽኑ ውይይት ማድረጉ መልካም ሆኖ እያለ ውሳኔው በዘገዬ ቁጥር ክፍያ እየጨመረባቸው በመሆኑ አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ በድጋሚ ማሳሰባቸው ይታወቃል።

ለዚሁ ቅሬታ ምላሽ የጠየቅነው የኮሚሽኑ ኮሚዩኒኬሽን ክፍልም፣ በጉዳዩ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ግልጾ፣ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፡፡

ጉዳዩ ከምን ደረሰ? አስመጪዎችስ ምን አሉ ?

አስመጪዎችን ቅር ያሰኘው ሰርኩላር ላይ ኮሚሽኑ ማስተካከያ እንዳደረገበትና፣ በማስተካከያው መሠረት ደንበኞች እንዲስተናገዱ ማዘዙን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ማስተካከያ የተደረገበት ሰርኩላር ያስረዳል፡፡

ማስተካከያውን ተከትሎም አስመጪዎች ዛሬ (ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ/ም) ወደ ጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እቃቸውን ለማውጣት እንደሄዱ፣ ነገር ግን የሚያስተናግዳቸው ባለመኖሩ እየተጉላሉ መሆኑን ዛሬም ለቲክቫህ አቤት ብለዋል፡፡

“ ሞጆ ቅርንጫፍ እየተጉላላን ነው። ትላንት የተላከውን ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ ‘አልመራበትም’ ብሎ ” ነው ያሉት፡፡

“ ትላንት የእቃ መልቀቂያ ደብዳቤ ወጥቶልን ነበር፡፡ ሞጆ ቅርንጫፍ ግን ጭራሽ እያስተናገዱን አይደለም፡፡ እንዳለ ሠራተኞች ቁጭ ብለዋል፡፡ የሚጭን መኪና ቆሟል፡፡ ከትላንትና ከሰዓት ጅምሮ ግን ምንም ሥራ እየተሰራ አይደለም ” ሲሉ አማረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አስመጪዎቹ እየተጉላላን ነው የሚል ቅሬታ አላቸው ለምን አታስተናግዷቸውም ? ሲል የኮሚሽኑን ሞጆ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ክፍልን ጠይቋል፡፡

የደንበኞች አገልግሎት ክፍል በሰጠው ምላሽ፣ “ ጉዳዩን እናጣራው እኛ ሙያተኞች ነን፡፡ አመራሮች ጋ ጉዳዩን እናጣራ፡፡ ወደ አመራር ሂደው ጉዳያቸው እንዲፈታ ነው የምናደርገው እንጅ ዝም ብለን የምናጉላላበት ጉዳይ የለም ” ብሏል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪም፣ አስመጪዎች “ ሥራ አስኪያጅ ደብዳቤ አልተመራም ” በሚል እያጉላላቸው መሆኑን ቅሬታ አቅርበዋል፤ ደብዳቤው አልደረሳችሁም ? ሲል የኮሚሽኑም ሞጆ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ክፍል ጠይቋል፡፡

የሥራ አስኪያጅ ክፍሉ ፀሐፊ አመራሮቹ ስብሰባ እንደገቡ ገልጸው፣ “ ደብዳቤው ትላንትና ከመሸ ነው እኛ ጋ የደረሰው ከዋና መስሪያ ቤት፡፡ እሱን ተመርቶ ለሚመለከተው ክፍል ሰጥጠናል ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

(ኮሚሽኑ ማስተካከያ ያደረገበት ደብዳቤ ከላይ የተያያዘ ሲሆን፤ ጉዳዩ ከምን እንደሚደርስ የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። መረጃው  የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው። @tikvahethiopia
#Update

" አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው " - በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ

በጋሞ ዞን፣ ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካማአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ በደረሰ የናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይወቃል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ከሰላሳ ሰባት በላይ የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ 15 ቤቶችም መፍረሳቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የሟቾችን ቀብር ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በክብር አስፈጽመናል " ብለዋል።

በአካባቢዉ ችግር ይከሰታል የሚል ቅድመ ትንበያም ይሁን ግምት ፈጽሞ እንዳልነበር ይልቁኑ በቀርከሀ የተሞላ ደን እያለ አደጋዉ መከሰቱ ሁኔታዉን አስደንጋጭ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል።

አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል መሆናቸዉን የገለጹት አስተዳዳሪው በአንድ ቤት ዉስጥ ከነበሩት ሰባት ሰዎች ውስጥ በጓዳ የነበሩት አራቱ ሞተው ሶስቱ ከጓዳ ወጭ የነበሩት መትረፋቸውን ነግረውናል።

የሟቾች ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመ በኃላ ወደ ቀጣይ ተግባር ተገብቷል ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ የዝናቡ መጠን ከፍ እንደሚል መረጃ ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት እንቅስቃሴ መጀመሩንና የአካባቢውን ሰው በማሸሽ በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የጤና ኬላዎችና የእምነት ቦታዎች ማሳረፍ መጀመሩን አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል። አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት…
#Update

በህወሓት ምትክል ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው የዛሬው የመቐለው ስብሰባ ቁጥራቸው አንድ ሺህ መሆኑ የህወሓት አባላትና አመራሮች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የአንድ ቀን ስብሰባቸውን ከምሽቱ 2:30 አጠናቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ካወጡዋቸው ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አራቱ ነጥቦች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈጠረው አንፃራዊ ምቹ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያስታውስ ነው።

" ሰላም አማራጭ የሌለው አማራጭ መሆኑ በመቀበልና በመረዳት ማንኛውም ወደ ግጭትና ጦርነት የሚመራ የውስጥና የውጭ ተንኮል በፅኑ እንቃወማለን " ይላል።

በአቋም መግለጫው ከተገለፁ አራት ነጥቦች  በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው ጉባኤ ኢ-ህጋዊነት የሚያትት ሆኖ " ተደናግረው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የህወሓት አባላት ወደ ቀልባቸው በመመለስ ከህዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ " ሲል ያሳስባል።

ዘጠነኛው ነጥብ ደግሞ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው የክልሉ ተወላጅ ፣ የድርጅቱ አባልና ደጋፊ ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ማህበራት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ደግፈው እንዲቆሙ ጥሪ ያቀርባል።

" የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች በድርጅታችን ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት እንደ ሁሉ ጊዜ በጥሞና በማየት በማያዳላ መንገድ የህዝቡ ፀጥታና ሰላም ማስከበር ይገባል " ያለው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስረኛ ነጥብ የአቋም መግለጫ የፀጥታ ሃይሎች አሁን የያዙት የማያዳላ አቋም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርበዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Via @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል በማለት በቁጥጥር ስር አውሎ የሽብር ወንጀል ምርመራ የከፈተባቸውን 6 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ማንነት የሚያሳይ ፎቶ ይፋ አድርጓል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው በሀገራችን ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት " ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ አውሮፕላን…
#Update

የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ ፈጥረዋል የተባሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia