THIQAH
11K subscribers
4.35K photos
48 videos
1 file
38 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia
(ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።
Download Telegram
"የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገና ዜሮ ነው" - ዘለንስኪ

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል መተማመን የለም አሉ።

ቮለድሚር ዘለንስኪ በአቡዳቢው የሦስትዮሽ ውይይት የተሳተፈውን ልዑካን ሪፖርት ካደመጡ በኋላ፣ "ሩሲያውያን ለእኛ ያላቸው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ምክንያቱም እኛን ይጠሉናል" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ፣ "የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገነሠ ዜሮ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"ስላለፈ ታሪክ ማውራት አቁመዋል፣ እኛ ምን እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ ነው ያውቃሉ፣ ተኩስ አቁም ስለሚደረግበት ሁኔታ ብቻ" ሲሉም አክለዋል።

"እነርሱ ወደኛ የመጡት በጦርነት ነው፣ ጦርነቱን የጀመረችው ዩክሬን አይደለችም" በማለትም ገልጸዋል።

"እኛ አሜሪካን ጨምሮ የውጭ ሀይሎች እቅዳችንን ለማስፈጸም እንደሚያስፈልጉን ተናግረናል፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ይህንን በደምብ ያውቃሉ" ነው ያሉት።  #interfax

@EyobTikuye  @ThiqahEth
5😱2😢2🥰1
THIQAH
በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አለፈ። መስጊድ ላይ በተፈጸመው በዚህ ፍንዳታ ከሟቾች በተጨማሪ 169 ሰዎች ከባድ ጉዳት ማስተናገዳቸው ተገልጿል። በዋና ከተማዋ በሚገኝ አንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የሟቾች እና የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል የኢስላማባድ ከተማ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢርፋን ሜሞን ተናግረዋል። ፖሊስ የጥቃቱን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ…
#Update

አይኤስ በፓኪስታን ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት ወሰደ።

በዓለማቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት የተፈረጀው የአይኤስ (IS) ቡድን በዋና ከተማዋ እስላማባድ በሚገኝ መስጊድ ላይ የደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በቡድኑ የተቀነባበረ መሆኑን ገልጿል።

ሺቴ ሙስሊሞች የሚገለገሉበት የባርጋህ ቃጅር ኩርባህ መስጊድ ላይ ትናንት በጁምአ ሶላት ወቅት በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት 31 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 169 ተጎድተዋል።

የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። #france24

@EyobTikuye  @ThiqahETH
😡175🥰4🕊2😭1
በሱዳን "በአማፂያኑ ጥቃት" 8 ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 24 ተፈናቃዮች ተገደሉ።

በጦርነቱ ምክንያት ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ተፈናቃዮችን የጫነ መኪና ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) አስታውቋል።

ተፈናቃዮቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከሰሜን ኮርዶፋ ወደ ደቡብ ኮርዶፋ ሲጓዙ አል ራሃድ ከተማ ላይ እንደሆነ ገልጿል።

ጥምረቱ ጥቃቱን የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) አባላት ናቸው ብሏል።

ከሟቾቹ ውስጥ ስምንት ህፃናት እና በርካታ እናቶች ይገኙበታል ተብሏል።  

በሱዳን በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ቢያንስ 114 ሰዎች በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) መረጃ ያመላክታል። #shafaaqnews

@EyobTikuye  @ThiqahETH
😢115😭2🕊1😡1
ታይላንድ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።

በዚህ ምርጫ ለመሳተፍ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል።

ወደ 5000 የሚጠጉ እጩዎች ለ500 የፓርላማ መቀመጫ ይወዳደራሉ ተብሏል።

19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሶስት ዕጩዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መምረጣቸው ሲገለፅ 12 ሀለቱ በቀጣይ እንደሚያሳውቁ፣ ቀሪዎቹ 12 ደግሞ በጋራ አንድ ዕጩ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መርጠዋል ነው የተባለው።

ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርናቪራኩል ይገኙበታል።

የምርጫ ውጤቱ ከሶስት ወር በኋላ ኤፕሪል 9 ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።  #bloomberg

@EyobTikuye  @ThiqahEth
3🥰1🙏1
"የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" - የአፍሪካ ህብረት

"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" - ኤም 23

የአፍሪካ ህብረት በኪሳንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ "የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" ሲል ገለጸ።

