የአዲስ አበባ ከተማ በ6 ወራት ከ10 ሺሕ በላይ አካላት ብልሹ አሰራርና ጥፋት መፈጸማቸውን ተናገረ።
በዚህም፣ በ2018 ዓ/ም 6 ወራት ብቻ ከ10 ሺሕ 500 በላይ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች፣ ሠራተኞች ብልሹ አሰራር መፈጸማቸውን ገልጿል።
ይሁን እንጂ፣ "ተጠያቂ ተደርገዋል" ከማለት በዘለለ ምን አይነት እርምጃ እንደተወሰደባቸው አልተገለጸም።
በከተማዋ፦
- ባለፉት 6 ወራት ከ162 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ደረሰኝ ሳይቆርጡ በተገኙ 7 ሺሕ 678 ነጋዴዎች፣ ብልሹ አሰራር በፈጸሙ 282 ሠራተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል።
- 18.72 ቢሊዮን ብር ለተማሪ ምገባ፣ ለዩኒፎርም፣ ለጤና መድህንና ለትራንስፖርት ድጎማ ውሏል። በልማታዊ ሴፍቲኔት ደግሞ 1.135 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል"።
- 370 አገልግሎት በቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት እንዲሰጡ፤ በተቋማት ውስጥ 183 የህጻናት ማቆያ፣ 100 የሰራተኞች ካፊቴሪያ፣ 166 የሸማቾች ሱቆች እንዲደራጁ ተደርጓል።
- ተገልጋዮችን በማንገላታትና ጥፋት የፈጸሙ 61 አመራሮች፣ 126 ዳይሬክተሮችና የቡድን መሪዎች፣ 3 ሺህ 542 ሰራተኞች በፈጸሙት ጥፋት ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡ #AMN
@EyobTikuye @ThiqahETH

❤9😢2
ትራምፕ ከኦባማ ጋር በተያያዘ ያጋሩት የዘረኝነት ተንቀሳቃሽ ምስል ተቃውሞ አስከተለ።
ዶናልድ ትራምፕ ከምርጫ ሴራ ጋር የተገናኘና የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ጋር የተያያዘ ምስል ማጋራታቸው ተቃውሞ አስከትሎባቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በባይደን የተሸነፉበት የ2020 ምርጫን የሚመለከት እንጂ ሆን ብለው ያጋሩት አለመሆኑን ገልጸዋል።
60 ሰከንድ የሚረዝመው ተንቀሳቃሽ ምስል የድምፅ መሰጫ ጣቢያዎች ሲጭበረበሩ ኦባማ ደስተኛ መሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። #associatedpress
@EyobTikuye @thiqaheth

😡7❤4🕊1
"ዳግም ወደ ኔፓል መግባት እንዳይችሉ ተወስኗል" - ቲኪራም ዳካል
ኔፓል በ6 ወራት በተደረገ ዘመቻ በህገወጥ ተግባራት የተሰማሩ 333 የውጭ ዜጎች መያዛቸው አሳወቀች።
የኔፓል ኢሚግሬሽን ዲፓርትመንት (DOI) ኃላፊ ቲኪራም ዳካል በመግለጫቸው፣ "ብዙዎች በቱሪስት/በቢዝነስ ቪዛ ገብተው ነገር ግን መንግስት በህግ በከለከላቸው ጉዳዮች ላይ ሲሳተፉ ነበር" ብለዋል።
"ህገ ወጥ የትዳር እና የእምነት ተቋማት ቢሮ በማቋቋም ስራ ተሰማርተው እንደነበር ደርሰንበታል" ያሉት ኃላፊው፣ "ለማሳያነት የኔፓል ሴቶችን በጋብቻ ወደ ቻይና ሲልኩ ነበር" ነው ያሉት።
ሁሉም 333 ሰዎች ከሀገር መውጣታቸውን የገለፀው ቢሮው "ዳግም ወደ ኔፓል መግባት እንዳይችሉ ተወስኗል" ሲሉም ገልጸዋል።
በ2025 ብቻ 501 የውጭ ዜጎች ከሀገር መባረራቸውን ጠቁመዋል። #thekathmandupost