የ"የኪሳንጊ ጥቃት በሀገሪቱ የሽብር ጥቃቶች የሚያበረታታ አሰቃቂ ጥቃት ነው" ሲልም አውግዟል።

የማርች 23 (M23) በበኩሉ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተችቷል።

የኤም 23 አማፂ ቡድን በኮንጎ ጦር፣ በሩዋንዳ ቅጥረኛ ገዳዮች እና በቡርንድ አጋዥ ኃይሎች ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል።

የኤም 23 ዋና ፀሐፊ ቤንጃሚን ምቦኒምፓ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ "የተዛባ እና ስም የሚያጠፋ መግለጫ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" ያሉት ምቦኒምፓ "ተቋሙ ገለልተኛ አለመሆኑን በግልጽ ያሳየ መግለጫ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።

"የኪንሻሳ መንግስት ኃይሎች ባለፉት 2 ወራት ብቻ በምዌቦቤ፣ ሪትሳንኩ፣ ካቶጎታ፣ ሳንጌ እና በከፍተኛው ፕላቶ የሚገኙ ንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት 12 ጊዜ ፈፅመመው ያወገዘ አካል አልነበረም" ብለዋል።   #thenewtimes  #nilepostnews

@EyobTikuye  @ThiqahEth
9🕊2👏1
"የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው ገብተዋል" - ኢትዮጵያ

ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ "ወረራ" ያለችውን "ጥቃት" መፈጸሟን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለኤርትራ በይፋ በደብዳቤ አሳወቀች።

በዚህም፣ "የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በቀጥታ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።

ባለፉት ቀናት ያለው ሁኔታ የኤርትራ መንግስት ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያመላክቱ ናቸው። የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው ገብተዋል። በሰሜን ምዕራብ በኩልም ከአማፂ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የጋራ ወታደራዊ ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ፀብ አጫሪነት ብቻ ሳይሆን ወረራ ነው።

እንዲህ አይነቱን ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ለመቋጨት የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙ ሀይሎችን በአስቸኳይ እንዲያስወጣ እና ከታጣቂ ቡድኖች ጋር ያለውን ትብብር እንዲያቆም በአስቸኳይ እንጠይቃለን።

ከግማሽ በላይ ለሚሆን ክፍለ ዘመን ግጭት የሁለቱ ሀገራት መለያ ገፅታ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አይነቱን የጦርነት አዙሪትና አለመተማመን በውይይትና በዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ማስወገድ ይገባል ብለን እናምናለን።

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ፍላጎታችን አወንታዊ ምላሽ ካገኘን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ጉዳዮችን እና በአሰብ በኩል የቀይ ባህር አቅርቦትን ጨምሮ በጋራ ጥቅሞቻችን ላይ በጥሩ መተማመን ለመነጋገር ፍላጎት አለው።

በጋራ መከባበርና ትብብር ግንኙነታችንን በማሳደግ ብዙ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ያሏቸውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች አዲስ የሰላም እና የብልግና ዘመን ማምጣት እንችላለን" ብላለች። (ሙሉ የደብዳቤው ሀሳብ ከላይ ያለው ነው)

@EyobTikuye @ThiqahETH
19😱2🕊2😢1🙏1😡1
"የዓለም ሀገራት ለእስራኤል ትጥቅ መስጠታቸውን አላቆሙም" - የሃማስ አመራር

የሃማስ ፖለቲካ መሪ ካሊድ ማሻል ከእስራኤል ጋር የተፈጸመው ስምምነት ጉዳቱ ማመዘኑን ገለጹ።

ማሻል "ህዝባችን በጠላት ቁጥጥር ስር ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የቡድኑ የፖለቲካ መሪ በሰጡት አስተያየት "በቀላሉ በእስራኤል እየጠፋ ነው፣ የዓለም ሀገራት ለእስራኤል ትጥቅ መስጠታቸውን አላቆሙም" ሲሉ ወንጅለዋል።

"እኛን ትጥቅ ማስፈታት ፍልስጤማውያንን ለጥፋት አጋልጧል" ሲሉም ስምምነቱ ተግባራዊ አለመደረጉን ጠቁመዋል።

"በስምምነቱ መሰረት አሁን መነጋገር ያለብን ስለ መልሶ ግንባታ እና ሰብዓዊ እርዳታ ነበር፣ ግን ያ አልሆነም" በማለት አጥብቀው ተችተዋል። #thejerusalempost