❤5🕊1
THIQAH
"ኢራን ውይይቱን የፈለገችው ከጥቃት ለመዳን ነው" - ትራምፕ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራን የድርድር ፍላጎት "ከፍርሃት የመነጨ" መሆኑን መናገራቸው ተሰምቷል። ይህን ያሉለት ነገ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን የአሜሪካና ኢራን ውይይት ነው። ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "እኛ እንድናጠቃቸው አይፈልጉም" ብለዋል። "ኢራን ውይይቱን የፈለገችው ከጥቃት ለመዳን ነው" ሲሉም ተናግረዋል። የሁለቱ ሀገራት ውይይት ነገ…
"ስምምነቱ ውጤታማ ካልሆነ አሜሪካ ለኢራን ከዲፕሎማሲ ጎን ለጎን ብዙ አማራጭ አላት" - ካሮሊን ሌቪት
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለሚደረገው ውይይት ወደ ኦማን አቅንተዋል።
የዋይትሐውስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ካሮሊን ሌቪት "ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን በኑክሌር ፕሮግራም ላይ ድርድሮች ካልተሳኩ በሚል ሌሎች አማራጮችን አዘጋጅተዋል" ብለዋል።
"ፕሬዚደንት ትራምፕ ግልጽ ፍላጎታቸውን አስቀምጠዋል" ያሉት ሀላፊዋ "የኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ዜሮ መሆን አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌቪት በሰጡት መግለጫ "ስምምነቱ ውጤታማ ካልሆነ አሜሪካ ለኢራን ከዲፕሎማሲ ጎን ለጎን ብዙ አማራጭ አላት" ካሉ በኋላ ትራምፕን "በአለም ታሪክ የጠንካራው ጦር አዛዥ ናቸው" ሲሉ አማራጩ የሀይል እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሌቪት በመግለጫቸው ስለ ኩባ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ "የኩባ መንግስት በመጨረሻ እግሩ ላይ ነው፣ ለመውደቅ ተቃርቧል" ሲሉ መልሰዋል።
"ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዲፕሎማሲ ሁሌም ዝግጁ ስለሆኑ ከኩባ ጋርም ተመሳሳይ ነገር ያለ ይመስለኛል" ብለዋል። #trtworld

❤7🥰1😡1
THIQAH
"ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" - ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኩባ የሚገባው ነዳጅ መቆም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ "ውይይት" ያስፈልጋል አሉ። "ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" ብለዋል። ትራምፕ "ኩባ ከዋሽንግተን ጋር መስማማት ከቻለች ሰብዓዊ ቀውስ አይፈጠርም" ሲሉ አብራርተዋል። "ኩባ ለአሜሪካ…
"ለውይይት ዝግጁ ነን፣ ግን በጫና ውስጥ ሆነን አይደለም" - ፕሬዚዳንት ካኔል
ኩባ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።
ፕሬዚዳንት ሜጉዌል ዲያዝ ካኔል ሀገራቸው ለንግግር መዘጋጀቷን ገልጸው፣ "የትኛውም ውይይት በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ መግባትን አያካትትም" ብለዋል።
ካኔል "ለውይይት ዝግጁ ነን፣ ግን በጫና ውስጥ ሆነን አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
የኩባ እና የአሜሪካ ውይይት በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
"ኩባ በቅርቡ ትወድቃለች" ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ኩባ ነዳጅ እንዳይገባ ከልክለዋል።
የነጩ ቤተመንግስት ዋና ፀሐፊ ካሮሊን ሌቪት በበኩላቸው፣ "የኩባ መንግስት በመጨረሻ እግሩ ላይ ነው፣ ለመውደቅ ተቃርቧል" ብለዋል። #aninews #dw

❤6😢2😡1
THIQAH
Photo
#Update
"ኢራን እና አሜሪካ ጥሩ ለውጥ ያሳየ ውይይት አካሂደዋል" - አልቡሳይዲ
የኢራን እና አሜሪካ (የቴህራን እና የዋሽንግተን) የመጀመሪያውን ዙር ኢ-ቀጥተኛ ውይይት ዛሬ በኦማን መድና ሙስካት ተካሂዷል።
በዚህም ሁለቱ ሀገራት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል።
በዚህም የድርድሩ አሸማጋይ ሀገር ኦማን ቀጣዩ ውይይት ኤፕሪል 23 እንደሚካሄድ አስታውቃለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እና የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ የሀገራቱን ልዑካን በመምራት በውይይቱ ተሳትፈዋል ተሳትፈዋል።
አራግቺ "በአወንታዊ መንገድ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ተቀብሏል" ሲሉ የውይይቱን አንድምታ አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ ከውይይቱ በኋላ ለኢራን መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አጭር ቃል "ድርድሩን ለማስቀጠል ተስማምተናል፣ አካሄዱን እና ጊዜውን በሌላ ቀን እናሳውቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።
"ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው የኑክሌያር ፕሮግራም ላይ ብቻ ነው፣ ሌላ አጀንዳ አልነበረም" ብለዋል።
የአሜሪካ ልዑካን ግን ከኑክሌር ድርድር ባለፈ ኢራን በምትደግፋቸው የቀጠናው ታጣቂዎች ላይ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።
የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አልቡሳይዲ በኤክስ ገፃቸው፣ "ኢራን እና አሜሪካ ጥሩ ለውጥ ያሳየ ውይይት አካሂደዋል" ሲሉ አስፍረዋል።
አልቡሳይዲ "ውጤት የሚያመጣ ተመሳሳይ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት አልመናል" በማለት የውይይቱን ቀጣይነት ጠቁመዋል። #euronews
@EyobTikuye @ThiqahEth

❤9🕊6
THIQAH
"እኔ የምፈልገው ካናዳን 51ኛዋ ግዛት ማደረግ ነው። ግሪንላንድ 52ኛዋ፣ ቬንዙዌላ ደግሞ 53ኛዋ ግዛት ሊሆኑ ይችላሉ" - ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳ፣ ቬንዙዌላ እና ግሪንላድን "የአሜሪካ ግዛቶች አደርጋለሁ" በሚል ዝተዋል። "ግሪንላንድን እንገዛታለን እንጂ አንወርም" ያሉት ትራምፕ፣ "ግሪንላንድን 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት የማድረግ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። እኔ የምፈልገው ካናዳን…
ፈረንሳይ እና ካናዳ በግሪንላንድ ዙሪያ ከፍተኛ ውይይት እንደሚያስፈልግ ገለጹ።
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በዋና ከተማዋ ኑክ ተገናኝተዋል።
መሪዎቹ ራስ ገዝ በሆነችው የዴንማርክ ግዛት ተገኝተው ባደረጉት ውይይት የኔቶ አባል ሀገራት ለድርጅቱ መርህ መገዛት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በግሪንላንድ ብዛት ያላቸው የሁለቱም ሀገራት ዜጎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው አሜሪካ ለብሄራዊ ደህንነቷ ስትል ግሪንላንድን ታስተዳድራለች ማለታቸው ይታወቃል።
የሩቴ እና የማክሮ ውይይት የተካሄደውም ፕሬዝዳንቱ ይህን አቋማቸውን ባልቀየሩበት ወቅት ነው። #kyivpost

❤3🥰2👏1😢1
THIQAH
#Update "ኢራን እና አሜሪካ ጥሩ ለውጥ ያሳየ ውይይት አካሂደዋል" - አልቡሳይዲ የኢራን እና አሜሪካ (የቴህራን እና የዋሽንግተን) የመጀመሪያውን ዙር ኢ-ቀጥተኛ ውይይት ዛሬ በኦማን መድና ሙስካት ተካሂዷል። በዚህም ሁለቱ ሀገራት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል። በዚህም የድርድሩ አሸማጋይ ሀገር ኦማን ቀጣዩ ውይይት ኤፕሪል 23 እንደሚካሄድ አስታውቃለች። የኢራን የውጭ ጉዳይ…
"ቴህራን በመጥፎ ሁኔታ ስምምነት ማድረግ የፈለገች ይመስለኛል" - ዶናልድ ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ከስምምነት ለመድረስ የተጠቀመችበትን አካሄድ ነቅፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሌሊት ላይ በኦማን ከተደረገው የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ድርድር በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ "ኢራን ስምምነት ላይ ካልደረሰች ውጤቱ ውድቀት ነው የሚሆነው" ሲሉ ዝተዋል።
"የስምምነታቸውን ሀሳብ ማየት አለብን" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ "ቴህራን በመጥፎ ሁኔታ ስምምነት ማድረግ የፈለገች ይመስለኛል" ብለዋል።
አክለውም፣ "ውይይቱ ቀጣይ ሳምንት ይቀጥላል፣ የኑክሌር ፕሮግራም ደግሞ ዋነኛ አጀንዳችን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
"ይህ ስምምነት ከሁለት አመት በፊት ነበር የሚያልቀው፣ ግን በእነሱ በኩል ፍላጎት አልነበረም" በማለትም ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።
ምንም እንኳን ትራምፕ ባያደንቁትም በአንፃሩ
አደራዳሪዋ ሀገር ኦማን እና ኢራን ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር አስታውቀዋል። #aa