@EyobTikuye   @ThiqahEth
😢1312😡2🙏1
ደቡብ አፍሪካ ከ700 የሚልቁ ወታደሮቿን ከኮንጎ አስወጣች።

ጆሃንስበርግ የመለሰቻቸው በተመድ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ (MINUSCO) ስር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተሰማርተው የነበሩ ወታደሮች ናቸው።

ወታደሮቹ የተመለሱት፣ የሀገሪቱን ጦር የሰው ኃይል "ለማመጣጠን ነው" ሲል የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጽ/ቤት አሳውቋል። 

ደቡብ አፍሪካ ከ1999 ጀምሮ ላለፉት 27 አመታት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት ከፍተኛ የሰላም ማስከበር ኃይል ከሚያዋጡ አስር ሀገራት መካከል አንዷ ናት። #iol

@EyobTikuye  @ThiqahETH
5👏1😢1
#AddisAbaba

11 አመራሮች እና ሠራተኞች ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀረቡ።

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራርና ሰራተኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመጠቀም ወንጀል ተጠርጥረው በፓሊስ ተይዘው ፍ/ቤት ቀረቡ።

"በ2016 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አየር መንገድ አከባቢ የህዝብ እና የመንግስት ይዞታ የሆነውን በ9ኛው መዋቅራዊ ፕላን በአደዋ ፓርክነት ተይዞ የነበረውን እና በ10ኛ መዋቅራዊ ፕላን በዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ልዩ ልዩ የከተማው መተንፈሻ አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት በከተማ ደረጃ በመናፈሻነት ለህዝብ አገልግሎት የተያዘ እና በመሬት ባንክ ውስጥ ያለን ይዞታ ያለ ህጋዊ ምክንያት ሰነድ አልባ ይዞታ ነው በማለት፦

ለዮርዳኖስ፤ ዘውዲቱ እና ጓደኞቻቸው የሲሚንቶ አከፋፋይ ህብረት ሽርክና ማህበር የቦታው ስፋት 2905 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የቦታው ሊዝ ዋጋ 168 ሚሊዮን 724 ሺሕ 405 ብር የሚገመትን ጉዳት" አድርሰዋል ተብሏል።

በዚህም "ከወረዳ፤ ክ/ከተማ እና መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ድረስ በጥቅም ተሳስረው ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል" ተጠርጥረዋል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበውም ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠይቆ ምርመራው ቀጥሏል ተብሏል። #FMC

@EyobTikuye  @ThiqahEth
14👏3😢1🙏1
THIQAH
#AddisAbaba 11 አመራሮች እና ሠራተኞች ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀረቡ። የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራርና ሰራተኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመጠቀም ወንጀል ተጠርጥረው በፓሊስ ተይዘው ፍ/ቤት ቀረቡ። "በ2016 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አየር መንገድ አከባቢ የህዝብ እና የመንግስት…
በከ168 ሚሊዮን በላይ ብር ሙስና የተጠረጠሩት አመራሮች እና ሠራተኞች እነማን ናቸው?

- የቀድሞ አዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሞሊቶ አባይነህ ኤርቃሎ፤

- የቀድሞ የቦለ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳዳር ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ቸርነት አበበ የአደቴ፤

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቴክኒክ ጉዳይ ወሳኝ ባለሙያ ሰለሞን በላይ መኮንን፤

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቅሬታ እና አቤቱታ ባለሙያ አድማሱ አዳነ ወንድሙ፤

- የከተማ አስተዳዳሩ መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ ግዛቸው ሙሉጌታ ደሴ፤

- የቀድሞ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደረጀ ጎሹ ሀይሌ፤

- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 መሬት ልማትና አስተዳዳር የሰነድ አጣሪ ባለሙያ አለምፀሃይ ለማ ኪ/ማርያም፤

- የከተማ አስተዳዳሩ መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ህግ /ቴክኒክ ጉዳይ ክትትል ዳይሬክተር ግርማ ተፈራ አያና፤

- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ አማኑኤል አለማየሁ ማሞ፤

- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13  የቴክኒክ ባለሙያ ቢኒያም ሀይሉ ገብሬ እንዲሁም፤