❤11🕊4🙏2😱1
THIQAH
ታይላንድ ለ1700 ተጓዦች "የኒፓህ ቫይረስ" ምርመራ ማድረጓን ገለጸች። በህንድ የተከሰተውን የኒፓህ ቫይረስ ተከትሎ አየር መንገድ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች እንደምትገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ምርመራው ያተኮረው ከህንድ ቤንጋል ክልል በሚመጡ ተጓዦች ላይ ብቻ መሆኑን አመላክቷል። ይሁን እንጂ ምርመራ ከተደረገላቸው 1700 ተጓዦች ካሁን በፊት በበሽታው የተያዘ ሰው አለመገኘቱን…
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባንግላዴሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በኒፓህ ቫይረስ ሞት መመዝገቡን አስታወቀ።
በዚህም አንዲት ሴት በኒፓህ ቫይረስ ህይወቷ አልፏል። ሟቿ የውጭ ሀገር ጉዞ አላደረገችም ተብሏል።
በህንድ የተከሰተው የኒፓህ ቫይረስ ወደተለያዩ የእስያ ሀገራት እንዳይስፋፋ ስጋት ደቅኗል።
ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኢንዶኔዥያ እና ፓኪስታን በአየርመንገድ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሚገኙ የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ቫይረሱ የመስፋፋት እድሉ ዝቅተኛ በመሆኑ የጉዞ ገደብ መጣል አስፈላጊ አይደለም ብሏል።
ድርጅቱ ቫይረሱን ለመከላከል እውቅና የተሰጣቸው መድሃኒቶች አለመኖራቸውን ጠቁሟል። #straitstimes

❤6🕊2🥰1😢1
"በተፈጸመብን ጥቃት በብዙ ክልሎች መብራት ጠፍቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሽምይሀል
ሩሲያ በዩክሬን የኃይል መሰረተ ልማት ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ።
በቡርሽትንስካ እና ዶብሮትዢስካ ከተሞች በደረሰው በዚህ ጥቃት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሀይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል ተብሏል።
ሌሊት ላይ በከተሞች በደረሰው ጉዳት የተቋረጠውን ኃይል ለመተካት ከፖላንድ የእርዳታ ድጋፍ መጠየቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ደኒስ ሽምይሀል ተናግረዋል።
ሽምይሀል፣ "ሞስኮን ሆን ብላ በኢነርጂ ጣቢያዎች ላይ የታቀደ ጥቃት እየፈጸመች ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "በጠላት አማካኝነት በተፈጸመብን ጥቃት በብዙ ክልሎች መብራት ጠፍቷል" ብለዋል።
"ጥቃቱ አሁንም ቀጥሏል" ያሉት ደኒስ ሽምይሀል "የተቋረጠውን ሀይል ለመመለስ የተቻለንን እየሰራን እንገኛለን" ሲሉ ገልጸዋል።
የሦስትዮሽ ውይይቱ በቀጠለበት ወቅት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አላቆመችም ተብሏል።
በአሜሪካ አደራዳሪነት በአቡዳቢ የተወያዩት ሞስኮ እና ኪቭ የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ እና ተኩስ ለማቆም ተስማምተው፣ ሦስተኛ ዙር ውይይታቸውን በቀጣይ ሳምንት ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘው መለያየታቸው ይታወሳል። #euractive

❤8😭5🕊4
#Gambella
"ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል" - ጋምቤላ ክልል
የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ "ከሰኞ የካቲት 2/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል" ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት አስታወቁ።
በዚህም፦
- እስካሁን ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት 30 የነበረው የሥራ ሰዓት ከ1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት 30፤
- እንዲሁም ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ተኩል የነበረው ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት 30 እንዲሆን ተወስኗል።
- የሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተመልክቷል። #GMMS

❤3🙏2🥰1
"የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገና ዜሮ ነው" - ዘለንስኪ
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል መተማመን የለም አሉ።
ቮለድሚር ዘለንስኪ በአቡዳቢው የሦስትዮሽ ውይይት የተሳተፈውን ልዑካን ሪፖርት ካደመጡ በኋላ፣ "ሩሲያውያን ለእኛ ያላቸው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ምክንያቱም እኛን ይጠሉናል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ፣ "የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገነሠ ዜሮ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ስላለፈ ታሪክ ማውራት አቁመዋል፣ እኛ ምን እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ ነው ያውቃሉ፣ ተኩስ አቁም ስለሚደረግበት ሁኔታ ብቻ" ሲሉም አክለዋል።
"እነርሱ ወደኛ የመጡት በጦርነት ነው፣ ጦርነቱን የጀመረችው ዩክሬን አይደለችም" በማለትም ገልጸዋል።
"እኛ አሜሪካን ጨምሮ የውጭ ሀይሎች እቅዳችንን ለማስፈጸም እንደሚያስፈልጉን ተናግረናል፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ይህንን በደምብ ያውቃሉ" ነው ያሉት። #interfax

❤5😱2😢2🥰1
THIQAH
በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አለፈ። መስጊድ ላይ በተፈጸመው በዚህ ፍንዳታ ከሟቾች በተጨማሪ 169 ሰዎች ከባድ ጉዳት ማስተናገዳቸው ተገልጿል። በዋና ከተማዋ በሚገኝ አንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የሟቾች እና የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል የኢስላማባድ ከተማ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢርፋን ሜሞን ተናግረዋል። ፖሊስ የጥቃቱን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ…
#Update
አይኤስ በፓኪስታን ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት ወሰደ።
በዓለማቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት የተፈረጀው የአይኤስ (IS) ቡድን በዋና ከተማዋ እስላማባድ በሚገኝ መስጊድ ላይ የደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በቡድኑ የተቀነባበረ መሆኑን ገልጿል።
ሺቴ ሙስሊሞች የሚገለገሉበት የባርጋህ ቃጅር ኩርባህ መስጊድ ላይ ትናንት በጁምአ ሶላት ወቅት በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት 31 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 169 ተጎድተዋል።
የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። #france24

😡17❤5🥰4🕊2😭1
በሱዳን "በአማፂያኑ ጥቃት" 8 ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 24 ተፈናቃዮች ተገደሉ።
በጦርነቱ ምክንያት ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ተፈናቃዮችን የጫነ መኪና ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) አስታውቋል።
ተፈናቃዮቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከሰሜን ኮርዶፋ ወደ ደቡብ ኮርዶፋ ሲጓዙ አል ራሃድ ከተማ ላይ እንደሆነ ገልጿል።
ጥምረቱ ጥቃቱን የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) አባላት ናቸው ብሏል።
ከሟቾቹ ውስጥ ስምንት ህፃናት እና በርካታ እናቶች ይገኙበታል ተብሏል።
በሱዳን በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ቢያንስ 114 ሰዎች በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) መረጃ ያመላክታል። #shafaaqnews

😢11❤5😭2🕊1😡1
ታይላንድ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።
በዚህ ምርጫ ለመሳተፍ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል።
ወደ 5000 የሚጠጉ እጩዎች ለ500 የፓርላማ መቀመጫ ይወዳደራሉ ተብሏል።
19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሶስት ዕጩዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መምረጣቸው ሲገለፅ 12 ሀለቱ በቀጣይ እንደሚያሳውቁ፣ ቀሪዎቹ 12 ደግሞ በጋራ አንድ ዕጩ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መርጠዋል ነው የተባለው።
ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርናቪራኩል ይገኙበታል።
የምርጫ ውጤቱ ከሶስት ወር በኋላ ኤፕሪል 9 ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። #bloomberg

❤3🥰1🙏1
"የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" - የአፍሪካ ህብረት
"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" - ኤም 23
የአፍሪካ ህብረት በኪሳንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ "የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" ሲል ገለጸ።
የ"የኪሳንጊ ጥቃት በሀገሪቱ የሽብር ጥቃቶች የሚያበረታታ አሰቃቂ ጥቃት ነው" ሲልም አውግዟል።
የማርች 23 (M23) በበኩሉ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተችቷል።
የኤም 23 አማፂ ቡድን በኮንጎ ጦር፣ በሩዋንዳ ቅጥረኛ ገዳዮች እና በቡርንድ አጋዥ ኃይሎች ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል።
የኤም 23 ዋና ፀሐፊ ቤንጃሚን ምቦኒምፓ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ "የተዛባ እና ስም የሚያጠፋ መግለጫ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።
"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" ያሉት ምቦኒምፓ "ተቋሙ ገለልተኛ አለመሆኑን በግልጽ ያሳየ መግለጫ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
"የኪንሻሳ መንግስት ኃይሎች ባለፉት 2 ወራት ብቻ በምዌቦቤ፣ ሪትሳንኩ፣ ካቶጎታ፣ ሳንጌ እና በከፍተኛው ፕላቶ የሚገኙ ንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት 12 ጊዜ ፈፅመመው ያወገዘ አካል አልነበረም" ብለዋል። #thenewtimes #nilepostnews

❤9🕊2👏1