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቢዮት ጁፋሬ ባይሳ ናቸው ተብሏል።

@EyobTikuye  @ThiqahEth
12👏7🥰1🕊1😡1
THIQAH
ኢራናዊቷ ኖቬል ተሸላሚ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ፋውንዴሽኗ ጠየቀ። ኢራናዊቷ የኖቤል ተሸላሚ ናርገስ ሞሀመድ መታሰሯ ተነግሯል። ናርገስ በአንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መታሰቢያ ላይ በተገኘችበት ወቅት በኢራን መንግስት በቁጥጥር ስር መዋሏን በስሟ የተቋቋመው ፋውንዴሽን አስታውቋል። በማሻድ ከተማ በደህንነት ሰዎች መያዟን የገለጸው ፋውንዴሽኑ፣ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ጠይቋል።  #theindependent…
በኢራን የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ናርገስ መሀመዲ የሰባት አመት እስር ተፈረደባት።

ታዋዊዋ ኢራናዊ አክቲቪስት መሀመዲ የፍርድ ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት የረሃብ አድማ ጀምራ እንደነበር ጠበቃዋ ሙስጦፋ ኒሊ በኤክስ ገፃቸው አስፍረዋል።

የ53 አመቷ ናርገስ መሀመዲ ክስ የቀረበባት "ግጭት በመቀስቀስ ወንጀል" መሆኑን ኒሊ ገልጸዋል።

መሀመዲ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የህግ ባለሙያው እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበረው ኮስሮው አልኮርዲ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ነበር በደህንነት አካላት ተይዘው የተወሰዱት።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ፣ የኢራን ባለስልጣናት በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሷቸውን የመብት ጥሰቶች በመቃወሟ ለእስር ተዳርጋ ቆይታለች።  #huffpost

@EyobTikuye @ThiqahETH
😢8👏43😱1
አንቶኒዮ ጆሴ ሰጉሮ የፖርቱጋል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

የሶሻሊስት ፓርቲ መሪው ሰጉሮ 66.2% ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸውን እና የቼጋ ፓርቲ ተወካዩ አንድሬ ቬንቱራ 33.8% ድምፅ ማገኘታቸውን የፖርቱጋል ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ጆሴ ሰጉሮ ለሁለት የስልጣን ዘመን ፖርቹጋልን ያስተዳደሩትን ማርሴሎ ሮቤሎን በመተካት የሀገሪቱ መሪ መሆን ችለዋል ተብሏል።

የ63 አመቱ ሰጉሮ ከዚህ ቀደም በነበረው ምርጫ ቢሳተፉም ማሸነፍ ሳይችሉ፣ 11 ሚሊዮን መራጮች በተሳተፉበት ሁለተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ አሸንፈዋል ተብሏል።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ከ2001-2002 የፖርቱጋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። #radiowpsu

@EyobTikuye @ThiqahETH
5👏2🙏1
THIQAH
"የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው ገብተዋል" - ኢትዮጵያ ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ "ወረራ" ያለችውን "ጥቃት" መፈጸሟን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለኤርትራ በይፋ በደብዳቤ አሳወቀች። በዚህም፣ "የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በቀጥታ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ባለፉት ቀናት ያለው ሁኔታ የኤርትራ መንግስት ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስ…
ኤርትራ ለኢትዮጵያ ምላሽ ሰጠች።

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳልህ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ለተፃፈላቸው ደብዳቤ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሚንስትሩ፣ "በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤርትራ ላይ የቀረበው የሀሰት ክስ አስደናቂና አጠቃላይ ዓላማዋው ሌላ ምኞት እንዳለው የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

ኦስማን፣ "በሚያሳዝን ሁኔታ በኤርትራ ላይ ከሁለት አመት ለበለጠ ጊዜ የቆየው ዘመቻ ላይ ተጨማሪ ወቀሳ ነው" ሲሉም ገልጸዋል።

"ካሁን በፊት እንደተገለጸው የኤርትራ መንግስት ትርጉም በሌለው ነገር ሁኔታውን ለማባባስ አሁን ካለው ውዝግብ ላይ በመሳተፍ ነዳጅ የመጨመር ፍላጎት የለውም" በማለት ሀገራቸው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንደማይትገባ አስታውቀዋል።

@EyobTikuye @ThiqahEth
😡136🙏6👏1
በሊባኖስ በደረሰ የህንፃ መደርመስ ቢያንስ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

እስካሁን ባለው የተጣራ መረጃ 8 ሰዎች ተጎድተው ወደሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።

ባለ ስድስት ፎቅ የመኖሪያ አፓርታማ በድንገት መደርመሱን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

አደጋው የደረሰው በሰሜን የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ በሆነችው የትሪፖሊ ከተማ ነው።

ለህንፃው መደርመስ ዋነኛ ምክንያቱ የግንባታ ጥራቱ ደካማ መሆኑ ነው ተብሏል። #mailonline

@EyobTikuye @ThiqahETH
😭74😢3😱2💔2👏1🙏1
በሊቢያ የ53 ስደተኞች ህይወት አለፈ።

55 ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በሊቢያ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ የ53 ሰዎች ማለፉ ተገለጸ።

በዚህ አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ስደተኞች ናቸው ተብሏል። በህይወት የተገኙት ሁለቱ ስደተኞች የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ሴቶች ናቸው።

ስደተኞቹ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸውን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ ለስድስት ሰዓታት ያክል አልተገኘችም ነበር ተብሏል።

IOM 2026 ከገባ ወዲህ 500 ስደተኞች በተመሳሳይ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ሲል ገልጿል። #bbc

@EyobTikuye  @ThiqahETH
😭176😢2🙏1
በናይጄሪያ በተከሰተ የመንገድ አደጋ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞቱ።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በካኖ ግዛት የተከሰተው በአሽከርካሪ ድክመት የተከሰተ ነው ተብሏል።

በናይጄሪያ ባለፈው አመት መንገድ ላይ በደረሰ አደጋ 5,421 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።

በዓለም ላይ 3% ተሽከርካሪዎች የሚገኝባት ናይጄሪያ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ትራንስፖርት የምታስተናግድ ሀገር እንደሆች ተመላክቷል። #thegleaner

@EyobTikuye  @ThiqahEth
💔43😱2😢2😭1
ኩባ የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት እንደገጠማት አስታወቀች።

ሀቫና በቅርብ ጊዜ ውስጥ አለማቀፍ በረራዎች ሊቋረጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቃለች።

በዋና ከተማዋ ሀቫና የሚገኘው የጆዜ ማርቲ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሰሩ ፓይለቶች የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን በዚህ ሳምንት መግቢያ የመንግሥት ባለስልጣናት ነግረዋቸዋል።

አሜሪካ በኩባ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ለአውሮፕላን ነዳጅ እጥረቱ እንዳጋለጣት ተገልጿል።

ለኩባ ነዳጅ የሚያቀርቡት ሜክሲኮ እና ቬንዙዌላ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ውሳኔ ያቆሙ ሲሆን፣ ሌሎች ሀገራትም ነዳጅ እንዳያቀርቡ በአሜሪካ የታሪፍ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። #9news

@EyobTikuye  @ThiqahEth
😢63😡3👏1😱1
"በቡድኑ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣል ንጹሐንን ከሞት መታደግ ይገባል" ቮልከር ተርክ

ተመድ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) በኤልፋሽር ወንጀል መፈጸሙን በመግለጽ፣ ማዕቀብ እንዲጣልበት አሳሰበ።

በተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ በሱዳን የርስበርስ ጦርነት ከሱዳን ጦር ጋር ውጊያ ውስጥ የሚገኘው "የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እና አጋሮቹ በኤልፋሽር የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል" ብለዋል።

"ስጋቱ ግልጽ ነው፣ ግን ማስጠንቀቂያዎች አይሰጡም፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ የተሻለ መስራት አለበት" ነው ያሉት።

"RSF በአሳዛኝ ሁኔታ ግድያ፣ ፆታዊ ጥቃት እና እገታ ፈጽሟል" ሲሉ ወንጅለዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ፣ "ቡድኑ ኤልፋሽርን ታህሳስ 1/2025 ከተቆጣጠረ በኋላ ከ62,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል" ብለዋል።

"በቡድኑ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣል ንጹሐንን ከሞት መታደግ ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል።  #unnews  #eurasiareview

@EyobTikuye  @ThiqahETH
6😭2